Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት የፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ የቀብር ስንስርዓት እሁድ ጷጉሜን 3/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን ይፈፀማል። በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት ባስተማሩበትና በሰሩበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ራስ መኰንን አዳራሽ የስንበት…
የፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ የቀብር ሥነ-ሥርዓት  ዛሬ ተፈጽሟል።

የፕሮፌሰር እንድሪያስ የቀብር ሥነሥርዓት የተፈፀመው በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ነው።

በቀብር ሥነሥርዓቱ ላይም ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ የሀይማኖት አባቶች የፕሮፌሰር እንድርያስ ወዳጅ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ከቀብር ሥነሥርዓቱ አስቀድሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፊት ለፊት በተጣለ ድንኳን የሽኝት ሥነሥርዓት ተካሄዷል።

በዚያ የስንብት ዝግጅት ላይ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የክልል ፕሬዚዳንቶች ፣የፕሮፌሰር እንድሪያስ ወዳጆችና ቤተሰቦች ተገኝተው እንደነበር ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

ፕሮፌሰሩ በመምህርነታቸው ፣ በፍልስፍናቸው ይታወቁ ነበር።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ሆነው  ለ9 ዓመታት አገግለዋል። የየቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አማካሪም ሆነው ሰርተዋል።

በተወለዱ 79 ዓመታቸው ነሀሴ 23/2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ  የአሉላ አንድሪያስ ወላጅ አባት ናቸው።

Photo Credit : Sheger FM, Abel G/Egziabeher, Addis Admas Newspaper

@tikvahethiopia
#ትንሳኤ70እንደርታ

" የመቐለ ከተማ አስተዳደር የፈቀድልን ህዝባዊ ስብሰባ ተከለከልን " ሲል ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታውን አሰማ።

የፓርቲው ሊቀመንበር ከበደ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃል ፥ _ እሁድ ጳጉሜን 3/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አስተዳደር ግቢ በሚገኘው አግኣዚ የስብሰባ አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ተፈቕዶልን አባልና ደጋፊዎቻችን ጠርተን ስናበቃ አዳራሽ እንዳንገባ በታጣቂዎች ተከልክለናል " ብለዋል።

" በህጋዊ መንገድ የተፈቀደ ህዝባዊ ውይይት መከልከልና ታዳሚዎች ማንገላታት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው " ያሉት የፓርቲው ሊቀመንበር በተግባሩ ማዘናቸው በመግለፅ ከሚመለከተው አካል ግልፅ ማብራርያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተናግረዋል።

" የመቐለ ከተማ ፀጥታ ፅ/ቤት በፃፈልን ደብዳቤ መሰረት ስብሰባውን የፀጥታ ጥበቃ ለማድረግ ፓሊስ መድቦ በቦታው የተገኙ ሲሆን ማንነታቸውና ተጠሪነታቸው የማይታወቁ ሌሎች ሃይሎች ተሳብሳቢው ወደ ግቢ እንዳናሰግባ የአዳራሹ ሰራተኞች ሳይቀር እንዳይገቡ በር ላይ ለነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ትእዛዝ በመሰጠቱ ምክንያት ስብሰባው ሳይደረግ ቀርተዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

" እንደምክንያት ያቀረቡትም የከንቲባ ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ለጋስ ማርያም ' እኔ ካልደወልኩኝ እንዳይገቡ ብለዋል ' የሚል ሲሆን ግለሰብዋ በደብዳቤ የፈቀዱትን ስብሰባ በዚህ መንገድ የከለከሉበት ምክንያት ለመጠየቅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስላካቸውን በመዝጋታቸው ምክንያት ልናገኛቸው አልቻልንም " በማለት ገልጸዋል።

የመቐለ ከተማ ፀጥታ ዘርፍና ፓሊስ መንግስታዊ ሃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት መሞከሩን አመልክተው " ምስጋና ይገባዋል " ብለዋል።

የመቐለ ከተማ አስተዳደርና ፓሊስ እስከ አሁን ሰዓት ስለ ክልከላው የሰጠው ይፋዊ ማብራርያም ሆነ መግለጫ የለም። 

ትንሳኤ 70 እንደርታ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ከአንድ ዓመት በፊት ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግል ለማካሄድ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ መመስረቱ ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Urgent🚨 በአማራ ክልል፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ፣ ጠለምት ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት አልፏል። በርካቶችም ችግር ላይ ወድቀዋል፤ ተፈናቅለዋል። ለተፈናቃዮቹ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል። ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ወረዳው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርቧል። የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ቃል ፦ “…
#ጠለምት🚨

“ ናዳው ቀጥሏል፡፡  አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 25 ነው ” - ወረዳው

የመሬት መንሸራተት አደጋው መቀጠሉ የተነገረለት ሰሜን ጎንደር ዞን በተለይ ጠለምት ወረዳ የሟቾች ቁጥር መጨመሩን ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የተከተው ይሄው አደጋ የብዙዎችን ሕይወት መቀጠፉ የሚታወስ ሲሆን፣ በተለይ በጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ከመሬት መንሸራተቱ በተጨማሪ በሌሎች ቀበሌዎችም “ የህድሞ ” ቤት ናዳ አደጋ መከሰቱን ወረዳው ከሳምንት በፊት ገልጾልን ነበር፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ፣ እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ደግሞ የሟቾች ቁጥር በ15 መጨመሩን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጋሻው እንግዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

“ ናዳው ቀጥሏል፡፡ በጠለምት ወረዳ የሟቾች ቁጠር 25 ደርሷል ” ነው ያሉት፡፡

አስተዳዳሪው በዝርዝር ምን አሉ ?

“ በወረዳው በሚገኙ ቀበሌዎች በናዳና የጎርፍ አደጋ ምክንያት በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡

ከነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ብቻ አራት ወንዶች፣ 11 ሴቶች በአጠቃላይ 15 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች በድምሩ አራት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 29 ቀን ድረስ በአጠቃላይ በወረዳው የሞቱ ሰዎች ብዛት 25 ደርሷል፡፡

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ብዛት ደግሞ 10 ደርሷል፡፡ 456 ሰዎች የእርሻ መሬት ተጎድቶባቸዋል፡፡ 476.5 ሄክታር ሰብል ተጎድቷል፡፡

2911 እንስሳት ሞተዋል፡፡ 28 መኖሪያ ቤቶችና 236 የንብ ቀፎዎች ወድመዋል”
ብለዋል፡፡

የተለያዩ ተቋማት የተለያዩ ድጋፎችን እንዳደረጉ የገለጸው ወረዳው፣ አደጋውና መፈናቀሉ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመሆኑ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል፡፡

አደጋው የተከሰተው በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ሲሆን፣ በተለይም ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት መቆም እንዳልቻለ መገለጹ ይታወሳል፡፡

በዞኑ በሚገኙ ሌሎች ወረዳዎች አደጋው በምን ደረጃ እንደሚገኝ በቀጣይ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡

ፎቶ ፦ ፋይል

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል። ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል። የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል። @tikvahethiopia
ዘንድሮስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ?

የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይገለጻል።

ትምህርት ሚኒስቴር በፈተናው ውጤት ዙሪያ ነገ ከሰዓት ማብራሪያ ይሰጣል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያውን ተከታትሎ ያቀርባል።

ከዚህ ቀደም የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መረጃ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡ 701,749 ተማሪዎች መካከል 684,205 ተማሪዎች ወይም 97.5 በመቶዎቹ ፈተናውን ወስደዋል።

ቀሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶችና ትምህርታቸውን ዘግይተው በመጀመራቸው ፈተናውን አልወሰዱም።

ከተፈታኞቹ ውስጥ 29,718 የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የኦንላይን ፈተና አማካኝነት ፈተናቸውን የወሰዱ ናቸው።

የብሔራዊ ፈተናው ውስጤት ነገ ሰኞ ጳጉሜን 4/2016 ዓ/ም ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፉት ዓመታት በተለይም ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲ) አስገብቶ ፈተና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት / በብዛት ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት የማያስመዘግቡበት መሆኑ ይታወቃል።

ለአብነት በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ 845,099 ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አምጥተው ማለፍ የቻሉት 27,267 / 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

ከዛ በፊት በ2014ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው 50 በመቶና በላይ አምጥተው ያለፉት 30,034 / 3.3 በመቶ ብቻ ናቸው።

ትምህርት ሚኒስቴር በቀጥታ የሚያልፉ ተማሪዎች ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ የሬሜዲያል ፕሮግራም በመስጠት ያን ያለፉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር።

ይህ ስራ " ለአንድ ጊዜ ብቻ " ተብሎ የነበረ ሲሆን በ2015 ቀጥታ ያለፉ ተፈታኞች ውስን በመሆናቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ቃላቸውን ስላጠፉ በይፋ ይቅርታ ጠይቀው የሬሜዲያል ፕሮግራሙ እንዲቀጥል አድርገው ነበር።

° ዘንድሮውስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ?
° ምን ያህል ተማሪ የማለፊያ ነጥብ ያስመዘግባል ?


ሁሉንም አብረን የምናየው ይሆናል።

ነገ ከሰዓት የፈተናው ውጤት በትምህርት ሚኒስቴር ይገለጻል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ ተከታትሎ ያደርሳችኋል።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ መጪውን የ2017 አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የሚያስገኝ የጥያቄና መልስ ውድድር ይዞላችሁ መጥቷል፡፡

እርስዎም የሽልማቱ ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያሉትን የባንኩን ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፆች በመቀላቀል እና ጥያቄውን ቀድመው በመመለስ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉ፡፡

ጥያቄው የሚካሄዳው ማክሰኞ ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን ፤ ጥያቄውን ቀድመው ለመለሱ 5 ተሳታፊዎች በቅደም ተከተል ሊሸልም ዝግጅቱን ጨርሷል።

ከአንድ እስከ አምስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የተለያዩ ሽልማቶችን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።

እርስዎም ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የውድድሩ ተሳታፊ ይሁኑ!! ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
[Telegram] ( https://www.tg-me.com/LionBankSC )
[Facebook] ( https://www.facebook.com/LionBankSC )

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
#Sidama

" በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰና እያስመረረ የሚቀጥል አመራር አይኖርም " - አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ

በሲዳማ ክልል የጸጥታ አካላት ግምገማ መደረጉን ተከትሎ በርካታ የፖሊስ አዛዥች ከስልጣን ሲነሱ በጥቂቶች  ላይ ከህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ምርመራ እንደተጀመረባቸው ተሰምቷል።

ከሰሞኑ በክልሉ ሲካሄድ የሰነበተውን የግምገማና የውይይት መድረክ አሰመልክተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ኃላፊዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ " በህዝብ ላይ ጉዳት እያደረሰና እያስመረረ የሚቀጥል አመራር አይኖርም " ብለዋል።

" በዚህ መሰረት በተደረገ ግምገማ በክልሉ በተለያዩ ዞን ወረዳና ከተማ አስተዳደር ውስጥ
ባሉ መዋቅር ይሰሩ ከነበሩ አመራሮች ውስጥ ሰባት የፖሊስ አዛዦችና ሙሉ የአንድ ክፍለ ከተማ የማኔጅመንት አባላት ላይ ከህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ጋር በተያያዘ ምርመራ እንዲጀመር ታዟል " ሲሉ ገልጸዋል።

ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ከተደረጉ አመራሮች መካከል ፦
- የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ፣
- የሆኮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ
- የጨቤ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ይገኙበታል።

የዳዬ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ከኃላፊነታቸው ታግደው ከመልካም አስተዳደር ችግሮችና ከህገወጥ ንግድ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩባቸው ጉዳዮች እንዲጣራ ታዟል።

በተጨማሪም ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ በዞኑ ህገ-ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ እየተበራከተ በመምጣቱና መቆጣጠር ባለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው ሊነሱ ችለዋል።

በወረዳ ደረጃ ደግሞ የሁላ ወረዳ፣ የአለታ ጩኮ ወረዳ፣ የቡርሳ ወረዳና የጠጢቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ተጣርቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በሀዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ ያሉ ጠቅላላ ማኔጅመንቱ ከኃላፊነት እንዲነሱ መደረጋቸው ተነግሯል።

በመድረኩ በርካታ ችግሮች የተነሱ ሲሆን ለአብነትም ኪራይ ሰብሳቢነትና ባለጉዳይን ማማረር ጎልተዉ የተነሱ ክፍተቶች ናቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ_ከጠቀማችሁ 1. በአዲስ አበባ ከተማ የሜትር ታክሲ አገልግሎት የምትሰጡ ወንድም እህቶቻችን እባካችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። ማክሰኞ ምሽት 4 ሰዓት ገደማ ወደ ጎተራ ማሰለጫ መውረጃ ወይም በተቃራኒ ወደ ቄራ የሚወስደው መስቀለኛ መንገድ አካባቢ አንድ አገልግሎት ሰጪን 3 ተሳፋሪ መስለው የገቡ ወንበዴዎች መሃል አስፓልት ፣ በብዛት መኪና በሚመላለስበት መንገድ ላይ ከውስጥ እቃ ይዘው ሲሮጡ መመልከቱን…
#AddisAbaba

“ የጫት መቃሚያ ፣ የሺሻ ቤቶች የወንጀል ድርጊት የሚዶለትባቸው ቤቶች ናቸው ” - ፓሊስ

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ወንጀሎች እንደሚደርሱባቸው ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡፡

አንዳንዶቹ እንደሚሉት ከሆነ፣ የጸጥታ አካላት ልብስ ለብሰው ጸጥታ አስከባሪ በመምሰል ወንጀል የሚፈጽሙ አሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፦

°  ተመሳስለው ወንጀል የሚሰሩ አካላት ላይ ምን አይነት ክትትል እየተደረገ ነው ?

°  ወንጀል በከተማዋ በምን ደረጃ ይገኛል ?

° ሕዝቡ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ? ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምን አሉ ?

“ ሌባ የተለያዬ የወንጀል አፈጻጸም ስልት አለው፡፡ አንዱ የጸጥታ አካል መስሎ፣ ልብሱን በተለያዬ አይነት መንገድ ለማግኘት ሙከራ አድርጎና ለብሶ ወንጀል ሊፈጽም ይችላል፡፡

ይሄ በጣም ከበ ሁለት ጥፋት ነው፡፡

አንደኛው ህብረተሰቡ ፖሊስ ሊመስለው ከቻለ በፖሊስ ላይ ያለው አመኔታ ምንም ጥያቄ የለውም ይወርዳል፡፡ ሁለተኛው ጉዳት ደግሞ ወንጀሉ በፖሊስ ላይ ጫና/ሥራ ይፈጥራል፡፡

ስለዚህ ጥንቃቄ ማድረግና መረጃዎች በሚኖሩ ሰዓት ቶሎ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በተለይ በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች የሚፈጸሙ ወንጀሎች በጣም አደገኛ ናቸው፡፡ በጣም በጣም፡፡ ትልቅ ዋጋም የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡

ወንጀል ፈጻሚውን በመያዛችን የጸጥታ አካላትን ልብስ ከየት አመጣህ ? ብሎ ለመጠየቅና ተባባሪ የሆነ አካል ካለ ተገቢ እርምጃ ለመውሰድ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርልናል፡፡

ወንጀሉ ላይ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድና ለህዝብ ግልጽ በማድረግ በእንደዚህ አይነት ወንጀል የተሰማሩ ሰዎች ሁለት፣ ሦስቴ እንዲያስቡ እናደርጋለን፡፡

ግን ሰው መረጃ በመስጠት ተባባሪ መሆን መቻል አለበት፡፡

መረጃ ማድረስ ብቻ ሳይሆን ፈጣን ማድረስ ነው መሆን ያለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ሰው መክሯቸው ' መረጃ ስጡ ' ተብለው ነው የሚናገሩት፡፡ ፈጣን ነው መሆን ያለባቸው፤ እንደዚያ ከሆነ ወዲያው በቁጥጥር ሥር እናውላቸዋልን፡፡

ወንጀሎች ከመፈጸማቸው አስቀድሞ ለመፈጸሙ ምክንያት የሆኑ ነገሮችን አስቀድሞ በማወቅ የማስወገድ ሥራ መሰራት አለበት፡፡

ለምሳሌ ፦ የወንጀል መንስኤ ብለን እኛ የምናያቸው የጫት መቃሚያ፣ የሽሻ ቤቶች የወንጀል ድርጊት የሚዶለትባቸው ቤቶች ናቸው፡፡

በዚህ በኩል ፖሊስ የሚወስደው በጣም ጠንካራ የሆነ እርምጃ አለ፡፡ ግን መረጃ ከመስጠት በኩል አሁንም ክፍተቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ እንዳውም ለፖሊስ መረጃ ከመስጠት ይልቅ የመደበቅ ሁኔታ አለ፡፡

ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሆነን ነው የወንጀል መከላከልን ሥራ የምንሰራው፡፡ ግን ግለሰቦቹ ወንጀል ከተፈጸመባቸው ወደ ሚዲያ ሳይሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነው መሄድ የሚጠበቅባቸው፡፡ በትክክል የከተማውን የጸጥታ ሁኔታ ቼክ የምናደርግበትም አግባብ ያ ነው፡፡

ስለዚህ ወንጀል ሰዎች ላይ ሊፈጸም ይችላል፡፡ በተቻለ አቅም በከተማው ላይ የወንጀል ስጋት እንዳይኖር ነው እየተሰራ ያለው፡፡ በ2016 ዓ/ም አጠቃላይ የተቋማችን አፈጻጸም 31 ፐርሰንት ወንጀልን ቀንሰናል፡፡

አዲስ አበባ ትልቅ ከተማ በመሆኗ ለተለያዩ ወንጀል መፈጸሞች ምክንያት የሆኑ ነገሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡ ከክልል ከተሞችም በብዛት ሰዎች ይመጣሉ፡፡ ሰው ሥራ፣ ቋሚ አድራሽ ከሌለው ያለው አማራጭ አንድም መለመን ካልሆነም ወደ ዘረፋ የሚገባበት ሁኔታ ይኖራል፡፡

አጠቃላይ የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ ተቋቁመው ከግምት ውስጥ በማስገባት የወንጀል መከላከልን ሥራ በመስራት ከተማዋ የጸጥታ ሁኔታ ላይ እንድትሆን ማድረግ እጅግ በጣም ትልቅ ሥራ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡

ከመደበኛ ሥራችን ጎን በጎን ኦፕሬሽናል የሆኑ ሥራዎችንም በመስራት በሌቦች ላይ ብቻ አይደለም በተቀባዮችም ጭምር ትልቅ ሥራ እየተሰራ ነው፤ በተለይ የመኪና እቃ ስርቆት በሚፈጽሙት፣ እቃውን በሚሸጡ፣ በሚደልሉ ላይ፡፡

በአዲስ ከተማና በልደታ ክፍለ ከተማ እንኳ በተሰራው ሥራ ወደ 71 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውለናል፡፡ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የመኪና እቃም ይዘናል፡፡

ሆኖም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ' ወንጀል ተፈጸመብኝ ' የሚል ሰው ሊያጋጥም ይችላል፡፡ እሱን ለመከላከል ደግሞ የምንሰራቸው ሥራዎች አሉ፡፡

ወንጀል የሚፈጽማባቸው አካላት ወደ ፖሊስ መጥተው ያመልክቱ፡፡ በርካታው ሰው ከዚያ ይልቅ ወደ ሚዲያ ይሄዳል፡፡ ወደ ሚዲያ አይሂድ ማለት አይደለም ግን ወደ ፖሊስ ቢመጣ ያለንበት የመከላከል አቅም የቱ ጋ ድርሷል ለማለት ይረዳናል።
"

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል። የፖሊስን የምርመራ…
#Update

ፍ/ቤት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ።

" የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ፤ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል " ተብለው የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱ ተሰማ።

የፌደራል መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ቡድን፦
- ዮሃንስ ዳንኤል
- አማኑኤል መውጫ፣
- ናትናኤል ወንድወሰን፣
- ኤልያስ ድሪባ፣
- ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ በተባሉ ግለሰቦች ላይ ሲያከናውን የቆየውን የምርመራ ማጣሪያ ስራ አጠናቆ መዝገቡን ለዐቃቤ ሕግ ማስረከቡን አስታውቋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ በችሎት ተሰይሞ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም መረከቡን ጠቅሶ፤ ማስረጃ ተመልክቶ ክስ ለማቅረብ እንዲያስችለው ክስ ለመመስረቻ ጊዜ 5 ቀን እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች " ዐቃቤ ህግ ምርመራውን ሲመራ ቆይቶ እንደአዲስ መዝገቡን ተመልክቼ ክስ ለመመስረት፣ ለመወሰን እንዲያስችለኝ የክስ መመስረቻ ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱ " ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።

ጠበቆቻቸው ደንበኞቻቸው ተጨማሪ ጊዜ በእስር ሊቆዩ እንደማይገባ ገልጸው፤ የዋስ መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ዐቃቤ ህግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ መፍቀድ ስነ ስርዓታዊ መሆኑን በማመን የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለዐቃቤ ህግ የ5 ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በዚህም መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ/ም ክስ ይመሰረታል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ባጋጠመ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ከ10 በላይ ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ተቀጠፈ።

የትራፊክ አደጋው ዛሬ  ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት አከባቢ የተከሰተ ሲሆን የሰሌዳ ቁጥር TG - 04539 የሆነ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከዓድዋ ወደ መቐለ ሲጓዝ ወርዒ ልዩ ቦታ  እንዳፈላሲ ቁልቁለት ሲወርድ ወደ ገደል በመግባቱ ነው አደጋው ያጋጠመው።

በውስጥ ከተሳፈሩ ሰዎች ከ10 በላይ ወድያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ 5 ሰዎች በፅኑ ተጎድተዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የደረሰው መረጃ እንደሚያመላክተው 48 ሰዎች የመጫን አቅም ያለው መለስተኛ አውቶቡስ በአጋጣሚ 20 ሰዎች ብቻ አሳፍሮ መጓዙ ለሟችና ቁስለኞች መቀነስ ምክንያት ሆኗል።

የአደጋው ምክንያት ገና በመጣራት ላይ ነው።

ይህ ወር በርካታ በዓላት የሚከበሩበት በመሆኑ ብዙ የትራፊክ እንቅስቃሴ ይኖራል ፤ በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ አይለያችሁ።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia 
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ውጤት : የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይገለጻል።

የትምህርት ሚኒስቴር በውጤቱ ዙሪያ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል።

ይጠብቁ !

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
2024/09/30 14:30:05
Back to Top
HTML Embed Code: