Telegram Web Link
#Tecno #Camon30Pro5G

ፍጥነት እና ቅልጥፍና መገለጫው የሆነውን MediaTek Dimensity 8200 ፕሮሰሰር አካቶ Tecno Camon 30 pro 5G ቀርቦሎታል

#Camon30Et #Camon30proEt #Camon30 #Camon30Pro #TecnoEt
#ወጋገን_ባንክ

ወጋገን ባንክ ባዘጋጀው የጥያቄ እና መልስ ውድድር ጠቀም ባሉ አጓጊ ሽልማቶች አሸናፊዎችን ማንበሻበሹን አሁንም ቀጥሏል !!

ታዲያ እርስዎስ ምን ይጠብቃሉ
?

አሁኑኑ ከስር የተቀመጡትን የወጋገን ባንክ ይፋዊ የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገፅ ሊንኮች ተጭነው በመቀላቀል እና ሌሎችም እንዲቀላቀሉ በመጋበዝ ፣ ጥያቄዎችን አስቀድመው እየመለሱ አጓጊ ሽልማቶችን የራስዎ ያድርጉ !

በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ

|
Facebook | Telegram

ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው

https://www.tg-me.com/WegagenBanksc
#አበረታቷቸው🙏

" ከበርካታ ችግሮች ጋር እየታገልንም ቢሆን ከ90 በላይ ህጻናትን ቁርስ አብልተን ወደትምህርት ቤት እንልካለን " - ተዋናይትና ደራሲ ሀና ፍቃዱ

የበጎ ልቦች የእርዳታ ድርጅት በቅን አሳቢ ወጣት የሀዋሳ ልጆች የተመሰረተ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ሲመሰረት ጥቂት አረጋዉያንን በየቤቱ እየሄዱ ማገዝና አልፎ አልፎ ለህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ የማገዝ አላማ አንግቦ ነበር።

አሁን ላይ ከ90 በላይ ህጻናትን ቁርስ አብልቶ ወደትምህርት ቤት የሚልክና ከ30 በላይ አረጋዉያንን እየተንቀሳቀሰ የሚረዳ ድርጅት ለመሆን በቅቷል።

በድርጅቱ ውስጥ በማስተባበርና ቅን ልብ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እየጠየቀች ገንዘብ በማሰባሰቡ በኩል የነቃ ተሳትፎ የምታደርገዉ ተዋናይትና ደራሲ ሀና ፈቃዱ ፥ " እቅዳችን በምግብ ችግር ትምህርት ቤት የሚያቋርጡ 30 ልጆችን መርጠን ቁርስ በማብላት ወደ ትምህርት ቤት መላክ ቢሆንም አሁን ላይ ከ90 በላይ ልጆችን እያስተናገድን ነው " ብላለች።

" ለዚህም ሀገር ውስጥና ውጭ ሀገር የሚኖሩ ልበ ቀናዎች እያገዙን ነው " የምትለው ሀና ፥ " እገዛዉ ከጠበኩት በላይ ሆኖ በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ አድርጎኛል " በማለት በሶሻል ሚዲያና በአካል የሚያግዟቸውን አካላት አመሰግናለች።

ይሁንና አሁን ላይ ያለው የህጻናት ቁጥር በጣም በማሻቀቡ ከፍተኛ ድጋፍ ያሻናል በማለት ማህበረሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርባለች።

በድርጅቱ ውስጥ " የሰኞን የቁርስ ወጭ እኔ እሸፍናለሁ " ብሎ ህጻናቱ ጋር ያገኘነዉ የባህርዳር ከነማዉ ተጫዋች ፍሬዉ ሰለሞን ወይም ጣቁሩና ባለቤቱ በህጻናቱ ሁኔታ ልባቸዉ እንደተነካና ለወደፊቱም ቤተሰብ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

" ሁላችንም ተባብረን ህጻናቱን ልንረዳ ይገባል " የሚለዉ ተጫዋቹ በሚቀጥለዉ ሲመጣ ጓደኞቹን ይዞ እንደሆነ ገልጾ " የበጎ ልቦችን ሁኔታ እየመጣችሁ ጎብኙ " በማለት ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎቹን ቁርስ አብሎት ለመሸኘት በቀን ከ8 ሺህ እስከ 10 ሺህ ብር የሚጠይቅ ሲሆን ሀና ፍቃዱን ጨምሮ ሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በሚያደርጉት ጥረት ተማሪዎቹ የሚመገቡት።

አስተባባሪዎችን በስልክ ቁጥር 0911992312 ወይም 0926441657 ደውለው አግኟቸው።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ዙሪያ የአሶሳ ፖሊስ ምን አለ ? የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው " ሰላም ሰፈር " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ረቡዕ ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ እንደሆነ አመልክቷል።…
#Update

የተማሪ ደራርቱ ገዳይ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል።

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ ላይ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ አስታውቋል።

ረቡዕ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አቶ ዩሀንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰብ የሴት ጓደኛው የሆነችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የግድያ ወንጀል በመፈፀሙ ተከሳሽ በፈፀመው ሰው በመግደል ወንጀል ተከሷል።

መርማሪ ፖሊስና ዐቃቢ ህግ በጋራ ተጠርጣሪው ላይ ክስ መስርተው ምርመራ በማጣራት የወንጀል ድርጊቱን የሚያስረዱ የሰው ማስረጃና የህክምና ማስረጃ በማስደገፍ ለሚመለከተው ፍ/ቤት ልከዋል።

የክስ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በቀን 15/9/2016 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት #በ18_ዓመት_ጽኑ_እስራት እንዲቀጣ ውስኗል።

መረጃው የአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።

#AssosaUniversity

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አጠገብ ያለ ቤት ውሃልክ እና አፈር ተደርምሶ የአንድ ወጣት ህይዎት አልፏል።

አደጋው የደረሰው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ " የረር ጉሊት " ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነው።

በግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ከአጠገቡ ዳገት ላይ የነበረ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሃ ልክ እና አፈር ተደርምሶ የ28 ዓመት ወጣት ህይወት አልፏል።

አደጋው መፈጠሩ ከተሰማ ጀምሮ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰራተኞችን ህይዎት ለመታደግ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸው ተነግሯል።

በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ ከተማዋ ውስጥ በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ሲታይ ዘንድሮ መጨመሩን ፤ በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሞ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

🏆የዋንጫውን አሸናፊ ይገምቱ🏆

🔥 ማንቼስተሮቹ ለዚህ ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ ለኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ፍፃሜ ይገናኛሉ!

🤔 የእናንተን ግምት ከታች አጋሩን!

👉 ጨዋታውን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
#WHO🚨

በግብረ ስጋ ግኝኑነት የሚተላለፉ ሽታዎች ወይም የአባላዘር በሽታዎች በዓለም ዙሪያ እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየጨመሩ እንደሚገኙ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) አዲስ ሪፖርት አሳይቷል።

ሪፖርቱ ፥ በየዓመቱ በመላው ዓለም 2.5 ሚሊዮን ሰዎች በግብረ ስጋ ግኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ፣ በኤችአይቪ እንዲሁም ሄፓታይተስ እየሞቱ ናቸው ብሏል።

በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉት እና ሊታከሙ የሚችሉ በሽታዎች እጅግ በፍጥነት እየተስፋፉ ሲሆን ሁኔታው አሳሳቢ ስለመሆኑ በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።

ሪፖርቱ ፦ https://www.who.int/news/item/21-05-2024-new-report-flags-major-increase-in-sexually-transmitted-infections---amidst-challenges-in-hiv-and-hepatitis

በዓለም ላይ በየዕለቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፉ የተለያዩ የሽታ አይነቶች ይያዛሉ።

ዲኤንኤ ዊክሊ የተሰኘ የጤና ድረገጽ እንደሚለው ፤ ዛሬም ድረስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ስለሚመጡ በሽታዎች መነጋገር ' እንደ ሚያሳፍር እና እንደ ተከለከለ  ' አድርገው የሚቆጥሩ ብዙ ናቸው።

ከጤና ባለሞያዎች ጋር መመካከር ፣ ስለጉዳዩ ማወቅ ፣ ሲታመሙ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ የሚያፍሩ ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።

ነገር ግን በበሽታዎቹ በየዕለቱ ሚሊዮኖች የሚያዙ ሲሆን በየአመቱም ሚሊዮኖች የሞታሉ።

በመሆኑ ስለ ጉዳዩ አሳስቢነት ሳያፍሩ መነጋገር ፣ የመተላለፊያ የመከላከያ መንገዶች ማወቅ ፣ የጤና ባለሞያዎችን ማማከር ምክራቸውንም መስማት ይገባል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ዛሬ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ ' ከፖሊስ ስራ ' ጋር በተያያዘ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮግራም አለ።

ይህ ተከትሎ መንገዶች ተዘግተዋል።

የተዘጉት መንገዶች ፦
- ከልደታ በላይኛው መንገድ  ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከአፍሪካ ህብረት  ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከጠማማ ፎቅ  በንግድ ምክር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከገነት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከሰንጋ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከቡናና ሻይ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ሲሆኑ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ያሳወቀው።

በመሆኑም ፦
° በስራ ላይ ምትገኙ አገልግሎት የምትሰጡ አሽከርካሪዎች ፣
° ወደ ስራ እየገባችሁ ያላችሁ ሰራተኞች
° ከስራ ወጥታችሁ ወደ የቤታችሁ እየሄዳችሁ ያላችሁ ነዋሪዎች ይህን መረጃ ተመልክታችሁ አማራጭ መንገድ ተጠቀሙ።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
" ሞቶ የመገኘቱ ጉዳይ እንቆቅልሽ ነው የሆነብን " - የጋዜጠኛው ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች

የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት የሆሳዕና ቅርንጫፍ ጋዜጠኛ የሆነው አብይ አበራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ስርአተ ቀብሩም በትዉልድ መንደሩ በአንጋጫ ወረዳ ፉነሙራ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

ወጣቱ ጋዜጠኛ አብይ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ተቀጥሮ ሲሰራ በጠንካራ አቋሙና በታታሪነቱ የሚታወቅ ቢሆንም ከሰሞኑ በቤቱ ውስጥ ሞቶ መገኘቱን ተከትሎ በቤተሰቦቹ  በጓደኞቹ እና በስራ ባልደረቦቹ ላይ  ታላቅ ድንጋጤ የፈጠረ ጉዳይ ሆኗል።

በጋዜጠኝነት ስራ ላይ የሚያዉቁት ጓደኞቹ  ስለታላላቅ ህልሞቹ የሚናገሩለት አብይ ትናንት ጠዋት ሞቶ የመገኘቱ ጉዳይ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸዉ ገልጸዋል።

ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የጋዜጠኛው ጓደኞች እና የስራ ባልደረቦች ፥ " አብይ ራስን የማጥፋት ተግባር ይፈጽማል ብለን ፈጽሞ አናስብም " ብለዋል።

ከጋዜጠኝነት ስራው ባለፈ ራሱን ለመደገፍ ማንኛዉንም ስራ በመስራቱ ለብዙዎች አርአያ መሆኑን የሚናገሩት ባልደረቦቹ በቅርቡ የራሱን ምግብ ቤት ከፍቶ በሰዎች ሲያሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።

ላመነበት ጉዳይም ወደኋላ የማይል ጠንካራ አቋም ያለዉ ሰው መሆኑን ተከትሎ " የአሟሟቱ ጉዳይ እንቆቅልሽ ሆኖብናል " ብለዋል።

ይህን ጉዳይ ይዘን  ያነጋገርናቸዉ የጸጥታ አካላት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ምላሽ ምንም ፤ ሁኔታዉን ለማጣራት አስከሬኑ  በተገኘ  ቅጽበት  ወደ ወራቤ ሪፈራል ሆስፒታል ለምርመራ መላኩን ገልጸዋል።

ፖሊስ ፤ ጋዜጠኛው ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ሞቶ የተገኘ መሆኑን በመጥቀስ ከአስከሬን ምርመራዉ በተጨማሪም ሌሎች  የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና የሚገኘዉን ውጤት እንደሚሳውቅ ተናግሯል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
2024/09/28 03:14:59
Back to Top
HTML Embed Code: