Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#የሀገር_ተስፋዎች 👏 በ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት አንዷ የአዲስ አበባ ፣ ብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት ተማሪዋ ማዕዶት እስክንድር ናት ፤ ተማሪዋ በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600ው 573 በማምጣት ከሀገሪቱ 3ኛውን ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሰቅላለች። @tikvahethiopia
#የሀገር_ተስፋዎች 👏

በ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በማህበራዊ ሳይንስ ከ600ው ከመላ ሀገሪቱ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣችው የኢትዮ ፓረንትስ ት/ቤት ተማሪዋ ዎይናብ ሰለሞን ስትሆን ከ600ው 538 በማስመዝገብ ነው የሰቀለችው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" እንደ ባሪያ ነው የምንታየው ፤ እባካችሁ ጭሁልን !! " - በማይናማር የሚገኙ ወጣቶች ማይናማር እና ታይላንድ ድንበር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የበየነ መረብ ማጭበርበር (Online Scam) ተግባራት ከሚፈጸምባቸው አንዳንድ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክቶችን በቴሌግራም እየተቀበለ ይገኛል። እነዚህ ቦታዎች ላይ በርካታ የሀገራችን ወጣቶች ያሉ ሲሆን " ታይላንድ እንልካችኋለን " በሚል…
#Update

° " ብዙ አካላቸው የጎደለ ሰዎች አሉ፡፡ አካል እስከ ማጉደል ድረስ ነው ቅጣቱ " - ኢትዮጵያዊያን በማይናማር

° " መረጃው ትክክል ነው፡፡ ዜጎች ችግር ላይ ናቸው ተቋሙም ኃላፊነት ወስዶ ለወገኖቻችን ለመድረስ ጥረት እያደረገ ነው " - ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር

በማይንማርን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በከፋ ችግር ውስጥ እንደሆኑ ከወራት በፊት በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ድምጻቸውን አሰምተው እንደነበር ይታወሳል።

አሁንም ኢትዮጵያውያኑ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል።

መጀመሪያ ከአገር ሲወጡ የተዋዋሉት የሆቴል ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ ሀኪም እና የመሳሰሉትን ሥራዎች ሊሰሩና ዳጎስ ያለ ክፍያ ሊፈጸምላቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጅ ከዚያ ከደረሱ በኋላ ሽፍታ ወዳለበት የማይናማር ክልፍ እንደወሰዷቸው፣ ጭራሽ ደመወዝ እንደማይፈጽሙላቸው ፣ ከውላቸው ውጪ ዶላር ማጭበርበር እንደሚያሰሯቸው አስረድተዋል፡፡

የሌሎች አገር ዜጎች በአገራቸው መንግስት አማካኝነት እየተለቀቁ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያኑ ግን የከፋ ስቃይ ውስጥ እንደሆኑ ገልጸው መንግስት እንዲደርስላቸው በአንክሮ ጠይቀዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸው በበኩላቸው፣ መንግስት የልጆቻቸውን ሕይወት እንዲያተርፍላቸው ተማጽነዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ በዝርዝር ምን አሉ ?

" እያንዳንዱ ሰው የግድ በቀን 17 ሰዓት መስራት አለበት፡፡ የተሰራበት ደመወዝ ግን አይከፈልም፡፡ ገቢ ካላስገባ ቅጣት አለ፡፡ አለንጋም አላቸው ይገርፋሉ፡፡ ጨለማ ቦታ ላይ ወስደውም ያስራሉ፡፡

በአንድ ጊዜ ሦስት 20፣ 20 ሊትር ጀሪካን ያሸክማሉ፡፡ ሁለቱን በሁለቱ ትክሻቸው፣ አንዱን በእግርና እግር መካከል እንዲሸከሙ የሚገደዱ ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡

በተጨማሪ ብዙ ሰዎች ባሉበት አካባቢ ፊት ለፊት እንደ ማሳያ ተደርገን እንገረፋለን፡፡ በቀን አምስት ሰዓት ብቻ ነው የሚታረፈው፡፡

እጅና ኮምፒዩተር ለአፍታ ከቦዘኑ፣ የሆነ ስህተት ከተሰራ ድብደባ አለ፡፡ ምንም ነጻነት የሌለበት አገር ነው፡፡

ብዙ አካላቸው የጎደሉ ሰዎች አሉ፡፡ አካል እስከማጉደል ነው ቅጣቱ፡፡ እግራቸው፣ እጃቸው፣ ሁሉ ነገራቸው የተጎዳ ሰዎች አሉ " ሲሉ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያዊያኑን ካሉበት የከፋ ችግር ለማውጣት ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ ያቀረብንላቸው  የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

" በማይናማር የሚገኙ ዜጎቻችን ጉዳይ ይታወቃል፡፡ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በተለይ ሳወዝ ኤዢያ ካሉ ኤምባሲዎቻችን ውስጥ አንዱ ጃካርታ ነው፤ ኢንዶኖዢያ፡፡ ጉዳዩ እነርሱም ደርሷቸው እየጠከታተሉ ነው " ብለዋል።

" ይሄ መስመር በአጠቃላይ እንደ አዲስ የሕገ ወጥ ፍልሰት መንገድ ሆኖ ነው እየታዬ ያለው፡፡ እስከሁን ባልተለመደ ሁኔታ ወደዚህ አቅጣጫ ከዚህ ቀደም ከምናውቃቸው ትንሽ ወጣ ያለ ነው። ጉዳዩም ጥናት የሚፈልግ ሆኖ ነው የተገኘው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" ዜጎች የትም አገር፣ የትም ቦታ ይሁኑ የመጀመሪያው መዳረሻ ችግራቸውን ለመፍታት ውጪ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ክትትል እየተደረገበት ነው " ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያኑ የአካል ጉዳት ጭምር እየደረሰባቸው በመሆኑ በፍጥነት እንዲደረስላቸው እየጠየቁ እንደመሆኑ  ከኤምባሲዎቹ ጋር ያለው ንግግራችሁ ተስፋ አለው ? በምን ደረጃ ላይ ነው ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ለአምባሳደሩ አቅርቧል።

አምባሳደሩ በምላሻቸው፣ " እንደ አጋጣሚ ሆኖ ኢትዮጵያ ማይናማር ውስጥ ኤምባሲ የላትም፡፡ ምንም አይነት ዲፕሎማሲክ ውክልና የለንም " ብለዋል።

" ስለዚህ ከእርቀት ሆነው ነው ይህን ነገር የሚከታተሉት፡፡ መረጃው ትክክል ነው፡፡ ዜጎች ችግር ላይ ናቸው። ተቋሙም ኃላፊነት ወስዶ ለወገኖቻችን ለመድረስ ጥረት እያደረገ ነው " ሲሉ አክለዋል።

በችግር ላይ እንደሆኑ የሚነገርላቸው
ከ3000 በላይ ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ ነው፡፡ ተቋምዎስ ስንት እንደሆኑ ያውቃል? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄም ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

" ቁጥር ልንሰጥ አንችልም፡፡ ነገር ግን ቁጥራቸው 3000ም ሆኑ ሦስት ኢትዮጵያዊያን ችግር ላይ እስካሉ ድረስ ችግራቸው ችግራችን ሆኖ ተቋሙ ዜጎችን ለመታደግ ይንቀሳቀሳል " ነው ያሉት።

ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወታቸዉን መታደግ ተቻለ።

ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጀርመን ድልድይ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥረት ህይወታቸዉን ማትረፍ እንደተቻለ የእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

እናትና ልጇ በወንዝ ዳርቻ ካለዉ የጎመን ማሳቸዉ ዉስጥ ጎመን በመሰብሰብ ላይ ሳሉ በድንገት ደራሽ ጎርፍ ሊወስዳቸዉ የነበረ ቢሆንም በወንዝ መሀል ባለ ድንጋይ ጫፍ ላይ ሆነዉ ህይወታቸወን ማቆየት ችለዋል።

ይሁንና የጎርፉ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ እናትና ልጁ በጎርፉ ሊወሰዱ በተቃረቡበት ሰዓት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች ደርሰዉ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸዉ የእናትና ለጇን ህይወት መታደግ እንደተቻለ ተገልጿል።

በአካባቢዉ ቀደም ሲል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህ አካባቢ ከወንዙ የሚገኘዉን ዉሀ በመጠቀም የጎመንና ሌሎች ተክሎች ማሳ የሚገኝበት ነዉ።

በአሁኑ ሰዓት የክረምቱ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ባለማሳዎች ተክሎቹን ለመሰብሰብ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም የሚችል በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡
- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን  ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)
- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)
🌟 17% የገንዘብ ስጦታ ያግኙ፤ የበረራ ትኬት ጨምሮ ልዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ!

ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሐዋላ የተላከልዎን ገንዘብ ሲቀበሉ 17% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

💁‍♂️ በተጨማሪም 5 ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ሲቀበሉ አጓጊ ለሆነው ልዩ የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!

✈️ ደርሶ መልስ የበረራ ትኬት - እያንዳንዳቸው 480,000 ብር
🏞 ኩሪፍቱ ወተር ፓርክ ቤተሰብ ፓኬጅ - እያንዳንዳቸው 44,000 ብር
🐏 የበግ ስጦታዎች - እያንዳንዳቸው 20,000 ብር...

የሚቀበሉት የገንዘብ መጠን ሲጨምር የጨዋታ ዕድልዎም ይጨምራል!

🗓 እስከ መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba #ባጃጅ በአዲስ አበባ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት በሂደት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ አይቀሬ እንደሆነ ተሰምቷል። በአዲስ አበባ ከተማ የባለሶስት እና አራት እግር ተሽከርካሪ ወይም ባጃጅ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች  የአሰራር ፣ የአጀረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የዲሲፒሊን ቁጥጥር አፈጻጸም መመሪያ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጎ ነበር።                               …
#AddisAbaba

“ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ከተማው ጸጥታ ስጋት የሆኑ ባጃጆች አሉ ” - የኡ/ ትራንስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ውጪ መጥተው የሚሰሩ ባለሦስትና አራት እግር አሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ መታወቂያ፣ የአዲስ አበባ ሰሌዳ እስከሚያሟሉና በማኅበር እንስከሚደራጁ ድረስ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይሰጡ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።

ቢሮው ይህን ያለው በእነዚህ የተሽከርካሪ አይነቶች ወንጀል እየተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ ነው፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ጉዳዩን በተመለከተ ከወጣው መግለጫ በተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ ከከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

Q. በታገዱት የትራንስፖርት አይነቶች ሥራ ተሰማርተው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ አሽከርካሪዎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለምን ሰፋ ያለ ጊዜ አልተሰጣቸውም ? ቀድሞ ማሳወቅ አይቻልም ነበር ?

አቶ ዳኛቸው ፦

“ አዲስ አበባ ዋና ከተማ እንደመሆኗ መጠን የሚበረታታውና የሚደገፈው ማስ ትራንስፖርት ነው፡፡ ከማስ ትራንስፖርት አንጻር አዲስ አበባ አውቶብስ ድርጅት አለ፡፡ ድጋፍ ሰጪ የምንላቸው ሦስት ቁጥር ታክሲዎች አሉ፡፡ ከዚያ ውጪ ቁጥር አንድ የምንላቸው ታክሲዎች አሉ፡፡

ከእነዚህም የበለጠ የሚበረታታውና የሚደገፈው ማስ ትራንስፖርቱ ነው፡፡ ከባጃጅ ትራንስፖርት ጋር ባለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደራጅቶ ስምሪት መስጠት የሚችለው በአዋጁ መሠረት ራሱ የሰጠውን ታርጋ ብቻ ነው፡፡

ይሄ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልሎችና ከተሞች በራሳቸው ታርጋ የሰጡት፣ የመዘገቡት ብቻ ነው አደራጅተው ማሰማራት የሚችሉት፡፡

ከባጃጂ ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ ውስጥ ወደ 5,000 አካባቢ የሚጠጉ ባጃጆች በ93 ማኅበራት፣ እንዲሁም በ73 መስመሮች አካባቢ ላይ ታፔላ ወስደው እየተሰማሩ ነው ያሉት፡፡

አዲስ አበባ በዚህ ደረጃ አጣዳፊ ሥራውን ማሰማራት ተገቢነት የለውም፡፡

ከአዋጅ ውጪ ነው የሚል ቅሬታዎች በተደጋጋሚ ሲነሳ ነው የቆየው፡፡ ቅሬታውም ተገቢ ነው፡፡  ስለዚህ በዚህ ሰዓት ባጃጅን ማበረታታት፣ ማሰማራት አይደገፍም፡፡

በአንድ በኩል የአዲስ አበባ ታርጋ የላቸውም ኦልሞስት 99 ፐርሰንት፡፡ 243 ብቻ ናቸው የአዲስ አበባ ታርጋ ያላቸው ከ5 ሺዎቹ፡፡

አንደኛ ሕጉ መከበር አለበት፡፡ ስህተት በስህተት ላይ መደገም የለበትም፡፡ ሁለተኛ እነዚህ ባጃጆች አካባቢ ሌብነት ይካሄዳሉ፡፡

ህዝቡም እሮሮ ያቀርበል፡፡ ብዙ ቅሬታዎች ናቸው የሚቀርቡት፡፡ የጽንፈኛ ኃይልም አጋዢ ሆነው የሚሰሩ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ለከተማው ጸጥታ ስጋት የሆኑ ባጃጆች አሉ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ የሚሰጠው ለከተማው ሰላም ነው፡፡ ስለዚህ እንዚህ ባጃጆች እንዲቆሙ ሳይሆን ወደ ሕግ እንዲመለሱ ነው፡፡ ወደ ሕግ እንዲመለሱ ሲደረግ ደግሞ አንደኛ መደረግ ያለበት አንደኛ ታርጋ ማውጣት ነው፡፡

ታርጋ ለማውጣት ደግሞ እዘዚህ ባጃጆች ታርጋ ያወጡበት ሂደው ክሊራንስ፣ ሊብሬ አምጥተው የአዲስ አበባ ታርጋ ወስደው እንዲደራጁና ወደ ስምሪት እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ታርጋ ይወስዳሉ፣ ይዘጋጃሉ፣ ወደነበሩበት ይመለሳሉ”።


Q. ቢሮው አጣድፎ ውሳኔውን የወሰነበት ምክንያት ምንድን ነው? አጭር ጊዜ አልሆነም ወይ? ለሚለው ጥያቄ ቀጥታ ምላሽ እንዲሰጡ በድጋሚ ጠይቀናቸዋል፡፡

አቶ ዳኛቸው፦

“ ከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ የሚሰጠው ለከተማው ሰላም ነው፡፡ ትራንስፖርት ሰላምን መሆንን፣ ምቹ መሆንን፣ ተደራሽ መሆንን ይፈልጋል። ስለዚህ በባጃጆች አካባቢ ያለው ሌብነት፣ ዝርፊያ፣ ያለው የከተማውን ሰላም የማናጋት መጠቀሚያነት ከህዝብ በተደጋጋሚ እሮሮ የመጣበት ነው።

ሁለተኛ ታርጋ የሰጥዋቸው ክልሎች፣ ‘አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እኛ የሰጠነውን ካርታና ሊብሬ አደራጅቶ የማሰማራት ስልጣን የለውም ሕገ ወጥ ሥራ ነው እየሠራ ያለው’ የሚል ቅሬታ፣ ስሞታ፣ ክስ አለ፡፡

እውነት ነው በሰላማዊ መንገድ ሥራ የሚሰሩ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነርሱንና ጤናማ ያልሆኑትን ለመለየት ወደ ሕጋዊ መስመር መመለስ ግድ ስለሆነ፡፡

ሰፊ ጊዜ የሚፈልግ ጉዳይ አይደለም፤ ምርምር አይደለም፡፡ ታርጋ ያወጡበት፣ መረጃቸው ያለበት ሂደው ማምጣት ነው፡፡ አብዛኛው ደግሞ መረጃ የሚያሳየው ሸገር ዙሪያ ነው፡፡

ምክንያቱም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባጃጂ ታርጋ ሲሰጥ ስላልነበረ አብዛኛው ያወጡት እዚህ አካባቢ ናቸው። አማራ ክልልም ተጭነው የመጡ አሉ ይታወቃል፡፡ ሌሎች አካባቢዎችም ተጭነው የመጡ አሉ ይታወቃል፡፡

ዞሮ ዞሮ ግን ለምን ተጣደፋችሁ? ለሚለው ነገር የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ማንኛውም ተሽከርካሪ ሕግ አክብሮ እንዲሰራ ለማድረግ ነው”፡፡


Q. አሽከርካሪዎቹ በከተማዋ ለመስራት እንደያሟሉ ከተጠየቁት መስፈርት አንዱ የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ መሟላት ነው፡፡ ይህን አገልግሎት ደግሞ ኤጀንሲው እየሰጠ አይደለም፡፡ መታወቂያውን የት አምጥው ያሟላሉ ተብሎ ነው እንዲህ የተደረገው ? ቢሮው ጉዳዩን አጢኖት ነበር ?

አቶ ዳኛቸው፦

“ ይሄ ጥያቄ ለምን Issue ሆኖ ይነሳል? የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መታወቂያ እየሰጠ አይደለም የሚለው መረጃ ስህተት ነው፡፡

ወሳኝ ኩነት ከከተማ ጀምሮ እስከ ወረዳ አደራጅቶ በቴክኖሎጅ ታግዞ ነዋሪው ግልጽ በሆነ መንገድ መታወቂያ እንዲያገኝ አመቻቾቶ መስራት ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። "


Q. ከክልል ከተሞች በመሸኛ ለሚመጡት እየሰጠ እንዳልሆነ መረጃው እንዳለን ገልጸንላቸው፣ በድጋሚ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀናቸዋል፡፡
አቶ ዳኛቸው፦


“ አሁን እኛ እያወራን ያለነው ከክልል ሰው አዲስ አበባ ውስጥ መታወቂያ አውጥቶ ሥራ ይስራ እያልን አይደለም ያለነው፡፡ ግልጽ ነው አቅጣጫው ለምንድን ነው የአዲስ አበባ ነዋሪ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈለገው ?

ዝርፊያዎች፣ ሌብነት፣ ተለያዩ ጽንፈኛ ኃይሎች መጠቀሚያ መሆን ማስቀረት ከተፈለገ የነዋሪነት ወታወቂያ የግድ ያስፈልጋል። ”
ብለዋል፡፡

ሌላ ጥያቄ እያቀረብንላቸው በነበረበት ወቅትም ማብራሪያቸውን መቅዳት እንድናቆም አስገድደው፣ ለጥያቄው ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምላሽ ላልሰጠባቸው ሌሎች በርከት ያሉ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፍ/ቤት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቀደ። " የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ፤ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል " ተብለው የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ክስ መመስረቻ ጊዜ መፍቀዱ ተሰማ። የፌደራል መርማሪ ፖሊስ የምርመራ ቡድን፦ - ዮሃንስ ዳንኤል - አማኑኤል መውጫ፣…
ክስ ተመሰረተባቸው።

" የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል " በተባሉ 6 ግለሰቦች ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ክስ ተመሰረተ።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ የመሰረተው ክስ ምን ይላል ?

- አውሮፕላንን ያለአግባብ መያዝ ወንጀል፣
- የመንግስት ሰራተኛ የስራ ግዴታውን እንዳይፈጽም መቃወምና አለመታዘዝ የሚል የወንጀል ክስ ነው።

በተጨማሪም በ1ኛ ተከሳሽ ዮሃንስ ዳንኤል ላይ ብቻ " የአየር መንገዱን መልካም ስም ለማጉደፍ ተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒውተር ስርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ወንጀል የሚል ክስ " አቅርቧል።

ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ፦
- ዮሃንስ ዳንኤል
- አማኑኤል መውጫ፣
- ናትናኤል ወንድወሰን፣
- ኤልያስ ድሪባ፣
- ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

የበዓል ጉዞውን በM-PESA እንቁረጥ እና 5% ተመላሻችን ፈጥኖ ይደርሰናል!
Bon voyage !

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
 
#FurtherAheadTogether
#flyethiopian
" 60 ሰዎችን አግተው ወስደዋል ፤ 369 ከብቶች ተዘርፈዋል ፤ 19 ቤቶችን አቃጥለዋል " - በትግራይ ክልል የምስራቃዊ ዞን

የኤርትራ መንግስት ወታደሮች 60 ሰዎች አግተው መውሰዳቸው 369 ከብቶችን በመዝረፍ 19 ቤት ማቃጠላቸው ተገልጿል።

የኤርትራ መንግስት ወታደሮች የእገታ የዝርፍያና ቤቶች የማቃጠል ተግባር የፈፀሙት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የኢሮብና ጉሎመኸዳ ወረዳዎች እንደሆነ የዞኑ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት አሳውቋል።

ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፥ ታግተው ከተወሱዱት 60 ሰዎች ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወጣቶችና የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ናቸው።

የኢሮብና የጉመኸዳ ወረዳዎች 8 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት የትግራይ ጦርነት ከተጀመረበት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወዲህ ሙሉ በሙሉና በከፊል በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

ለድህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉት የጉሎመኸዳ ወረዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት ፥ ባሳለፍነው ዓመት መጨረሻ በዜጎች ላይ ያነጣጠረ አፈና ተባብሶ መቀጠሉ አመልክተዋል።

" በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የትግራይ ክልል ግዛታዊ አንድነት ወደነበረበት ባለመመለሱና የኤርትራ ሰራዊት ከአከባቢያቸው ሙሉ በሙሉ ባለመውጣቱ ለአፈናና ለከባድ የፀጥታ ስጋት አደጋ ተጋልጠናል " ብለዋል።

የጉሎመኸዳ ወረዳ የሰላምና የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ ነብዩ ስዩም በበኩላቸው " በሙሉና በከፊል በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ከሚገኙ የወረዳው 4 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት አስከአሁን 52 ወገኖች ታፍነው መወሰዳቸው እረጋግጠናል " ብለዋል።

" ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ሙሉ በሙሉ ሸዊት ለምለም በከፊል በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " ያሉት ሃላፊው " የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሰራዊት በአከባቢው የለም " ሲሉ ገልፀዋል።

በተያያዘ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከተለያዩ የኢሮብ ወረዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት 8 ሰዎች ታፍነው 222 ከብት፣ 157 ፍየልና በጎች ሲዘረፉ 19 ቤቶች በኤርትራ መንግስት መቃጠላቸው የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) ሊቀ-መንበር ዶሪ አስገዶም አስታውቀዋል። 

የወረዳው የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት እንደገለፀው አራት ቀበሌ ገበሬ ማህበራት በሙሉና በከፊል በኤርትራ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

በኤርትራ መንግስት ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኘው የአከባቢው ማህበረሰብ ለአራት ዓመታት በከፍተኛ የፀጥታ አደጋ ስጋትና ተስፋ መቁረጥ ስሜት እንደሚገኝ የገለፁት የወረዳዎች ነዋሪና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ገልጸዋል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተተግብሮ የኤርትራ ጦር ከያዘው አካባቢ እንዲወጣ ፣ የህዝብ ደህንነት እንዲጠበው፣ ተፈናቃዮች ወደ ቂያቸው እንዲመለሱ ተጠይቋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
2024/10/01 09:25:19
Back to Top
HTML Embed Code: