Telegram Web Link
የፐርፐዝ ብላክ አካውንቶች ታገዱ።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አካውንቶች በመንግስት ታግደዋል።

ድርጅቱ አካውንት ሲታገድብኝ ይህ በዓመት ለ3ኛ ጊዜ ነው ብሏል።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጰያ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ፍስሐ እሸቱ ፥ የድርጅቱ አካውንቶች ለምን እንደታገዱ ምክንያቱን እንደማያውቁት ገልጸዋል።

በአመት ውስጥ ምክንያቱ  ሳይታወቅ ለሶስት ጊዜ አካውንታቸው መታገዱን አመልክተዋል።

ስለ ጉዳዩ " ደብዳቤ እንኳን አልደረሰንም " ብለዋል።

መታደጉን የሰሙትም ከባንኮች እንደሆነ ከነሱ አገኘን ባሉት ደብደቤ ከ ' ፍትህ ሚኒስቴር ' በተጻፈ ደብዳቤ መታገዱን እንደሚልጽ አስረድተዋል።

ከድርጅቱ አካውንቶች በተጨማሪም #የራሳቸው የስራ አስፈጻሚው ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ የባንክ አካውንትም ታግዷል።

ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ ፥ " አሁን ላይ ለሰራቸኞቻችን ደሞዝ መክፈል ፤ አስፈላጊ ወጪ መሸፈን የማንችልበት ሁኔታ ላይ ነን " ብለዋል።

በአካውንቶች መታገድ ምክንያት የቤት ኪራይ ክፍያ እና የፕሮጀክት ስራዎች መቆማቸውንም አሳውቀዋል።

አሁን በተፈጠረው ችግር የድርጅቱ የቀጣይነት አደጋ ከተጋረጠ ፐርፐዝ ብላክ ተጠያቂ እንደማይሆን " ለባለአክሲዮኖቹ መግለጽ እንፈልጋለን " ብለዋል።

እግዱ ህጋዊ መንገድ ያልተከተለ በመሆኑ መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

የ1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ ይከበራል።

የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የሶላት ስነስርዓቱ የሚካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በዙሪያው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ነው።

ይህ ተከትሎ ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የሶላት ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዚህም መሰረት ፦

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ

- ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

- ከብሔራዊ ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

- ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ

- ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን መገንጠያ ላይ

- ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

- ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#አረፋ

መልካም በዓል !

" ይህን የተባረከ #የአረፋ_ቀን እምነታችንን በልባችንና በተግባራችን የምናድስበት ፤ ስላጠፋነው ጥፋት / ስህተት ከልብ አዝነን ዳግመኛ ወደዛ ላለመመለስ ቃል የምንገባበት እና ወደ ሁሉን ቻይ አምላካችን #አሏህ 🤲 የምንቀርብበት ቀን ነው። " - ሙፍቲ ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር)

#መልካም_በዓል !!
#TikvahFamily ❤️

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ

የ2016 የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

ጥዋት የኢድ ሶላት ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች ተከናውኗል።

ከኢድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን በዓሉን እያከበረ ነው።

#ኢድአልአድሃ #አረፋ

መልካም በዓል

ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
2024/09/28 21:27:00
Back to Top
HTML Embed Code: