Telegram Web Link
#ኢትዮጵያ

የ2016 የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

ጥዋት የኢድ ሶላት ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች ተከናውኗል።

ከኢድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን በዓሉን እያከበረ ነው።

#ኢድአልአድሃ #አረፋ

መልካም በዓል

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
#Hajj1445

ዘንድሮ #ምን_ያህል የእስልምና እምነት ተከታዮች #ሐጅ አደረጉ ?

እንደ ሀራሜይን መረጃ ከሆነ ዘንድሮ በ1445 (AH) 1,833,164 (ከ1.8 ሚሊዮን በላይ) የእስልምና እምነት ተከታዮች ከመላው የዓለም ክፍል የሐጅ ጉዞ አድርገዋል።

ከአጠቃላዩ የሐጅ መንፈሳዊ ጉዞ ተጓዦች 221,854 የእስልምና እምነት ተከታዮች ከዛው ከሳዑዲ አረቢያ ሲሆኑ 1,611,310 የሚሆኑት ዓለም አቀፍ የሐጅ ተጓዦች ናቸው።

በተጨማሪም ከአጠቃላይ የሐጅ ተሳታፊ 52 በመቶ ወንዶች ሲሆኑ 48% ደግሞ ሴቶች ናቸው።

#ሐጅ 🤲 ከእስልምና #መሰረቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን አቅሙ የፈቀደት ሙስሊም ወንድም ሆነ ሴት በዕድሜ ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ሐጅ የማድረግ ግዴታ አለበት።

#Islam ❤️

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
የፌደራል_መንግስት_ሠራተኞች_ረቂቅ_አዋጅ_አጭር_ማብራሪያ_1.pdf
" አንዳንዴ ሠራተኞች ቢሮ መጥተው ያለቅሱብናል ፤ ' ምሳ የምንበላበት የለም ' በማለት በግልጽ ይናገራሉ !! "

በ2010 ዓ/ም ተሻሽሎ ወደ ሥራ ገበቶ የነበረው ባለ 106 አንቀጽ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ከ6 ዓመታት አገልግሎት በኋላ፣ በ160 አንቀጾች ተዋቅሮ በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት እየተደረገበት ነው።

ምን አስተያየት ተሰጠ ?

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ አቶ አብርሃም ደግፌ ፦

" በከተማ አስተዳደሩ 70 ያህል የመንግሥት ተቋማት ላይ ክትትል እናገደርጋለን ፤ የሠራተኛው ሕይወት እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ይገኛል።

በከተማ አስተዳድሩ አንድ ከፍተኛ የሚባል ባለሙያ ያልተጣራ ደመወዙ 9,056 ብር ነው። ከዚህ ግብር ተከፍሎበት በእጁ የሚደርሰውን ገንዘብ አስልታችሁ ድረሱበት።

በዚህ ደመወዝ የቤት ኪራይ የከተማዋ ጫፍ እንኳ ቢኬድ 10,000 ብር ደርሷል።ነገር ግን ይህ ከፍተኛ ባለሙያ ሙሉ ደመወዙን ለቤት ኪራይ ላድርግ ቢል ገንዘቡ አይበቃውም።

በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ አንድ ሠራተኛ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይቻላል ወይ?  ተፈጥሯዊ ሁኔታውስ በራሱ ይፈቅድለታል ወይ ?

ይህ ችግር ደመወዝ በመጨመርም ይፈታል ብዬ አላስብም።

በሌሎች አማራጮች ሰራተኛ እንዲጠቀም ቢደረግ ችግሩ ሊቀል ይችላል እንጂ 2,000 ብር ቢጨመር እንኳን ሕይወቱ ላይ ለውጥ አያመጣም።

በዚህም የተነሳ ሠራተኞች አንዳንዴ ቢሮ መጥተው ያለቅሱብናል፣ ምሳ  የምንበላበት የለም በማለት በግልጽ ይናገራሉ።

ገንዘብ አልበቃቸው ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች ደግሞ በምሳ ሰዓት ወደ ቤተ እምነቶች ሄደው ያሳልፋሉ።

የመንግሥት ሠራተኛው ታማኝ ግብር ከፋይ ቢሆንም፣ ነገር ግን የሠራተኛውን ሕይወት የሚቀይር ነገር እስካልመጣ ድረስ በሚፈለገው ደረጃ አገልግሎት ሊሰጥ አይችልም። "

Via https://telegra.ph/Ethiopian-Reporter-06-16

@tikvahethiopia
#Sudan #Ethiopia

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ በቀን የምትወስደው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ200 ሜጋዋት ወደ 50 ሜጋዋት መውረዱን ገለጸ።

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትወስደው የኤሌክትሩክ ኃይል በእጅጉ መቀነሱን ተነግሯል፡፡

ሱዳን #ጦርነት_ውስጥ_ከመግባቷ_በፊት ከኢትዮጵያ የምትገዛው የኤሌክትሪክ ኃይል በቀን እስከ 200 ሜጋዋት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን 50 ሜጋዋት እና ከዚያ በታች ሆኗል ሲል አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡

ለሱዳን የሚቀርበው ኃይል ከመውረዱም በላይ " ለተጠቀሙት የኤሌክትሪክ ኃይል እየከፈሉ አይደለም " ብሏል።

በታሰረው ውል መሰረት #ለተጠቀሙበት_ካልከፈሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚቻል ቢሆንም ግንኙነቱ እንዳይሻክር ኢትዮጵያ ይህንን አላደረገችም ሲል ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ከጅቡቲ እና ከኬኒያ የኃይል ትስስር ያላት ሲሆን በቀን እስከ ሁለት ቴራ ዋት ሀወር ለሶስቱ ሀገራት ኃይል እንምድታቀርብ ተነግሯል።

ጅቡቲ የምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል አብዛኛው ከኢትዮጵያ የሚሄድ ሲሆን ኬኒያም ከምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል 10 ከመቶ ከኢትዮጵያ የሚሄድ ነው ተብሏል፡፡

#ShegerFM

#Sudan #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ስልክአምባ " 12 ሰዎች ናቸው የተገደሉት፤ .. ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶችም እየተነዱ ተወስደዋል " - ነዋሪዎች " 11 ሰዎች ስለመገደላቸው መረጃ ደርሶናል መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው " - ኢሰመኮ ️በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ስልክ አምባ ከተማ ባለፈው ሠኞ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።…
#ኦሮሚያ #ኖኖ #ስልክአምባ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ሰርገኞችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት እና ነዋሪዎች ገለጹ።

የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ቅዳሜ ሰኔ 8 ንጋት ላይ ነው የተፈጸመው።

ጥቃት አድራሾቹ " ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች  ናቸው " ብለዋል።

ኃላፊው " ሰርገኞቹ ቤት ውስጥ እያሉ በር ዘግተውባቸው ቦምብ ወረወሩባቸው። ቤት ውስጥ ከነበሩት አንድም በሕይወት የወጣ የለም። እዚያው ተቃጥለው አልቀዋል "  ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ታጣቂዎቹ ሰርግ ቤቱ ላይ ከአንድ በላይ ቦምብ ወርውረው ሙሽሮቹን እና አብረዋቸው የነበሩ ሰዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል።

የኮማንድ ፖስት ኃላፊን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ቃል ፥ በሰርግ ቤት ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂዎቹ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ የሟቾች ቁጥር ከ30 እስከ 50 ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

በጥቃቱ ሙሽሪት እና ሙሽራውን ጨምሮ የሰርጉ ታዳሚዎች የሆኑ ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪው ተናግረዋል።

የወረዳው የኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ፥ " በእሳት ተቃጥለው የሞቱ ሰዎችን ቁጥር መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር መለየት አልተቻለም " ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ በዚህ ወረዳ በ5 ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ፤ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ከብቶችም እየተነዱ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢሰመኮም መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራ እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም።

ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደነበሩ ፤ ጥቃት ፈጻሚዎችም የ " ሸኔ (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) ታጣቂዎች " እንደሆኑ ነዋሪዎች መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም በ2017 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1332 የማስተማር ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል።

43 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው መሰረዙን አመልክቷል።

150 ትምህርት ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

41 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና ስታንዳርዱን ባለማሟላታቸው ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑ ተመላክቷል።

የትምህርት ቤቶቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
2024/09/27 04:25:36
Back to Top
HTML Embed Code: