Telegram Web Link
ለእያንዳንዱ ጉዳይ መብከንከናችንን እናቁም

በዙሪያዬ ያሉ ጥቂት ሰዎች ኑሯቸው እንዲህ ነው፡፡ ለረባውም ላረባውም፣ ለትንሽ ትልቁ፣ ለሚለከታቸውም ለማይመለከታቸውም ነገር ትኩረት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ለእያንዳንዷ ጥቃቅን ጉዳይ ትኩረት ከሰጠንና ከተጨነቅን ኑሯችን ጤናማ አንሆንም፡፡

እንዴት አንድ ሰው ስለሁሉም ነገር ሊጨነቅ ይችላል? ለራሳችን ጉዳይመ ተጨንቀን፣ ለሰዎች ተጨንቀን፣ ሊሆን ይችላል እያልን ተጨንቀን እንዴት እንችለዋለን? 

በጣም የሚገርመው እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች፡
✍️ የመፍትሄ ሰዎች አለመሆናቸው ላይ ነው፡፡
✍️ አንድን ጉዳይ ለረጅም ግዜ ይተክዙበታል፡፡ 
✍️ነገሮችን በአሉታዊ መንገድ መረዳት ይቀናቸዋል፡፡
✍️ሲታመሙ አንኳን የሚድን አይመስላቸውም፡፡
✍️በህይወታቸው ውስጥ ያሉትን መልካም እድሎችን  መጠቀም አይችሉበትም፡፡

ከዚህ ባህሪ ለመላቀቅ፡

1️⃣ መፍትሄ መስጠት የምንችለውን መፍትሄ መስጠትና መተው ያለብን ደግሞ መተው መለማመድ
2️⃣ ሌሎች ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ማየት፣ መጠየቅና ትምህርት መውሰድ
3️⃣ ጓደኞችን ማፍራትና ከእነሱ ጋር ግዜ ማሳለፍ ተቃሚ መፍትሄዎቸ ናቸው፡፡

@ተመስገን አብይ Psychologist

@psychoet
መልካም የእናቶች ቀን
❖አንባቢ እናት ጥሩ ትውልድን ትገነባለችና ይቺን የመሰሉ እናቶች ይብዙልን ፡፡ ፎቶው የተላከልኝ ከወደ አዋሳ ነው ፡፡
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖
ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ የሕይወት ምክሮችና እውነታዎች
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖

📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡

ሜሎሪና አንብቡ አስነብቡ❤️❤️❤️

መልካም የእናቶች ቀን

www.tg-me.com/psychoet
ዝምታ

ለምን ዝም እንላለን ? ዝምታ ይጠቅማል ወይስ ይጎዳል? መልሱን ቀጥሎ ታገኙታላችሁ፡፡

ዝምታ ሁለት አይነት መልኮች አሉት፡፡

አንዱ ስህተትን በመፍራት፣ ላለመሞከር፣ በሰዎች አይን ውስጥ ላለመግባት፣ ድፍረት የማጣት፣ የፍርሃት ምልክት ነው፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ሌሎችን ማድመጥ ብቻ እንጂ የራሳቸውን ማጋራት፣ መጠየቅ፣ በቂ ምላሽ መስጠት አይችሉበትም፡፡ በዚህም ምክንያት ለራሳቸው ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡ የሰዎች ሁሉ ሃሳብ ማጠራቀመሚያ ቋት ይሆናሉ፡፡ የራሳቸውን ሃሳብ በድፍረት መግለጽ አይችሉበትም፡፡ የሚረዳቸው ሰው እንደሌለም ይሰማቸዋል፡፡

ሁለተኛው ዝምታ ደግሞ ባለመቻል ሳይሆን ፈልገን የምናደርገው ነው፡፡ ለማዳመጥ፣ ለመረዳት፣ ለማሰብ፣ ለራሳችን ግዜ ለመስጠት፣ ተራችንን ለመጠበቅ፣ ወዘተ. ስንፈለግ ዝምታን እንመርጣለን፡፡ አንዳንዴም ሁኔታው ልክ እንዳልሆነ እያወቅን ጭቅጭቁን ለማስወድ ወይም ጉዳዩ በኛ ብቻ ሊፈታ እንደማይችል ስለተረዳንና ለማሳለፍ ስንል ዝምታን እንመርጣለን፡፡

ራሳችሁን የትኛውን ዝምታ ስትጠቀሙ አስተውላችሁ ታውቀላችሁ? የመጀመሪያውን ወይንስ ሁለተኛውን? ጻፉልን፡፡

©ተመስገን አብይ Psychologist
@psychoet
በእራስህ ህይወት ላይ ሹፌር ካልሆንክ
በሌሎች ህይወት ተሳፋሪ ትሆናለህ

@psychoet
#Share አድርጉ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2016 ዓ.ም ለድኅረ- ምረቃ ትምህርት አመልካቾች

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2016 ዓ.ም ለድህረ ምረቃ ትምህርት በቀን መርሃ ግብር ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ እና በርቀት መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለዚህም በዩኒቨርስቲዉ ድረ-ገጽ (http://aau.edu.et) ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡

የአ.አ.ዩ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) የማመልከቻና መፈተኛ ቀናት ከግንቦት 15 እስከ ነሐሴ 06 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን፤

የአ.አ.ዩ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና ላለፉ በ(https://portal.aau.edu.et) ላይ የማመልከቻና የትምሕርት ማስረጃዎችን የማስገቢያ ቀናት ከግንቦት 18 እስከ ነሐሴ 10 2015 ዓ.ም፤

የትምሕርት ማስረጃዎችን በማስገባት የማመልከቻ ቦታ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203 መሆኑን ያሳዉቃል፡፡

@Psychoet
ትስማማላችሁ?
ጀምሮ መጨረስ መቻል

ብዙ ነገሮችን እንጀምራለን ነገር ግን የጀመርናቸውን ሁሉ አንጨርስም፡፡ በጣም በጉጉት፣ በተነሳሽነት፣ በፉከራ እንጀምርና ከጥቂት ቀናት በኋላ ስንቀጥለው አይታይም፡፡ ለምን ይመስላችኋል?

አንድ ሰው አንድን ነገር ጀምሮ የማይጨርስ ከሆነ ቀጥሎ ካሉት ውስጥ የማይችላቸው ነገሮች አሉት ማለት ነው፡፡

1️⃣ ፍላጎት፡ ፍላጎቱን ለይቶ የማያውቅ ሰው በጀመረው ነገር ላይ መጽናት አይችልም፡፡ ምክንያቱም በራሱ ፍላጎት ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ፍላጎትና ግፊት ስለሚጀምሩ ከጊዜ በኋላ ያስጠላቸውና ይተውታል፡፡
2️⃣ ውሳኔ፡ ውሳኔ ማለት የጀመርኩትን ነገር መጨረሻውን ሳላይ አላቆምም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከጫፍ እስከምደርስ ድረስ ጉዞዬን እቀጥላለሁ ማለት ነው፡፡ ውሳኔ የአንድን ሰው ሙሉ ህይወት የማስተካከል ሀይል ያለው ትልቅ ችሎታ ነው፡፡
3️⃣ ትኩረት፡ ትኩረቱን የሚፈልገው ነገር ላይ ማድረግ ያልቻለ ሰው የሚጀምረው ብቻ እንጂ የሚጨርሰው ነገር የለውም፡፡ ትኩረታችን በፈለግነው ነገር ላይ ብቻ ለማድረግ ከወሰንንና ከጠበቅን የጀመርነውን ለመጨረስ እንችላን፡፡
4️⃣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በህብረት መስራት መቻል፡ አንዳንዶቻችን የጀመርነውን ነገር ያለማንም እርዳታ ብቻችንን ለማድረግ እንለፋለን በኋላም ከአቅማችን በላይ ይሆንብንና እንተወዋለን፡፡ ሰዎችን የመያዝ ጥበብ የሌለው ሰው የጀመረውን ማንኛውንም ነገር ለመጨረስ ይከብደዋል፡፡ በህብረት መስራት መቻል የጀመርነውን ለማሳክት በጣም ቁልፍ ችሎታ ነው፡፡
5️⃣ በለውጥ ውስጥ መማር መቻል፡ ሁሉም ነገሮች እኛ በምንፈልገው ፍጥነትና መንገድ ብቻ አይሄዱም፡፡ አንዳንዴም ከጠበቅናቸው ውጪ የሆኑ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ ስለዚህ የጀመርነውን ነገር በማሳካት ሂደት ውስጥ ለሚገጥሙን ማንኛውን ነገር ራስን ማዘጋጀትና ራስን ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡
©Temu
ራስን መግለጽ መቻል

እስቲ ራሳችሁን ግለጹት? ተብለው ሲጠየቁ ብዙ ሰዎች “እንዴት እኔ ራሴን እገልጻለሁ ሌሎች ሰዎች ይግለጹኝ እንጂ” ይላሉ፡፡ ይህ ትክክለኛ መልስ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እኛ በእኛ ውስጥ ነው የምንኖረው እንጂ በሌሎች ሰዎች ውስጥ አይደለም፡፡ ሲቀጥል ሌሎች ሰዎች የራሳቸው ጉዳይና ህይወት ያለባቸው ናቸው ስለዚህ እኔን በደንብ መግልጽ አይችሉም፡፡

ሰዎች ስለኛ የሚናገሩት ያሳየናቸውን ባህሪ ብቻ ነው፡፡ ይህን ሊያዉቁ የሚችሉት ደግሞ ለጅም ግዜ አብረናቸው ካሳለፍን ነው፡፡ አንዳንድ ባህሪያቶች ደግሞ የተለዩ ሁኔታዎችን ጠብቀው ነው የሚገለጹት ስለዚህ ሰዎች ስለኔ ይናገሩ የሚለው የሚያዋጣ አይደለም፡፡
ስለራስ መናገርም በኩራት መንፈስ ራስን መካብ አይደለም፡፡ እኛ ምን አይነት ሰው እንደሆንን ስለራሳችን የምናውቀውን መንገር ማለት ነው እንጂ ራስን መስቀል ማለት አይደለም፡፡

ለምሳሌ አንድ ሰው እኔ ስሜቴ ቶሎ ቶሎ የምቀያየር አይነት ሰው ነኝ ብሎ ራሱን ቢገልጽ ተገቢነት አለው፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለውን ማንነቱን ነው የነገረን፡፡ ስለዚህ ራስን መግለጽ አሁን ላይ ያለንን ባህሪና ማንነት መንገር ማሳየት መቻል ነው፡፡

በእርግጥ ከራሱ ጋር ያልተገናኘና ስለራሱ ማንነት አስቦ ለማያውቅ ሰው ይህ ጥያቄ ከባድ ነው፡፡ የዘወትር ትኩረቱ በሰዎችና በሁኔታዎች ላይ ብቻ ለሆነ ሰውም ቢሆን ይህን ጥያቄ መመለስ አይችልም፡፡

ራስን መግለጽ ራስን ከማወቅ ከጥሎ የሚመጣ ችሎታ ነው፡፡ ስለዚህ ራሱን ያወቀ ሰው ብቻ ነው ራሱን መግለጽ የሚችለው ማለት ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች እኛ ለተናገርነው ማንነታችን ማረጋገጫ የሚሰጡ አካላቶች ናቸው እንጂ ስለኛ ከእኛ የተሻለ የሚገልጹ አይደሉም፡፡
ራሰን መግለጽ መቻል በጣም ጤናማና ትክክል የሆነ ችሎታ ነው፡፡


©ተመስገን አብይ
15 ወርቃማ #አባባሎች! ሼር
ቴሌግራም ቻናል - @PSYCHOET

1) ምቀኞች መብዛታቸው በስኬት መንገድ ላይ የመሆንህ ምልክት ነው!

2) #ወንድ #ልጅ እናቱ በሕይወት እስካለች ድረስ #ሕፃን ነው..ለእናቱ!

3) በፈተና ላይ አለመታገስ ሌላ #ፈተና ነው!

4) #ፈገግታ ቃላት የሌለው መልካም ንግግር ነው!

5) ካንተ የባሰ አለና አመስግን ፈገግ በል!

6) ትንሽን ለመስጠት አትፈር ምንም አለመስጠት ከሱ የባሰ ነውና!

7) የተሸናፊዉ #ፈገግታ ያሸናፊውን #ደስታ ይቀንሳል!

8) የሁሉን #ሰው ውዴታ ማግኘት ሊደረስበት የማይቻል ግብ ነው!

9) #ነፍስ በኩራት ስትሞላ ጎደሎ የመሆኗ መገለጫ ነው!

10) ኩራተኛ ሰው ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ሌሎችን ትንሽ አድርጎ እንደሚያይ ነው ነገርግን እሱንም ትንሽ አድርገው እንደሚያዩት አያውቅም!

11) ብዙ ጊዜ በጉጉት ከምንጠብቀው ይልቅ ድንገት የምናገኛቸው ነገሮች ውብ ናቸው እኛ ከለፋነው ጌታ የፃፈው መልካም ነውና!

12) ግኡዝ የሆኑት ውሃና አፈር ለእፅዋት አግልጋይ ናቸው ፤ እፅዋቶች ደግሞ ለእንስሳት ያገለግላሉ እንስሳት ፣እፅዋትና ግኡዛን ደግሞ የሰውን ልጅ ያገለግላሉ ... በተቃራኒው የሰው ልጅ ወደታች ወርዶ ለግኡዛን አገልጋይ (አምላኪ) መሆን ከጀመረ ያኔ ከነሱ የባሰ ይሆናል።

13) ብዙ ሰው ልጅ ለዘለዓለም እንደሚኖር ሆኖ ይለፋል አንድ ቀን ሳያልፍለት ይሞታል!

14) በሕይወት ትልቁ ስኬት የሕይወትን ትርጉም ማግኘትና አላማ ያለው ኑሮ መኖር ነው፡፡

15) በዚህ ቦታ .... ካነበባችሁት ፣ ከሰማችሁት ፣ ከምትከተሉት እምነት የምትወዱትን አባባል በcomment አሳውቁኝና ሌሎችም ያንብቡት፡፡

ሜሎሪና መጽሐፍ
#Share ይደረግ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
#ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት

(Social Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ)
==================
1. ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም
"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
============

6. አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።
9. ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
===================

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
==========================

16. ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ 
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት
በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!

ሳይኮሎጂ  ፔጅን #Like በማድረግ ቤተሰብ ኹኑ

@psychoet
©Abraham Tsehaye
ትስማማላችሁ?
ሀምሌ 3፣ 2015
ሜሎሪና መጽሐፍ ከወጣ ዛሬ ድፍን 3 ዓመት ኾነው።😃
በመጀመሪያ፥ በብዙ ሰዎች በመነበቡ እግዚአብሔርን አመሠግናለሁ። በመቀጠልም፥ አንብባችሁ መልካም አስተያየትና ትችታችሁን ለለገሳችሁኝ በሙሉ እግዚአብሔር ክብረት ይስጥልኝ ማለት እፈልጋለኹ።

በቀረው፥ ሜሎሪና ቁጥር ሦስትን በዚህ ዓመት ክረምት ላይ የማውጣት እቅድ እንደነበረኝ በተለያዩ ሚዲያዎች ስገልጥ የነበረ ቢኾንም፣ በተለያዩ ከመጽሐፋ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ግላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ምክንያት ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ወደ ቀጣዩ ዓመት ከገና በዓል አካባቢ ለማውጣት ወስኛለሁ። እወዳችኋለሁ ❤️
@psychoet
……… በጣም ገራሚ ታሪክ

      😍 ትንሿ ቆንጅዬ ልጅ ሁለት አፕል እንደያዘች እናቷ መጣች ።
        እናትም " የኔ ጣፋጭ አንዱን ለኔ ለእናትሽ ትሰጪኛለሽ ?" ስትል በትህትና ትጠይቃታለች ።
      ልጅም ትኩር ብላ ከተመለከተቻት በኋላ አንዱን አፕል ግምጥ አደረገችው ። ቀጠለችና ሁለተኛውንም ደገመችው 😳 እናት በልጇ ሁኔታ ደንግጣ ፍዝዝ ብላ ቀረች ።
             ስሜቷን በቁጣ ልታሳያት ብትሞክርም ድንጋጤው ከለከላት ☺️እንዴት በእኔ በእናቷ ትጨክናለች …? ብላ አሰበች ።
   
           በዚህ መሀከል ልጅ የገመጠችውን አንዱን ለእናቷ እያቀበለቻት "እንኪ ማሚ ይበልጥ የሚጣፍጠው ይሄኛው ነው ።" አለቻት ። እናት ያልጠበቀችውን ክስተት በማየቷ ልጇን አቅፋ ተንሰቅስቃ አለቀሰች 😍

መልካም ቀን 💕

@psychiet
አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ⛔️⛔️⛔️
ሁላችሁም በየግሩፑ #ሼር አድርጉት

በእነዚህ ሳምንታት በጓደኞቻችሁ ወይም በግሩፕ የሚላኩ ይሄን የመሰሉ መልዕክቶች ቴሌግራማችሁን ከሚጠልፉ ሰዎች የሚላኩ ሲኾን Linkun ከፍታችሁ ከገባችሁ የእናንተንም ቴሌግራም ጠልፈው ለሌሎች ወዳጆቻችሁ መልዕክት ይልካሉ። ስለዚህ እንደዚህ አይነት መልዕክት ከደረሳችሁ
1. Linkun እንዳትከፍቱት
2. የላከውን ሰው ካወቃችሁት ደውላችሁ ቴሌግራሙ እንደተጠለፈ ንገሩት

እባካችሁ ብዙ ሰው በዚህ እየተሸወደ ስለኾነ ይሄንን ማስጠንቀቂያ በየግሩፑ #ሼር አድርጉ።

@psychoet
ግጭትን ማስተናገድ መቻል

“እኔ ከማንም ሰው ጋር መጣላትም ሆነ መቀያየም አልፈልግም!” ሲሉ የምንሰማቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ከሰዎች ጋር አብረን እስከኖርን ድረስ ደግሞ ከግጭት መራቅ አንችልም፡፡

ግጭት እንዳይፈጠር ከመታገል ይልቅ ግጭትን የምናስተናግድበትን አቅም መፍጠር ነው ያለብን፡፡

ግጭት ለምን ያስፈልጋል?

1️⃣ ግንኙነትን ለማደስ ያስፈልጋል፡፡
2️⃣ ልዩነትን ለማወቅና ለማክበር ያስፈልጋል፡፡
3️⃣ ያመንበትን ነገር እንድናሳይ እድል ይሰጠናል፡፡
4️⃣ መተማመንን ይፈጥርልናል፡፡
5️⃣ አቅማችንን ለመፈተሸ ይረዳናል፡፡
6️⃣ ሁሌም የሚፈጠር ጉዳይ መሆኑን እንድንረዳ ይጠቅመናል፡፡ 

ከግጭት ለመሸሽ ከመመሞከር ይልቅ ያመንበትን ነገር ለማሳየት መሞከር የተሻለ ደስታን ይፈጥርልናል፡፡

ግጭት ሁሌም ያለ መልካም ነገር ነው፡፡

ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት!

ተመስገን አብይ Psychologist
2024/09/27 09:26:59
Back to Top
HTML Embed Code: