Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተከፍቷል

በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ጋር በተያያዘ  ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ክፍት ተደርገዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከብሯል።

ከላይ በፎቶ የተያያዘው በላዛሪስት ገዳም  ፂዮን ማርያም ቤተክርስቲያን የነበረውን የደመራ በዓል አከባበር የሚያሳይ ነው።

#የኢትዮጵያካቶሊካዊትቤተክርስቲያን

@tikvahethiopia
#Tigray

° " እርባና የሌለው ልዩነታችንን ትተን ለህዝባችን ሰላምና እፎይታ እንስጠው " - አቶ ጌታቸው ረዳ
 
° " ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግላችን ማጠናከር ይገባል " - የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ በትግራይ ፣ መቐለ ጮምዓ ተራራ ሲከበር የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ሌ/ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ተገኝተው ነበር።

አቶ ጌታቸውም ንግግር አድርገዋል።

" በፓለቲካዊ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ትርጉም የሌለው ልዩነት ወደ ጎን በመተው የህዝቡ ሰላም ማስጠበቅ ከስጋት ተላቅቆ ኦፎይታ እንዲያገኝ መስራት ይገባል " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው " እንደ አመራር እርባና የሌለው ልዩነታችንን ወደ ጎን በማለት ለህዝባችን ሰላምና እፎይታን እንስጠው ፤ አንድነታችንን አጠናክረን ብቁ አመራር በመስጠት ወጣቶቻችንን ከህገወጥ ስደት እንታደግ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" ከቡድናዊነት በመውጣት የጋራ ፍላጎት በማስቀደም ለህዝብና አገር መስራት አለብን " ብለዋል።

" መስቀላችን አንድነታችን የምናጠናክርበት ፣ ሰላማችን ጠብቀን በመከራ ላይ የሚገኘው ተፈናቃይ ህዝባችን ወደ ቄየው የምንመልስበት ፤ የትግራይ ግዛት ሙሉ በሙሉ ተረጋግጦ ወደ እድገት የምናማትርበት ጊዜ ይሁንልን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ የመስቀል በዓልና ደመራን ምክንያት በማድረግ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት ያስተላለፉት የህወሓት ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለመላ ህዝቡ ፣ ለዳይስፖራው እና ለጸጥታ ኃይሎች እንኳን አደረሳችሁ ካሉ በኃላ" " የተጠናከረ ፓለቲካዊ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ ይገባል " በማለት አሳስበዋል።

በዓሉ መስከረም 17/2017 ዓ.ም በዓዲግራት መከበር የሚቀጥል ሲሆን የሃይማኖት መሪዎችና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መምእምናን በተገኙበት እንደሚከበር ዓዲግራት የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል። 

ፎቶ/ቪድዮ፦ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በመቐለ ጮምዓ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ። #ኦርቶዶክስተዋሕዶ @tikvahethiopia
#Ethiopia

" በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል " - የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በመላው ሀገሪቱ በተለይም #በአዲስ_አበባ መስቀል አደባባይ የተከበረው የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ህዝብ ፣ ለሀይማኖት አባቶች ፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ፣ ለወጣቶችና በተለይ ደግሞ  የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡት የፀጥታ እና ደኅንነት ኃይሎች ምስጋና አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ጨምሮ በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቀዋል።

ከንቲባዋ ፥ " በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አስተዋፅዖ ላደረጉ የሀይማኖት አባቶች ፣ የከተማው ወጣቶች ፣ ሲያስተባብሩ ለነበሩ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እንዲሁም ዶፍ ዝናብ ሳይበግራቸው በዓሉ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዲከበር ላደረጉ የጸጥታ ሃይሎችና የከተማው ነዋሪዎች ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና እናቀርበላ " ብለዋል።

#የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋሕዶቤተክርስቲያን
#Ethiopia #AddisAbaba

@tikvahethiopia
2024/09/27 00:12:22
Back to Top
HTML Embed Code: