Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ዙሪያ የአሶሳ ፖሊስ ምን አለ ?

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው " ሰላም ሰፈር " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ረቡዕ ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ እንደሆነ አመልክቷል።

" በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረ በሀሳብ ያለመግባባት ምክንያት ተጠርጣሪው በአሰቃቂ ሁኔታ ጀርባዋ ላይ #በጩቤ_በመውጋት የተማሪዋ ህይወት እንዲያልፍ አድርጓል " ሲል ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝም አሳውቋል።

የከተማው ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርስቲው ግቢ ውጭ እንደሆነ አመልክቷል።

ተጠርጣሪው የግቢ ተማሪ ያልሆነና ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለስራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊቱን እንደፈጸመ ገልጿል።

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚድያዎች " ድርጊቱ የተፈጸመው በግቢ ውስጥ ነው " በሚል የሚሰራጨው እና የብሔር ግጭት አስመስለው የሚወራው ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው የነበሩ መሆኑን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

#AssosaPolice

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች ለ2ተኛ ዙር የቀረበ ጥሪ!

ስቴም ፖወር (STEMpower) ከፊንላንድ ኤምባሲ (Embassy of Finland Ethiopia) እና ከአይቢኤም (IBM) ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሥራ አጥ ወጣት ሴቶችን ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ለመስጠት ያለመ "ትጋት" የተሰኘ ፕሮግራም አስተዋውቀዋል።

በመጀመያ ዙር 700 በላይ ለሚሆኑ ሴቶች በ Project Management, Web Development , Cyber Security, Digital Marketing , Data Analytics , Information Technology , Job Readiness , Work Readiness ስልጠና የሰጠ ከመሆኑ በተጨማሪ የስራ እድል በመፈጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል አመቻችቷል፡፡

#ነጻ በሚሰጠውና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት በሚያስገኘው በዚህ ስልጠና እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ሴቶች ምዝገባ የጀመርን መሆኑን እያሳወቅን ምዝገባው የሚቆየው ከ ግንቦት 7 - 20, 2016 ዓ/ም ሲሆን ቀድማችሁ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን፡፡

እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ
👉 https://forms.office.com/r/i0fNZG4021
#Hawassa

➡️ " ንፋስ በመጣ ቁጥር ጉዳት እየደረሰ ነው። እሮብ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል " - የሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል

➡️ " ጉዳት የደረሰበት የካፌ አስተናጋጅ ነው። በወቅቱ ወደህክምና ተወስዶ የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ህይወቱ ግን ሊተርፍ አልቻልም " - የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ

በሀዋሳ ከተማ ፤ ፒያሳ በሚገኘው ንብ ባንክ ህንጻ ላይ የወደቀ መስታወት የአንድ ወጣት ህይወት ቀጥፏል።

ህንጻው በዝናብና ንፋስ ወቅት እቃ ሲወድቅበት የመጀመሪያው እንዳልሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ የቤተሰብ አባላቱ ጥቆማ ደርሶታል።

በቅርቡ የተመረቀዉ የንብ ህንጻ ከዘጠነኛ ፎቅ ላይ የወደቀ መስታወት የህንጻው ወለል ላይ ስራ ላይ የነበረ ሰራተኛ ላይ ማረፉን ተከትሎ ሰራተኛው ህይወቱ አልፏል።

በሀዋሳ እሮብ ከ9 ሰአት በኋላ የነበረው ከባድ ዝናብና ውሽንፍር ባስከተለዉ ነፋስ ከህንጻዉ ላይ የወደቀ መስታወት የሰዉ ህይወት ማጥፋቱን ለማረጋገጥ ችለናል።

አንድ የሀዋሳ የቤተሰባች አባል ፤ " ንፋስ በመጣ ቁጥር ከህንጻው ላይ በሚወድቅ ቁስ ተደጋጋሚ ጉዳት በግለሰቦች ላይ ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ነው። እሮብ አንድ ሰራተኛ መስታወት ወድቆበት እጁ የመቆረጥ ፣ አናቱ ላይ የመጎዳት በኃላም ህይወቱ አልፏል። ህንጸው ግልጽ የሆነ የግንባታ ጉድለት ይታይበታል " ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የሰጡት የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ወንድማገኝ ቶርባ ፤ ጉዳት የደረሰበት ወጣት የካፌ አስተናጋጅ መሆኑንና በወቅቱ ወደህክምና ተወስዶ የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ህይወቱ ግን ሊተርፍ እንዳልቻለ ገልጸዋል።

ይሁንና " ህንጻው ላይ ተደጋጋሚ ችግር ተስተውሏል " ለሚባለዉ ቅሬታ ካሁን በፊት የደረሰ አደጋን የተመለከተ ሪፖርት የለም ሲሉ ገልጸዋል።

በወቅቱ በዚህ ህንጻ ውስጥ ከደረሰዉ አደጋ  ውጭ በከተማዉ የተከሰተዉ ነፋስ በርካታ የንብረት ጉዳት ማስከተሉንም አስታውሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የህንጻዉን አስተዳዳሪዎች በጉዳዩ ዙሪያ ለማነጋገር ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካም። ምላሽ አለም ካሉ መስተናገድ ይችላሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopiaRegion በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ የሶዶ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች ለወራት ያልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ እንዲሰጣቸዉ በአደባባይ ሠልፍ ጠይቀዋል። በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የግቢ በሮች ላይ የተሰበሰቡት ሠራተኞች እንደገለጹት እስከ 3 ወራት የሚደርስ ደሞዝ አልተከፈላቸዉም። ሠራተኞቹ ደሞዝ ሥላልተከፈላቸዉ እራሳቸዉንና…
#SouthEthiopiaRegion

➡️ " ... በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነው " - የሶዶ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኞች

➡️" ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " - የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ

የ2 ወራት ደሞዛችን ይከፈለን ያሉ የወላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች አደባባይ መውጣታቸዉን ተከትሎ  በርካታ ያልጠበቋቸዉ ጉዳዮች እንደገጠሟቸዉ ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ ሰራተኞች ፥ " ጥያቄያችን ለመጠየቅ የተገደድነዉ ረሀቡ ስለጠናብን ነው " በማለት ላለፉት ወራት ከፍተኛ ችግር ውስጥ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ደሞዝ ከወሰድን 2 ወራችን ነዉ የሚሉት ሰራተኞቹ ከዚያ በፊትም በፐርሰንት እየተቆራረጠ ይሰጥ የነበረው ደሞዝ የማንወጣው እዳ ውስጥ አስገብቶን ነበር ብለዋል።

" በፐርሰንት ሲከፈለን በነበረበት ወቅት ችግሩን ለመቋቋም አበዳሪ ተቋማት ጋር ሂደን የምንበደረው ገንዘብ ወለዱ አሰቸጋሪ መሆኑ ሳያንስ ደሞዝ ሲቀርብን ደግሞ ሌላ ጣጣ ውስጥ ገባን " በማለት የችግራቸዉን ውስብስብነት አስረድተዋል።

" በዚህ ምክንያት በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነዉ " በማለት ተናግረዋል።

ሰራተኞቹ " እስካሁን በየደረጃዉ የነበሩ የመንግስት አካላትን ስንጠይቅ ውክቢያና ማስፈራራት ነበር የሚገጥመን በተለይም መጀመሪያ ወደ ዞን አስተዳዳሪ ስናመራ ፖሊስ በትኖን መልሰን መሰባሰብ ሁሉ ከብዶን ነበር " ብለዋል።

" በመጨረሻ ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ ስንሄድ ሌላዉ ቢቀር ሀሳባችን ሰምተዉ አካሄዱን በማስረዳት ሀሳባችን በደብዳቤ እንድንገልጽ ፈቅደዉልናል " ብለዋል።

" ይሁንና አሁንም ጥያቄያችን ምላሽ አላገኘም " የሚሉት ሰራተኞቹ ተመልሰን ጥያቄያችን የት ደረሰ እንዳንልም ስላልተደራጀን በየጊዜዉ መሰባሰቡ ከበደን ብለዋል።

በመጀመሪያዉ ቀን የሰላማዊ ሰልፍ ሙከራ "  ፖሊስ ሰራተኛዉን በትኗል " መባሉን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ በጉዳዩ ሰራተኛዉ ጥያቄ መጠየቁን እንጅ ከፖሊስ ጋር ግጭት እንደገባ መረጃ እንደሌላቸዉ ገልጸዋል።

ያም ሆኖ " ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " ሲሉ ገልጸው " ችግሮች ተከስተዉ ከሆነ ወደፊት መረጃ እንሰጣችኋለን " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Tecno #Camon30Pro5G

የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት 
ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋወቀ።

አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሰኢድ አራጋው በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ‘’ ኢትዮ ቴሌኮም እና ቴክኖ ሞባይል በጋራ በመሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይሰራሉ’’ ብለዋል።

#Camon30Et  #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እኛም በተፈጠረው በጣም አዝናል ፤ ነገር ግን ተደጋጋሚ የሚባለው ፍፁም ትክክል አይደለም " - ሀዋሳ የሚገኘው የንብ ባንክ ህንጻ

ረቡዕ በሀዋሳ ከተማ በነበረው ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ወቅት ፒያሳ ከሚገኘው የንብ ባንክ ህንጻ ላይ ወደታች የወደቀ መስታወት የአንድ ወጣት የካፌ አስተናጋጅን ህይወት ቀጥፏል።

ጉዳዩን በተመለከተ ጥቆማ እየሰጡ አንድ የሀዋሳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፤ ችግሩ ተደጋጋሞ ይከሰታል የሚል ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

የሀዋሳ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ እሮብ ከህንጻው በወደቀ መስታወት አንድ ወጣት የካፌ አስተናጋጅ ተጎድቶ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱ ሊተርፍ እንዳልቻለ አረጋግጦ ነበር።

ነገር ግን " ተደጋጋሚ ችግር አለ " ለሚባለው ቅሬታ " ምንም አይነት የደረሰ አደጋን የሚመለከት ሪፖርት ከዚህ ቀደም እንዳልመጣለት አሳውቋል።

ዛሬ ህንጻው አስተዳደር ክፍል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥቷል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ አካል ፤ እሮብ የተፈጠረው ትክክል ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሰጥተው በተፈጠረው ነገር ሁሉም እጅግ ማዘኑን ገልጸዋል።

ነገር ግን " ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ችግር ተስተውሏል " የሚለው ፍጹም ትክክል እንዳልሆነ እና ህንጻው ጉድለት እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

" ተደጋጋሚ ችግር " ተብሎ የተሰጠው ጥቆማ ምናልባትም ከወር በፊት ከጎን ካለ #የአዋሽ_ባንክ ህንጻ በንፋስ ምክንያት ወደ ታች የወደቀ ቁስ በንብ ህንጻ ስር ባለ ካፌ የመኪና ማቆሚያ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ዋቢ ተደርጎ ሊሆን ይችላል እንጂ ህንጻው ከዚህ ቀደም ምንም ችግር ገጥሞት አያውቅም ብለዋል።

የሀዋሳ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የሰጠው መረጃም ትክክለኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
10 ዓመት ?

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ መንደር 44 ቀበሌ በሁለት #የ8_አመት_ህፃናት ላይ የግብረ-ስጋ ድፍረት (አስገድዶ የመድፈር) ወንጀልን የፈፀመ የ41 አመት ጎልማሳ በ10 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።

ተከሳሽ አብዱ ወዚር የሚባል ሲሆን ነዋሪነቱ አሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ መንደር 44 ቀበሌ ነው።

በጥር 3 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት በአካባቢው የማሽላ ሰብል ማሳ ውስጥ በመደበቅና ህፃናቱን " ጥንቅሽ ልስጣችሁ ኑ ብሉ " ብሎ በመጥራት ወደ ውስጥ ካስገባቸው በኋላ ሁለቱንም በሀይል አስሮ የግብረ ስጋ-ድፈረት (አስገድዶ መድፈር) መፈፀሙ ተገልጿል።

በተጨማሪም በህፃናቱ ላይ ያደረሰባቸውን ሁለንተናዊ ጉዳትም ለማንም ትንፍሽ እንዳይሉ አስፈራርቶ እና በገንዘብ አታሎ ከቦታው ይሰወራል።

ፓሊስም ግለሰቡ በቁጥጥር ስር አውሎ ፍርድ ቤት ያቀርበዋል።

የባምበሲ ወረዳ ፍርድ ቤትም ግለሰቡ በ10 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ግለሰቡ ግን " በፍርድ ውሳኔው ላይ ቅር ተሰኝቻለሁ " በማለት ይግባኝ ብሎ ጉዳዩ በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እንዲታይ ይጠይቃል።

የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም " የ10 አመት " ፅኑ እስራት ውሳኔው አስተማሪ ነው በማለት አጽድቆ መዝገቡን ዘግቷል"

Via @TikvahethMagazine
#Axum

" የሃውልቱ ዲዛይንና መሬት ላይ የተገነባው ለየቅል ነው ፤ አይገናኝም ! "
 
ዛሬ በአክሱም ከተማ የማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሃውልት ተመርቋል።

ነገር ግን ከሃውልቱ ግንባታ ጋር በተያያዘ በርካቶች " አይመጥንም " በሚል ተቃውመዋል።

በአክሱም በይፋ የተመረቀው የማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሃወልት ለግንባታው አራት (4) አመት መፍጀቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል።

በምረቃ ስነ-ሰርዓቱ የተገኘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሃውልቱ ግንባታ ዙሪያ የተነሳው ተቃውሞ ተከታትሏል።

በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ ምእመናን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የኢትዮጵያና የዓለም የዜማ አባት የሆነው ማህሌታይ ቅዱስ ያሬድ የሚያስታውስ ሃወልት መቆሙ ቢያስደስታቸውም " ሃውልቱ የዜማ አባቱን ክብርና ዝና የሚመጥን አይደለም " ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በስነ-ሰርዓቱ ላይ የተገኙት የአክሱም ገዳማት ወ አድባራት አስተዳዳሪ ንቡረ እድ ጎደፋ መርሃ ምእመናኑና እና ታዳምያን " ሃወልቱ አይመጥንም " ሲሉ ያነሱትን ቅሬታ ተጋርተውታል።

የምረቃ ስነ-ሰርዓቱ በሚድያ ለህዝብ ይፋ ከሆነ በኃላ ' ሃወልቱ ቅዱስ ያሬድን አይወክልም ፤ አይመጥም ' የሚል በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያለው ወገን ተቃውሞውን በማህበራዊ ሚድያ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እያጋራ ነው።

ከዚህ አለፍ ሲል ፈርሶ ድጋሜ እንዲገነባና ሃወልቱ ማህሌታይ ያሬድን በሚመጥን መልኩ በሀገር ያሉና በውጭ ያሉ ባለሞያዎችን አሳትፎ እንዲገነባ " ገንዘብ እናዋጣለን " እንዲሁም እውቀታችንን እናካፍላለን ያሉ አሉ።

" የሃውልቱ ዲዛይን እና መሬት ላይ የተገነባው ለየቅል ነው አይገናኝም " ያሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ባለመከታተሉ ወቅሰዋል።

ሃወልቱ #በመቐለ_ዩኒቨርስቲ እና በአክሱም ገዳማት ወ አድባራት አስተዳደር ትብብር የተገነባ ሲሆን ለግንባታው ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle                                               
@tikvahethiopia            
ኢሕአፓ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ / #ኢሕአፓ / ፥ " ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቀጥል በአገራችን የሕግ የበላይነት ሊኖር ይገባል " አለ።

ፓርቲው በላከው መግለጫ ላይ ፥ " የአገር ሕገ -መንግሥት ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ መንግሥትም የሚገዛበት የአገሪቷ ሉዓላዊ ሕግ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል " ብሏል።

" የመንግሥት ፈርጣማ ጉልበት በሕገ መንግሥት የሚገታ ካልሆነ አንድ መንግሥት ሕዝብን ብቻ እንዳፈተተኝ አስተዳድርበታለሁ ካለ ሕገ መንግሥቱ ቅቡልነት አይኖረውም " ሲል ገልጿል።

ፓርቲው " የመንግሥት አካላት ዜጎችን እንደፈለጉ ፦
- ማሰር፣
- መግደል፣
- ማፈናቀል፣
- መደብደብ፣
- ማፈን፣
- ማንገላታት፣
- ማሳደድ፣
- ቤት ንብረታቸውን መቀማት ከጀመሩ መንግሥትንና ሕዝቡን የሚያስተሳስረው ሕግዊ ሥርዓት ትርጉም-አልባ ሆኗል ማለት ነው " ብሏል።

" መንግሥት በቅድሚያ ሕግ አክባሪ ሲሆን ነው ሕግን ማስከበር የሚችለው " ሲልም አክሏል።

" በኢትዮጵያ ውስጥ እስከዛሬ ድረስ የፈሰሰው የደም ጎርፍ ሊበቃ ይገባል " ያለው ኢሕአፓ " የብልጽግና መንግሥት በአገራችን ሠላምን ለማስፈን ተቀዳሚ እርምጃ ፦
° በሕዝብ ላይ ጦር መስበቁን፣
° ሠራዊት ማዝመቱን፣
° በድሮን
° በአየር ኃይል ሠላማዊ ሕዝብን መፍጀቱን በአስቸኳይ ማቆም ይኖርበታል፡፡ ሕዝብን ከዕልቂት ሀገርንም ከውድመት ማዳኛው ብቸኛው መንገድ ዛሬም ሠላማዊ የትግል መንገድ ነውና " ብሏል።

ፓርቲው በመግለጫው ሊቀመንበሩ፣ ረ/ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ  የታረሱ አባላቱ እንዲፈቱ ጠይቋል።

አባላቱና ሌሎች የእስረኞች አያያዙ እና ቆይታው ሰቅጣጭ በሆነበት " አዋሽ አርባ "  እንደታሰሩ ነው ያመለከተው።

" እስር እና ማሰቃየት የስልጣን መንበርን ለአጭር ጊዜ ሊያጸና ይችል ይሆናል እንጂ ዘለቄታ የለውም " ያለው ፓርቲው " ገዢው ፓርቲ አገራችን እንደ አገር እንድትቀጠል እንዲሁም የወገኖቻችን ደህንነት እንዲጠበቅ ፣ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እስራቱ ፣ አፈናው ፣ ግድያው ፣ ወከባው ፣ ማስፈራራቱ ፣ ሕግን መጣሱ ማብቃት አለበት " ብሏል።

" የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ሁሉ ማፈን አምባገነናዊ የሆነ ሥርዓትን ማንበርና በፍርሃት እየተናጡ ሌሎችንም እፎይታ ነስቶ መቆየትን እንጂ ለአገር ሠላም እና መረጋጋትን አያመጣም፣ ወደ ማኅበራዊና ኤኮኖሚያዊ እድገትም በፍጹም አይወስድም " ሲል አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
2024/11/16 12:52:32
Back to Top
HTML Embed Code: