Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_17
#ሰዎች_እንዴት_ይወዱናል?
በሰዎች መካከል ያለ መሳሳብ / Interpersonal Attraction /
(ናሁሰናይ ፀዳሉ እና )
www.tg-me.com/psychoet

ሰዎችን እንዴት እንወዳቸዋለን?
የማህበረሰብ ሳይኮሎጂስቶች ለምን ሰዎችን እንወዳለን ለምንስ እንወደዳለን ብለው ያወጡትን በጥናት የተደገፉ ነጥቦች እንይ እስኪ፡፡እዚህ ጋር ግን ማፍቀር እና መውደድ የተለያዩ እንደሆኑና መውደድ የማፍቀር መነሺያው እንደሆነ ልብ ማለት ይገባናል፡፡

ሌላን ሰው ለመውደድ ምክኒያት የሚሆኑን ጉዳዬች እነዚህ ናቸው ፡፡

1. Physical attractiveness (ሳቢ ተክለ-ሰውነት) ነው፡፡ ብዙዎቻችን ቆንጆ የሆነ ነገር ሁሉ መልካም እና ጥሩ ይመስለናል (beautiful=good) ፤ ስለዚህ ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች እንኳን እኩል ቢሆኑ መልከ መልካምና ያማረ ተክለ-ሰውነት ያላቸው ከሌላቸው ሰዎች ይበልጥ ተወዳጅነት ያገኛሉ (እዚህ ጋር ግን ውበት እንደ ተመልካቹ እና እንደ ሀገሩ ባህል ስለሚለያይ መለኪያችንም ይለያያል) ይሄ ነጥብ ግን ቀስ በቀስ አብረው ብዙ በሚቆዩ ሰዎች መካከል እየጠፋ ይሄዳል፡፡

2. Proximity (አካላዊ ቅርበት)
በአቅራቢያችን ከሚኖሩ ሰዎች ጋር መልካም የሆነ የጓደኝነት ስሜት እንፈጥራለን፡፡ ብዙ ጥናቶችም እንደሚያመላክቱትም በተመሳሳይ የመኖሪያ ስፍራ ከሚኖር ሰው ጋር የምንፈጥረው ወዳጃዊ ግንኙነት ወደ መውደድ እና መወደድ ይወስደናል ብለው ነው፡፡ (you became friendliest with those who lived geographically closest to you).

3. Mere exposure (አዘውትሮ የሚደረግ ግንኙነት
ወይም መስተጋብር )

ሲሆን በዚህም ከሰዎች ጋር የሚኖረን ተደጋጋሚ የሆነ ግንኙነት መልካም የሆኑ ስሜቶችን በመፍጠር ወደ መውደድ ይወስደናል፡፡ ይሄ ግን ሁልጊዜ የሚሰራ አይደለም ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያጋጥመን መጥፎ የሆነ ግንኙነት በተደጋጋመ ቁጥር ለዛ ሰው የምናዳብረው መውደድ ሳይሆን ጥሩ ያልሆነ መጥፎ ስሜት ነው፡፡

4. Similarity (ተመሳሳይነት)

ከእኛ ጋር ተመሳሳይነታቸው የሚበዛ ሰዎችን እንወዳለን ሆኖም ግን በዚህ ነጥብ ላይ የሚነሱ ሁለት ዓይነት ተቃራኒ ሀሳቦች አሉ የመጀመሪያው Birds of the same feather fly together በግርድፉ አማርኛ የሰው ልጅ እሱን የሚመስለውን ይፈልጋል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ opposite forces attract each other ሁለት ተቃራኒዎች ይፈላለጋሉ የሚሉ ናቸው፡፡የማህበረሰብ ሳይኮሎጂስቶች በዚህ ላይ ጥናት በማድረግ የትኛው ሀሳብ የተሻለ ትክክል ነው ወደሚል መደምደሚያ ደርሰዋል፡፡ በዚህም ሰዎች ከራሳቸው ጋር ተመሳሳይ ስነ ባህርይ፣ ስነ ልቡና፣ እሴቶችና የመሳሰሉት ያሏቸውን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ መነሻው ተመሳሳይ በሆነ ሚዛን እንመዘናለን ተብሎ ስለሚታሰብ እና የሚወዱንን እና የሚመስሉንን እንወዳለን (reciprocity of liking) የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡

5. Reciprocal Liking (መልሶ መውደድ)

ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚወዷቸውን የሚያደንቋቸውን መልሰው የመውደድ ሁኔታ አለ፡፡ በተጨማሪም ሰዎች እንደወደዱን ስናውቅ እኛሞ የበለጠ እንዲወዱን ራሳችንን ወደሚፈልጉት ሁኔታ የመዉሰድ ዝንባሌ አለ፡፡

6. Complementarity ተሟሟይነት (ጎዶሎአችንን የሚሸፍን)

ብዙ ሰዎች ጉለታቸውን የሚያጎላ ሳይሆን የሚሞላ ሰው ይፈልጋሉ ፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………
www.tg-me.com/psychoet
❖_____________________________❖
Source: Zepsychology , AAU Intro to Social psychology lecture note by Dawit

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook/Telegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!
እወዳችኅለሁ !
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
❖__________________________________❖
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
የአሸናፊነት ሳይኮሎጂ
በናሁሰናይ ፀዳሉ

በአንዳንድ የፔጁ ተከታዮች ጥያቄ መሰረት ለሚቀጥሉት 4 እሑዶች ስለ አሸናፊነት ሳይኮሎጂ እፅፋለሁ ፡፡

አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡

10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ

1. Self Projection
ይህ ማለት ወደፊት ልንሆነው ፣ ልንደርስበት እና ሊኖረን ስለምንፈልገው ነገር ጥርት ያለ እይታ / አመለካከት መኖር ነው ፡፡ የመጨረሻ መዳረሻ ግባችንን አስበን ወደዛ ለመጓዝ የምናረገውን ሂደት በአይነ ሕሊናችን መሳል / መመልከት ነው ፡፡

2.Setting Goals

ይህ ደግሞ በአይነ ሕሊናች የሳልናቸው የመጨረሻ ውጤቶች ጋር ለመድረስ የምናበጀው ግብ ነው ፡፡ የምናዘጋጃቸው ግቦች ተግባራዊ የሚሆኑ ፣ በጊዜ የተወሰኑ ፣ ሊደረስባቸው የሚችሉ ፣ ሊለኩ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡ አለበለዚያ ግቡን ማሳካት አንችልም / እጅጉን ይከብደናል ፡፡

3.Focus positive side

ፍርሀት ጭንቀትንና ውጥረትን ይወልዳል ፡፡ ፍርሀት ደግሞ በአብዛኛው የሚመነጨው ከአሉታዊ አመለካከት ነው ይህ አመለካከት ደግሞ በሕይወታችን አሸናፊዎች እንዳንሆን ይይዘናል ፡፡ ስለዚህ አሸናፊዎች ሁልጊዜም ቀና / አወንታዊ አሳቢዎች ናቸው ፡፡

4.power of self determination

ቆራጥነት ሌላው የአሸናፊነት ሥነልቡና መነሻ ነው ፡፡ ብዙ ሰው ለሚሰራው ስራ ፣ ለሚወዳደረው ውድድር ፣ ለሚያጋጥመው ፍልሚያ ቆራጥ አይደለም ፡፡ የምንሰራውን ስራ የምንሰራው ግድ ስለሆነ ፣ ገንዘብ ለማግኛ ብቻ እንጂ በሕይወታችን ደስታን ለማግኚያ አይደለም ፡፡ ስለዚህ የአሸናፊነት ሥነልቡና ለማዳበር በስራችን ቋራጥና የምናረገውን ነገር ሁሉ ለሌላ ሰው ብለን ሳይሆን ለራሳችን ብለን ማድረግ አለብን ፡፡

5.Self Awareness

በዚህ ምድር አንድም ፍፁም ሰው የለም ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ ፍፁምነት / ሁሉን አዋቂነት ሳይሆን በምንወዳደርበት ነገር ተሽሎ (በልጦ) መገኘት ነው ፡፡ ለዚህ ደግሞ ራስን ማወቅ ( ደካማና ጠንካራ ጎናችንን) ወሳኝነት አለው፡፡

የሚቀጥሉትን 5 ባህሪያት በቀጣዩ ሳምንት እንመለከታለን ፡፡

👍 #Like ▶️ #Share በማረግ ሁላችንም ባለንበት ቦታ አሸናፊ እንሁን !

መልካም እሑድ!
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት
1. ጥሩ አድማጭ መሆን

ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡

2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን

በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡

3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ

የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡

4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ

ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡

5. አቀማመጥን ማስተካከል

ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡

6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት

እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡

7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ

ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡

8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡

9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር

በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡

ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet
ለሌሎች #Share በማረግ ተግባቦታችንን እናሳድግ

©Zepsychology.com (በዘመነ ቴዎድሮስ)
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ለቤተሰብዎ ስንተኛ ልጅ ነዎት?

የተወለድንበት ቅደም ተከተል በባህሪያችን ፤ የትምህርት አቀባበላችንና፤ ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ላይ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል፡፡

1. የመጀመሪያ ልጅ (the President/ leader)

የመጀመሪያ ልጆች ከተከታዮቻቸው በተሻለ በቤተሰብ ውስጥ ከበሬታና ተደማጭነት አላቸው፡፡ የቤተሰባቸውን ህግና ደንቦች በማክበርና በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት በማምጣት ወላጆቻቸውን ለማስደሰት ይተጋሉ፡፡

በቀጣይ የሚወለዱ ልጆች/ታናናሾቻቻው/ አስተዳደግ ላይ ከወላጆች ጋር ኃላፊነት ስለሚጋሩ ሲያድጉ በሳሎች፤ በራሳቸው የሚተማማኑ፤አመራር ቦታ ላይ ቢቀመጡ ደግሞ ብቁ መሪ የመሆን ዕድላቸው የሰፋ ነው፡፡

ሰዎችን ላለማስከፋት የሚተጉ፤ ተባባሪዎች፤ በቡድን ስራ መሳተፍ የሚወዱና ለሚወስዱት ስራ ኃላፊነት የሚሰማቸው የመሆን ዕድል አላቸው፡፡

አብዛኞቹ የመጀመሪያ ልጆች ከተከታዮቻቸው የተሻለ ነገሮችን የመረዳት (Intellegency) አቅም እንዳላቸው ይታመናል፡፡

የመጀመሪያ ልጆች ከሚሳቡባቸው የስራ መስኮች ውስጥ መሪ መሆን፤ ዳኛ ፤ ሃኪም ፤ የኮምፒውተር ፕሮግራመርና አርቴክተር ይጠቀሳሉ፡፡ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት እስካሁን ከመሯት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሆኑት የመጀመሪያ ልጅ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን ከመሯት ውስጥስ ስንቶቹ የመጀመሪያ ልጅ ናቸው?

በዓለም ላይ ካሉ በስራ ፈጣሪነት (entrepreneurs) በጣም ታዋቂ የሆኑት አብዛኞቹ የመጀመሪያ ልጆች ናቸው

በተቃራኒው አንዳንድ የመጀመሪያ ልጆች፤ በተለይም ደግሞ በቤተሰብ ጉዳይ ላይ በጣም ጫና በዝቶባቸው የሚያድጉ ከሆነ፤ በ 9 ዓመታቸው እንደ አርባ ዓመት እንዲያስቡ ተጽእኖ የሚደርስባቸው ከሆነ የልጅነትን ጣዕም ሳያውቁት ወደ ወጣትነት ስለሚሸጋገሩ ቁጥቦች፤ ራስ ወዳዶች፤ ተቆጣጣሪዎች፤ ሰው የሚሰጣቸውን መመሪያ የማይቀበሉ፤ የሚጨናነቁ እና በህይወታቸው ደስታ የማይሰማቸው ሊሆኑ ይችላሉ

2. መካከል ላይ የሚወለድ ልጅ (ሁለተኛ፤ ሶስተኛ) (The Diplomat)

በሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ የሚወለዱ ልጆች ከሰው ጋር በቀላሉ የሚግባቡ፤ ጓደኝነት መመስረት የማይከብዳቸው ፤ ታጋሾች፤ ሃሳባቸውን ለመግለጽ የማይቸገሩና የሰውን ስሜት ማንበብና መረዳት የሚችሉ ናቸው

መካከል ላይ የሚወለዱ ልጆች እንደ መጀመሪያ ልጅ በቤተሰብ ውስጥ ትኩረት ላይሰጣቸው ይችላል

በመካካል ላይ የሚወለዱ ልጆች “ታላቅህን እክብር እና ታናሽህን ደግሞ ተንከባከብ” እየተባሉ በሁለት ጎን ተወጥረው ስለሚያዙ በቤተሰብ ውስጥ ያለቸው ተቀባይነትና ቦታ ያሳስባቸዋል፡፡ ስለሆነም በመካከል የሚወለዱ ልጆች ከታላቃቸውም ሆነ ከታናሻቸው ጋር መቃረንን የሚያበዙ፤ ለቤተሰብ ህጎች መገዛት የሚከብዳቸውና አመጸኞች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ፍላጎታቸው ካልተሟላላቸው ቤተሰብ የሚቸገርባቸው፤ ህጎችና ደንቦችን ለመከተል የሚቸገሩ፤ዓይና አፋሮችና፤ ገለልተኞች ልጆች ሊሆኑም ይችላሉ፡፡

መካከል ላይ የሚወለዱ ልጆች ብዙ ጊዜ የሚወዷቸው የስራ መስኮች የጥበብ ስራዎች (ሙዚቃ፤ ስዕል)፤ ዲፕሎማት፤ የማስታወቂያና የጋዜጠኝነት ሙያዎች ናቸው፡፡

3. የመጨረሻ ልጅ (The Clown/ Joker)

የመጨረሻ ልጆች በቤተሰብ ውስጥ ሁሌም እንደ ህጻን የመታየት ዕድላቸው የሰፋ ነው፡፡ ትልቅ ሆነው፤ አግብተው፤ ወልደውም ቢሆን እንኳ በቤተሰብ አባላት መካከል እንደ ትንሽ ልጅ ሊታዩ ይችላሉ

ከእነሱ ቀድመው የተወለዱ ልጆች ያለፉባቸው የቤተሰብ ህጎች እነሱ ጋር ሲደርስ ተግባራዊነታቸው ይቀንሳል፡፡ የሁሉንም ቤተሰብ ትኩረት የማግኘት ዕድል ያላቸው ሲሆን በጣም ስሜተ ስስና፤ ቀበጦች፤ በቀላሉ የሚያኮርፉ ሊሆኑ ይችላሉ

የመጨረሻ ልጆች በአግባቡ ከተያዙ ጠንካራና ስራ ወዳዶች፤ ተግባቢዎችና የሰውን ቀልብ መሳብ የሚችሉ፤አዳዲስ ነገሮችን መፍጠር የሚያስደስታቸው፤ አደጋ ያለባቸው የሚመስሉ ጉዳዮችን ለመሞከር ወደኋላ የማይሉ ናቸው

የመጨረሻ ልጆች ብዙ ጊዜ ከሚወዷቸው የስራ መስኮች ውስጥ የንግድ ስራ (Business and Salesman) ይጠቀሳል፡፡

#Share
©zepsychologist (በሰብለወንጌል አይናለም)

@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ለሥነልቡና ፔጅ ቤተሰቦች በሙሉ መልካም ዜና ፡፡

በመጪው
ቅዳሜ ጥር 23 ከ 10:00 - 11:00 እንዲሁም
እሑድ ጥር 24 ከ 11:00 -12:00
#ልዩ_የነፃ_የስልጠና_እድል_ተዘጋጅቷል ፡፡

ያለው ቦታ ለቅዳሜ (35) ለእሑድ (35) ቦታ ብቻ ስለሆነ ቀድማችሁ በመደወል በአንዱ ቀን ብቻ #በነፃ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን ፡፡

የመመዝገቢያ ሰአት
ሮብ ፣ ሐሙስ ፣ አርብ ከጠዋቱ (3:00 - 10:00) ብቻ +251946333951
ለሰው መመዝገብ አይቻልም ! ቀድሞ የተመዘገበ ቀድሞ ቦታ ያገኛል ፡፡

የስልጠናው አላማ ፦ በየወሩ በክፍያ ከምንሰጠው ስልጠና በተጨማሪ ህብረተሰባችንን በነፃ በሙያችን ለማገልገል ካለን ፍላጎት የተነሳ በተጨማሪም ሁሉም ሰው በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ እንዲሆን መንገድ ለማሳየት ነው፡፡

የስልጠና አድራሻ ፦ አዲስ አበባ ካዛንቺስ ቅ/ኡራኤል ቤ/ክ አጠገብ ሸገር ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 202

ቴሌግራም ፦ www.tg-me.com/psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ለሥነልቡና ፔጅ ቤተሰቦች በሙሉ መልካም ዜና ፡፡ በመጪው ቅዳሜ ጥር 23 ከ 10:00 - 11:00 እንዲሁም እሑድ ጥር 24 ከ 11:00 -12:00 #ልዩ_የነፃ_የስልጠና_እድል_ተዘጋጅቷል ፡፡ ያለው ቦታ ለቅዳሜ (35) ለእሑድ (35) ቦታ ብቻ ስለሆነ ቀድማችሁ በመደወል በአንዱ ቀን ብቻ #በነፃ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን ፡፡ የመመዝገቢያ ሰአት ሮብ ፣ ሐሙስ ፣…»
በጣም ከቻልክ አካባቢህን ለውጥ
ካቃተህ ራስህን ለውጥ

ሁለቱም ካልሆነ ግን ለሌሎች ችግር አትሁን!
የነፍስ ጥሪያችንን መከተላችንን የሚጠቁሙ 10 ምልክቶች

አንዳንዴ በዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ይህ ስራ፣ ይህ ህይወት የምፈልገው ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ አእምሮችንን ሰቅዞ ይይዛል፡፡ በተለይ የምንሰራው ስራ ደስታ አልባ ሲሆን፣ ሁልጊዜ እንደው አንድ ቀን ይህንን አድርጌ ብሞት እንኳ አይቆጨኝም የምንለው ነገር ውስጣችን ሲመላለስ፣ አጋጣሚው ተፈጥሮ ስንሰራውም ሆነ ስንሆነው ትልቅ ደስታ የሚሰጠን ነገር ሲኖር እና አሁን እየሰራን እና እየኖርን ያለነው ህይወት ግን ከዚህ የተለየ ሆኖ ሲገኝ የነፍሳችንን ጥሪ ማግኘት አለማግኘታችን ህይወታችን ውስጥ ትልቅ ጉዳይ ይሆናል፡፡
የነፍስ ጥሪ እያልን ያለነው ማንኛውም መስራት፣ መሆን፣ ማግኘት የምንፈልገውን ነገር ሲሆን ዓላማ፣ ራዕይ፣ የህይወት ግብ የመሳሰሉት ቃላት ሊተኩት ይችላሉም፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ነጥቦች አንድ ሰው የነፍስ ጥሪውን ማግኘቱን የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡

ከውልደታችሁ ጊዜ ጀምሮ ለነፍስ ጥሪያችሁ እየተዘጋጃችሁ እንደ ነበር ትረዳላችሁ

ሌላው ቀርቶ ያዘናችሁበት እና የተጎዳችሁበት ነገር እንኳ ለነፍስ ጥሪያችሁ ልምምድ እንደነበር ይሰማችኋል፡፡ የምትወዱት ሰው ሞት፣ ፍቺ፣ ሲያጋጠማችሁ አደጋ ወዘተ ነፍሳችሁ መሆን ለምትሻው ነገር የዝግጅት ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዴ አሳዛኝ ነገሮች ከተፈጠሩ በኋላ ውጤቱ ግን ጥሩ ሲሆን ሰዎች “ለበጎነው” የሚሉት ከዚህ አኳያ ነው፡፡ ህመም አጋጥሞን የተማርነው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ ሰዎች ጎድተውን የተማርነው ነገ ርሊኖር ይችላል፡፡ ቅርባችን ያለሰው ህይወት አልፎ የተማርነው እና ህይወታችንን የቀየረ አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ በህይወታችሁ ከውልደታችሁ ጀምሮ ያጋጠማችሁ ክፉ እና ደግ ነገር ለነፍስ ጥሪያችሁ የዝግጅት ጊዜ እንደነበር ትረዳላችሁ፡፡

ምስጥራዊ ነገሮች ይፈጠራሉ

ህይወታችሁ ውስጥ ይሆናል ያላሰባችሁት አስደናቂ ነገሮች ሲፈጠሩ ተአምራዊ አጋጣሚ ብላችሁ ልታስቧቸው ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ ህልማችሁን ለማሳካት የሚያስችሏችሁ አንዳንዴ ለማመን ሁሉ የሚከብዷችሁ ሚስጥራዊ አጋጣሚዎች የነፍስ ጥሪያአችሁን እየተከተላችሁ እንደሆነ ያሳያሉ፡፡

ከመንገድ ስትወጡ ወደ መንገዳችሁ ሊመልሷችሁ የሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይፈጠራሉ

የነፍስ ጥሪያችሁ እየተከተላችሁ ካልሆነ አንዳንዴ መንገዱ አልጋ በአልጋ አይሆንላችሁም፡፡ ህይወት አስቸጋሪ ሲሆንባችሁ እያቀናችሁ ያለበት መንገድ የእናንተ መንገድ አለመሆኑን ትገነዘባላችሁ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ስትሆኑ ገንዘብ ሊቸግራችሁ፣ በርትታችሁ እንድትቆሙ ያገዟችሁ ሰዎች ከጎናችሁ ሊሸሹ፣ ደስታ ሊርቃችሁ ወዘተ ይችላል፡፡

በችግር እና ፈተና ፊት ተረጋግታችሁ ትቆማላችሁ

መንገዳችሁ ፈተና የበዛበት ሲሆን የትኛው ምክንያት የፈተናው ምንጭ እንደሆነ አንዳንዴ ለመረዳት ሊከብድ ይችላል፡፡ ቁርጠኝነታችሁ እየተፈተነ ነው ወይስ የተሳሳተ መንገድ ውስጥ ገብታችኋል? መሰናክሎች የዕድገታችን አካል፣ እንድንጠነክር የሚያደርጉን ሂደቶች፣ ውስጣችሁ የሚገኘው ጀግና ጉዞ አካል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአንፃሩ የተሳሳተ መንገድ እየተከተላችሁ እንደሆነ የሚጠቁሙ ምልክቶች ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ ልዩነቱን እንዴትነው ማወቅ የምትችሉት? ልዩነቱን የምትረዱት ውስጣችሁ እየተፈጠረ በሚሄደው መረጋጋት እና ሰላም (Ease) ነው፡፡ ሁኔታዎች አስቸጋሪ ሆነው፣ ችግር እና ፈታና ፊታችሁ ተከምሮ እንኳ ውስጣችሁ ሰላም እና መረጋጋት የሚሰፍን ከሆነ የነፍስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ መሆኑን ያሳያል፡፡

አስደናቂ አስተማሪዎችን ታገኛላችሁ

የነፍስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ ከሆነ ልምዳቸውን የሚያካፍሏችሁ፣ እገዛ የሚያደርጉላችሁ፣ የሚያበረታቷችሁ ሰዎች በየጊዜው ይፈጠራሉ፡፡

ጤናችሁ ሊሻሻል ይችላል

እንግዳ የሚመስል ነገር ነው፡፡ ነገር ግን የነፍስ ጥሪያችሁን እየተከታላችሁ ከሆነ አንዱ የምታገኙት ነገር መልካም ጤንነት ነው፡፡ ለጤናችሁ የማይበጅ ምግብ የመመገብ ፍላጎታችሁ ይቀንሳል፤ ሰውነታችሁን እንደልባችሁ ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ኃይል ታገኛላችሁ፤ እረፍት የሚነሷችሁ ህመሞች፣ መፍለጥ መቁረጦች ሊጠፉ ይችላሉ፤ ድካም አጠገባችሁ ድርሽ ላይል ይችላል፤ ስር የሰደደ ህመም ካለባችሁ እንኳ መሻሻል ልታዩ ትችላላችሁ፡፡

ገንዘብ ማግኘት ትጀምራላችሁ

የነፍስ ጥሪያችሁን መከተል ስትጀምሩ ጨርሶ ገንዘብ አትቸገሩም ማለት አይደለም፡፡ የሚላስ የሚቀመስ የምታጡበት ደረጀ ላይ ሁሉ ልትደርሱ ትችላላችሁ፡፡ እዳ ውስጥ ልትነከሩ ትችላላችሁ፡፡ የቤት ኪራይ የምትከፍሉት ገንዘብ እጃችሁ ላይ ላይኖር ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ የነብስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ ከሆነ ገንዘብ እንደ ልብ ታገኛላችሁ፡፡

ብዙ ሊያሳስባችሁ የሚችል ነገር እያለ በሚገርም ሁኔታ ሰላም ውስጣችሁ ይሰፍናል

በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች በሙሉ “አብዳችኋል” ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እናንተም በአንድ ጎናችሁ በእነሱ ሃሳብ ልትስ ማሙ ሁሉ ትችላላችሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ውስጣችሁ/ነፍሳችሁ የምትፈልጉትን እንዳገኘ ስለሚያውቅ ሰላም እና መረጋጋት ይበዛላችኋል፡፡ ነብሳችን ኃላፊነታችን ምን እንደሆነ ሁልጊዜም መግለጽ ትፈልጋለች፡፡ ምንም እንኳን በዙሪያችን የሚገኙ ብዙ ነገሮች አስደሳች ባይሆኑም አንድ ጊዜ የነፍስ ጥሪያችንን መከተል ስንጀምር ግን አስደናቂ ሰላም እና መረጋጋት ውስጥ እንገባለን፡፡

ዓለም ይተባበራችኋል

አንድ በጣም ትልቅ የህክምና ባለሙያ ሰው እንዲህ ትላለች “ለምን ወረቀት አይሆንም እኔ ከፈለኩት እግር አውጥቶ ይመጣል”፡፡ የነፍስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ ከሆነ የሚተባበራችሁ ሰው በየአቅጣጫው ይገኛል፡፡ የሚጻፍ ነገር ስትፈልጉ ፀሐፊ ደጃችሁ ድረስ ሊመጣ ይችላል፡፡ የሚታተም ነገር ስትፈልጉ ከአታሚዎች ጋር በሆነ አስደናቂ አጋጣሚ ልትገናኙ ትችላላችሁ፡፡ ሰዎች እየደገፏችሁ፣ እያበረታቷችሁ፣ ዕድለኛ እየሆናችሁ እንደሆነ ይሰማችኋል፡፡ እያንዳንዱ ነገር ግልጽ ባይሆን እንኳን በዚህ ድጋፋ እና ማበረታቻ ምክንያት ትክክለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኙ ትረዳላችሁ፡፡

አጋሮቻችሁያገኟችኋል

ማንም ሰው ቢሆን ህልሙን ብቻውን ለማሳካት ይቸገራል፡፡ ትልልቅ ለውጦች፣ ትልልቅ ፈጠራዎች፣ ትልልቅ ስራዎች በአጠቃላይ የብዙ ሰው የተባበረ አእምሮ እና ክንድ ውጤት ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ዓለም በፈታና እና በብዙ ውጣውረድ የተሞላች ነች፡፡ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ብቻን ማለፍ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ እናንተ የነብስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ ከሆነ መንገድ ላይ አብረዋችሁ የሚሰሩ አጋሮችን ታፈራላችሁ፡፡

©በነጋሽ አበበ (Zepsychologist)
@psychoet

#Share
ከመሞታችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 20 ነገሮች
Join Telegram www.tg-me.com/psychoet

1.ትላንትናን እና ነገን እያሰባችሁ አትጨነቁ፡፡ ትናንት አልፏል ነገ አልመጣም ስለዚህ ዛሬን ቀን በሙላት ፣ በደስታ ፣በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፡፡

2.የበደሏችሁን ሰዎች ይቅርታ አድርጉላቸው ፡፡

3.ሁሉንም ሰው በእኩል ዓይን እዩ፡፡

4.ወደዚህ ምድር ያመጧችሁን እናትና አባታችሁን ውደዱ ፣ አክብሩ ፣ ታዘዙ ። *

5.የምትጠሉትን ስራ አትስሩ፡፡

6.የሕይወት ግባችሁን በመለየት በቅጡ ኑሩ፡፡

7.መስታወት ውስጥ ራሳችሁን ተመልክታችሁ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ራሳችሁን ውደዱ፡፡

8.እዚህ ምድር የመጣችሁት በፈጣሪ አላማና እጅግ በጣም ጠቃሚ ሰዎች እንደሆናችሁ አስቡ ፡፡

10.ዘወትር መሄድ እፈልጋለሁ ወደምትሉት ስፍራ ሂዱ፡፡

11.በየቀኑ ለሌሎች ቢያንስ አንድ መልካም ነገር አድርጉ፡፡*

12.ለውጥን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ፡፡

13.ሁሉንም ዓይነት የሕይወት ትምህርት በፀጋ ተቀበሉ፡፡

14.የሕይወት ፈተና ውስጥ ያለውን መልካም አጋጣሚ አስተውሉ እንጂ ተስፋ አትቁረጡ፡፡

15.በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አዎንታዊ እና በጎ አሳቢ ሆናችሁ ዝለቁ፡፡

16.በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ሁሉ ለመውደድ ጣሩ ፡፡*

17.ከቁሳ ቁስ ጋር ያላችሁን ትስስር አላሉ፡፡

18.ልባችሁን ተከተሉ፡፡

19.ሁልጊዜም ትልቅ በመሆን ሌሎችን አነቃቁ፡፡

20.ከሰዎች ሁሉ ጋር ተጫወቱ በሰላም በመግባባት ኑሩ ፤ የተቸገሩትን ደግፉ ፡፡ ደግሞም ይህን ጽሑፍ #Share አርጉ ፡፡*😍😍😍

ዘጠነኛውን አንብባችሁታል ግን? .......
የዘለልኩት እስቲ እኔ ያልጠቀስኩት መደረግ ያለበት ነገር እንድታስቡ ነው?

ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ !
እወዳችኀለሁ 😍

(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Join Telegram www.tg-me.com/psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_18
#የሳይኮሎጂ_ጎሎች #Goals of Psychology
(ናሁሰናይ ፀዳሉ www.tg-me.com/psychoet )

እያንዳንዱ ሙያ የራሱ የሆነ አላማ / ግብ እንዳለው ሁሉ ሳይኮሎጂም እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ የራሱ የሆነ ዋና ዋና ግቦች አሉት ፡፡ በመሆኑም ሳይኮሎጂ በትምህርት ደረጃ ቢሰጥም እንዲሁሞ በለት ተለት የሕይወት ተግባራችን ብንጠቀመው የመጨረሻ ዋና ዋና ግቦቻችን የሚሆኑት አራት ናቸው እነርሱም ፦

1.ባህሪን መግለፅ (Describe )
2.ባህሪን ማብራራት (Explain)
3.ባህሪን መተንበይ (predict)
4.ባህሪን መምራት /መቆጣጠር እና መለወጥ (control & Change )

1.ባህሪን መግለፅ (Describe )

ይህ የአንድ አካልን ባህሪ መመልከት ፣ ማጤን እና እያንዳንዱን እያንዳንዱን ነገር ማስተዋል ያካትታል ፡፡ ይህ ግብ ስለ ምንፈልገው ነገር የሚከተሉትን ነገሮች ይመልስልናል ፡፡ " ምን እየሆነ ነው? " " ነገሩ መች እና የት ሆነ ? " ነገሩ ማን ላይ ሆነ?" ነገሩ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነ " የሚሉትን ያካትታል ፡፡

ለምሳሌ ፦ በአቅራቢያችን ያለ ሰው በተለያየ ምክንያተት ፀባዩ ቀስ በቀስ እየተለወጠብን ሲሄድ ፣ ለኛ ያለው ዋጋ ሲቀንስ / ሲጨምር የምናስተውልበት መንገድ ነው፡፡


ይህን ለማድረግ የምንጠቀመዉ የስሜት ህዋሶቻችንን (መስማት ፣ ማየት ...) ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ ምልከታዎች ፣ መጠይቆች ፣ አጫጭር ውይይቶች የመሳሰሉትን በመጠቀም ባህሪውን መግለፅ እንችላለን።

2.ባህሪን ማብራራት (Explain)

ይህ ደግሞ "ለምን ይህ ሆነ ? "ብለን ለምንጠይቀው ጥያቄ ማብራሪያ መልስ ነው ፡፡ ማብራራት ለእያንዳንዱ ለተመለከትናቸው ባህሪያት መነሻ ምክንያታቸውን የምንፈልግበት ሂደት ነው ፡፡

ለምሳሌ ፦ ባህሪው በጊዜ ሂደት እንደተለወጠብን ያስተዋልነውን የቅርብ ሰው " ለምን ይህ ሊሆን ቻለ ብለን የበለጠ በቅርቡ ያሉ ሰዎችን / እራሱን ስለ ምክንያቱ ስንጠይቅ ነው ፡፡

3.ባህሪን መተንበይ (predict)

ይህ ትንበያ ደግሞ ማንኛውም ሰው አሁን ካለው ባህሪ ተነስተን ወደፊት ምን ሊሆን ይችላል ብለን መላምት ማስቀመጥ ነው ፡፡

ለምሳሌ ፦ በቅርባችን ያለ አንድ ሰው ከቀን ቀን ባህሪው እየተበላሸ ሲመጣ ከዚህ በፊት ሌሎች ላይ ካየነው የባህሪ መበላሸት ውጤት አንፃር ይል ልጅ በዚህ ከቀጠለ እንደዚህ ይሆናል ብለን predict የምናረግበት ነው ፡፡

ይህን ለማድረግ የምንጠቀመው ተዛምዶአዊ ግንኙነት (Corelation) በመስራት ነው ፡፡

4.ባህሪን መምራት /መቆጣጠር እና መለወጥ (control & Change )

ይህ ማለት ደግሞ የማይፈለግ ፣ የማይወደድ ፣ በህብረተሰቡ ቅቡልነት የሌለውን ባህሪ ወደ መልካም የምንመራበት የምናስተካክልበት መንገድ ነው ፡፡ በዚህ ጊዜ ባህሪን በእጅጉ ለማሻሻል ብዙ ሳይኮሎጂካል መንገዶችን እንጠቀማለን ፡፡

የሶስቱ ቀደምት ግሎች መደምደሚያ የባህሪ ለውጥ ነው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………
www.tg-me.com/psychoet
❖_____________________________❖
Source: General Psychology (Psyc 1011) Higher Education Manual

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook/Telegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ ።

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
❖__________________________________❖
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
የአሸናፊነት ሥነልቡና
#ክፍል_2
በናሁሰናይ ፀዳሉ

አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡

10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ

ከተራ ቁጥር 1 - 5 ያሉትን ባለፈው በዝርዝር አይተናል፡፡ ዛሬ ከተራ ቁጥር 6-10 ያሉትን እናያለን ፡፡
__________________________________
1.ልንሆነው/ልንደርስበት ስለምንፈልገው ነገር የጠራ እይታ / አመለካከት
2.ግብ ማስቀመጥ
3.አወንታዊ አመለካከት
4.ቆራጥነት
5.ራስን ማወቅ
__________________________________

6.Self Esteem / ራስን ማክበር

አሸናፊ ሰዎች ለራሳቸው ትልቅ ክብርና አድናቆት ያለቸው ናቸው ፡፡ስለራሳቸው ጥሩ አወንታዊ አመለካከት አላቸው ይህ ማለት ግን ሌሎችን ይንቃሉ / አያከብሩም ማለት አይደለም፡፡ ራስን ማክበርና ሌሎችን ማክበር መነጣጠል የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ተሳካልን ፣ ትልቅ ደረጃ ደረስን አሸነፍን የሚሉ ሰዎች ከታች ያሉ ሰዎቾን የመናቅ ያለማክበር ሁኔታ ይታያል ይህ ግን ትልቅ ችግርና ያልተሟላ አሸናፊነት ብሎም ለወደፊነቱ ወደ ተሸናፊነት የሚወስድ መንገድ ነው ፡፡ አሸናፊ እራሱን ያከብራል ደግሞም ያስከብራል ብሎም ደግሞ ሌሎችን አክብሮ ያስከብራል ፡፡

7.Self Discipline / ስርአት መኖር

ይህ በተግባር የሚገለፅ የአሸናፊነት ባህሪ ነው ። በዚህ ዘመን ብዙ ሰው የወሬ እንጂ የስርአትና የተገባር ሰው አይደለም ከላይ አመራር ጀምሮ እስከታች ድረስ ብዙ ጊዜ ወሬ እንጂ ስርአትና / ተግባር አይታይም ፡፡ ጠንካራ ልምምዶችን እንደ ልምድ አድርጎ በተግባር አለመግለፅ አሸናፊ እንዳንሆን ያረገናል ፡፡ ለምሳሌ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ብንመለከት ልምምዳቸውን በየጊዜው በስርአት ካልሰሩ ብዙ ሽንፈት ሊገጥማቸው ይችላል ፡፡

8.Self Talk / ከራስ ጋር ማውራት (ጊዜ መውሰድ)

አሸናፊዎች ሁልጊዜ የሚራራጡ ፣ እረፍትና እርጋታ የሌላቸው ፣ ሁሌ ሳያቋርጡ የሚሰሩ አይደሉም ፡፡፡ይልቁንስ በቂ ሰአት ስራቸው ላይ የሚያጠፉ እንዲሁም ተመጣጣኝ ጊዜ ደግሞ ለራሳቸው የሚሰጡ ፣ ነገሮችን በትኩረት ረጋ ብለው የሚያስቡ (ሳይጨነቁ ነገሮችን የሚያወጡ የሚያወርዱ) ናቸው ፡፡ ከራሳቸው ጋር በቂ ጊዜ የሚወስዱ ሰዎች ሁሌ ከውጥረት ብሎም ከጭንቀት ራሳቸውን ያስመልጣሉ ፡፡

9.Complete person / ሙሉ ሰውነት

ትክክለኛ አሸናፊ ሰው አንድ ወገን ብቻ ያደገ ፣ ሌላው ጎኑ የጎደለ ሳይሆን በሙሉ ማንነቱ የሞላ ያሸነፈ ነው ፡፡ ሕይወት ትምህርት ጥሩ ውጤት ማምጣት / ሩጦ 1ኛ መውጣት ፣ ተዋግቶ ማሸነፍ ፣ በሀብት ትልቅ ደረጃ መድረስ ብቻ አይደለችም ፡፡ አንዳንድ ሰው በገንዘብ አቅሙ ትልቅ ደረጃ ይደርስና በማህበራዊ ሕይወቱ ደግሞ 0 ይሆናል ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው ሙሉ ሰው አንለውም ፡፡

#ሙሉ ሰውነት ላይ ወደፊት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይዤ እቀርባለሁ ፡፡

10.Live in the present/ አሁንን መኖር

ይሄ ብዙዎች አሸናፊ እንዳይሆኑ የሚያረግ የአመለካከት ችግር ነው ፡፡ ነገራችንን በሙሉ በነገ ተስፋና በትናንት ፀፀት / ወቀሳ ዛሬ ላይ በደንቡ ሳንኖር በሀዘን እንዘልቃለን ፡፡ አሁንን በአሸናፊነት ሀሳብ/ አመለካከት ሳንኖር የነገን ያልተጨበጠ ድል በማለም በተስፋ ብቻ እንደክማለን ፡፡ ስለዚህ አሸናፊ ለመሆን የሚያስብ ሰው አሸናፊነት ስለ ነገና ስለ ወደፊት ሳይሆን ስለ አሁን ነው ፡፡


👍 #Like ▶️ #Share በማረግ ሁላችንም ባለንበት ቦታ አሸናፊ እንሁን !

አሸናፊነት የሚጀምረው ከአስተሳሰብ ነውና አስተሳሰባችሁን ቀና ፣ በጎ ፣ ጥሩ ጥሩውን ማድረግ ጀምሩ ፡፡ አሉታዊ አስተሳሰባችሁን በአወንታዊ ሀሳቦች ለውጡ ፡፡

#በመጪው_ሳምንት_እሑድ_ይቀጥላል ፡፡

#መልካም_እሑድ!
@Psychoet
GreenFire-Feb2020.pdf
1 MB
" አለማችን ከዓይን ጥቅሻ በፈጠነ የለውጥ ግስጋሴ ላይ ትገኛለች ፡፡ ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላው ጫፍ የሚደረገው ግስጋሴ ለማመን ያስቸግራል ፡፡ ወደዚህ ምድር እስከአሁን ድረስ 108 ቢሊዮን በላይ የሰው ልጆች መተዋል ተብሎ ይታመናል ፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ሰው ደስታን የሚሻ ነው ። ..."

በዚህ ሳምንት ስለ ደስተኛ ሕይወት እናያለን
😀😃😄😁😆
📌አንድ ሰው ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ምን ምን ነገሮችን ማድረግ አለበት ?

📓 ይህ ትውልድ በተለይ ወጣት የሆናችሁ (Generation y )የሕይወትን ደስታና እርካታ እንዴት ያግኝ? በሚል የፃፍኩትን አጭር መጣጥፍ #በገፅ_8 ላይ ታገኙታላችሁ ፡፡
መልካም ንባብ !

አስተማሪ ስለሆነ ባለንበት ግሩፕ #Share እናርግ 🧳ONLY 1.0 MB
@Psychoet
2024/10/01 13:27:58
Back to Top
HTML Embed Code: