Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#TeamEthiopia 🇪🇹

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ልዑክ ቡድን የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር መክፈቻ ስነ ስርዓት አምርቶ በስፍራው ይገኛል።

ብሔራዊ ልዑክ ቡድናችን በሀገር ባህላዊ አልባሳት ደምቆ የመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ለመካፈል ወደ ስፍራው አቅንቷል።

የ20 ኪሜ የርምጃ ተወዳዳሪው አትሌት ምስጋና ዋቁማ እና የ50ሜ የነጻ ቀዘፋ የውሀ ዋና ተወዳዳሪዋ ሊና አለማየሁ ሰንደቅ ዓላማችንን በመያዝ ይመሩታል።

ብሔራዊ ልዑክ ቡድናችን የመክፈቻው ፕሮግራም ከጀመረ በኋላ ተራ ቁጥር 65ኛ ላይ ስንገኝ የሰንደቅ ዓለማችንን ይዘው የሚታዩ ይሆናል።

ቪድዮ ምንጭ ፦ ሲሳይ ዮሐንስ ( የፕሬስ አታሽ )

Via @tikvahethsport 
“ መሬት እንቁ የሆነበት ዘመን ስለሆነ ሁሉም አሰፍስፎ ዓይኑ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሆኗል ” - ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በየካ ክፍለ ከተማ የኮተቤ ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን እድሳት መርቀዋል።

የቤተ ክርስቲያኗ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ፣ ለአስፋልት ንጣፉ ቁፋሮው ስራ በአንድ ወር እንደተጠናቀቀ ገልጸዋል።

በቅጥር ግቢ የአስፋልትና የቴራዞ ንጣፍ፣ የምዕመናን እድሳት ማረፊያ እድሳትና የመሳሰሉት ተግባራት መከናወናቸው አስረድተዋል።

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በበኩላቸው፣ " ከደብሩ በሚስማማ ምድራዊ ገነት በሚመስል መልኩ ቅጥር ግቢው እንደለማ በመግለጽ የእንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል። 

ኢትዮጵያዊያን የሚሰሯቸው ህንፃዎች ከ30 ዓመታት በላይ የሚያስቆጥሩ መሆናቸውን መስክረው፣ የሰው ልጅ ግን እየተዘነጋ መሆኑን አስምረውበታል።

“ ህንጻ መስራቱ ለትውልድ የሚተላለፍ ሆኖ ነገር ግን ህንፃ ሥላሴ ደግሞ (ካህናቱ፣ አገልጋዮቹ፣ ምዕመናኑ) የሚበላ፣ የሚላስ ነገር በማጣት እየተቸገሩ መሆኑን ዘንግተናል ብዬ አስባለሁ ” ነው ያሉት።

ብፁዕነታቸው አክለው፣ “ ትልቁን ህንፃ እንሰራለን ህንፃ ሥላሴ (የሰው ልጅ) ግን ወደ መዘንጋት የደረሰ ይመስለኛል ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ 50፣ 50 ማድረግ ብንችል ! በጎን ልማቱን የማፋጠን ሥራ፣ ሥራ አጥ የሆኑ ልጆቻችን ሥራ የሚያገኙበትን ሥራ መስራት ትችላለች ቤተክርስቲያኗ ” ብለዋል።

“ ቤተ ክርስቲያኒቱ ብዙ አቅም አላት። ያንን አቅም የማስተዳደር፣ የማሰባሰብ፣ ባለሃብቶችን ጋብዛ ባላት መሬት ላይ ልማት እንዲያለሙ በማድረግ ገቢ የመፍጠር ሥራን ጎን በጎን ደግሞ ብትሰራ ጥሩ ነው ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

“ እንደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሬት አስተዳደር በኩል የወጣ አንድ ፕሮጀክት አለ ” ብለው፣ በዚያ መሠረት አባላት ወደ ልማት እንዲየመሩ ስልጠና በመስጠት የማንቃት ስራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

መንግስት የልማት ሥራ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ብፁዕነታቸው፣ “ ቤተ ክርስቲያንም ጎን በጎን ተሯሩጣ ልማትን ካላለማች ቆሞ ቀር ትሆናለች፣ ትወቀሳለች ” ብለዋል።

አክለው፣ “ ያላትም መሬት ደግሞ እንዳይወሰድ ስጋት አለን። ባላት መሬት ላይ ልማት ልታለማ ይገባል ” ነው ይሉት።

“ መሬት እንቁ የሆነበት ዘመን ስለሆነ ሁሉም አሰፍስፎ ዓይኑ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሆኗል። እኛ ተኝተን ሌሎች መጥተው እንዳይወስዱብን ነቅተን በንቃት፣ በብልሃት እና በጥበብ ወደ ልማት መግባት ከእኛ ይጠበቃል ” ሲሉ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Tassa Tassa Tasssa ! በጎፋ ዞን ፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችን የማጽናናት እና የመደገፍ ስራ እየተሰራ ነው። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች ድጋፋቸውን ይዘው ወደ ስፍራው በመሄድ አስረክበዋል። በርካቶች ተጎጂዎችን ለማጽናናትና ለመደገፍ ወደ ስፍራው በየዕለቱ እየተጓዙ ይገኛሉ። በቁሳቁስ ከሚደረገው…
#ጎፋ 🕯️

“ ህብረተሰቡ እየተረባረበ አስከሬኖችን በቻሉት ልክ እያወጡ ነው። ቁፋሮው እንደቀጠለ ነው ” - ጎፋ ዞን

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከቀናት በፊት በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾችን አስክሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራው እንደቀጠለ መሆኑን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።

ቃላቸውን የሰጡት የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት አቶ ገነነ እንዳሻው፣ ቁፋሮው እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል።

ቁፋሮ እንደቀጠለ ከሆነ የሟቾች ቁጥር ስንት ደረሰ ? ለሚለው ጥያቄ “ ተገምግሞ ‘ ከአንድ ቋት መረጃ መውጣት አለበት ’ ስላሉ አሁን እንዲህ አይነት መረጃዎች እየወጡ አይደለም ” ሲሉ መልሰዋል።

ድጋፉን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ “ ድጋፉ ከመላ ሀገሪቱ እየመጣ ነው። ክልሎች ዞኖችም ድጋፍ እያመጡ ነው። በድጋፉ በኩል ብዙም ክፍተት የለም። ጥሩ እንቅስቃሴ አለ ” ብለዋል።

በአደጋው ለተጎዱት ምን ያህል ድጋፍ ያስፈልጋል ? ምን ያህል ሰዎችስ ድጋፍ ይሻሉ ? ተብሎ ላቀረብነው ጥያቄ ፣ “ አልታወቀም ገና ሟቾችም፣ ሁሉም ነገር ስላልተለዬ ” ነው ያሉት።

አደጋው የተፈጠረበት አካባቢስ ስንት ቤቶች ናቸው የወደሙት ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ መጀመሪያ ላይ የወደሙት 3 ቤቶች ናቸው። አጠቃላይ አካባቢው ላይ 12 ቤቶች ናቸው የወደሙት ” ሲሉ መልሰዋል።

“ መጀመሪያ 3 ቤቶች ላይ ነው አደጋው የደረሰው። 3 ቤቶች ላይ 6 ሰዎች ሞተው ነው ነፍስ አድን ሊሰሩ የሄዱ ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ” ብለዋል።

አክለውም ፣ “ አደጋው በ3 ቤቶች ላይ ከደረሰ በኋላ ነው። አካባቢው ላይ 12 ቤቶች ነው ያሉት (ወረድ ብሎ ናዳው የደረሰበት ቀበሌ ላይ ሳይሆን ከላይ)። 12 ያክል ቤቶች ተጎድተዋል ” ሲሉ አስረድተዋል።

የተፈናቀሉ ሰዎችስ ስንት ናቸው ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ “ ብዙም ስላልተደመደመ አሁን ቁጥራዊ መረጃዎችን በውል አላውቃቸውም ” ነው ያሉት።

“ አካባቢው ለማሽን ይከብዳል የገባ ማሽንም የለም ” ያሉት አቶ ገነነ፣ “ ከዚያ አንፃር በሰው ኃይል ነው እየተቆፈረ ያለው። እጅግ አድካሚ ነው። ሆኖም ግን ህብረተሰቡ እየተረባረበ አስከሬኖችን በቻሉት ልክ እያወጡ ነው ያሉት ” ብለዋል።

ዛሬ (አርብ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ/ም) ጠ/ሚ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስፍራው ሊመጡ እንደነበር በአጋጣሚ አየሩ ደመናማ ሆኖ ለጉዞ ባለመመቸቱ እንዳልመጡ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን
#ኮደሮችን ለማሰልጠን ያለመ ፕሮጀክት አስጀምራለች።

ለ3 ዓመታት ያህል የሚቆየው ይሄ ፕሮጀክት ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው ተብሏል።

ምን መማር ይቻላል ?

- Android Kotlin Development Fundamentals
- Data Science Fundamentals
- Programming Fundamentals

ትምህርቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል ?

ስልጠናዎቹ በዩዳሲቲ (Udacity) በተሰኘው ኦላይን የትምህርት ፕላትፎርም ተዘጋጅተው የቀረቡ ናቸው።

ሰልጣኞች ያለ አንዳች ክፍያ በነጻ ኮምፒውተራቸውን ወይም ስልካቸውን በመጠቀም መሰልጠን ይችላሉ።

ስልጠናዎቹ 6-7 የሚሆኑ ሳምንታትን የሚፈጁ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ ሞያዊ ሰርተፊኬት ይሰጣል።

የስልጠናዎቹን ይዘት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች በተዘጋጀው ድረ-ገጽ (
https://ethiocoders.et/ ) ላይ መመልከት ይችላሉ።

@tikvahethiopia
Applications for the Jasiri Talent Investor Program Cohort 7 are now open!

If you are a highly skilled individual, we at Jasiri deeply care about how you choose to use your skills. We have a place for you because we believe entrepreneurship is the most effective way to impact the world.

Apply now at jasiri.org/application

#Jasiri4Africa
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የ3 ቀን ብሔራዊ ሐዘን ዛሬ ጀምሯል።

ዛሬ በጀመረው ብሔራዊ የሐዘን ቀን በጎፋ ዞን፣  ገዜ ጎፋ ወረዳ ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሽራተት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡና የተጎዱ ወገኖቻችን ይታሰባሉ።

በነዚህ ብሔራዊ የሐዘን ቀናቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች ፤ በሁሉም የኢትዮጵያ መርከቦች ፤ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤቶች የሪፐብሊኩ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እየተወለበለበ ይገኛል።

#Ethiopia #GOFA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎፋ 🕯️ “ ህብረተሰቡ እየተረባረበ አስከሬኖችን በቻሉት ልክ እያወጡ ነው። ቁፋሮው እንደቀጠለ ነው ” - ጎፋ ዞን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከቀናት በፊት በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾችን አስክሬን በቁፋሮ የማውጣቱ ስራው እንደቀጠለ መሆኑን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል። ቃላቸውን የሰጡት የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት አቶ ገነነ እንዳሻው፣ ቁፋሮው እንደቀጠለ መሆኑን…
#Update

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ ተገኝተዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፣ ከቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ ፣ ከፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በማሆን በገዜ ጎፋ ወረዳ ተገኝተው በመሬት ናዳ የተጎዱ ወገኖችን እያጽናኑ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንትና ወደ ስፍራው ሊያቀኑ የነበረ ቢሆንም አጋጣሚ አየሩ ዳመናማና ለጉዞ አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት እንደቀሩ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

° " የከተማዉ ከንቲባ ሙሉ ደሞዛችን በሂደት እንደሚከፈለን ቃል ገብተው ወደስራ ብንመለስም ፈርማችሁ ስራ ጀምሩ መባላችን አስፈርቶናል " - ሰራተኞች

° " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተው እንደወጡ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


ከሰሞኑ " የሶስት ወር ደሞዝ ዘግይቶብናል " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ስራ ማቆማቸውን ይህን ለማሳወቅም ወደዞኑ ዋና ከተማ ሲያቀኑ ፖሊስ " ሆሳዕና አትገቡም " ብሎ ከከተማው መግቢያ እንዳስመለሳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ሰራተኞቹ ምንም እንኳን ወደዞኑ አመራሮች ቀርበው አቤቱታቸውን ባያቀርቡም ስራ አቁመው መሰንበታቸዉን ተከትሎ የሾኔ ከተማ ከንቲባና ሌሎች ባለስልጣናት አወያይተዋቸው ነበር።

በውይይቱም የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ማለትም የሰኔን ቅድሚያ  እንዲወስዱና ቀሪውን የግንቦት ወር ደግሞ በሂደት እንደሚያገኙ ከንቲባው ቃል ገብተውላቸው ወደስራ ቢመለሱም እስካሁን ስራ በማቋረጣችሁ የይቅርታ ደብዳቤ አስገቡ መባሉን ተከትሎ ስራውን መጀመር አለመቻላቸውንና መፈረም የሚለዉ ሀሳብ እንዳስፈራቸው ገልጸዉልናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከቀናት በፊት ወደስራ ከገቡ በቃል ሪፖርት አድርገው ስራቸዉን መጀመር ይችላሉ ያሉን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ሎምቤ ምን ሀሳባችሁን ቀየራችሁ ? ስንል ላቀረብንላቸዉ ጥያቄ " ሀሳብ መቀየር ሳይሆን የድርጅቱ አሰራር ስለሆነ ነው " ሲሉ መልሰውልናል።

" ሰራተኞቹ ፍርሀት ሊሰማቸው አይገባም " ያሉት ስራ አስኪያጁ " ህጋዊ ደብዳቤ አስገብተዉ እንደወጡ ሁሉ ህጋዊ ደብዳቤ  አስገብተው ሊመለሱ ይገባል ይህ ደግሞ ሊያስፈራቸዉ አይገባም ብ ጉዳዩ ችግር የለውም ብለን አስረድተናቸዋል " ሲሉም ገልጸዉልናል።

አሁን ላይ የተወሰኑ ሰራተኞች ፈርመዉ ስራ ሲጀምሩ  የተወሰኑት ፊርማዉን ባለመፈረማቸው ምክኒያት ወደስራ አለመመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ሰራተኞቹ ያለፈው የደከሙበት ደመወዛቸውን ተብልቶ ይቀራል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ሳይናገሩ አላለፉም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
መቐለ እና የወንጀል የተግባር መስፋፋት !

" ፀጥታ እና ሰላም ከሌለ ሁሉም የለም "
- የመቐለ ከንቲባ

በመቐለ ከተማ በያዝነው ዓመት ከአምናው በ1,841 በመቶኛ ሲሰላ 68 ፐርሰንት / የሚበልጥ የወንጀል ተግባር መፈፀሙ የከተማዋ የሰላምና የፀጥታ ዘርፍ አስታውቋል።

በ2015 ዓ/ም ላይ የተፈፀሙት የወንጀል ተግባራት 2,895 ሲሆኑ በያዝነው 2016 ዓ/ም 4,735 የወንጀል ተግባራት ተፈፅሟል።

ይህ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ የ1,841 የወንጀል ተግባራት መጨመር አሳይቷል።

" ፀጥታ እና ሰላም ከሌለ ሁሉም የለም " ያሉት የከተማዋ ከንቲባ ይትባረኽ ኣምሃ " ለፀጥታና ሰላም መጠበቅና የወንጀል ተግባር ለመቆጣጠር የሚያግዙ የድህንነት ካሜራዎች በተለያዩ የከተማ አከባቢዎች በመገጠም ላይ ናቸው " ብለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በህገ-ወጦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ " በከተማዋ የሚካሄደው ህግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል " ያሉት ከንቲባው እስካሁን በምን የወንጀል ተግባር የተሳተፉ ፣ ምን ያህል ፣ እነማን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ በይፋ አልገለፁም። 

መቐለን ጨምሮ ሌሎችም ከተሞች ከደም አፋሳሹ ጦርነቱ በፊት በዚህ ልክ ወንጀል ተስፋፍቶባቸው አያውቅም።

በተለይም መቐለ ከተማ በደህንነት እና በጸጥታ ረገድ አንጻር ቀንም ማታም መንቀሳቀስ የሚቻልባት ነበረች። ወንጀልም በዚህ ልክ የተስፋፋባት ከተማ አልነበረችም።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
" ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የምሽት በረራ እንጀምራለን " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እንዲሁም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ የምሽት በረራ የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ TPLF ምን አሉ ? ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦ " የምርጫ ቦርድ ' ምርጫ አራዝማለሁ ' ሲል ብዙዎቻችን ስንስማማ TPLF አልስማማም ብሎ የገባንበት ቀውስ ይታወሳል። ምን ያክል ሰው እንደወደመ፣ ምን ያክል ሃብት እንደወደመ መገመት ይቻላል። ያ የወደመ የሰው ህይወት እና የወደመ ሃብት በትክክል ሳይገመገም እንዴት ጠፋ ሳይባል ሌላ ጥፋት ማምጣት ጥሩ አይደለም። ህዝቡ ይጎዳል።…
#TPLF

" ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር ግጭት አይኖርም  " - የህወሓት ሊቀመንበር

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ዛሬ ሀምሌ 20/2016 ዓ.ም በክልሉ ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር። 

በዚህም ፥ ከ2 ቀናት በፊት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን ነው ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ ድርጅታቸው ህወሓት በሁለት ሳምንት ውስጥ እውቅና እንዲሰጠው የፌዴራል መንግሥትን መጠየቃቸውን አመልክተዋል።

" ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር አንዳች ግጭት የለም " ያሉ ሲሆን " በአዲስ አበባ በነበረን ውይይትም ጥሩ መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyaMK

@tikvahethiopia            
2024/10/01 02:27:06
Back to Top
HTML Embed Code: