Telegram Web Link
መልካም አጋጣሚ!
🎊🎉🎉🎁🎉🎉🎊

በመጪው ቅዳሜ ጠዋት ( 3:00 - 4:30)

የሕይወት አላማን ማወቅና የውጤታማ የሕይወት እቅድ አዘገጃጀት ላይ ስልጠና ስለተዘጋጀ ባሉት ጥቂት ቦታዎች መመዝገብ ይቻላል ፡፡

🧩
👉ለምን እንደተፈጠሩ ያውቃሉ ?

👉ሕይወት ትርጉም አልባ ፣ አሰልቺና
ድግምግሞሽ ሆናባችኀለች ?

👉የበታችነት ፣ያለመቻል እንዲሁም ጠቃሚ ያለመሆን ስሜት ይሰማዎታል ?

👉 🎯እቅድ ማቀድ ያስቸግርዎታል ፣🎯 አቅደውስ ማሳካት ከብድዎታል ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው እንዴትስ ይሻሻላል ?

እነዚህን ሁሉ ከሳይኮሎጂ እና ከ ማኔጅመንት አንፃር እንመለከታለን ፡፡ ለቀሪው ሕይወትዎ መልካም እውቀትን ይሰንቁ !

መግቢያ ዎጋ * 150 ብር ብቻ
📞 +251946333951

@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «መልካም አጋጣሚ! 🎊🎉🎉🎁🎉🎉🎊 በመጪው ቅዳሜ ጠዋት ( 3:00 - 4:30) የሕይወት አላማን ማወቅና የውጤታማ የሕይወት እቅድ አዘገጃጀት ላይ ስልጠና ስለተዘጋጀ ባሉት ጥቂት ቦታዎች መመዝገብ ይቻላል ፡፡ 🧩 👉ለምን እንደተፈጠሩ ያውቃሉ ? 👉ሕይወት ትርጉም አልባ ፣ አሰልቺና ድግምግሞሽ ሆናባችኀለች ? 👉የበታችነት ፣ያለመቻል እንዲሁም ጠቃሚ ያለመሆን ስሜት ይሰማዎታል…»
የስብዕና መዛባት (Personality Disorders)


በዓለም ላይ ከሚኖሩ አጠቃላይ ህዝቦች ውስጥ ከ 1-20% የሚያህሉት ለተለያዩ ዓይነት የስብዕና መዛባት ችግሮች ተጋላጭ ናቸው፡፡ የስብዕና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስንል ወደ አእምሯችን የሚመጣው መንገድ ላይ ጨርቁን ጥሎ የሚሄደው፤ አማኑኤል ሆስፒታል የተኛችው ፤ ወይም ደግሞ ሰውን በአረመኔያዊ ሁኔታ ገድሎ እስርቤት ውስጥ በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቀው ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን  በዓለም ላይ በጣም በጥቂቱ ከ 25 ሰው አንዱ  ለተለያየ ዓይነት የስብዕና መዛባት ተጋላጭ ሲሆን፤ እነዚህ ሰዎች የቤተሰባችን አካል፤ ጎረቤት፤ ወይም ደግሞ የስራ ባልደረቦቻችን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ለስብዕና መዛባት ዋና መንስኤዎች የትወልድ ሃረግ (Genettics)፤ በልጅነት ዕድሜ የሚደርስ አካላዊ፤ ወሲባዊና ስነልቦናዊ ጥቃት፤ እንዲሁም ያደግንበት ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው፡፡ የስብዕና መዛባት ያለባቸው ሰዎች በአጠቃላይ በሶስት ቡድን (Clusters) ይከፈላሉ፡፡

ቡድን ሀ የስብዕና መዛባቶች (Cluster A Personality Disorders)

1. በምክንያት ያልተደገፈ ጥርጥር እና ከመጠን ያለፈ ሰዎችን ያለማመን ችግር (Paranoid Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ የትዳር ጓደኛቸው ከሌላ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው ብለው ሊያምኑ ይችላሉ፡ ከአስር አመት በፊት ወልደው ያሳደጉትን ልጅ የእኔ አይደለም ብለው ሊክዱ ይችላሉ፤ ዙሪያ ገባውን ሁሉ በጥርጣሬ የሚመለከቱ እና ሰዎቸ በመሰረቱ አደገኞች ናቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው፤ ለእነዚህ ሰዎች በቅንነት የወረወራችሁት ሃሳብ እንደ ጥቃት ሊቆጠር ይችላል

2. ከውጪዉ ዓለም ወይም ከእውነታው ሸሽተው  በራሳቸው አለም (ሃሳብ) የሚኖሩ (Schizoid Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች በራሳቸው ዓለም አብዝተው የሚመሰጡ፤ በእውኑ ዓለም ተጨባጭ ያልሆኑ ሃሳቦችን የሚያልሙ ሲሆን ለማኅበራዊ ደንቦች ግድ የሌላቸውና ከሰዎች ጋር ስሜታዊ ትስስር ለመፍጠር ፍላጎት የሌላቸው ናቸው

3. በአነጋጋራቸው፤ በባህሪያቸው፤ በአስተሳሰባቸው ላይ መዛባት ያለባቸው ሰዎች (Schizotypal Disorder):- 
እነዚህ ሰዎች ከሌሎቹ የስብዕና መዛባት ዓይነቶች በተለየ መልኩ በቀላሉ ችግር ውስጥ እንደሆኑ በአነጋገራቸው፤ ከተለመደው ወጣ ባለው ባህሪያቸው እንለያቸዋለን፡፡ ምንአልባትም በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ እንደ “እብድ” የምንቆጥራቸው አብዛኞቹ የእዚህ ስብዕና መዛባት ተጋላጮች ናቸው

ቡድን ለ የስብዕና መዛባቶች (Cluster B Personality Disorders)

1. ለማኅበረሰብ ህግና ደንቦች ግድ የሌላቸው (Antisocial Personality Dsiroder)፡-
ሌሎች ሰዎች ላይ ሆን ብለው አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት የሚያደርሱ፤ ርህራሄ የሌላቸው እና የሰዎችን ስሜት የማይረዱ፤ ባጠፉት ጥፋት መጸጸት የማይሰማቸው እና ከህይወት ተሞክሮ ትምህርት ወስደው ራሳቸውን ለማሻሻል የማይሞክሩ ናቸው:: ብዙ ጊዜ ጥቃት አድርሰው፤ወንጀል ፈጽመው ወደ ህግ ሲቀርቡ ብናያቸውም አብዛኞቹ ግን በረቀቀ መንገድ የሚንቀሳቀሱ፤ ከህግ ከለላ በቀላሉ የሚያመልጡና በዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ሰዎች ናቸው

2. ስለራሳቸው ማንነት ማወቅ የተቸገሩ (Boarderline Personality Disorder):-
እነዚህ ሰዎች  አበዝተው ባዶነት፤ የስሜት አለመረጋጋትና ፍርሃት የሚሰማቸው ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ቁጡዎች፤ ራሳቸውን ለመጉዳትና ለማጥፋት የሚሞክሩ ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የስብዕና መዛባት በልጅነታቸው የጾታ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ላይ የተለመደ ነው፡፡

3. በሰውነታቸው ያላቸውን መልካም ዋጋ የማይረዱ (Histrionic Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች የሌሎችን ትኩረት አብዝተው የሚሹ እና በዕቅዳቸው ሁሉ የሌሎችን አበረታችነት የሚጠብቁ ናቸው:: ሌላ ሰው ቀጥሉ ካላላቸው ምንም ዓይነት ውሳኔ ለመወሰን ይቸገራሉ፡፡ከመጠን በላይ ለውበታቸውና ለአለባበሳቸውም የሚጨነቁም ናቸው

4. ክፉ ሰዎች (Narcissistic Personality Disorder)፡-
ሲበዛ ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎች፤ በነገሮች ሁሉ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሰሉና በጣም ተቆጣጣሪዎች ናቸው፡፡ የዚህ ስብዕና መዛባት ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሌሎችን የሚቀርቡት በሆነ መንገድ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ሲያስቡ ብቻ ነው፡፡ እነሱ የፈለጉት ነገር ካለሆነ ለበቀል የሚጋበዙ ፤ዓለም በእነሱ ዛቢያ ብቻ የምትሽከረከር የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው፡፡

ቡድን ሐ የስብዕና መዛባቶች (Cluster C Personality Disorders)

1. ከማኅበራዊ ህይወት ራሳቸውን የሚያገሉ (Avoidant Personality Disorder)፡-
ሲበዛ የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው በዚህም ምክንያት ሰዎች ስለነሱ መጥፎውን እንደሚያወሩ የሚያስቡ፤ ሰዎች የወቀሷቸውና ያገለሏቸው የሚመስላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ራሳቸውን ከማኅበራዊ ህይወት ያገላሉ፡፡ ሰርግ እና ሃዘን ቤት መሄድ፤ ከጓደኞች ጋር ሻይ ቡና ማለት ያስጨንቃቸዋል፡፡

2. በሌሎች ሰዎች ላይ ሲበዛ ጥገኛ የሆኑ ሰዎች (Dependent personality Disorder)፡- በራሳቸው መተማመን የሌላቸው፤ በዕለት ተዕለት ኑሯቸው ውስጥ የሌሎችን ውሳኔ የሚጠብቁ፡ ሲበዛ ሽቁጥቁጥና ለሰው አጎብዳጅ የሆኑ ሰዎች ናቸው

3. ስህተት አልባ ህይወት ፈላጊዎች (Anankastic Personality Disorder)፡- ለህጎች ፤ ስርአቶች ፤ ዕቅዶች ሲበዛ አብዝተው የሚጨነቁ፡፡ ያቀዱት ጉዳይ ካልተፈጸመ ዕረፍት የሚነሳቸው፤የሚለብሱት ልብስ መዛነፍ ወይም አለመተኮስ ቀኑን ሙሉ የሚረብሻቸው ሰዎች ናቸው፡፡

(በሰብለወንጌል አይናለም)
@Zepsychologist


ከእነዚ በአንዱ አልያም የተለየ የአዕምሮ ሕመም አለብኝ ብለው ካሰቡ ( በዚህ የሚጠቃ የቅርብ ሰው ካለ) የስነልቡና አማካሪዎች ጋር እንዲሄዱ እመክራለሁ ፡፡ ከታች አድራሻ አስቀምጫለሁ ፡፡ በመደወል ስለህክምናውና ክፍያ መረጃ ማግኘት ይቻላል ፡፡
ሃዘንን መቋቋም የሚያስችሉ ዘዴዎች

በህወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው እና መልካም አቀጣጫን በመጠቆም ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱልን ሰዎች አሉ ይኖራሉም፡፡ የቤተሰብ አባል ፤ የልብ ጓደኛ ወይም አርአያ የሆኑን በልባችን አግዝፈን የምናያቸው ምግባራቸው ያስከበራቸው ሰዎችን ለምሳሌ ያህል መጥቀስ ይቻላል፡፡ በመወለድ ወደ ህይወት መምጣት እንዳለ ሁሉ የማይቀረው ህልፈተ ህይወት አለና በሞት ሲለዩን የሚሰማንን የቅስም መሰበር፤ የቁጭት፤ የጥፋተኝነት ፤ የጸጸት፤ የንዴት፤ የናፍቆት አልፎ ተርፎም የመንኮታኮትና የውድቀት ስሜት በግርድፉ ለማጠቃለል ያህል የሃዘን ስሜት ብለን እንጠራዋለን፡፡ የሰው ልጅ እንደ ጸባዩ ይህንን የሃዘን ስሜት የሚያመጡበት ገጠመኞችና ሁኔታዎች የተለያዩ ሲሆኑ የስሜቱም ጥልቀት እና ቆይታ ጊዜ የዚያኑ ያህል ይለያያል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሃዘን ስሜትን መቋቋም የምንችልባቸውን ጥቂት ዘዴዎችን እንመለከታለን፡፡

1. የሃዘን ስሜትን አለመካድ

የገባንበትን የሃዘን ስሜት መወጣት እንዳንችል ወደኋላ ወጥረው ከሚያሰቃዩን ስሜቶች ውስጥ አንዱ የሃዘን ስሜትን መካድ ነው፡፡ የገባንበትን መጥፎ ስሜት መካድ ከስሜቶቹ ጋር ያለንን ቆይታ ያረዝመው ይሆናል እንጂ እንድንላቀቃቸው አያግደንም፡፡ ስለዚህም ምንም እንኳን ከማንም እና ከምንም በላይ እናፈቅራቸው ነበረ ቢሆንም ላናገኛቸውና ላይመለሱ እንደተለዩን አምነን ባንወደውም የሚደርስብን ሃዘን መቀበል ከስሜቱ መላቀቅ እንድንችል ይረዳናል፡፡

2. ጠንካራ ነኝ እቋቋመዋለው ብሎ እራስን አለማታለል

አብዛኛውን ጊዜ አሉታዊ የሆኑ ስሜቶችን በመቋቋም ለማለፍ “ዋጥ” አድርገን ለማለፍ ስንጣጣር የባሰ እራሳችን ላይ ከሚደርስብን የመንፈስ ስብራት አልፎ የእንቅልፍ ማጣት፤ የምግብ ፍላጎት መዛባት፤ የድብታ ችግር፤ እንዲሁም ሌሎችንም ሊያመጣብን ይችላል፡፡ ስለዚህም ተመራጭ የሚሆነው የሚሰማንን ስሜት ለመቋቋምና ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ ስሜቱን እንደ አመጣጡ መቀበል ስላጣነው የህይወት አጋር ስንል እራሳችንን ካለንበት የስሜት ዝቅታ ማንሳት እንድንችል ለእራሳችን ዕድል ልንሰጠው ይገባል፡፡

3. የሃዘን ስሜትን ገልጾ ማውጣት ስለስሜቱ ከሌሎች ጋር መነጋገር

ብዙዎች የወዳጃቸውን የማጣት ስሜት አውጥተው ከመናገር ይልቅ በውስጥ አምቆ መብሰልሰልን እንደ አማራጭ አድርገው ይይዛሉ፡፡ ይህ ግን ስሜቱን ያለረዳት ብቻችንን በጫንቃችን ተሸክመን ለመጓዝ እንደ መሞከር ነውና የመድከምና የመሰላቸት ስሜት ይፈጥርብናል፡፡ የሆዴን በሆዴ ለሃዘን ስሜት አይሰራምና ለትዳር አጋራችን፤ ለቤተሰባችን፤ ለልብ ጓደኞቻችን ወይም ደግሞ ለስነ-ልቦና ባለሞያዎች የተሰማንን ስሜት በመናገር፤ በመጻፍ፤ ስዕል በመሳል ወይም በማንኛውም ችሎታችን በሚፈቅደው መንገድ መተንፈስ የሃዘንን ስሜት ይቀንሳልና ስሜታችንን ገልጾ ማጋራት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

4. ታጋሽ መሆን

የሃዘን ስሜቱ ከባድነት የተነሳ ብዙውን ጊዜ በሞት የተለየንን ግለሰብ የሚያስታውሱንን ነገሮች ለማራቅ እንሞክራለን፡፡ ስሜቱን ያራቅነው እየመሰለን ይጠቀሙበት የነበሩ ንብረቶችን ማራቅ፤ መኖርያ ቤታችንን መቀየር፤ የስራ ቦታችንን መቀየር፤ እንደው በአጠቃላይ እንደ ፎቶ ያሉ ትዝታ የሚቀሰቅሱ ንብረቶችን ለማስወገድ አለመቸኮል ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ የሃዘን ስሜቱም ካለፈ በኋላ የእነዚህ ንብረቶች መኖር ያጣናቸውን ግለሰቦች በመልካምነት እንድናስባቸውና እንዳንረሳቸው፤ ለእኛ የነበራቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንድናስታውስ ይረዱናል፡፡

5. የጤናችንን ጉዳይ ቸል አለማለት

ሰዎች በሃዘን ጊዜ እራሳቸውን ይጥላሉ፡፡ ለእራሳቸው ያላቸው ክብር፤ እንክብካቤ ከመቀነስም ባለፈ እራሳቸውን በረሃብ ይቀጣሉ፡፡ የምናደርጋቸው ማናቸውም ድርጊቶች ያጣነውን ግለሰብ አይመልሱምና የጤናችንን ጉዳይ ቸል ልንለው አይገባም፡፡ የምናስበውን ያህል የምግብ ፍላጎት ባይኖረን እንኳን ምግብ መመገብ ይገባናል፡፡ ያጣናቸው ሰዎች በህይወት ቢቆዩ እንዲህ እንድንጎሳቆል እንደማይፈልጉ ለእራሳችን ደጋግመን ልንነግረው ይገባል፡፡

6. የሃዘን ስሜትም ያልፋል

በሃዘን ስሜት ውስጥ ስንሆን አብዛኛዎቻችን ስሜቱ የማይላቀቅና ሽሮ የማያልፍ አድርገን እንስለዋለን፤ ይመስለናልም፡፡ የፈጀውን ያህል ቢፈጅ የሃዘን ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን እየቀነሰ የሚመጣ ነው፡፡ መዘንጋት የሌለብን መኖር ማለት አሉታዊ ስሜቶችን ሳይሰሙን ተንደላቀን የምንፈላሰስበት ሳይሆን ተጋፍጠንና ተቋቁመን የምናልፍበት ነው፡፡ በህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ማናቸውም ነገሮች የሚያልፉ መሆናቸውንና ህይወት የሚቀጥል መሆኑን ልናስተው ይገባል፡፡

በአጠቃላይ ጊዜ የማይሽረው ነገር የለምና ለማንነታችን ሃቀኛ በመሆን ካጋጠመን የተጠበቀ ይሁን ድንገተኛም የሃዘን ስሜት በመቋቋም ማንነታችንን ልንመልስ ይገባል፡፡

©(በዘመነ ቴዎድሮስ zepsychologist)
@Psychoet
አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ...እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰው አየ ... እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ እንኳን እንደዚህ ሰዉዬ አልሆንኩ አለ"።
:
ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ከዚያም የታመመው ሰውየ ሆስፒታል ሲደርስ የሞተን ሰው ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና አለ"።
:
ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም? ከሌለን ነገር እኮ ያለን በእጅጉ ይበልጣል ፡፡
:
* # ሕይወት * # ምንድን_ነው ?
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
* 1. መቃበር *
* 2. ሆስፒታል *
* 3. እስር ቤት *
:
በመቃብር ቦታ ሕይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትገነዘባለህ።
:
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ።
:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው።

ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ እንሁን። ስንት ቤተሰቦቻችን ፣ ጓደኞቻችን ዛሬ በሕይወት የሉም እኛ ግን በፈጣሪ ፈቃድ ጊዜያችንን እየጠበቅን በሕይወት መቆየት ችለናል ፡፡ ከሞትን በኀላ ደግሞ በዚህች አለም በሰወች ዘንድ የሚቀርልን ትዉስታ ስራችን ከተጨመረ ደግሞ ፎቶአችን ነዉ ፡፡ ስለዚህ ለሰዋች ደግሞ ሁል ጊዜ መልካም ነገር ሰሪ እንሁን ፡፡ በተጨማሪ ሁሌ አመስጋኝ እንሁን ሌላዉ ቢቀር ይህን ፅሁፍ በማንበባችን አምላክን እናመስግን ምክንያቱም ብዙ ሰዋች
1.ማንበብ ስለማይችሉ አያነቡትም
2.ይህን መልዕክት ስላልደረሳቸዉ አያነቡትም
ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን።
መልካም ምሽት

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
#Share if you really like it
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychology
@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_16
#ሶስት_የአዕምሮ_ደረጃዎች
/ንቃተ ህሊና ፣ ውስጠ ህሊና ፣ ንቁ ያልሆነ ህሊና/
www.tg-me.com/psychoet
(ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ እና በአቤል ታደሰ )

ታዋቂው የስነ-ልቦና ባለሙያ የሆነው ሲግመንድ ፍሮይድ: ባህሪ እና ስብዕና የሚመነጨው በሦስት የተለያዩ የግንዛቤ ደረጃዎች መካከል በሚፈጠር የስነ-ልቦና ኃይሎች(Psychic Forces) ልዩ መስተጋብር ነው ብሎ ያምናል ፡፡
ፍሮይድ እያንዳንዱ የአእምሮ ክፍሎች በባህሪ ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ያምናል ፡፡

የፍሮይድ ፅንሰ-ሀሳቦችን ለመረዳት በመጀመሪያ እያንዳንዱ የባህርይ ክፍል እንዴት እንደሚሠራ እና ለሰው ልጅ ባህሪ እድገት አስተዋፅኦ የሚያደርጉበትን መንገድ ማወቅ አስፈላጊ ነው ፡፡

#የፍሩድ ሦስት የአእምሮ ደረጃዎች :-

#1 The Preconscious Mind(ውስጠ ህሊና)
#2 The Conscious Mind (ንቃተ ህሊና)
#3 The Unconscious mind (ንቁ ያልሆነ ህሊና)

#1 The Preconscious (ውስጠ ህሊና)
ወደ አእምሮ ሊመጣ የሚችለውን ማንኛውንም ነገር ያካትታል ፡፡

#2 The Conscious Mind (ንቃተ ህሊና) በማንኛውም ጊዜ የምናውቃቸውን ሁሉንም ሀሳቦች ፣ ትውስታዎች ፣ ስሜቶች እና ምኞቶች ይይዛል። ይህ በአዕምሯችን ማሰብ እና ማውራት የምንችልበት የአዕምሯችን ሂደት ገጽታ ነው ፡፡ ሁልጊዜ የእኛ የንቃተ ህሊና አካል ያልሆነ ነገር ግን በቀላሉ ሊገኝ እና ወደ ግንዛቤ ሊመጣ የሚችል ማህደረ ትውስታችንን ያካትታል።

#3 The Unconscious Mind (ንቁ ያልሆነ ህሊና) ከስሜታችን ግንዛቤ ውጭ የሆኑ የስሜት ፣ የሀሳብ ፣ የምኞት እና ትውስታዎች ማጠራቀሚያ ነው ፡፡ እንደ ህመም ፣ ጭንቀት ወይም ግጭት ያሉ ተቀባይነት የሌላቸውን ወይም ደስ የማይሉ ይዘት ያላቸውን ትውስታዎችን ይይዛል።

The Unconscious Mind (ንቁ ያልሆነ ህሊና) የተደበቁ ትውስታዎችን የተደቆሱ ስሜቶችን ፣ ልምዶችን ፣ ሀሳቦችን ፣ ምኞቶችን እና ግብረመልሶችን ያካትት ይችላል ፡፡

እንደ ፍሮይድ ገለፃ ፣ ምንም እንኳን እነዚህን ውስጣዊ ተጽዕኖዎች የማናስተውል ቢሆንም በባህሪያችን እና በማንነታችን ላይ ተጽዕኖ ማድረጉን ይቀጥላል።


_____________________በሌላ ጊዜ ደግሞ እነዚህ ሦስት የአዕምሮ ደረጃዎች እንዴት ባህሪያችንን እንደሚገነቡ እንመለከታለን ፡፡ ለምሳሌ "የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም" የሚል ትልቅ አባባል ኢትዮጵያኖች አለን እና ይሄ "የአፍ ወለምታ" ከየትኛው ክፍል ይመነጫል ፣ ለምንና እንዴት ይመነጫል የሚለውን ጨምሬ አሳያችኅለሁ ፡፡ ሰው አምልጦኝ ተሳደብኩ ፣ ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ፣ ሰይጣኔን አታምጣው ፣ ደሜን አታፍላው የሚልበትን ምክንያት ከነዚህ ሦስት የአዕምሮ ደረጃዎች መስተጋብር አንፃር እናያለን ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
www.tg-me.com/wikihabesha
❖_____________________________❖
Source: verywellmind.com (web)

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook/Telegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!
እወዳችኅለሁ !
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
❖__________________________________❖
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።

6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።

7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።

8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።

9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።

10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
#በቅንነት ሼር አድርጉ

@psychoet
ነገሮች ሲደክሙህ ሲሰለቹህ ሲያቅቱህ
😣😣😣
ማቆምን ሳይሆን
ማረፍን ተማር !

@psychoet
ለጓደኞቻን #Share በማረግ እናበርታቸው !
መልካም ቀን!
😂😂😂😂🙆‍♀🙆‍♂ አንብቦ አለመሳቅና #Share አለማረግ አይቻልም!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የ 3ኛ አመት የሳይኮሎጂ ተመራቂ ጓደኛሞች ነገ Final ፈተና እያላቸዉ ማታ ሲጠጡና ሲጨፍሩ አመሹ ፡፡ እናም ወደ ተከራዩበት ቤት ሲመለሱ ለማጥናት ጊዜ ስላልነበራቸዉ ወዲያዉ ተኝተዉ ጠዋት በመነሳት ወደ መፈተኛ ክፍሉ ይሯሯጣሉ ፡፡

በዚህ ጊዜ ሳያጠና መፈተኑ የጨነቀዉ አንድ ተማሪ አሪፍ ሀሳብ ያቀርባል ፡፡ "ለምን ግን ሳናጠና ከምንፈተን ፥ አስተማሪያችንን ትናንት ማታ ወደ ግቢ ላይብረሪ ስንመጣ የምንመጣበት ታክሲ ጎማ ፈንድቶ እሱ እስኪስተካከል ጠበቅን ከዛም ደግሞ በመንገድ ላይ አንዱ ጓደኛችን ታሞ እሱን ሆስፒታል ወሰድን ግቢ እንደገባንም ስለደከመን ሳናጠና አደርን ፣ አሁንም በጣም ሳይኮሎጂካል ጉዳትና (ውጥረት ፣ ጭንቀት... የመሳሰሉት) ስለደረሱብን በዚህ ሁኔታ መፈተን ይከብደናል አንለዉም " የሚል ሃሳብ አቀረበ ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁለቱም በሀሳቡ በደስታ ተስማምተዉ ለአስተማሪዉ ሊነግሩት ወደ ቢሮዉ በፍጥነት አመሩ ፡፡ የሳይኮሎጂዉ ፕሮፌሰርም ባጋጠማቸዉ ነገር እጅግ በጣም አዝኖ ካረጋጋቸው በኅላ ለነሱ ብቻ ሌላ ፈተና አዉጥቶ በነጋታዉ ሊፈትናቸዉ ተስማሙ ፡፡

3ቱ ጓደኞችም በብልጠታቸዉ እጅግ በጣም ተደስተዉ "በቃ ሳይኮሎጂ መማር ጥቅሙ ይሄ ነው ፤ አስተማሪያችንን ሰራንለት" እያሉ ቀጥታ ወደ ኬኔዴ ላይብረሪ ገብተዉ ማጥናት ጀመሩ ፡፡ በዛን ቀን ደግሞም ማታዉን ጨምረዉ ወጥረዉ ሲያጠኑ ካመሹ በኅላ ፣ በለቱ ከተፈተኑ የክፍል ጓደኞቻቸው በለቱ ስለተፈተኑት ፈተና መረጃ ወስደው በነጋታዉ ለፈተና ቀረቡ ፡፡ አስተማሪዉም ሌላ አንድ ፈታኝ አስተማሪ ጨምሮ 3ቱን ተመራቂ ተማሪዎች ሰፊ ክፍል ካስገባቸዉ በኀላ አራርቆ አስቀምጦ የፈተና ወረቀ ሰጣቸዉ ፡፡

3ቱም ጎደኞች ያለፈዉ ቀን እጅግ በጣም አጥንተዉ ስለነበር በተጨማሪ ትናንት ከተፈተኑት ጓደኞቻቸዉ ስለ ፈተዉ ብዙ መረጃ ይዘዉ ገብተዉ ስለነበር ፈተናዉን እንደሚሰቅሉት ያላንዳች ጥርጣሬና በሙሉ መተማመን ነበር የገቡት ፡፡

የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩም የፈተና ወረቀቱን ሰጣቸዉና "በሉ ስሩ ተማሪዋቼ " አለ ፡፡ 3ቱም ተማሪዋች ፈተናቸዉን ገልብጠዉ ስማቸዉንና ID ቁጥራቸዉን ከፃፉ በኀላ ጥያቄዉን ማንበብ ጀመሩ ፡፡ ጥያቄዋቹ እንዲህ የሚሉ ነበሩ ?
1. የፈነዳዉ የታክሲ ጎማ የትኛዉ ነበር ?
ሀ.የፊት ቀኝ ለ.የፊት ግራ
ሐ. የኀላ ቀኝ መ.የኀላ ግራ
2.ጎማዉ የፈነዳዉ የት አካባቢና ስንት ሰአት ነዉ?___________________
3. ጎማዉ የተቀየረዉ የት ጎሚስታ ቤት ነዉ?
____________
4.የታመመዉን ጓደኛችሁን የት ሆስፒታል ወሰዳችሁት?
___________

መልካም ፈተና !
ይህን ፈተና ሁላችሁም ከደፈናችሁ ከሰአት Final exam ለመፈተን ብቁ ናችሁ !
😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂

#Share #Share #Share
Final ፈተና ላይ ላላችሁ መልካም ፈተና!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
አስተማሪ መልዕክቶችን ለማግኘት ፔጁን #Like ያርጉ !
#ጭንቀትን_መቀነሻ_ቴክኒኮች

ይህም በሥልጠናና በባለሙያ የካውንሰሊንግ አገልግሎት ሊገኝ ይችላል፡፡

ሁለት ቴክኒኮችን ብቻ እንመልከት (በርካታ ቴክኒኮች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል)፡-

1⃣ #ABCDE_ቴክኒክ :

ይህ ቴክኒክ አልበርት ኤሊስ (Albert Ellis) በተባሉ የስነልቦና ባለሙያ የተገኘ ዘዴ ነው፡፡

አልበርት ኤሊስ ሰዎች ወደ ጭንቀት የሚገቡት አግባብ ያልሆነ አስተሳሰቦችና እምነቶች (Irrational beliefs and thoughts) ሲጠናወቷቸው ነው ብለው ያምናል።

ለምሳሌ:-

👉ሰው ሁሉ ይጠላኛል፣
👉ሰው ሁሉ ይወደኛል፣
👉ከሰው ሁሉ ተቀባይነትን ማግኘት አለብኝ፤
👉በምሰራው ስራ ሁሉ መሳሳት የለብኝም...ወዘተ የሚሉ እምነቶችና አስተሳሰቦች ለጭንቀት እንደሚዳርጉ ያሰምሩበታል።

እኚህ ሰው እንደሚሉት፥

✔️አሉታዊ ነገሮችን አጋኖ ማየት (Awfulising)

✔️ጥቁርና ነጭ እሳቤ (Black and White thinking)

👉ይህ እንግዲህ አንድን ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ ብሎ መመደብና በውስጡ ሊኖር የሚችለውን የተወሰነውን ጥሩ ነገር አለማየት ነው።

✔️ጠቅላይ እሳቤ(Over generalizing)

👉ሁልጊዜ፣ ሁሉም ሰው፣ በፍፁም.....ወዘተ የሚሉ ቃላትንና ሃሳቦችን መጠቀም፤
(ሁሉም የሚል አባዜ አለባቸው)

✔️Personalizing

የማይመለከተንን ነገር ከራሳችን ጋር አቆራኝቶ ማየት፤

✔️Filtering

በሁኔታዎች ውስጥ አሉታዊን ነገር ብቻ መርጦ ማየት፤

✔️Mind reading

ይህንን አስቦ ነው ብሎ ያለምንም ማስረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ፤

✔️Blaming

👉ሰዎችን መተቸትና መውቀስ

✔️Labeling

👉ለራስ ስያሜ መስጠት

ለምሳሌ: ደካማ ነኝ፤ዋጋ ቢስ ነኝ...ወዘተ ማለት አግባብ ላልሆኑ አስተሳሰቦች ምክኒያት ናቸው ይሉናል፡፡

ቴክኒኩን ተንትነን ለማየት እንሞክር

#Antecedent (Activating event, Stimulus)፡

ይህ ማለት ጭንቀትን የሚቀሰቅሰው ሁኔታ ወይም ነገር ነው (ተንኳሽ እንበለው)፡፡
" ይህ ተንኳሽ የኛን ምላሽ (Response) ይጠይቃል።

ለምሳሌ:- ከስንት አንድ ቀን ቀጠሮ ብናረፍድ ጭንቀት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት ጭንቀትን የሚፈጥርብን ጉዳይ ማርፈዳችን ነው ማለት ነው፡፡

#Belief_our_cognition_about_the_situation ፡-

ይህ እንግዲህ ስለ ተንኳሹ ያለን ሃሳብና እምነት ነው፡፡

ለምሳሌ ማርፈዴ ያለኝን ተቀባይነት ያሳጣዋል፣ በምንም አይነት ምክኒያት ቢሆን ማርፈድ አሳማኝ አይደለም...ወዘተ የሚል እምነት ማለት ነው፡፡

#Consequences-

the way that we feel and behave፡

ይህ ውጤት ነው - ጭንቀታችን፡፡ ይህ ምን ባህሪ ይፈጥራል? ቶሎ ለመድረስ አላግባብ ጣልቃ እየገባን መኪናችንን መንዳትን፣ በእጃችንም በአንደበታችንም የተንቀረፈፈ የመሰለንን ሾፌር መስደብ፣ መቆጣት፤ ከአስፋልት ወጥቶ በእግረኛ መንገድ መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ አልበረት ኤሊስ ይሞግታሉ “ያስጨነቀን ማርፈዳችን ነው ወይስ ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው?”

አሳቸው እንደሚሉት፤ ውጤቱን የፈጠረው ማርፈዳችን (stimulus) ሳይሆን ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው ባይ ናቸው፡፡

#Dispute

:- is the process of challenging the way we think about situations:

ይኸኛው አስተሳሰባችንን የምንሞግትበት ዘዴ ነው። እሳቸው አግባብነት የሌለውን አስተሳሰብና እምነት መሞገት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

ለምሳሌ ከላይ የጠቀስነውን ማርፈድ ብንወስድ እምነታችንን ስንሞግተው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
“ብዙ ጊዜ በሰዓቱ የምገኝና ቀጠሮ አክባሪ የሆንኩ ሰው ነኝ፡፡

አንድ ዛሬን ባረፍድ ተቀባይነቴን አያሳጣም”፣ “ለማርፈዴ ምክኒያት የሆነኝ የትራፊክ መጨናነቅና ያልጠበቅሁት የመንገዶች መዘጋጋት ነው፡፡ ስለዚህ በቂ ምክኒያት ሊሆን ይችላል፡፡

” እነዚህን ምክኒያቶች በማሰብ ነባሩን ሃሳብ መሞገት እንደሚገባ ይጠቁማሉ፤ አልበርት ኤሊስ፡፡

#Effect :

ይሄ አዲሱ ውጤት ነው።
አስተሳሰባችንን ከሞገትነውና በአዲስ አስተሳሰብ ከተካነው በኋላ የሚፈጠር ባህሪ ነው፡፡ የላይኛውን ምሳሌ ብንከተል ተረጋግቶ መንዳት፤ ተራ መጠበቅ፤ በተፈቀደው አስፋልት መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

👉ማስተዋል ያለብን ሃሳብ ስሜታችን እና ባህሪያችን ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል፡፡

👉ማወቅና አስተሳሰብን መለወጥ ደሞ አስፈላጊ ነው፡፡

#share

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
ፈተናው በዝቶብሽ
ትግሉ በርትቶብሽ
ውጣ ውረዱ ሰልችቶሽ
ትዕግስትሽን ተፈታትኖ
ሊሆን ይችላል

መርሳት የሌለብሽ ነገር ግን
#ብርቱና_ጠንካራ_ሴት
እየሆንሽ መምጣትሽን ነው !

@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች አሉት

ተፈጥሮ በኡደት (Process) የተመላች ናት፡፡ ዘመናትን በጊዜ ቀመር አስልታ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላኛው ታሻግራለች፡፡ የኡደት ስሌትዋ ከትልቅ ወደ ትንሽ ሳይሆን ከትናንሽ ወደ ትላልቅ የሚያመራ ነው፡፡

የሰው ልጅ የዕድገት ለውጥ ዓላማ በተፈጥሮ የወረሰውን እምቅ ኃይል ከከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው፡፡ ኤልሳቤጥ ሃርሎክ የተባለች የሳይኮሎጂ ምሁር እንደገለጸችው ሰዎች በአእምሮ ፤ በአካል ከሌሎች የተሻሉ ሆነው ለመገኘት የሚያደርጉት ጥረት ወደ ዕድገት ለውጥ ግብ ለመድረስ የሚደርጉት ጥረት ስለሆነ እነዚህን ጥረቶቻቸውን እውን ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሉ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ሰዎች እራሳቸውን ለማሻሻል እምቅ አቅምና ችሎታ ካላቸው ከወዴት ነው የሚጀሚሩት የሚለው ነው፡፡ ብዙዎቻችን በስራችንና በህይወታችን የምንፈልገውንና የምንሻውን ያህል ውጤታማ መሆን ያልቻልነው ዕቅዶቻችንንና ስኬቶቻችንን ከታች ከትንንሽ ነገሮች ስለማንጀምራቸው ነው፡፡ ቀድሞ የሚታየን ትልቁ ስዕል እንጂ ወደ ትልቁ የስኬት ጎዳና ለመድረስ ከትንሽ ነገር መጀመር እንዳለብን አንገነዘብም፡፡ ከዚህ በታች ከትንንሽ ነገር ተነስተን ወደ ትልቁ ስኬት ለመጓዝ የሚረዱንን ነጥቦች እንመለከታለን፡፡

1.ትምህርት

የተሻለ የትምህርት ደረጃ ያለቻው ሰዎች ስራዎቻቸውን የሚያከናውኑት ዕውቀትንና ዕቅድን መሰረት አድርገው ነው፡፡ በስራዎቻቸው ላይ ወሳኝ ጉዳዮችን በደንብ ስለሚያውቁ ከሌላው ሰው በተሻለ ሃሳብና መረጃ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ ዕውቀቶቻቸውን በመመንዘርና ማኅበራሰባቸውን በማገልገል የተሻለና የተሳካ ህይወት (ገቢንም ጨምሮ) መኖር ይችላሉ፡፡ ዕውቀት በጨመረ ቁጥር የሰው አስተሳሰብ አድማሱ ስለሚሰፋ ምን ሰርቶ ምን ማግኘትና የት እንደሚደርስ አቅጣጫን ይጠቁማል፡፡ ትምህርት ስንል በአንድ የትምህርት መስክ የምናገኛውን የሰርተፍኬት ብዛት ብቻ ሳይሆን በህይወት ልምድና ተሞክሮ ያገኘነውን ዕውቀት ትርጉም ባለው ስራ ላይ ማዋልና በትንሽ በትንሹ በመደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ ትምህርት ታግዘን ህይወትን ለማሸነፍ የምንሄድበትን የህይወት ጉዞን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

2. ክህሎት

በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን ክህሎት የምናስመዘግበውን ውጤት ብዛትና ጥራት ይወስናል፡፡ የምንሰራውን ስራ በደንብ ካወቅነው በስራችን ቅልጥፍና ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ በብቃት መሸጋገር እንችላለን፡፡ ከማናውቀው ነገር አንድ ብለን ከመጀመር የምናውቀውን ነገር አሻሽሎ በመስራትና ክህሎትን በማዳበር የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡
3. ግንኑነትን ማስፋት
በምንሰራው ስራ ላይ ብዙ ሰዎችን ለማወቅ ከጣርን ግንኙነታችንን በማጠናከር አማራጮችን ማስፋት እንችላለን፡፡ ስለዚህ የግንኙነት አድማስን ለማስፋት ዘውትር ማኅበራዊ ገመዶቻችንን በረጅሙ መዘርጋት አለብን፡፡

4. ጥሩ የስራ ልምድ

ጥሩ የስራ ልምድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስራዎችን እንድንሰራ ይረዳናል፡፡ ይህን ለማድረግ ስራዎቻችንን በዕቅድ መስራት አለብን፡፡ ጥሩ የስራ ልምድ አንድን ነገር ከማከናወናችን በፊት አስቀድመን እንድናስብበት ስለሚያስችለን ከስራው በኋላ የሚከሰቱትን ማንኛውንም አወንታዊና አሉታዊ ውጤቶችን አስቀድሞ መገመት ስለሚያስችል ኪሳራን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

6. አወንታዊ አመለካከት

የምንሰራው ስራ እኛነታችንን ስለሚገልጸው በስራችን ላይ አወንታዊ አመለካከት ፤ በእራስ መተማመን ፡ ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር ጥሩ መስተጋብር ካለን ሁሌም መልካም ነገር እንድናስብ ስለሚረዳን ወደ ምንፈልግበት ደረጃ እንድንደርስ አወንታዊ አመለካከት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

7. ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ይኑረን

ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ወይም ምልከታ መያዝ የምንፈልገውንና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረን ይረዳናል፡፡ ሰዎች በውጫዊ ገጽታችን ሊገምቱንና ሊፈርጁን ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውጫዊ ምልከታ የእኛንም ሆነ የሌላውን ስለማይገልጽ ስለእራሳችንም ሆነ ስለሌሎች ሰዎች ጥሩና የተቃና አመለካከት ሊኖረን ይገባል፡፡

8. ፈጠራ

ፈጠራ አንድን ነገር ዘውትር በተሻለ ፍጥነት፤ ቅልጥፍና ፤ በቀላል አኳሃን እንድንተገብረው ይረዳናል፡፡ ፈጠራ አዲስ ነገር ፈጥሮ ወይም ሰርቶ ማሳየት ብቻ ሳይሆን ነገሮችን ከዚህ ቀደም ከምናያቸው ዕይታና ግንዛቤ በአዲስ መልኩና በሌላ አቅጣጫ ማየትንም የሚያካትት ነው፡፡

9. ማንነት

እራስን መግራትና ግልጽነት ብዙ የስኬት በሮችን እንድንከፍት ይረዳናል፡፡ መተማመን የግንኙነት ሁሉ መሰረት ነው፡፡ ሰዎች የሚያውቁን በድርጊታችንና በቃላችን የምንታመን ከሆነ ነገሮችን በፍጥነት በቀላልና በታማኝነት በእኛ በኩል እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡ ይህም ብርታትና በራስ መተማመንን ስለሚፈጥርልን ወደምንፈልገው ደረጃ ለመድረስ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡
ዕቅድህ 15ኪሎ ክብደት መቀነስ ከሆነ በቀላሉ እንቅስቃሴ ማድረግና አመጋገብህን በማስተካከል ከትንሹ መጀመር ትችላለህ፡፡ ከዚያ ወደ ምትፈልገው ደረጃ ስትደርስ እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች እንዳሉት ትገነዘባለህ፡፡ ሻሎም

አንቶኒዮ ሙላቱ
©Zepsychologist
@psychoet
ነገን አናውቅም!

ነገን በማወቅ ህይወትን የሚመራት ሰው ማን ነው?? ማንም፡፡ ነገን በተስፋ እንጂ በሙሉ ልብ ይሄ ይሆናል ያኛው ደግሞ አይሆንም በማለት በዕርግጠኝነት የሚያውቅ ማንም ፍጡር የሰው ልጅ የለም፡፡ ምክንያቱም ዓለም እርግጠኛ ባለመሆን የተሞላች ናት እኛ ሰዎች ደግሞ የነገን የማወቅ ስልጣን እና ክህሎት የሌለን ፍጡራን ነን ፡፡ እስኪ ከዚህ በፊት ይሆናል… ይሳካል ….ይፈጸማል ብላችሁ ፍፁም እርግጠኛ የሆናችሁበትን እና ያልተሳካበትን ሁኔታ …….አልያም ከዚህ ሰው ጋር ብዙ እቆያለሁ ወይም ብዙ እሰራለሁ ብላችሁ ያልሆነበትን ሁኔታ አስቡ እስኪ……. አሁን ደግሞ ይህ የፈጠረባችሁን አሉታዊ ስነ-ልቡናዊ እና አካላዊ ጉዳቶች ለአፍታ አስቧቸው፡፡ የተረሳ ዶሴ አስከፍቼ ትካዜን ጫርኩኝ እንዴ?? እንግዲያውስ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ምናልባትም እስከ አሁን ድረስ ከእነዚህ ጉዳቶች ጋር እየታገላችሁ የምትኖሩ ይሆናል፡፡ መቼም ህይወት በአቀበት… በቁልቁለት እና ለጥ ባለ ለምለም መስክ የተሞላች ናት፡፡ ባንዱ ሲሞላልን… በሌላው ሲጎልብን ….ባንዱ ስናጣ በሌላው ስናገኝ ….ባንዱ ስንደሰት በሌላው ስናዝን እንኖራለን ፡፡ ባለፈው ስለ ይቅርታ በለጠፍነው ጽሁፍ ላይ ህይወት የሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ሙሌት ናት ብለንም የለ!! ስለዚህ በቅድሚያ የሆነ ነገር ለመፈጸም ስንነሳ በአዕምሮአችን ይሳካል ብለን ማሰባችን መልካም እና ለመስራት ላሰብነው ስራ አነቃቂ ቢሆንም፤ ላይሳካ ይችላል የሚለውንም በመጠኑ ማየት ይኖርብናል። ለምን አላችሁኝ?? ምክንያቱም ጉዳታችን ከጥበቃችን እኩል ነውና ነው መልሴ። ታላቁ የጥበብ ሰው ዊሊያም ሼክስፒር ባንድ ወቅት ቅድመ ጥበቃ የጉዳት ምንጭ ነው (expectation is the root of heartache) ብሎን ነበር፡፡

አብዝተን የሻትነው እና ጫፍ ለማድረስ የቋመጥንለት ሳይሳካ ሲቀር በእራስ መተማመናችን ይሻክርብናል ፣ ለእራሳችን የሚኖረን ግምትና እውቀት አናሳ ይሆናል። አካላችን እና አእምሮአችን እንደ አለቃና ምንዝር በሆነ ግንኙነት ውስጥ ሰለሰለሚሰሩ አዕምሮአችን እነዚህን አሉታዊ ስሜቶች ሲያስተናግድ የአካላችንን አምራችነት በእጅጉ ያሳንሰዋል ። በተጨማሪም ለአዕምሮ መታወክ አንደ ምክያትነት cognitive ሳይኮሎጂስቶች ከሚጠቅሱዋቸው ነገሮችን አንዱ ሁኔታው ከመከሰቱ አስቀድሞ አብዝቶ አልያም አሳንሶ መጠበቅ እንደሆነ ምን ያህሎቻችን እንገነዘብ ይሆን?? ስለዚህ መፍትሄው ከላይ የጠቀስነው ነው። አመክኖአዊ እና ነባራዊ የሆነ ቅድመ ግምት ለነገሮች ሊኖረን ይገባል። ይህ ማለት ግን ቀድሞ አይሳካም ብሎ በማሰብ ነገሮችን አለመፈጸም ሳይሆን አሁን የጀመርኩት የሞከርኩት ነገር ባይሳካ ቀጣይ ዕቅዴ (plan B) ምንድንነው ብሎ ማሰብ ነው፡፡ አልያም ደግሞ ሙከራችን አልተሳካም ማለት ሰማይ ተደፋብን ፣ የዓለም ፍጻሜ ሆነ ማለት እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል፡፡ በመጨረሻም ሁልጊዜ ቅድመ ጥበቃችን እና ጉዳታችን እኩል እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል ፡፡ ምዕራባውያኖቹ እንደሚሉት (expectation=disappointment) ነውና ጎበዛዝት ….ስለነገ ስለማናውቅ ……ጠንቀቅ!! ብለን የዛሬን በዚሁ እንቋጨው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ….

በቁምላቸው ደርሶ ©Zepsychology
@psychoet
2024/10/01 11:41:10
Back to Top
HTML Embed Code: