Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 " #ኢትዮጵያ ሶማሊያ እንደ አገር ትቆም ዘንድ ብዙ መስዋዕትነትን ከፍላለች፡፡ ብዙ ሺሕ የሚቆጣጠሩ ወንዶችና ሴቶች መስዕዋት አድርገናል ገብረናል፡፡ የቆጠብነው ነገር የለም ሕይወት ሰጥተናል፣ ደም ሰጥተናል፣ ላብ ሰጥተናል፣ ጉልበት ሰጥተናል፡፡ ነገር ግን በሶማሊያ በኩል ይህንን አስተዋጽኦ ከቁብ ላለመቁጠርና ውለታ ለማስቀረት የሚደረግ መግለጫ መስማት እንደ ኢትዮጵያዊ ይኮሰኩሳል።…
#ETHIOPIA🇪🇹

የቀን ቅዠት ነው !!!

" እንደ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምንም ዓይነት የፀጥታ ሥጋት እንዲኖር አልፈልግም ነገር ግን በኢትዮጵያ አቅም በተለይም በሕዝቦቿ ስለምተማመን እንቅልፍ አልባ ሌሊት የለኝም፡፡ #ግብፅ በሶማሊያ በኩል መጥታ ኢትዮጵያን አጣቢቂኝ ውስጥ መክተት ትችላለች ማለት የቀን ቅዠት ነው። " - አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ (የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦ " ሱዳን እና ግብፅ በጣም መደገፍ ያለባቸው ግድብ ነው። ሰሞኑን በቀን እስከ 900 ሚሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ በየቀኑ ይይዛል። ምን ማለት ነው በየቀኑ አንድ አንድ ቢሊዮን ከያዘ ይሄ አጠቃላይ አቅሙ 74 ቢሊዮን ስለሆነ በ74 ቀን ውስጥ ሙሉ ግድቡን መያዝ እንችላለን። አንዳንዴ ሽርፍራፊ ስላለ በ100 ቀን ውስጥ ይሄ ግድብ ከ0 ተነስቶ ሙሉ መሆን…
#GERD🇪🇹

ፕ/ር አታላይ አየለ ምን ነበር ያሉት ?

ኢትዮጵያ የሁለተኛውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት ባከናወነችበት ወቅት በግብፅ ጉዳይ አንድ አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ፕ/ር አታላይ አየለ ፦

" ግብፆች ' ግድቡን እንመታለን ' ምናምን የሚሉት ፣ የሚያስፈራሩት ነገር አለ።

የግድቡ ግዝፈት እንዲሁም ሚሰራበት ጥራት እውነት ለመናገር መቼውንም ቢሆን ተመቶ ይፈርሳል ተብሎ የሚታሰብ አይደለም።

እንደው ተሳክቶላቸው እንኳ ቢሆን የውሃ ሙሌቱ ልክ እንደ #ኒውኩሌር_ቦምብ ማለት ነው ለራሳቸው የሚሆነው ፤ ጠራርጎ ሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ነው የሚጨምራቸው።

የቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ' ግድቡን እኛ ሳንሆን እነሱ ናቸው የሚጠብቁት ' ብለዋል።

ስለዚህ ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ ብዙ የሚያስጨንቃት አይደለም።

ቢፈልጉ ይደራደሩ በአካሄድ በሌሎች ጉዳዮች ፣ የውሃ ፣ አካባቢ ጥበቃና በሌሎች የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ። "

#TikvahEthiopia
#ETHIOPIA
#GERD🇪🇹

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎችን አወዳድሬ ነው የምቀበለው " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ-ገዝ ዩኒቨርሰቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በራሱ ፖሊሲና መስፈርት ፤ ምዘናና የክፍያ ስርዓት ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል አሳውቋል። በመደበኛ፣ በማታና በርቀት በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ አመልካቾች በቅርቡ ዝርዝር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ…
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን አስተዋወቀ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም የአዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫው ተከታትሏል።

ዩኒቨርስቲው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል በዚሁ መግለጫ አስታውቋል።

የዩኒቨርስቲው ተጠባባቂ ፕረዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፥ ራስ-ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆኖ የተቋቋመው ዩኒቨርሲቲው ተቋማዊ ነጻነት፤ አስተዳዳሪዊ ነጻነት፤ የፋይናንስ ነጻነት እና አካዳሚክ ነጻነት ማግኘቱን ገልጸዋል።

" ይህም መምህራኑን ሆነ ተማሪዎችን የመምረጥ መብት ይሰጠዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

አዲስ ይተገበራል በተባለው የቅበላ አሰራር በ2014፤ 2015 እና 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የሚወጣውን መስፈርት ታሳቢ አድርገው በዩኒቨርሲቲው ፖርታል https://portal.aau.edu.et መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

መስፈርቶቹ ምንድን ናቸው ?

ዶ/ር ሳሙኤል ፥ አንዱ መስፈርት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን 50 በመቶ በላይ ማምጣት እንደሆነ ገልጸዋል።

ይህ ግን የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ባገናዘበ መልኩ 60 ወይም 70 በመቶ ድረስ ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል።

በመቀጠልም ዩኒቨርስቲው በራሱ የሚያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና (Undergraduate Admission Test) የሚኖረው ሲሆን ይህንን ፈተና ማለፍም ሌላው ዩኒቨርሲቲው ያስቀመጠው መስፈርት ነው ብለዋል።

ፈተናው ምን መልክ ይኖረዋል ?

በዩኒቨርስቲው መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የሚቀርበው የፈተና ይዘት ምን መልክ አለው በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር ሳሙኤል ፈተናው የአፕቲቲውድ (Apptitude) መልክ የሚኖረው እንደሆነ ጠቅሰው የተማሪዎችን የቋንቋ፤ የማመዛዘን እንዲሁም የቀመር አቅማቸውን የሚለካ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ፈተናው ከሌሎች የመግቢያ ፈተና ጋር ተመሳሳይነት ሊኖረው እንደሚችል ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ሆኖም የሚወጣው ፈተና ሙሉ በሙሉ የዩኒቨርስቲው እንደሚሆን አስረድተዋል።

የክፍያ እና የስኮላር ሺፕ ሁኔታ በተመለከተ ምን ተባለ ?

በዩኒቨርስቲው ለመማር ጥያቄ የሚያቀርቡ ተማሪዎች በሁለት አይነት መንገድ እንደሚስተናገዱ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

አንደኛው መስፈርቱን አሟልተው እና ሙሉ ክፍያ ከፍለው የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ ሌላው መንግስት ስፖንሰር ሺፕ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ተማሪዎች ናቸው።

ይህን በተመለከተ የተቀመጠ ኮታ እንደሌለ የገለጹት ዶ/ር ሳሙኤል እንደ እቅዳቸው ግን 50 በመቶ በመንግስት 50 በመቶ በግል ወጪያቸው የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች ለመቀበል እንደሆነ ገልጸው ካልሆነም ቁጥሩ በተወሰነ መልኩ ልዩነት ሊኖረው እንደሚችልም ጠቁመዋል።

መንግስት ከፍተኛ ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለሀገር በሚፈለጉ የስልጠና መስኮች ወጪን ጭምር በመሽፈን የሚያስተናግድበት ሥርዓት እንደሚኖር እና ለሴቶች ለአካል ጉዳተኞች እና ከታዳጊ ክልል ለሚመጡ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥም ተመላክቷል።

ተማሪዎች በሚያመለክቱበት ወቅት ብዙ ቅጾችን እንደሚሞሉ ፤ ስኮላርሺፕ የሚጠይቁ ተማሪዎች ከፍለው መማር እንደማይችሉ የሚያሳይ ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው እና የሚያስገቡት መረጃ ትክክለኛነቱ እንደሚጣራና ሐሰተኛ ሆኖ ከተገኘ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ጭምር አንስተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ዩኒቨርስቲው በተከታታይ እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
📣 የ Jasiri Talent Investor Fully-Funded Program ተመልሷል

- ባሉበት የስራ መስክ በቂ የሆነ ችሎታ ካሎት፣ አዲስ እና በፍጥነት የማደግ አቅም ያለው ተቋም የመመስረት ፍላጎት ካሎት ፣እንዲሁም ችግር የመፍታትና ተጽዕኖ የመፍጠር ብቃት ካሎት ይህ ዕድል ለእርሶ ነው፤

- ሙሉ ወጪያችሁ ተሸፍኖ በሩዋንዳ የ 3 ወር ስልጠና፤ የቢዝነስ መነሻ እንዲሁም ቢዝነሱ እስኪቋቋም ለተወሰኑ ወራት የሚያቆይ የኪስ ገንዘብ የሚያገኙበት፤

- ክህሎት ያላቸው ብቁ አለም አቀፍ አማካሪዎችን ጨምሮ ስልጠናችሁን ጨርሳችሁ ወደ ኢትዮዺያ ስትመለሱ ለተወሰነ ግዜ የምትጠቀሙበት የጋራ ቢሮ (co-working space) ተመቻችቷል።

- ኬንያ ወይም ሩዋንዳ ቢዝነስ መጀመር ምርጫችሁ ከሆነም በየሀገሩ ተመሳሳይ ድጋፍ ይደረጋል።

7ኛው ዙር ለመቀላቀል፣ ይመዝገቡ 👉🏾 https://bit.ly/3A8rxtV

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉🏾 @Jasiri4africa
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የህዝብድምጽ የአማራ ህዝብ አስተማማኝ ሰላምን ካጣ ዓመታት አልፈዋል። በየጊዜው የሚያገረሸው የተኩስ ልውውጥ የሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል። በክልሉ ያሉ ሲቪል ሰዎች በሰላም ወጥቶ መግባት ቅንጦት እንደሆነ ይናገራሉ። የኢኮኖሚውና የሰላም እንቅስቃሴውም ከሌሎች ክልሎች አንጻር እየተዳከመ ይገኛል። ከዚህ ቀደም የሀገርና የውጭ ቱሪስት የሚጎርፍባቸው አካባቢዎች ዛሬ ሰው አይታይባቸውም። በዚህ…
🔈 #የነዋሪዎችድምፅ

“ ግድያና እገታ የሚፈጸመው መሀል ከተማ ላይ ነው፡፡ ለዛውም ፖሊስ ጣቢያ ባለበት አጠገብ፡፡ ዛሬ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቷል፡፡ ፖሊስና ሚሊሻ ወደ ህዝቡ ነው የተኮሰው ” - ነዋሪዎች

በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች በተለይ ከሦስት ወራት ወዲህ " በታጠቁ አካላት አማካኝነት ግድያ፣ እገታና ዝርፍያ " በመበራከቱ ሰቆቃ ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ድርጊቱ የሚፈጸመው በከተማው ምንም አይነት የተኩስ ልውወጥ በማይደረግበትና አገር ሰላም በተባለበት ወቅት እንደሆነ፣ የጸጥታ አካላት ቅሬታው ከነዋሪዎቸ ቢቀርብላቸውም ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠታቸው ጥቃቱ እንደተባባሰ አስረድተዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ምን አሉ ?

- ኧረ የፍትህ ያለህ ! አገራችን ይሄው ሆነ፡፡ ታዲያ አገራችንን ትተን የት እንሂድ ? ሞትና እገታ በቃ እንደ ደና አደርክ ሁሌም የምንሰማው ቃል ሆነብን እኮ፡፡

- የታጠቁ አካላት ሌሊት የተኩስ ሩምታ ይከፍታሉ፡፡ የነዋሪዎችን ቤትም ሰብረው ይገባሉ፡፡ ከዚያ ሰዎቹን በማስፈራራት አግተው ይወስዳሉ፡፡ እንደገና ታጋቾቹን ለመልቀቅ እስከ 3 ሚሊዮን ብር ይጠይቃሉ፡፡ ገንዘቡ ተልኮም ታጋቾቹን ይገድሏቸዋል፡፡

- ሁሌም ሌሊት ላይ በጣም ይተኮሳል፡፡ እናም ተኩስ ከተሰማ የሆነ ሰው እየታገተ እንደሆነ ይታወቃል ከድርጊቱ መደጋገም ተነሳ፡፡

- የ ‘ፋኖ’ ታጣቂዎች በከተማው የሉም። ከተማው ላይ ያለው ሚሊሻ ነው፡፡ ፖሊሶች ራሱ ከተማ ላይ ሲንቀሳቀሱ አይታዩም፡፡

- ጎንደር ላይ ፋኖም፣ መከላከያም የለም፤ ስለዚህ ጦርነት የለም፡፡ እገታ፣ ግድያና ዝርፊያው የሚፈጸመው በከተማው ጦርነት እየተካሄደ ሆኖ እንኳ አይደለም፡፡

- እንዲህ የሚያደርጉትን አካላት ማንነት ሌሊት ስለሚመጡ በደንብ ማወቅ አይቻልም፡፡

- በየቀኑ በመኪና እየመጡ አጥር ዘለው ይገባሉ፡፡ ግቢ ከበው ሌሎች ሙሉ አባበሎቻቸውን አስገብተው ነዋሪዎቹን አግተው ይወስዳሉ፡፡ እንደዚህ መሆን ከጀመረ ሦስት ወራት አስቆጥሯል፡፡

- አጋቾቹ ገንዘብ ሲጠይቁ የታጋች ቤተሰብ በባንክ ነው ገንዘብ የሚልከው፡፡ በባንክ ነው የሚላክላቸው። ስለዚህ እነርሱን ማግኘት ለምን አልተሻለም ? ሙሉ መረጃው ባንክ ላይ አለ።

- የጸጥታ አካላት በቀበሌ ሰብስበውን ነበር፡፡ ሁሉም ሰዎች ‘ እናንተ የምታመጧቸው ሚሊሾች ናቸው እንዲህ የሚያደርጉን፡፡ ' ነው ያሉት።

- ትላንት ከሚሊሻ በተተኮሰ ጥይት አንድ ልጅ ተገድሏል፡፡

- ግድያና እገታ የሚፈጸመው መሀል ከተማ ላይ ነው፡፡ ለዛውም ፖሊስ ጣቢያ ባለበት አጠገብ፡፡ ዛሬ ህዝቡ ሰላመዊ ሰልፍ ሲወጣ ፖሊስና ሚሊሻ ወደ ህዝቡ ተኩሷል ፒያሳ ላይ። ሰዎችም ተጎድተዋል። ተገድለዋል።

- እንዲህ የሚያደረገው የነዋሪው ሥነ ልቦና እንዲጎዳ፣ ተስፋ እንዲቆርጥ ነው፡፡ ፍላጎታቸው ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ ምክንያቱም ገንዘብ ከተላከ በኋላም ታጋቾቹን ይገድሏቸዋል፡፡

- ጡት እንኳን ጠብታ ያልጨረሰች ኖላዊት የተባለች ህፃን ልጅ በአጋቾች ታግታ አጋቾቹ 1 ሚሊዮን ተጠየቀባት ፤ አቅም የለንም ሲሉ 500 ሺህ አደረጉ ከዛ  200 ሺህ ብር ከተቀበሉ በኃላገድለዋት አስክሬኗን በር ላይ ጥለዋል። ለማን እንጩህ ፤ የት እንሂድ ?

- በቅርቡ ደግሞ እናት እና ልጅን ለማፈን ብለው ለሊት ቢመጡም አልመች ስላላቸው ገለዋቸው ሂደዋል። የፍትህ ያለህ።

- ባለሃብቱ ከከተማው እየወጣ ነው ፤ ሌላውም ይህን ሽሽት በቻለው አቅም ወደ አዲስ አበባ እየገባ ነው። እዚህ የቀረው መሄጃ ቢያጣ ነው።

- ባለሀብቱ እየወጣ ሲያስቸግራቸው አጋቾቹ ያገኙትን አፍነው ለምናቹ አምጡ ማለት ጀምረዋል። የሚጠይቁት 1 እስከ 3 ሚሊዮን ብር ነው ሚጠይቁ ደሀም ያዙ ሀብታም ይህን ነድ የሚጠይቁት።


ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ከተማው እና የክልሉ ጸጥታ አካላት ሙከራ ብናደርግም ስልክ ላመንሳት ፈቃደበኛ አልሆኑም፡፡

ምላሽ ከሰጡ በድጋሚ የምንጠይቃቸው ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines🇪🇹 " የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤነው እንጠይቃለን ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ የሚጎዱት ወደ ኤርትራ የሚጓዙ ተጓዦች ናቸው " - " አቶ መስፍን ጣሰው የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 30 / 2024 ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው…
#EthiopianAirlines

ወደ አስመራ የሚያደርገው በረራ ከነገ ጀምሮ ይቋረጣል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በረራውን የሚያቋርጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር እንደሆነ ገልጿል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመብረር ትኬት የቆረጡ መንገደኞች ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በሌሎች አየር መንገዶች ጉዟቸውን እንዲያደርጉ ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቋል።

" የትኬት ገንዘብ ይመለስልን " የሚሉ ካሉም ለቲኬታቸው ሙሉ ገንዘብ ተመላሽ እንደሚያደረግ ገልጿል።

በበረራው መቋረጥ ምክንያት ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" በረራውን ለማቋረጥ የተገደድኩት ገንዘብ እንዳላንቀሳቅስ በመታገዴ ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚያደርገው በረራ ከመስከረም 20፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቆም የሚያሳውቅ ደብዳቤ ጽፎ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ አየር መንገዱ በሰጠው መግለጫ ውሳኔው ይሻሻላል በሚል ሲጠብቅ እንደነበር እና የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንን ለማናገር በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ አለማሳካቱን አስታውቋል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በመግለጫው እንደጠቀሱት በአስመራ የሚገኘው ተወካያቸው ከሽያጭ የተሰበሰበ ገንዘብ ለማስገባት ሲል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ መላክ እንደማይቻል ተነግሮታል። ይህ የሆነው ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ አማካኝነት ነው።

" ' ከነሐሴ 25/ 2016 ዓ.ም በኋላ ሂሳባችሁ ታግዷል ለሀገር ውስጥ ወጪም (oppration fee) መጠቀም አትችሉም ' መባሉን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ በረራውን ለማቋረጥ ተገደናል። የበረራ ወጪያችንን መሸፈን ባለመቻላችን ተገደን ወጥተናል " ሲሉ ነው የገለጹት።

አየር መንገዱ እንዳያንቀሳቅስ የታገደበት ገንዘብ መጠን ስንት ነው ?

ይህ ጥያቄ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው የገንዘቡን መጠን ከመግለጽ ተቆጥበው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አየር መንገዱ በኤርትራ ሁለት አካውንት እንዳለው የገለጹት አቶ መስፍን፥ አንዱ የናቅፋ አካውንት ሲሆን የቆየ እንዲሁም ወደ ዶላር መቀየር ያልተቻለ የማይንቀሳቀስ የሂሳብ አካውንት መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላኛው የባንክ አካውንት ደግሞ የዶላር ሲሆን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ትኬት ሲሸጥ የነበረው በውጭ ምንዛሬ መሆኑን ገልጸው ይህንን ገንዘብም እገዳው እስከተላለፈበት ቀን ድረስ በተለያዩ ጊዜዎች ገንዘቡን ሲያንቀሳቅስ እንደነበረ ገልጸዋል።

" የበረራ እገዳውን ካወጡብን በኋላ ነው Block ያደረጉብን " ሲሉ ነው የገለጹት።

አቶ መስፍን አክለውም ፥ "ለእኛ ገንዘቡ ካልተለቀቀልን ከዚህ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ ነው የሚሆነው " ሲሉ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ ለሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን እና ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቃቸውን ገልጸዋል።

" አየር መንገዱ ከኤርትራ የወጣው ተገዶ ነው " ያሉት አቶ መስፍን ዋናው ችግሩ ለምን እንደታገድን አለማወቃችን ነው፤ በተጻፈው ደብዳቤም ላይ ምንም የተገለጸ ነገር የለም ብለዋል።

" ከዚህም በተጨማሪ በደብዳቤም በስልክም ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም " ሲሉ ገልጸዋል።

የአየር ቀጠናውን አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚው አሁን ባለው ሁኔታ በኤርትራ የአየር ክልል መብረር እንዳልተከለከሉ ገልጸው የሚያስገድድ ጉዳይ ካለ ግን አማራጭ መጠቀም እንደሚችሉ አንስተዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መግለጫ
TIKVAH-MAGAZINE
" የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚደረገውን መደበኛ በረራ ከዛሬ ሴፕቴምበር 3/2024 ጀምሮ አቋርጧል። " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

(ሙሉ መግለጫውን ከድምጽ ቅጂው ያዳምጡ)

@tikvahethiopia
🌟 ዓለም አቀፍ የበረራ ትኬትን ጨምሮ በትላልቅ ሽልማቶች ይንበሽበሹ!!

መጪውን አዲስ ዓመት አስመልክቶ ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሐዋላ የተላከልዎን ገንዘብ ሲቀበሉ 5% የገንዘብ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

በተጨማሪም 5 ሺህ ብር እና ከዛ በላይ ሲቀበሉ አጓጊ ለሆነው ልዩ የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!

✈️ ደርሶ መልስ የበረራ ትኬት - እያንዳንዳቸው 480,000 ብር
🏞 ኩሪፍቱ ወተር ፓርክ ቤተሰብ ፓኬጅ - እያንዳንዳቸው 44,000 ብር
🐏 የበግ ስጦታ - እያንዳንዳቸው 20,000 ብር
💰 5 ሺህ ብር - 450 ስጦታዎች
🌐 ወርኃዊ ያልተገደበ ዳታ + ድምጽ - 300 ስጦታዎች

🗓 እስከ መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የጊግ ኢኮኖሚን ጥቅም ማወቅ ይፈልጋሉ?

በቢዝነስ፣ በህግ እና በፋይናንስ ዙርያ የሚሰጠውን የጊግ ኢኮኖሚ ስልጠና በቴሌግራም ቦት በኩል ይውሰዱ!

🔗http://www.tg-me.com/mesirat_academy_bot ተመዝግበው ስልጠናውን ይጀምሩ!

ስልጠናውን ሲጨርሱ ሰርተፍኬቶን እንዳይረሱ!

#MesiratEthiopia #Entrepreneurship #BusinessGrowth #GigEconomy #Workshops #Mesirat
2024/10/01 09:41:27
Back to Top
HTML Embed Code: