Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦ " የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል። ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው። መንግስት በህዝብ…
" እኛ ደመወዝ የማንከፍለው ፤ ሌሎች ኃይሎች የቀጠሩት ፣ ለሌሎች ኃይሎች ሪፖርት የሚያደርግ ተቋም ከፈቀድን ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለናተው መተው ነው " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የሰብዓዊ መብት አዋጅ ፣ ተቋም፣ አሰራር ይፈተሽ " አሉ።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " ሰብዓዊ መብት ደስ የሚል ቋንቋ ነው - ለሰዎች የሚደረግ መብት ! በግርድፉ ሲታይ ደስ የሚል ቋንቋ ነው ግን ይሄ ቋንቋ ከዋናው የትርጉም ግንዱ ወጥቶ የፖለቲካ መጠቀሚያ እየሆነ ነው " ብለዋል።

ብዙ የአፍሪካ ሀገራት የሚታመሱት በዚህ (ሰብዓዊ መብት) ታርጋ ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

" የሰብዓዊ መብት ስለ ሰው ልጆች ማሰብ፣ ማክበር ፣ የተሻለ ቤት፣ ጥሩ መማሪያ እንዲኖራቸው ፣ እንዲበሉ ማድረግ ጭምር ነው እንጂ ስለ ምግባቸው እና ስለ ቤታቸው ሳይጨነቁ በሚዲያ በዩትዩብ መናገር መብት ሊሆን አይችልም " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ " የተከበረው ምክር ቤት የሰብዓዊ መብት የሚባል አዋጅ፣ ተቋም፣ አሰራር መፈተሽ ያስፈልጋል " ብለዋል።

" እኛ ደመወዝ የማንከፍለው ፤ ሌሎች ኃይሎች የቀጠሩት ፣ ለሌሎች ኃይሎች ሪፖርት የሚያደርግ ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ከፈቀድን ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለናተው መተው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኔ የሰብዓዊ መብት የሚባሉ ሃሳቦችና ተቋማት በየትም ቦታ ያሉ የማያቸው ልክ እንደመርፌ ነው ፤ መርፌ የራሱን ቀዳዳ መስፋት አይችልም። የራሳቸውን ድክመት ማየት አይችሉም። ይሄ ጥሩ አይደለም ሀገር ያፈርሳል ጥቅም የለውም፤ ተቋሞቻችንን ጸዳ ማድረግ አለብን " ብለዋል።

የሰብዓዊ መብት ተቋማት ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከሌላ ሀገራትና ፍላጎቶች ነጻ መሆን አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ያሉት ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ነጻ ቢሆኑም ከሌሎች ኃይሎች ነጻ አይደሉም ብለዋል።

ይህ ማለት ግን በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም ማለት እንዳለሆነና ስህተቶችን መገምገም ኃላፊነትም መውሰድ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በዚህ ረገድ መከላከያ እና ፌዴራል ፖሊስ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የሀገር መከላከያ በወታደራዊ ፍርድ ቤት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱን ከ code of conduct ውጭ ኦፕሬሽን ሰርተዋል በሚል ምክንያት እስር ቤት እንዳስገባ ጠቁመዋል።

የአብን አባሉ አቶ አበባው ደሳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ ባለፉት 10 ወራት በአስቸኳይ አዋጅ ሰበብ በአማራ ክልል ፦

- የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደፈጸሙ፤
- በበርካታ የአማራ ከተሞች ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች በጅምላ እንደተገደሉ (ለምሳሌ ፦ በመርዓዊ ፣ በጅጋ ፣ በደብረ ኤልያስ ፣ በፍትኖተ ሰላም፣ ደብረሲና አካባቢ ፣ ጎንደር እና ወሎ)
- የጅምላ እስር አማራን መሰረት አድርጎ እንደሚፈጸም
- የምክር ቤት አባላት ሳይቀር በፖለቲካዊ አመለካከታቸው እስር ቤት እየማቀቁ እንዳለ

... ይህንን ጉዳይም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት መዘገባቸውን አንስተው ነበር።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR " ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦ " ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ። ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና…
#Ethiopia

🟠 " የመንግስት መዋቅር በሌቦች ተጠልፏል ፤ ... ከፍተኛ የሀገር ሀብትም ከሀገር እየሸሸ ነው " - የምክር ቤት አባል

🔵 " የኢትዮጵያ መንግሥት መንግስታዊ ሌብነት አያካሂድም። ውሸት ነው ! " - ጠቅይላይ ሚኒስትሩ

ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት ከተነሳው ጉዳይ አንዱ የሙስናን የሚመለከት  ነው።

የኢዜማ አባል የሆኑ የምክር ቤት አባል አቶ አብርሃም በርታ ፦
° ዓለም አቀፍ ሪፖርት ሙስና በኢትዮጵያ ከዓመት ዓመት እየባሰበት እንደሄደ እንዲያሳይ፤
° የመንግስት መዋቅር በሌቦች መጠለፉን፣
° ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ መሆኑን
° ዜጎች የዕለት ኑሯቸውን ለመግፋት በአደባባይ ገንዘብ እየተጠየቁ መሆኑን
° ከፍተኛ የሀገር ሀብት ከሀገር ወጥቶ እየሸሸ መሆኑን አንስተዋል።

ሙስና የሰሩና የሰረቁ ባለስልጣናት ሲቀጡ ሳይሆን ቦታ ዝውውር እና ተጨማሪ ሹመት ሲሰጣቸው እንደሚታይም ገልጸዋል።

ሙስናን ለመከላከል ከቃል ባለፈ በተግባር ምን እርምጃ ለመውሰድ እንደታሰበ ጠይቀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ምላሽ ምን ነበር ?

- ሙስናን ለመታገል እየተሰራ ነው። አዲሱ የንብረት ማስመልስ አዋጅም ይህንን ሊያግዝ የሚችል ነው።

- እርምጃን በተመለከተ እናተው ያለ መከሰስ መብት አንስታችኃል፣ በሺህ የሚቆጠር ሰው ታስሯል፣ በርካታ ሃብት ተመልሷል። ግን በቂ አይደለም።

- የኢትዮጵያ መንግሥት 100 ፐርሰት ከፈለጋችሁ 1 ሚሊዮን ፐርሰት እርግጠኛ ሆኜ የማወራው መንግስታዊ ሌብነት አያካሂድም። ውሸት ነው !

- የፈለገ የዓለም ተቋም የፈለገ የዓለም ሳይንቲስት መርምሮ መንግስታዊ ሌብነት 1 ብር ሊያገኝብን አይችልም። እኛ የኢትዮጵያን ሃብት አናሸሽም። ለዚህ ነው ከተማችንን የምንሰራው።

- ያገኛትን ስሙኒ ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እያፈሰስን ነው።

- መንግስታዊ ሌብነት የለም። ይሄ ማለት ግለሰቦች፣ ስራ ላይ ያሉ ኃላፊዎች አይሰርቁም ማለት አይደለም።

- እስቲ የፓርላማ አባል የተጨበጠ ነገር ያቅርብና እርምጃ ካልወሰድን ጠይቁን፤ ጥቅል ንግግር ከሆነ መንግስት ይቸገራል።

- ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና የትም የአፍሪካ ሀገር ውስጥ ካለው ሙስና አይወዳደርም። በብዛት የአፍሪካ ሀገራት የአንድ ፓርላማ አባል የሚበላው ደመወዝ እንዚህ ካላችሁት 10 ፣20 ፣30 ሰዎች ሊበልጥ ይችላል። አንዳንድ የአፍሪካ መሪዎች የአንድ ሳምንት ደመወዛቸው የኔን የአመት ደመወዝ ሊያክል ይችላል።

- ኢትዮጵያ ውስጥ ፓርላማው፣ አፈጻሚውም ፣በየደረጃ ያለው አመራር ህይወቱን ጎድቶ፣ ተቸግሮ ነው ሀገሩን የሚያገለግለው።

- በትናንሽ ገንዘብ ህዝባችሁን እያገለገላችሁ የናተን አይነት ስራ የሚሰሩ ሰዎች በጣም የገዘፈ ነገር እየወሰዱ እኩል መንግስታዊ እንትን ከተባለ ጥሩ አይመጣም።

- ሌብነት አለ ትክክል ነው ሌብነቱን አጋኖ ማሳየት ተገቢ አይደለም።

- የኛን ኑሮ የምናውቀው እኛ ነን የትኛው ሀገር ነው የኛን ሌብነት የሚያጠናልን ? የእኛ ኑሮ እኛ እናቅዋለን የነሱን ኑሮ ያውቁታል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-04

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Reminder 🔔 የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ምዝገባ ሊጠናቀቅ 11 ቀናት ቀርቶታል። አከራይ እና ተከራዮች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም አስፈላጊ ሰነዶችን በመያዝ ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀርቧል። ከሰኔ 30 በኃላ የሚደረግ ማንኛውም ምዝገባ ቅጣት እንደሚኖረው ተገልጿል። @tikvahethiopia
#ተራዘሟል

በአዲስ አበባ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ  እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ።

ምዝገባው ሰኔ 30 ያበቃል መባሉ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል ምዝገባ ተከናውኗል።

አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ ይገኛል ብሏል።

ነገር ግን ፦
- በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ
- ቀሪ ያልተመዘገበው የተከራይ አከራይ ውል እስከ ሰኔ 30/2016 መዝግቦ ለማጠናቀቅ አዳጋች ስለሚሆን
- ቀኑ እንዲራዘምም ከህብረተሰብ በቀረበ ጥያቄ  የምዝገባ ጊዜው እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ/ም መራዘሙን ቢሮው ገልጿል።

ነዋሪዎች ጊዜው ተራዘመ ብለው ሳይዘናጉ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ፣ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ሳይጨናነቁ ምዝገባ እንዲያካሂዱ ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaHousingDevelopmentandAdministration

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎጆብሪጅ #ጤናባለሙያዎች ➡️ " ውላችን ይቋረጥ ፣ #ገንዘባችንም_ይመለስልን ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " - የቤት እጣ ቆጣቢዎች ➡️ " ከጤና ሚኒስቴር፣ ከዳሽን ባንክ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " - ጎጆ ብሪጂ ከ7 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ #የጤና_ባለሙያዎች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከዳሽን ባንክ የሦስትዮሽ ውል የፈረመው ጎጆ…
#Update

“ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት እንገደዳለን ” - የጎጆ ብሪጂ ቆጣቢዎች

“ ሶስቱም ተቋማት ቃለ ጉባኤውን አጽድቀውታል ፤ መፈራረም ነው የቀረው እንደደረሰ ይጀመራል ” - ጎጆ ብሪጂ 

የጎጆ ብሪጂ ሃውሲንግ የቤት እጣ ቆጣቢ ከ7,500 በላይ የጤና ባለሙያዎች “ ድርጅቱ ውሉ መሠረት እየሰራ ባለመሆኑ ” 4,000 የሚሆኑት ጤና ባለሙያዎች ገንዘብ እንዲመልስላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።

በወቅቱም ምላሽ የጠየቅነው ጎጆ ብሪጂ የሦስትዮሽ ውሉን ከተዋዋሉት ተቋማት ጋር ተነጋግሮ በሳምንት እንደሚመልስ ገልጾ ነበር።

አሁንስ የጤና ባለሙያዎቹ ምን አሉ?

- የመውጫ ፎርሙን ሞልተን ካስገባን በኋላ ገንዘብ መመለሱን በ1 ሳምንት ውስጥ እንደሚጨርሱልን ተነጋግረን ነበር። ነገር ግን 2 ሳምንታት አለፋቸው።

- ሂደን ' ለምንድነው የዘገየው  ? ' ብለን ስንጠይቅ የተለዬ የማይረባ አጀንዳ ዘርግተው ‘ የሦስትዮሽ ውሉን ጤና ሚኒስቴር ስላልፈረመልኝ አናስገባም ’ አሉ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አልማው።

- ጤና ሚኒስቴር ያልፈረመው ገና ከጅምሩ ስንዋዋል ለጎጆ ብሪጅ የምዝገባና የሥራ ማስኬጃ በሚል ቅድሚያ 4,000 ብር ተከፍሏቸው ስለነበር ምንም ስራ ስላልሰራ፣ ውሉንም ስላፈረሰ ከ4,000 ብሩ ላይ ተቀናንሶ ተመላሽ እንዲሆን እና ፎርሙን ጎጆ ባዘጋጀው ብቻ ላለመፈረም ስለፈለገ ነው።

የቆጠቡት ገንዘብ እንዲመለስላቸው የሚፈልጉት አባላት ብዛት ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4,000 ወደ 7,000 ከፍ ማለቱን አስረድዋል።

አሁን ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት እንደሚገደዱ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎቹን ቅሬታ ይዞ ጎጆ ብሪጂ ሃውሲንግን አነጋግሯል።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጂ የሆኑት አቶ አልማው ጋሪ ፥ “ በሦስትዮሽ ውል ነው ስራውን የጀመርነው። ‘ ገንዘባችን ይመለስልን ’ ብለው ሲጠይቁ ተነጋግረን በምን አይነት መንገድ ገንዘቡ ይመለሳል የሚለውን ተስማማን። ቃለ ጉባኤ ተዘጋጀ፣ ፈርመን ላክን ፈርመው እንዲመልሱልን ” ብለዋል።

“ በመካከል እንዳይቆም ተብሎ እንዲመለስላቸው የጠየቁትን ዝርዝር ላኩልን ከሰነዶቹ ጋር። ጉዳዩን እያጣራን ነው። ፊርማ እንደደረሰልን ግን መመለስ መጀመር እንችላለን ” ሲሉም አክለዋል።

“ ይሄ ደግሞ የሆነበት ምክንያት እጣም የደረሳቸው ሰዎች አሉ። እኛ ከፍተኛ ገንዘብ ቀብድ ብለን ሰጥተን እየተጠባበቅን ነበር። የእነርሱን የያዘ ጉዳይ ስለሆነ በመካከላችን መግባባት መኖር አለበት ” ብለዋል።

“ ጎጆ ብቻውን ምንም ማድረግ አይችልም ” ያሉት አቶ አልማው፣ የሦስትዮሽ ውሉን የተዋዋሉት ተቋማት ቃለ ጉባኤው ላይ እስከሚፈርሙ እየጠበቁ እንደሆነ፣ እንደፈረሙ መመለስ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

ውሉ በጋራ የገባችሁት እንደመሆኑ መጠን ተቋማቱ እንዲፈርሙ ጠይቃችኋቸው ነበር ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ ተነጋግረን፣ ተግባብተን ቃለ ጉባኤ ሰጥተን ነበር እሱ ነው እንዲፈረም እየጠበቅን ያለነው ” ሲሉ መልሰዋል።

ገንዘብ የመመለስ ተግባሩ በመዘግየቱ የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተም መዘግየቱን አምነው፣ “ ትንሽ ይታገሱ። የአንድ ግለሰብ ጉዳይ ስለሆነ ተግባብቶ መጨረሱ ጥሩ ነው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#አውቶሞቢሎች #ኮድ2

ስለ አዲስ አበባ ትራንስፖርት ጉዳይ ...

" 11 ሰዓት 12 ሰዓት መንገድ ላይ ወጥታችሁ ማየት ከቻላችሁ በጣም ነው የሚያሳዝነው " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ለነዳጅ በዓመት 4 ቢሊዮን ዶላር ገደማ እናወጣለን።

ሰፋ ያሉ ጥናቶች ለማድረግ ሞክረን ነበር።

ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ 1.5 ሚሊዮን ገደማ መኪናዎች አሉ። የለውጡ ጊዜ ከነበረው እጥፍ ሆኗል።

መኪና ቁጥር በእጥፍ ሲጨምር የነዳጅ ፍላጎታችንም አድጓል።

ነገር ግን አሳሳቢው ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ መኪኖች ከ355 ሺህ በላይ ኦውቶሞቢሎች ወይም ታርጋ 2 ቁጥር የግለሰብ መኪኖች ናቸው።

ለህዝብ ትራንስፖርት የሚውለው ለንግድ ስርዓት ከሚውለው ቁጥር በላይ አንደኛ ቁጥር የያዘው ኦውቶሞቢል ነው።

የኢትዮጵያ ኦውቶሞቢል ባለቤቶች በዚሁ አጋጣሚ እንዲገነዘቡ የሚያስፈልገው ከሌለን ሃብት ላይ በከፍተኛ መጨናነቅ የምናመጣው ነዳጅ መጥቶ ግለሰቦችን subsidize አድርገን ከማገልገል አልፎ ብዙሃኑን ማገልገል ወደሚችልበት ደረጃ ማድረስ አልቻልንም።

በትራንስፖርት በኩል የተቀናጀ intervention ካላደረግን በስተቀር 11 ሰዓት 12 ሰዓት መንገድ ላይ ወጥታችሁ ማየት ከቻላችሁ በጣም ነው የሚያሳዝነው (ሰራተኛው)።

ህዝቡ ስራ ውሎ በጣም ረጃጅም ሰልፎች አሉ፣ እዛው ጎን ብዙ ኦውቶሞቢሎች አንድ ሰው ሁለት ሰው ጭኖ ሲንቀሳቀሱ ሊታይ ይችላል።

እንደ ሀገር ሀብት እንዴት ነው በራይድ የጀመርነውን ስርዓት አጠናክረን በሰራተኛ መውጫ እና መግቢያ ሰዓት ሁሉም መኪኖች የመንግስትንም የግልም ህዝቡን ማገልገል የሚችሉበት መንገድ ካልተከተልን በስተቀር ነዳጁን subsidize እያደረግን ያ ገንዘብ ድሃ ጋር የማይደርስ ፣ የህዝቡን እንቅስቃሴ የማያግዝ ከሆነ እንደ ሀገር ለምናስበው እድገት ጸር ነው።

ግለሰቦች ባለመኪና መሆናቸው ጥሩ ነው። እንፈልገዋለን። ነገር ግን ግለሰቦች አንድ ሰው ሁለት ሰው በመኪና እየሄዱ ሶስት እና አራት ሰው የሚጭን ቦታ እያላቸው ሰዎች አለአግባብ ለሰዓታት የሚሰለፉ ከሆነ ያ ጉልበት ፤ ያ ጊዜ እንደ ሀገር ባከነ ማለት ነው።

ይሄን በተለየ መንገድ መፍታት የምንችልበት ስራ ካልሰራን በከተማችን የትራንስፖርት ጉዳይ ምንም እንኳን ለነዳጅ ከፍተኛ ገንዘብ ብናወጣም አሁንም መከራ ነው።

ሰዎች ይቸገራሉ።

በቅርቡ በካቢኔ ገምገመን የመንግስት መኪኖች በስራ መውጫ ሰዓት ህዝቡን እንዲያገለግሉ ተብሎ ሙከራዎች ተጀምሯል። በቂ አይደለም።

ድሃውን ለመርዳት የቀደመ ተግባር መስራት ስላለብን ይሄን ያለውን ክፍተት በመውሰድ ለመፍትሄ የምንሰራ ይሆናል። "

https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-04-2

@tikvahethiopia
#ATTENTION🚨

“ የ2 አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” - ከእገታ ያመለጠ ተማሪ

“ ‘ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም ፤ ታግተናል ’ አለችኝና ከዛ ስልኳ አይሰራም ” - የአንዷ ታጋች ተማሪ እህት

“ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው ” - የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት

ሰኞ እለት ተሳፍረው ወደ ቤተሰብ እየተጓዙ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የዓይን እማኝ፣ የታጋች ቤተሰብና ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አንድ ከእገታው አመለጥኩ ያለ ተማሪ ፥ ሶስት (3) አውቶብሶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተጓዙባቸው የነበሩ ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ ገብረ ጉራቻ የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ከ3 አውቶብሶች 2ቱን ታጣቂዎች እንዳስቆሟቸው፣ ተሳፋሪዎቹን ካስወረዷቸው በኋላ አግተው ወደ ጫካ እንዳስገቧቸው፣ እርሱ ገለባ ውስጥ ተደብቆ እንዳመለጠ ገልጾ፣ “ የሁለቱ አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” ብሏል።

ከታጋቾቹ መካከል የሚያውቃቸው የIT ፣ የአኒሚል ሳይንስ ዲፓርትመንት ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ፣ ያገቷቸው “የሸኔ ታጣቂዎች” መሆናቸውን አስረድቷል።

አንዷ የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል፣ “ ረቡዕ 3 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ደወለችልኝ (እየሮጡ ነበር፣ የተኩስ ድምጽም ነበር) ‘በቃ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም። ላታገኝኝ ትችያለሽ በታጣቂዎች ታግተናል’ አለችኝ። መለሽ ስደውል ስልኳ አይሰራም ” ብላለች።

ቤተሰቡ ሁሉ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ታጋቾቹን በህይወት እንዲያተርፏቸው ተማጽናለች።

በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፤ የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በበኩሉ፣ እገታው እውነት መሆኑን እንዳረጋገጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ኀብረቱ በሰጠው ቃል “ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው። ‘ ገንዘቡን ካላመጣችሁ እንገድላችኋለን ’ እያሏቸው ይገኛል ” ሲል የሰማውን አስረድቷል።

የሞቱ ፣ የተጎዱ ስለመኖራቸው የደረሰው መረጃ እንደሌለ የገለጸው ማህበሩ ፣ የሚመለከታቸውን  አካላት ሁሉ ለማነጋገር ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

በጉዳዩ ላይ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሰጠንን ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🚨 “ የ2 አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” - ከእገታ ያመለጠ ተማሪ “ ‘ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም ፤ ታግተናል ’ አለችኝና ከዛ ስልኳ አይሰራም ” - የአንዷ ታጋች ተማሪ እህት “ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው ” - የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ሰኞ እለት ተሳፍረው ወደ ቤተሰብ እየተጓዙ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛ እስከ…
#Update

“ ለትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ሪፓርት አድርጌአለሁ ” - ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ ገብረ ጉራቻ ላይ በታጣቂዎች የታጋቱ ተማሪዎች ቤተሰቦች በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ናቸው ፤ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ደባርቅ ዩኒቨርሲቲን ጠይቋል።

የዩቨርሲቲ ተወካይ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስማማው ዘገዬ፣ “ ጉዳዩን ሰምተናል። ከዚህ ድርጊት ያመለጡ ተማሪዎች ነግረውናኛል ” ብለዋል።

“ እንደነገሩኝ እኔ ማድረግ ያለብኝን ለሚመለከተው የፌደራል መስራያ ቤት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ሪፓርት አድርጌአለሁ ” ነው ያሉት።

“ እነርሱም ‘ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል ሪፓርት እናደርጋለን ’ ብለውኛል ” ያሉት ዶክተር አስማማው፣ “ እኔ ከእገታ ያመለጡትን ልጆች Informally communicate አድርጌአቸው ነበር ” ብለዋል።

አክለው፣ “ መከላከያ አብዛኛዎቹን ልጆች አስመልሶ መከላከያ ካምፕ ውስጥ ያደሩ ልጆች እንዳሉ ሰምቻለሁ። የተወሰኑ ደግሞ በሌላ መኪና ተሳፍረው አዲስ አበባ የገቡ እንዳሉ ሰምቻለሁ ” ነው ያሉት።

“ ግን ቀሪ ልጆች በጣም ዝናባማ ስለነበር መከላከያና ፓሊስ ሳይደርስባቸው አጋቾቹ ይዘዋቸው የሄዱ የተወሰኑ ልጆች እንዳሉ ሰምቻለሁ ” ሲሉ ተናግረዋል።

ከዩኒቨርሲቲው የወጡት ተማሪዎች ቁጥራቸው ስንት ነው ? ለሚለው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “ ቁጥራቸውን አናውቀውም የኛ ሲነር ተማሪዎች የመጨረሻ ግቢ የቆዬ 2ኛ፣ 3ኛና 4ኛ ዓመት ተማሪዎች ከደባርቅ ጎንደር ነው የተሳፈሩት በአውቶብስ ” ብለዋል።

“ ቁጥራቸውን በእርግጠኝነት አላውቀውም ” ያሉት ዶክተር አስማማው ፥ “ ግን በሶስት አውቶብስ የኛ ተማሪዎች እንደተሳፈሩ መረጃው አለኝ። ከ3ቱ ሁለቱ አውቶብሶችን ነው ያስቆሟቸው ” ነው ያሉት።

የታጋች ተማሪዎች ሁኔታ የሚመለከታቸው አካላትን በመጠየቅ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል። 

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

“ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው። ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት፤ ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው እየመጡ የሚሰሩት። ይህ ችግር ግን የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ፤ ያንን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት። ” - ዶክተር በሀሩ በዛብህ (የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር የቦርድ አባል - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

#EMA
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው ፈጣን የቪዛ ካርድ ከአቢሲንያ ባንክ !

ደንበኞች በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከል በመሄድ የቪዛ ካርድ መጠየቅና ወዲያውኑ በስማቸው የተዘጋጀውን ካርድ መረከብ ይችላሉ፡፡

ይህንን አገልግሎት በጀሞ፣ ብሄራዊ ሙዝየም፣ ጎፋ እና መሀል ሰሚት በሚገኙት የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻንን ማግኘት እንደሚችሉ እየገለጽን በቅርቡም ወደ ሌሎቹ የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች አገልግሎቱን የሚያስፋፋ ይሆናል፡፡

አጠቃቀሙን ለማየት ሊንኩን ይጫኑ: https://www.youtube.com/watch?v=-8RXiJo-bzs

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia #Abyssiniabank
የዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ጊዜ አበቃ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ጊዜ አብቅቷል።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ ዋና ኮሚሽነሩን አሰናብተዋል።

ዶክተር ዳንኤል በቀለ ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ/ም ነበር የተሾሙት።

በአምስት ዓመታት የሥራ ቆይታቸው ተቋማቸው እጅግ በርካታ የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶችን ለህዝቡ ይፋ አድርጓል።

ዛሬ የዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ዘመን ማብቃቱን በተመለከተና የዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት በኮሚሽኑ ይፋ ይደረጋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዶክተር ዳንኤል በቀለ ስንብትን እንዲሁም የዓመታዊ የሰብዓዊ መብት ሪፖርቱን ተከታትሎ ያደርሳችኋል።

Photo Credit - ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ጊዜ አበቃ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ጊዜ አብቅቷል። የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ ዋና ኮሚሽነሩን አሰናብተዋል። ዶክተር ዳንኤል በቀለ ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ/ም ነበር የተሾሙት። በአምስት ዓመታት የሥራ ቆይታቸው ተቋማቸው እጅግ በርካታ የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶችን ለህዝቡ ይፋ አድርጓል። ዛሬ…
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ዓመታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ሪፖርት ይፋ ያደርጋል።

የዛሬው ሪፖርት ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመት የሚቀርብ ነው።

ሪፖርቱ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው፡፡

ይኸው ሪፖርት በሚሸፍነው ጊዜ የነበረውን የሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠቅለል ባለ መልኩ ይቃኛል።

በትኩረት ዘርፎች (Thematic Areas) የተስተዋሉ እና የተለዩ ቁልፍ እመርታዎች፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮች፣ ተግዳሮቶች እና ምክረ ሐሳቦችን ጨምሮ ልዩ ትኩረት የሚሹ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችም ተካትተዋል።

ላለፉት ዓመታት በርካታ የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶችን ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ ሲመሩ የቆዩት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ጊዜያቸው በማብቃቱ ይሰናበታሉ።

(ዓመታዊ ሪፖርቱ እንደደረሰን እንልክላችኋለን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ዓመታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ሪፖርት ይፋ ያደርጋል። የዛሬው ሪፖርት ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመት የሚቀርብ ነው። ሪፖርቱ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው፡፡ ይኸው ሪፖርት በሚሸፍነው ጊዜ የነበረውን የሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠቅለል ባለ መልኩ ይቃኛል። በትኩረት ዘርፎች…
#Update

ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የኃላፊነት ቦታውን ይረከባሉ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ ሰጥቷል።

ላለፉት 5 አመታት ያገለገሉት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የአገልግሎት ጊዜያቸው ማብቃቱን አሳውቀዋል።

በሕ/ተ/ም/ ቤት ዋና ኮሚሽነር እስኪሰይም ድረስ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የኃላፊነቱን ቦታ እንደሚረከቡ ተገልጿል።

ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " ከዛሬ ጀምሮ ፓርላማው ስለተዘጋ በሚቀጥለው ሲከፍቱ ነው የዕጩዎች ሂደቱ የሚጀምረው እስከዛው ድረስ በአዋጁ መሰረት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ተረክቦ ይሰራል ስለሚል እኔ ነው የምሰራው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ_ዓመታዊ_የሰብአዊ_መብቶች_ሁኔታ_ሪፖርት_ከሰኔ_ወር_2015_ዓ_ም_እስከ_ሰኔ_ወር_2016_ዓ.pdf
7.8 MB
#ኢሰመኮ : የትጥቅ ግጭቶች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋነኛ ምክንያት ሆነው መቀጠላቸውን ኢሰመኮ አሳውቋል።

ይህም  " አካታችና ተዓማኒ የሆነ ሰላማዊ መፍትሔ እና የሽግግር ፍትሕ ሂደት አፋጣኝ አስፈላጊነት አመላካች ነው "
ብሏል።

ይህን ያለው ዛሬ ይፋ ባደረገው 3ተኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ ነው።

ሪፖርቱ ባለ 132 ገጽ ሲሆን ከሰኔ ወር 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ/ም ያለውን ጊዜ ይሸፍናል።

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ተጨማሪ የሥራ ዘመን መቀጠል የሚችሉበት እድል ነበር ?

" ቴክኒካሊ ይቻላል ማድረግ (በኃላፊነት ቦታው ላይ መቀጠል)  ፤ ... ሙሉ በሙሉ በፍላጎቴ ነው ላለመቀጠል የወሰንኩት " - ዶክተር ዳንኤል በቀለ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የ5 ዓመት የሥራ ዘመን አብቅቷል።

ምንም እንኳን ዶክተር ዳንኤል ለተጨማሪ የኃላፊነት ዘመን በቦታው ላይ ለመቆየት እድል ቢኖራቸውም ለ2ኛ ዙር የኃላፊነት ዘመን መቀጠል እንደማይፈልጉ ወስነዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ም/ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለን የዋና ኮሚሽነሩ ስልጣናቸው ሊራዘም ይችል ነበር ወይ ? ሲል ጠይቋል።

እሳቸውም ፦

" አንዱ የሪፎርሙ ሀሳብ የኃላፊነት ጊዜው ሲያልቅ ሊለቅ ይችላል የሚል ነው። ሌላ የሚከተለውን ሰው እንዲያመጣ።

ሁል ጊዜ ቢሆን እስከመጨረሻ ድረስ በአዋጁ ላይ የተቀመጠውን ለጥጦ መጠቀም ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ አንድ የኃላፊነት ዘመን / ዙር ጨርሶ ሌላ ሰው ይምጣ ፤ በተለይም ውስጥ ያለ ሰው መተካት ይቻላል ነው።

ዋና ኮሚሽነሩ እራሳቸው ናቸው ከዚህ በኃላ ለሁለተኛ የኃላፊነት ዘመን አልሄድም ብለው የወሰኑት " ሲሉ መልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚሁ ጉዳይ ላይ ዶክተር ዳንኤል በቀለንም አነጋግሯቸዋል።

ሁለተኛ ዙር ላለመቀጠል በራስዎት ፍላጎት ወስነው ነው ? ቢፈልጉ ሕጉ ይፈቅድሎታል ? ሲል ጠይቋል።

ዶክተር ዳንኤል ፥ " አዎን !!! በራሴ በፍላጎቴ ነው። ቴክኒካሊ ይቻላል ማድረግ (በኃላፊነት መቀጠል) ከተቋም ግንባታ አንጻር እኔ እንደዛ አልመክርም ምክንያቱም ተቋም መገንባት ማለት አንድ ሰው ዝም ብሎ መቀጠል ሳይሆን (renewal ስለሚፈቅድ) ተቋም ፈጥረህ ከዛ ማሸጋገር ይመስለኛል። ሙሉ በሙሉ በፍላጎቴ ነው ላለመቀጠል የወሰንኩት " ብለዋል።

በቀጣይ የት ሊሰሩ ይችላሉ ? የሚለውን በተመለከተ " ያህንን ለማሰብ ጊዜም አላገኘሁም። እስካሁን ምንም አላውቅም። ቀጣይ ስራዬ ምን እንደሆነ አልወሰንኩም። " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ዳታ በሽ በሽ! ... በሱፐርአፕ እስከ 80% ቅናሽ!

በአዲሱ ልዩ የሱፐርአፕ ጥቅል በአንድ ላይ ተሰናድተው በቴሌብር ሱፐርአፕ በቀረቡት የቲክቶክ፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም ጥቅሎች ዘና ፈታ እያሉ፤ ቁም ነገር ይገብዩ።

ጥቅሎቹን በዕለታዊ፣ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ አማራጮች በቴሌብር ሱፐርአፕ ብቻ http://onelink.to/fpgu4m ያገኟቸዋል!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
2024/09/29 16:27:02
Back to Top
HTML Embed Code: