Telegram Web Link
#ቢሾፍቱ

ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል።

ሆስፒታሉ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተገኙበት ነው የተመረቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆስፒታሉ ፦
- እጅግ ዘመናዊ የሆነ የሞሎኪዩላር ላብራቶሪ፣
- የአጥንት ምርመራ ማዕከል፣
- ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ክፍል
- እንደ የኩላሊት እጥበት፣ የነርቭ፣ የሳምባ እና መተንፈሻ አካላት የህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

" በሀገራችን ውስጥ ካሉ ግምባር ቀደም ዘመናዊ ሆስፒታሎች አንዱ ነው " ብለውታል።

ፊ/ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው " ሆስፒታሉ ለሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን ለህዝባችንም ትልቅ ጠቀሜታ ይዞ መጥቷል " ብለዋል።

" ታካሚዎችን ውጭ አገር ሲላኩበት የነበረውን የአሰራር ሂደት ይቀይራል ፤ በሀገር ወስጥ ከፍተኛ ሕከምና መሰጠት ስለሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ወጪን ያስቀራል " ብለዋል።

ሆስፒታሉ 425 የህሙማን ተኝቶ መታከሚያ አልጋ አለው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ሀላባ

- " ባለቤቴ ከወንድሙና እህቱ ጋር በመሆን ፊቴ እስኪበላሽ ደበደቡኝ " - ተበዳይ

- " እንዲህ አይነቱን የሴት ልጅ ጉዳት አንታገስም " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊዉ አቶ ሙደሲር ጉታጎ

በሀላባ ከተማ " ባለቤቴ ከእህትና ወንድሙ ጋር በመሆን አደጋ አድርሶብኛል " ያለች ተበዳይ የህግ ድጋፍ ስጡኝ ስትል በማህበራዊ ሚዲያ ጥያቄ አቅርባለች።

ጉዳዩን የተመለከተው የሀዋሳ የቲኪቫህ ቤተሰብ አባል ባደረገዉ ማጣራት ፥ ተጎጅዋ ፊቷ ላይ ጉዳት መደረሱን በተጨማሪ የሷና የመጀመሪያ ልጇ ሰዉነት ትክሻቸዉ አካባቢ ' ጥርስ ንክሻ ' እንደደረሰባቸዉ ለማወቅ ችሏል።

የግል ተበዳዩዋ እናት ለቲክቫ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ልጃቸዉና የልጅ ልጃቸዉ በደም ተዘፍቀዉ በምሽት ወደቤት እንደመጡና በወቅቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገንተው እንደነበር ገልጸዋል።

የግል ተበዳዩዋ ወ/ሮ አበባ ቦረና ፤ " ምንም እንኳን የጋራ አራት ልጆች ቢኖሩንም ካሁን በፊት በመካከላችን በነበረ ግጭት ምክኒያት በፍርድ ቤት ለመለያየት ጫፍ ከደርሰን በኋላ  በሽማግሌ ተመልሰን አንድ ላይ መኖር ከጀመርን 3 ወር አልሆነም " ብላለች።

" ምንም እንኳን ቀን ላይ ቀላል ጭቅጭቅ ውስጥ ብንገባም ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ እንዲህ ያደርጋል ብዬ ፍጹም አልጠበኩም " ስትል ተናግራለች።

" በተለይ ተሰብስበዉ ሲደበድቡኝ ለመገላገል የገባዉን የመጀመሪያ ልጃችን ላይ ላይ በዚህ ልክ ይጨክናል ብዬ አላሰብኩም ነበር "  ብላለች።

ጉዳዩን በተመለከተ የጸጥታ አካላት ምን እየሰሩ ነዉ ? በማለት የጠየቅናቸው የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ሀላፊ አቶ ሙደሲር ጉታጎ ፤ " እንዲህ አይነቱን የሴት ልጅ ጉዳት አንታገስም " ብለዋል።

ጉዳዩን በሰሙ ቅጽበት የከተማው ፖሊስ በፍጥነት ችግር ፈጣሪዎችን  ይዞ እንዲያጣራ ማዘዛቸዉንም ነግረዉናል።

አቶ ሙደሲር  ጉዳዩ ተጣርቶ የሚደረስበትን ውጤት እንደሚያጋሩን ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት…
#Update

የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) የበይነ መረብ (Online) ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆነ፡፡

የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በበይነ መረብ ይሰጣል።

በዚሁ መሠረት በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከላይ በተገለጸው አድረሻ ብቻ የሚፈተኑ ይሆናል፡፡

ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድረጋቸው አስፈላጊ በመሆኑ ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአድራሻው ተፈታኞች በሚገኙበት ክልል የተደለደሉ ስለሆነ ልምምድ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል / ከተማ አስተዳደር ቀድሞ የተላከውን የይለፍ ቃልና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች #ከተደለደሉበት_ክለስተር_ዉጪ ሲሰትሙን መጠቀም #የማይችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Yonatan_BT_Furniture
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር

የዘመናዊነት ተምሳሌት!


አድራሻችን፦
1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727
2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686
3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282

👉 Telegram:  https://www.tg-me.com/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
#SirajChiffon

የተለያዩ ምርጥ ሽፎኖች በተመጣጣኝ ዋጋ !

አድራሻ ፦ መርካቶ አዲሱ ሚሊተሪ ተራ / የሱቅ ቁጥር: F1-133C

ያናግሩን ፦ @bilalsiraje
ስልክ ፦ +251929091179 or +251931223346

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/siraj1945
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ? ፕ/ር…
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" ግጭቶች ከትንሽ ነገር እየተነሱ እያደጉ ነው አሁን ያሉበት ደረጃ የደረሱት። ይሄ ደግሞ በመንግስት ቸልተኝነት ፣ ትዕግስት ማጣት የሚመጣ ነው " - ኢዜማ

በኢትዮጵያ ለሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያለውን ግምገማ በተመለከተ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። 

Q. በተለያየ ጊዜ ዜጎች በሰላም ወጥተው መግባት እንደማይችሉ ይገለጸል። ከሰው ሕይወት የሚበልጥ ነገር ደግሞ የለም። እንደ ፓርቲ ለመፍትሄ ምን እየሰራችሁ ነው ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" ችግሮችን በየትኛውም ወገን በኃይል ለማስፈጸም ከመሞከር በፊት በውይይት እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጠይቀናል።

ነገር ግን በየትኛውን አካል ተሰሚነት አላገኙም። ላለማግኘታቸው ማስረጃዎቹ አሁን ያሉት ግጭቶች ናቸው።

ግጭቶች ከትንሽ ነገር እየተነሱ እያደጉ ሂደው አሁን ያሉበት ደረጃ ላይ የደረሱት። ይሄ ደግሞ በመንግስት ቸልተኝነት፣ ትዕግስት ማጣትም ጭምር የሚመጣ ነው። የግጭቶቹን መንስኤ በማየት እንዲፈቱ ማሳሰቢያዎችን እየሰጠን ነው። "

Q. አንዳንዶች " መንግስት በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን ግጭት ስለሚፈልገው እንጂ ማስቆም አቅቶት አይደለም " የሚሉ ትችቶች ሲያቀርቡ ይስተዋላል። በዚህ ጉዳይ ፓርቲዎ ምን ይላል ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" አንድ መንግስት የተረጋጋ ሰላም ሲኖር ነው ሊጠቀም የሚችለው ብለን እናምናለን።

ችግሮች ባሉበት መንግስት ዘላቂ የስልጣን ማራዘም፣ የልማት ውጤት ማምጣት አይችልም። ስለዚህ ግጭቶቹ እንዲባባሱ ፍላጎት አለው ብለን አናምንም።

ግን ለ5 ዓመታት መንግስት ለምን ችግሮቹን ማስቆም አልቻለም ? ብለን ካየን አንደኛ የግጭቶቹን ባሕሪ መውሰድ ያስፈልጋል።

ቀውሶቹ ውጫዊና ውስጣዊ ብለን ብንከፍል እንኳ ግጭቶች እየተነሱ ያሉት ብልጽግና ውስጥ ባሉ ኃይሎች ነው። 

የክልል ልዩ ኃይልን ትጥቅ ከማስፈታት፣ ተፈናቃዮችን ከማስመለስ ጋር ተያይዞ መንግስት ይወስዳቸው የነበሩ እርምጃዎች ፓለቲካዊ ጉዳዮች ፓለቲካዊ የሆነ መፍትሄ ማግኘት ሲገባቸው ያንን ላለማድረግ እየተፈጠረ ያለ ግጭት ነው። "

Q. ፓርቲያችሁ ኢዜማ “ የመንግስት ተለጣፊ ” የሚል ስያሜ / አስተያዬት ሲሰጠው ይስተዋላል። ምላሽዎ ምንድን ነው ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" መንግስት እየሰራቸው ያሉ ግድፈቶችን እያስቀመጥን ነው። እንደዛ የሚባለው በምን መስፈርት እንደሆነ አይገባኝም። እኛ በአግባቡ ስራችንን እየሰራን ነው።

ለሚነሱ አሉቧልታዎች ምላሽ መስጠት አንችልም ፤ ጊዜ የለንም ፤ እኛ ሥራ ላይ ነን።

እንደዚህ የሚሉት መስራት የማይችሉ ሰነፎች ናቸው። "

Q. በኢትዮጵያ ስላለው የጸጥታ እና የደኀንነት ሁኔታ የፓርቲዎን ግምገማ ቢያጋሩ ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ በተለይ ባለፉት 3 ዓመታት እየተባባሰና መልኩን እየቀየረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።

መጠኑ በተለያየ ደረጃ ይሁን እንጂ በተለያዩ ክልሎችና ወረዳዎች ላይ ያሉ ግጭቶች የጸጥታ ሁኔታውን እያወኩት ይገኛሉ።

የሚታዩት የጸጥታና ደህንነት ችግሮች ዜጎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ጉዳያቸውን እንዳይፈጽሙ ፤ የፓለቲካ ፓርቲዎችም #በነፃነት_ተንቀሳቅሰን የምንፈልገውን የፓለቲካ ሥራ እንዳንሰራ እንቅፋት እየፈጠረ ነው። "

Q. የኑሮ ወድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ ፈትኖታል። ለዚህም  “ መንግስት ትኩረት አልሰጠም  ” የሚሉ ቅሬታዎች ሲሰነዘሩ ይስተዋላል። መንግስት ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" ኑሮ ውድነቱ በተለይም #መካከለኛ_ገቢ የሚኖረው ህብረተሰብ ተመግቦ ማደር የማይችልበት፣ ልጆቹን የማያስተምርበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

የኑሮ ውድነቱ በየቀኑ ከቁጥጥር ውጪ እየወጣ ነው ያለው።

በዚህ ሁኔታ እንኳ ሠራተኞች የወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው እየሰሩ ነው።

በተቃራኒው ደግሞ መንግስት ለቅንጡ ፕሮጀክቶች የሚያወጣቸው በጀቶች አሉ። መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ ኑሮ ውድነቱን የዘነጋ ነው። "

Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ? ለቀጣዩ ምርጫስ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ፦

" የጸጥታው ችግር የፓለቲካ ፓርቲዎች በሚፈለገው ደረጃ ተንቃሳቅሰው አባሎቻቸውን እንዳይቀሰቅሱ፣ ደጋፊዎቻቸውን እንዳያገኙ አድርጓል። እኛም ያንን እያደረግን አይደለም።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የመንግስት ሚዲያዎችን እንኳ መጠቀም አይችሉም።

የመንግስት ሚዲያዎች የብልጽግና ልሳን ሆነዋል። የብልጽግና እንጂ የመንግስት ሚዲያ ሊባሉ አይችሉም። 

ስለዚህ የፓለቲካ ምህዳሩ ከቀን ቀን እየጠበበ ነው። ይሄ ደግሞ መድብለ ፓርቲ በታወጀበት አገር ላይ አይጠቅምም።

የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን እያራመድን ነው እንላለን፤ መሬት ላይ ያለው ሀቅ ግን አንድ አውራ ፓርቲ ብቻ ኖሮ (ብልጽግና) እሱን ብቻ እያሞገስን እንድንኖር ነው።

ብልጽግና በቀጥታ እየሄደ ያለው ራሱን ወደ አውራ ፓርቲ ለመቀየር እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።

‘ 13 ሚሊዮን ፣ 14 ሚሊዮን #አባላትን_አፍርቻለሁ ’ ይላል፤ ከመራጩ ሕዝብ ግማሹን አባል አድርጌአለሁ የሚል ከሆነ ምርጫ ቢመጣም ትርጉም የለውም። ለይስሙላ የሚደረግ ምርጫ ነው። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#EZEMA #የፖለቲካፓርቲዎችምንይላሉ?

@tikvahethiopia
2024/11/16 10:18:11
Back to Top
HTML Embed Code: