TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የተማሪ ማህሌት ተኽላይ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
የማህሌት አስክሬን አጋቾች ከቀበሩበት ወጥቶ የአስከሬን ምርመራ ተጠናቅቆ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በዓድዋ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን የቀብር ስነ-ሰርዓት ተፈጽሟል።
የቀብር ስነ-ስርዓቱ የክልል ፣ የዞን እና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም በርካታ የዓድዋ ነዋሪዎች ተገኝተው ነበር።
ተማሪ ማህሌት ተኽላይ በዓድዋ ከተማ " ዓዲ ማሐለኻ " የሚባል ቦታ ታግታ ከተወሰደች በኃላ አጋቾች ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር ቤተሰቦቿን ጠይቀው ነበር።
የት እንደ ደረሰች ላለፉት 91 ቀናት ሳይታወቅ ቆይቶ ማህሌት ተገድላ ፤ ተቀብራ አስክሬኗ ዛሬ ተገኝቷል።
ከእገታው እና ግድያው ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ገድለው የቀበሩበትን ቦታ ለፖሊስ መርተው በማሳያት አስክሬኗ እንዲወጣ እና ምርመራ እንዲደረግ ተደርጓል።
የትግራይ ማዕከላይ ዞን ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ፀጋይ ኣስፍሃ ፥ አጋቾቹ የጠየቁትን ብር ቤተሰቦቿ አቅም ስለሌላቸው መክፈል ባለመቻላቸው ማህሌትን ገድለው እንደቀበሯት ገልጸዋል።
#Adwa #Tigray
@tikvahethiopia

#ኦሮሚያ #ኖኖ #ስልክአምባ በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ሰርገኞችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት እና ነዋሪዎች ገለጹ። የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ቅዳሜ ሰኔ 8 ንጋት ላይ ነው የተፈጸመው። ጥቃት አድራሾቹ " ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች ናቸው " ብለዋል። ኃላፊው…
* Update
በኦሮሚያ ክልል ፣ በኖኖ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ30 ማለፉን ፣ 12 ቁስለኞች ወሊሶ ሆስፒታል መግባታቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" ታጣቂዎቹ በሰርገኞች ቤት #ቦምብ ወረወሩባቸው። ሁሉም አልቀዋል። ትልላቅ ሰዎች ትንሽ አጥንታቸው ይታያል። ህጻናት ግን ተቃጥለው አልቀዋል " ሲሉ ነው ያስረዱት።
የሟቾች ቁጥር ከ30 በላይ እንደደረሰ፣ በተፈናጣሪው 12 ሰዎች እንደቆሰሉና ሆስፒታል እንደገቡ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ 4 ቤቶችም እንደተቃጠሉ አመልክተዋል።
ከኖኖ ወረዳ ጥቃት ማግስት በምዕራብ ደቡብ ሸዋ ዞን አማያ ወረዳ ታጣቂዎቹ ሰነዘሩት በተባለ ሌላ ጥቃት 2 ሰዎችና 15 ላሞችን እንደተገደሉ ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በወቅቱ ፤ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ፤ በኃላም መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ስፍራው እንደገባና ሁኔታውን መቆጠጠሩን ፤ ነዋሪዎች ግን ወደ አጎራባች ቦታዎች ለመፈናቁል እንደተገደዱ አስረድተዋል።
የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው " መረጃው የለኝም " ብለዋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ወርቁ ፣ የአማያ ወረዳ ባለስልጣናት ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

#Hawassa
በሀዋሳ እንደ አዲስ አበባው አይነት የመንገድ ማስፋትና የማስዋብ ስራ / የኮሪደር ልማት / መታሰቡን ተከትሎ " የሚፈርሱ ይዞታዎቻችን ግምት ባልታወቀበት እና በቂ የሆነ የዝግጅት ጊዜ ባልተሰጠበት ይዞታችሁን አፍርሱ " ተብለናል ያሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ስራው ወደተግባር ከመግባቱ በፊት ካንዴም ሁለቴ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጿል።
በቅርቡ በነበረ መድረክ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ ፤ 10 መንገዶች መለየታቸውን እና እነዚህን ውብና ዘመናዊ አድርጎ በመስራት ለትዉልድ የሚተላለፍ አሻራ የመጣል እቅድ መያዙን ገልጸው ነበር።
በመድረኩ ተገኝተው የነበሩ ነዋሪዎች ልማቱን እንደሚደግፉ የካሳ እና የዝግጅት ጊዜ ግን እንዲሰጣቸዉ ጠይቀው ነበር።
ይህን ተከትሎ የንብረት ግምትን በተመለከተ ተመጣጣኝ ካሳ እንደሚኖርና የቦታ ሽግሽጎችም እንደሚደረጉ በመግለጽ ከንቲባዉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ይሁንና የከተማ መስተዳድሩ ከመረጣቸዉ 10 ቦታዎች መካከል 3ቱን ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ማሰቡን ተከትሎ በተለይ ከስሙዳ በሳዉዝ ስታር ሆቴል ወደ ኢንዱስትሪ መንገድ የሚሄደው እና ከሻፌታ አደባባይ አስከሳዉዝ ስፕሪንግ ያለው መስመር ያሉ ነዋሪዎች ጥያቄ እንዳላቸው ገልጸዋል።
በዚህ በኩል በርካታ የመኖሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶችና ትምህርት ቤቶች የሚነኩ መሆኑን ተከትሎ ነዋሪዎች ድንጋጤ ውስጥ መግባታቸዉን ተናግረዋል።
በከተማ መስተዳድሩ በእቅድ የተያዘዉ የከተማ ልማት የምንደግፈዉ ቢሆንም የካሳና የቦታ ሽግሽግ ጉዳይ ባልተወሰነበትና ሰዉ ዝግጅት ባላጠናቀቀበት " በቅርቡ ፈረሳ ይጀምራል " መባሉ አሳስቦናል ብለዋል።
ነዋሪዎቹ በተሰጣቸው ደብዳቤ በ2 ቀን ውስጥ አፍርሰው ማስተካከያ እንዲያደርጉ መባላቸውን ጠቁመዋል።
በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የሚፈርሱ ድርጅቶች መኖሪያ ቤቶችና አጥሮች ምልክት በመደረጉና ስራውበፍጥነት ይጀመራል መባሉን ተከትሎ ፦
➡️ የካሳና የቦታ ለዉጥ ወይም ሽግሽግ ጉዳይ ምን ይመስላል ?
➡️ በትክክል ስራዉስ መች ይጀምራል ? በማለት ጥያቄ ይዘን የሚመለከተዉን አካል ለማናገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ይዞ በቅርቡ ለመምጣት ይሞክራል።
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

#ስራ #ደመወዝ ° " ያለስራና ደመወዝ በመቆየታችን ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀናል " - የመንግስት ሰራተኞች ° " ጉዳዩን እናውቀዋለን እየተወያየንበት ነው ፥ በአጭር ቀናት መፍትሄ ይሰጣቸዋል " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለስልጣን የደቡብ ክልል መበተኑን ተከትሎ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመደቡ የ " ውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን ሰራተኞች " ከስራ እና ከደመወዝ ውጭ ሆነው ወራት እንደተቆጠሩ…
#Update
የሰራተኞቹ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?
" ... እንዴት ምላሽ ተከልክሎት ለሀገር የሚጠቅም ሰራተኛ ጎዳና ሲወጣ ዝም ይባላል " - ሰራተኞች
የደቡብ ክልል መበቱኑን ተከትሎ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመደቡ የውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሰራተኞች " እስካሁን ደሞዝ ስላልተከፈለን ጎዳና ላይ ልንወጣ ነው " ማለታቸውን መረጃ ሰጥተናችሁ ነበር።
በወቅቱ ይህን ችግር አስመልክተን ጥያቄ ያነሳንላቸዉ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ አስረስ ፤ " ችግሩን እናዉቀዋለን " በማለት በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንደሚገኝና ሰራተኞችንም እንደሚያናግሩ ገልጸውልን ነበር።
ይሁንና ለወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸዉና አሁንም ከስራ ውጭ እንደሆኑ የነገሩን ሰራተኞቹ ዛሬም በባሰ ችግር ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው እስካሁን ያናገራቸው አካል እንደሌለ ነግረውናል።
ሰራተኞቹ በተደጋጋሚ ጊዜ ውሀ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮን ለማነጋገር እንደጣሩ ነገር ግን ሊያናግራቸው እንዳልፈለገ ጠቀሙዋል።
" ለምን ሊያነጋግረን እንዳልፈለገ ግልጽ አልሆነልንም ፤ እንዴት ለሀገር የሚጠቅም ሰራተኛ ጎዳና ሲወጣ ዝም ይባላል " በማለት ቅሬታቸውን በድጋሜ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ውሀ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ሻምበል አብዬ ፤ " እስካሁን ድረስ ሰራተኛዉ ስራ ያልጀመረዉ እጃችን ላይ ፕሮጀክት ስላልነበረ ነው ፤ አሁን ላይ ግን ፕሮጀክቶች እየተፈራረምን በመሆኑ በቅርቡ ወደስራ ይገባሉ " ብለዋል።
" ወደ ስራ ቦታቸዉ ሆሳዕና ከተማ ጥሪ ከተደረገላቸዉ በኋላ ' የትራንስፖርት ክፍያ አልተከፈለንም ' ለተባለዉ የኛ ድርጅት ከሲቪል ሰርቪስ የተለየ በመሆኑ ነው " ያሉት ኃላፊው " አሁን ላይ ያለው የሰራተኛዉ ችግር ይገባናል አይደለም ሰራተኞቻችን ሆነዉ ይቅርና ማንም ኢትዮጵያዊ እንዲህ አይነት ችግር ላይ ሲሆን መፍትሄ መፈለግ ይገባል " ብለዋል።
" አሁን ላይ እየሄድንበት ያለነዉ የመፍትሄ መንገድ አለ " በማለት በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ ነገር ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን እስከመጨርሻ ይከታተላል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW

#Somalia
• " የትውልድ ሀገሬ እየሄደችበት ያለው አቅጣጫ በዚህ መጠን አስግቶኝ አያውቅም "- ሙርሳል ካሊፍ
ጎረቤት ሶማሊያ በሀገሪቱ የጸጥታ ክፍተት ሊፈጠር ይችላል ስትል አስጠንቅቃ ፤ የአፍሪካ ሰላም አሰከባሪ ኃይሎች ከሶማሊያ ለቀው የሚወጡበትን ፍጥነት እንዲቀንሱ መጠየቋ ተሰምቷል።
ሮይተርስ ተመለከትኳቸው ያላቸው ሰነዶች እንደሚያሳዩት ከሶማሊያ ጋር ድንበር የሚዋሰኑ አጎራባች ሀገሮች፣ ዳግም እያንሰራራ የሚገኘው የአል-ሻባብ ቡድን ስልጣን ሊቆጣጠር ይችላል የሚል ስጋት ገብቷቸዋል።
በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ሰላም አስከባሪ ኃይል እ.አ.አ በታህሳስ መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ሶማሊያን ለቆ ለመውጣት ዝግጅቱን የጨረሰ ሲሆን በቁጥር አነስተኛ የሆነ ኃይል በቦታው እንደሚተካ ይጠበቃል።
ሆኖም የሶማሊያ መንግስት ለአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ጸጥታ ም/ቤት ጊዜያዊ ሊቀመንበር ባለፈው ወር በላከው ደብዳቤ፣ አሁን ካሉት 4 ሺህ ወታደሮች ግማሽ የሚሆኑትን እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ለማስወጣት የተያዘውን እቅድ ወደ መስከረም እንዲያሻግር ጠይቋል።
መንግስት ቀድም ሲል ለህብረቱ አስገብቶት በነበረው እና ሮይተርስ በተመልከተው ሰነድም፣ ሰላም አስከባሪው ኃይል ለቆ የሚወጣበት ጊዜ በሶማሊያ ኃይሎች " ዝግጁነት እና አቅም ላይ እንዲመሠረት " ጠይቆ ነበር።
በተመድ የፀጥታው ም/ቤት ተልዕኮ የተሰጠው ቡድን ባካሄደው የጋር ግምገማም " የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል በችኮላ መውጣታቸው የፀጥታ ክፍተት እንደሚፈጥር " አስጠንቅቋል።
የፓርላማው መከላከያ ኮሚቴ ገለልተኛ አባል የሆኑት ሙርሳል ካሊፍ ፤ " የትውልድ ሀገሬ እየሄደችበት ያለው አቅጣጫ በዚህ መጠን አስግቶኝ አያውቅም " ብለዋል።
ሶማሊያ ለሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ጸጥታ ኃይል ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ደጋፊ የሆኑት አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የሰላም አስከባሪውን ኃይል ለመቀነስ የወሰኑት ዘላቂነት ያለው የረጅም ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ የማድረጉ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ስለከተታቸው መሆኑን አራት የዲፕሎማቲክ ምንጮች እና አንድ የዩጋንዳ ከፍተኛ ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንትና የጠ/ሚ ፅ/ ቤት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም።
#ሮይተርስ #ቪኦኤ

አዲስ አበባ እና ውሃ ?
➡ " ኧረ የመፍትሄ ያለህ " - ነዋሪዎች
➡ " ችግሩ የውሃ አቅርቦት አይደለም። የኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚቋረጥ ነው " - የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን
➡ " ለ15 ቀን እና ከአንድ ወር በላይ ውሃ እንዲጠፋ የሚያደርግ የኃይል መቋረጥ ገጥሞ አያውቅም " - የኤሌክትሪክ አገልግሎት
በሀገሪቱ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ውሃ በፍረቃ ያውም በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያገኙ አመታት አልፈዋል።
በሳምንት ሁለት ቀን የማይመጣበትም አለ።
ዛሬም ድረስ በመዲናው ያለው የውሃ ችግር (በተለይም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ) ከመፈታት ይልቅ እየባሰበት ነው እየሄደ ያለው።
ውሃ በፈረቃ ቢመጣም ኃይል ስለሌለው በተለይ ፎቅ ላይ የሚኖሩ ዜጎች ውሃ አያገኙም። አንዳንድ ጊዜ በፈረቃ ጭራሽ ላይመጣም ይችላል።
ይህ የአያት 49 ቁጥር 2 አካባቢ ነዋሪዎች እያሳለፉ ስላሉት የከፋ ችግር ለኤፍቢሲ የሰጡት ቃል ነው ፦
ነዋሪ 1.
" ላለፉት 8 ዓመት እዚህ ነው ያለሁት። የመጀመሪያ ፎቅ ላይ ነው ያሉት የውሃ ችግር በጣም burning ነው። እንኳን ኮንዶሚኒየም ቀርቶ ቪላ ቤት ውስጥ ውሃ ያስፈልጋል። እሮብ እና ሀሙስ ነው ቀናችን እሮብ ሙሉ ቀን አይመጣም። ለምሳሌ ፥ ሀሙስ 8 ሰዓት መጣ 11 ሰዓት ተዘጋ፤ ኡኡ ስንል የቴክኒካል ቃላትን ይጠቀማሉ ሰዎቹ ፤ በስርጭታችን መሰረት ማግኘት እንፈልጋለን። "
ነዋሪ 2.
" እኛ 50 ብር ለውሃው እንቀዳለን። ወደላይ ማስወጫ ለአንድ ጄሪካን 20 ብር እንከፍላለን። 4ኛ ላይ ስለሆንኩኝ ወደላይ ፓወር ስለሌለው ስለማይወጣ ለአንድ ጄሪካን 70 ብር እየከፈልን ነው የምንቀዳው። "
ነዋሪ 3.
" ታች ግራውንድ አለ ፎቅ ላይ አንድም ውሃ የለም። ይኸው ወራችን ነው። "
ነዋሪ 4.
" እኛ እዚህ ሰፈር ከገባን አስር (10) ዓመታችን ነው። የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ነን። ከ10 ዓመታ ይሄ 3 ዓመት የምንገባበት ቀዳዳ አጥተናል። በአሁኑ እንኳን ውሃ ሳላገኝ 1 ወሬ ነው። 1 ወር ሙሉ ውሃ ማጣት ማለት ምን ማለት ነው ? "
ነዋሪዎች መፍትሄ ይሰጠን ይላሉ።
ውሃና ፍሳሽ ሲጠይቁ " መብራት የለም " የሚል ነው መልሱ።
የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ለኤፍቢሲ በሰጠው ቃል ፥ " ውሃ እየሰጠን እየሄደ እያለ በተደጋጋሚ መብራት ይጠፋል። ለምሳሌ 3ኛ ላይ ውሃው ደርሶ እያለ መብራት ከጠፋ ውሃው ወደኃላ ይመለሳል " ብሏል።
መስሪያ ቤቱ ፥ " የውሃ አቅርቦት ችግር የለም። ችግሩ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ነው። ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር እየሰራን ነው። እያንዳንዱ መብራት ሲጠፋ ሪፖርት የማድረግ ፣ የመናበብ ስራ አለ " ሲል ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፤ " የውሃ ስርጭት እንዲቋረጥ የሚያደርግ የከፋ የኃይል መቋረጥ ገጥሞ አያውቅም ፤ በተቋም ደረጃ ቅሬታ ቀርቦም አያቅም። 1 ወር እና 15 ቀን በላይ ውሃ ጠፍቶ ምክንያቱ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው የሚል ነገር መረጃ ጭራሽ ደርሶን አያውቅም። " ሲል መልሷል።
#AddisAbaba #Water

#አቢሲንያ_ባንክ
የጥያቄና መልስ ውድድር ቅዳሜ ሰኔ 15 ከረፋዱ 4:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አስር አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ቴሌግራም ፕሪምየምን ይሸለሙ!
የቴሌግራም ሊንክ፡ https://www.tg-me.com/BoAEth
#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

#ኢትዮጵያ
በቀጣዮቹ 10 ቀናት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከቀን ወደ ቀን በተሻለ መልኩ ይጠናከራሉ።
በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ መካከለኛው እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በቀጣይ 10 ቀናት ....
☑ አዲስ አበባ
☑ ከኦሮሚያ ክልል ፦
- ቡኖ በደሌ
- ኢሉባቦር
- ጅማ
- ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ቄለም ወለጋ
- ምዕራብ ሀረርጌ
- አርሲ እና ምዕራብ አርሲ
- ሰሜን ሸዋ (ሰላሌ)
- ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች
☑ ከአማራ ክልል ፦
- ሰሜን፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር
- ሰሜን እና ደቡብ ወሎ
- የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን
- አዊ
- ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋህግምራ
☑ ከትግራይ ክልል ፦ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፤ ምስራቅ፤ ደቡብ፤ እና ምዕራብ ዞኖች
☑ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፦ መተከል፣ ፓዌ፤ አሶሳ ፣ ካማሺ ዞኖች
☑ ከጋምቤላ ክልል ፦ ማዣንግ እና አኝዋክ ዞኖች
☑ ከሱማሌ ክልል፦ ሲቲ እና ፋፋን ዞኖች
☑ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፦ ጉራጌ፣ ሀላባ ፣ ስልጤ ፣ ጠምባሮ ፣ ሃዲያ ፣ የየም ልዩ ዞን
☑ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፦ ቤንች ሸኮ ፣ ዳውሮ ፣ ከፋ ፣ ሸካ ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች
☑ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፦ ጎፋ ፣ ጋሞ ፣ ኮንሶ ፣ ወላይታ ፣ ጌድኦ ፣ አማሮ ፣ አሪና ደራሼ ዞኖች
☑ የሲዳማ ክልል ዞኖች
☑ ሀረር እና ድሬዳዋ
... ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
ከዕለት ወደ ዕለት ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ገጽታዎች ላይ በመነሳት ፦
° ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤
° ከሱማሌ ክልል ጀራር፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ አፍዴር፣ ሊበን እና ዳዋ ዞኖች፤
° ከአፋር ክልል ቅልበቲ፣ ፈንቲ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች፤
° ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን፤
° ከጋምቤላ ክልል ንዌር እና የኢታንግ ልዩ ዞን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
#EthiopianMeteorologyInstitute

#ማስታወሻ " የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 " ምን ይዟል ? ➡ የመኖሪያ ቤት አከራዮች #በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ መጨመር #አይችሉም። ➡ አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪ አካል #በዓመት_አንድ_ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ…
የቤት ኪራይ ?
የአከራይ ተከራይ አዋጅ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የቤት ተከራዮች " ኪራይ ጨምሩ ካለዚያ ለቃችሁ ውጡ " እየተባሉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በተለይ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩና ቃላቸውን የሰጡን ተከራዮች ፥ አከራዮቻቸው በአንድ ጊዜ ከፍተኛ የኪራይ ብር እንዲጨምሩ ያን የማያደርጉ ከሆነ አስወጥተዋቸው ለሌላ ሰው እንደሚያከራዩ እንደነገሯቸው ገልጸዋል።
አንድ ተከራይ ፤ " በአንድ ጊዜ ብዙ ሺህ ብር ጨምር ተባልኩኝ ካለዚያ ቤቱን ልቀቀ ነው የሚሉት ፤ የትሄጄ እንደምኖር ግራ ነው የገባኝ " ሲል በሀዘን ስሜቱን ገልጿል።
በአነስተኛ ወርሃዊ ደመወዝ ከመሃል ከተማው እጅግ ርቆ በተከራየትበት አካባቢ ጨምር የተባለው ብር ብዙ በመሆኑ የሚገባበት እንደጠፋው አስረድቷል።
ሌላ አንዲ እናት ከባለቤቷ እና ከልጆቿ ጋር ተከራይታ እንደምትኖር ገልጻልን ፤ የአዋጁን ወደ ተግባር መግባት የሰሙት አከራዮቿ የኪራይ ብር እንድትጨምር ካልሆነ እንድትለቅ እንደነገሯት ጠቁማለች።
" ልጆቼን ይዤ የት አባቴ ልሂድ ? ጨነቀኝ " የምትለው ይህች እናት " አሁን እራሱ የምንከፍለውን ብር እንዴት ተሰቃይተን እንደምናገኘው እኛ ነን የምናውቀው ፤ አይደለም ኪራይ ተጨምሮ የአሁኑም ከብዶናል " ስትል ተናግራለች።
ቃላቸውን የሰጡን ተከራዮች ገቢያቸው ወራዊ እና ቋሚ እንደሆነ አመልክተው ሁኔታው እንዳስጨነቃቸው ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ምን ይላል ?
ቢሮው የ ' አከራይ ተከራይ አዋጅ ' ወጥቶ ተግባራዊ ከሆነበት ቀን (ከመጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም) ጀምሮ መንግስት ከሚያስቀምጠው የኪራይ ውሳኔ ውጪ በአከራዮች የሚደረግ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ውል ማቋረጥ ፈፅሞ የተከለከለ እንደሆነ አስጠንቅቋል።
የህግ ክልከላውን ተላልፎ የተገኙ የቤት አከራዮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስቧል።
የቤት ኪራይ እንዳይጨመር አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር እንደሚደረግም አመልክቷል።
#TikvahEthiopia

ኢትዮ ቴሌኮም
ልዩ የማጣሪያ ሽያጭ!
እንዳያመልጥዎ!!
እስከ 64% በሚደርስ ቅናሽ ያቀረብናቸውን የስልክ ቀፎዎች፣ ታብሌቶች እና የኢንተርኔት ሞደሞች የራስዎ ያድርጓቸው!!
ቁጥራቸው ውስን በመሆኑ አሁኑኑ ወደ አገልግሎት ማዕከሎቻችን ጎራ ይበሉ፤ የዚህ አጋጣሚ ተጠቃሚ ይሁኑ!
#Sale #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

#Hajj1445 ዘንድሮ #ምን_ያህል የእስልምና እምነት ተከታዮች #ሐጅ አደረጉ ? እንደ ሀራሜይን መረጃ ከሆነ ዘንድሮ በ1445 (AH) 1,833,164 (ከ1.8 ሚሊዮን በላይ) የእስልምና እምነት ተከታዮች ከመላው የዓለም ክፍል የሐጅ ጉዞ አድርገዋል። ከአጠቃላዩ የሐጅ መንፈሳዊ ጉዞ ተጓዦች 221,854 የእስልምና እምነት ተከታዮች ከዛው ከሳዑዲ አረቢያ ሲሆኑ 1,611,310 የሚሆኑት ዓለም አቀፍ የሐጅ…
#Hajj1445
የዘንድሮው የሐጅ ስነ ስርዓት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ዕለት ማጠቃለያውን አግኝቷል።
በሃይማኖታዊ ስርዓቱ ከመላው ዓለም ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተሳትፈዋል።
በሚያሳዝን ሁኔታ ግን በሳዑዲ አረቢያ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
የሚበዙት ከግብፅ የሄዱ ሑጃጆች ሲሆኑ የሌሎችም 9 ሀገራት ዜጎች ከሟቾቹ ውስጥ ይገኙበታል።
እስካሁን ባለው መረጃ 1,126 ሑጃጆች ህይወታቸው አልፏል።
ከኢትዮጵያ ሑጃጆች በሙቀት ህይወታቸው ያለፈ አለ ?
የፌደራል መጅሊስ በሳዑዲ በተፈጠረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በኢትዮጵያውያን ሃጃጆች ላይ ጉዳት አልደረሰም ብሏል።
ምንም እንኳን በሙቀቱ ሳቢያ ህይወቱ ያለፈ ባይኖርም በመኪና አደጋ አንድ አባት እንደሞቱ ፤ እዚሁ አዲስ አበባ ኤርፖርት አንድ ሰው እንዲሁም በሳውዲ አረቢያ 3 ኢትዮጵያውያን በህመም ህይወታቸው እንዳለፈ ገልጿል።
በዘንድሮው የሐጅ ስነስርዓት ላይ ከኢትዮጵያ 12,000 ምዕመናን የተሳተፉ ሲሆን ሑጃጆቹ የሐጅ ኢባዳቸውን አገባደው ወደሀገራቸው ለመመለስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መጅሊሱ ለ " ሀሩን ሚዲያ " በሰጠው ቃል አሳውቋል።
#Hajj1445 #SaudiArabia #Harun

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Kenya
ጎረቤት ኬንያ ታቃውሞ እየናጣት ነው።
መንግሥት በታክስ ላይ ጭማሪ ሊያደርግ ማቀዱን ተከትሎ በተለይም ወጣቱ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል።
ከወጣቶቹ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ትላንት አንድ ሰው #ተገድሏል፡፡
ግድያው የተፈጸመው በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ነው ተብሏል።
ዛሬም በናይሮቢና የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል።
ተቃዋሚዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸው ተነግሯል።
ይህ በኬንያ ወጣቶች መሪነት የተነሳው እና ባለፈው ማክሰኞ በናይሮቢ ከተማ ተጀምሮ በመላው አገሪቱ የተሰራጨው ተቃውሞ በመጭው ማክሰኞ ብሔራዊ የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል።
ተቃዋሚዎቹ ለምን አደባባይ ወጡ ?
ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደስተኛ አይደሉም።
አካሄዳቸውም ለብዙ ኬንያውያን ኑሯቸውን አስቸጋሪ ማድረጉን ይገልጻሉ።
በተለይም መንግሥት አሁን ያዘጋጀው የታክስ ጭማሪ ረቂቅ አዋጅ የህዝቡን ኑሮ የሚያመሰቃቅል እንደሆነ በመግለጽ እየተቃወሙ ነው።
የታክስ ጭማሪውን በመቃወም ለወራት በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቶ ነው ወደ ተቃውሞ ሰልፍ የተቀየረው።
የኬንያ መንግሥት ምን ይላል ?
መንግሥት የታክስ ጭማሪ ሊያደርግ ያቀደው ብድር ለመክፈል እና ለልማት ሥራዎች እንደሆነ ገልጿል።
ተቃውሞውን ተከትሎ ከረቂቅ አዋጁ ላይ የተወሰኑትን እንደሚተው ቢያስታውቅም ተቃውሞው ግን ዛሬም ቀጥሏል።
የታክስ ጭማሪው ምን ላይ ነው ?
መንግሥት በያዘው እቅድ የታክስ ጭማሪው በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የሚደረግ ነው።
በነዳጅ ላይ ሊጨመር የታሰበው 9 ሺልንግ ሲሆን ጭማሪው ለፈረሱ መንገዶች መጠገኛ እንደሚሆን የአዋጁ አርቃቂዎች አስታውቀዋል።
መንግስት በተጨማሪ አካባቢን ለመጠበቅ በሚል ታክስ ለመጣል ያቀደ ሲሆን ይህም ደግሞ የፕላስቲ ውጤቶች የሚያስከትሉትን ብከላ ለመከላከል እንደሆነ አስታውቋል።
ብሔራዊ ሸንጎው ረቂቅ አዋጁን ሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ለተቃውሞ የወጡት ኬንያውያን ግን በተቃውሟቸው እንደሚገፉበት አስታውቀዋል።
#AFP
#VOA

ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ? ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር። በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል። በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል። " በእርግጥም ፤ የBRICS…
" ፖሊሲያችንን ግልጽ አድርገናል ፤ ቡድኑን ለመቀላቀል ወስነናል " - ማሌዢያ
ማሌዢያ የ ' BRICS+ ' ን ለመቀላቀል እንደምትፈልግ አሳውቀች።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስብሰቡን ለመቀላቀል የሚፈልጉ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው።
የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ከአንድ የቻይና ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ ሀገራቸው የBRICS+ ቡድንን ለመቀላቀል እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
ስብሰቡን የመቀላቀል ሂደት በቅርቡ እንደምትጀምር አሳውቀዋል።
" ፖሊሲያችንን ግልጽ አድርገናል ፤ ውሳኔያችንንም ወስነናል። በቅርቡ መደበኛውን ሂደት እንጀምራል " ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የአሜሪካን ዶላር በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ ያለውን ከፍተኛ የበላይነት በመተቸት የሰጡትን አስተያየትም ደግፈዋል።
በባለፈው አመት ላይ ማሌዢያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንደነበራት ነገር ግን ገንዘቡ አሁንም እንደተመታ እንደሆነ አመልክተዋል።
" ለምን ? ከ2ቱ አገሮች የንግድ ሥርዓት ውጪ የሆነና በአገሪቱ ውስጥ ካለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አንፃር የማይገናኝ ምንዛሪ የበላይ ለመሆን የበቃው ለዓለም አቀፍ ምንዛሪነት ስለሚውል ብቻ ነው " ብለዋል።
በቅርብ ቻይናን ጎብኝተው የነበሩት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ሀገራቸው ቱርክ የBRICS+ ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ሲሉ መልሰው እንደነበር ይታወሳል።
BRICS+
🇧🇷 የብራዚል
🇷🇺 የሩስያ
🇮🇳 የሕንድ
🇨🇳 የቻይና
🇿🇦 የደቡብ አፍሪካ
🇪🇹 #የኢትዮጵያ
🇮🇷 የኢራን
🇪🇬 የግብፅ
🇸🇦 የሳዑዲ አረቢያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ስብሰብ ነው።

የቤት ኪራይ ? የአከራይ ተከራይ አዋጅ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የቤት ተከራዮች " ኪራይ ጨምሩ ካለዚያ ለቃችሁ ውጡ " እየተባሉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩና ቃላቸውን የሰጡን ተከራዮች ፥ አከራዮቻቸው በአንድ ጊዜ ከፍተኛ የኪራይ ብር እንዲጨምሩ ያን የማያደርጉ ከሆነ አስወጥተዋቸው ለሌላ ሰው እንደሚያከራዩ እንደነገሯቸው ገልጸዋል።…
#AddisAbaba
" ... የቤት አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ ነው " - ቤቶች ልማትና አስተዳደር
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ቢሮው ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ120 ወረዳዎች ምዝገባ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጿል።
በቀሪ የ15 ቀናት ጊዜ ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ወረዳዎች በማቅናት ምዝገባ እንዲያካሂዱ አሳስቧል።
አከራዮች የውል ስምምነቱን ሳይፈጽሙ እስከ 3 ወር ድረስ ከቆዩ የ2 ወር የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ ይደረጋል ተብሏል።
ይህንን ስራ ብቻ የሚያከናውን ቡድን መቋቋሙንም ቢሮው ገልጿል።
የውል ምዝገባው ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በምሽት ጭምር እየተሰጠ እንደሆነ ያመለከተው ቢሮው ፥ " የተሰጠው የምዝገባ ጊዜ በቂ በመሆኑ የቀን ጭማሪ ላይኖር ይችላል " ሲል አሳውቋል።
ቢሮው በመግለጫው ከመጋቢት 24 ጀምሮ የሚደረግ የቤት ኪራይ ጭማሪ እና ውል ማቋረጥ ክልክል እንደሆነ እና ተቀባይነትም እንደሌለው አመልክቷል።
መንግስት ጥናት በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ እንደሚሆን አስገንዝቧል።
#FBC
#AddisAbaba #HousingDevelopmentandAdministration