#የጤናባለሞያዎች
" የ5 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ አልተከፈለንም ! አፋጣኝ ምላሽ እንፈልጋለን " - በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የንግስት እሌኒ መሐመድ ሆስፒታል ሰራተኞች
" በጀቱ ስለተለቀቀልን ክፍያዉን በሁለት ቀን ውስጥ እናጠናቅቃለን ተረጋጉ " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ
በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሀመድ ሆስፒታል ውስት የሚሰሩ ሰራተኞች 5 ወር ሙሉ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ለወራት የትርፍ ሰአት ክፍያ ስንጠይቅ ነበር " ያሉት ሰራተኞቹ ከሰሞኑ ድምጻቸዉን ለማሰማት ሰልፍ ለመውጣት መገደዳቸውን አመልክተዋል።
" የዘገየዉ ገንዘባችን ይሰጠን !! " ሲሉም ለሚመለከተዉ አካል መልእክታቸዉን አሰምተዋል።
" የኑሮ ዉድነት ምን ያክል ፈተና እንደሆነብን እየታወቀ የትርፍ ሰአት ክፍያችን በጠየቅን ቁጥር ቀጠሮ መስጠት የማይሰለቸዉ የሆስፒታሉ አስተዳደር ትእግስታችን ተፈታትኖታል " የሚሉት ሰራተኞቹ " ከዚህ በላይ መታገስ የምንችልበት ሁኔታ ላይ ባለመሆናችን ጥያቄያችን በቶሎ ይመለስ " ሲሉ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞቹን ጥያቄ ይዞ የሆስፒታሉን ስራ አስኪያጅ ዶክተር አያኖ ሻንቆን አነጋግሯል።
" ምንም እንኳን ችግሩ የታወቀ ቢሆንም የ5 ወር መዘግየት ሰልፍ የሚያስወጣ አልነበረም " ብለዋል።
አሁን ላይ ክፍያዉን ለማጠናቀቅ ቢበዛ 2 ቀናት ብቻ እንደሚበቃቸዉ ገልጸዋል።
የገንዘብ እጥረቱ የተከሰተዉ የነበረውን የበጀት እጥረት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲው ቅድሚያ ለተማሪ በማለቱ እንደሆነ አስረድተዋል።
" አሁን ላይ በጀቱ ተለቋል " ብለዋል።
ለክፍያው የተፈቀደው ገንዘብ በጽሁፍ እንጅ በካሽ አለመለቀቁን ተከትሎ ክፍያዉ በቶሎ አለመጀመሩን የገለጹት ስራ አስኪያጁ ፥ " አሁን ገንዘቡ በመድረሱ በ2 ቀን ውስጥ ክፍያዉ ይጠናቀቃል " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
@tikvahethiopia

" እኔ ያያሁት 3 ሰዎች ሞተዋል እና የቆሰሉ ሰዎችም ነበሩ " - ነዋሪ
በአዳማ ከተማ ፤ በቦኩ ሸነን ክፍለ ከተማ ሀሮሬቲ ወረዳ እና ቶርበን ኦቦ ወረዳ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የሰው ሕይወት ማለፉና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ለመስማት ችለናል።
በነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞ እንዲቀሰቀሰ ምክንያት የሆነው የከተማ አስተዳደሩ በወረዳዎቹ የሚገኙ ቤቶችን ሕገ-ወጥ ናቸው በሚል የማፍረስ ሂደት ሊጀምር ሲል መሆኑን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም ይፈርሳሉ ያሏቸውን ቤቶች በቀይ ቀለም " X " እያረጉ እንደነበር እና ዛሬ ለማፍረስ ሲመጡ ነዋሪዎች ተቃውሞ እንዳነሱ ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሎች ተኩስ መክፈታቸውን አንድ የዐይን እማኝ አስረድተዋል።
ቦታዎቹ ላለፉት ዓመታት ግብር ሲከፈልባቸው የነበሩ እንደሆኑም ጠቁመዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የአከባቢው ነዋሪ እንዳሉት " በተቀሰቀሰው ግጭት እኔ ያያሁት 3 ሰዎች ሞተዋል እና የቆሰሉ ሰዎችም ነበሩ። በዛ አከባቢ ከሰዓት በኋላ እንቅሰቃሴ አልነበረም። ሁሉም ሰው በቤቱ ውስጥ ተቀምጧል እና በአጠቃላይ ያለውን ነገር ማወቅ አልቻልንም " ሲሉ ገልጸዋል።
ከማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያገኘናቸው ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ የያዙ በርካታ ሰዎች ተቃውሞቸውን ለማሰማት መንገድ በመዝጋት እና " ፈረሳው ይቁም !! " የሚሉ መፈክሮች እየሰሙ እንደነበር ነው።
በሌላ አንድ ቪዲዮ ላይ ነዋሪዎቹ በዱላ እንዲሁም በድንጋይ መንገድ ዘግተው እንደነበር ተመልክተናል።
ነዋሪው ተቃውሞውን ማሰማት በጀመረበት ወቅት ተኩስ መጀመሩና በሰልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች ሲበታተኑም ተመልክተናል።
በዚህ ውስጥ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዐይን እማኞች መስማት የቻለን ቢሆንም ምን ያህል ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ ማረጋገጥ አልተቻለም።
ከከተማው አመራርና የጸጥታ አካላት ጉዳዩን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
#TikvahEthiopiaFamilyAdama

TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቄያቸው ሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማይ ፀብሪ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል " ሲል አሳውቋል። ከ3 ዓመት በላይ በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ለመጓዝ ዝግጁ እንዲሆኑ አርብ ማታ ተነግሯቸው…
#Update
የሀገር መከላከያው ስለ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ እንቅስቃሴ ምን አለ ?
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ብርሃኑ በቀለ ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።
የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነትን መሰረት በማድረግ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሀገር መከላከያው ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንዲያስተባብር አቅጣጫ ተሰጥቶ እየሰራ እንዳለ አመልክተዋል።
የፀለምት እና አካባቢው ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ ኃላፊነት የተሰጠው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ መሆኑን ተናግረው " ስራው እጅግ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው " ብለዋል።
ዛሬን ረቡዕ ጨምሮ ባለፉት ቀናት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቄያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ሌ/ጄነራሉ ፥ ተፈናቃዮች እየተመለሱ ያሉት አስፈላጊና መሟላት አለባቸው የተባሉ ቅድመ ሁኔታዎች ከጎን እየተሰሩ ነው ብለዋል።
ስራው በፍጥነት እየሄደ ያለው አብዛኛዎቹ አርሶ አደር የክረምቱ ወቅት ሳያልፍ እርሻውን እንዲሰራና ህይወቱን እንዲመራ በማሰብ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በፀለምት ካሉ 25 ቀበሌዎች አብዛኛው ተፈናቃይ ከ22 ቀበሌዎች ነው አሁን ባለው ሁኔታ በአስራዎቹ ቀበሌዎች ተፈናቃይ ተመልሷል ፤ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀሪ 11 ቀበሌዎች አብዛኛው እንዲገባ ይደረጋል ሲሉ አሳውቀዋል።
የቀረውም ስራ በቀጣይ ይሄዳል ብለዋል።
ስለ ታጣቂዎች መውጣት ምን አሉ ?
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የትግራይ ታጣቂዎች በኃይል ገብተዋል " ስለሚባለው ጉዳይ ሌ/ጄነራሉ ፥" ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ በፀለምትም ይሁን በወልቃይት በኃይል የገባባቸው ቦታዎች የሉም " ሲሉ መልሰዋል።
ፀለምት ካሉት ቀበሌዎች 3 ቀበሌዎች ላይ የትግራይ ታጣቂዎች እንዳሉ እነዚህም ጦርነት ሲቆም ባሉበት የቆሙ ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።
ባለው መግባባት ከሁለቱም ክልል ጋር የሁለቱም ክልል ታጣቂ መውጣት ስላለበት ተፈናቃዮችን በመመለስ ታጣቂዎቹን የማስወጣት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዚህም ፀለምት ያለው የትግራይ ታጣቂ እንዲወጣ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ከተፈናቃይ ጋር ታጣቂ እንዳይመለስ ስለሚሰራ ስራ ምን አሉ ?
በአማራ በኩል " ከተፈናቃይ ጋር ታጣቂ ይገባል " የሚል ስጋት እንዳለ ያልሸሸጉት አዛዡ ፥ በትግራይ በኩልም " ታጣቂዎች (በአማራ በኩል ያሉ) እንደ አዲስ ተደራጅተዋል ስጋት ናቸው " የሚል ነገር እንዳለ ገልጸዋል።
" የሀገር መከላከያው ከሁለቱም በኩል ከተፈናቃዮች እና እዛው ከነበሩት ነዋሪዎች ( ካልተፈናቀሉት ) ሽማግሌዎች እንዲውጣጡ አድርጎ የተፈናቃዮችን ዝርዝር ለመከላከያ ተሰጥቶ ከዛም መከላከያው ከሽማግሌዎቹ ጋር አብሮ ሰዎቹ የዛ ቦታ ነዋሪ መሆናቸውን እየጠየቀና እያረጋገጠ ተፈናቃዮች ይመለሳሉ " ብለዋል።
' ይሄ ታጣቂ ነው ፣ ይሄ ሚሊሻ ነው ' የሚል ክርክር በሽማግሌ ደረጃ ከተነሳ ወደ ህዝብ ተወስዶ ህዝቡ እራሱ ይፈርዳል ሲሉ ተናግረዋል።
" እንግዳ ሰው ሲገባ ይታወቃል ይህ ጉዳይ አሳሳቢ አይደለም " ያሉት አዛዡ ፥ ገጠር ይሁን ከተማ መሬት ከሌላቸው / ሊገቡበት የሚችሉበት ቤት ከሌላቸው ተለይቶ ይታወቃል ብለዋል።
#Ethiopia
#FDREDefenseForce

#Update የሀገር መከላከያው ስለ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ እንቅስቃሴ ምን አለ ? የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ብርሃኑ በቀለ ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነትን መሰረት በማድረግ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል። ሀገር መከላከያው ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንዲያስተባብር አቅጣጫ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ በጦርነት ከፀለምት እና አካባቢው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን ወገኖች ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
በርካታ የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ተፈናቃዮችን እያደረሱ ነው።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማስተባበር ኃላፊነት እየተወጣ ነው።
በፀለምት ውስጥ ካሉ 25 ቀበሌዎች በአብዛኛው ከ22ቱ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
እነዚህን ዜጎችን ነው በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የተገለጸው።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በቀጣይም የሌሎች አካባቢዎች ተፈናቃዮች እንደሚመለሱ አሳውቋል።
Video Credit - DW

የአሜሪካ ኤምባሲ ነገ ለምን ተዘግቶ ይውላል ?
በአዲስ አበባ የአሜሪካ አሜባሲ ነገ ሀሙስ ሙሉ ቀን ተዘግቶ ይውላል።
የሚከፈተውም በነጋታው አርብ ዕለት ነው።
ኤምባሲው ተዘግቶ የሚውለው የሀገሪቱን የነጻነት ቀን ለማክበር ነው።
አሜሪካ በየአመቱ እኤአ ሃምሌ 4 ላይ የነጻነት ቀኗን ታከብራለች።
ሀገሪቱ እኤአ በ1776 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ በ1769 ዓ.ም ነው ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷዋን ያወጀችው።

#CHAPA
የይለፍ ቁጥሮን ባለማጋራት ራስዎን ካጭበርባሪዎች ይጠብቁ!
🚫አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ ወደ 📞8911 በመደወል ሪፖርት ያድርጉ
🌐 ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ፡ https://chapa.co/
#chapa #chapapayments #Fraudawareness #Digitalpayment

#HoPR
ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተዋል።
በስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
በአሁን ሰዓት የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው።

#የጤናባለሙያዎች
° “ የ3 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተሰጠንም ” - የጤና ባለሙያዎች
° “ ለጉዳዩ ምላሽ መስጠት ያለበት ወረዳው ነው ” - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ
° “ የጀበት ችግር ገጥሞን ነው ” - የኪንፋዝ በገላ ጤና ጽ/ቤት
በአማራ ክልል፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኪንፋዝ በገላ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች ከሚያዚያ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።
የጤና ባለሙያዎቹ፣ “ የ3 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተሰጠንም። ስንጠይቃቸውም ‘ አንከፍልም ’ ነው የሚሉት ” ብለው፣ ክፍያው እንዲፈጸምላቸው ጠይቀዋል።
የቅሬታ አቅራቢዎቹ ብዛት ከ30 በላይ እንደሆነ፣ የክፍያ መጠኑ እንደዬደረጃቸው እንደሚለያይ ገልጸው፣ ይህ ቅሬታ የተፈጠረው ፦
- በስላሬ
- በጭቅቂ
- በሮቢት በገላ በተሰኙ 3 የወረዳው ጤና ጣቢያዎች መሆኑን አስረድተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች የጤና ኤክስቴንሽን፣ ጤና ሙያተኞች ደህንነታችን ዋስትና ሳይሰጠው ‘ የክትባት ዘመቻ ካልዘመታችሁ ’ እየተባልን በስጋት ውስጥ ነው ያለነው ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎቹን ቅሬታ ይዞ የዞኑን ጤና መምሪያ አነጋግሯል።
ለምን ብራቸውን አትከፍሏቸውም ? ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ ፤ “ለጉዳዩ ምላሽ መስጠት ያለበት ወረዳ ነው። በወረዳው በጀት ዞን ጤና መምሪያው የሚመለከተው ስላልሆነ ” ብሏል።
ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ገ/ህይወት በሰጡት ቃል፣ “ የበጀት እጥረት ገጥሞን ነው ” ብለዋል።
ታዲያ ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግራችሁ ነበር ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ በሚቀጥው በአዲሱ በጀት ተይዞ ይከፈላቸዋል ” ነው ያሉት።
“ ለዚህም ደግሞ አስተዳደሩ ደብዳቤ ጽፏል። ‘በቀጣይ እከፍላለሁ’ የሚል ” ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ባለሙያዎቹ ' የጸጥታ ችግር ባለበት ለክትባት ውጡ ተብለናል ' የሚል ቅሬታ አላቸው፤ ለመሆኑ ይህን ስታደርጉ ለደህንነታቸው ከለላ ታደርጉላቸዋላችሁ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
ኃላፊው በምላሻቸው፣ “ የጸጥታ ችግር የሌለበት የለም። ዞሮ ዞሮ ግን በሚቻለው አግባብ የአገር ሽማግሌዎችን ይዘን እንሰራለን ” ነው ያሉት።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#HoPR ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተዋል። በስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ በአሁን ሰዓት የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው። @tikvahethiopia
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?
" አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ ላይ ናቸው ?
በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው።
የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል።
መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው።
ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመወጣትና የህዝቡን ጥያቄ ለመፍታት በምን ደረጃ ታቅዷል። "
(አቶ አቤነዘር በቀለ - የተ/ም/ቤት አባል)

የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? " አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ ላይ ናቸው ? በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው። የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል። መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው። ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት…
#HoPR
" ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?
አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦
" ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ።
ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና ለመዋጋት ብሔራዊ የጸረሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን ብንሰማም አርቂ ስራ ሲሰራም ሆነ በሙስና ምክንያት ያንዣበበውን ሀገራዊ አደጋ ለመቀልበስ እርባና ያለው ስራ ሲሰራ አልታየም።
በአጠቃላይ መንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ይሄ ነው የሚባል መፍትሄ እየሰጠ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱም ላይ ጥያቄ ይነሳል።
ምክንያቱም የህዝብ እና የመንግስት ሀብት በዘረፉ ሙሰኛ ባለስልጣናት ላይ መቀጣጫ የሚሆን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ተጨማሪ ሹመት እና የቦታ ዝውውር በመስጠት መንግስት ሙሰኞችን አብሮ አቅፎ ይኖራል ማለት ይቻላል።
ከዚህ የተነሳ ፦
➡ የመንግስት መዋቅር በሌቦች ተጠልፏል።
➡ ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል።
➡ ዜጎች የዕለት ኑሯቸውን ለመግፋት በአደባባይ ገንዘብ እየተጠየቁ ነው።
➡ ከፍተኛ የሀገር ሀብት ከሀገር ወጥቶ እየሸሸ ነው።
➡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት እያባከኑ ነው።
➡ በኦዲት ሪፖርት መሰረት በየመ/ቤቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ይታያል።
➡ መ/ቤቶች ገንዘብ ያለማስረጃ ወጪ በማድረግ ይጠቀማሉ ፣ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ በወጪ ይመዘግባሉ፣ ከፋይናንስ መመሪያና ደንብ ውጭ የገንዘብ ክፍያ ይፈጸማል።
እንደሚታወቀው ብዙ ሀገራት ለችግሩ በሰጡት ትኩረት የማያወላውል እርምጃ ስለወሰዱ ችግሩን ማቃለል ችለዋል።
ለምሳሌ በቅርቡ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ለልምድ ልውውጥ የጎበኟቸው የእስያ ሀገራት እነ ሲንጋፖር ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ ስንመለከት ለእድገታቸው ዋናው መሰረት በሙስና ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት ነው።
በሀገራችን የሌብነት ችግር ለመቅረፍ አፋጣኝ እና አስተማሪ የሚሆን እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር የጸረ ሙስና ህጋችንን አሻሽለን ቢሆን በሀገራችን አሁን የምናያቸው ፈተናዎች ተደምረው ሙስና የሀገራችንን ህልውና መፈተኑ አይቀርም።
ክቡር ጠ/ሚኒስትር በህዝቡ የሚቀርበው ተደጋጋሚ ቅሬታና የጄነራል ኦዲተር መ/ቤት በማስረጃ አስደግፎ ያቀረበልን ስር የሰደደ የሙስናን ችግር ለመቅረፍ መንግስትዎ ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ?
በተደጋጋሚ እንደታዘብነው ቃል ከመግባት ባለፈ ምን ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ታስቧል ?
ህዝቡስ ከመንግስትዎ ምን ይጠብቅ ? "

#HoPR " ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦ " ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ። ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና…
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦
" የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል።
ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው።
መንግስት በህዝብ ዘንድ እምነት አልገነባም ብለን እናስባለን። ይሄም የሚገናኘው ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር ነው።
ባለፉት 10 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል።
ከነዚህ ጥሰቶች ውስጥ የጅምላ ግድያ፣ በሰብዓዊ / ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች።
ጥቂቱን ለመጥቀስ በመርዓዊ ፣ በጅጋ ፣ በደብረ ኤልያስ ፣ በፍትኖተ ሰላም፣ ደብረሲና አካባቢ ፣ ጎንደር እና ወሎም እንዲሁ ተፈጽሟል።
ይህንንም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋማት የዘገቡት የአይን እማኞችም የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው።
ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጾታዊ ጥቃት፣ ድብደባ ፣ ዘረፋ ፣ ንብረት ማውደም ፣ የሲቪል ተቋማት በጤና ፣ በትምህርት ተቋማት ላይ ውድመት እንደደረሰ በርካታ ምስክሮች ገልጸዋል።
ሌላው የሰብዓዊ መብት ችግር በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ምክንያት በርካታ ፖለቲከኞች የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ታስረዋል።
ከዚህ ባለፈ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች፣ አጠቃላይ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በተለይ በአማራ ክልል አማራዎች በጅምላ ለወራት በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
የምክር ቤት አባላትን ስናነሳ የምክር ቤት አባላችን አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኖ መንግስትን ከምዝበራ ያዳነ በሰላማዊ ትግልም በእጅጉ የሚያምን ሰው ነው አንድ አመት ለሚሞላ ጊዜ በእስር እየማቀቀ ያለው።
ሌሎችም በለውጡ ከእርሶ ጋር አብረው የሰሩ እንደ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ፣ ዶ/ር ካሳው ተሻገርና አቶ ታዬ ደንደአ ያሉም ለውጡ ስህተት ፈጽሟል በትክክለኛው ጎዳና እየሄደ አይደለም ብለው ስለሞገቱ ብቻ ለወራት ታስረዋል።
ከዚህ የከፋው ግን የት እንኳን እንደታሰረ የማይታወቅ አንድ የአብን አባላችን ነው ሀብታሙ በላይነህ ይባላል።
ሀብታሙ በላይነህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ነው። እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነው። ላለፉት 4 ወራት የት እንደገባ አይታወቅም። ይህን ጉዳይ ቤተሰቡም እኔም ለተለያየ የመንግስት ኃላፊዎች አቤት ብለናል ምላሽ አላገኘንም። ዛሬ እርሶ ምላሽ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ እንማጸናለን።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ልክ እንዳበቃ ህጋዊ አሰራሩ ይቀጥላል ብለን እንገምት ነበር ነገር ግን አዋጁ አብቅቶ በኮማንድ ፖስቱ እየተዳደርን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
የጅምላ እስር አሁንም አለ፣ ህገመንግስቱ በትክክል እየሰራ አይደለም። በደረቅ ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ብቻ መጠየቅ ሲገባቸው አሁንም በፖለቲካ አመለካከታቸው ዜጎች በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
ስለዚህ ህብረተሰቡ ስለ ሽግግር ፍትህና ስለ ሀገራዊ ምክክር መንግስት ሲያወራ ይመነው ? እምነት አልገነባንም።
በጅምላ የታሰሩ፣ የህሊና እስረኞች ቢፈቱ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መርምረው አጥፊዎች ተጠያቂ እዲሆኑ ቢደረግ ያኔ እምነት መገንባት ይቻላል።
መንግስት ምን እቅድ አለው እምነት ለመገንባት ? የህሊና እስረኞችን ለመፍታት እና የጅምላ ግድያና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማቆም ምን ወስኗል ? "
#TikvahEthiopia
#HoPR
@tikvahethiopia
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦
" የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል።
ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው።
መንግስት በህዝብ ዘንድ እምነት አልገነባም ብለን እናስባለን። ይሄም የሚገናኘው ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር ነው።
ባለፉት 10 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል።
ከነዚህ ጥሰቶች ውስጥ የጅምላ ግድያ፣ በሰብዓዊ / ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች።
ጥቂቱን ለመጥቀስ በመርዓዊ ፣ በጅጋ ፣ በደብረ ኤልያስ ፣ በፍትኖተ ሰላም፣ ደብረሲና አካባቢ ፣ ጎንደር እና ወሎም እንዲሁ ተፈጽሟል።
ይህንንም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋማት የዘገቡት የአይን እማኞችም የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው።
ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጾታዊ ጥቃት፣ ድብደባ ፣ ዘረፋ ፣ ንብረት ማውደም ፣ የሲቪል ተቋማት በጤና ፣ በትምህርት ተቋማት ላይ ውድመት እንደደረሰ በርካታ ምስክሮች ገልጸዋል።
ሌላው የሰብዓዊ መብት ችግር በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ምክንያት በርካታ ፖለቲከኞች የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ታስረዋል።
ከዚህ ባለፈ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች፣ አጠቃላይ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በተለይ በአማራ ክልል አማራዎች በጅምላ ለወራት በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
የምክር ቤት አባላትን ስናነሳ የምክር ቤት አባላችን አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኖ መንግስትን ከምዝበራ ያዳነ በሰላማዊ ትግልም በእጅጉ የሚያምን ሰው ነው አንድ አመት ለሚሞላ ጊዜ በእስር እየማቀቀ ያለው።
ሌሎችም በለውጡ ከእርሶ ጋር አብረው የሰሩ እንደ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ፣ ዶ/ር ካሳው ተሻገርና አቶ ታዬ ደንደአ ያሉም ለውጡ ስህተት ፈጽሟል በትክክለኛው ጎዳና እየሄደ አይደለም ብለው ስለሞገቱ ብቻ ለወራት ታስረዋል።
ከዚህ የከፋው ግን የት እንኳን እንደታሰረ የማይታወቅ አንድ የአብን አባላችን ነው ሀብታሙ በላይነህ ይባላል።
ሀብታሙ በላይነህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ነው። እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነው። ላለፉት 4 ወራት የት እንደገባ አይታወቅም። ይህን ጉዳይ ቤተሰቡም እኔም ለተለያየ የመንግስት ኃላፊዎች አቤት ብለናል ምላሽ አላገኘንም። ዛሬ እርሶ ምላሽ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ እንማጸናለን።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ልክ እንዳበቃ ህጋዊ አሰራሩ ይቀጥላል ብለን እንገምት ነበር ነገር ግን አዋጁ አብቅቶ በኮማንድ ፖስቱ እየተዳደርን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
የጅምላ እስር አሁንም አለ፣ ህገመንግስቱ በትክክል እየሰራ አይደለም። በደረቅ ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ብቻ መጠየቅ ሲገባቸው አሁንም በፖለቲካ አመለካከታቸው ዜጎች በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
ስለዚህ ህብረተሰቡ ስለ ሽግግር ፍትህና ስለ ሀገራዊ ምክክር መንግስት ሲያወራ ይመነው ? እምነት አልገነባንም።
በጅምላ የታሰሩ፣ የህሊና እስረኞች ቢፈቱ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መርምረው አጥፊዎች ተጠያቂ እዲሆኑ ቢደረግ ያኔ እምነት መገንባት ይቻላል።
መንግስት ምን እቅድ አለው እምነት ለመገንባት ? የህሊና እስረኞችን ለመፍታት እና የጅምላ ግድያና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማቆም ምን ወስኗል ? "
#TikvahEthiopia
#HoPR
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? " አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ ላይ ናቸው ? በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው። የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል። መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው። ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት…
#DrAbiyAhmed
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ለተጠየቀው ጥያቄ ምን መለሱ ?
" የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡
በአንዳንድ ሀገራት ከ60 በመቶ በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡
በኢትዮጵያም የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሸቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው፡፡
በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ይገኛል፡፡
ምርታማነትን ማሻሻልም ሌላኛው ስራ ነው፡፡
በዘንድሮው ዓመት ከዓለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ ተችሏል፡፡
በተጨማሪም መንግስት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ አድርጓል፡፡
ይህ ሁሉ የሚከናወነው የኑሮ ውድነቱ ዜጎቻችን ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለማቃለል ነው፡፡ በዚህም የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ ተችሏል፡፡ "
#PMOEthiopia

#DrAbiyAhmed ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ለተጠየቀው ጥያቄ ምን መለሱ ? " የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአንዳንድ ሀገራት ከ60 በመቶ በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡ በኢትዮጵያም የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሸቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው፡፡ በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት…
ስለ ኑሮ ውድነት ...
" ልማትን የሚያፋጥን መንግስት እዛው ላይ እያለ የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር በጣም ፈታኝ ነው " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ ኑሮ ውድነት ምን አሉ ?
" የኑሮ ውድነት ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሁሉ ዓለም ዋነኛ አጀንዳ ነው።
የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ስብራት፣ ጭንቀት ፣ ውጥረት እንደሆነ መገንዘብ ይገባል። የተለየ ለኢትዮጵያ ብቻ የሆነ ችግር አይደለም።
በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሰሩ የፋይንናንስ ባለሞያዎችን ለማነጋገር ሞክረናል።
ችግሩን ምን ብናደርግ ነው የምንፈታው ? ብለን።
ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ልማትን የሚያፋጥን መንግስት እዛው ላይ እያለ የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር በጣም ፈታኝ ነው።
የኮሪደር ልማት ፣ ህዳሴ ግድብ ምናምን እያልን እዛው ላይ እያለ ኑሮ ውድነትን መቆጣጠር ያስቸግራል ፤ ምክንያቱም በርከታ ሀብት ስለሚፈስ።
ኢንፍሌሽንን ለመቀነስ አንዱ መንገድ እየተፋጠነ ያለውን ልማት መግታት ነው ልማቱን ብንገታው በሌላ መንገድ ከኑሮ ውድነት ያላነሰ የስራ አጥነት ችግር ስላለ አንደኛውን ብንፈታው አንደኛው ቁስል መልሶ ጠልፎ ስለሚይዘን ይሄን ባላንስ አድርጎ ልማትም ሳናስቆም ስራ አጥነትንም ለመቀነስ እየሞከርን ኢንፍሌሽን መቀነስ ቀላል ጉዞ አልነበረም።
የብዙ አማካሪዎች ፣ የሞያተኞችም ምክር የነበረው ያለው መፍትሄ አንድ ብቻ ነው በፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ነው።
ይህን ለማድረግ ደግሞ ምርታማነትን ማሳደግ ነው። "

የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦ " የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል። ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው። መንግስት በህዝብ…
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ታሳሪዎች ምን አሉ ?
" 4 ኪሎ ተቀምጦ ' ጉዞ ወደ 4 ኪሎ' ከሚሉ 4 ኪሎ ተቀምጠው ጉዞ ወደ ፓርላማ እያሉ በሰላም ቢታገሉ ችግር የለብኝም " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦
" እስረኛ መፍታት ላይ እኛ እንታማለን ? ' እንዴት እስረኛ ትፈታለህ ? ' ተብለን ስንገመገም እና ስንወቀስ እንዳልነበረ።
ያልፈታነው ጉድ አለ እንዴ ? እስር ቤቱን በሩን ከፍተን ነው የለቀቅነው። በዚህ እንኳን አንታማም።
ከዚህ ፓርላማ የታሰሩት ወንድማችንን በተመለከተ (አቶ ክርስቲያንን ማለታቸው ነው) ሁሉም ተቃዋሚ የሚታሰር ከሆነ ጠያቂዬ (አቶ አበባውን ማለታቸው ነው) ለምን አልታሰሩም ?
ጠያቂዬ ተቀምጠው እየጠየቁ ነው እዚህ።
እርሶን የሚያስቀምጥ እሳቸውን የሚያሳስር ነገር ካለ ልዩነት አለ ማለት ነው። ልዩነቱን ግን እኔ ዳኛ አይደለሁም። ወንጀለኛ ናቸው ፣ ጥፋተኛ ናቸው ልል አልችልም። የፍትሕ ስርዓቱ አይቶ መርምሮ ፈትሾ ፍርድ ይስጥ።
የግል ምኞትህ ያሉኝ እንደሆነ እርሶም እርሳቸውም ከእርሶ ጎን ተቀምጠው ባያቸው ደስታውንም አልችለውም።
በሰላማዊ መንገድ 4 ኪሎ ተቀምጦ ' ጉዞ ወደ 4 ኪሎ' ከሚሉ 4 ኪሎ ተቀምጠው ጉዞ ወደ ፓርላማ እያሉ በሰላም ቢታገሉ ችግር የለብኝም።
የግል ጥላቻ የለኝም። የግል መግፋትም የለብኝም።
ህግ ከፈታቸውና ከኛ መካከል ቢሆኑ ደስታውን አልችለውም። ነገር ግን ሁላችንም ማወቅ ያለብን ፦
- የፓርላማ አባል መሆን
- ጋዜጠኛ መሆን
- ሚኒስትር መሆን
- ማዕከላዊ ኮሚቴ መሆን ከወንጀል እና ከጥፋት አይታደገንም። አለማጥፋት ነው።
የኔ ዋስትና አለማጥፋት ነው። ካጠፋው እመጣለሁ ያለመከሰስ መብቴ ይነሳል እጠየቃለሁ።
እዚህ አካባቢ ላይ መቀመጥ ለማንኛውም ጥፋት ዋስትና አድርገው ፤ ዝም ብሎ መንገደኛ ይነሳና ዩትዩብ ከፍቶ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው እንደዛ ትክክል አይደለም።
ጋዜጠኛም ህግ አለው ፣ ወታደርም ቢሆን ህግ አለው መጠየቅ አለበት ፣ ሚኒስትርም ህግ አለው።
በዚህ አግባብ ማየት ካልቻልን ስራችንን ቆርጠን ጥለነው በኋላ የማንጠግነው ነገር ይፈጠራል። "

" የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ወታደር ዜጎችን በጅምላ አይገድልም " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ሀገር መከላከያ ሰራዊት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱን በወታደራዊ ፍርድ ቤት ስርዓት እስር ቤት እንደሚገቡ ማድረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ዶ/ር ዐቢይ ፤ መከላከያ ከ ' Code of conduct ' ውጭ በማይገባ መንገድ ኦፕሬሽን ሰርታችኋል በሚል በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱን እስር ቤት እንዳስገባ አሳውቀዋል።
የጅምላ ግድያን በተመለከተ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ወታደር ዜጎችን በጅምላ አይገድልም " ሲሉ ተናግረዋል።
" በጅምላ ለማሸነፍ ይነሳና ሲሞት ነው በጅምላ ሞትኩኝ የሚለው እንጂ መንግሥት አይገድልም " ሲሉ ገልጸዋል።
" ማንኛውም ስህተት በፈተጠረበት ደግሞ ኃላፊነት ወስደን እናርማለን " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " እንዴት አድርገን ህዝባችንን እንገድላለን ? ማነው እራሱን የሚገድለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማለት ሁሉም ነው " ብለዋል።
ያም ቢሆን ግን ለተፈጠሩ ስህተቶች ፣ በየቦታው ለሚያጋጥሙ ስህተቶች ግለሰብም ቢሆን ችግር ከፈጠረ ይጠየቃል ሲሉ ተናግረዋል።
መከላከያ ሰራዊቱ ስርዓት ያለው ቢሆንም በግለሰብ ደረጃ ችግር የፈጠረ ይጠየቃታል ሲሉ አክለዋል።

" መፈንቅለ መንግስት በጭራሽ አይሳካም " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ በቅርቡ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ውይይቶች ሲደረጉ እንደነበር ተናገሩ።
ውይይት ሲያደርጉ የነበሩትም ' አባቶች ' ያሏቸውና በስም ያልጠሯቸው ግለሰቦች ናቸው።
" እኛ ወታደሮች ነን ተቋም የገነባነውም መፈንቅለ መንግስት እንዳይሳካ አድርገን ነው " ያሉት ጠ/ሚስትሩ ፤ " ኢትዮጵያ ውስጥ በጭራሽ አይሳካም በኃላ ዋጋ ትከፍሉበታላች " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምን አሉ ?
" ለአባቶቼ ፤ ለታላላቅ ወንድሞቼ ምክር ቢጤ ልለግሳቸው።
በቅርቡ አንዳንድ ቦታ ላይ ' መፈንቅለ መንግስት እናካሂዳለን ' ብለው አንዳንድ አባቶቻችን ውይይት ያደርጋሉ።
መፈንቅለ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አይሳካም። እኛ ወታደሮች ነን መፈንቅለ መንግስት እንዳይሳካ አድርገን ነው ተቋማት የሰራነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት አንዴ ተሳካ የዛሬ 50 ዓመት ከ50 ዓመት በኃላ ብዙ የሚረቡ እና የማይረቡ ሙከራዎች ነበሩ አልተሳኩም።
አሁን ጭራሽ አይሳካም። ጭራሽ።
ለወንድሞቼና ታላላቆቼ ምክር መስጠት የምፈልገው ጊዜ አታባክኑ ፣ የወዳጆቻችንን ሀገር ገንዘብም አታባክኑ፣ ገስት ሀውስም አታጣቡ አይሳካም !
በግጭት ፣ በጦርነት ፣ በሽፍታነት ፣ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ኢትዮጵያ ውስጥ መያዝ ማለት ብሎን እንደ ተበላበት ጥርስ ማለት ነው ፤ የሚሽከረከር እንጂ የማይሻገር።
በተደጋጋሚ እንዲህ አይነት ምክር ስንለግስ ቀለል አድርገው የሄዱ ሰዎች በኋላ ዋጋ ይከፍላሉ። "

#DStvEthiopia
💥 ከአስገራሚ ትንቅንቅ በኋላ የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ተፋላሚዎች ታውቀዋል!
ግማሽ ፍፃሜ የሚድርሱትን 4ቱን ሃገራት አሁኑኑ ይገምቱ!
ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የአውሮፓ ዋንጭ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎችን በጎጆ ፓኬጅ በ350ብር በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia

#Ethiopia የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት አመት 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ከጸደቀው ገንዘብ ውስጥ ፦
➡️ 451,307,221,052 ለመደበኛ ወጪዎች
➡️ 283,199,335,412 ለካፒታል ወጪዎች
➡️ 222,694,109,445 ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ
➡️ 14,000,000,000 ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የተመደበ ነው፡፡
@tikvahethiopia
ከጸደቀው ገንዘብ ውስጥ ፦
➡️ 451,307,221,052 ለመደበኛ ወጪዎች
➡️ 283,199,335,412 ለካፒታል ወጪዎች
➡️ 222,694,109,445 ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ
➡️ 14,000,000,000 ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የተመደበ ነው፡፡
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦ " የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል። ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው። መንግስት በህዝብ…
" እኛ ለንግግር ዝግጁ ነን ! " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ አቶ አበባው ደሳለው በተለይ አማራ ክልል የተለያዩ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መኖራቸውን በዝርዝር በመግለጽ ' ከምክክር እና ሽግግር ፍትሕ በፊት እምነት መገንባት ይቀድማል፤ መንግስት እምነት አልገነባም ' በማለት ላነሱት ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተውበታል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " ህዝቡን ከእናተ በላይ እኛ እናውቀዋለን። ከእናተ በላይ እኛ እንመራዋለን። ከእናተ በላይ እኛ እናወያየዋለን " ሲሉ መልሰዋል።
" እኛ እንደ ድሮ መንግስታት የተደበቅን ሳይሆን ህዝቡ ውስጥ የምንውል ነን " ብለው " ህዝቡን እናውቀዋለን " ሲሉ ተናግረዋል።
" ስለ ህዝብ ለኛ መንገር ሳይሆን ' እኛ አናምናችሁም ' ቢባል እኛ እና እናተ (አቶ አበባውን ማለታቸው ነው) እንደ ፓርቲ ለመተማመን ልንነጋገር እንችላለን " ሲሉ ገልጸዋል።
" የአማራ ህዝብ ወይም የኦሮሞ ህዝብ መንገድ የሚሰራለትን ሰው ሳያምን በመንገድ ላይ ድንጋይ እየደረደረ የሚዘጋበትን ሰው እንዴት ያምናል ? ትምህርት ቤት የሚገነባለትን ሰው ሳያምን ልጆቹ ትህርት ቤት እንዳይሄዱ የሚከለክልበትን ሰው እንዴት ያምናል ? ምን ያክል ህዝቡን ብንንቀው ነው ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
" ግብርና ይሳለጥ፣ የበጋ ስንዴ ይብዛ ልመና ይቁም ብሎ የሚተጋውን ጠርጥሮ እንዴት ማዳበሪያ እንዳይንቀሳቀስ የሚያደናቅፈውን አርሶ አደሩ ሊያምን ይችላል ? " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " እንደዚህ አንታለል። ህዝቡ ሰላም ይፈልጋል። ለውጥ ይፈልጋል። እድገት ይፈልጋል " ብለዋል።
" ነገር ግን ጫካ የገቡትም ቢሆኑ ልጆቹ ስለሆኑ እንደውጭ ወራሪ ጠላት ' በቃ ጫርሷቸው ' ብሎ አሳልፎ አይሰጥም። የልጅ ነገር ነው። ይሄን መቀበል ያስፈልጋል " ሲሉ ተናግረዋል።
" ኢትዮጵያውያን ከማንም ሀገር ጋር ብንዋጋ ፈተናው እንዳሁኑ አይደለም። እርስ በእርስ ትላንትም መከራ ነው ነገም መከራ ነው " ሲሉ አክለዋል።
" አባት ልጁን ጠላ ማለት እንዲገደል ልጁን ይሰጣል ማለት አይደለም። ህዝቡ ተነጋገሩ የሚለን ለዛ ነው። እኛም ለንግግር ዝግጁ ነን ! " ብለዋል።
" እምነትን ለመፍጠር ተገናኝቶ መነጋገር ነው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " በደብዳቤ አንተማመን ፤ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ አንተማመን ተገናኝቶ አላምንህም አምንሃለሁ እንዴት ? ዋሽተሃል ተሳስተሃል ብለን ተነጋግረን ጥፋት ካለም ደግሞ ይቅር ተባብለን ነው መተማመን የሚፈጠረው " ብለዋል።
" እንነጋገር ያለው እኮ መነጋገርን ሲለምኑ ኖረው አሁን ተነጋገሩ ስንል መነጋገር አያስፈልግም " ይላሉ ሲሉ ወቅሰዋል።
" በንግግርና ውይይት በምርጫ የተመረጠ መንግስት ብዙ የሚያገኘው ነገር የለም ፤ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠናል ሁለት ዓመት አለም ማንም አይነካብንም። ንግግርና ውይይት እድል የሚሰጠው በምርጫ ላላሸነፉና ሃሳቦች አሉን ህዝብ ሃሳባችንን ቢያደምጥ አውድ ቢፈጠር ሃሳባችን ሊገዛ ይችላል የሚሉ ሰዎች ናቸው የሚጠቀሙት እምቢ ባዮችም እነሱው ናቸው " ብለዋል።