Telegram Web Link
#Tigray

➡️ " እስከ ሰኔ 30 ወደ ቄያችን መልሱን !! - ተፈናቃዮች

➡️ " ከክረምት በፊት ወደ ቄያችሁ እንድትመለሱ ከፌደራልና ከአማራ ክልል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ 

በእንዳስላሰ ሽረ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ዓዲግራት ፣ ዓብዪ ዓድዋና መቐለ የሚገኙ ከምዕራብ ፣ ከሰሜናዊ ምዕራብና ምስራቅ የትግራይ ዞኖች የተፈናቀሉ ወገኖች ዛሬ እሁድ ሰኔ 16/2016 ዓ.ም ወደ ቁያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተነግሯል።

ከምዕራባዊ ዞን ወረዳዎች ፣ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ባድመ ፣ ፀለምቲና አከባቢው  እንዲሁም ከምስራቃዊ ዞን ዛላንበሳና የኢሮብ ወረዳዎች ከቄያቸው መፈናቀላቸውን የገለጹት ተፈናቃዮቹ ፦
- እስከ ሰኔ 30 ወደ ቄያችን መልሱን !
- አርሰን እንድንበላ ወደ ቄያችን መልሱን !!
- የፕሪቶሪያ ውል በአግባቡ ይተግበር !
- የፌደራልና የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሃላፊነታቸው ይወጡ !
- የትግራይ ግዝታዊ አድነት ይከበር !
- የተፈናቃዮች ድምፅ ይሰማ ! የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን አሰምተዋል።

በተለይ በመቐለ ከተማ የሚገኙ በርካታ ተፈናቃዮች በሰልፋቸው ማጠቃለያ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት በመሄድ ድምፃቸው ያሰሙ ሲሆን ክረምት ከመግባቱ በአስቸኳይ ወደ ቄያችን መልሱን ብለዋል።

ሴቶችና ህፃናት የሚበዙባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቃይ ሰልፈኞቹ ምሬት የተሞላበት ድምፅና ሃሳብ ያደመጡትና ምላሽ የሰጡት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ " የዛሬው ሰልፍ የመጨረሻው እንዲሆንና ከክረምት በፊት እንድትመለሱ ከሚመለከተው አካል በቅንጅት እንሰራለን " ብለዋል።

" ወደ ቄያችሁ መመለስ በማስመልከት ከአማራ ክልል መንግስት እየተነጋገርን ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ህዝቡ ወደ ቄየው ሲመለስ ከቂምና በቀል በፀዳ መልኩ በቦታው ከቆዩ ወንድም እህቶቻቹ  የመተማመንና የመቻቻል መንፈስ በማጎልበት በአብሮነት መኖር ይገባዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
#ኢትዮጵያ

ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው በዚህ መመሪያ ዉስጥ የእህልና ጥሬጥሬ ፣ የግብርና ምርቶች እና የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች ይገኙበታል ።

በዚህ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ  እቃዎችን ለመወሰን በወጣው  መመሪያ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ማድረግ የወጪ ጫናውን በማርገብ ረገድ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ከተደረጉት መካከል ፦
➡️ ጤፍ፣
➡️ ስንዴ፣
➡️ ገብስ ፣
➡️ ማዳበሪያ ፣
➡️ የእንስሳት መድሃኒት እንዲሁም በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርብ የካፒታል ዕቃዎች ይገኙበታል።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
BK  C  O  M  P  U  T  E  R S

ማንኛውንም አይነት አዳዲስ ላፕቶፖች ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ዴስክ ቶፖችን ጨምሮ ከብዛትና ቅናሽ ጋር ያዘንላቹ መተናል።
ለቢሮዎች ፣ ለተማሪዎች፣ለግሪፊክስ ዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች እንዲሁም ለጨረታ የሚሆኑ በጥራት እና በ ብዛት  ከ1 አመት ዋስትና ጋር እኛ ያገኛሉ።

የላፕቶፕ አማራጮችን ለማየት የቴሌግራም ፔጃችንን Join ያድርጉ https://www.tg-me.com/BKComputers
Inbox @bkcomputer27
አድራሻ አዲስ አበባ መገናኛ ሲቲ ሞል ከ መሰረት ደፋር ህንፃ አጠገብ 1 ፎቅ ላይ እንገኛለን ፤ 0911448148. 0955413433
we make IT easy!
#ሴጅ_ማሰልጠኛ

20% ቅናሽ ሊጠናቀቅ 5 ቀናት ቀሩት ፤ ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Principles and Practices of Accounting) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን። 
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

ስልክ ፦ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ
Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#EthiopianOrthodoxTewahedo

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመቱ ውስጥ ከሚጾሙ አጽዋማት መካከል  ' ጾመ ሐዋርያት ' (በተለምዶ የሰኔ ጾም) በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

ይህ ጾም የሚፈሰከው ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ነው።

ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነው ጾመ ሐዋርያት በየትኛውም አመት ላይ ቢውል ሰኞ ቀን ከሚጀምሩት አፅዋማት አንዱ ነው፡፡

ይህ ጾም የሚፈሰክበት ከሐምሌ 5 አይበልጥም ፤ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ነው።

እንደ ቤተክርስቲያኗ አስተምሮ ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሰማያዊ ተልእኮ ስለተሰማቸው ከ5ዐ ቀን በኋላ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማግስት የጀመሩት ጾም ነው።

ጾሙ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ነው።

ቤተክርስቲያኗም ትንሳኤ ከዋለ ከበዓለ 50 በኃላ የፆሙን አዋጅ ለልጆቿ አውጃለች።

ይህ ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ እንደሆነ ቤተክርስቲያን ታዛለች።

ከዚህ ጾም በኃላ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል የሆነው ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና ዓርብ) የሚጀምር ይሆናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ…
🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ መንግስት እንደ መንግስት ሥራውን እየሰራ አይደለም ” ሲል ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ተቸ።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፤ ዶክተር አብዱልቃድር አደም ስለወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች የፓርቲያቸውን ምልከታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።

ሊቀመንበሩ በነበራቸው ቆይታ  ፦
- የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ጉዳይ
- የኑሮ ውድነት
- የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ
- ከሰሞኑን እየወጡ ስላሉ አዳዲስ አዋጆች
- ስለ ፖለቲካ ህዳሩ
- የመልካም አስተዳደር እጦት
- የኢኮኖሚ ጉዳይ ... ሌሎችም ተነስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም " መፍትሄው ምንድነው ? " ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፓርቲው ምላሽ ሰጥቷል።

ምጣኔ ሀብትን በተመለከተ ዶክተር አብዱልቃድር አደም ምን አሉ ?

“ የMacro Economy መናጋት አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የከፋ ሁኔታ ላይ ደርሷል።

የኢትዮጵያ የልማት ስትራቴጂ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ ነው።

ይልቁንም ትኩረት የሚሹት ፦
➡️ ኢንፍራስትራክቸር፣
➡️ መብራት፣
➡️ ጤና፣
➡️ ውሃ መሠረታዊ ችግሮች ናቸው፤ ዜጎች በእነዚህ ነገሮች ተቸግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚል የሚሰራቸው ፕሮጀክቶች መቃኘት አለባቸው።

ከፍተኛ የሆነ የንግድ ጉድለት አለ። የምንሸጠው እና የምንገዛው ልዩነቱ የሰፋ ነው። የበጀት Deficit አለ።

መንግስት የሚሰበስበውና የሚያወጣውን ገንዘብ ለዚያውም አስፈላጊነታቸው አጠራጣሪ ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘቡ ወጪ ይሆናል።

ይሄ ኢኮኖሚው እንዲናጋ አድርጓል ብለን እናምናለን።”

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-24

#ነእፓ #ኢትዮጵያ #የፖለቲካፓርቲዎችምንይላሉ?
#AddisAbaba

ግለሰብን አግተው የዘረፉ የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ።

አንድን ግለሰብ አስገድደው በያዙት ተሽከርካሪ ውስጥ በማገት ዶላርና የተለያዩ ንብረቶቹን ወስደዋል የተባሉ 3 የፖሊስ አባላት ላይ የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል።

3ቱ የፖሊስ አባላት ፦
ኮንስታብል ክብሩ በለጠ
ረ/ሳጅን ያለምሰው ዱሬ
ረ/ሳጅን ባህረዲን አለሙ ይባላሉ።

1ኛው ተከሳሽ በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ መምሪያ የተጠርጣሪ አስተዳደር ስር የጥበቃ አባል፣

2ኛው ተከሳሽ የተጠርጣሪ ክትትል እና ኦፕሬሽን ክፍል የኢኮኖሚ ነክ ጉዳዮች ወንጀሎች የፍርድ ቤት አስገዳጅ አባል፣

3ኛው ተከሳሽ በፎረንሲክ ምርመራ መምሪያ ስር በሹፌርነት ሲሰሩ ነበር።

ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ በ9 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 '  ጆን ጋራዥ  ' አካባቢ ካልተያዘ ሲቪል ከለበሰ ግብረአበራቸው ጋር በመሆን አንድ የግል ተበዳይን አስገድደው 3ኛ ተከሳሽ ለስራ አላማ የተረከበው ተሽከርካሪ ውስጥ በማገት ያስገባሉ።

አግተው ተሽከርካሪ ውስጥ ካስገቡም በኃላ ከግል ተበዳዩ ፦
° 2 ሺህ 600 ዶላር፣
° 2 የእጅ ስልክ
° 50 ሺህ ብር አስገድደው በመውሰድ ከተሽከርካሪው ገፍትረው ጥለውት እንደሄዱ በዐቃቤ ህግ የቀረበው የክስ መግዘብ ያስረዳል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ሕግ የተመሰረተውን ክስ ዝርዝር ለተከሳሾች እንዲደርሳቸው ካደረገ በኋላ ጉዳያቸውን ማረሚያ ቤት ወርደው  እንዲከታተሉ በማዘዝ ለሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

🔥 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች በድምቀት ቀጥለዋል!

🤔 እናንተስ ሉሲአኖ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን አሠልጣኝ ንግግር ምን ትላላችሁ? የእናንተን አስተያየት አጋሩን!    

የዛሬ ጨዋታዎች መርሃ ግብር፡

⚽️  Albania vs Spain ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM በSS Variety 4 229 ጎጆ ፓኬጅ በSS Premier League 23 በሜዳ  ፓኬጅ

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር ከ350 ብር ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya ጎረቤት ኬንያ ታቃውሞ እየናጣት ነው። መንግሥት በታክስ ላይ ጭማሪ ሊያደርግ ማቀዱን ተከትሎ በተለይም ወጣቱ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል። ከወጣቶቹ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ትላንት አንድ ሰው #ተገድሏል፡፡ ግድያው የተፈጸመው በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ነው ተብሏል። ዛሬም በናይሮቢና የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል። ተቃዋሚዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ የተቃውሞ…
#Update

በነገው ዕለት በኬንያ ምድር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሏል።

ይህ ሰልፍ የሀገሪቱ መንግስት ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅን የሚቃወም ነው።

የተቃውሞ ሰልፉ አይቀሬ እንደሆነ ያወቀው የሀገሪቱ መንግሥትም በአገር ውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ካቢኔ ሚኒስትር በኩል ሰልፉ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

ዛሬ በሰጠው ይፋዊ መግለጫ ማንኛውም ተቃዋሚ የመንግስትም ሆነ የግል ንብረትን እንዳያወድም ወይም እንዲያወድም እንደማይፈቀድለት አፅንዖት ሰጥቷል።

የተቃውሞ ሰልፈኛው የሚሄድበትን አቅጣጫ ቀደም ብሎ ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ እጅባና ጥበቃ እንዲደረግለት ማድረግ አለበት ተብሏል።

ሰልፈኞቹ ሰልፉን በፍጹም ሰላማዊ መንገድ ማድረግ እንዳለባቸው ያሳሰበው የሀገሪቱ መንግስት ትጥቅ ታጥቆ ሰልፍ መውጣት እርምጃ ሊያስወስድ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ተቃዋሚ ሰልፈኞች ፦
- የውሃ፣
- የኃይል አቅርቦት
- ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡት ወሳኝ ቦታዎች ላይ እንዳያገኙ ተከልክለዋል።

በተጨማሪ በህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ ተገልጿል።

በምንም መልኩ በየብስ ፣ በባቡር፣ በባህር ፣ በአየር ትራንስፖርት ላይ ጣልቃ መግባት እንደ ሌለባቸው ምንም ይሁን ምን ለሀገሪቱ ህግ የበላይነት ሁሉም ሰው ሊታዘዝ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ሁሉም ተቃዋሚዎች ሰልፉን ሁከት እና ብጥብጥን በማያበረታታ መንገድ እንዲያደርጉ እንዲሁም ደግሞ ፦
° ሰልፉን መሳተፍ የማይፈልጉ / ተቃውሞ ማድረግ የማይፈልጉ
° የፖሊስ አባላትን ፣
° የመንግስት አካላትን ማስፈራራት ፣ ማስጨነቅ እና መተንኮስ እንደሌለባቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

#Kenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል። ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው…
#ያንብቡ #ኢትዮጵያ

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ፤ ' መመሪያ ቁጥር 1006/2016 ' ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

መመሪያው ተግባራዊ የተደረገው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ለማድረግና የወጪ ጫናውን ለማርገብ ጠቀሜታ ስላለው መሆኑ ተገልጿል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆኑ እቃዎች እና አገልግሎቶች ዝርዝር ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ናቸው።

1ኛ. እህልና ጥራጥሬ
ጤፍ
ስንዴ
ገብስ
በቆሎ
ማሽላ
ዘንጋዳ
ዳጉሳ
አጃ
አተር ፣ ባቄላ ፣ ምስር፣ አኩሪ አተር፥ ሽምብራ፣ ግብጦ፥ ጓያ እና የመሳሰሉት ጥራጥሬዎች፤
የእነዚህ ዱቄት

2ኛ. የግብርና ግብአቶች
ማዳበሪያ
ጸረ-ተባይ ኬሚካል
የእንስሣት መድሃኒት
የመድሃኒት መርጫ

3ኛ. የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች
👉 እንጀራ
👉 ዳቦ
👉 ወተት

4ኛ. በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርቡ የካፒታል እቃዎች

5ኛ. የወባ መከላከያ አጎበር ፤ ኮንዶም እና ለውሃ ማከሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎች

#MinistryofFinance
#MinistryofRevenues

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ክብርን ተቀዳጀ።

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ' የአቪዬሽን ኦስካር ' ተብሎ በሚጠራው የስካይትራክስ መድረክ ነው ይህን ክብር የተቀዳጀው።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት፣

🏆 በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ተደራራቢ ድልን ተጎናጽፏል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በነገው ዕለት በኬንያ ምድር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሏል። ይህ ሰልፍ የሀገሪቱ መንግስት ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅን የሚቃወም ነው። የተቃውሞ ሰልፉ አይቀሬ እንደሆነ ያወቀው የሀገሪቱ መንግሥትም በአገር ውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ካቢኔ ሚኒስትር በኩል ሰልፉ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። ዛሬ በሰጠው ይፋዊ መግለጫ ማንኛውም ተቃዋሚ የመንግስትም…
#ኬንያ

" ዉጡ ! ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ወጥታቹ መቃወም ትችላላችሁ " - ኪቱሬ ኪንዲኪ

የኬንያ መንግሥት፤ ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን የሚቃወም የተቃውሞ ሰልፍ " ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ መካሄድ ይችላል " ብሏል።

የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ' ሰላማዊ ይሁን ብቻ ወጥታችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ' ብሏቸዋል።

' ያልተለመደ ነው ' በተባለው እርምጃ ፤ የሀገር ውስጥ የደህንነት ካቢኔ ሚኒስትር ኪቱሬ ኪንዲኪ ፥ " ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ የህግ የበላይነትን እና ህዝባዊ ስርዓቱን እስካከበሩ ድረስ በእቅዳቸውን መሰረት መቀጠል / ወጥተው መቃወም / ይችላሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የኬንያ መንግስት ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ በሰላማዊ መንገድ ፤ ትጥቅ ሳይታጠቅ ፦
° የመሰብሰብ ፣
° ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ፣
° የመምረጥ
° አቤቱታዎችን ለባለስልጣናት የማቅረብ የማይገረሰስ ህገ መንግስታዊ መብቱን ያከብራል ፤ እንዲፈጸምም ያደርጋል " ብለዋል።

ሰልፈኞቹ ወደ ሀገሪቱ ቤተ መንግስት ፣ በኃይል ወደ ፓርላማ ህንጻ እንዲሁም ወደ ሌሎችም የመንግሥት አካባቢዎች ለመጠጋት እንዳይዳፈሩ አስጠንቀቀዋል።

- ህግና ስርዓት አክብሩ ፤
- ህዝባዊ ስርዓቱን አክብሩ ፤
- የግል ፣ የመንግስት ንብረት አታውድሙ ፤
- መሰረተ ልማት አካባቢ አትጠጉ ፤
- የተከለከሉ ቦታዎች ጋር አትሂዱ፤
- የህዝባዊ አገልግሎት አታስተጓጉሉ፣
- እናተን የማይደግፏችሁ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣት የማይፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን አታስፈራሩ፣ አታዋክቡ፣ አታስጨንቁ
- የጸጥታ ኃይል አባላትን አትተንኩሱ ... ከዚህ ውጭ ግን እንደልባችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ብለዋቸዋል።

ሚኒስትሩ ፤ የጸጥታ ኃይል ጥበቃ እና እጅባ ለማድረግ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሰልፍ ለማድረግ የሚሄዱበትን አቅጣጫ ቀደም እያሉ ማሳወቅ እንዳለባቸው ገልጸው ፀሃይ ከመጥለቋ በፊት ተቃውሞው እንዲያበቃ አደራ ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyKenya

@tikvahethiopia
2024/06/25 05:31:07
Back to Top
HTML Embed Code: