Telegram Web Link
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል
በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
1. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ$ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማቅረብ
2. በ12ኛ ክፍል ውጤት የምታመለክቱ አመልካቾች ከ2010-2015ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
3. ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ2010-2014ዓ.ም. በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
4. ለዲፕሎማ ወይም ደረጃ 4 አመልካቾች በ2015ዓ.ም. ቅበላ አይኖረንም
ማሳሰቢያ፡-
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤
4. ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
5. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
6. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው ያመለከቱ ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የምዝገባ ቀን፡ ከየካቲት 10 እስከ ከየካቲት 16 2015ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ ፡ በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር
#ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት

(Social Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ)
==================
1. ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም
"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
============

6. አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።
9. ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
===================

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
==========================

16. ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት
በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!

ሳይኮሎጂ ፔጅን #Like በማድረግ ቤተሰብ ኹኑ

@psychoet
ስልጠናው ላለፉት 4 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙ መቶዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ስልጠና #የመጨረሻዉ ዙር ነው፡፡
የመጨረሻ ዙር LIT (Life Improvement Training) ስልጠና (13ኛ ዙር) የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንትየካቲት 25 ይጀምራል!
ስልጠናው ላለፉት 4 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙ መቶዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ስልጠና የመጨረሻዉ ዙር ነው፡፡
🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን 🔖ስኬታማ የሕይወት ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀት፣ ድብርትንና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!
ስልጠናው ለ5 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ይሰጣል፡፡ ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ 3-6 ➋ቅዳሜ 8-11
እሑድ 3-6 ➍እሑድ 8-11
ባሉን ውስን ቦታዎች በተመቻችሁ ፈረቃ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡ በዚህ ሳምንት ይጀምራል ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
👉ክፍያ :- ( የመመዝገቢያ፣ የሰርተፊኬት ፣ የ15 ሰአት የስልጠና ጨምሮ ) - 1000 ብር ነው
🏠አድራሻ:- 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221
🖼🎁ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ
የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡ ሰው እንደ ሰው ፣ ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ያለንበት ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ከተለያዩ የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

✍️አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

✍️ አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

✍️ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

✍️ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

✍️አወንታዊ ነገሮችን ማሰብ

ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

www.tg-me.com/psychoet
መልካም ቀን ! #Share_it
#ይቅርታ_እንዴት_እንጠይቅ?
www.tg-me.com/psychoet

ምን ያህሎቻችን ነን ይቅርታ ባለማረግ እና ይቅርታ ባለመጠየቅ ደስታችንን እየቀነስን ያለን ?

ይቅርታ እንዴት እንጠይቃለን በሚለው ዙሪያ ትንሽ ለማለት ዳዳው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሌላውን ሰው አስቀይመው ወይም ጥፋት አጥፍተው ይጸጸታሉ፡፡ ነገር ግን መጸጸትና ይቅርታ መጠየቅ ይለያያሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይቅርታቸውን ከአንገት በላይ ያደርጉና ተበዳዩን አዛኝ መስለው በከንፈር መጠጣ (lips service) ይሸነግሉታል፡፡ አልያም መልሰው እንደሚያጠፉ እርግጠኛ እየሆኑ እንኳን የይስሙላ ይቅርታ ይጠይቃሉ፡፡ ሺህ ግዜ እያጠፋ ከስህተቱ ለማይማር ሰው ይቅርታ ትርጉም የለውም፡፡ እንዲሁም ይቅርታን ለጥፋቱ መሸሸጊያ የመጨረሻ ምሽግ ያደርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የሌላውን ሰው ልብ ያደማል፡፡ ይቅርታው በተግባር ለውጥ ስለማይታጀብ ከአፍ አይዘልም፡፡ የዚህ ስሜት በእራሳችን ደርሶ ካላየነው በስተቀር ህመሙ አይሰማንም፡፡ ታዲያ አሳማኝ ይቅርታ እንዴት መጠየቅ ይቻላል?
አንድሪያ ብራንድ የተባለች ሳይኮሎጂስት ከዚህ የሚተሉት ስድስት ነጥቦች ይቅርታን ለመጠየቅ ጠቃሚዎች ናቸው በማለት ትመክራለች፡-

1.ከልብ የመነጨ ይቅርታ መጠየቅ፡- የተበዳይ የመንፈስ ስብራት እኛም በግለሰቡ ቦታ ብንሆን ምን ያህል እንደሚሰማን በማሰብ ከውስጥ በመነጨ ስሜት ይቅርታን መጠየቅ፡፡

2.ስለበደሉት ነገር ዕውቅና መስጠትና ዳግመኛ ላለመበደል ኃላፊነትን መውሰድ፡- ስለአጠፉት ጥፋት እቅጩን መናገር “አውቃለሁ እንዲህ ማድረግ አልነበረብኝም ፤ እኔ በእንተ ቦታ ብሆን ምን ያህል እንደሚሰማኝ እረዳለሁ፡፡ እባክህን ይቅር በለኝ!” በማለት ጥፍትን ለማረም ዝግጁ መሆንን ማሳየት፡፡

3.ዳግመኛ ላለመበደል ቁርጠኛ መሆን፡- የበደላችሁት ሰው ከጥፋታችሁ እንደተማራችሁ እንዲያውቅ ማድረግ፡፡ ይህንንም ዕለት ተዕለት በሚደረግ አግባቦትና ተግባር በግልጽ ማሳየትና ምንም ለውጥ ያላሳየን እንደሆን ወዳጆቻችን በግልጽ ቅሬታቸውን እንዲገልጹ ማድረግ፡፡

4.ይቅርታ የምትጠይቁት ሰው ለእናንተ ምን ያህል እንደሆነ መግለጽ፡- ከበደላችሁት ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በማድነቅ መግለጽ፡፡

5.ይቅርታ መጠየቅ፡- ይቅርታ መጠየቅ በሁለታችው መሃል ስላለው ግንኙነት አስፈላጊነት የሚያስረዳ ሲሆን፤ በምላሹ ተበዳይ ይቅርታ ለማድረግ ጊዜን ይፈልግ ይሆናል እንደ ጉዳቱ መጠን፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ሁኔታዎች ይቅር የሚባሉ ነገር ግን በደሉ ሊረሳ የማይችል ስለሚሆን፡፡ “Forgiven but never forgotten” እንዲል የባህር ማዶ ሰው፡፡

6.ለውጥን በተግባር ማሳየት፡- “የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” እንደሚባለው በአገረኛው ዘይቤ፤ ያጠፉትን ጥፋት ዳግመኛ ላለመተግበር ለእራስ ቃል ታማኝ መሆን፡፡ ይህም የአእምሮ ደውል በመውስጣችን በማቃጨል “እንዲህ ላለማድረግ እኮ እንዲህ ብለህ ቃል ገብተሃል” በተግባር ቃልህን አሳይ በማለት፡፡

በደል ያቆስላል ልብንም ይሰብራል ፤ ይቅርታ ግን ቁስልን ይሽራል የተሰበረ ልብንም ይጠግናል፡፡ ይቅርታ እንታረቅ! መልካም ጊዜ!

(አንቶኒዮ ሙላቱ)
©zepsychologist

www.tg-me.com/psychoet
በፍትህ በፍቅርና በይቅርታ የመኖር ዘመን ይሁንልን ፡፡
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ተቋርጦ የነበረው የዩቲዩብ ፕሮግራማችን በእናንተ ጥያቄ ዳግም ጀምሯል https://youtu.be/vTFZ4IM6jrg»
ስለ ለውጥ ካሰባችሁ ይህ ቪዲዮን እንድታዩ እመክራለሁ
1. ለምን ብዙዎቻችን መለወጥ እየፈለግን ያቅተናል 🤴
2. በአጭር ጊዜ ለመለወጥስ ማድረግ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው?*👸
https://youtu.be/ADjhpUzCkmM
ጤናማ ትዳር = ጤናማ ሕይወት!
ላገቡ፣ ላላገቡና ለማግባት በደጅ ላይ ለሚገኙ . . . በበርካታ ጥናቶች እንዲህ ይሉናል፡- አንድ ሰው ከትዳር አጋሩ ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ በሆነ ቁጥር የዚያ ውጤት በእድሜው ርዝመት ላይ ይንጸባረቃል፡፡
የሰመረ ትዳር ያላቸው ሰዎች ጤንነታቸው፣ ደስተኛነታቸውና ያላቸው ሙሉ የመሆን ስሜት ከሌሎቹ የተሻለ ነው፡፡ እነዚህ ሶስት ወሳኝ ሁኔታዎች ደግሞ ረጅምን እድሜ ጠግበው እንዲያሳልፉ ያግዛቸዋል፡፡
ያላገባችሁ ከሆነ የዚህን ጥናት ውጤት በመውሰድ የምታገቡት ሰው ማን ሊሆን እንደሚገባው በሚገባ አስባችሁበት ወደትዳር እንድትገቡ እንደማንቂያ ደውል ተጠቀሙበት፡፡
የወደፊት ታሪካችሁን ለጥሩ ወይም ለመጥፎ የመቀየር ጉልበት ካላቸው ምርጫዎችና ውሳኔዎች መካከል የትዳር አጋር ጉዳይ ቀዳሚው ነው፡፡
ይህንን ለመፈተሽ ከፈለጋችሁ ገና በፍቅር ግንኙነት ላይ የሚፈጠሩ ነገሮች በስሜታችሁ ላይ፣ አንዳንዴም በአካላችሁ ላይ ያላቸውን ጫና መመልከት በቂ ነው፡፡
ያገባችሁ ከሆነ ደግሞ ከትዳር አጋራችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት በጤንነታችሁና አልፎም በእድሜያችሁ ላይ ይህ ነው የማይባል ስፍራ እንዳለው ለመገንዘብ ሞክሩ፡፡
ስለዚህም፣ የግንኙነታችሁን መልካም ጎን በዚያው እንድትቀጥሉበትና ያላችሁ ደካማ ጎን ላይ ደግሞ የማሻሻያ ስራን ለመስራት የምትችሉትን እንድታደርጉ ትመከራላችሁ፡፡
🔉Dr eyob
ማህበራዊ ፍርሀት ወይም በተለምዶ አይናፋርነትን እንዴት ማስወገድ እንችላለን?
✍️በሰው ፊት ማውራት ፣ ሀሳብ መግለፅ ይፈራሉ
✍️ሁሌ ሰው ምንይለኛል ብለው ይጨነቃሉ
✍️ሰው በተሰበበት መካከል አልፈው መሄድ ያስጨንቅዎታል
✍️ትንሽ ስታወሩ ሰውነታችሁ በፍርሀት ላብ ይጠመቃል


ይህ አጭር Video ለነዚህ ሁሉ መፍትሔና መልስ አለው ፡፡
የምንለቃቸው የስነልቡና Videoዎች ቶሎ እንዲደርሳችሁ YouTube ቻናላችንን Subscribe አድርጉ ፡፡ https://youtu.be/1MZrizp9nxw
ጥንካሬን ማወቅ

በዚህ ርዕስ ላይ ስልጠና ስሰጥ እስካሁን የተረዳሁት አንድ ነገር አለ፡፡ ብዙዎቻችን ስለ ጥንካሬያችን ሳይሆን ስለ ድክመታችን ብዙ እንደምናውቅ ነው፡፡ ይኸም ደግሞ ደካማ፣ የማንችልና የበታች እንደሆንን እዲሰማን አድርጎናል፡፡

ህይወታችንን ከፍ አድርገን ለመኖርም ድክመቶቻችንን ላይ ትኩረት ማድረግ እንደ መፍትሄ እንጠቀመዋለን፡፡ ይህም ብዙ ውጤት የማያመጣ መፍትሄ ነው፡፡

ስለ ድክመቶቻችን ብቻ በማሰብና ለማሻሻል በመሞከር ብዙ ጊዜያችንን ማጥፋት ውጤት የማያመጣ ከሆነ፤ ታዲያ ውጤት የሚያመጣው ምንድን ነው?

1️⃣ ስለ ድክመታችን የምናውቀውን ያህል ስለጥንካሬያችን ማወቅ አለብን፡፡ ምን ተሰጥኦ አለኝ? ምን ችሎታዎች አሉኝ? ምን ማድረግ ያስደስተኛል? ምን ነገሮች ላይ ሃላፊነት እወስዳለሁ? ራሳችንን ጠይቀን ጥንካሬዎቻችንን ማወቅ የመጀመሪያው መፍትሄ ነው፡፡

2️⃣ ድክመቶቻችንን መቀበል አለብን፡፡ ድክመቶቻችንን ለመቀየር ከመታገል ይልቅ መቀበልና ማወቅ በቂ ነው፡፡ ለመቀየር ስንታገል አቅማችንን ወደታች እያወረደብን ይመጣል፡፡

3️⃣ ጥንካሬዎችንን ካወቅን በኋላ በየቀኑ መጠቀም መቻል፡፡ ጥንካሬዎቻችንን የሚያድጉት በየቀኑ ስንጠቀምባችው ነው፡፡ ዛሬ የትኛውን ጥንካሬዬን ተጠቀምኩበት? ራስን መጠየቅ

4️⃣ አዳዲስ ጥንካሬያችንን መፈለግ፡፡ በየጊዜ የማናውቀውን ጥንካሬ እናገኛለን፡፡ ይህም የሚሆነው አዲስ ነገሮችን ስንሞክር፣ ከአዲስ ሰዎች ጋር ስንገናኝ፣ ስንወስን ወዘተ. ነው፡፡

ጥንካሬዎቻችንን ላይ ትኩረት አደርገን መስራት ከቻልን ድክመቶቻችንን ማሸነፍ እንችላለን፡፡

ከወደዳችሁትና ከጠቀማችሁ ሼር አድርጉት!

by @temuabiy www.tg-me.com/psychoet
ስማኝ ልጄ!!!!!!! ተነቦ ሼር ይደረግ

1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!

2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!
©ከFb የተገኘ
እንኳን ለብርሀነ ትንሳዬው በሰላምና በጤና አደረሳችሁ
በቴሌግራም @psychoet
#ውሸት

ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን???
ለምን እንዋሻለን ??

ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡

ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡

ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡

ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡

ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡

ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡

ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡

ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity)  እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡

የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን  የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና  ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም  ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………..

(በቁምላቸው ደርሶ)
©Zepsychologist
@psychoet
መልካም የሰራተኛ ቀን ይኹንላችሁ። ግን ደግሞ በተሰማራችሁበት ሥራ ስትለፉና ስትደክሙ ይሄንን 👆 እንዳትረሱ።
@psychoet
በፍቅር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ዋና ዋና መገለጫቸው አነዚህ ናቸው፡፡

❤️መቀበል፡ ሰዎችን፣ ሁኔታዎችን፣ ራሳቸውን ያለ ምንም ተጨማሪ ሃሳብ አሁን ባሉበት ላይ መቀበል የሚችሉ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ከማንም ሰው ጋር በምንም ሁኔታ ውስጥ መኖር እንደሚችሉ የሚሰማቸው ሰዎች ናቸው፡፡

❤️መረዳት፡ ሰዎችም ሃሳባቸውን እንዲገልጹ፣ አይታቸውን እንዲያካፍሉ፣ ምክንያታቸውን እንዲገልጹ እድል የሚሰጡ ናቸው፡፡ የተፈጠሩት ነገሮችም ለምን አላማ እንደሆነ ለማወቅ የበኩላቸውን ጥረት የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡ የራሳቸወን ሃሳብ ከመወርወራቸው በፊት መረዳትን  ማስቀደም ይችሉበታል፡፡

❤️ተፈጥሮን መውደድ፡ በፍቅር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እንደ ተፈጥሮ የሚመስጣቸው ሌላ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ በሰው አፈጣጠር፣ በውሃ፣ በእጽዋት፣ በእንስሳት፣ በአየር፣ በደመና፣ በዝናቡ ወዘተ እጅግ ይደመማሉ፡፡

❤️ለሁሉም፡ ማንን ታፈቅራላችሁ ብትባሉ ማንን ትላላችሁ? በፍቅር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉንም የሚል መልስ ነው ያላቸው፡፡ ሁሉም ነገር ፍቅር አለው፤ ፍቅር ይገባዋል ይላሉ፡፡ ለቀረባቸው፣ ላገኙት፣ ለገጠማቸው ሁሉ መልሳቸው ፍቅር ነው፡፡

❤️መፍቀድ፡ ራሳቸውን እንዲያፈቅርና ነጻ እንዲሆን ይፈቅዱለታል፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን በነጻነት ይቀርባሉ፡፡ ሰዎች የፈቀዱትን እንዲያደርጉ ይተዋቸዋል፡፡ በዙሪያቸው ያለ ነገር ሁሉ የፈቀደውን እንዲሆን መፍቀድ፣ እገዛቸውንም መለገስ ይችሉበታል፡፡ በዚህም ምክንያት በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተርፋሉ፡፡

❤️ራስን መሆን፡ በፍቅር የሚኖር ሰው ትኩረቱ ራሱን በመሆን ላይና በማሳደግ ላይ ነው፡፡ ሌሎች ሰዎችም ራሳቸውን እንዲሆኑ ያግዟቸዋል፡፡ ትክክለኛ ፍቅር ራስን በመሆን ውስጥ እንደሆነ ያውቃሉ፡፡

ታዲያ የፍቅር ሰው ናችሁ .. ጻፍልን

ተመስገን አብይ (Psychologist)
@psychoet
2024/09/27 11:16:49
Back to Top
HTML Embed Code: