#Amhara
የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል ምን አለ ?
- ይህ የ ' ሰላም ካንውስል ' በአማራ ክልል ውስጥ የተፈጠረውን አለመስማማት እና አለመግባባት ተከትሎ የተከሰተውን የእርስ በእርስ ጦርነት በሰላም ለመቋጨት መንግሥትን እና ታጥቀው ጫካ የገቡ የፋኖ አባላትን ለማደራደርና ለማወያየት ይቻል ዘንድ ለመመቻቸት የተሰየመ ነው።
- ድርሻው መንግሥት እና የፋኖ አባላትን ለድርድር፣ ለውይይት እንዲበቁ ማመቻቸት ብቻ ነው።
- ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ደረጃ ፣ በየትኛውም ቦታ ፣ በየትኛውም አደራዳሪ የመንግሥት ኃይሎች እና በጫካ የሚገኙ የፋኖ ወንድሞቻችን ቢያስን ዘላቂ ተኩስ ለማቆም ንግግር እና ድርድር እንዲያደርጉ ይህ ካውንስል ተሰይሟል።
- በጦርነት እንጨራረሳለን እንጂ አንሸናነፍም።
- የአማራ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ምስቅልቅል ውስጥ ይገኛል።
- ግጭቱ አጠቃላይ ሀገሪቱን ለከፍተኛ ጉዳት እና ወደባሰ የድህነት አረንቋ እየከተታት ይገኛል።
- ለዚህ ግጭት መነሻ የአማራ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቃቸው የነበሩ ጥያቄዎች በሰለጠነ ንግግር እና ድርድር አለመፈታታቸው ወይም ደግሞ የሚፈቱበትን ሂደት የሚያመለክት ግልጽ ፍኖተ ካርታ አለመቀመጡ ነው።
የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ተብለው የተለዩት ፦
° የተዛባ ትርክት ማረቅና ማስተካከል
° ህገመንግስት ይሻሻልልን
° የወሰን እና ማንነት ጉዳይ
° ፍትሃዊ የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ውክልና ጉዳይ
° በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ የአማራ ህዝብ ጉዳይ
° የአዲስ አበባ የመልካም አስተዳደር እና አድሏዊ አሰራር ችግር አለመቀረፉ
° በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ንጹሃን የአማራ ተወላጆች ለሚደርስባቸው ግድያ እና መፈናቀል ተጠያቂነት አለማስፈን ጉዳይ .. የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
- እነዚህ ጥያቄዎች በቅንነት በሀገሪቱ ጥላ ስር በንግግር እና በድርድር ሊፈቱ የሚገባቸው እንጂ ወደ ጦርነት የሚያስገቡ አልነበሩም።
- የክልሉ መንግሥት በህዝብ ዘንድ ያለው ቅቡልነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ሄዷል።
- ክልሉም ከችግሩ ሚያወጣው ፣ የተደራጀ የፖለቲካ እሳቤ የሚፈጥርለት ምሁር የመከነ እስከሚስል ደርሷል።
- ላለፉት ዓመታት የኢኮኖሚን ችግር የሚቀርፍ የማሻሻያ ድጋፍ ይደረጋል ሲባል በተለያዩ አጀንዳዎች በመወጠር እና የደህንነት ስጋት ውስጥ እንዲወቅ ሆኖ በከፋ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ውስጥ ይገኛል።
- ከ ' ህወሓት ' ጋር የተደረገው ስምምነት በአግባቡ ሳይተገበርና የአማራ ህዝብ ህልውና ስጋት ዋስትና ሳይበጅለት ቀርቶ ነው የክልሉ የጸጥታ ችግር ተባብሶ ከ2015 ሀምሌ መጨረሻ አንስቶ በነፍጥ የታገዘ ግጭት የጀመረው። በዚህ ምክንያት ለአንድ አመት የሚጠጋ ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነበር።
- ለአንድ አመት በተጠጋው ጦርነት የክልሉ ህዝብ መከራ እና ምስቅልቅል ህይወት ውስጥ ይገኛል።
- በአሁን ጊዜ በርካታ የክልሉ አካባቢዎች በመንግስት እና የአማራን ህዝብ ጥያቄ ለማስመለስ ጫካ ገብተናል ባሉ ' ፋኖዎች ' መካከል በሚካሄድ በትጥቅ የታገዘ ጦርነት ፦
➡ ንጹሃን ተገድለዋል።
➡ ከ12 እስከ 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
➡ ከ3.6 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ሆነዋል።
➡ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ክፉኛ ተጎድቷል።
➡ የግል እና የመንግስት ተቋማት ከቦታ ቦታ ለመጓጓዝ ባለመቻላቸው አገልግሎት አሰጣት ክፉኛ ተዛብቷል።
➡ ነፍሰጡር እናቶች በአግባቡ የአምቡላንስ አገልግሎት አያገኙም።
➡ እናቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ከጦርነት ተሳትፎ ውጭ የሆኑ ዜጎች ለከፋ የስነልቦና ጫና ተዳርገዋል።
➡ እጋታ ተስፋፍቷል።
➡ ዜጎች ያለ ከልካያ በጠራራ ጸሀይ ይዘረፋሉ፤ ይገደላሉ።
➡ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ተስተጓጉለዋል።
➡ ህዝቡ ለሁለት ወገን ግብርና ቀረጥ ይከፍላል።
ይህ ጦርነቱ ካመጣቸው መዘዞች መካከል ነው።
- ችግሩን ለመቅረፍ በአዲስ አበባ እና ከባህር ዳር ከህብረተሰቡ የተውጣጣ ክፍል ውይይት አድርጓል። በውይይቶቹ የሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሲቪል አመራሮችም ተገኝተው ነበር።
- ጦርነቱ አሸናፊነት የሌለው የእርስ በእርስ ጦርነት ስለሆነ በንግግር በውይይት በድርድር ይፈታ የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል።
- በክልል ፣ በሀገር ደረጃ በየትኛውም መንገድ ይሁን የአማራን ህዝብ ጥቅም ይዤ ነው የምዋጋው ከሚል ኃይል ጋር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር እንዲደረግ የመፍትሄ ሀሳብ ተቀምጧል።
- መንግሥት አሸናፊ የሌለው ይሄ አውዳሚ ጦርነት በንግግር እና ድርድር ለመፍታት " ፍቃደኛ ነኝ ነገር ግን ፋኖ አደረጃጀቱና መሪው ብዙ ነው ለመደራደር አንድ መሆን አለባቸው " በማለቱ የድርድሩ ደረጃ ጊዜ ፣ ቦታ እና ተደራዳሪዎች ተለይተው ለንግግር እና ድርድር እንዲበቁ ይህ 15 አባላት ያሉት የሰላም ካውንስል ተመርጧል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia

#Tigray
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቄያቸው ሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማይ ፀብሪ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል " ሲል አሳውቋል።
ከ3 ዓመት በላይ በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ለመጓዝ ዝግጁ እንዲሆኑ አርብ ማታ ተነግሯቸው እንደነበር እና ቅዳሜ የማጓጓዝ ስራው መጀመሩ ተሰምቷል።
ወደ ቄያቸው እንደሚማለሱ የተነገራቸው ተፈናቃዮች ወደ 10 ሺህ እንደሚደርሱ ተነግሯል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምንጮች ሌሎችንም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስና ወደ ቤታቸው የማስገባት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በምዕራባዊ ዞን በቀጣይ ሳምንታት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#ደመወዝ #ደቡብኢትዮጵያ ° " ...ድርጊቱ የደመወዝ ቅሸባ ነው ሊባል የሚችለው ፤ እንዲህ አይነት የደመወዝ አከፋፈል ሰምተንም አናውቅ " - ሰራተኞች ° " ከእኛ #የሚወርደው የበጀት ሀብት እኮ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል የሚያስችል ነው " - የክልል ፋይናንስ ቢሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች " የደመወዝ ይከፈለን " ጥያቄ በብርቱ ከተነሳባቸው አካባቢዎች አንዱና ዋነኛው…
#SouthEthiopia
° " የግንቦት ወር ደመወዝ እስከ ዛሬ አልወሰዱም " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር
° " ተቸግረን ያዘገየነውን የመምህራን ደመወዝ ከሰኞ ጀምረን ክፍያ እንፈጽማለን " - የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያሉ መምህራን ከደመውዝ ጋር በተያያዘ ያቀርቡ የነበሩትን ተደጋጋሚ ጥያቄ ስናቀብላችሁ እንደነበር ይታወሳል።
በተደጋጋሚ ይነሱ የነበሩ የደመውዝ ጥያቄዎች አሁን ላይ በተወሰነ መልኩ ምላሽ ቢያገኙም አሁንም ጥያቄያቸው ያለተመለሰላቸው የመንግስት ሰራተኞች በተለይ በወላይታ ዞን ያሉ መምህራን ችግር ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በተጨማሪ የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝደንት አቶ አማኑኤል ጳዉሎስ ፥ " በወላይታ ዞን ሆብቻ ወረዳ የግንቦት ወር ደመወዝ እስከ ዛሬ አልወሰዱም " ብለዋል።
ሌሎች 2 ወረዳዎች ማለትም ቦሎሶ ሶሬ እና ካዎ ኮይሻ 50% ብቻ መውሰዳቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" የመምህራን ችግር መባባሱን ተከትሎ ከዞኑ ባለስልጣናት ጋር ልንነጋገር ቀጠሮ ይዘናል " ያሉት አቶ አማኑኤል " ችግሩ በቶሎ መቀረፍ አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎበዜ ጎዳና ፤ ችግሩ የተፈጠረዉ ክልሉ ለማዳበሪያ ውዝፍ እዳ የሰጠዉ ትኩረት የካሽ እጥረት በመፍጠሩ መሆኑን ገልጸዉ ይህ ችግር አሁን ላይ መፈታቱን ገልጸዋል።
" የዘገየውን የመምህራን ክፍያ በጣም ባጠረ ሁኔታ ለመክፈል ገንዘብ ጠይቀን ተፈቅዶልናል " ያሉት ኃላፊው " ከተቻለ ሰኞ ጀምረን መክፈል እንጀምራለን " ብለዋል።
መምህራንም ከችግራቸዉ ይወጣሉ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaHawassa

#Ethiopia የደቡብ ክልል ፈርሶ እንደ አዲስ የተዋቀሩት #ሁሉም አዳዲስ ክልሎች በጀት የሚደለደልላቸው በነበረው የድሮ ቀመር እንደሆነ ተገልጿል። ገንዘብ ሚኒስቴር #አዲስ_ቀመር የማዘጋጀት ምንም ስልጣን እንደሌለው ይህ ስልጣን የፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሆነ አመልክቷል። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የ2017 በጀት ረቂቅን ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባብራሩበት ወቅት ስለ አዳዲሶቹ ክልሎች…
የበጀት ጉዳይ !
" ' ቀመሩ እኔን ተጠቃሚ እያደረገኝ አይደለም ' የሚሉ ክልሎች እየመጡ ነው " - አቶ አገኘሁ ተሻገር
የፌዴሬሽን ም/ቤት በተለይም ከአዳዲሶቹ ክልሎች የድጎማ በጀት ቀመሩ እንዲሻሻል ጥያቄ እየቀረበለት መሆኑን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል።
አቶ አገኘሁ ፥ " ' ቀመሩ እኔን ተጠቃሚ እያደረገኝ አይደለም ' የሚሉ ክልሎች እየመጡ ነው ይሄ ቀመር እየጠቀመን ስላልሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሻሽልልን የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
በመሆኑም ም/ቤቱ ጉዳዩን በልዩ ትኩረት ተመልክቶ እምርጃ መውሰድ እንዳለበት አስገንዘበዋል።
ይህ ካልሆነ ግን ፍትሃዊ እኩል የመልማት እድል ማረጋገጥ እንደማይቻል ተናግረዋል።
ለመጨረሻ ጊዜ የክልሎች የበጀት ድጎማ ቀመር የተሻሻለው በ2010 ዓ/ም ነበር። በወቅቱ 3 ዓመት ይቆያል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ፦
- የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ
- የግብርና እና የቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ መረጃዎች አለመሟላት ቀመሩን ለማሻሻል እንቅፋት ሆኗል።
ያለፉት 30 ዓመታት የበጀት ድጎማ ቀመር ለ9 ጊዜ ተሻሽሏል። የመጨረሻው ማሻሻያ 2010 ላይ ነበር።
በቅርቡ በድጎማ በጀት ቀመር ዙሪያ በተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ፤ የደቡብ ክልል ፈርሶ እንደ አዲስ የተዋቀሩት ሁሉም አዳዲስ ክልሎች በጀት የሚደለደልላቸው በነበረው የድሮ ቀመር እንደሆነ ገልጸው ነበር።
ሚኒስቴሩ አዲስ ቀመር የማዘጋጀት ምንም ስልጣን እንደሌለው በመግለጽ " ይህ ስልጣን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው " ሲሉ ተናግረው ነበር።
በአዳዲሶቹ ክልሎች ከበጀት ጋር በተያያዘ ፤ " የበጀት እጥረት " የሚሉ ጥያቄዎች እንደሚነሱ ይታወቃል።
የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ መዘግየትና በአግባቡ አለመክፈልም በስፋትም ከአዳዲሶቹ ክልሎች የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው።

#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቄያቸው ሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማይ ፀብሪ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል " ሲል አሳውቋል። ከ3 ዓመት በላይ በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ለመጓዝ ዝግጁ እንዲሆኑ አርብ ማታ ተነግሯቸው…
#Update
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ ከትላንትና ጀምሮ በጦርነት ምክንያት ከቤትን ንብረታቸው ተፈናቅለው እስካሁን በመጠለያ የነበሩ የሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማፀብሪ ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ መጀመሩን አሳውቋል።
ከማይ ዓይኒ፣ ከማይ አንበሳ፣ ከመድኃኔዓለም እና ውሕደት ከተባሉ ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ከአንድ ሺሕ አምስት መቶ በላይ ተፈናቃዮች ትላንት ተመልሰዋል።
ዛሬም ማይ ፀብሪን ጨምሮ የፀለምቲ ወረዳ ስድስት ቀበሌዎች ተፈናቃዮች ተመልሰዋል።
አንዳንድ ቃላቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ተመላሾች ህዝቡ " እንኳን ደህንና መጣችሁ ! " ብሎ በመልካም ሁኔታ እንደተቀበላቸው ፤ ታጣቂዎች ግን እስካሁን እንዳልወጡ፣ ትጥቅም እንዳላወረዱ ይህ ስጋት እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል።
ይህ አካባቢ ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልላዊ መንግሥት ስር የጠለምት ወረዳ አስተዳደር ተብሎ ነበር።
የጠለምት አማራ ወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ አለቃ አለነ አሰጋ ፤ " የጠለምት ወረዳ አስተዳደር የጸጥታ መዋቅር፣ ከዛሬ 3 ቀናት በፊት በግዳጅ ሥራ እንዲያቆም ተደርጓል " ብለዋል።
አለቃ አለነ ፥ በሥራ ላይ የቆየው ፖሊስ እና የጸጥታ መዋቅሩ ወደ ዓዲኣርቃይ አካባቢ መንቀሳቀሳቸውን ገልጸዋል።
እርሳቸው ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ግን ከአካባቢው አለመልቀቃቸውን ጠቁመዋል።
በአካባቢው የጸጥታ ስጋት መኖሩን ጠቁመው፣ መንግሥትም ይህንኑ ተገንዝቦ፣ ነዋሪው ኅብረተሰብ የራሱን የጸጥታ መዋቅር እንዲዘረጋ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
አለቃ አለነ የጠለምት የወሰንና የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደመሆናቸው በአካባቢው ላይ ያላቸውን የወሰን እና የማንነት ጥያቄውን በቦታው ላይ እያሉ ማቅረባቸውን እንደሚቀጠሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ፌደራል መንግሥት የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው የትግራይ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈናቃዮች ወደቦታቸው ከተመለሱ በኃላ ከነዋሪው ህብረተሰብ ጋራ በመሆን የጋራ አስተዳደር ከአቋቋሙ በኋላ የሚነሳው ጥያቄ በሕዝበ ውሳኔ / ሪፈረንደም ምላሽ ቢያገኝ የተሻለ እንደሆነ መግለጹ አይዘነጋም።

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ የወረቀት የነዋሪነት መታወቂያ ሙሉ በሙሉ መቆሙ ይፋ ሊደረግ ነው።
ከተማዋ በነዋሪነት ለመዘገበቻቸው ነዋሪዎች ለዘመናት በወረቀት ስትሰጥ የነበረውን የነዋሪነት መታወቂያ /City Residency ID/ ካርድ ሙሉ ለሙሉ ማቆሟን ይፋ ታደርጋለች።
አ/አ በዘመናዊ የከተማ አስተዳደር የከተማ የነዋሪነት መታወቂያን በተደራጀ መልኩ በመስጠት ከ75 ዓመት በላይ እድሜን አስቆጥራለች።
የወረቀት መታወቂያን ለመጨረሻ ግዜ ተሰናብታ ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል መሻገሯን ሰኔ 25/2016ዓ.ም ይፋ እንደምታደርግ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሳውቋል።

" ፍጹም ሀሰተኛ / የውሸት ይዘት ነው ተጠንቀቁ " - የጠ/ሚ ጽ/ቤት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንደሰረዘው ተደረጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው። የጠ/ሚ ጽ/ቤት ያወጣው መግለጫ አስመስሎ አንድ የተቀነባበረ የጠ/ሚ ጽ/ቤት አርማ ያለበት መግለጫ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል። ይኸው መግለጫ ፦ - ኢትዮጵያ ከሶማሊያ…
#Ethiopia
ይህ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስም በተለይ በ X መተግበሪያ ላይ እየተራጨ ያለው መግለጫ ሀሰተኛ እና የተቀነባበረ ነው።
የሚኒስቴሩን የቀድሞ ሎጎ በመጠቀም እየተሰራጨ ያለው ይህ መረጃ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ፦
- በUN
- በEU
- BRICS (ኢትዮጵያ እራሷ አባል የሆነችበት)
- በኢስላሚክ ሀገራት ከፍተኛ ጫና እንደሰረዘችው የሚገልጽ ነው።
ይኸው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አወጣው የተባለው መግለጫ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ፣ ቱርክ ውስጥ ለውይይት መቀመጣቸውን እና በሚቀጥሉት ቀናት የጋራ መግለጫ (ከላይ ባለው ውሳኔ) እንደሚሰጡ ያመለክታል።
ከቀናት በፊት በጠ/ሚ ጽ/ቤት ሎጎ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሀሰተኛ መግለጫ ሲሰራጭ ነበር።
መግለጫው በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስም በሀሰት ተዘጋጅቶ የተሰራጨ ሲሆን ያሰራጩት አካላት የመ/ቤቱን የቀድሞ ሎጎ ነው የተጠቀሙት።
ሚኒስቴሩ በመግለጫዎቹ አዲሱን ሎጎ መጠቀም ከጀመረ ወራት ተቆጥሯል።
በሌላ በኩል ደግሞ ፥ በቱርክ አግባቢነት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ቱርክ ውስጥ ለውይይት እና ንግግር እንደሚቀመጡ የሚገልጹ ሪፖርቶች ሲወጡ ነበር። ነገር ግን ምንም ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሶማሊያ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት በይፋዊ የ X ገጹ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው በቱርክ አሸማጋይነት ከኢትዮጵያ ጋር ለሚደረግ ንግግር ወደ አንካራ ቱርክ እንዳቀኑ የሚገልጽ አንድ መረጃ ካሰራጨ በኋላ ሳይቆይ አጥፍቶታል።
ስለ ውይይቱ ሆነ እየተወራ ስላለው ጉዳይ እስካሁን ኢትዮጵያ ያለችው ነገር የለም።
#Ethiopia🇪🇹

" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው " ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት…
#Update
" ውሳኔዉ መስተካከሉ አስደስቶኛል ጥንካሬም ሆኖኛል " - ጸጋ በላቸዉ
" የይግባኝ ዉሳኔዉን ተከትሎ ፍርዱ ወደ 10 መቀነሱ ልክ አልነበረም " - የክልሉ ዋና ዐቃቤ ህግ
• ግለሰቡ በ14 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ተፈርዷል።
በሀዋሳ ፥ የዳሽን ባንክ ሰራተኛዋን ጸጋ በላቸዉ ላይ የጠለፋ ወንጀል የፈጸመዉ የጸጥታ አባሉ ምክትል አስር አለቃ የኋላመብራቱ ወልደማርያም የጠየቀው ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቶ ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መውረዱ ተሰምቶ ነበር።
በወቅቱ በዉሳኔዉ ያዘነችዉ ተበዳይ ጸጋ በላቸዉ ቅሬታ ውስጥ መግባቷን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈዉ ውሳኔ አግባብ አለመሆኑንና ቅጣቱ በጣም እንዳሳመማት ገልጻ ቅሬታ ማቅረቧን መዘገባችን ይታወሳል።
ይህን የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሳኔ በመቃወም ይግባኝ የጠየቀዉ የክልሉ ዐቃቤ ህግ ቅጣቱ መውረዱ ከህግ አንጻር አግባብ አይደለም ብሎ በመከራከር የቅጣት ማቅለያውን ውድቅ በማድረግ ቅጣቱ ተስተካክሎ የ14 አመት ከ6 ወር ውሳኔ ተሰጥቷል።
በዚህ የፍርድ ሂደት አስተያየቷን በመልእክት ያጋራችን ወይዘሪት ጸጋ በላቸዉ በፍርዱ መስተካከል ደስታ እንደተሰማትና ይህም ጥንካሬ እንደሚሰጣት ገልጻልናለች።
" እንደኔ አይነት ጉዳት የደረሰባችሁ እህቶች ሁሉ ወደህግ በመሄድ መጠየቅን አትፍሩ " የምትለው ጸጋ ፥ ከመጀመሪያውም በህግ ላይ እምነት እንደነበራት ተናግራለች።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ኃላፊው አቶ ማቶ ማሩ ፥ " ምንም እንኳን ሚዲያዎች ለዚህ ኬዝ የሰጡት ትኩረት ጉዳዩን ታዋቂ ቢያደርገውም ክልሉ ለሴት ልጅ ጥቃት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ በመሆኑ በርካታ ጠንካራ ውሳኔዎች ተላልፈዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ይህ የጸጋ በላቸዉ ኬዝ ማህበረሰቡን ያስተምራል ለተጎጅዋም ፍትህ ይሰጣል ብለን ስንከታተለዉ የነበረ ጉዳይ ከመሆኑ በላይ ድርጊቱን የፈጸመዉ ግለሰብ ማህበረሰብ ይጠብቃል ተብሎ ኃላፊነት የተሰጠዉ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተነው ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ማቶ ከወራት በፊት የተሰጠውን የይግባኝ ውሳኔ ህጋዊ ድጋፍ የለውም ብሎ በመቃወም የክልሉ ዐቃቤ ህግ ፍርዱ እንዲስተካከል የጣረው ለዚህ ነበር ብለዋል።
ቅጣቱ ከ10 ወደ 14 አመት መስተካከሉን ገልጸው " እንደክልል በዚህ አመት ብቻ ከ256 በላይ ሴቶችንና ህጻናትን የተመለከተ ኬዝ በትኩረት ይዘን እየሰራንበት ነው በተወሰኑት ላይም አስተማሪና ጠንካራ ውሳኔዎች እየተሰጡ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

#National_GAT
ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) መቼ ይሰጣል ?
የ2016 የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ሐምሌ ወር መጨረሻ ሳምንት ይሰጣል።
አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የ3ኛ ዙር አገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) በሐምሌ ወር የመጨረሻ ሳምንት እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።
የ2ኛው ዙር የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በህዳር 2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።
Via @tikvahuniversity

#Somaliland #Turkey
የራስ ገዟ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ሀርጌሳ ካሉት ከቱርክ የቆንጽላ ጄነራል ሌቬንት ቼሪ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ተሰምቷል።
ንግግራቸው ሶማሌላንድ ስለሚያሳስባት ጉዳዮች እና ከቱርክ ጋር ስላላት ግንኙት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር ተብሏል።
ምንም ዝርዝር መረጃ ግን ይፋ አልሆነም።
ንግግሩ ግን በቀጣይ አብሮ ለመጓዝ እና በትብብርም የመስራት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት በመስጠት መጠናቀቁ ተነግሯል።
በሶማሌላንድ ያሉ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቱርክ፣ ሶማሊያን ፦
- የምታስታጥቅ፣
- የምትደግፍ፣
- የምታሰለጥን ሀገር እንጂ የሶማሌላንድ ወዳጅ ሀገር ስላልሆነች ከእሷ ጋር ግንኙነትን ማቋረጥ እንደሚገባ እና ቆንጽላ ጽ/ቤቱ እንዲዘጋ ጥሪ ሲያደርጉ ተመልክተናል።
ከሰሞኑን የቱርክ ስም ተደጋግሞ እየተነሳ ይገኛል።
ሀገሪቱ ኢትዮጵያና ራስ ገዟ ሶማሌላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ በሶማሊያና ኢትዮጵያ በመካከል የተፈጠረውን መቃቃር መፍትሄ እንዲያገኝ የማሸማገል ስራ እየሰራች እንደሆነ የሚገልጹ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው።
በኢትዮጵያም ይሁን በሶማሊያም በኩል ይፋዊ መረጃ ባይሰጥም በአንካራ የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፊት ለፊት ተገናኝተው ይነጋገራሉ እየተባለ ይገኛል።
ትላንት የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ በX ገጹ ከኢትዮጵያ ጋር ለሚደረግ ንግግር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚመራ ልዑክ ወደ ቱርክ አንካራ እንዳቀና ከገለጸ በኃላ መረጃውን ከገጹ ላይ አጥፍቶታል።

#Sidama
በሲዳማ ክልል፣ በሥራ ላይ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ህይወቱ አለፈ።
አንድ ሹፌርም ህይወቱ አልፏል።
ዛሬ ከረፋዱ 3 ሰዓት ላይ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ የደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ ሾፌርን ጨምሮ በስራ ላይ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ ህይወት ቀጥፏል።
አደጋው በወረዳው ' ኤሬርቴ ወንዝ ' አጠገብ ' ቅጥቅጥ ' የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ተነግሯል።
በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ የሰጡት የሲዳማ ክልል ትራፊክና አደጋ መከላከል ተጠሪ ኮማንደር ከበደ ኮኔራ አደጋው ጠዋት 3:00 ሰዓት አካባቢ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር መድረሱን አረጋግጠዋል።
በወቅቱ የአካባቢውን የተሽከርካሪ ፍሰት ሲቆጣጠር የነበረው ትራፊክ ፖሊስ አንድ የሚኒባስ አሽከርካሪን አስወርዶ በመነጋገር ላይ እያለ አቅጣጫውን የሳተ ' ቅጥቅጥ ' የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከዳራቸዉ ከነበረው ሲኖ ጋር እንዳጣበቃቸዉና ሁለቱም ወዲያዉ ህይወታቸዉ እንዳለፈ ገልጸዋል።
" በአካባቢዉ የነበረዉ ብቸኛ የትራፊክ ፖሊስ እና መረጃ አቀባያችን በመሰዋቱ አሁን ላይ ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልቻልንም " ያሉት ኮማንደር ወደቦታዉ ያቀኑት ባልደረቦቻቸው የሚያቀብሉት መረጃ በኋላ ላይ ለህብረተሰቡ እንደሚያጋሩን ተናግረዋል።
በአደጋዉ የሁለቱ ዜጎች ህይወት ከመጥፋቱ ባለፈ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

ፕሮፌሰሮቹ አባት እና ልጅ 👏
ፕሮፌሰር ባዬ ይማም (አባት) እና ፕሮፌሰር ቃለአብ ባዬ ይማም (ልጅ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሙያቸው እያገለገሉና ተተኪ ምሁራንን እያፈሩ የሚገኙ ፕሮፌሰሮች ናቸው።
ፕሮፌሰር ባዬ 44 ዓመታት ፤ ፕሮፌሰር ቃለዓብ ደግሞ 15 ዓመታት በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ያገለገሉና እያገለገሉ የሚገኙ ምሁራን ናቸው።
2ቱም የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን በሰሩ በ10ኛው ዓመት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አገኝተዋል።
ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከሰጣቸው ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው።
Credit - AAU

#BenishangulGumuz
• “ የውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ችግር ላይ ወድቀናል ” - ነዋሪዎች
• “ የመብራት ችግር ነው ” - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ
• “ የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው ” - የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማን ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ገለጹ።
“ የውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ችግር ላይ ወድቀናል። ውሃ ካለበት ቦታ በጀሪካ እስከ 30 ብር ለመግዛት ተገደናል ” ሲሉ አማረዋል።
በወንበራ፣ በአሶሳ ከተማና ሌሎችም ቦታዎች የውሃ መብራት ችግር እንዳለ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው በአንክሮ ጠይቀዋል።
ቲክባህ ኢትዮጵያም ምን ተፈጥሮ ነው አገልግሎቱ የተቋረጠው ? ሲል የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮን ጠይቋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አድማሱ ሞርካ “ የመብራት ችግር ነው። ያለ መብራት አይደለም የሚሰራው ውሃው። ቅሬታቸው ትክክል ነው ” ብለዋል።
“ መንዲ የሚባል አካባቢ ላይ ኤሌክትሪክ ተበላሽቶ ተስካክሎ ነበር። በድጋሚ ተበላሽቶ ነው። በዚህ ምክንያት የከተማው ውሃ የተቋረጠበት ሁኔታ አለ ” ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ አሶሳ ከተማ ላይ የኤሌክትሪክ ችግር ከመከሰቱ ቀድሞም የውሃ አቅርቦት ችግር እንደነበር ተመላክቷል፤ ችግሩን ለመቅረፍ ቢሮው ምን እየሰራ ነው ? ሲል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል።
ኃላፊው በምላሻቸው፣ “ ችግሩን ለመቅረፍ ያቀድነው ጉድጓዶችን መጨመር ነው። 4 ነበር ያቀድነው 3ቱ ተቆፍረው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል ” ብለዋል።
“ ሁለተኛ አማራጭ ደግሞ ታንከሮች ናቸው። ከዚህ በፊት ለ500 ሺህ ህዝብ ነው ታንከር የተሰራው። ይሄም በቂ ባለመሆኑ 3 ታንከር ለመጨመር አቅደን አሁን ዝግጁ ሆነዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
የመብራት ችግሩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ከበደ፣ “ አሶሳ አካባቢ ተቋርጦ ነው ያለው። ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠ መስመር አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ቡድን የነቀምት ቢሮ ነው። ከእነርሱ እየገዛን ነው ኤሌክትሪክ ለማህበረሰቡ የምንሸጠው። የተቋረጠው ኤሌክትሪክ እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው። ድጋፍ እያደረግንም ነው ” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦ " ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በኋላ እንዲሁም ሰኔ 8 እና 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋናነት በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች " የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና መሣሪያ በቤታችሁ እንዳለ ተጠቁመናል፤ የደበቃችሁትን መሣሪያ አውጡ " በሚል ምክንያት ሴቶችና የአእምሮ ሕመምተኞችን ጨምሮ ቢያንስ 50 ሲቪል ሰዎች በተናጠል እና በጅምላ ከፍርድ ውጪ መገደላቸውን፣…
#Gambella
ንፁሃንን " መረጃ ሰጥታችኋል " በሚል በአቃቂ ሁኔታ #እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፤ ግድያው ላይም ተሳትፈዋል ከተባሉ ተከሳሾች ውስጥ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ በተከሰሱበት ክስ #ነጻ መባላቸው ተሰምቷል።
ሌሎች የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የልዩ ኃይል አዛዦችን ጨምሮ 12 ተከሳሾች ግን የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
ብይኑን የሰጠው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ-መንግሥት እና በሕገ-መንግሥት ሥርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው።
ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት እነማን ናቸው ?
➡የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ፣
➡ የቀድሞው ም/ኮሚሽነር ቱት ኮር፣
➡ የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞ ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኮንግ ሬክ
➡ የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞው ምክትል አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡጀዲ ባሬ እና የተለያዩ የፀጥታ አባላትን ጨምሮ አጠቃላይ 15 ተከሳሾች ናቸው።
ተከሳሾቹን ላይ የቀረበው ክስ ምንድነው ?
ሰኔ 7/2014 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ መንግሥት በአሸባሪ ቡድንነት የፈረጀው " ሸኔ " እና የጋምቤላ ነጻ አውጪ ግንባር (ጋነግ) በጋራ ሆነው ቀበሌ 03 በፌደራል ፖሊስ ካንፕ እና በክልሉ ልዩ ኃይል እንዲሁም በሌሎች ፀጥታ አካላት ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍተው ነበር።
በኃላም ጥቃት አድራሾቹም በፀጥታ ኃይሎች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።
ከዚህ ክስተት በኋላ ግን ማንነታቸው የተለዩ 35 ሰዎች እና ማንነታቸው ያልተለዩ ሌሎች ንፁሃንን " #መረጃ_ሰጥታችኋል " በሚል በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ትዛዝ ሰጥተዋል ፤ በግድያው ላይ የተሳተፉም አሉ የሚል ነው።
የክስ መዝገቡ የተከሳሾች የተሳትፎ ደረጃቸውን በዝርዝር አስቀምጧል።
ፍርድ ቤት ምን ውሳኔ አሳለፈ ?
ከ15ኛው ተከሳሽ ውጭ ሌሎቹ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።
ግለሰቦቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን አሰምቷል። ማስረጃዎቹን አቅርቧል።
ፍርድ ቤት ፦
° የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ፣
° ቀድሞው ም/ኮሚሽነር ቱት ኮር
° የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞው ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኮንግ ሬክ
° የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞ ምክትል አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡጀዲ ባሬን ጨምሮ 13 ተሳሾች በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።
ዛሬ በዋለው ችሎት 12 ተከሳሾች የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በበቂ ሁኔታ መከላከል አለመቻላቸው ተጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከላቸው ተጠቅሶ ነጻ ተብለዋል።
ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉ ተከሳሾችንና የዐቃቤ ሕግን የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ከዚህ ቀደም የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ አባል ኮ/ል አቶሬ ጉር እና የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ አባል ረ/ሳጅን ቾድ ቤንግን በተመለከተ ፍ/ቤቱ በቀረበባቸው ክስ ላይ በቂ ማስረጃ አለመሰማቱን ተገልጾ በነጻ እንዲሰናበቱ ተደርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤፍቢሲ ነው ያገኘው።

#አቢሲንያ_ባንክ
የመጀመሪያው ዲጂታል ቪዛ ካርድ በኢትዮጵያ!
በባንክ ቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅ የሆነው አቢሲንያ ባንክ ዛሬም በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ዲጂታል ቪዛ ካርድ እንሆ ብልዋል።
ይህ ዲጂታል ቪዛ ካርድ ደንበኞች ስልካቸውን እንደ ATM ካርድ መገልገል የሚችሉበት ሲሆን የአፖሎ መተግበሪያን በመጠቀም ቪዛ ካርዳቸውን ወደ ዲጂታል ቪዛ ካርድ በመቀየር ገንዘብ ከATM ለማውጣትም ሆነ POS ማሽኖች ላይ ለመክፈል ስልካቸውን ጠጋ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#DigitalVisacard #Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia

#Ethiopia ይህ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስም በተለይ በ X መተግበሪያ ላይ እየተራጨ ያለው መግለጫ ሀሰተኛ እና የተቀነባበረ ነው። የሚኒስቴሩን የቀድሞ ሎጎ በመጠቀም እየተሰራጨ ያለው ይህ መረጃ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ፦ - በUN - በEU - BRICS (ኢትዮጵያ እራሷ አባል የሆነችበት) - በኢስላሚክ ሀገራት ከፍተኛ ጫና እንደሰረዘችው…
#Ethiopia #Somalia
" ልዑካኑ የቀጥታ የፊት ለፊት ንግግር / ውይይት አላደረጉም " - የሶማሊያው ፕሬዜዳንት
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት ትላንት አንካራ ውስጥ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።
በቱርክ ጋባዥነት በተደረገው ውይይት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞሊም የመሯቸው ልዑካን አንካራ ተገኝተው ነበር።
ከውይይቱ በኃሏ የሶስቱ ሀገራት የጋራ መግለጫ ወጥቷል።
መግለጫው ፥ ሚኒስትሮቹ ያላቸውን ልዩነቶች ለሁለቱም ተቀባይነት ባለው ማዕቀፍ ውስጥ ለመፍታት ያሉ ሁኔታዎችን እንደዳሰሱ ገልጿል።
ሚኒስትሮቹ በተናጥል በግልጽነት ፣ ወዳጅነት ባለው እና የወደፊቱን ያለመ ውይይት እንደነበራቸው ነው የተመላከተው።
ሁለቱ አገራት ችግሮቻቸውን ለመፍታትና ቀጣናው እንዲረጋጋ የጀመሩትን ውይይት ለመቀጠል ተስማምተዋል የተባለ ሲሆን ለሁለተኛ ዙር ውይይት በአንካራ ነሐሴ 27/ 2016 ዓ.ም እንደሚገናኙ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ከ6 ወራት በፊት የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች ወዲህ በይፋ ተገናኝተው ሲመጋገሩ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።
የጋራ መግለጫው ሁለቱ አገራት ልዩነታቸውን ለሁለቱም ተቀባይነት ባለው ማዕቀፍ ለመፍታት ያሉ ሁኔታዎችን እንደዳሰሰ ቢገልጽም እነዚህ ተቀባይነት አላቸው ስለተባሉ ጉዳዮች የተጠቀሰ ጉዳይ የለም።
በሌላ በኩል ፥ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ትላንት ውይይቱ ካበቃ በኃሏ ባሰሙት ንግግር ፦
- ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ከተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ወደኋላ የምትመለስበትን ምንም ምልክት አላሳየችም፤
- ከያዘችው መንገድ እየተመለሳች ስለመሆኑ ምንም ምልክት የለም ፤
- አንካራ ውስጥ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ልዑካን ቀጥተኛ ንግግር አላደረጉም ይልቅም ቱርክ በመሃል እንደ አስታራቂ ሆና እየሰራች ነበር ብለዋል።
ከሰሞኑን የኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና ከዛም የውጭ ጉዳይ መ/ቤትን ሎጎ በመጠቀም አንካራ ውስጥ በተደረገ ውይይት " ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት ሰርዛለች " የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።
#Ethiopia #Somalia #Turkey

#Ethiopia #Somalia " ልዑካኑ የቀጥታ የፊት ለፊት ንግግር / ውይይት አላደረጉም " - የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት ትላንት አንካራ ውስጥ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል። በቱርክ ጋባዥነት በተደረገው ውይይት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞሊም የመሯቸው ልዑካን…
ኢትዮጵያ ስለ አንካራው ውይይት ምን አለች ?
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንካራው ውይይት ጉዳይ የፕሬስ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው በቱርኪዬ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ጋባዥነት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ ትላንት ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ተገናኝተው መወያየታቸውን አረጋግጧል።
" በቱርኪዬ መንግስት አመቻቺነት የተካሄደው የሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ላሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ግልፅና ወዳጅነት የተሞላበት የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት ነበር " ብሏል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን አመልክቷል።
የቱርኪዬ መንግስት ውይይቱን ለማመቻቸት ስለተጫወተው ገንቢ ሚናም ምስጋና እንደቀረበ ገልጿል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች መልካም ጉርብትናን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ከግምት በማስገባት መፍትሄዎችን ለማመላከት ያለሙ ምክክሮችን ለመቀጠልም እንደተስማሙ አረጋግጧል።
ሁለቱም ሚኒስትሮች የቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምከከሩን አገራቸው ለማስተናገድ የወሰዱትን ተነሳሽነት በማድነቅ ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ለመቀጠል እንደተስማሙ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።