Telegram Web Link
Tassa Tassa Tasssa !

በጎፋ ዞን ፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችን የማጽናናት እና የመደገፍ ስራ እየተሰራ ነው።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች ድጋፋቸውን ይዘው ወደ ስፍራው በመሄድ አስረክበዋል።

በርካቶች ተጎጂዎችን ለማጽናናትና ለመደገፍ ወደ ስፍራው በየዕለቱ እየተጓዙ ይገኛሉ።

በቁሳቁስ ከሚደረገው ድጋፍ በተጨማሪም የዞኑን የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000511561276 በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።

በተጨማሪ የጎፋ ዞን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በ8091 ድጋፍ እያሰባሰቡ ናቸው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሻሻሉ የቅጣት እርከኖች ፦

🗑 ለማንኛውም ግለሰብ/ድርጅት

- ደረቅ ቆሻሻ በግቢው ውስጥ በአግባቡ አለመያዝ፤ በዓይነት አለመለየት፤ ማዝረክረክ፤ ለጤናና የአካባቢ ገጽታ በሚጎዳ መልኩ ማከማቸት፤ ለግለሰብ 2 ሺ ብር ለድርጅት 50 ሺ ብር ቅጣት

- የሲጋራ ቁርጥራጭ፣ የሶፍት ወረቀት፣ ፌስታል የመሳሰሉት ጥቃቅን ደረቅ ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ ወይም በፓርኮች፣ በአረንጓዴ ቦታ፣ በኮሪደር ከጣለ 2 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከመኖሪያ ቤት ወይም ከድርጅት ግቢ ውጭ ያለውን የአካባቢ ንጹህና አረንጓዴ አድርጎ አለመጠበቅ ከመኖሪያ ቤት አጥር ግቢ ውጭ እስከ 5 ሜትር ርቀት አለማጽዳት፤ 20 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከድርጅት/ተቋም አጥር ግቢ ውጭ እስከ 10 ሜትር አለማጽዳት፤ 100 ሺ ብር ቅጣት

- ወቅታዊና ልዩ ዝግጅት አከናውኖ በዓሉ ሲጠናቀቅ በዕለቱና ወዲያው ዝግጅቱ የተከናወነበትን አካባቢ ከቆሻሻ ያላጸዳ የፕሮግራሙ አዘጋጅ፤ 50 ሺ ብር ቅጣት

- ዓመታዊ፤ ወርሃዊና ሳምንታዊ የእምነት በዓላት ሲከናወኑ ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ የዝግጅቱ ባለቤት በዕለቱና ወዲያው አካባቢውን ካላጸዳ፤ 20 ሺ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

🗑 ለጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት/ማኅበራት፦

- ማኅበሩ ደረቅ ቆሻሻ ሲሰበስብ ገጽታ ካበላሸ 25 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጭ የአገልግሎት ክፍያ ከደንበኛው ከተቀበለ  50 ሺ ብር ቅጣት፤

- ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦታዎችን እስከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱ ካላደረገ 50 ሺ ብር ቅጣት ይጣልበታል።

Credit ➡️ @tikvahethmagzine

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፎቶ ፦ ይህ የምትመለከቱት በካፋ ዞን ፣  በዴቻ ወረዳ፣ ሚዲዮ ጎምበራ ቀበሌ ትናንትና ምሽት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የተከሰተው የመሬት መንሸራተት ነው።

በአደጋው 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ሞተዋል።

አንድ ሰው ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

24 የአከባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

አደጋው በተከሰተበት አከባቢ ከጠሎ ወደ ቦንጋ የሚያስኬድ አስፓልት መንገድ ላይ በናዳ ተዘግቶ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል። የአከባቢው አስተዳደር ከነዋሪዎች ጋር ተረባርበው መንገዱ ለትራፊክ ክፍት ማድረግ ችለዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

እርስዎ ፈልገውን እኛን አያጡም! በአቢሲንያ አሚን ቨርቹዋል ባንካችን ፍላጎትዎን በየትኛውም ቀን በየትኛውም ሰዓት ያሟሉ።

አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! https://www.tg-me.com/BoAEth
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia  #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CHAPA

ደስተኛ ደንበኛ ፤ አዋጭ ንግድ!💫💸

በቻፓ ደንበኞት በመረጡት የክፍያ አማራጭ እንደ ቴሌ ብር፣ አሞሌ፣ ሲቢኢ ብር፣ ወጋገን ሄሎ ካሽ፣ ኩፕ ፔይ ኢ - ብር፣ አዋሽ ብር፣ አቢሲኒያ ኤቲኤም ካርድ፣ እናት ባንክ፣ ቪዛ፣ ማስተር ካርድ፣ ፔይ ፓል እና ሌሎች ክፍያን በፍጥነት መቀበል ይችላሉ። ለየት የሚያደርገው እርሶ ከሁሉም ወደአንድ ቦታ በቻፓ አማካኝነት መቀበል መቻሎ ነው።

ለደንበኞችዎ አማራጭን በማፋት ግብይትን ያቅልሉ።

ቻፓ ኢትዮጽያ ውስጥ ላሉ ንግዶች ሁሉ!

እርስዎ ንግድዎ ላይ ያተኩሩ ፣ ቻፓ ክፍያዎችዎን ይቆጣጠራል። ንግድዎን ዛሬውኑ ቻፓ ላይ በማስመዝገብ ክፍያዎትን ያዘምኑ!

🌐ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ፡ https://chapa.co/ ወይንም ዛሬውኑ በ 8911 ይደውሉልን።

Telegram | Website | Instagram | Facebook |LinkedIn |X
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ ይህ የምትመለከቱት በቤንች ሸኮ ዞን ፣ በጉራፈርዳ ወረዳ ውስጥ የተከሰተ የመሬት ናዳ ነው።

በዚህ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ናዳው በነባሩ ኮመታ 2 ህጻናት እና ከባዲቃ የመጣች አንዲት ሴት በድምሩ 3 ሰዎች ህይወት ነው የቀጠፈው።

3 ሄክታር የሚሆን ደን በናዳው ምክንያት መውደሙ ተነግሯል።

በናዳውና በከፍተኛ ሁኔታ የወንዝ ሙላት የተነሳ ወደ ነባሩ ኮመታና ኡይቃ ቀበሌዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል።

መረጃ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
 #Update #TPLF

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም " - የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት

የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኮሚሽኑ አባላት በጋራ በሰጡት መግለጫ " ትናንት ህዝባችን ላይ ያደረስነው ጉዳት በመረዳት ዛሬ መፀፀትና ለደህንነቱ መትጋት ይገባናል " ብሏል። 

" በኛ ጦስ ምክንያት በህዝባችን ላይ ሊከተል የሚችለው መከራ ከወዲሁ በመገንዘብ ሊካሄድ ከታሰበ ጉባኤ ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በህወሓት አቋም የሚባል ጠፍቶ ቦታውን ኔትወርክና መቦዳደን ተክቶታል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ግልፅነት ፣ አሳታፊ አሰራር እና ዴሞክራሲ ጠፍቶ ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም አይለዋል " ያሉት የኮሚሽን አባላቱ ፥ " 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለይስሙላ ቢቋቋምም ይህንን ወደ ጎን በመተው ስራውን የሚያከናውነው ሃይል የበላይነት አለኝ የሚል አካል ነው " በማለት ድርጊቱ አውግዘዋል።

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም ፤ ከመተማመን መግባባትና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ውጪ የሚካሄድ ህዝባዊ ጠቀሜታ ስለሌለው የዚሁ ተግባር አካልና ተባባሪ መሆን አንፈልግም " ብለዋል።

የኮሚሽኑ አባላት ፥ " አካሄዳችሁ አስተካክሉ ላለ አካልና ግለሰብ የሌለ ስም እየሰጡ ማጥላላት የትም አያደርስም " ያሉ ሲሆን " ከኔትወርክ እና መጠላለፍ ያልፀዳ ጉባኤ ማካሄድ ህዝብን ይጎዳል እኛም የዘህ ጉዳት ተባባሪ ላለመሆን ይካሄዳል ከሚባለው ጉባኤ ራሳችን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ።

ከሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሽራተት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን በማሰብ ብሔራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ እንዲታወጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወስኗል።

በእነዚህ ብሔራዊ የሐዘን ቀናት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች፤ በኢትዮጵያ መርከቦች፤ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች የሪፐብሊኩ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተወስኗል፡፡

@tikvahethiopia
📽 ሲኒማን በስልክዎ!! 📱

በተመልካች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኙትን ''ስድስት ሰዓት ከለሊቱ'' እና ''ትዝታ'' ፊልሞችን ባሉበት ሆነው በእጅ ስልክዎ በቴሌቲቪ ኦንላይን ሲኒማ ይመልከቱ!

ቴሌቲቪ መተግበሪያን በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ወይም ከ teletv.et/download ያውርዱ፤ ክፍያዎን በቴሌብር ይፈጽሙ!

📞ለበለጠ መረጃ 9801 ይደውሉ።

#teletv
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
2024/11/05 18:50:17
Back to Top
HTML Embed Code: