Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተማሪ ደራርቱ ገዳይ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ ላይ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ አስታውቋል። ረቡዕ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አቶ…
#Assosa

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ ዮሐንስ መርጋ በይግባኝ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ።

ደራርቱን በጩቤ ሶስት ቦታ ጀርባዋን በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ይታወሳል።

በውሳኔው ቅር የተሰኘው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቋል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከሳሹ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከአሶሳ  ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Via @tikvahuniversity
#Chapa

እራስዎን በዲጂታል ክፍያ ከሚፈፀሙ ማጭበርበሮች ይጠበቁ!

እነዚህን ቀላል የጥንቃቄ መንገዶች በመጠቀም እራሶን በዲጂታል ክፍያ ከሚፈፀሙ ማጭበርበሮች ይጠበቁ!
የላኪዉን አጠቃላይ መረጃ ያረጋግጡ
ፒኖትን አያጋሩ
ለተጀመሩ ግብይቶች ብቻ ምላሽ ይስጡ
🚨አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ ሪፖርት ያድርጉ
🔔ስለተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎች መረጃ ያግኙ

🚫አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ ወደ 📞8911 በመደወል ሪፖርት ያድርጉ

🌐 ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ፡ https://chapa.co/
🌐Visit our website Chapa.co or use our shortcode 📞8911 for more information

#chapa #chapapayments #Fraudawareness #Digitalpayment

Website
|Telegram | Instagram | Facebook |LinkedIn |X
#መምህራን

" ለልማት በሚል ከደመወዛችን እየተቆረጠብን ነው " - መምህራን

" እውነት ነው። ከህግ አግባብ ውጪ የመምህራን ደመወዝ እየተቆረጠ ነው " - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር

የደመወዝ በወቅቱ አመከፈል፣ የጥቅማጥቅም ክፍያ አለማግኘት ችግር ባልተቀረፈበት ሁኔታ፣ ያለፈቃዳቸው ከደመወዝ ለልማት በሚል እየተቆረጠባቸው መሆኑን መምህራን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረሩ።

መምህራኑ በሰጡት ቃል፣ " ለልማት በሚል እስከ 50 በመቶ ከደመወዛችን እየተቆረጠብን ነው። የወር አስቤዛን በቅጡ ከማይሸፍን ደመወዝ ላይ እየተቆረጠ እንዴት ቤተሰብ እናስተዳድር ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

ይህ የመንግስት ድርጊት ሰንበትበት እንዳለ ገልጸው፣ ጭራሽ ቤተሰብ ማስተዳደር አቅቷቸው በብድር እየማቀቁ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

መምህራኑ ያቀረቡት ቅሬታ እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበለት የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር፣ " እውነት ነው ችንሩን በደንብ ነው የምናውቀው "  ብሏል።

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ " በየክልሉ የተለያየ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ። ያለመምህራን ፈቃድ የደመወዝ  ቆረጣም በጣም #ትክክል ያልሆነ፣ #ጉልበተኝነት የበዛበት፣ #ሰሚ ያጣ ነው " ብለዋል።

ታዲያ ለቅሬታው ማኀበሩ ምን እየሰራ ነው ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ትክክል አይደለም ብለን እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድርሰናል። ባለፈው ነሐሴ ወር በነበረን ውይይት " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አሁንም በተለይ ዳውሮ ዞን የሚገኙ መምህራን እንደሚያለቅሱ፣ ማኀበሩም ለትምህርት ሚኒስቴር እንዳሳወቀ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ያለፈቃዳቸው ደመወዝ እንዳይቆረጥ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ደብዳቤ እንደጻፈ፣ ክልሉም ደመወዛቸው እንዳይቆረጥ ለሚመለከተው አካል እንዳሳወቀ አስረድተዋል።

" ዞኑ ላይ 'ለማዕከል ግንባታ' በሚል ለዛ ነው ደመወዛቸው እየተቆረጠ ያለው። መምህራኑም እዚህ ድረስ መጡ። እኛም ለእንባ ጠባቂ ተቋም ደብዳቤ ጻፍን። የተለያዩ አካላትን ለመድረስ ጥረት አደረጉ። ግን እንባ ጠባቂም ምን ያህል ኃላፊነቱን እንደተወጣ አላውቅም " ነው ያሉት።

" በእኛ በኩል ያላረግነው ነገር የለም " ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ " ግን አሁን ህግ የሌለ በሚስል ሁኔታ የመምህራን ደመወዝ እየተቆረጠ ነው " ብለዋል።

መምህራኑ ደመወዛቸውን ቀድመው ለተለያዩ ፕሮግራሞች ከፋፍለው የሚጠቀሙበት ብቸኛ ገቢያቸው እንደሆነ ገልጸው፣ " መካከል ላይ ደመወዝ ሲቆረጥ ምስቅልቅል ይወጣል " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህንን የማያይ ምን አይነት የዞን አመራር እንዳለ አይገባኝም በበኩሌ። እጅግ በጣም ጫፍ የወጣ ስልጣን መጠቀም እንደሆነ ነው የምረዳው። መምህራን እየተሰቃዩ ነው የሚያዳምጣቸው አጥተዋል " ሲሉ አክለዋል።

ምን ያህል መምህራን ናቸው ደመወዝ የተቆረጠባቸው ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ሽመልስ፣ " ለምሳሌ ዳውሮ ላይ የዞኑ መምህራን በሙሉ ተቆርጦባቸዋል። ኦሮሚያ ላይ የ230 ሺህ መምህር ይቆረጣል ደመወዙ " ነው ያሉት።

የሚቆረጠው መጠን በሁሉም ቦታ እንደየሁኔታው እንደሚለያይ አስረድተው፣ የክልል መንግስታት በማናለብኝነት ደመወዝ መቁረጥ አግባብነት እንደሌለው ቆም ብለው እንዲያስቡ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመምህራኑን ቅሬታ በተመለከተ ምን ሀሳብ እንዳለው በቀጣይ የመረጃ የምናደርሳችሀ ይሆናል።

#TikvahErhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ነገ ለስራ ይሁን ዘመድ ጥየቃ ወይም ደግሞ ለተለያየ ፕሮግራም ከቤት የምትወጡ ካላችሁ የሚዘጉ መንገዶች ይኖራሉ።

መንገዶች የሚዘጉት  80ኛውን የመቻል ስፖርት ቡድን ምስረታን ምክንያት በማድረግ በሚካሄድ የጎዳና ላይ ሩጫ ነው።

ሩጫው 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ነው።

በዚህም ፦

- ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ

- ከካዛንቺስ ወደ ባምቢስ

- ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ

- ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት

- ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ

- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ አንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ከነገ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ያስመርቃሉ፡፡

🎓 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
🎓 አክሱም ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
🎓 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
🎓 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
🎓 ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
🎓 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25-26/2016 ዓ.ም
🎓 ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
🎓 ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
🎓 ሠመራ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
🎓 ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26 እና 27/2016 ዓ.ም
🎓 ቦረና ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
🎓 አምቦ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ወራቤ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ዲላ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
🎓 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
🎓 ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
🎓 ደምቢ ዶሎዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
🎓 መቱ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 29/2016 ዓ.ም

Via @tikvahuniversity
#Chapa

የማያቁት ወይም በእርሶ ያልተነሳ የክፍያ መጠየቂያ (USSD) ሲላክልዎ የይለፍ ቃሎትን በፍጹም አያስገቡ።

🚫አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ ወደ 📞8911 በመደወል ሪፖርት ያድርጉ

🌐 ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ፡ https://chapa.co/ ወይንም ዛሬውኑ በ 8911 ይደውሉልን ።

#chapa #chapapayments #Fraudawareness #Digitalpayment

Website |Telegram | Instagram | Facebook |LinkedIn |X
#Amhara

ከሰሞኑን በአማራ ክልል፣ በባህርዳር ከተማ የተለያዩ የመንግሥት አካላት ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ከተካሄደ የሰላም ኮንፈረንስ በኃሏ ተቋቁሟል የተባለው ' አመቻች የሰላም ምክር ቤት ' በአማራ ክልል እየተደረገ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት ነው ብሏል።

ምክር ቤቱ በዚህ ጦርነት ፥ " ወንድም ከወንድሙ፣ ልጅም ከአባቱ ጋር ነው እየተገዳደለ ያለው " ሲል ገልጿል።

ለፌዴራል መንግሥት / ለአማራ ክልላዊ መንግሥት እና ለፋኖ ኃይሎች ሲል በስም ጠርቶ ባቀረበው የሰላም ጥሪ " የወገናችሁን ስቃይ ተረድታችሁ ምንም መሸናነፍ በማትችሉት ጦርነት ከመቆየት ሁለታችሁም ማሸነፍ ወደምትችሉት ንግግር እና ድርድር እንድትመጡ እንጠይቃለን " ብሏል።

ም/ ቤቱ መንግሥት እና የፋኖ ኃይሎች ወደ ሰላም መድረክ እንዲመጡ ለማመቻቸት እንደሚሰራ አመልክቷል።

" በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ንጹሃን ይገደላሉ፣ በጠራራ ጸሃይ ያለ ከልካይ ይዘረፋሉ  " ያለው ምክር ቤቱ ከ12 እስከ 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን አመልክቷል።

መንግሥት ጦርነቱን በድርድር ለመቋጨት ፍቃደኛ እንደሆነ ገልጾ " ብዙ መሪ እና አደረጃጀት ያላቸው የፋኖ ታጣቂዎች ለመደራደር ወደ አንድ መምጣት አለባቸው በማለቱ ይህ የሰላምና ድርድር አመቻች ምክር ቤት መቋቋሙ ተነግሯል።

ምክር ቤቱ 15 አባላት ያሉት ነው።

በሌላ በኩል ፥ ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በክልሉ መገደላቸው ተሰምቷል።

በሰሜን ጎንደር ዞን ፤ በዳባት ወረዳ፣ በመንግስት የጸጥታ አካላት እና ፋኖ ኃይሎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የፓሊስ አባላት መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ሁነቱን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ ነዋሪ ፤ " ከተማው ውስጥ አሁንም ሀዘን/ልቅሶ አለ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሀዘኑ የተፈጠረው በአካባቢው ላይ ከ ‘ ፋኖ ’ ጋር በነበረ ውጊያ በርካታ የአካባቢው የጸጥታ አባላት ስለተገደሉ መሆኑን አረጋግጫለሁ " ብለዋል።

የሟቾች ቁጥር ምን ያህል ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ " የሟቾች ቁጥር ከ115 በላይ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሟቾቹን በተመለከተም አድማ ብተና ሚሊሻና ፖሊስ እንደሆኑ ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ሌሎች ነዋሪዎች የሟቾች ቁጥር እስከ 130 እንደሚደርስ ንጹሐን እንደቆሰሉ ገልጸው ሰሞኑን ከተማዋ ከባድ ሀዘን እንዳስተናገደች ተናግረዋል።

ስለግድያው ምላሽ የጠየቅነው የዳባት ወረዳ ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ጉዳዩን በጽሞና ከሰማ በኋላ ማብራሪያ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም።

በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንትም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ባአዊ ዞን የቲሊሊ ወረዳ ነዋሪዎች ደግሞ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች 3 ሰዎችን ከቲሊሊ ሆቴል አውጥተው ገድለዋል ሲሉ ከሰዋል።

ሌሎች 2 ሰዎችም ተገድለዋል። በድምሩ 5 ንጹሐን በቲሊሊ ወረዳ መገደላቸውን ተናግተዋል።

በቦታው የተኩስ ልውውጥ ተደርጎ ነበር እንዴ ? በሚል ለነዋሪዎቹ ለቀረበው ጥያቄ ምንም ተኩስ እንዳልነበር፣ ግማሾቹን መንገድ ላይ በሚጓዙበት፣ ሌሎቹን ደግሞ ከሆቴል አስወጥተው እንደገሏቸው አስረድተዋል።

የመንግስት አካላት ስለሁኔታው እንዲያብራሩልን ብንጠይቅም ፍቃደኛ አልሆኑም።

ከዚህ ባለፈም ፥ በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ  " ሾላ  ሜዳ " በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሰኔ 19 በመንግሥት ኃይሎች ደርሷል በተባለ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና 4 የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ አማርኛው ዘግቧል።

በጥቃቱት ከአያቶቹ ጋር የሚኖር የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሉን ፥ አንድ የአይን እማኝ ደግሞ አንድ ሻይ ቤት 11 ሰዎች መገደላቸውን በ20ዎቹ እድሜ የሚገኝ ወንድማቸው ተገድሎ ሜዳ ላይ እንዳገኙት ተናግረዋል።

ሌላ የአይን እማኝ የ11ዱ ሟቾችን ስም ዝርዝር መሰብሰብ እንደቻሉ ሰኔ 20 ቀን/2016 ዓ/ም 4 ተጨማሪ አስከሬን እንደተገኘ ገልጸዋል።

የጸጥታ ኃይሎቹ በአካባቢው ለለቅሶ መጥተዋል የተባሉ 3 የፋኖ ታጣቂዎችን ተከትለው ሳይመጡ እንዳልቀረና ስለ ታጣቂዎቹ መረጃ በመፈለግ ግድያውን እንደተፈጸመ አክለዋል።

በተመሳሳይ በሰሜን ጎጃም ዞን ፤ በይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት ከተማ ሰኞ ሰኔ 17 ቀን 11 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፥ በእለቱ የፋኖ ታጣቂዎች እና የመንግሥት ኃይሎች ለሰዓታት የዘለቀ ከባድ ውጊያ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

ይህን ተከትሎ ጥቃቱ መፈጸሙን አንድ ሴትና 10 ወንዶች እንደተገደሉ ገልጸዋል።

ግድያው የ ' ፋኖ ታጣቂዎች ' ከተማይቱን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ 02 ቀበሌ እርሻ ሰብል በተባለ ሰፈር መንገድ ላይ እና ቤት ለቤት መፈጸሙን ገልጸዋል።

" ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ " በሚል ግድያው ተፈጽሟል ሲሉ ከሰዋል።

ፋኖ በከተማው ተቆጣጥሮ ውሎ በወጣበት ሰዓት የመንግስት ጸጥታ ኃይል ተመቶ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በተፈጠረው ክስተት ከተማዋ በከባድ ሀዘን ውስጥ መውደቋን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ፤ ያለው ጦርነት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን በተለያየ ጊዜ በተለያየ ቦታ እየተፈጠረ ባለው ግጭት የሰዎች ህይወት እየጠፋ ነው።

ከሰሞኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ህዝቡ በሰላም እጦት የከፋ ችግር ላይ ወድቆ እንደሚገኝ ተናግረው ፥ መገዳደሉና ፣ በጠላትነት መፈላለጉ እንዲያበቃ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ አገኘሁ ተሻገር፥ " በቃ! እስኪበቃን ተገዳድለናል ፣ እስኪበቃን ተዋጋን ስለዚህ አሁን ላይ ይብቃን ፣ መፍትሔው ንግግር ነው ፣ መነጋገር ነው ፣ መከባበር ነው " ሲሉ ነበር የተናገሩት።

#Ethiopia
#AmharaRegion

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በራሳቸው የዘጉ ተቋማት ዝርዝር.pdf
" ትምህርት ቤታችን አልተዘጋም " - ፕራይም ብሪጅ

ፕራይም ብሪጅ ትምህርት ቤት እንዳልተዘጋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳወቀ።

ከሰሞኑን የአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በከተማይቱ በራሳቸው የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይፋ አድርጎ ነበር።

ከዚህ ዝርዝር ውስጥ አንዱ ፕራም ብሪጅ ትምህርት ቤር ሲሆን ትምህርት ቤቱ ግን እንዳልተዘጋ ገልጿል።

ባለስልጣን መ/ቤቱም በጻፈው ደብዳቤ ኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ስር ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የእውቅና ፈቃድ እድሳት ሰርተፊኬት ወስዶ በማስተማር ሃደት ላይ እንደነበር ገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ እና አዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ መልሶ ማደራጀት ቀድሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ የነበረው በአዲሱ አደረጃጀት በሸገር ከተማ መስተዳድር በፉሪ ክ/ከተማ በሙዳ ፉሪ ወረዳ ስር በመካለሉ በባለስልጣን መ/ቤቱ የነበረውን የእውቅና ፈቃድ ሰርተፊኬት መመለሱንም አመልክቷል።

ቀጥሎም በአዲሱ አደረጃጀት በሽገር ከተማ በፉሪ ክ/ከተማ በሙዳ ፊሪ ወረዳ ስር ፈቃድ ወስዶ በማስተማር ላይ መቀጠሉን አሳውቋል።

በት/ቤቱ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች እና ማህበረሰቡ ይህን እንዲረዱ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#Tigray
 
ከቀናት በፊት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳባጉና ከተማ በጠራራ ፀሃይ በገበያ ቦታ በቢላዋ ዘግናኝ ግድያ ተፈጽሟል።

የግድያው መነሻ ቂም በቀል እንደሆነ ተነግሯል።

ግድያው መቼ ? እንዴት ? ለምን ተፈፀመ ?

ቀኑ ሰኔ 18/2016 ዓ.ም ሲሆን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ሰውና መኪና በብዛት በሚተላለፍበት በአስፓልት ላይ ነው ግድያው የተፈፀመው። 

የጭካኔ ግድያ የፈፀመው መምህር በየነ ገ/ማርያም የተባለ ግለሰብ ሲሆን ሟች ደግሞ ኣግደው ተስፋዓይኑ ይበላል።

ሟችና ገዳይ የስጋ ዘመዳሞች ሲሆኑ ሟች አግደው በ2013 ዓ.ም ታጣቂ ሚልሻ እያለ ከገዳይ መምህር በየነ ገ/ማርያም ታላቅ ወንድም ሆነው አልኮል ሲጠጡ እምሽተው በመካከላቸው በተፈጠረው ጊዚያዊ ጭቅጭቅ በመናደድ አግደው የመምህር በየነ ታላቅ ወንድም ደጋግሞ ተኩሶ በጭካኔ እንደገደለና በዚህም ቤተሰብ ክፉኛ ሀዘን ላይ ወድቆ ነበር።

በወንድሙ ላይ በተፈፀመው ግድያ ቂም የቋጠረው መምህር በየነ ገ/ማርያም በተራው ሰኔ 18/2016 ዓ.ም በቀን በጠራራ ፀሃይ ሰውና መኪና በብዛት በሚተላለፍበት አደባባይ በሰራው ወንጀል ታስሮ ከእስር ቤት የወጣውን አግደውን በቢላዋ ደጋግሞ በመውጋት እንደገደለው ተሰምቷል።

ለመሆኑ ግለሰቡ እንዴት ከእስር ወጣ ?

አሁን ግድያ የተፈፀመበት ግለሰብ ግድያ የፈፀመው ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ነው።

ያኔ በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር። ቢሆንም ጦርነት ሲጀመር ፍርዱ ሳይጨርስ ከሌሎች እስረኞች ጋር በጋራ ከእስር ቤት ተለቀቀ።

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ ተመልሶ ወደ እስር ቤት አልተመለሰም። በዚሁ ሁኔታ እያለ ነው በቂም በቀል የተገደለው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በ5ቱ ኮሪደር ልማት ስራ 16 ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ  ፦ ° መንገዶችን የማስፋት ፣ ° የመንገድ ዳሮችን የማሳመር ፣ ° የእግረኛና የሳይክል ብስክሌት መሄጃዎችን መስራት ° የቴሌ፣ የመብራት ኬብሎችን ወደ መሬት መቅበር ° የውሃ ፍሳሽ መሄጃዎችን መስራት ° ፕላዛዎችን መስራት የሚያጠቃልለው የኮሪደር ልማት ስራ በ5 ኮሪደሮች በመሰራት ላይ…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ፤ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ የክረምት ወቅቱ ሳይጠናከር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ከተማው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን ባለው የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር እንዲሁም ከሜክሲኮ እስከ ሳር ቤት ያለው ተጠናቆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል።

ከዚህ ቀደም ፦
- ከ4 ኪሎ - ፒያሳና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ፣
- ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ መገናኛ ፣
- ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣
- ከ4 ኪሎ መስቀል አደባባይ ቦሌ ድልድይ ፣
- ከቦሌ ድልድይ በመገናኛ እስከ አፍሪካ ኮንፌሽን አጠቃላይ 5 የኮሪደር ስራ እየተሰራ እንደሆነ መነገሩ ይታወሳል።

በከተማው እየተሰራ ያለው የኮሪደር ስራ ፥

ብዙሃን የሚጠቀሙበትን የእግረኞች መንገድ ማስፋት ምቹ ማድረግ፣
የተሽከርካሪ መንገዶችን ማስፋት፣ መታደስ ያለባቸውን የአስፋልት መንገዶች ማደስ፣
አላስፈላጊ ናቸው የተባሉ የመንገድ ማካፈያዎችን አንስቶ መንገድ ማስፋት፣
የመኪና ማቆሚያዎችን የመስራት፣
የመንገዶችን ዳር ማሳመር፣
የቴሌ፣ የመብራት ኬብሎችን ወደ መሬት መቅበር
ዘመናዊ የውሃ ፍሳሽ መሄጃዎችን መስራት
የሳይክል መንገድ መስራት
ፕላዛዎችን መስራት ሌሎች ተያያዥ ስራዎች የሚያጠቃልል ነው።

አብሮም ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃ ቤቶች እየተሰሩ ነው።

ሁሉንም የኮሪደር ስራዎች የክረምቱ ወቅት ሳይጠናከር ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማ አስተዳደሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

እንደ ከተማ አስተዳደሩ መረጃ ስራዎች በሳምንት 7 ቀን ለ24 ሰዓት (ማታ እና ቀን) እየተሰሩ ይገኛሉ።

ከዚህ ቀደም በአጠቃላይ ከ16 ሺ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው መገለጹ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፥ ህንጻዎችን የማደስ ፣ ወደ ንግድ / ቢዝነስ ማዕከልነት የመቀየር እና በስታንዳርድ የተቀመጠውን መስፈርት / የህንጻዎች ቀለም ጭምር) እንዲያሟሉ እየተደረገ ነው ተብሏል።

ሌላው ደግሞ የኮሪደር ልማት በሚከናወንባቸው አካባቢዎች እና በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚገኙ የንግድና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከተለመደው የሥራ ሠዓት በተጨማሪ ቢያንስ እስከ ምሽቱ ሶስት ሰአት ድረስ ክፍት በማድረግ የንግድ እና የአገልግሎት ስራዎች እንዲካሄዱ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ወስኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሃጫሉን ግድያ የፈጸሙትን ታውቃለችሁ አውጡልን " - ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ ትላንት በ " አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን " አዘጋጅነት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የተሰዋበት ዝክር እና የሃጫሉ አዋርድ ተካሂዷል። በዚሁ ዝግጅት ላይ የአርቲስት ሃጫሉ ባለቤትና የሃጫሉ ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ንግግር ያደረገች ሲሆን በንግግሯም ከባለቤቷ ግድያ ጋር በተያያዘ ዛሬም ድረስ ፍትሕ እንዳልተገኘ…
" ፍትህ እንዲረጋገጥ እሻለሁ " - ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ

ትላንት አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የተገደለበት 4ኛው የሙት ዓመት መታሰቢያ እና 3ኛው ዓመት " የሃጫሉ አዋርድ " የሽልማት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በኦሮሞ አርት ውስጥ በዓመቱ ጉልህ አሻራን ያኖሩ እና በተለያዩ ጊዜያት በአርቱ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦች እውቅና አግኝተዋል፡፡

በዚሁ መድረክ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት እና የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የበላይ ኃላፊ ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ ንግግር አድርገው ነበር።

ወ/ሮ ፋንቱ ፤ " ፍትህ እንዲረጋገጥ እሻለሁ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የሃጫሉ ባለቤት አሁንም ድረስ ትልቁ መሻታቸው የግድያው እውነታ ከምንጩ እንዲመረመር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

" አርቲስቱ የተገደለው ለፖለቲካ እቅድ ማስፈጸሚያ " መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

" ህዝብን ተስፋ እናስቆርጣለን ያሉ በራሳቸው ተስፋ ቆርጠው ሃጫሉን በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ አኖሩት " በማለት ገልጸዋል።

" እውነት ተደብቋል " ያሉት ወ/ሮ ፋንቱ የአርቲስቱ ፍትህ እስኪረጋገጥ ድረስ መናገር እና መጠየቅ እንደማያቆሙም አስረድተዋል፡፡

" የምታውቁት እያላችሁ ምንም እንደማያውቁ አትሁኑ " ያሉት ወ/ሮ ፋንቱ መንግስትም ሆነ ከመንግስት ውጪ ያሉ ያሏቸው የአርቲስቱን እውነተኛ የአገዳደል ሚስጥር የሚያውቁ " እውነታው ወጥቶ " ፍትህ እንዲረጋገጥ ስሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" ገዳይና አስገዳዩን ለህግ አቅርቡልን " በማለትም ማንም በዚህ ንጽህናውን እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል፡፡

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 22 ቀን 2012  ዓ/ም አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚታወቅ አከባቢ ተገድሎ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

ግድያውን ተከትሎም በማግስቱ በመላው ኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ከፍተኛ አመጽ የበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋቱና እጅግ የበዛ ንብረትም መውደም አይዘነጋም።

የአርቲስቱን ግድያ ተከትሎ ግድያው ላይ ተሳትፈዋል በተባሉት ሶስት ሰዎች ላይም አቃቤህግ ክስ መስርቶ በአንደኛው ተከሳሽ ላይ የእድሜ ልክ እስራት እና በሁለተኛው ላይ ደግሞ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ማበየኑ ይታወቃል፡፡

ነገር ግን የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ቤሰተቦች በዚህ የህግ ሂደቱ ብዙ እምነት እንደሌላቸውና " እውነተኛው ፍትህ " እንዲረጋገጥ እንደሚፈልጉ ደጋግመው ያነሳሉ፡፡

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ (DW) ነው።

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

ክረምቱን ልጆችዎ በዲኤስቲቪ እየተዝናኑ ይማራሉ፣ ዓለምን እየጎበኙ ይመራመራሉ! 👩🏽‍🚀

በየትኛውም ዕድሜ ላሉ ልጆችዎ እንደ ኒክ ጁኒየር፥ ማይንድሴት፥ ኒኮሎዲየን እና ጂምጃም ያሉ ቻናሎችን በወር ከ350 ብር ጀምሮ በዲኤስቲቪ።

ክረምቱን ልጆችዎ በዲኤስቲቪ እየተዝናኑ ይማሩ!

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/3yBcOHc

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው
2024/11/06 01:46:22
Back to Top
HTML Embed Code: