Telegram Web Link
#Tigray

° " እርባና የሌለው ልዩነታችንን ትተን ለህዝባችን ሰላምና እፎይታ እንስጠው " - አቶ ጌታቸው ረዳ
 
° " ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግላችን ማጠናከር ይገባል " - የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ በትግራይ ፣ መቐለ ጮምዓ ተራራ ሲከበር የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ሌ/ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ተገኝተው ነበር።

አቶ ጌታቸውም ንግግር አድርገዋል።

" በፓለቲካዊ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ትርጉም የሌለው ልዩነት ወደ ጎን በመተው የህዝቡ ሰላም ማስጠበቅ ከስጋት ተላቅቆ ኦፎይታ እንዲያገኝ መስራት ይገባል " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው " እንደ አመራር እርባና የሌለው ልዩነታችንን ወደ ጎን በማለት ለህዝባችን ሰላምና እፎይታን እንስጠው ፤ አንድነታችንን አጠናክረን ብቁ አመራር በመስጠት ወጣቶቻችንን ከህገወጥ ስደት እንታደግ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" ከቡድናዊነት በመውጣት የጋራ ፍላጎት በማስቀደም ለህዝብና አገር መስራት አለብን " ብለዋል።

" መስቀላችን አንድነታችን የምናጠናክርበት ፣ ሰላማችን ጠብቀን በመከራ ላይ የሚገኘው ተፈናቃይ ህዝባችን ወደ ቄየው የምንመልስበት ፤ የትግራይ ግዛት ሙሉ በሙሉ ተረጋግጦ ወደ እድገት የምናማትርበት ጊዜ ይሁንልን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ የመስቀል በዓልና ደመራን ምክንያት በማድረግ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት ያስተላለፉት የህወሓት ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለመላ ህዝቡ ፣ ለዳይስፖራው እና ለጸጥታ ኃይሎች እንኳን አደረሳችሁ ካሉ በኃላ" " የተጠናከረ ፓለቲካዊ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ይገባል " በማለት አሳስበዋል።

በዓሉ መስከረም 17/2017 ዓ.ም በዓዲግራት መከበር የሚቀጥል ሲሆን የሃይማኖት መሪዎችና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መምእምናን በተገኙበት እንደሚከበር ዓዲግራት የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል። 

ፎቶ/ቪድዮ፦ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በመቐለ ጮምዓ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ። #ኦርቶዶክስተዋሕዶ @tikvahethiopia
#Ethiopia

" በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል " - የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በመላው ሀገሪቱ በተለይም #በአዲስ_አበባ መስቀል አደባባይ የተከበረው የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ህዝብ ፣ ለሀይማኖት አባቶች ፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ፣ ለወጣቶችና በተለይ ደግሞ  የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡት የፀጥታ እና ደኅንነት ኃይሎች ምስጋና አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ጨምሮ በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቀዋል።

ከንቲባዋ ፥ " በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አስተዋፅዖ ላደረጉ የሀይማኖት አባቶች ፣ የከተማው ወጣቶች ፣ ሲያስተባብሩ ለነበሩ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እንዲሁም ዶፍ ዝናብ ሳይበግራቸው በዓሉ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዲከበር ላደረጉ የጸጥታ ሃይሎችና የከተማው ነዋሪዎች ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና እናቀርበላ " ብለዋል።

#የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋሕዶቤተክርስቲያን
#Ethiopia #AddisAbaba

@tikvahethiopia
#መስቀል

መልካም የመስቀል በዓል !

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦

" ባለፉት ዓመታት ሲፈታተኑን የቆዩ ዙሪያ መለስ ችግሮች መስቀሉ ባስተማረን ሰላማዊ መንገድ እልባት እንዲያገኝና ህዝባችን ያለምንም ስጋት ወጥቶ እንዲገባ ፣ ሰርቶ እንዲያተርፍ ፣ ተምሮ እንዲያውቅ ፣ ሃይማኖቱን በነጻነት እንዲከተል መንግሥትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለዘላቂ ሰላምና አንድነት አበክረው እንዲሰሩ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። "

@tikvahethiopia
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራትም፣ በብራንድም፣ በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ  በፈለጉት ስክሪን መጠን ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን።

ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፊት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ። በላፕፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
" አረጋዊ ካህኑ ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት መ/መ/ቀ/ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ አረጋዊ ካህን ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል።

መ/መ/ቀ/ወ/ኢየሱስ አያሌው በላስታ ላሊበላ ልዩ ቦታው ጥል አስፈሬ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ የተወለዱ ሲሆን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ስርስቲያን ለ41 ዓመታት ያህል ከዲቁና እስከ እልቅና ድረስ በትሕትና ሲያገለግሉ እንደነበር ተገልጿል።

መስከረም 16 ቀን 2017 በሽምግልና ዘመናቸው ባለቤታቸውን ጨምሮ ከልጆቻቸው ጋር እጅግ ልብ ሰባሪና ዘግናኝ በሆነ አሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉና ለረጅም ጊዜ ባገለገሉበት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክስርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

ሀገረ ስብከቱ ግድያ በማን እንደተፈጸመና ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የተያዘ አካል ይኖር እንደሆነ የሰጠው ቃል የለም።

ከልጆቻቸው አንዱ ዲያቆን መልአክ ወልደ ኢየሱስ የአባቱን ፈለግ ተከትሎ የቤተ መቅደሱ አገልጋይ ነበር ተብሏል።

ትላንትና መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ/ም መ/ሰ/ቆ/አባ ሰይፈ ገብርኤል ገረመው የወረዳው ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በሞጆ ደ/ብ/ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የጸሎተ ፍትሐት ተከናውኗል።

መረጃው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ነው።

@tikvahethiopia
#Oromia

" በኦሮሚያ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እኛ ዝግጁ ነን " - ጃል ሰኚ ነጋሳ

" በጃል መሮ (ኩምሳ ድሪባ) ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ የማዕከላዊ ዞን የቀድሞ አዛዥና የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ጃል ሰኚ ነጋሳ አሳውቀዋል።

' ከተመረጡ ' መገናኛ ብዙሃን ጋር በስልክ ቆይታ ያደረጉት ጃል ሰኚ ባለፈው ረቡዕ ዕለት ወጥቶ ሲዘዋወር የነበረው የማዕከላዊ ዞን ዕዝ በጃል መሮ ከሚመመራው ቡድን መነጠሉን የሚገልጸው መግለጫ " አዎ የኛ የቡድናችን ነው " ሲሉ አረጋግጠዋል።

ጃል ሰኚ ፥ " (የኦነሰ) ህግና ደንብ መተዳደሪያ ደንብ የሌለው ድርጅት ነው " ብለዋል።

" ጥፋት ሲሰራ ተጠያቂነት የሌለበት ድርጅት ነው፣ ህግና ደንብ ሲኖር አንዱ ሲያጠፋ ለማስተካከል የሚያስችል ህግ ይኖራል ግን አሁን በአንድ ሰው የሚመራ መሆኑን አይተንና ተረድተን እንዲሁም ወደ ድርጅቱ ህግና ደንብ ተመልሰን እርስ በእርሳችን እናስተካክል ብለን ለኦሮሞ ህዝብ ባለን ክብር ባህልና ወጉን ጠብቀን ነው በህዝቡ ውስጥ የምንቀሳቀሰው ከዚህ ባለፈ በህግ ሊታይ ይገባል፤ በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ በ2017 በተደነገገው ህግና ደንብ መመራት አለብን ብለን ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራር ጋር መቀጠል አንችልም ብለን ነው መግለጫ ያወጣነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" አሁን ዋና አዛዥ የምንለውን ወደፊት ኦሮሚያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት ጋር ተነጋግረን ነው የምንመርጠው ፤ ስለዚህ ከዚህ በኃላ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አይወክለንም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ጃል ሰኚ በኦሮሚያን ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።

" በሰላማዊ መንገድ ስንል በድርጅቱ ፕሮግራም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የቀጠለውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉም ይታትራል። ስለዚህ መንግሥት ከሰላማዊ መንገድ ከእኛ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ከሆነ እኛም ለመነጋገር ዝግጁ ነን ፤ እንዴት ነው የምንነጋገረው ? የት ነው ? ከማን ጋር ? የሚለውን የውይይቱ ጊዜ ሲደርስ ይገለጻል " ብለዋል።

አሁን ላይ ከመንግሥት ጋር ድርድር እየተደረገ እንደሆነ ተጠይቀው " አሁን ከመንግሥት ጋር የጀመርነው ግንኙነት የለም " ሲሉ መልሰዋል። #ቪኦኤአፋንኦሮሞ

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት🚨

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡

መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡

በዚህም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

መድኃኒቱ ' ሻይንፋርም ' በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ነው።

(የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)

@tikvahethiopia
2024/09/29 04:21:51
Back to Top
HTML Embed Code: