Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
የፐርፐዝ ብላክ አካውንቶች ታገዱ። የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አካውንቶች በመንግስት ታግደዋል። ድርጅቱ አካውንት ሲታገድብኝ ይህ በዓመት ለ3ኛ ጊዜ ነው ብሏል። የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጰያ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ፍስሐ እሸቱ ፥ የድርጅቱ አካውንቶች ለምን እንደታገዱ ምክንያቱን እንደማያውቁት ገልጸዋል። በአመት ውስጥ ምክንያቱ  ሳይታወቅ ለሶስት ጊዜ አካውንታቸው መታገዱን አመልክተዋል። ስለ…
#Update

" መጀመሪያ 250 ሚሊዮን ብር ከዛ 200 ሚሊዮን ብር ጉቦ ጠየቁን " - ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሀገር ጥለው አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ዛሬ አሜሪካ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል።

" ከሀገረ የወጣሁት በግፈኞች ምክንያት ተገድጄ ነው " ብለዋል።

ባልፈው የግላቸውን ጨምሮ የድርጅቱ የባንክ አካውንቶች በሙሉ በመንግስት መታገዱን መግለጻቸው ይታወሳል።

ይህን በተመለከተ በሰጡት ቃል፥ " አካውንቶቹ የታገዱት ጽንፈኛ የፋኖ ታጣቂ ኃይሎችን በመርዳት፣መሳሪያ በማዘዋወር በሙስና ወንጀል፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በሚል እና በሌሎች ነው  " ብለዋል።

" እኛ ምርመራ ይደረግ እያልን ነበር በኃላ እውነቱ ጫና የሚደረገው ብላክሜል ለማድረግ እና አስፈራርቶ የሚፈልጉትን ነገር ለመቀበል ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።

ዶ/ር ፍስሃ መጀመሪያ 250 ሚሊዮን ብር ከዛ ግን 200 ሚሊዮን ብር ጉቦ ክፈሉ እንደተባሉ ተናግረዋል።

ለዚህም " የስልክ እና ሌሎች ማስረጃዎች አሉን " ብለዋል።

" መቼ እና እንዴት ገንዘቡ እንደሚከፈል ፣ በምን ሁኔታ እንደሚከፈል ጭምር ፣ መቼ ገንዘቡ እንደሚወጣ ጭምር ነው ትዕዛዝ የተሰጠን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሰዎቹ ልክ ቼኩን እንደወሰዱ በማግስቱ ሁሉም እግድ እንደሚነሳ ቃል ገብተው ነበር " ብለዋል። 

" ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋርም እናገናኛችኋለን ስብሰባም ትቀመጣላችሁ ብለው ነበር " ሲሉ ጠቁመዋል።

የተጠየቀው ጉቦ የማይሰጥ/ የማይከፈል ከሆነ ግን ከማሰር እስከ መግደል የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ዛቻና ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረባቸው ገልጸዋል።

አጠቃላይ በጠራራ ጸሀይ እንዝረፋችሁ የሚል " የማፊያ " ስራ ነው የተሰራው ሲሉ አክለዋል።

" ሆን ተብሎ በደረሰብኝ ጫና፣ ማስፈራራትና ዛቻ እኔን አጥቅቶ ገንዘብ ለማግኘት ፣ ድርጅቱንም ለመቆጠር በሚሰራው ስራ ሀገር ለቄቄ ወጥቻለሁ " ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፤ " ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ያውቃሉ ብዬ አላስብም ፤ በእሳቸው የአመራር ዘመን እንደዚህ አይነት በአፍሪካ ሆነ በዓለም የሚዘገንን የዝርፊያና ሙስና ስራ ሲሰራ ዝም ብለው ያያሉ ብዬ አላምንም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እኛ ከቢዝነስ ውጭ ምንም የፖለቲካ ፍላጎት የለንም ፤ ' ፅንፈኞችን ይደግፋሉ ፣ መሳሪያ ያዘዋውራሉ ' የሚለው ክስ በሬ ወለደ ነው ከኛ ጋር አይገናኝም " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ያለው ችግር በሰላም ይፈታ ዘምድ መፍትሄ እንዲፈልጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

" ከአሁን በኃላ ከማንም ጋር መስራት አንፈልግም ፤ በሚኒስትር ደረጃ ያሉትን አነጋግረናል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጭ  መፍትሄ የሚሰጠን የለም " ብለዋል።

" ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለደህንነታችን ዋስትና ይስጡንና ስራችንን በሰላም እንስራ " ብለዋል።

" ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጭ ችግራችንን የሚፈታልን የለም ፤ ከሳቸው ውጭ ያየነው ነገር ቢኖር ከፍተኛ ሙስና የማፊያ ሰራ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከእሳቸው ውጭ ባሉት የበታች ሰዎች ምንም እምነት የለንም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ሽምግልና እንደሚሞከር ጠቁመው አስፈላጊ ከሆነም የአሜሪካ ኤምባሲ ጣልቃ ገብቶ እንዲያግባባ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ  " ሰዎቹ " እያሉ የጠሯቸው (200 ሚሊዮን ብር ጉቦ የጠየቋቸው) እነማን እንደሆኑ ፣ የስልጣን ደረጃቸው ፣ የተቋም ኃላፊነታቸው ምን እንደሆነ በግልጽ #ስማቸውን_ጠቅሰው አልተናግሩም።

" በደረሰብኝ የእስርና ግድያ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሀገር ለቅቄ ወጥቻለሁ " ያሉት የኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ  ከሀገር ሲወጡ የገጠማቸው ነገር ስለመኖሩ የሰጡት ቃል የለም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ethiotelecom #Oromia

በኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ ሪጅን በጸጥታ ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁመው የነበሩ 87 የሞባይል ጣቢያዎች ተጠግነው በ42 ወረዳዎች የሚገኙ 83 ቀበሌዎችና ከተሞች ዳግም የቴሌኮም አገልግሎት እንዳገኙ ዛሬ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

ተቋሙ ፤ በጸጥታ ችግር ምክንያት በምዕራብ እና በምስራቅ ወለጋ፣ ሆሩ ጉዱሩ እንዲሁም ቄለም ወለጋ ዞኖች የሚገኙ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን የመጠገን ስራ ሲሰራ እንደነበር ገልጿል።

የኃይል አቅርቦትን ባላገኙ አካባቢዎች ላይ ጀነሬተር ፣ ነዳጅና አስፈላጊ ግብዓት በማሟላት የጥገና እና የማሻሻያ ስራዎች በማጠናቀቅ 87 የሞባይል ጣቢያዎችን አገልግሎት ዳግም በማስጀመር በ42 ወረዳዎች የሚገኙ 83 ቀበሌዎች እና ከተሞች አገልግሎት እንዳገኙ አሳውቋል።

እስካሁን በተከናወኑ ስራዎች ፦
- በሆሩጉዱሩ 18 የሞባይል ጣቢያዎች፣
- በምዕራብ ወለጋ 19 ጣቢያዎች፣
- በቄለም ወለጋ 17 ጣቢያዎች፣
- በምስራቅ ወለጋ 12 ጣቢያዎች
- በምዕራብ ሸዋ 1 ጣቢያ ጥገና ተደርጎ አገልግሎት ማስጀመር እንደተቻለ አመልክቷል።

በተጨማሪ ከዚህ በፊት በተሟላ መልኩ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ አጠቃላይ 20 የሞባይል ጣቢያዎች አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን በተቀሩት አካባቢዎችም ላይ ጥገናው እንደሚቀጥል አሳውቋል።

@tikvahethiopia @ethio_telecom
#Tecno #Camon30pro

ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ በሞርኒግ ስታር ሞል በተለያዩ የስራ ዘርፍ በተለይም ደግሞ በፍሽን እና ሜክ አፕ  ስራዎችን ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ እና ስኬታማ እየሆኑ ያሉ የሀገራችን ሴቶችን ለማበረታታት እና አዲሱን የቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ 5G ልዩ ስልክ ማስተዋወቅን አላማው ያደረገ በአይነቱ ለየት ያለ የማስተዋወቂያ ዝግጅት ተካሂዷል፡፡

በዝግጅቱ የተለያዩ ፋሽን ሾዎች በታዋቂ ዲዛይነሮች የቀረቡ ሲሆን በሀገራችን በአይነቱ አዲስ በሆነ መልኩ የመክፈቻ የዳንስ ትርዒት/Flash Mob/ እንዲሁም ለተሳታፊዎች ሜክ አፕ ጨምሮ የተለያዩ የመዝናኛ እና የፋሽን ትዕይንትን በማዘጋጀት ታዳሚው እንዲዝናና እና ከስልኩ ጋር እንዲተዋወቅ ተደርጓል፡፡

የቴክኖ የብራንድ አምባሳደር የሆነችው ዳናይት መክብብን ጨምሮ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ቲክቶከሮች በሁነቱ የተገኙ ሲሆን የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞችን በታዋቂ ዲጄዎች ታጅበው ለታዳሚው ቀርበዋል፡፡

ቴክኖ ካሞን 30 5G በቅርቡ በደማቅ ስነ ስርአት በሸራተን አዲስ ሆቴል ለሀገራችን ተጠቃሚዎች መተዋወቁ ይታወሳል፡፡

#Tecno #Camon30 #TecnoEt
#Amahra

" ከ4 በላይ ወረርሽኞች ተከስተዋል። ከ2,400 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል። ከፍተኛ ሞት አለ " - የዋግኸምራ ብሔረሰብ ጤና መምሪያ

በአማራ ክልል ፤ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከተከሰተ በሰነበተው ድርቅ ሳቢያ ከአራት በላይ ወረርሽኞች መከሰታቸውን ተከትሎ ሰዎችና እንስሳት እየሞቱ መሆኑን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊው አቶ አሰፋ ነጋሽ በሰጡት ቃል፣ " ከ4 በላይ ወረርሽኞች ተከስተዋል። ከ2,400 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ተጠቅተዋል። ከፍተኛ ሞት አለ " ብለዋል።

በወረርሽኙ ምን ያህል ሰዎች ሞተዋል ? ለሚለው ጥያቄ፣ " ሞቱ ከፍተኛ ነው። ቁጥሩን Specifically ለመናገር እርግጠኛ አይደለሁም " ነው ያሉት።

ቢያንስ ከ5,000 በላይ እንስሳት እንደሞቱ፣ ለመከተብ አቅም እንዳልተገኘ፣ በሽታው (አባሰንጋ) ከእንስሳት ወደ ሰው እየተላለፈ መሆኑን ገልጸው፣ ከአንድ ወረዳ ብቻም ወደ  140 ሰዎች አባሰንጋ እንደተላለፈባቸው አስረድተዋል።

- ኮሌራ
- ኩፍኝ
- እከክና
- አባሰንጋ (የከብት በሽታ) እና ሌሎች ወረርሽኞች በሁሉም በሚባል ደረጃ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ላይ ተከስተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

" ኩፍኝ በሁሉም ወረዳዎች ተከስቷል። በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ህፃናት ታመውብናል " ያሉት አቶ አሰፋ፣ " ለወረርሽኙ ምላሽ ክትባት እየሰራን ነው " ብለዋል።

" እከክ በተለይ ድርቁ በስፋት ባጠቃቸው ወረዳዎች ተከስቶ ነበር ለመቆጣጠር እየተሞከረ ነው። የውሃ አቅርቦት፣ የንጽህ እና መጠበቂያ ግብዓት ካልቀረበ እሱንም መቅጣጠር እጅግ አስቸጋሪ ነው " ነው ያሉት።

ድርቅ ከመከሰቱ በፊትም አካባቢው ትርፍ አምራች ስላልነበር የምግብ እጥረት እንደነበር አሁን የድርቁ መከሰት የምግብ እጥረቱን እጅጉን እንዳባባሰው ፤ የሥርዓተ ምግቡን ችግርም መቀልበስ እንዳልተቻለ አስረድተዋል።

ሞቱን ለመከላከል የሚሰጠውን ህክምና አጠናክረው እንደቀጠሉ የገለጹት ኃላፊው፣ " በተለይ መካከለኛ የምግብ እጥረት ያለባቸውን ህጻናትና እናቶች ተደራሽ ለማድረግ የጸጥታ ችግሩ በጣም አስተቸጋሪ ሆኗል " ብለዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታዎች እንደተቀዛቀዙ አስረድተው፣ " በጸጥታ ምክንያት ተደራሽ ያልሆኑ እናቶችና ህጻናት ምንም እየተደረገላቸው አይደለም " ብለዋል።

ያለው የምግብ እጥረት በቋሚነት ካልተቀረፈ ችግሩን መቀልበስ ፈተና ስለሆነ አጋር ድርጅቶች ርብርብ ኦንዲያደርጉ ዞኑ ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Tigray

" ከዚህ (ከሰላማዊ) ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

36ኛው ዓመት " የትግራይ የሰማእታት ቀን " ዛሬ ሰነ 15 ቀን 2016 ዓ/ም በመቐለ የሰማእታት ሀውልት ተከብሯል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " ልጆቻችን በአጋቾች ለሞት እየተጋለጡ ፣ ተፈናቃዮች በመቆያ መጠለያዎች በፀሀይና በብርድ እየተሰቃዩ ባሉበት ወቅት የሰማእታት ቃልና አደራ በተሟላ መልኩ እያከበርን ነው በማለት ማምለጥ አይቻለንም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የሰማእታት ቃል አክበረናል የምንለው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆን ይገባዋል " ብለዋል።

" የሰማእታት ቃል ማክበር ማለት በትግራይ የሃሳብ ብዙህነት እንዲከበር መስራት ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ጥቅም መዋደቅ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " አንዳንዶቻችን ይህንን በመዘንጋት ለስልጣንና ለሃብት ስንባላ መታየት አሳፋሪ ነውና ከዚሁ መውጣት ይህንን መቀየር አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው " ተፈናቃዮችን በጀመርነው ሰላማዊ መንገድ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በአንድነት መንፈስ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን መስራት አለብን " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ... የቤት አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ ነው " - ቤቶች ልማትና አስተዳደር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። ቢሮው ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ120 ወረዳዎች ምዝገባ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጿል። በቀሪ የ15 ቀናት ጊዜ ዜጎች…
" ' የቤት ኪራይ ጨምሩ ' ወይም ' ቤቱን ልቀቁ ' የሚል ግፊት ከደረሰባችሁ ደውላችሁ ጠቁሙኝ " - የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

በአዲስ አበባ ፤  ' ከአከራይ ተከራይ  የውል ስምምነት ' ጋር በተያያዘ ተከራዮች የሚገጥማቸውን ማንኛውም ችግር ጥቆማ ሊሰጡ እንደሚችሉ የከተማው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው ማንኛውም አከራይ ከመጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን አስገንዝቧል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ ተከራዮች የቤት ኪራይ ጭማሪ አልያም ' ቤቱን ይልቀቁልኝ ' የሚል ግፊት ከአከራዮች ከደረሰባቸው በስልክ ቁጥር +251118722917 / +251118553820 ላይ በመደወልና ጥቆማቸውን በመስጠት መብታቸውን ማስከበር እንደሚችሉ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ሰኔ 1 ላይ የጀመረው የአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ሊጠናቀቅ  14 ቀናት የቀሩት ሲሆን ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙት ወረዳዎች በማቅናት ምዝገባ እንዲያካሂዱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

አከራዮች የውል ስምምነቱን ሳይፈጽሙ እስከ ሶስት ወር ድረስ ከቆዩ የሁለት ወር የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ ተገልጿል።

መንግስት ጥናት በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ እንደሚሆን ተነግሯል።

#TikvahEthiopia
#HousingDevelopmentandAdministration

@tikvahethiopia
#አፖሎ_ሆስፒታል #ላንድማርክ_አጠቃላይ_ሆስፒታል

አፖሎ ሆስፒታል ከላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ልዩ የህክምና አገልግሎት ይዞላችሁ መጥቷል ።

የጉበት የጣፊያ ከአልኮል መጠጦች ጋር ተያይዞ የጉበት ህመሞች ፣ የጭንቅላት እጢ የነርቭ ችግር የአንገት የጀርባ አጥንት ህመም እና ሌሎች ተያያዥ ህክምናዎች ይሰጣል ።

ህክምናው የሚሰጠው ሰኞ እና ማክሰኞ ሰኔ 17 እና 18 2016 አስቀድሞ ቀጠሮ ለማስያዝ 0944038928 & 0947327953 ይደውሉ ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።

ቦርዱ ከዚህ ቀደም ምርጫ ባልተደረገባቸው ፦
- በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣
- በአፋር፣
- በሶማሌ
- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ነው ምርጫ እየተደረገ እንደሚገኝ ያመለከተው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

 በየዓመቱ ከ8 ቢሊዮን እስከ 5.6 ቢሊዮን ብር በጀት ሊመደብለት ይችላል።

የፌዴራል መንግሥት ፤ በየዓመቱ ከአገር ውስጥ ገቢ ምንጭ ከሚመድበው ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከ0.5 በመቶ እስከ አንድ በመቶ ያህል ለአረንጓዴ አሻራ እና ለተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ እንዲሰጥ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ረቂቅ አዋጁ ፤ " የአረንጓዴ አሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ለማቋቋም እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ " የሚል ስያሜ አለው።

ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ?

ለም/ ቤቱ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ባለበት ሁኔታ ከፀደቀ በልዩ ፈንድ ከ2.8 ቢሊዮን ብር እስከ 5.6 ቢሊዮን ብር የሚደርስ በጀት ከመንግሥት ብቻ ሊቀርብለት ይችላል።

ልዩ ፈንዱ ዘጠኝ ዓላማዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል ፦
- የተጎሳቆለ መሬት በተፈጥሮና በመልሶ ማልማት መርህ በመታገዝ እንዲያገግም ማድረግ፣
- የደን ልማትና የደን መልሶ ማልማትን መደገፍ፣
- የአገሪቱን የካርቦን ልቀት ቅነሳ ግብ እንዲሳካ አስተዋጽኦ ማድረግ፣
- የከተማ ማስዋብ እና አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን መደገፍ የሚሉ ይገኙበታል።

የልዩ ፈንዱ የፋይናንስ ምንጮች ፦
1ኛ. የፌዴራል መንግሥት የሚመድበው በጀት፣
2ኛ. የልማት አጋሮች፣
3ኛ. የሲቪክ ማኅበረሰቦች፣
4ኛ. የግል ዘርፍ የሚሰጡት ድጋፍ ነው።

የፌዴራል መንግሥት ለፈንዱ ከሚመድበው በጀት የሚሰበሰበው ገንዘብ ለልዩ ፈንዱ በተከፈተው የባንክ ሒሳብ በየ3 ወራቱ በገንዘብ ሚኒስቴር ተቀማጭ ይሆናል። የሌሎች ምንጮች ድጋፍ የሚተዳደርበት አኳኋን የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመርያና የአሠራር ሥርዓት ይወሰናል።

መንግሥት የሚመድበው ዓመታዊ በጀት የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መሥፈርት መሠረት ለፌዴራል መንግሥትና ለክልሎች ይደለደላል።

ለክልሎች ከሚደለደለው በጀት ላይ የእያንዳንዱን ክልል ድርሻ ለመወሰን የሚያገለግለውን የገንዘብ ሚኒስቴር አዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይቀርባል። ሆኖም ለመሸጋገሪያነት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያፀደቀው ጠቅላላ የበጀት ድጋፍ ቀመር በጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

ከተደለደለው ዓመታዊ የሀብት ድርሻ ላይ በየ3 ወሩ ወደ ተጠቃሚ አካላት ገንዘብ ሊተላለፍ የሚችለው የሥራ አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ፣ ክልሎች ተጓዳኝ በጀት ሲመድቡና በክልሉ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ፈሰስ ሲያደርጉ ይሆናል።

ክልሎች የሚመድቡት ዝቅተኛ ተጓዳኝ በጀት ተፈጻሚ የሚሆነው በተጓዳኝ በጀቱ መጠን ላይ በረቂቅ አዋጁ የልዩ ፈንዱ አስፈጻሚ አካላት በሚል የተዘረዘሩት ፦
° የገንዘብ ሚኒስቴር፣
° የግብርና ሚኒስቴር፣
° የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣
° የኢትዮጵያ ደን ልማት በክልሎች የገንዘብ ቢሮዎች መካከል በሚደረግ ምክክር የጋራ ስምምነት ላይ ሲደረስና በየክልሉና በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤቶች ሲፀድቅ ነው።

እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ሳይተላለፍ የቀረ ገንዘብ በቀጣዩ ዓመት ለልዩ ፈንዱ ከሚመደበው በጀት ጋር ተደምሮ ይደለደላል።

የልዩ ፈንዱ ዓብይ ኮሚቴ አስፈጻሚ አካላት፦
° ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣
° ከኢትዮጵያ ደን ልማት
° ከክልሎች የገንዘብ ቢሮዎች የበላይ ኃላፊዎች ይዋቀራል። የገንዘብ ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ይሆናሉ።

ገንዘብ ሚኒስቴር ከተጠቃሚ አካላት ሚቀበለውን የሒሳብ ሪፖርት በማጠቃለል የልዩ ፈንዱን ሒሳብ ዘግቶ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ3 ወራት ውስጥ በፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይም የፌዴራል ዋና ኦዲተር በሚወክለው ኦዲተር እንዲመረመር የማድረግ ኃላፊነት አለበት።

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በዚህም በ2017 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1332 የማስተማር ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል። 43 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው መሰረዙን አመልክቷል። 150 ትምህርት ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ወደፊት…
#AddisAbaba

" በ2017 ዓ/ም መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን መቀጠል ይችላል " - ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ

ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን  በ2017  የትምህርት ዘመን 41 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና ስታንዳርዱን ባለማሟላታቸው ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

ከነዚህ ትምህርት ቤቶች አንዱ ፍኖተ ሎዛ ቅድመ አንደኛ፤ የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ነው።

ይህ ትምህርት ቤትን በተመለከተ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባስስልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አንድ ደብዳቤ ጽፏል።

ጽ/ቤቱ በዚህ ደብዳቤው ት/ቤቱ ፦

" በማዕከል ደረጃ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ቅርንጫፍ እና እርክን ሳይጠቀስ በጅምላ የት/ቤቱ ስም ተጠቅሶ ' ከስታንዳርድ በታች በመሆኑ የተዘጋ ' በሚል የተቋሙን ስምና ዝና በማይመጥን መልኩ ተዘግቧል።

በዚህ ደረጃ የተዘጋ ተቋም ሳይኖር በትምህርት ቤቱ ባለቤቶች እና ማሕበረሰቡ ላይ ውዥንብር ተፈጥሮብኛል " በሚል እንዳመለከተ ገልጿል።

በዚህም ፍኖተ ሎዛ ሃና ማርያም ቅርንጫፍ ከቅደመ ስንደኛ እስከ ሁስተኛ ደረጃ ያለው ምንም ዓይነት የስታንዳርድ ችግርም ሆነ የስርዓተ ትምህርት ጥሰት የሌለበት መሆኑን አመልክቷል።

ፍኖተ ሎዛ ተብሎ የተጠቀሰው ትምህርት ቤት በቅርንጫፉ ወረዳ 15 የሚገኝ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤትም ውል ባለማቅረቡ ምክንያት ስሳልተገመገመ ስታንዳርድ ማሟላት አለሟሟላቱ አሁን መግለጽ እንደማይቻል አስረድቷል።

በሀና ማርያም የሚገኘው ተቋም ግን በ2017 ዓ/ም መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን መቀጠል እንደሚችል የን/ስ/ላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
በስርአተ_ትምህርት_ጥሰትና_ስታንዳርድ_ባለማሟላት_የተዘጉ_ተቋማት_ዝርዝር.pdf
901.1 KB
#AddisAbaba : በስርዓተ ትምህርት ጥሰት እና ስታንዳርድ ባለለመሟላት የተዘጉ ትምህርት ቤቶች ዝርዝር።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን አይቀጥሉም የተባሉ ናቸው።

ፍኖተ ሎዛን በተመለከተ ግን ይህን ያንብቡ፦ https://www.tg-me.com/tikvahethiopia/88408

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
በራሳቸው የዘጉ ተቋማት ዝርዝር.pdf
1015.4 KB
#AddisAbaba

በራሳቸው የዘጉ ትምህርት ቤቶች ዝርዝርን ይመለከቱ።

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
ለ2017_የትምህርት_ዘመን_መስፈርቱን_አሟልተው_ምዝገባ_ማከናወን_የተፈቀደላቸው_የቅድመ_አንደኛ_ተቋማት.pdf
10.8 MB
#AddisAbaba : ለ2017 የትምህርት ዘመን መስፈርቱን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይመልከቱ።

#ETQRA
#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
2024/09/27 09:34:52
Back to Top
HTML Embed Code: