Telegram Web Link
የተሻለ ሆኖ መገኘት ያለብህ
በዙሪያህ ካሉ ሰዎች ሳይሆን
ከትናንትናው ማንነትህ ነው ፡፡

@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ክፍል 2
ደስተኛ ሕይወት ለመኖር እነዚህን ተግባሮች ልምዳችን እናድርግ

1. ምስጋና ለደስተኛ ሕይወት

አመስጋኝ የሆኑ ሰዎች ምስጋና ቢስ ከሆኑ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ እውነት ነው ህይወት በፈተና፣ ችግር እና ውጣ ውረድ የተሞላች ናት፡፡ ይሁን እንጂ ፈተናም ቢሆን ራሱን የቻለ በጎ ጎን ይኖረዋል፡፡ ፈተና ሊያስተምረን፣ ሊያንጸን፣ መልካም አጋጣሚ ሊፈጥርልን ይችላል፡፡ ስለሆነሞ በማንኛውም አጋጣሚ አመስጋኞች መሆን የበለጠ ደስተኛ ያረገናል ፡፡ በቅርባችን የሚገኙ ሰዎች የሚገባ ነገርም አድርገውልን ቢሆን እነሱን ማመስገን ከውስጣችን የሚወጣው አወንታዊ ሀይል (Positive energy ) ስለሆነ ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች መልካም አቅምን እንገነባለን ፡፡


2. ቀና ማሰብ ለደስተኛ ሕይወት

ቀና ማሰብ ብዙ እጅግ በጣም ብዙ ጥቅም አለው፡፡ አንዱ ትርፉ ደስታ ነው፡፡ ቀና አሳባዎች ቀና ከማያስቡ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለግን “ይሆናል፤ ይቻላል፤ ይሳካል፤ ለበጎ ነው ወዘተ” ማለትን እንለማመድ፡፡ ከተራራው ባሻገር ላለለችው ፀሐይ ትኩረታችንን እንሰብስብ፡፡

የዓለምን ችግር ሁሉ ጫንቃቸው ላይ ተሸክመው የሚኖሩ ይመስል ፊታቸው የማይፈታ፤ በጎ ነገር የማይታያቸው፤ ሳቅና ጨዋታ ጠል የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ ኑሯቸው ዳገት በዳገት ብቻ የሆነው አእምሮአቸው በአሉታዊ ሃሳቦች በመሞላቱ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዕድል በራቸውን ሲያንኳኳ ድምጹ ረበሸን፤ እንቅልፍ ነሳን ወዘተ ብለው የሚያማርሩ ዓይነት ናቸው፡፡ ኖርማን ቪንሰንት “The Power Of Positive Thinking” በሚለው መጽሐፉ እንዲህ ይላል፡- “የደስታ ምስጢር ልብን ከጥላቻ ማጽዳት፤ አእምሮን ከጭንቅት ነፃ ማድረግ እና ብዙ መስጠት ነው፡፡ ፀሐይ ስትወጣ እና ስትጠልቅ የምታንጸባርቀውን ውበት እያያችሁ የምትደነቁ ሰዎች ሁኑ፤ ለሌሎችም እንደ ራሳችሁ አስቡ፡፡ ይህንን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት ያህል ሞክሩት፤ በውጤቱም ትደነቃላችሁ”፡፡

3. ከልክ በላይ ማሰብ እና ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማቆም ለደስተኛ ሕይወት

“ከልኩ አያልፍ” ትል ነበር አያቴ ሃሳብ ከልክ በላይ እንደገባት ወይንም አጠገቧ ያለ ሰው ከልክ በላይ እንደተጨነቀ ሲሰማት፡፡ ሺህ ዓመት አይኖርም፡፡ ሁሉም የሚያጭደው የዘራውን ነው፡፡ ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የተረጋገጠ ራስን የማሰቃያ መንገድ ነው፡፡ ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ ሊኖር አይገባም፡፡
ከልክ በላይ ማሰብ በጤናችን ላይ ውጥረትን ያመጣል ይህ ደግሞ ወደ ጭንቀት ይመራናል ፡፡ ራሳችንን ከሌሎች ማወዳደር ደግሞ አቅማችንን በተገቢው መንገድ እንዳንጠቀም ያረገናል ፡፡ በተጨማሪም ከአቅማችን በላይ ሩጠን እንድንበጠስ አልያም ከአቅማችን በታች ሩጠን መድረስ የሚገባን ቦታ እንዳንደርስ ይይዘናል ፡፡

መልካም የደስታ ሕይወት!
መልካም የደስታ ቀን!

ይቀጥላል ...
#Share #Like
@psychoet
እባካችሁ #Share አድርጉት !

በቻይና ውሀን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በረሀብ ሊሞቱ ነው ፡፡ እንደሚታወቀው በሽታው ስርጭት መጠኑን መጨመሩ ተከትሎ በቻይና ባሉ ብዙ ግዛቶች የለት ተእለት ስራ ፣ ትምህርት ...ብዙ እንቅስቃሴዎች ቆመዋል ፡፡ ሰው ከቤት የሚወጣው ምግብ ለመግዛት ብቻ ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ በቻይና ያሉት ኢትዮጵያውያን (በተለይም በዉሀን) ግዛት ያሉ በጣም በሥነልቡና ህመም ውስጥ ይገኛሉ ፡፡

ስለዚህ እባካችሁ መልዕክቱን #Share በማረግ ድምፅ እንሁን!

1.የቫይረሱ ክትባት እስኪገኝ ድረስ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን መንግስት ወደ ሀገር ያስገባቸው፡፡

2.የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቫይረሱ መድኃኒትና ክትባት እስኪገኝ ድረስ ወደ ቻይና የሚደረገው በረራ ይቁም አልያም ( ከዚያ የሚመጣ ሰው ከ 1-2 ሳምንት በማቆያ ገብቶ ጤነኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ወደ ሀገሪቱ ይግባ ምክንያቱም ቫይረሱ 2 ሳምንት ድረስ ላይታወቅ ስለሚችል ከቻይና ቫይረሱ ያለበት ሰው ምልክት ሳያሳይ ቢገባ እዚህ ብዙ ችግር ሊፈጠር ይችላል ) ፡፡ በተጨማሪ በአውሮፕላን ጉዞ ላይ በአንድ አውሮፕላን ከሚመጡ ከመቶ በላይ ሰዎች እርስ በእርስ የመለተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው አንዱ ሰው በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳፋሪዎች ላይ ሊያስተላልፍ ይችላል ፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ የሀገራችን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንኳን በሽታውን ሊያክም ይቅርና የበሽታውን ምርመራ ራሱ የሚደረገው ደቡብ አፍሪካ ልኮ ነውና ለሀገራችን በችግር ላይ ችግር ይሆንባታል በተጨማሪም የበሽታውን ከባድነትን ያዩ በቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ራሱ አየር መንገዱ በረራ ለጊዜው እንዲያቆም እየጠየቁ ነው ፡፡

ስለዚህ መንግስት ለነዚህ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥ እጠይቃለን ?


በሀሳቡ የሚስማማ #Share ያድርግ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

@Psychoet
ክፍል 3
ደስተኛ ሕይወት ለመኖር እነዚህን ተግባሮች ልምዳችን እናድርግ
4. ደግነት ለደስተኛ ሕይወት

ደግ መሆን ደስተኛ ያደርጋል፡፡ ደግ መሆን ይቅርና ሰዎች ደግ ስራ ሲሰሩ መመልከት እንኳን ደስተኛ እንደሚያደርግ ሳይኮሎጂስቶች አረጋግጠዋል፡፡ ደስታ ከህይወታችን እንደ ራቀ ሲሰማን አንዱ መልሶ ማቅረቢያ ስልት መልካም ስራ መስራት ነው፡፡ በርካታ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች አሉ፡፡ አንዱ ጋር የተወሰነ ጊዜ መስዋዕት በማድረግ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ለራስም ለሌላውም ደስታን ይፈጥራል፡፡

5. መልካም ማኅበራዊ ግንኙነት ለደስተኛ ሕይወት

“ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው” ብለው አበው ጨርሰውታል፡፡ የልባችንን የምናዋየው የልብ ወዳጅ ዘመድ አንዱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ የሚያሳስበንን ነገር ከውስጣችን አውጥተን መናገር ጭንቀትን ይቀንሳል፡፡ በዛው ልክ ደስታም ይጨምራል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰብሰብ ብሎ ሳቅና ጨዋታ መፍጠርም ራሱን የቻለ የደስታ ምንጭ ነው፡፡

6. ጭንቀትን እና ውጥረትን የምንቆጣጠርበት ዘዴ መቀየስ ለደስተኛ ሕይወት

ደስታን የሚፈጥረው ቀደም ሲል በሌላ በምንም አይደለም በተግባር ነው ብያለሁ፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የምናከናውነው አንድ ሁለት ጤናማ የሆነ የደስታ ምንጭ መሆን የሚችል ዘዴ መቀየስ ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ ኳስ መጫወት፣ ተራራ መውጣት፣ ብስክሌት መንዳት፣ ዳንስ ስልጠና መውሰድ ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡

መልካም የደስታ ሕይወት!
መልካም የደስታ ቀን!

ይቀጥላል ...
#Share #Like
@psychoet
መልካም ዜና!
ሁለተኛና የመጨረሻ ዙር የነፃ ስልጠና ቀናቶች !

ቅዳሜ ጥር 30 ከ 10:00 - 11:00 እንዲሁም
እሑድ የካቲት 1 ከ 11:00 -12:00
#ልዩ_የነፃ_የስልጠና_እድል_ተዘጋጅቷል ፡፡

ያለው ቦታ ለቅዳሜ (35) ለእሑድ (35) ቦታ ብቻ ስለሆነ ቀድማችሁ በመደወል በአንዱ ቀን ብቻ #በነፃ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን ፡፡

የመመዝገቢያ ሰአት
ረቡዕ ፣ ሐሙስ ከጠዋቱ (3:00 - 11:00) ብቻ በ +251946333951 በመደወል መመዝገብ ፡፡
ቀድሞ የተመዘገበ ቀድሞ ቦታ ያገኛል ፡፡

⚠️⚠️⚠️ይህ የነፃ ስልጠና የመጨረሻ ሲሆን ከቀጣይ ሳምንት በኀላ ያለው የክፍያ ስልጠና ብቻ ነው ፡፡

የስልጠና አድራሻ ፦ አዲስ አበባ ካዛንቺስ ቅ/ኡራኤል ቤ/ክ አጠገብ ሸገር ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 202

ቴሌግራም ፦ www.tg-me.com/psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ክፍል 4
ደስተኛ ሕይወት ለመኖር እነዚህን ተግባሮች ልምዳችን እናድርግ

7. ይቅርታ ለደስተኛ ሕይወት

“ቂም መቋጠር ማለት መርዝ ጠጥቶ ሌላኛው ሰው እንደሚሞት ማሰብ ነው” ይባላል፡፡ ይቅርታ የምናደርገው ከሁሉ በፊት ለገዛ ራሳችን ደህንነት ነው፡፡ ይቅርታ ማድረግ የጥንካሬ ምንጭ እና መገለጫም ነው፡፡ ማህተመ ጋንዲ “ደካማ ሰው ይቅር ብያለሁ ማለት አይችልም፡፡ ይቅርታ የጠንካራ ሰው መገለጫ ነው (The week can never forgive. Forgiveness is the attribute of the strong)” ይላሉ፡፡ ይቅር ብያለሁ ማለት በመንፈስ የበላይ መሆን ነው፤ መብለጥ ነው፤ ገናና የሞራል ከፍታ ላይ መውጣት ነው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ደስታን ወደ ህይወታችን የምንጋብዝበት መጥሪያ ካርድ ነው፡፡

8. የምንወደውን ነገር ማድረግ ለደስተኛ ሕይወት

አንዳንድ ነገሮች አሉ ስናደርጋቸው ሌላውን ዓለም የሚያስረሱን፤ ፍጹምነት እንዲሰማን የሚያደርጉ፤ ምንም የጎደለን ነገር እንደሌላ የሚያረጋግጡልን፡፡ ፈረንጆቹ መሰል አጋጣሚዎችን “Flow Experiences” ይሏቸዋል፡፡ እንደየሰው እንደዚህ ዓይነት ስሜት የሚፈጥሩብን ነገሮች ይለያያሉ፡፡ መደነስ፣ ስዕል መሳል፣ መጻፍ፣ የእርዳታ ስራ መስራት፣ ማንበብ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 2007 ዓ.ም ከማለፉ በፊት ወደ ደቡቡ የአገራችን ክፍል ለእረፍት ከጓደኞቼ ጋር ሄጄ ነበር፡፡ የአካባቢው የተፈጥሮ ውበት እና ውስጤ የተፈጠረው እርካታ ከኋላዬ ትቼው የመጣሁትን ነገር በሙሉ ለአራት ቀናት ያህል አስረስቶኝ ነበር፡፡ ልዩ ልዩ አስደሳች የህይወት ገጠመኞችን ማጣጣም ህይወት በሚደገሙም በማይደገሙም በርካታ አስደሳች ገጠመኞች የተሞላች ናት፡፡ እያንዳንዱን ገጠመኝ ለሁለተኛ ጊዜ እንደማይደገም በመቁጠር አጣጥሞ ማለፍ ደስታ ውስጣችን በጥልቀት እንዲሰርጽ ያደርጋል፡፡ እነዚህ የህይወት ገጠመኞች ልደት፣ ምርቃት፣ በዓላት ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

9. ያቀድነውን ዕቅድ እውን ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ለደስተኛ ሕይወት

ያሰቡትን ማሳካት በራሱ ትልቅ ደስታን ይፈጥራል፡፡ ሁልጊዜ ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ ከሆንን ግን ደስታ ውስጣችን አይለመልምም፡፡ የጀመርነውን ነገር ዳር የማድረስ ልምዱ ይኑረን፡፡ የምንኖረው የአማራጮች ዓለም ውስጥ ነው$ ብዙ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች ተችለው የምንመለከትበ ዓለም፡፡

መልካም የደስታ ሕይወት!
መልካም የደስታ ቀን!

ይቀጥላል ...
#Share #Like

@Psychoet
መልካም ዜና!
ሁለተኛና የመጨረሻ ዙር የነፃ ስልጠና ቀናቶች !

ቅዳሜ ጥር 30 ከ 10:00 - 11:00 እንዲሁም
እሑድ የካቲት 1 ከ 11:00 -12:00
#ልዩ_የነፃ_የስልጠና_እድል_ተዘጋጅቷል ፡፡

ያለው ቦታ ለቅዳሜ (35) ለእሑድ (35) ቦታ ብቻ ስለሆነ ቀድማችሁ በመደወል በአንዱ ቀን ብቻ #በነፃ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን ፡፡

የመመዝገቢያ ሰአት
ረቡዕ ፣ ሐሙስ ከጠዋቱ (3:00 - 11:00) ብቻ በ +251946333951 በመደወል መመዝገብ ፡፡
ቀድሞ የተመዘገበ ቀድሞ ቦታ ያገኛል ፡፡

⚠️⚠️⚠️ይህ የነፃ ስልጠና የመጨረሻ ሲሆን ከቀጣይ ሳምንት በኀላ ያለው የክፍያ ስልጠና ብቻ ነው ፡፡

የስልጠና አድራሻ ፦ አዲስ አበባ ካዛንቺስ ቅ/ኡራኤል ቤ/ክ አጠገብ ሸገር ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 202

ቴሌግራም ፦ www.tg-me.com/psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «መልካም ዜና! ሁለተኛና የመጨረሻ ዙር የነፃ ስልጠና ቀናቶች ! ቅዳሜ ጥር 30 ከ 10:00 - 11:00 እንዲሁም እሑድ የካቲት 1 ከ 11:00 -12:00 #ልዩ_የነፃ_የስልጠና_እድል_ተዘጋጅቷል ፡፡ ያለው ቦታ ለቅዳሜ (35) ለእሑድ (35) ቦታ ብቻ ስለሆነ ቀድማችሁ በመደወል በአንዱ ቀን ብቻ #በነፃ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን ፡፡ የመመዝገቢያ ሰአት ረቡዕ ፣ ሐሙስ…»
ክፍል 5
ደስተኛ ሕይወት ለመኖር እነዚህን ተግባሮች ልምዳችን እናድርግ

10. ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ለደስተኛ ሕይወት

ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ደስተኛ እንደሚያደርጉ በጥናት ጭምር ተረጋግÚል፡፡ ሃይማኖት ያለን እንደየቤተ እምነታችን፣ መንፈሳዊ ብቻ ነን የምንልም እንዲሁ የመንፈስ ፍሬዎች የሚባሉ ተግባራትን በማከናወን ጎጇችን በደስታ ጸዳል የደመቀ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን፡፡

11. አካላችንን መንከባከብ ለደስተኛ ሕይወት

አእምሮአችን ከአካላችን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም የአካላችን ደህንነት የአእምሮአችም ደህንነት ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል፡፡ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፤ ስፖርት መስራት ወዘተ የአካላችንን ጤና በመጠበቅ የአእምሮችንም ጤና ይጠብቃል፡፡ “Take care of your body. It’s the only place you have to live.” ይባላል፡፡ “አካላችሁን በሚገባ ተንከባከቡ፡፡ ብቸኛው የምትኖሩበት ስፍራ እሱ ነውና” እንደ ማለት ነው፡፡ አበቃሁ!

መልካም የደስታ ሕይወት!
መልካም የደስታ ቀን!

ተጠናቀቀ
#Share #Like
@psychoet
#ተሰሚነት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ብዙዎቻችን የሚጎለን ክህሎት ስለሆነ ሌሎችም እንዲማሩ አንብበን #Share እናርገው

“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡ ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡

ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡

ቅለት

ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡

ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ

“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡

በራስ መተማመን

አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ ጉልበት አላቸው፡፡

በሌሎች ዓይን ማየት

ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣ ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ መቼም አይጠፋም፡፡

ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡

እጥረትን መፍጠር

ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣ የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣ በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡

ዝግጅት

ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመናችንንም ይገነባል፡፡

ለምሳሌ እነዚህን በሙሉ ክህሎቶች ዶ/ር ምህረት ላይ እናገኛለን ፡፡ የመሰማቱ አንዱ ሚስጢር ይሄ ነዉ ፡፡ ሲያስተምር አይታችሁ ከሆነ የሚያስተምረውን ነገር ቀለል አርጎ ፣ በራስ መተማመን ለአድማጭ በሚስብ መልኩ ያደርጋል ፡፡ ይህ በሁላችን አድማጮቹ ዘንድ ተሰሚነትን ፈጥሮለታል ፡፡ በሌላ በኩል አንድ ሰፈር /ስራ ቦታ የምናውቀውን ሳያቋርጥ የሚያወራ ፣ ንግግር የማያስጨርስ ሰው ስናስብ እንኳን ለመስማት ከሱ ጋር ለማውራት ይቀንቀናል ፡፡ እንግዲህ ሚስጥሩ ይሄው ነው ፡፡

በሰዎች ዘንድ ለመሰማት በዕውቀትና በጥበብ እናውራ !
(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#Share & #Like oue page - fb.com/psychologyet
_____________________________
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#Emotional_Intelligence&Communication
#የስሜት_ብልሃትና_ተግባቦት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)


የስሜት ብልህነት ማለት ስሜታችንን የማወቅ ፣ የመረዳት የመምራት ችሎታ ነው ፡፡ ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው ፡፡

በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት ( Emotional Intelligence ) ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪ ምክኒያት ሰሚ ያጡ ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ይኖራሉ ፡፡

#ለዛሬ እነዚህ የተግባቦትና የስሜት ብልሀት አለመኖር በሕይወታችን የሚያመጡትን ችግር እንመልከት ፡፡

እኔ አንዱን ድግሪዬን በማኔጅመንት ስሰራ የመመረቂያ ጽሑፌ (Competency development in business areas ) የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ጥናት ያገኘሁት አንዱ ግኝት ሰዎች ለቢዝነሳቸው መውደቅ አንዱ ምክንያት ያላቸው አነስተኛ #የተግባቦትና #የስሜት_ብልሀት ነው ፡፡ በእርግጥ ተግባቦትም ሆነ የስሜት ብልህነት ሳይንሳዊ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማሳደግ ይቻላል ፡፡

#የስሜት_ብልሃትና_ጥሩ_ተግባቦት_የሌላቸው_ሰዎች_መገለጫዎች

★የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም ( በቀላሉ ይናደዳሉ ፣ ይበሳጫሉ ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል )

★ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም ፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል ፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም

★በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ

★በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል

★ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ ፣ ይረበሻሉ ፡፡

★ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም ፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ ፣

★ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው

ከላይ የዘረዘርኳቸው መገለጫዎች( የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው ። በእርግጥ እነዚህ ሁሉ መገለጫዎች ሳይኮሎጂካል ህክምና አላቸው ፡፡

ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች በራሳችሁ ላይ የምታዩ ሰዎች ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ በጥቂት ጊዜ ጥሩ የሆነ ተደጋጋሚ ሳይኮሎጂካል ልምምዶችን በማረግ መዉጣት ይቻላል ፡፡
___________________________

#በሚቀጥለው_ሳምንት_የካቲት7እና8_የምጀምረው ስልጠና ላይ እነዚህን ጉዳዮች በስፋት የማነሳቸው ሲሆን በየቀኑ ለሳምንት የሚሰራ እነዚህን ክህሎት የሚያሳድጉ ልምምዶችን በተግባር እናያለን፡፡ ለመለወጥ የወሰናችሁ ሰዎች ወደ ስልጠናው እንድትገኙ እጋብዛለሁ ?
+251946333951
ምዝገባው ከመጪው (ሰኞ - አርብ) ይሆናል!

፠፠______________________________፠፠
ምንጭ ፦ ከማሰለጥንበት ማስተማሪያ ማኑዋል የወሰድኩት

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍


ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠______________________________፠፠
የሳምንት ሰው ይበለን!
ክፍል 3
የአሸናፊነት ሕይወት

አሸናፊ ለመሆን እና ለመባል በምንወዳደርት / በምንሮጥበት የሕይወት ውድድር ባሰብነውና ባቀድነው መገኘት ይኖርብናል ፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቻችን የምንሮጥበትን / የምንወዳደርበትን መስክስ በቅጡ አልተረዳንም ሌላም ከማን ጋር መወዳደር እንዳለብን አልተረዳም ለዚህም ነው ሁሌ በሕይወታችን የተሸናፊ ፣ የአለመቻል ሥነልቦና ይዘን የምንመላለሰው ፡፡

ዛሬ ጠዋት የተለመደውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴዬን ጃንሜዳ በጠዋቱ እየሰራሁ ነበር ፡፡ ግማሹ ይሮጣል ፣ ሌላው ኳስ ይጫወታል ፣ ቀሪው ይመለካታል ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ይታያል ፡፡

እኔ ከሚሮጡት ወገን ነበርኩ ፡፡ ስሮጥ ግን ሁሌ የምገነዘበው ነገር አለ ፡፡ እኔ መንገዴን ይዤ ስሮጥ ሁልጊዜ ከለሊት ጀምረው የሚሮጡ ሯጮች ከኀላዬ መተው ይቀድሙኛል እሱ ብቻ አይደለም እኔ አንዱን ዙር ሳልዞር ይደርቡኛል ፡፡ ፅናታቸው፣ ጥንካሬያቸው ይገርመኛል ፡፡ እኔ ጥቂት ዙር ሳልሮጥ እነሱ ብዙ ዙር ይዞራሉ ፡፡

ነገር ግን አንድም ቀን ከነሱ ጋር ለመፎካከር አስቤ አልያም ለምን ቀደሙኝ እና ደረቡኝ ብዬ አዝኜ አላውቅም ፡፡ ምክንያቱም ከነሱ ጋር አንድ ዙር እንኳን ብሄድ አይደለም እንደነሱ ሌላ ዙር መሮጥ ለብቻዬ እንኳን በእርምጃ የምደግመው አይመስለኝም ፡፡ ሁሌ መሮጥ ያለብኝን እርቀት እና ግዜ ስለማውቅ ውድድሬ ከሌሎች ጋር ሳይሆን ከራሴ እቅድ ነው ፡፡ እኔ ለምን እንደምሮጥ አውቃለሁ ፡፡ ከኔ የሕይወት ውድድር ውጭ ከሆነ ሰው ጋር ተወዳድሬ አንድም አልዘገይም ደግሞም ፈጥኜ አልደክምም፡፡

አሸናፊነት ሥነልቦና ኀላም ድርጊት እንጂ ቀድሞ ነገሮችን ስለመጨረስም ብቻ አይደለም ...

ሳምንት ይቀጥላል ፡፡
መልካም እሑድ !
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

@psychoet
#መልካም_የካቲት_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

አንድ ቀን ነገር ሁሉ ቀላል ይሆናል ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
#እወዳችኀለሁ!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
ለፔጁ ቤተሰቦች
www.tg-me.com/psychoet
fb.com/psychologyet

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ አዳዲስ የሥነልቦና ትምህርቶችን በ FACEBOOK እንዲሁም በTELEGRAM እጀምራለሁ ፡፡

ስለዚህ እስካሁን ያነሳኀቸው ነጥቦች ከጠቀማችሁ ወይም ጠቃሚ እንደሆኑ ካመናችሁ ጓደኞቻችሁን ወደዚህ ፔጅ እንድትጋብዙ እጠይቃለሁ ፡፡ ይህንንም መልእክት ደግሞ #Share እንድታረጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ ፡፡

በቅርቡ የምፅፋቸው ውስጥ
*የአስተዳደግና የባህሪ ቁርኝት
*የአቻ ግፊትን ማሸነፍ
*የፍቅርና የጋብቻ ህይወትና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ
ስለ ሁለንተናዊ የሕይወት ስኬት
*ስለ አዕምሮና አስተሳሰብ ጤንነት ወዘተ ...

መልካም ጊዜ !
ቴሌግራም ቻናሌ ፦ www.tg-me.com/psychoet
ዕውቀት ከአስተሳሰብ ጨለማ ነፃ ያወጣል ፡፡
2024/10/01 07:12:42
Back to Top
HTML Embed Code: