#AD
ፋና የወይባ ጡሽ የተመሰረተበትን 22ኛ አመት በአሉንና 4ኛ ቅርንጫፉ የመክፈቻ ስርአት አካሄደ።
በወ/ሮ ፋና ገ/መድህን ከ22 አመት በፊት የተመሰረተው ‘ ፋና የወይባ ጡሽ ’ በደንበኞቹ ዘንድ ያተረፈውን መልካም ስም እና ዝም በመጠበቅ ለአመታት መዝለቅ የቻለ ነው።
በአዲስ አበባ ሳር ቤት ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ገባ ብሎ ካለው የመጀመርያ ቅርንጫፍ በተጨማሪ ቦሌ ከዮድ አቢሲኒያ ፊት ለፊት ፣ በመቐለ ሐውልቲ ፕላኔት ሆቴል ፊት ለፊት እንዲሁም 4ኛ ቅርንጫፉን ሲኤምሲ መሪ አካባቢ ለደንበኞች በሚመች አማካይ ቦታዎች ቅርንጫፎችን በመክፈት አገልግሎቱን አስፋፍቷል።
ቅዳሜ መስከረም 11 ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሀገራዊ በሆነ ግብአት የ22 አመታት አገልግሎት የሰጠው 'ፋና የወይባ ጡሽ ፦
- የበርካቶች የማህፀንና የወገብ ጤና የተመለሰበት ፤
- የቆዳቸው ውበት የተጠበቀበት ፤
- በኑሮ ውጣ ውረድ የደከመ ሰውነታቸው ዘና ያለበት መሆኑ በደንበኞች ተመስክሮለታል ተብሏል።
ወይባ ፤ ቦለቂያ ፤ ጡሽ እና የመሳሰለው አካባቢያዊ መጠሪያና ስያሜ ተሰጥቶት በተለያዩ የሃገራችን አከባቢዎች ጤናንና ውበትን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፉ በመጡ እና ረጅም ዘመን በዘለቁ ማኅበረሰባዊ እውቀቶች ተፈጥሯዊ የሆኑ እጽዋቶችን የመጠቀም
የቆየ ባህላዊ ሥርዐትና ወግ አላቸው።
ይህን የቆየ ሀገረሰባዊ እውቀት ወደ ከተማ በማምጣት ፣ በማስተዋወቅና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት 'ፋና የወይባ ጡሽ ' ላበረከተው አስተዋፅኦ '' የባህል ጥበባት ለማህበረሰብ ትስስርና ለሀገረ‐መንግስት ግንባታ " በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በተካሄደው ሀገር አቀፍ የባህል ፌስቲቫል፣ ኤግዚቢሽን እና የኪነ-ጥበብ ስነ-ጥበብ ፈጠራ ውድድር እና ትዕይንት ላይ በላቀ ደረጃ ሰኔ 2016 ተሸላሚ ሲሆን ሌሎች ሽልማቶችንም አግኝቷል።
በእለቱ የፋና ወይባ ጡሽ አጀማመርና ስለአገልግሎት አሰጣጡ የተዘጋጀ መፅሄት ይፋ ተደርጓል።
@tikvahethiopia

" ተለዋጭ መጓገድ ለመገንባት ጥረት እያደረግን ነው " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
ከአዲስ አበባ - ጅማ - መቱ - ጋምቤላ መስመር በቡኖ በደሌ ዞን ደዴሳ ወረዳ ከጅማ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለው መጓገድ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክጓያት መንገዱ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል።
ችግሩ ለመቅረፍ በኢትዮጵያ መንገዶ አስተዳደር የጅማ መጓገድ ጥገና ዲስትሪክት ጊዜያዊ ተለዋጭ መጓገድ ለመገንባት ጥረት እያደረገ እንደሆነ አመልክቷል።
በመኾኑም ተለዋጭ መጓገድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ ለትራፊክ ክፍት እስኪደረግ ድረስ አሽከርካሪዎች በትዕግስት እንይጠባበቁ ጠይቋል።
ከመሃል ሃገር ለሚነሱ _ አሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ - ነቀምት - በደሌ - መቱ - ጋምቤላ መሥመርን በአማራጭነት እጓዷጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

#TigrayRegion
" የሚሰራጨው ወሬ መሬት ላይ የሌለ ነው " - የምስራቃዊ ዞን አስተዳደር
በትግራይ ዛላኣንበሳና ኢሮብ የኢትዮ-ኤርትራ ደንበር ከቆየው የተለየ እንቅስቃሴ እንደሌለ የምስራቃዊ ዞን አስተዳደር አሳውቋል።
አሁንም ላለፉት 4 ዓመታት አከባቢ በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ስምንት የሚደርሱ የጉሎመኻዳና የኢሮብ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ላይ የታየ አዲስ ለውጥ እንደሌለ ተመላክቷል።
ከሰሞኑን አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች " በትግራዩ ዛላኣንበሳ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከቆየው የተለየ እንቅስቃሴ አለ " ዘገባ ሲያሰራጩ ነበር።
የአከባቢው ነዋሪዎችና የትግራይ ምስራቃዊ ዞን አስተዳደር ግን ይህ ሀሰት ነው ሲሉ መልሰዋል።
ነዋሪች እና የዞኑ አስተዳደር " በዛላኣንበሳ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከቆየው የተለየ እንቅሰቃሴ የለም " ብለዋል።
የምስራቃዊ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህ/ቤት የጉሎመኻዳና ኢሮብ ወረዳ አስተዳደሮች ጠቅሶ ባሰራጨው መረጃ ፥ አከባቢዎቹ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊትም ሆነ በኋላ በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።
" ሉኣላዊ ግዛት ያለመከበር ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ባላፉት ቀናት በአከባቢው አዲስ ወታደራዊ እንቅሰቃሴ የለም " ብሏል።
" በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች በዛላኣንበሳና በኢሮብ አከባቢ ከኤርትራ መንግስት በኩል የተለየ እንቅሰቃሴ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው ወሬ መሬት ላይ የሌለና የአከባቢው ነዋሪዎች ይሁንታ ያለገኘ ነው " ሲል አክሏል።
አስከ አሁን ድረስ ዛላኣንበሳ ከተማ ጨምሮ 5 የጉሎመኸዳ ወረዳ የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም ከኢሮብ ወረዳ 4 የገጠር ቀበሌዎች በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ፅ/ ቤት አስታውሷል።
ዞኑ " በሬ ወለደ ወሬ የሚናፍሱ ሚድያዎችና የማህበራዊ ትስስር ገፅ ፀሃፊያን ከድርጊታቸው እንደዲታቀቡ እናሳስባለን " ሲል አስጠንቅቋል።
በቅርብ እና በረቁ የሚገኙ የዓጋመና አከባቢዋ ተወላጆችና ወዳጆች በየዓመቱ በትግራይ ደረጃ በዓዲግራት ከተማ የሚከበረው የመስቀል በዓል ለማከበር እንዲታደሙ ጥሪ በማቅረብ አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ እንዳለ አመልክቷል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#ቀረጥ_ነጻ
ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ አውጥቷል።
ይኸው መመሪያ " መመሪያ ቁጥር 1023/2017 " ይሰኛል።
በዚህ መመሪያ መሰረት ፥ ለህብረተሰቡ በነጻ የሚሰጡ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንዲሁም በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች የማህበራዊ ልማት ቀረጥ የተጣለበትን አላማ ለማሳካት የሚያግዙ በመሆኑ ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል።
ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የተደረጉ እቃዎች ?
የሚከተሉት እቃዎች ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር ይገባሉ፡፡
1. ለሚከተሉት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች :-
ሀ/ በመንግስት ባለቤትነት ስር ያሉ ወይም ለህብረሰሰቡ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ :
- የትምህርት ተቋማት፣
- የጤና ተቋማት፣
- የሕጻናት፤ የሴቶች፤ የአረጋውያን፣ የአእምሮ ህመምተኞች እና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅቶች
ለ/ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚሰጡ ድርጅቶች ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች
2. ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው ወደአገር እንዲገቡ የተፈቀደ እቃዎች።
3. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋሞች፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት እና ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሕግ በተፈቀደው መሰረት ወደ አገር የሚያስገቧቸዉ የመከላከያ እና የህዝብ ደህንነት መሳሪያዎች፣ ለነዚሁ አገልግሎት የሚዉሉ ክፍሎችና እና አክሰሰሪዎች፡፡
4. በብሔራዊ ባንክ ወደ ሀገር የሚገቡ ሳንቲሞች፣ የገንዘብ ኖቶች እንዲሁም የብርና የወርቅ ጠገራዎች፡፡
ከቀረጥ ነፃ #የማይሆኑ እቃዎች ምንድናቸው ?
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች ከማህበራዊ ቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ #አይችሉም።
ሀ/ ከ8 መቀመጫ በታች ያላቸው አውቶሞቢሎች እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።
ለ/ ባለአንድ ወይም ባለሁለት ጋቢና ፒካፕ ተሽከርካሪዎች እና የእነዚህ መለዋወጫዎች።
ሐ/ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችና መሣሪያዎች።
በዚህ መመሪያ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ሆነው ሊገቡ የሚችሉ እቃዎች ማስረጃዎች ማቅረብ የግድ ይላል።
ምን አይነት ማስረጃዎች መቅረብ አለባቸው ?
1. እቃዎቹ በእርዳታ የተገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ የእርዳታ የምስክር ወረቀት።
2. የእቃዎቹን ዝርዝር እና ዋጋ የሚያሳይ ኢንቮይስ፣
3. እቃዎቹ ለተገለጸው አላማ የሚውሉ መሆኑን እንዲሁም ስለእቃዎቹ አጠቃቃም ለገንዘብ ሚኒስቴር እና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሪፖርት የሚቀርብ መሆኑ የሚያረጋግጥ አግባብ ባለው ከመንግስት መስሪያ ቤት የተጻፈ የድጋፍ ድብዳቤ።
#TikvahEthiopia #MinistryofFiance

Discover the unique opportunity to build a high-impact venture with the Jasiri Talent Investor Programme - Cohort 7!
This fully-funded 13-month program provides comprehensive support for aspiring entrepreneurs, including an introduction to understanding your 'why' and intensive residential training in Rwanda to help you dive deep into solving the problem you aim to address. You’ll also receive mentorship, coaching, and venture creation support.
Apply now and experience the difference!
👉🏾 https://bit.ly/3A8rxtV
For more information, Join our telegram channel 👉🏾 @Jasiri4africa

#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!
የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡
የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡
- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)
- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (No.9) በታጣቂዎች የታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከምን ደረሱ ? ሁለት አውቶብስ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት " ገርበ ጉራቻ " ላይ መታገታቸው ይታወሳል። የታገቱት ሰኔ 26/2016 ዓ/ም ረፋድ 4 ሰዓት ገደማ ሲሆን፣ ከታገቱ ወር አልፏቸዋል። ሁለት ታጋቾች 50 ሺህ እና 300 ሺህ ብር ከፍለው ከእገታ መለቀቃቸውን፣…
#Update (No.10)
“ ግማሽ፣ ግማሽ ሚሊዮን ብር ከፍለን ልጆቻችንን በገንዘባችን ገዝተናል፡፡ አሁንም ያልተለቀቁ ልጆች አሉ ” - የተማሪ ወላጆች
ትህምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ የነበሩ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ሁለት አውቶብስ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በ“ሸኔ”
ታጣቂዎች እንደታገቱ የተሰማው ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ነበር፡፡
ተማሪዎቹ የታገቱት “ገርበ ጉራቻ” የሚባል ቦታ ሲደርሱ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ገደማ እንደነበር ከገለባ ክምር ተደብቆ ያመለጠ ተማሪ በወቅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጰያ መግለጹ ይታወሳል፡፡
ከዚያ በኋላ ደግሞ 50 ሺሕ እና 300 ሺሕ ከፍለው የተለቀቁ ተማሪዎች እንዳሉ፣ ታጣቂዎች የጠየቁትን ገንዘብ ካልሰጡ ታጋች ተማሪዎቹን እንደማይለቋቸው በመግለጻቸው ወላጆች አቅም ስለሌላቸው ባነበር አሰርተው ለልማና አደባባይ ለመውጣት መገደዳቸውንም አሳውቀናችሁ ነበር፡፡
ከዚያ በዘለለም ከሳምንታት በፊት የተወሰኑ ተማሪዎች ገንዘብ ከፍለው ከእገታ መለቀቃቸውን አንድ ከእገታው ያመለጠ ተማሪ በቲክቫህ በኩል መግለጹ ይታወሳል፡፡
የታጋቾቹ ጉዳይ አሁንስ ከቶ ከምን ደረሰ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካነጋገራቸው የታጋች ቤሰቦች መካከል በደቡብ ክልል የሚገኙት፣ “ ግማሽ፣ ግማሽ ሚሊዮን ብር ከፍለን ልጆቻችንን በገንዘባችን ገዝተናል፡፡ አሁንም ያልተለቀቁ ልጆች አሉ ” ብለዋል፡፡
በታጣቂዎቹ ታግተው የነበሩ የደቡብ ክልል ተማሪዎች ቤተሰብ የትም አምጥተው ገንዘቡን በመላካቸው እንደተለቀቁ ገልጸው፣ ልመና በወጡበት ወቅት እርዳታ ላደረጉላቸው ሁሉ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ትምህርት እንዲማሩ የላኳቸው፣ እራሳቸው እየከፋቸው በተቻላቸው መጠን ምንም ሳያጎድሉ ያሳጓቸው ልጆቻቸው ሰውነታቸው ተጎሳቁሎ፣ ድብደባና ረሃብ ተፈራርቆባቸው እንደገኟቸው አስረድተው፣ የሀገር ተረካቢ ትውልድን በዚሁ መልኩ ማሰቃየት ጥሩ ዓርዓያ የለውም ሲሉ ተናግረዋል።
የተደፈሩ ሴት ተማሪዎች እንዳሉ የገለጹት የተማሪ ወላጆች፣ " እነዚህ ተማሪዎችን በድጋሚ ወደ ትምህርት የምንልክበት፣ እነርሱስ የሚሄዱበት ምን አይነት ሞራል ይኖራል ? " ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ከእገታ የተለቀቁ ተማሪዎች ስልካቸውንና ልባሳቸውን ሙሉ እንደተዘረፉም ገልጸዋል፡፡
#TikvahEthiopiaFamlyAA

7 ዓመት ?
" ለአራት በመሆን 15 ዓመት ታዳጊ አስገድደው የደፈሩ ተከሳሾች በ7 አመት ጽኑ እስራት ተቀጡ " ይለናል ከአመያ ወረዳ የተገኘው መረጃ።
ተከሳሽ ፦
- አስፋቸው አለሙ፣
- አሻግሬ አበራ፤
- ማቲዎስ ደዋና
- አስማማው አሉላ የተባሉ ግለሰቦች (ከላይ ፎቷቸው ተያይዟል) በአመያ ዙሪያ ወረዳ ኦፓላሼ ቀበሌ በቀን 27/10/2016 ዓ.ም በግምት 8:00 አካባቢ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ኦፓላሼ ቀበሌ እየሄደች የምትገኝ የ15 አመት ታዳጊ አስገድደው ደፍረዋል።
" ግለሰቦቹ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመሀኘታቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 7 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥተዋል " ተብሏል።
አራተኛ ተከሳሽ ዕድሜው 10-13 ዓመት ውስጥ መሆኑ ተከሳሹ አዋቂ እስረኞች ጋር አብሮ መታሰር የማይችልና እንደዚህ ዓይነት ታዳጊ እስረኞችን የሚቀበል ማረምያ ተቋም ባለመኖሩ ቤተሰቡ ፈርሞ ወስዶት ክትትልና በቁጥጥር እንዲያደርግ በማለት ፍርድ ቤት ወስኗል።

' ስካይ ላይት ሆቴል ' ውስጥ ተሸሽገው ነበር የተባሉ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ኃላፊ ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ፀጋዬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ።
ግለሰቡ ሲፈለጉ ቆይተው ዛሬ ' ስካይ ላይት ሆቴል ' ውስጥ ተደብቀው ከነበሩበት መያዛቸውን የከተማ አስተዳደሩ አመልክቷል።
" ተጠርጣሪው በኮሪደር ልማት ስም ከመንግስት አሰራር እና ውሳኔ ውጪ #በመደራደር ባልተገባ መንገድ ለግል ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የካሳ ግምት በማናር ውስን የሆነዉን የህዝብ እና የመንግስትን መሬት ከአሰራር ውጪ በማሰተላለፍ ለግለሰቦች አላስፈላጊ ጥቅም በማዋል ተጠርጥረው " መያዛቸው ነው የተገለጸው።
በተጨማሪ በክ/ከተማው ወረዳ 4 ዉስጥ በኮሪደር ልማት ኘላን ልማት ውስጥ የማይካተት ከመመሪያና አሠራር ዉጪ 6 መኖሪያ እና አንድ የንግድ ቤት የሆነውን ከ ' ዋይልድ አፓርትመንት ' የተባለ ህንፃ ባለቤት ጋር ተመሳጥረው ቤቶቹን እንዲፈርሱ በማድረግና ለህንፃው ማስፋፊያ እንዲሆን የሰጡ መሆኑ ተመላክቷል።
የመንግስት ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ግለሰቦችም የእቃ የማጓጓዥያ ሳይከፈል እንዲነሱ በማድረጉ እንዲሁም " ምትክ ቦታ እስጣቿለው " ፤ " አንደኛ ቦታ አስቀይርላቿለው " እና የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን በማድረግ ህብረተሰቡ ሲያደናግሩ ፤ ያልተገቡ ጥቅሞችን ሲያደርጉ ነበር ተብሏል።
ከተሸሸጉበት ' ስካይ ላይት ሆቴል ' ውስጥ የተያዙት ግለሰቡ " ከሀገር ውጪ ወተዋል " አስብለው እንደነበር ተገልጿል።

ቤንዚን ?
በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል።
ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል።
በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው።
በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።
በሜትር ታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ዜጎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት ተቸግረዋል። ቀናቸውን ሁሉ በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ናቸው።
በክልል ከተሞችም የቤንዚን ነገር ብሶበታል።
ቀድሞውንም ቤንዚን በማደያ እንደልብ በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የማይቻልባቸው የክልል ከተሞች አሁንም ችግሩ እንዳለ ነው።
በክልል ከተሞች አሽከርካሪዎች ቤንዚን በማደያ " የለም " የሚባሉ ሲሆን በጀርባ ግን በየቦታው በህገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸበቸብ ይታያል።
ይህ ህዝብን እያማረረ ያለው የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሰንሰለት መቼ እንደሚበጠስ አይታወቅም። ከዚህ ጀርባ እጃቸው የረዘመ አካላት መኖራቸውን ግን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ።
ቤንዚን በክልል ከተሞች ከማደያ ውጭ በእጥፍ ዋጋ ነው የሚቸበቸበው።
#TikvahEthiopia

#DStvEthiopia #Gojo
🔥ከባድ ትንቅንቅ የማያጣው የ ማንቸስተር ሲቲ ከ አርሰናል በጎጆ ፓኬጅ
🏆 አስተማሪው ከ ተማሪው ጋር ይገናኛሉ! የቱ ቡድን 3 ነጥብ ይዞ ወደ ቀጣዩ ሳምንት ማለፍ ይችላል?
ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በጎጆ ፓኬጅ በቀጥታ ይከታተሉ
🎉ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ወደ ጎጆ በማራዘም ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃትእስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው

#ዋሪት !
ዘወትር የደንበኞቻችንን ፍላጎት ማርካት ቀዳሚ የሚያደርገው ዋሪት ዛሬም የበርካቶቻችሁን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የአዲስ ዓመትን ቅናሽ እስከ መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ማራዘሙን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው። የዋሪትን የውሃ ማጣሪያ ለየት የሚያደርገው ከሽያጭ በኋላ ለሚኖር ብልሽት አስተማማኝ የጥገና እና የመለዋወጫ አገልግሎት መስጠታችን !
ትክክለኛ ምርጫ!
ለተጨማሪ መረጃ: ☎️ 0911210706 / 07