Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዮናስንጉሰ #ሔለንበርኸ👏 በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሀገሪቱ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው የትግራይ ፣ የቓላሚኖ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪው ዮናስ ንጉሰ ነው። በትግራይ ሀገር አቀፉ ፈተና ከ700 መሰጠቱ ይታወሳል። ተማሪ ዮናስ ንጉሰ ከ700ው 675 በማምጣት በሀገር ደረጃ ታሪካዊ ነው የተባለውን ውጤት አስመዝግቧል። ከዚህ ቀደም ከ700 በተሰጠ ፈተና ይሄን ያህል ከፍተኛ ውጤት (675)…
👏 #ሲፈን_ተክሉ

የአዲስ አበባዋ ተማሪ ሲፈን ተክሉ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600ው 575 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።

ሲፈን የኦግዝሌየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት።

ተማሪዋ " ጌዜን ትምህርት ላይ ማሳለፌ ፣በቡድን ማጥናቴ ፣ የቤተሰብና የመምህራኖቼ ድጋፍ ለዚህ ስኬት አብቅቶኛል " ብላለች።

ለቤተሰቦቿ 2ኛ ልጅ የሆነችው ሲፈን የስርዓተ ምግብ ባለሙያ የመሆኑ ዝንባሌ እንዳላትም ተናግራለች። #AMN

@tikvahethiopia
ከዘመን ዘመን ስንሻገር፣ መስኩ በአደይ ሲንቆጠቆጥ
በአደይ አበባ ጥቅል፣ በአዲስ ዓመት ስጦታ እናሸብርቅ!


🤩 ተናፋቂዋን አደይ አበባ ጥቅል እስከ 20% ከሚደርስ ቅናሽ ጋር በቴሌብር ይግዙ፤ የበዓል ስጦታ ለወዳጅ ቤተሰብ ያበርክቱ!

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን https://onelink.to/uecbbr ወይም *127# ይጠቀሙ

🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

እንኳን አደረሳችሁ !

በካሽ ጎ ከውጭ ሀገር የተላከልዎትን ገንዘብ በአቢሲንያ ባንክ ሲቀበሉ ከዕለታዊ ተመን በተጨማሪ 16% ጉርሻ ያገኛሉ። ከነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ።

የሞባይል መተግበሪያውን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#cashogo #newyear #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
TIKVAH-ETHIOPIA
👏 #ሲፈን_ተክሉ የአዲስ አበባዋ ተማሪ ሲፈን ተክሉ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600ው 575 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች። ሲፈን የኦግዝሌየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት። ተማሪዋ " ጌዜን ትምህርት ላይ ማሳለፌ ፣በቡድን ማጥናቴ ፣ የቤተሰብና የመምህራኖቼ ድጋፍ ለዚህ ስኬት አብቅቶኛል " ብላለች። ለቤተሰቦቿ 2ኛ ልጅ የሆነችው ሲፈን የስርዓተ ምግብ…
#ደሴልዩአዳሪትምህርትቤት👏

“ ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ውጤት በኢትዮጵያ አንደኛ ፤ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ደግሞ ሁለተኛ ነው ” - የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት

በ2016 ዓ/ም አገር ዓቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኢትዮጵያ በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በአማራ ክልል፣ የይሁኔ ወልዱ ደሴ መታሰቢያ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ነው፡፡

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው ትምህርት ቤቱ፣ የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 574 መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህን ውጤት ያስመዘገው ተማሪ ጌታቸው እያዩ ይባላል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ በትምህርት ቤቱ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 562 መሆኑን ትምህትር ቤቱ ገልጿል፡፡

በትምህርት ቤቱ በሴቶች የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 546 ነው፡፡ ውጤቱ የተመዘገበው በሀያት አብዱ ነው።

የተመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት ደግሞ 458 ነው፡፡

ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ያስፈተናቸው ተማሪዎች ብዛት 65 ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 45 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል ተብሏል፡፡

“ ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ውጤት በኢትዮጵያ አንደኛ ነው፡፡ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ሁለተኛ ነው ” ሲል ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

አክሎ፣ “ አጠቃላይ ውጤት የሚባለው፣ አንደኛ ትምህርት ቤቱ ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100 ፐርሰንት ሲያሳልፍ፣ ሁለተኛ ደግሞ የተማሪዎቹ ውጤት ተደምሮ ሲካፈል ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ቤቱን ማንም ትምህርት ቤት አይበልጠውም አንደኛ ነው ” ብሏል፡፡

“ ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ውጤት በኢትዮጵያ አንደኛ፤ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ደግሞ ሁለተኛ ነው ” ነው ሲል ገልጿል፡፡

የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የሚገኝበት የአማራ ክልል ዘንድሮ በብዙ የሰላም እና ፀጥታ ችግር ውስጥ እያለፈ ያለ ክልል ነው።

ባለፉት ዓመታትም ክልሉ በጦርነትና የከፋ የፀጥታ ችግር ላይ ሆኖ እንኳን የሀገሪቱን ከፍተኛ ውጤቶች ያስመዘገቡ ተማሪዎች የወጡበት ነው።

ዘንድሮም ከሀገር ሁለተኛው ከፍተኛ ውጤት በዚሁ ክልል ተመዝግቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ።

ብሔራዊ ሎተሪ አስታዳደር የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ዛሬ ጳጉሜን 5 በህዝብ ፊት መውጣቱን አሳውቋል።


የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0103072 ➡️ 20,0000,000 (ሃያ ሚሊዮን ብር)

የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0348478 ➡️ 10,000,000 (አስር ሚሊዮን ብር)

የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 1546933 ➡️ 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን ብር)

የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0604640 ➡️ 2,000,000 ብር (ሁለት ሚሊዮን ብር)

(ሁሉንም የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴና መሳሳብ ህዝብ ስላልወደደው አሁኑኑ መቆም አለበት !! " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ም/ ፕሬዚደንትና የሰላምና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ካቢኔ ሃላፊ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ፥ " በአሁኑ ወቅት ለሁለት በተከፈለው ህወሓት መካከል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴና መሳሳብ ህዝብ ስላልወደደው…
#TPLF

" በሕወሓት ውሳኔ መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ከኤርትራ መንግስት ባለሥልጣናት ጋር ዱባይ ላይ ተገናኝተዋል " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

ዛሬ የህዝባዊ ወያነ ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በአብዛኛው በእርሳቸው እና በፓርቲያቸው ዙርያ የሚቀርቡ ክሶች አስመልክተው ማብራርያ መስጠታቸው ነው የተነገረው።

በተለይ " ከኤርትራ ጋር ግንኙነት አላቸው " ተብሎ ለሚቀርበው ክስ ምላሽ ሰጥተዋል።

ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ በሕወሓት ውሳኔ መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ከኤርትራ መንግስት ባለሥልጣናት ጋር ከወራት በፊት በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣ ዱባይ መገናኘታቸውን ገልጸዋል።

" ፕሬዝደንት ጌታቸው ከኤርትራ መሪዎች ጋር ግንኙነት አድርጓል። ሥራ አስፈፃሚው እና እኔ የማውቀው ግንኙነት ተደርጓል። " ብለዋል።

" ይህ መጥፎ አይደለም። ለሰላም ብለን ነው። ያለፈው በተጠያቂነት አሠራር ይታያል፥ አሁን ግን ወደ ችግር አታስገቡን፣ ወሰኖች ነፃ አድርጉ፣ ሰው ያግቱ ነበር አታግቱ ለማለት፣ እንስሳት ይዘርፉ ነበረ ሰዎች ያስሩ ነበር አቁሙ ለማለት ከኤርትራ መሪዎች ጋር በውጭ ሀገር ግንኙነቱ ተደርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እንዲያውቁት ተደርጓል። እሳቸውም ከእናንተ ጋር ቅሬታ አላቸው ተገናኙ ብለዋል። ይህ የታወቀ ነው። ይህ ስህተት የለውም። ጌታቸው ግን አይጠቅስም፣ ' ሌሎች አሉ የሚገናኙ ነው ' የሚለው " ሲሉ አክለዋል።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
👏

በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከ600ው በተፈጥሮ እና በማህበራዊ ሳይንስ (575 እና 538) ከፍተኛውን ውጤት አምጥተው የሰቀሉት ሴት ተማሪዎች ናቸው።

ከዚህ ባለፈ እጅግ በርካታ ሴት ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት በማምጣት የዘንድሮውን ፈተና ሰቅለዋል።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል በተሰጠው ከ700 ፈተናም ሴቶች ከፍተኛ አኩሪ ውጤት ነው ያስመዘገቡት።

ከላይ ለማሳያ የተወሰኑ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ፎቶ ይያዝ እንጂ ሌሎችም በርከታ ሰቃይ ሴት ተማሪዎች አሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ2017

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !

ፈጣሪ አዲሱን ዓመት ፦
- የሰላም
- የፍቅር
- የአንድነት
- ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሰው ልጅ ሞት የማንሰማበት
- ደመ የማይፈስበት
- ሰው ታገተ፣ ተገደለ፣ ታፈነ የሚል ቅስምን ሰባሪ ዜና የማንሰማበት
- በመላ ሀገሪቱ ፍጹም እርጋታ ያለበት
- እናት የማታለቅስበት
- ሰው ወጥቶ ቀረ የማይባልበት
- ፍትሕ ለተነፈጉ ሁሉ ፍትህ የሚሰፍንበት
- ፍትሕ አጥተው የሚያነቡ ፍትሕ አግኝተው እንባቸው የሚታበስበት
- እየፈተነን ያለው የኑሮ ጫና መፍትሄ የሚያገኝበት
- በሰላም በነጻነት ያሻን ቦታ ወጥተን የምንገባበት
- በሁላችንም ዘንድ የማያስማሙን ጉዳዮች መፍትሄ የሚያገኙበት
- እርስ በእርስ ልክ እንደጠላት የማንተያይበት ፣ የማንሰዳደብበት
- እሮሮ፣ ስቃይ በደል የማንሰማበት
- ያዘንን ተስፋ የቆረጥን ፤ የምንጽናናበት ተስፋ የምናደርግበት
- ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች ፍጹም የተሳካ ዓመት የሚያሳልፉበት
- ከምንም በላይ በሀገራችን የትኛውም ቦታ ሰላም ተረጋግጦ ፣ ስምምነት መጥቶ በሀገራችን ፍጹም ደስታ የምናገኝበት
- ሁሉም በአንድ መንፈስ ለእናት ሀገሩ " አለሁልሽ " ብሎ የሚቆምበት ያደርግል ዘንድ #ቲክቫህ_ኢትዮጵያ ይመኛል።

ፈጣሪ ምኞታችንን ያሳካልን !

መልካም አዲስ ዓመት !
ከዓመት ዓመት ያደረሰን ፈጣሪ ቀጣዩን እንድናይ ይርዳን !
ለሁላችሁም ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኛለን !

#TikvahEthiopiaFamily
#ቲክቫህኢትዮጵያቤተሰቦች

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ሰራተኞቹ ከሥራ ፈቃድ ወስደው ቤተሰብ ለመጠየቅ ሃና ማሪያም ተብሎ ወደ ሚጠራው ሰፈር ሲጓዙ ነበር " - የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 3 የሆቴል መስተንግዶ ሠራተኞች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው " ቀይ አፈር " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቀን 8፡20 ላይ ነው እንደደረሰ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

አንድ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ መንገድ ሲጠቀሙ የነበሩ እግረኞችን ገጭቶ ባደረሰው አደጋ ነው የ3ቱ ሰራተኞች ህይወት ያለፈው።

ሟቾቹ ሶስቱም ሴቶች ሲሆኑ ዕድሜያቸው ከ25-30 ይገመታል።

ሰራተኞቹ ከሥራ ፈቃድ ወስደው ቤተሰብ ለመጠየቅ " ሃና ማሪያም " ተብሎ ወደ ሚጠራው ሰፈር ሲጓዙ ነበር።

ከሟቾቹ ጋር አብራ ስትጓዝ የነበረች አንዲት ሴት እራሷን ስታ ሕክምና እየተከታተለች ትገኛለች።

በበዓል ወቅት መሰል አደጋ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እና በእርጋታ እንዲያሽከረክሩ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡
- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን  ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)
- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)
#MesiratEthiopia

ድሬዳዋ ውስጥ ከሆናችሁ : ቢዝነስዎን ስኬታማ ለማድረግ እንደግፍዎታለን!
https://forms.gle/34U9fXkRmPxyZzsT6 ተመዝግበው ቦታዎን ያሲዙ።

🗓️ መስከረም 09, 2017 ዓ.ም
🕒 ከጠዋቱ 3:00 እስከ 7:00 ሰዓት
📍 በኤም ኤም ሆቴል (MM Hotel), ድሬዳዋ

የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም Info Session ጥቅሙ ምንድን ነው?
- መስራት ምን እንደሆነና ቢዝነስዎትን እንዴት እንደሚደግፍ ያውቃሉ፣
- ፕሮግራሙን እንዴት መቀላቀል እንደሚቻል ያውቃሉ፣
- ስለሚሰጡት ድጋፎች እና ለሚኖርዎት ጥያቄ መልስ ያገኙበታል።
- በቴሌግራም ቦት በኩል ለሚሰጥ ሥልጠና መመዝገብ ይችላሉ።
#DStv

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የለንደን ደርቢ ጨዋታ 💥
⚽️ ደማቁ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ! አርሰናል የለንድን ተቀናቃዩን ቶተንሀም እሁድ መስከረም 5 ከሰዓት 10፡00 ሰዓት በቶተንሃም ሜዳ ይገናኛሉ!

🤔 አርሰናል እያሳየ የለውን ብቃት መቀጠል ይችላል? የእናንተን ግምት ያጋሩን
👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👉 የዲኤስቲቪን ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk
2024/10/01 07:42:16
Back to Top
HTML Embed Code: