Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
ምስጋና እና ዘርፈ ብዙ ጥቀሞቹ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet

በርካታ ጥናቶችም የምስጋና ባህል በተቻለ መጠን መዳበር እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ ጥናቶች መካከል የ “Positive Psychology” መስራች ሴሊግማን 411 ሰዎች ላይ ያካሄደው ጥናት ቀዳሚ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው የተለያዩ አዎንታዊ ሀሳቦች እና ድርጊቶች ያላቸውን ውጤት በመለካት (Testing) ሲሆን ምስጋና ከሁሉም የላቀ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ታውቋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሕይወታችን ትልቅ ቦታ አለው የሚሉትን እና በሚገባ አመስግነው ለማያውቁት ሰው የምስጋና ደብዳቤ ፅፈው በራሳቸው እጅ እንዲያደርሱ ከተደረገ በኋላ ውጤቱን ተጠንቶ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ተሳታፊዎቹ ላይ ታይቷል፡፡ ለውጡ ይበልጥ አስደናቂ ሊሆን የቻለው የተፈጠረው የደስታ ስሜት ለብዙ ወራት መቆየት በመቻሉ ጭምርም ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከየትኛውም ድርጊት በበለጠ መልኩ ምስጋና አመስጋኙን ደስተኛ የማድረግ ኃይል እንዳለው ታውቋል፡፡

የምስጋና ጥቅሞች

#ደስተኛ_ያደርገናል
በቀን ለአምስት ደቂቃ ያህል ማመስገን ከአማካይ ጤንነት በላይ 10% ሁለንተናዊ ጤንነትን ያሻሽላል፡፡

#ሰዎች_እንዲወዱን_ያደርጋል
በሁለት የተለያዩ ጥናቶች ከአብዛኘው ሰው 10 % በላይ የሚያመሰግኑ ሰዎች 17.5 % ከሌሎች የበለጠ የሰው መውደድ እንዳላቸው ታውቋል፡፡ ምስጋና ሰዎች እምነት እንዲጥሉብን፣ እንዲቀርቡን እና እንዲወዱን ያደርጋል፡፡

#በሥራ_ቦታ_ስኬታችንን_ይጨምራል
ምስጋና የተሻለ መሪ፣ ተግባቢ፣ የውሳኔ ሰው እና ስኬታማ እንድትሆኑ ያግዛል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ምስጋና ጤናማ ስሜት እንዲኖረን፣ ቁሳዊ አመለካከታችን (Materialism) እንዲቀንስ፣ ራስ ወዳድነት እንዲቀንስ፣ ለራሳችን ያለን አመለካከት እንዲሻሻል፣ ጥሩ እንቅልፍ እንድንተኛ፣ ረጅም እድሜ እንድንኖር ወዘተ ያደርጋል፡፡

ምስጋና ባህል እንደመሆኑ መጠን ደግመን ደጋግመን እስከተለማመድነው ድረስ ይሻሻላልም፡፡ ይህንን ለማድረግ የምስጋና ደብዳቤ መጻፍ፣ ጊዜ ቢታጣ እንኳ በልቦናችን ማመስገን፣ የምስጋና የግል ማስታወሻ መፃፍ፣ በረከቶቻችንን መቁጠር፣ ፀሎት የመሳሰሉት የምስጋና ባህላችንን ለማሻሻል የሚረዱ ልምምዶች ናቸው፡፡

___________________
ይህን ካነበባችሁ አይቀር የማመስገን ባሕልን ዛሬውኑ መለማመድ ጀምሩ ፡፡ ሕይወታችሁ ሲለወጥ ታዩታላችሁ ፡፡

አንድ ምሳሌ ልጨምርላችሁ ፦ አንድ ዳቦ ይዛችሁ ሶስት የተቸገሩ ሰዎችን ተመለከታችሁ ፡፡ ከዛ ዳቦውን እኩል ቦታ ቆርሳችሁ አካፈላችኀቸው፤ ሰዎቹም ሲበሉም ቆይተው ሲጨርሱ
#አንዱ ይሄ ምን ያጠግባል ፣ ደግሞ የማይጣፍጥ ዳቦ ነው ብሎ ተነስቶ ሄደ
#ሌላው ደግሞ ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ሄደ
#የቀሪው ግን እጅግ አመስግኖ እያለቀሰ ምግብ ከበላሁ 1 ቀኔ ነበር በማለት ሰጪውን ደጋግሞ አመሰገነ

እናም በዚህ ሁኔታ ሰጪው ላይ ምን አይነት አስተሳሰብ የሚጎለብት ይመስላችኀል? ተቀባዮቹስ ላይ?

ሰጪው በጣም የሚያስደስተው የሰጠው ጥቂት ዳቦ ሳይሆን ያመሰገነንውና እሱ በሰጠው ጥቂት ዳቦ ከርሀብ የወጣው ሰው ታሪክ ነው ፡፡ አማሮ ለሄደው ሰው ግን ለወደፊቱ ሞልቶ ቢተርፈውም ላይሰጠው ያስባል ስለ ሶስተኛው ሰው ግን እንዴት ምንም ሳይል ይሄዳል በሚል ብዙ ጥያቄዎችን ያወጣል ያወርዳል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ስንባል ምንም ነገር ስናደርግ ምላሽ እንጠብቃለን ፡፡

ስለዚህ ለመልካም ግንኙነት ስንል መልካም ነገር መናገር አማራጭ የሌለው ነገር ነው ፡፡ ካልተቻለ ግን መጥፎ ነገር ከመናገር ዝም እንበል ፡፡ መልካም ነገር የሚጀምረው ደግሞ ከቀላል ምስጋና ነው፡፡

Like & Share
fb.me/psychologyet
የአሸናፊነት_ሕይወት_በናሁሰናይ_ፀዳሉ.PDF
223.6 KB
በአምስት ክፍል ሲቀርብ የነበረው የአሸናፊነት ሕይወት ትምህርት በአንድ ላይ ተቀናጅቶ በPDF ተዘጋጅቶአል ፡፡
ለሌሎችም #Share በማረግ የአሸናፊነት ሕይወት እንኑር
@psychoet @psychoet
የሰዉ ልጅ ትልቁ ጠላትም ሆነ ትልቁ ወዳጅ ሰው ራሱ ነው ፡፡
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
ወላጆች በልጆቻቸው ፊት መጠቀም የማይገባቸው ቃላት
#Share

ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደ መሆናቸው መጠን የዕለት ተዕለት ዕድገታቸውን የሚያቀላጥፍ ማንኛውም ነገር ችላ ሊባል አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ወላጆች በልጆቻቸው ፊት አስተውለው ፤ መርጠውና ተጠንቅቀው የማይጠቀሟቸው ጸያፍና ባዕድ ቃላት በሂደት የልጆቻቸው በራስ መተማመን እንዲያሽቆለቁልና ስለዓለም የሚኖራቸው እይታ እንዲንሸዋረር ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ከዚህ በታች ወላጆች በልጆቻቸው ፊት ማለት የማይገባቸውን 9 ቃላት እንመለከታለን፡፡

1. ዝጋ! በስነ ምግባር የታነጸ ልጅን ማሳደግ ቀላል አይደለም ነገር ግን ወላጆች ስሜታቸውን ሳይቆጣጠሩ በብስጭትና በንዴት ልጃቸውን ማናገር አይጠበቅባቸውም፡፡ ልጆች ወላጆቻቸው በቃላት እየነገሩ ከሚያስተሙሯቸው ነገረ ይልቅ የእነሱን ምግባር አይተው የሚማሩት ነገር ይበልጣል፡፡

2. ትምህርት ይደብራል፡፡ ወላጆች የልጆቻቸው የመጀመሪያዎቹ መምህራን እንደመሆናቸው መጠን ልጆቻቸው በምንም ዓይነት መልኩ ትምህርት መጥላት የሚችሉበትን ቀዳዳ መክፈት የለባቸውም፡፡ ልጆቻቸው መምራኖቻቸውን በማመን ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር ተላምደው እንዲሄዱ ማድረግ ግድ ይላል፡፡ ወላጆቻቸው የጠሉትን ነገር ልጆቻቸውም ይጠላሉ፡፡

3. ሞት እንቅልፍ አንደ መተኛት ነው፡፡ ልጆች ከዕድገታቸውና ከዕድሜአቸው አንጻር አንዳንድ ጉዳዮችን በቀላሉ ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ልጆቻቸውን ለማስፈራራትም ይሁን በእነሱ ጥያቄ መሠረት ሞትን ከእንቅልፍ ጋር አመሳስለው ከነገሯቸው ልጆች በሚመሽበት ሰዓት ወደ መኝታ ቤት መሄድን ስለሚፈሩ ወላጆች ለልጆቻቸው የማይመጥናቸውን ነገር ባይነግሯቸው ይመረጣል፡፡

4. እስቲ አየዋለሁ፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ማድረግ የማይችሉትን ነገር በቀጥተኛ ንግግር ሊነግሯቸው ይገባል፡፡ እሺም እንቢም ሊሆን የሚችል ነገር መናገር በወላጆችና በልጆች መካከል ሊኖር የሚገባውን መተማመን ይቀንሳል አልያም ያጠፋል፡፡ ስለዚህ እንዳንዴ እቅጩን መናገር ትልቅ ጠቀሜታ ስለሚኖረው ልጆች አንድን ነገር የተከለከሉበትን ምክንያት በቀላሉ እንዲረዱ ያስችላቸዋል፡፡

5. ወይኔ ወፍሬአለሁ! ወላጆች በልጆቻቸው ፊት ስለ ውፍረትና ክብደት መጨመር እያነሱ የሚጨነቁ ከሆነ በልጆቻቸው ጤናማ አመጋገብ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራሉ፡፡ ወላጆቻቸው ብዙ በመብላት ነው የወፈሩት ብለው ስለሚያስቡ እንደ ወላጆቻቸው ላለመሆን ሲሉ የተዛባ የአመጋገብ ስርዓት እንዲከተሉ ማለትም ከምግብ እንዲታቀቡ ይገፋፋቸዋል፡፡

6. አትፍራ! ልጆች ደፋርና አካባቢያቸውን በደንብ እንዲያውቁ አድርጎ ማሳደግ ትልቅ ችሎታ ነው፡፡ ነገር ግን ወላጆች በደፈናው ልጆቻቸውን ምን መፍራት እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው ሳያሳውቋቸው በደፈናው አትፍሩ ማለት ልጆችን ወደ አደጋ ቀጠና እንደመገፋፍት ስለሚቆጠር አግባብነት ያለው ድፍረት ልጆችን ከአደጋና ለአደጋ ተጋላጭ ከመሆን ይታደጋቸዋል፡፡

7. ወይኔ በትኩሳት ነደሃል/ነደሻል፡፡ ልጆች ከአዋቂዋች ጋር ሲነጻጸሩ በቀላሉ ለበሽታ ተጋላጭ ናቸው፡፡ ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸው በሚታመሙበት ወቅት በፍጹም ስለ በሽታቸው መጠን መንገር አይጠበቅባቸውም ምክንያቱም ህክምና ከተከታተልን ህመማችን ይባባሳል ብለው ስለሚያስቡ፡፡ አልያም ከበሽታው ይልቅ ስነ-ልቦናዊ ጫናው ያይልባቸዋል፡፡

8. የብልግና ቃላትን መጠቀም፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው ጸያፍና የብልግና ቃላትን እንዳይጠቀሙ ከፈለጉ በመጀመሪያ ወላጆች እራሳቸው አንደበታቸውን ከጸያፍ ቃላት መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስም ይነሳል ከቤት ይደርሳል ጎረቤት እንደሚባለው፡፡

9. ደደብ ነህ/ሽ፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን በቁመት ያነሱ በአእምሮ ግን ትልልቅ ሰዎች አድርገው የሚስሏቸው ከሆነ ልጆቻቸው ስህተትን በሚሰሩበት ሰዓት ዘለፋና ወቀሳ ያወርዱባቸዋል፡፡ ልጅነት ወድቆ መነሳት ስለሆነ ልጆችን ደደብ ብሎ መሳደብ በፍጹም አያስፈልግም፡፡ እንዲሁም ልጅ ተሳስተው እየተማሩ ሲያድጉ ነው ደስ የሚለው ፍጹምነትን ከመጠበቅ ይልቅ፡፡


እንግዲህ ከላይ የተመለከትናቸው ወላጆች በልጆቻቸው ፊት መጠቀም የማይጠበቅባቸውን ቃላት ከብዙ ጥቂቱን ነው፡፡ እኔ መንገድ ካሳየዋችሁ እናንተ ደግሞ በየቤታችሁ አዳብሩት፡፡

#Share #Like
©zepsychologist (በአንቶኒዮ ሙላቱ)
የዚህ ሳምንት ስልጠናዎች!
የለውጥ ሰአት አሁን ነውና ለመሰልጠን ሌላ ጊዜ አትቅጠሩ ፡፡
★በ150 ብቻ ★

ሳይኮሎጂን መረዳት
ከ እንዳልካቸው ጋር
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ ሁለት 10 አመታት በሳይኮሎጂ መምህርነት ያሳለፈና በሳይኮሎጂ የ PHD እጩ ምሩቅ

ሰው መሆን
ከተመስገን አብይ ጋር
ወጣቱ አነቃቂ ተናጋሪና አሰልጣኝ

በተመችዋት ፈረቃ በመደወልና ቦታ በማስያዝ ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት በቦታው ተገኝቶ መመዝገብ ይቻላል
ቅዳሜ (3:00- 4:30)
ቅዳሜ (10:00-11:30)
እሑድ (10:00- 11:30)

ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ቁጥር ይደውሉ
0946333951
አድራሻ ፦ ካዛንቺስ ቅ /ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ሸገር ሕንፃ ቢሮ 201

@PSYCHOET
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂ pinned «የዚህ ሳምንት ስልጠናዎች! የለውጥ ሰአት አሁን ነውና ለመሰልጠን ሌላ ጊዜ አትቅጠሩ ፡፡ ★በ150 ብቻ ★ ሳይኮሎጂን መረዳት ከ እንዳልካቸው ጋር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ ሁለት 10 አመታት በሳይኮሎጂ መምህርነት ያሳለፈና በሳይኮሎጂ የ PHD እጩ ምሩቅ ሰው መሆን ከተመስገን አብይ ጋር ወጣቱ አነቃቂ ተናጋሪና አሰልጣኝ በተመችዋት ፈረቃ በመደወልና ቦታ በማስያዝ ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት…»
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_19
ማሕበራዊ ተፅዕኖ (በናሁሰናይ ፀዳሉ )

ማሕበራዊ ተፅዕኖ ማለት የአንድ ሰው (ግሩፕ) ተግባር የሌላው ሰው ባህሪን በአሉታዊ ሆነ በአወንታዊ መንገድ ተፅእኖ ሲያሳድር ነው ፡፡

ይሄ ተፅዕኖ በሶስት መንገድ ሊመጣ ይችላል እነርሱም
1. Conformity ፧ መስማማትና መከተል
2. Compliance ፧ ማሟላት ማክበር
3. Obedience ፧ መታዘዝ

1. conformity ፦ ማለት የአንድን ሰው እምነትና ስርአት (ሌሎች የሚሰሩትን) ለመከተል በምናረገው ጥረት የሚመጣ የባህሪ ለውጥ ነው ፡፡

2. Compliance ፦ ይህ ደግሞ አንድን ነገር እንድናደርግ የሚደርስብን ማሕበራዊ ግፊት ነው

በዚህ ስር ያሉ የግፊት አይነቶች
# ሰዎችን መጀመሪያ ቀላል ነገር እንጠይቅና ሲፈቅዱልን ወዲያው ወደ ከባዱ ጥያቄ እንሄዳለን
#ሰዎችን በመጀመሪያ ከባድ ነገር እንጠይቅና ወዲያው መልሳቸውን ከሰማን በኀላ ቀለል እናረገዋለን
ለምሳሌ ፦ ብዙ ነጋዴዎች እቃ ስንጠይቃቸው በመጀመሪያ ዎጋውን ከፍ አድርገው ይነግሩንና ከነሱ ወደ ሌላው ነጋዴ ስናመራ ወዲያው ቀለል ያለ ሂሳብ ይጠይቁናል ፡፡

ሌላው ደግሞ በብዛት በንግድ ስፍራዎች ላይ ተለቅ ያለ ዋጋ ፅፈው እሱን ይሰርዙና ካጠገቡ ደግሞ አነስ ያለ ዋጋ ይፅፋሉ በሌላ በኩል ደግሞ 20% 30-50% ቅናሽ ተብሎ ይለጠፍና ገዢዎችን ለመሳብ የስነልቦና ግፊት ይደረጋል ፡፡

3. Obedience ፦ የሌሎችን ትዕዛዝ መከተል /መፈፀም

ይሄ ደግሞ ለተለያዩ ከበላይ ላሉ ሰዎች ለአስተማሪዎቻችን ፣ ለስራ አለቆቻችን የምናሳየው የተገዢነት ሁኔታና በዚያ የምናደርገው የባህሪ ለውጥ ነው ፡፡

እነዚህ ሶስቱም መንገዶች አስተሳሰባችንን ፣ ድርጊታችንን ይቀርፃሉ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ማሕበራዊ ፍጥረት እንደመሆናችን መጠን በሌሎች እጅግተፅዕኖ ይደርስብናል ፡፡ ማንኛውንም አይነት ተፅዕኖ እንዴት ማሸነፍ እንችላለን በሚል ርዕስ ወደፊት እፅፋለሁ ፡፡

እስከዛ ከሳይኮሎጂ ትምህርት ውስጥ ስለ ምን ማወቅ እንደምትፈልጉ #Comment ብታረጉ ብዙ ሰው በመረጠው ርዕስ ላይ ወደፊት ፅሑፍ አዘጋጃለሁ ፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………
ቴሌግራም ቻናሌ www.tg-me.com/psychoet
❖_____________________________❖
Source: General Psychology (Psyc 1011) Higher Education Manual

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook/Telegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ ።

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
❖__________________________________❖
GreenFire መፅሔት .pdf
1 MB
ሰውን እንዳይችል የሚያረገው ምንድነው ?

በሚል በወጣቱ የሥነልቡና ተማሪና አነቃቂ ንግግሮች ተናጋሪ ተመስገን አብይ የተጻፈውን በዚህ መፅሔት ላይ ያገኙታል ፡፡

በተጨማሪም
ከማማረር ማሳመር
እንዳይታለሉ
የሚሉ ድንቅ ጽሑፎችን ያገኛሉ ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።

6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።

7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።

8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።

9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።

10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
#በቅንነት ሼር አድርጉ

@psychoet
የሰው ሕይወት #ተግባር

አብዛኞቻችን እቅዳችንን የማናሳካው የወሬ እንጂ የተግባር ሰው ስላልሆንን ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ወሬም ሆነ ተግባር ሁለቱም የሀሳብ ውጤት መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብናል ፡፡ ስለዚህ ሃሳባችንን ጠብቀን ወሬውን በተግባር ቀይረን ዉጤታማ ለመሆን መትጋት አለብን፡፡

ሁላችን እንዲሳካል እናስባለን ፣ እንመኛለን ፣ እናቅዳለን ፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን ምን ያህሎቻችን እቅዳችንንና ሀሳባችንን ለማሳካት ጠንክረን እንሰራለን የሚለው ጥያቄ ነው ? ለዚህስ ደግሞ ምን ያህል ተነሳሽነት አለን?

መልካም የተግባር ቀን!!!
www.tg-me.com/psychoet
ሰው መሆን በቂ ነው!

አንድ ቀን አንድ ሰው በድንገት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀና መውጣትም አልቻለም፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ደክሞት በጉድጓዱ መካከል ቁጭ እንዳለ …

• ከንፈር መጣጭ ሰው አየውና - “ሁኔታህን ሳስበው በጣም በሃዘን እሞላለሁ” ብሎት ሄደ፡፡

• ተመራማሪ ሰው አየውና - “ይህ ጉድጓድ ከተማ መሃል ሆኖ ሰው መውደቁ አያስደንቅም” ብሎት ሄደ፡፡

• ፈራጅ ሰው አየውና- “ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው እንደዚህ ሊወድቁ የሚችሉት” ብሎት ሄደ፡፡

• ነጭናጫና አጉረምራሚ ሰው አየውና- “እኔ ወድቄ የነበረበትን ጉድጓድ አላየህ” ብሎት ሄደ፡፡

• አነቃቂ ንግግር አስተማሪው አየውና- “በራስህ ብታምን ከዚህ ትወጣለህ” ብሎት ሄደ፡፡

• ዘረኛ ሰው አየውና - “የምን ሃገር ሰው ነህ?” በማለት ከጠየቀው በኋላ የእርሱን ቋንቋ ስላልተናገረ ጥሎት ሄደ፡፡

•ውሸተኛ የሀይማኖት ሰው አየውና - " የኔ እምነት ተከታይ ብትሆን አወጣህ ነበር " ብሎት ሂደ፡፡

• በመጨረሻ ይህንን ሁሉ ድራማ ሲመለከት የነበረ አንድ ጨዋ ጎልማሳ ሰው ከብዙ ጥረት በኋላ እየሳበ አወጣው ፡፡


ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? በእርግጥ ሰውነት ከሁሉ ይበልጣል ፡፡

ምንጭ :- ከዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

በቅንነት ሼር ያድርጉ👇
http://www.tg-me.com/psychoet
የዚህ ሳምንት ስልጠና!
የለውጥ ሰአት አሁን ነውና ለመሰልጠን ሌላ ጊዜ አትቅጠሩ ፡፡

የሕይወት አላማን መረዳት
ለምን እንደተፈጠርን የምናውቅባቸው መንገዶች ምንድናቸው?
ስለ እራሳችን ያለን አመለካከት ምን መምሰል አለበት?
አንድ ሰው በምድር ላይ ምን ያህልአስፈላጊ ነው?

አሰልጣኝ - ናሁሰናይ ፀዳሉ

በተመችዋት ፈረቃ ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት በቦታው ተገኝቶ መመዝገብ ይቻላል

★በ150 ብቻ ★
ቅዳሜ (3:00- 4:30)
ቅዳሜ (10:00-11:30)
እሑድ (10:00- 11:30)

ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ቁጥር ይደውሉ
0946333951
አድራሻ ፦ ካዛንቺስ ቅ /ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ሸገር ሕንፃ ቢሮ 201
@PSYCHOET
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂ pinned «የዚህ ሳምንት ስልጠና! የለውጥ ሰአት አሁን ነውና ለመሰልጠን ሌላ ጊዜ አትቅጠሩ ፡፡ የሕይወት አላማን መረዳት ለምን እንደተፈጠርን የምናውቅባቸው መንገዶች ምንድናቸው? ስለ እራሳችን ያለን አመለካከት ምን መምሰል አለበት? አንድ ሰው በምድር ላይ ምን ያህልአስፈላጊ ነው? አሰልጣኝ - ናሁሰናይ ፀዳሉ በተመችዋት ፈረቃ ስልጠናው ከመጀመሩ በፊት በቦታው ተገኝቶ መመዝገብ ይቻላል ★በ150 ብቻ ★ …»
#ማኅበራዊ_ክህሎት
Telegram www.tg-me.com/psychoet

ማኅበራዊ ህይወት ከውልደት እስከ ሞት የሚኖር እና ቀጣይነት ያለው ሂደት ሲሆን በትምህርት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት የሚዳብር ነው፡፡የሰው ልጅ ስለራሱ እና ስለሚኖርበት ማኅበረሰብ የሚኖረውን ዕውቀት በተለያየ መልኩ ማለትም የመግባቢያ ቋንቋ በመማር ፤ አካባቢያዊ ሁኔታውን በመመልከት እንዲሁም ማኅበራዊ ክህሎቶችን በመማር እያሳደገ ይሄዳል፡፡ ይህ የማኅበራዊ ህይወት ክህሎት በአግባቡ መዳበር ለተሟላ ስብዕና እና ዕድገት ወሳኝነት አለው፡፡

 የማኅበራዊ ህይወት አስፈላጊነት

#ለተሟላ አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት እንዲኖር እና የህይወት ቀጣይነት እንዲረጋገጥ፡፡
#ለሁለንተናዊ ሰላም ፤ ጤናና ደስታ፡፡
#ረጅም ዕድሜ ለመኖር፡፡
#ፍቅር ፤ መረዳዳት ፤ ስነ-ምግባር… እነዚህን የአንድ ማኅበረሰብ ህጎች እና ስርዓቶች ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ፡፡
#የሎሎችን ፍቅርና ድጋፍ ለማግኘት፡-

አዎንታዊ የእርስ በርስ ግንኙነት እንቅፋቶች

የግል ባህሪ

ራስ ወዳድነት ፤ ይሉኝታ ማጣት ፤ ግዴለሽነት ፤ሃቀኛና ታማኝ አለመሆን ፤ ኩራት ፤ ንቀት ፤ ያለፈ ጊዜ መጥፎ ተሞክሮ….

የሌሎች ዕሴቶችን እና አመለካከት ልዩነቶችን አለመረዳት

እሴቶች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ዕሴቶችን መረዳት እና የአመለካከት ልዩነቶችን ማክበር ለማኅበራዊ ግንኙነት መሻሻል ወሳኝ ነው፡፡ ይህም ማለት እሴቶቻችንን ወይም በህይወታችን ከፍተኛ ቦታ የምንሰጠውን ነገር ለይቶ ማወቅ ዓላማ ያለው ህይወት ለመምራት ይረዳናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሌሎችን ሰዎች እሴት ማወቅም እንዲሁ ከሰዎች ጋር ለሚኖረን መልካም ግንኙነት ወሳኝነት አለው፡፡ ምክንያቱም ሌሎች ሰዎች በህይወታቸው ዋጋ የሚሰጡትን ነገር ለይተን ካወቅን እና ለፍላጎታቸው አክብሮት ከሰጠን ሰላማዊ ግንኙነት ለመመስረት እንችላለን፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው የሚኖርበትን ማኅበረሰብ እሴቶች በሚጣረስ መልኩ ሲንቀሳቀስ ከማኅበረሰቡ የመገለል ዕጣ ሊገጥመው ይችላል፡፡

በአጠቃላይ ታማኝነት ፤ እውነት ፤ ግልጽነት ፤ ፍቅር ፤ መረዳዳት ፤ ትዕግስት ፤ መቻቻልና ኃላፊነትን መቀበል መቻል የመሳሰሉት በማኅበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ዕሴቶች ናቸው፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#የስሜት_ብልሃትና_ተግባቦት
#Emotional_Intelligence&Communication
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE

የስሜት ብልህነት ማለት ስሜታችንን የማወቅ ፣ የመረዳት የመምራት ችሎታ ነው ፡፡ ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው ፡፡

በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት ( Emotional Intelligence ) ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪ ምክኒያት ሰሚ ያጡ ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ይኖራሉ ፡፡

#ለዛሬ እነዚህ የተግባቦትና የስሜት ብልሀት አለመኖር በሕይወታችን የሚያመጡትን ችግር እንመልከት ፡፡

እኔ አንዱን ድግሪዬን በማኔጅመንት ስሰራ የመመረቂያ ጽሑፌ (Competency development in business areas ) የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ጥናት ያገኘሁት አንዱ ግኝት ሰዎች ለቢዝነሳቸው መውደቅ አንዱ ምክንያት ያላቸው አነስተኛ #የተግባቦትና #የስሜት_ብልሀት ነው ፡፡ በእርግጥ ተግባቦትም ሆነ የስሜት ብልህነት ሳይንሳዊ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማሳደግ ይቻላል ፡፡

#የስሜት_ብልሃትና_ጥሩ_ተግባቦት_የሌላቸው_ሰዎች_መገለጫዎች

★የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም ( በቀላሉ ይናደዳሉ ፣ ይበሳጫሉ ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል )

★ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም ፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል ፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም

★በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ

★በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል

★ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ ፣ ይረበሻሉ ፡፡

★ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም ፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ ፣

★ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው

ከላይ የዘረዘርኳቸው መገለጫዎች( የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው ። በእርግጥ እነዚህ ሁሉ መገለጫዎች ሳይኮሎጂካል ህክምና አላቸው ፡፡

ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች በራሳችሁ ላይ የምታዩ ሰዎች ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ በጥቂት ጊዜ ጥሩ የሆነ ተደጋጋሚ ሳይኮሎጂካል ልምምዶችን በማረግ መዉጣት ይቻላል ፡፡
___________________________
#በየሳምንቱ በምሰጠው ስልጠና ላይ እነዚህን ጉዳዮች በስፋት የማነሳቸው ሲሆን በየቀኑ ለሳምንት የሚሰራ እነዚህን ክህሎት የሚያሳድጉ ልምምዶችን በተግባር እናያለን፡፡ ለመለወጥ የወሰናችሁ ሰዎች ወደ ስልጠናው እንድትገኙ እጋብዛለሁ
+251946333951

፠፠______________________________፠፠
ምንጭ ፦ ከማሰለጥንበት ማስተማሪያ ማኑዋል የወሰድኩት

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍


ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠______________________________፠፠
የሳምንት ሰው ይበለን!
አስተሳሰብን መቆጣጠር

አስተሳሰብን መቆጣጠር ማለት ወደ እኔ የሚመጣውን ወይም በውስጤ የሚፈጠረውን ሃሳብ በማጣራት ማስተናገድ ማለት ነው፡፡ አስተሳሰባችንን ሳንለውጥ ሕይወታችንንም ሆነ ሁኔታችንን መለወጥ አንችልም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የሁሉ ነገር መጀመሪያ አስተሳሰብ ስለሆነና አስተሳሰባችን የማንነታችን “ወፍጮ” በመሆኑ ነው፡፡ በመጀመሪያ አንድ ሃሳብ ወደ አእምሮአችን ይገባል፡፡ በመቀጠልም ይህ ሃሳብ በውስጣችን ይብላላና በንግግርና በተግባር መገለጥ ይጀምራል፡፡ ይህ ተግባር ወደ ልማድ ከተለወጠ በኋላ ፍጻሜአችንን የመለወጥና የመቅረጽ ጉልበት ይኖረዋል፡፡ ይህ ሃሳብ ጤናማም ሆነ ጤና ቢስ ሂደቱ ያው አንድ ነው፡፡

ጤና ቢስ አመለካከቶችን ለማስወጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. በሕይወትህ የምታሰላስላቸውን ሃሳቦች ለይተህ እወቅ፡፡

ለማንነትህና ለሕይወትህ አላማ የሚመጥኑ ሃሳቦች ምን እንደሆኑ ለይተህ ማወቅ አለብህ፡፡ ይህንን ለይተህ ስታውቅ በሃሳቦች መካከል መለየትንና የትኛውን ማስተናገድ እንዳለብህ ጥርት ባለ መልኩ እንድታውቅ ይረዳሃል፡፡

2. ጤና ቢስ አስተሳሰቦችን አታስተናግዳቸው፡፡

የመጣ ሃሳብ ሁሉ በአእምሮህ ስፍራ ማግኘት የለበትም፡፡ ለጤናማ አመለካከትህና ላስቀመጥከው የሕይወት ከፍታና ደረጃ የማይመጥነውን ተራ ሃሳብ በመጣበት ፍጥነት እንዲወጣ ተቃወመው፡፡ ይህንንም ልምምድ የዘወትር አድረገው፡፡

3. ጤና ቢሱን አስተሳሰብ በጤናማ አስተሳሰብ ቀይር፡፡

ከዚህ በፊት በውስጥህ ያስተናገድካቸውን ጤና ቢስ ሃሳቦች መልካምና ስኬታማ በሆኑ ጤናማ ሃሳቦች መለወጥ መጀመር አለብህ፡፡ ከአእምሮህ ክፉውን ሃሳብ አስወጥተህ በጤናማው ካልተካኸው ሌላ ሃሳብ መሙላቱ አይቀርም፡፡

ምንጭ : ከዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ
በቅንነት ሼር ያድርጉልኝ 👇
http://www.tg-me.com/psychoet
መልካም የሴቶች ቀን !
እናቱን ፣ እህቱን የሚወድ ሁሉ #share በማረግ ፍቅሩን ይግለፅላት !

💢ሴት ማለት 9ወር ሰለችን ደከመኝ ሳትል በሆዷ የተሸከመችህ ናት!
💢ሴት ማለት አንተ ስትመታ የሚያማናት ናት
💢ሴት ማለት እሷ ተርባ አንተን የምትመግብ ናት
💢ሴት ማለት ብዙ ጉድ ተሸክማ አንተን ለማስደሰትና መልካሙን ለመስጠት የምትሮጥ ናት
💢 ሴት ማለት ብዙ መልካም ነገር ናት .....

♨️♨️♨️ እስቲ ስለ እናት ፣ እህት ልጅነት ባህሪ አንድ ነገር Comment ላይ ግለፁ ???

#Happy_day
#መልካም_ቀን

👍👍👍 የሥነ ልቡና ፔጅ #Like በማረግ በየቀኑ መልካም መልካም ሀሳቦችን ያግኙ ፡፡ ስለ ሰዉ አስተሳሰብና ባህሪ ብዙ ይረዱበታል ፡፡

@Psychoet
2024/11/05 19:08:33
Back to Top
HTML Embed Code: