Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara " ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ነው እቅድ የተያዘው ከነሐሴ 20/2016 ዓ/ም ጀምሮ የተመዘገቡት ግን 1.7 ሚሊዮን ናቸው - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በየጊዜው የተኩስ ልውውጥ የሚስተዋልበት አማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዘገብ እንዳቀደ፣ ከነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ…
#Amhara

“ የእኛ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶቻችን ደረጃ 2 ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ደረጃቸው ዝቅተኛ ግን መማር ማስተማሩን ማስኬድ የሚችሉ እንደማለት ነው ” - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በአማራ ክልል በተለይ በጸጥታ ችግር ሳቢያ የግብዓት እጥረት ያለባቸው ትምህርት ቤቶች እንዳሉ፣ ይህም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ማነቆ እንደሆነባቸው ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገጸዋል፡፡

ለአብነትም እንደ መጽሐፍት፣ ወንበር መሰል ቁሳቁሶች እንደሌሉ፣ የወደሙ ትምህርት ቤቶች አለመጠገን፣ በግጭት የቀጠና ውስጥ የሆኑ አቅመ ደካማ ወላጆች ደግሞ ለልጆቻቸው እንኳ የትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዳልቻሉ ነው ያስረዱት፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጥ የክልሉን ትምህርት ቢሮ ጠይቋል፡፡

ቢሮው ምን ምላሽ ሰጠ ?

“ የግብዓት እጥረት አለብን ያሉ ትምህርት ቤቶች ይኖራሉ፡፡ ትክክል ነው፡፡ የግብዓት እጥረታቸው በሁለት መንገድ ነው የሚፈታው፡፡

አንደኛ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በክልል ደረጃ ደግሞ የሚሟሉ አሉ፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍት በክልል ነው የምናሟላው፡፡

ከ14 ሚሊዮን በላይ መጽሐፍት ታትመው ስርጭት ተደርጓል፡፡ አሁንም በቀጣይ የሚሰራጩ አሉ፤ ከ1 ቢሊዮን በላይ በጀት የክልሉ መንግስት መድቦ አሁንም የሚታተሙ መጽፍት አሉ፡፡

እነርሱን አሳትመን እናሰራጫለን፡፡ የመምህራን ቅጥርም እናሟላለን፣ ትክክል ነው፡፡

የእኛ ክልል ትምህርት ቤቶች ሙሉ ግብዓት የተሟላላቸው፣ ስንታንዳርዳቸውን ያሟሉ አይደሉም፡፡

ትምህርት ቤቶች በ4 ደረጃ ይከፈላሉ፡፡ ደረጃ 1፣ 2፣ 3 እና ደረጃ 4 ተብለው፡፡ ደረጃ 4 የሚባል ትምህርት ቤት በክልሉ የለንም፡፡

ደረጃውን ያሟላ በጣም ኢንተርናሽናል እንደማለት ነው፡፡ ደረጃ 3 የሚባለው ደግሞ ለተማሪዎች መማር ማስተማር የተሻለ የሆነ ትምህርት ቤት ማለት ነው፡፡

የእኛ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶቻችን ደረጃ 2 ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ደረጃቸው ዝቅተኛ ግን መማር ማስተማሩን ማስኬድ የሚችሉ እንደማለት ነው፡፡ ይሄ ማለት ብዙ ግብዓት የሚጎድላቸው ናቸው፡፡

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 3ቱም ሳይንስ ቤተ ሙከራ እንዲሟላ፣ ደረጃውን የጠበቀ የኳስ ሜዳ እንዲኖረው፣ አጥር እንዲኖረው፣ ስታንዳርዱን እንዲያሟላ፣ ፋሲሊቲውን በማሟላት ረገድ መስራት የሚጠይቀን ሥራ አለ፡፡

እሱን በእቅድ ለመምራት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ግን ሙሉ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ የሚጠይቅ ሥራ ነው፡፡

የእኛን ትምህርት ቤቶች በስንት ዓመት እንቀይራቸዋለን ደረጃቸውን ለማሻሻል ብለን አንድ በጣም ትልቅ የለውጥ እቅድ አቅደን ወደ ሥራ በገባን ማግስት ነው የጸጥታው ችግር የተፈጠረው፡፡

በዚህ ዓመት ውስጥ ትምህርት ቤቶቹን እንቀይራለን ብለን ነበር ዞሮ ዞሮ ወደ ሥራ መግባት አልተቻለም ”
ብሏል፡፡

የግብዓት እጥረት ላለባቸው ከባለሀብቶችና ባለንብረቶች ድጋፍ የማሰብሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" መፍትሄ ሳይዘጋጅና በቂ ጥናት ሳይደረግ የተላለፈው ውሳኔ ፍጹም አግባብነት የሌለው ነው " - የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አካላት

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አማራጭ መፍትሔ ሳያዘጋጅና በቂ ጥናት ሳያካሂድ " ከ30 ዓመት በላይ አገልግሎት የሰጡ ድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪዎች፣ አገልግሎት እንዳይሰጡ " ብሎ ውሳኔ አስተላልፏል ፤ ይህ ደግሞ አግባብነት የሌለውና ከትራንስፖርት ዘርፍ የሚገኘውን ኢኮኖሚዊ ጥቅም የሚያሳጣ ነው ሲሉ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ቅሬታቸውን አቀርበዋል።

የኅብረት ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር መሥራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ባይሳ አየለ ምን አሉ ?

" የትንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ግልጽ የሆነ መመርያ ሳያወጣ፣ ለዓመታት አገልግሎት የሰጡ ድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ብሏል። ይህ አግባብነት የለውም፡፡

ሚኒስቴሩ በዋናነት እነዚህ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ያለበት ምክንያት፣ የአየር ብክለትን ለመከላከል አስቦ ነው። መንግሥት እንዲህ ዓይነት አሠራር ሲዘረጋ የብድር አገልግሎትና ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይኖርበታል።

በኢትዮጵያ 60 በመቶ የሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪዎች ከ30 ዓመታትና ከዚያ በላይ አገልግሎት የሰጡ ናቸው፡፡ ተሽከርካሪዎቹ ደግሞ በምን ዓይነት ሁኔታ ነው የሚቀጥሉት የሚለውን መንግሥት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት ማድረግ አለበት " ብለዋል።


የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ምን አሉ ?

" ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚሆን የመሠረተ ልማት በአግባቡ ሳይሟላ መንግሥት በፍጥነት ተሽከርካሪዎቹ ወደ #ኤሌክትሪክ ይቀየሩ ማለቱ ትክክለኛ አካሄድ አይደለም።

በአሁኑ ወቅት ዕድሜያቸው ከ30 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪዎቹ የማጓጓዝ አገልግሎት እንዳይሰጡ ፈቃድ በመከልከላቸው፣ እንዲቆሙ ተገደዋል።

ተሽከርካሪዎቹ በብቃትና በጥንካሬ የሚሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ አስተማማኝ አቅርቦት እስኪኖር ድረስ ተሽከርካሪዎቹ እንዲሠሩ መደረግ አለበት።

ዓመታዊ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለማደስ ጥያቄ ያቀረቡ አብዛኛዎቹ አክሲዮን ማኅበራት ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች መግዛት ባለመቻላቸው ፈቃዳቸው አልታደሰም።

በዚህ ምክንያት አክሲዮን ማኅበራቱ ለጭነት አገልግሎት ሥራ በማንኛውም ጨረታ እንዳይሳተፉ ስለሚከለከል ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች ለመግዛት ያለው የአቅም ውስንነት ታሳቢ በማድረግ የጊዜ ገደብ እንዲራዘምላቸው መደረግ ይኖርበታል።

ከ30 ዓመታት በላይ አገልግሎት የሰጡ ድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ፣ የተሻለ አሠራር እንዲፈጠርና የንብረቱ ባለቤቶችም ምቹ ሁኔታ እንዲያገኙ ለገንዘብ ሚኒስቴር፣ ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት በተለያዩ ጊዜያት ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ አልተገኘም " ብለዋል።

(ከሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
ባለ ብዙ ቀለሟ ኢትዮጵያ !

(አሁን ላይ እየተከበሩ ያሉና በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ በዓላት)

የሀዲያ የዘመን መለወጫ ' ያሆዴ '
የወላይታ የዘመን መለወጫ  ' ዮዮ ጊፋታ '
የካፊቾ የዘመን መለወጫ ' ማሽቃሮ '
የጋሞ የዘመን መለወጫ ' ዮ ማስቃላ ' 
የጊዲቾ የዘመን መለወጫ  ' ባላ ካዳቤ '
የዘይሴ የዘመን መለወጫ ' ቡዶ ኬሶ '
የቦሮ ሺናሻ የዘመን መለወጫ ' ጋሪ ዎሮ '
የጎፋ የዘመን መለወጫ ' ጋዜ ማስቀላ '
የኦይዳ የዘመን መለወጫ ' ዮኦ ማስቃላ '
የከምባታ ዘመን መለወጫ ' መሳላ '
➡️ የጠምባሮ ዘመንድ መለወጫ ' መሳላ '
የዶንጋ ዘመን መለወጫ ' መሳላ '
የየም ዘመን መለወጫ ' ሄቦ '

ይህ የመስከረም ወር በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ነው።

#ኢትዮጵያ

እንኳን አደረሳችሁ ፤ መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
🔈#የወጣቶችድምጽ

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር ያለባት ሀገር ናት።

ካለው ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር አንጻር ያለው የስራ እድል አነስተኛ ነው። የስራ እድል ቢገኝ እንኳን የሚከፈለው ክፍያ ዝቅተኛ በሆኑ ህይወትን መቀየር እና ያሰቡትን ማሳካት ፈተና ነው።

በዚህ ምክንያት ብዙ ወጣቶች የተሻለ ኑሮና ገቢ ፍለጋ ከሀገር ለመውጣት ይፈልጋሉ።

ወጣቶቹ ያደጉ ሀገራት / በኢኮኖሚ የተሻሉ ሀገራት ሄደው ሰርተው ፣ ጥሩ ገቢ አግኝተው ለራሳቸው ተርፈው ፤ ዋጋ ለከፈለላቸውና ተቸግሮ ላሳደጋቸው ቤተሰባቸው እንዲሁም ለህብረተሰባቸው መድረስ እና ' አለሁላችሁ ' ማለት ይፈልጋሉ።

እድሜ ቆሞ አይጠብቅምና ፈጣሪ በሰጣቸው የወጣትነት ጊዜ ጉልበትና እውቀታቸውን ተጠቅመው ቢያንስ እነሱ ባይደላቸው ለልጆቻቸው የሚሆን ነገር ማስቀረት ትልቁ ምኞታቸው ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወጣቱ ዘንድ ከሀገር ወጥቶ ለመስራት የሚታየው ፍላጎት እጅግ በጣም መጨመሩን በተለያየ መንገድ ለመገንዘብ ችሏል።

በተለይ ወደ ካናዳ፣ ጣልያን፣ አሜሪካ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሳዑዲ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ሮማኒያ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ... ሌሎችም የውጭ ሀገራት በትምህርት እና በስራ ለመሄድ ፕሮሰስ የሚያደርጉ በርካታ ወጣቶችን ማነጋገር ችለናል። ሀሳባቸውንም ተቀብለናል።

አንድ ካናዳ ለመሄድ በዝግጅት ላይ ያለ ወጣት ፥ " እኔ ከዩኒቨርሲቲ በትልቅ ውጤት ከተመረቅኩ አንስቶ ባለፉት 3 ዓመታት ያልሞከርኩት የስራ ሙከራ የለም ባለሁበት አካባቢ አጠቃላይ የቅጥር ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ሆኖብኝ በግሌ ለመንቀሳቀስ ሞክሬ አይደለም ህይወቴን ላሻሻል ዳግም የቤተሰብ እጅ ጠባቂ ሆኛለሁ " ሲል ገልጿል።

" በዚህም ምክንያት ከሰዎች ብር አፈላልጌ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ያለውን ነገር ሁሉ ለመስራት እየጣርኩኝ ነው " ብሏል።

ሌላኛዋ ወጣት በተመሳሳይ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ስትሆን " በተግባር የስራ እድል ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ ነው ፤ የሚሰራው በትውውቅ በብሄር እና በዝምድና ነው እንዴት ይሄንን ማለፍ እንዳለበኝ አላውቅም " ብላለች።

ለበርካታ ወራት እዚሁ ሀገር ውስጥ ሆኖ ሰርቶ ለመቀየር በሚል ብዙ ሙከራ ብታደርግም ስላልተሳካ የውጭ ሀገር እድል እየሞከረች እንደሆነ አመልክታለች።

ሌላኛው ቃሉን የሰጠ ክሩቤል የተባለ ወጣት ፥ ምንም እንኳን በስራ ላይ በሚገኝም በወር የሚያገኘው ገቢ አነስተኛ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ትዳር ይዞ፣ የራሱን ሃሳብ አሳክቶ፣ ለቤተሰብ ፣ ለወገን ተርፎ መኖር የማይታሰብ ስለሆነበት ውጭ ሀገር ሰርቶ የመመለስ ፍላጎት እንዳለውና ይህን ለማድረግ እየሞከረ እንደሆነ ጠቁሟል።

ሌሎች ያናገርናቸው ወጣቶችም ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ፣ ስራም ለማግኘት የሚያደርጉት ጥረት ተስፋ ስላስቆረጣቸው ውጭ ሀገር ለመሄድና ማንኛውም ስራ ለመስራት ሲሉ እድላቸውን እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

" ማንኛውም ሰው ሀገሩን ጥሎ የሚወጣው ሀገሩን ጠልቶ ሳይሆን የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ነው " የሚሉት ወጣቶቹ በዚህ እድሜ ካልሰራን መቼ ልንሰራ ነው ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ቃላቸውን የሰጡት ወጣቶች ፦
- በሀገር ውስጥ ያለው የስራ እድል እንዲሰፋ ፣
- በትውውቅ፣ በብሄር፣ በዝምድና የሚፈጸም ቅጥር እንዲቆም
- በገንዝብ የሚፈጸም ቅጥር እንዲቀር ካልተደረገ ወጣቱ እዚህ ሰርቶ የመለውጥ ተስፋው እንደሚሞት አስገንዝበዋል።

ሌላው " በሙስና የሚዘረፈው ብር ብዙ ነው እሱን ተከላክሎ ለወጣቶች አንዳች ነገር እንኳ ማድረግ ይቻላል ፤ ግን ዘራፊው የበለጠ ሃብቱን እያካበተ ወጣቱ የበለጠ ተስፋ እየቆረጠ ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ በየመስኩ ሙስና መንሰራፋቱን ስራ ለመቀጠር፣ ጉዳይ ለመጨረስ እጅ መንሻ ካልተሰጠ እንደማይሆን በተግባር እንደተመለከቱ ጠቁመው ይሄ እያደር መዘዙ የከፋ ይሆናል ሲሉ አሳስበዋል።

" በሙስና በየአመቱ የሚዘረፈው የዚህች ሀገር ሃብት ለስንት ወጣቶች ህወይት መቀየሪያ ይበቃ ነበር ? " ሲሉም ጠይቀዋል።

ወጣቶች በሀገራቸው ላይ ሰርተው እንዲቀየሩ ምቹ ሁኔታ ከሌለ፣ እድሎችና ለስራ ለፈጠራ የሚሆን ሀቀኛ መደላደሎች ካልተፈጠሩ በሀገር ሰርቶ መቀየር አስቸጋሪ ስለሚሆን ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል።

" ፖለቲከኞችም ሆኑ ለሀገር እናስባለን ተፅእኖ ፈጣሪ ነን የሚሉ ሰዎችም የወጣቶችን የኢኮኖሚ ጉዳይ አጀንዳ ሊያደርጉ ይገባል ዘውትር እነሱን የሚጠቅም ነገር ካልሆነ የመናገር እና ተፅእኖ የመፍጠር ፍላጎት የላቸውም " ሲሉ ተችተዋል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ አ/አ)

#ቲክቫህኢትዮጵያ #የወጣቶችድምጽ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#SafaricomEthiopia

የሙዚቃ ኮከቦቹን በላይካችን ምርጥ 20 ውስጥ እናስገባቸው! 👏🏽 

እስከ መስከረም 20 ብቻ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ #Safaricomet ታግ እናድርግ

እንዝፈን! እንፖስት! እናሸንፍ!
መልካም ዕድል!

#1Wedefit #FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
ፎቶ፦ ከአዳማ ወደ ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል፡፡

የባቡር ትራንስፖርት ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ውስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ የሚያገለግል ነበር።

የአገልግሎቱ መጀመር ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ይጨምራል ፤ የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል ብለዋል።

#Ethiopia #EngTakelUma

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
NGAT_EXAM_SCHEDULE_FFF1.xls
#NGAT

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የማለፊያ ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ እንደሆነ ተገልጿል።

የፈተናው ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

በ2017 ዓ.ም የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለሚማሩ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

የተፈታኞች ውጤት ዛሬ ይፉ የሆነ ሲሆን ተፈታኞች የምዝገባ ቁጥር / Username በማስገባት ውጤታቸው በተከታዩ ሊንክ መመልከት እንደሚችሉ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ውጤት መመልከቻ - https://result.ethernet.edu.et/ngat_result

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፅ ነገር #2 ? ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር በባህር በር ጉዳይ የመግባቢያ ስምምነት በተፈራረመች ወቅት ሰዓታት ሳይቆጠር ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ነበረች። ከሶማሊያ ጋር ተደዋውላም  " አይዞሽ እኔ አለሁልሽ፤ በማንኛውም መንገድ አብሬሽ ቆማለሁ " ብላት ነበር። ባለስልጣናቶቿም ኢትዮጵያ ለሶማሊያን ስንትና ስንት የደም ዋጋ እንዳልከፈለች ዛሬ ደፍረው " ኢትዮጵያን እንዳለመረጋጋት ምንጭ "…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግብፅ ?

ግብፅ፣ ሶማሊያን እያስታጠቀች ነው።

ሶማሊያ የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከግብፅ እንደተሰጧትና ተጨማሪ መሳሪያዎችን በቀጣይነት እንደምትጠብቅ አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተናግረዋል።

ስማቸው ሳይጠቀስ ለቢቢሲ ሶማሊኛ የተናገሩ ባለሥልጣን ባለፉት ቀናት በመርከብ ተጭነው ወደ ሞቃዲሾ ወደብ የደረሱት የጦር መሳሪያዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

እነዚህ መሳሪያዎች የሶማሊያ መንግሥት ጦር የሚታጠቃቸው ነው ብለዋል።

ወደ ሶማሊያ የገቡት የጦር መሳሪያዎች ፦
- ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤሎች፣
- መድፎች
- ሌሎች አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች መሆናቸውን ባለሥልጣኑ ጨምረው ተናግረዌ።

ይህንን ከፍተኛ የሆነ መጠን ያለውን የጦር መሳሪያ በሞቃዲሾ ወደብ በኩል ወደ ሶማሊያ መግባቱን በተመለከተም የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ናቸው።

በርካታ የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን የጦር ማሳሪያዎቹ ወደ ሞቃዲሾ ወደብ ደርሰው የተራገፉት #በግብፅ መርከብ አማካኝነት መሆኑን ዘግበዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ከትናንት እሁድ ጀምሮ የተለያዩ ዓይነት ያላቸው ከባድ መሳሪያዎች እና በጭነት መኪና ተሸፍነው የሚጓዙ ወታደራዊ ቁሶች በሞቃዲሾ ጎዳናዎች ላይ ሲተላለፉ ታይተዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣን አሁን ከገባው የጦር መሳሪያ ጭነት በተጨማሪ በቀጣይነት ታንኮችን እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

ይህ እየሆነ ያለው ግብፅ ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ደርሳ ሠራዊቷን በአገሪቱ ውስጥ ለማሰማራት ፍላጎት እንዳላት መግለጿን ካሳወቀች በኃላ ነው።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሁለት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የጦር መሳሪያ ጭነው ሞቃዲሾ መግባታቸው የሚዘነጋ አይደለም። #ቢቢሲሶማሊ

@tikvahethiopia
2024/11/15 09:48:42
Back to Top
HTML Embed Code: