Telegram Web Link
የትብብር ጥያቄ!
ይህንን መልዕክትና ጥያቄ ቢያንስ ባላችሁበት አንድ የቴሌግራም ግሩፕና ለአምስት ጓደኞቻችሁ አድርሱልኝ?
😔🙏😔

=======================
፩. በዚህ ምድር ላይ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ቢሆን ኑሮ አሁን ምን ታደርጉ ነበር?
፪. በጣም የምትወዱት/ የምታፈቅሩት ሰው ዛሬ የመጨረሻው ቀን ቢሆን ምን ታረጋላችሁ?
=======================

ይህንን ጥያቄ ሳትመልሱ እንዳትተኙ
መልካም አዳር!
@Psychoet
ትዕግስት ይኑርህ
ትዕግስት ይኑርሽ
15 ወርቃማ #አባባሎች!
------------------------ሼር
1) ምቀኞች መብዛታቸው በስኬት መንገድ ላይ የመሆንህ ምልክት ነው!

2) #ወንድ #ልጅ እናቱ በሕይወት እስካለች ድረስ #ሕፃን ነው..ለእናቱ!

3) በፈተና ላይ አለመታገስ ሌላ #ፈተና ነው!

4) #ፈገግታ ቃላት የሌለው መልካም ንግግር ነው!

5) ካንተ የባሰ አለና አመስግን ፈገግ በል!

6) ትንሽን ለመስጠት አትፈር ምንም አለመስጠት ከሱ የባሰ ነውና!

7) የተሸናፊዉ #ፈገግታ ያሸናፊውን #ደስታ ይቀንሳል!

8) የሁሉን #ሰው ውዴታ ማግኘት ሊደረስበት የማይቻል ግብ ነው!

9) #ነፍስ በኩራት ስትሞላ ጎደሎ የመሆኗ መገለጫ ነው!

10) ኩራተኛ ሰው ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ሌሎችን ትንሽ አድርጎ እንደሚያይ ነው ነገርግን እሱንም ትንሽ አድርገው እንደሚያዩት አያውቅም!

11) ብዙ ጊዜ በጉጉት ከምንጠብቀው ይልቅ ድንገት የምናገኛቸው ነገሮች ውብ ናቸው እኛ ከለፋነው ጌታ የፃፈው መልካም ነውና!

12) ግኡዝ የሆኑት ውሃና አፈር ለእፅዋት አግልጋይ ናቸው ፤ እፅዋቶች ደግሞ ለእንስሳት ያገለግላሉ እንስሳት ፣እፅዋትና ግኡዛን ደግሞ የሰውን ልጅ ያገለግላሉ ... በተቃራኒው የሰው ልጅ ወደታች ወርዶ ለግኡዛን አገልጋይ (አምላኪ) መሆን ከጀመረ ያኔ ከነሱ የባሰ ይሆናል።

13) ብዙ ሰው ልጅ ለዘለዓለም እንደሚኖር ሆኖ ይለፋል አንድ ቀን ሳያልፍለት ይሞታል!

14) በሕይወት ትልቁ ስኬት የሕይወትን ትርጉም ማግኘትና አላማ ያለው ኑሮ መኖር ነው፡፡

15) በዚህ ቦታ .... ካነበባችሁት ፣ ከሰማችሁት ፣ ከምትከተሉት እምነት የምትወዱትን አባባል በcomment አሳውቁኝና ሌሎችም ያንብቡት፡፡

Share
@psychoet
በአንድ መድረክ ላይ ቻርሊ ቻፕሊን አንድ ቀልድ ቀልዶ ሁሉንም ታዳሚሚዎች በጣም ይስቃቸዋል።ሁለተኛም ያንኑ ቀልድ ደገመዉ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሳቁ።ለሶስተኛ ጊዜ ያንኑ ቀልድ ደገመዉ፤በዚህን ጊዜ ግን ማንም አልሳቀም ነበር።ይህን ያየዉ ቻርሊ ለታዳሚዎቹ እንዲህ አላቸዉ........

"በአንድ ቀልድ ደጋግማችሁ ካልሳቃችሁ ለምን ታዲያ በአንድ ችግር ደጋግማችሁ ትጨነቃላችሁ።" ነበር ያላቸዉ።

በዚህች አለም ላይ ምንም ዘላቂ ነገር የለም ችግራችንም ቢሆን!!!!!!
©ማህበራዊ ሚዲያ

በደስታ #ሼር አድርጉት
@Psychoet
📌🔖አዲሱን አመት በብሩህ ተስፉ ይቀላቀሉ!
የ 2013 የመጨረሻ 8ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ነሀሴ 25 ጀምሮ ይሰጣል

ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ

የሚሰጡት ስልጠናዎች
📝ሳይኮሎጂን መረዳት
📝የሕይወትን አላማ ማወቅ
📝ለ2014 እቅድና ግብ አዘገጃጀት
📝ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
📝የስሜት ብልሀት
📝ተግባቦትና ፍርሀትን ማስወገድ

የስልጠና ቀናት ለተከታታይ 4 ቀናት(ያሉን ፈረቃዎች)
📆📆📆 ነሃሴ 25፣26፣27፣28
ማክሰኞ፣ ረዕቡ፣ ሀሙስ ፣ አርብ
4-6 ወይም 8-10

በኹለት ቀን ለመጨረስ
📆📆📆 ነሃሴ 29 እና 30
ቅዳሜና እሑድ
3-6 ወይም 7-10


🔔በአንድ ፈረቃ ጥቂት ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው በሚያመችዎት ፈረቃ ይመዝገቡ ፡፡

💸ክፍያ (የመመዝገቢያ ፣ የስልጠና ፣ የሰርተፍኬት ጨምሮ)- 500 ብር ብቻ

ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
በአካል ለመመዝገብ የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 219 (Nova Training Center)

ትርፋችን የሰው ህይወት መለወጥ ነው፡፡ 📖

@psychoet
#ክፍል_1
ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አርጉት !

Psychology - ሥነ ልቡና /Ψ/
ሥነልቡና በታሪኩ ውስጥ የተለያየ ትርጓሜ ይዞ የመጣ ሲሆን አሁን በደረሰበት የዕድገት ደረጃ ግን አብዛኞቹ ተመራማሪዎች የሚስማሙበት ትርጉም ይህን ይመስላል ፡፡

ሳይኮሎጂ ከሁለት የግሪክ ቃላት ሳይኪ እና ሎጎስ (Psyche & logos ) የሚሉ ቃላቶች የተወሰደ ነው ፡፡
❖(Psych )ሳይኪ | Mind (ነፍስ - አዕምሮ - መንፈስ) ሲሆን
❖(Logos) ሎጎስ | Disclosure (ገለፃ /ጥናት) ማለት ነዉ ፡፡

በዚህም መሰረት ሥነልቡና ማለት፦
ስለ #ባህሪይ እና #የአዕምሮ አሰራር ሂደት የሚያጠና #ሳይንስ ነው ፡፡

#ባህሪይ ስንል ማናቸውም የምናረጋቸዉና በአይን የሚታዩ ነገሮች ሲሆኑ
#የአዕምሮ አሰራር ሂደት ደግሞ በአይን የማይታይ ግን በተግባር የሚገለፅ ነዉ ፡፡
#ሳይንስ ስንል ሳይንስ የሚያልፍባቸውን ሂደቶች ስለሚያልፍ ነዉ እነርሱም (Emperical / በሙከራ የተረጋገጠና መመልከት የምንችለው ,
Objective / ከግል ስሜት ጋር ያልተያያዘና ከገሀዱ አለም ጋር የተገናኘ ,
Systematic / በስርአት የተቀረፀና የሚሰራ ,
Replicable / ውጤቱ ሆነ ሂደቱ በሌላ ሰው መደገም የሚችል) ናቸው ፡፡

ሌላው ሥነልቡና ማህበራዊ ወይስ ተፈጥሮአዊ ሳይንስ ነው የሚለው ጥያቄ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ባለንበት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም የትምህርት ተቋም እንደማህበራዊ ሳይንስ የሚታይና የሚሰጥ ሲሆን ባብዛኞቹ ባደጉት ሀገራት ግን ከህክምና ትምህርት ክፍል ስር የሚሰጥ በተፈጥሮአዊ ሳይንስ ስር ያለ ትምህርት ነው ፡፡
Social science is the scientific study​ of human society and social relationships. Whereas natural science deals with the physical world. By these definitions then psychology would fall under the category of a natural science.
https://www.thestudentroom.co.uk/showthread.php?t=4949812

ሥነ ልቡና አዕምሮን አያጠናም ይልቁንስ ስለ አዕምሮ አሰራር ሂደት እንጂ። (ስለአዕምሮ የሚያጠኑት ኒውሮሎጂስት እና ሳይካትሪስቶች ናቸዉ ፡፡ )

የሥነልቦና ትምህርት ዋና አላማ / ግብ (goal) አራት ናቸው እነርሱም ፦
1.ባህሪን መግለፅ (Describe )
2.ባህሪን ማብራራት (Explain)
3.ባህሪን መተንበይ (predict)
4.ባህሪን መምራት /መቆጣጠር (control )

ሥነልቡና (Psychology ) መገለጫ ምልክት (Symbol) ያለዉ ሲሆን ምልክቱ የግሪኩ 23ኛ ካፒታል ሊተር Ψ ሳይ (Psi ) ነዉ፡፡ የ ሳይ ምልክት የተገለበጠ "ሐ" ይመስላል ፡፡ በዚህ ምልክት ' Ψ ' ላይ ያሉት ሶስት አምዶች አንዳንድ ጠቢባን በነዚህ ሶስት ነገሮች ይመስሏቸዋል
1. ነፍስን #Soul
2. ሀሳብን(አዕምሮ) #Mind
3. መንፈስን #Spirit

❖❖______❖______❖❖
Source:- personal knowledge from d/f text books But If you wish to read to Intro Books I can suggest
ምንጭ ፦ ካለኝ ዕውቀት ማለትም ከዚህ በፊት ከሰማኀቸው ፣ ከተማርኩት እንዲሁም ካነበብኩት ለአንባቢ እንዲቀር አድርጌ በአማረኛ የፃፍኩት ነው ። ጠሩ መጸሐፎች የሚፈልግ መጠቆም እችላለሁ ፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል፡፡ ማንኛውም ጥያቄ / ተጨማሪ ሀሳብ Comment ማረግ ይቻላል ፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት እንዚህን እናያለን ፦
1. በሥነልቡና ስር ያሉ ዋና ዋና ሙያዎች (Sub fields )
2. የሥነልቡና ታሪካዊ አመጣጥ ፣ ከፍልስፍና ጋር ያለው ቁርኝትና በዘርፉ ብዙ ሚና ያበረከቱ ሰዎች
3. እንዴት ነገሮችን እንደምናስታውስና እንደምንረሳና ከዚህ ጋር ተያይዞ መርሳት የሚባል ነገር በሥነ ልቡና አለ ወይ
4.ሥነ ልቡና ስለ ህልም ምን ይላል ብለን እንመለከታለን

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የTelegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!

Join
@psychoet
@psychoet
@psychoet
ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ መጨነቅን ለማቆም ቀላል ዘዴዎች
Telegram www.tg-me.com/psychoet
አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎችም #Share ያድርጉ

‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!

1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡- እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም አንችልም፡፡

2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::

3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:- እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡

4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን፡፡

5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው ”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን መረዳት ይጠበቅብናል::

6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡

7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ: ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::

8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ) በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡

9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም) ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን ልናጣ እንችላለንና፡፡

10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!

(በአለበል አዲስ)
©Zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ነገ ይጀምራል ! 📌🔖አዲሱን አመት በብሩህ ተስፉ ይቀላቀሉ!
የ 2013 የመጨረሻ 8ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ነሀሴ 25 ጀምሮ ይሰጣል

ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ

የሚሰጡት ስልጠናዎች
📝ሳይኮሎጂን መረዳት
📝የሕይወትን አላማ ማወቅ
📝ለ2014 እቅድና ግብ አዘገጃጀት
📝ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
📝የስሜት ብልሀት
📝ተግባቦትና ፍርሀትን ማስወገድ

የስልጠና ቀናት ለተከታታይ 4 ቀናት(ያሉን ፈረቃዎች)
📆📆📆 ነሃሴ 25፣26፣27፣28
ማክሰኞ፣ ረዕቡ፣ ሀሙስ ፣ አርብ
4-6 ወይም 8-10


በኹለት ቀን ለመጨረስ
📆📆📆 ነሃሴ 29 እና 30
ቅዳሜና እሑድ
3-6 ወይም 7-10


🔔በአንድ ፈረቃ ጥቂት ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው በሚያመችዎት ፈረቃ ይመዝገቡ ፡፡

💸ክፍያ (የመመዝገቢያ ፣ የስልጠና ፣ የሰርተፍኬት ጨምሮ)- 500 ብር ብቻ

ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
በአካል ለመመዝገብ የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 219 (Nova Training Center)

ትርፋችን የሰው ህይወት መለወጥ ነው፡፡ 📖

@psychoet
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት
1. ጥሩ አድማጭ መሆን

ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡

2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን

በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡

3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ

የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡

4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ

ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡

5. አቀማመጥን ማስተካከል

ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡

6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት

እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡

7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ

ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡

8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡

9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር

በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡

ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet

የቻናሉ ቤተሰቦች በቅርቡ የኅትመት ብርሃን ያየውና በአስገራሚ የታሪክ ፍሰቱና ስነልቦናዊ ምክሮቹ የቀረበው የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ተከታታይ ልብወለድ መጽሐፍ "ሜሎሪና" እንድታነቡ እጠይቃለሁ ፡፡ ያነበቡት ኹሉ ወደውታል ፣ ተምረውበታል ፣ ሕይወትን ዘወር ብለው አይተውበታል ፡፡ መጽሐፉን ( በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መደብሮች ያገኙታል ) ።

ለሌሎች #Share በማረግ ተግባቦታችንን እናሳድግ
ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet
©Zepsychology
ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት
Telegram www.tg-me.com/psychoet

ግጭት የአንድ ሰው ድርጊት ወይም አመለካከት ሌላውን ሲረብሽ የሚፈጠር ሲሆን ይህም በቤተሰብ ፤ በጓደኛ ፤ በስራ ቦታ፤ በጋብቻ.. ወዘተ መካከል ሊከሰት ይችላል፡፡ የግጭቱ ሁኔታ መክረር ወይም በቀላል መፈታት  እንደተጋጪዎቹ ባህርይ ፤ግንኙነትና  የግጭቱ ዓይነት ይለያያል፡፡ የተለያዩ የግጭት ዓይነቶችን በአራት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት (Intra-personal)

ምንም እንኳን የተለያዩ የግጭት ዓይነቶች ቢኖሩም በማኅበረሰባችን ውስጥ የላቀ ትኩረት የሚሰጣቸው ከውጫዊ አካላት ጋር ለሚፈጠሩ ግጭቶች ነው፡፡ ይሁንና ሰው ከራሱ ጋር የሚፈጥረው ግጭት ከሌሎች ግጭቶች በተለየ መልኩ አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን እንደሚያስከትል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት በተለያዩ  ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው ሰው በህይወት ዘመኑ በሚፈጽማቸው ስህተቶች ከህሊናው ጋር የሚፈጥረው ግጭት ነው፡፡

ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር ግጭት (Inter-personal)

በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የግጭት ዓይነት ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ሲሆን ይህም በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዋነኛዎቹ የዚህ ግጭት መንስኤዎች መካከል በሃሳብ አለመግባባት ፤ ግትርነት ፤ ነገሮችን በትዕግስት አለማሳለፍ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡

በአንድ ቡድን አባላት መካከል የሚፈጠር (Intra-group)

ይህ የግጭት ዓይነት በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠር ሳይሆን ለአንድ ዓላማ በተመሠረተ ቡድን ውስጥ ባሉ አባላት መካከል ምክንያታዊና ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች የራስን አቋም በማጣት የሌላውን ሃሳብ ተከትሎ በመሄድና የተዛባ መረጃ በመያዝ ከሌሎች የቡድን አባላት ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡

በቡድኖች መካከል የሚፈጠር ግጭት (Inter-group)

የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሁለትና ከዚያም በላይ የሆኑ ቡድኖች በሚያገናኟቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተው መስራት ሳይችሉ ሲቀር ወይም አንዱ ሌላውን በበላይነት ማስተዳደር ሲፈልግ የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው የግጭት ዓይነቶች በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

*የአመለካከት ልዩነት
*የባህል ፤ አስተዳደግ ፤ የባህርይ ልዩነት
*የዓላማ እና የፍላጎት ልዩነት
*የስልጣን/የኃይል ልዩነት
*እውነታና ፍላጎት አለመስማማት

★የግጭት አፈታት ዘዴዎች

ማንኛውም ዓይነት ግጭት ለማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ሊዳርግ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ጊዜ የሚያጋጥሙትን ለግጭት የሚዳርጉ ሁኔታዎችን ከግጭት በራቀ መልኩ የመፍታት ክህሎትን ማዳበር ስኬታማ የሆነ ህይወት ለመምራት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ግጭትን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ ነጥቦች

1.የግጭቱን መንስኤ ለይቶ ማወቅ፡–

ግጭቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ መንስኤያቸውን ለይቶ ማወቅ ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግና በቀላሉ መፍትሄ ለማፈላለግ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ  ግጭት በሃሳብ አለመግባባት ቢፈጠር ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው ተጋጪው ካለው የአስተሳሰብ፤ የባህል ፤ የአስተዳደግ ፤ ወይም ከግለሰቡ የግል ባህርይ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ መቻል ግጭቱን በቀላሉ ለመፍታት ይረዳል፡፡

2.አማራጭ መፍትሄዎችን ማየት

ለተከሰተው የሃሳብ ልዩነት ወይም ግጭት እንደመፍትሄ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጭ መንገዶችን ማየት ግጭትን በቀላሉ ለመፍታት ያስችላል፡፡

3.ስሜታዊነትን ማስወገድ

አብዛኛውን ጊዜ በስሜታዊነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው የጎላ ነው፡፡

በመሆኑም ግጭት በሚነሳበት ወቅት እራስን ለመቆጣጠር እና ከስሜታዊነት የጸዳ ውሳኔ ለመወሰን ይቻል ዘንድ ግጭቱ ከተነሳበት አካባቢ በመራቅ ረጋ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

4.ስምምነት መፍጠር

 የተፈጠረውን አጋጣሚ አንስቶ ፊት ለፊት በግልጽ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እንደ አስፈላጊነቱ ሌላ ሦስተኛ አካል ገብቶ የሚያነጋግርበትን መንገድ በመፈለግ ከግጭት ይልቅ ስምምነት የሚፈጥርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል ፡፡

መልካም ቀን ተመኘሁላችሁ ፤ ሰላም!
©zpsychologist


Telegram www.tg-me.com/psychoet
እራስን ማክበር
www.tg-me.com/psychoet #Share

እውነት ነው እኛ ኢትዩጵያውያን ሰው አክባሪዎች ነን፡፡ግና ሰው ማለት ማን ነው? ሌሎች ሰዎች?  ወይስ እኔ እራሴ? እርግጥ ነው አምናለሁ እኛ ኢትዩጵያውያን እንግዳ አክባሪዎች ነን ፤በዕድሜ ጠና ያሉ አባቶችን እና እናቶችን እናከብራለን  ከመቀመጫጭን ብድግ ብለን “ኖሩ አባቴ” ብለን ወንበራችን እንለቃለን፡፡አሪፍ ባህል! ባህል እንግዲህ አንጻራዊ አይደል… እዚህ ለፈረንጆቹ ብድግ ብላችሁ ተቀመጡ ብትሏቸው ምላሹ ተቃራኒ ነው፡፡ በእኔ እይታ እንደተረዳሁት ከሆነ አረጋውያንን ለመርዳት ብትሞክሩ ውጤቱ እንደ ሀገራቸን “ተባረኩ“ “ክፉ አይንካችሁ” ሳይሆን ግልምጫ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም መረዳታቸውን ከጥገኝነት ጋር ስለሚያይዙት፡፡  ሁሉም ግን እንደዚህ ያስባሉ ማለት አይለደም፡፡ እንዲያው በዚያው ወግ ቢጤ አሰኝቶኝ ነው እንጅ የዛሬ ትኩረቴስ ሌላ ነው… እነሱም ጥገኝነታቸውን ያባሩ እኛም መልካም ባህላችንን እናበለጽግ፡፡ እንከባበር…ተባረኩ!

ሌሎችን ማፍቀር ከእራስ ማፈቀር ይጀምራል እንደሚባለው፤ ሌሎችን ማክበር እራስን ከማክበር ይጀምራል ብየ አምናለሁ፡፡ እራስን ማክበር ከእራስ ጋር ለመስማማት፤ ስለ እራስ መልካም አመለካከትና ስሜት ለማዳበር መሰረታዊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌጨው ባለዕዳ አይቀበለውም ይሉ አይደል አበው ሲተርቱ፡፡  ብዙ ጊዜ “እራስ” የሚል ጽንሰ ሃሳብ በጽሁፎቼ በተደጋጋሚ እጠቀማለሁ ምክኒያቱም የሁሉም ፀባይና ባህርይ መጀመሪያ እራሳችን ስለሆን፡፡ ደስ የሚለው ነገር እራሳችሁን ሁሌም ታገኙታላችሁ በቁጥጥራችሁ ውስጥ ስለሆነ መልካሙን አሊያም አሉታዊውን ነገር ማስረጽት ችላላቸሁ፡፡ ስለዚህ ለሚሰማን፣ለምናስበው፣ለምንተገብረውና ለአጠቃላይ ማንነታችን የላቀ ሀላፊነት አለን ማለት ነው፡፡ የችግሩ መንስኤ ሌላ ሰው ነው ብለን ምናምን ከሆነ ግን የቁጥጥር መጠናችን አናሳ ነው፡፡ የምንፈልገውን ለመሆን እራሳችን ላይ እንጀምር…

በአጭር አገላለጽ እራሳችን ማክበር እንለማመድ ምክኒያቱም ከሌሎች ግለሰቦች ጋር በሰላም ለመኖር መከባባር እንደሚያስፈልግ ሁሉ ከእራሳችን ጋር መልካም ግንኑነት ለመፍጠር እራሳችን ማክበር ቀዳሚ ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ወዳጃችሁ በሆነ ባልሆነ በእራሱ ጥፋት ከፍቅረኛው ጋር እየተጋጨ እንደሆነ ቢያማክራችሁ… በአብዛኛው እንዴት እንደዚህ አይነት ጥፋት ታጠፋለህ ብላችሁ አትቆጡትም፡፡ በእርጋታና በአክብሮት ትሰሙታላችሁ እንጅ፡፡ እናንተ ይህ ወዳጃችሁ ያጠፋውን ጥፋት ብትፈጽሙ ከእራሳችሁ ጋር እንዴት ባለ መንፈስ ነው የምትነጋገሩት?  በአክብሮት ልክ ሌሎች ግለሰቦችን እንደምታዋዩ ? ወይስ በብስጭትና በቁጣ? ስለማንኛውም ጉዳይ ከእራሳችን ጋር በምንነጋገርበት ጊዜ በአክብሮት መንፈስ ከሆነ ለነገሩ ተገቢ መፍትሄ እንዲሁም በጉዳዩ ምክኒያት የሚሰማንን መጥፎ ስሜት ይቀንሰዋል፡፡ ማድረግ የሌለብንን ነገር ስንፈጽም እራሳችንን በትሁት መንፈስ የማውራታችንን ጥቅም ለመረዳት ቆም ብላችሁ “ይህን የፈጸምኩትን ጉዳይ አከሌ ቢፈጽመው እንዴት ብዬ አዳምጠውና ምክር እለግሰው ነበር?” ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ይህ ባልንጀራችሁ ብትበሳጩበት እንዴት ነገሩን እንደሚያባብስበት መረዳት ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ እራሳችን በሆነ ባልሆነው የምናመናጭቅ ከሆነ እንደዚሁ ለችግሩ መፍትሄ ከስጠት ይልቅ ሚዛናዊ አስተሳሰባችን በማሳት የበለጠ ችግሩን እናባብሳለን፡፡

ሌሎችን ማክበር እራስን ከማክበር ይጀምራል ! ሰላም!

አሸናፊ ካሳሁን
©zepsychologist
የቅዳሜና የእሑድ ስልጠና አንድ ቀን ቀረው፡፡

📌🔖አዲሱን አመት በብሩህ ተስፉ ይቀላቀሉ!
የ 2013 8ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ነሀሴ 29 እና 30 ጀምሮ ይሰጣል

ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ

የሚሰጡት ስልጠናዎች
📝ሳይኮሎጂን መረዳት
📝የሕይወትን አላማ ማወቅ
📝ለ2014 እቅድና ግብ አዘገጃጀት
📝ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
📝የስሜት ብልሀት
📝ተግባቦትና ፍርሀትን ማስወገድ

የስልጠና ቀናት ለተከታታይ 2 ቀናት(ያሉን ፈረቃዎች)

በኹለት ቀን ለመጨረስ
📆📆📆 ነሃሴ 29 እና 30
ቅዳሜና እሑድ 3-6 ወይም 7-10


🔔በአንድ ፈረቃ ጥቂት ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው በሚያመችዎት ፈረቃ ይመዝገቡ ፡፡

💸ክፍያ (የመመዝገቢያ ፣ የስልጠና ፣ የሰርተፍኬት ጨምሮ)- 500 ብር ብቻ

ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
በአካል ለመመዝገብ የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 219 (Nova Training Center)

ትርፋችን የሰው ህይወት መለወጥ ነው፡፡ 📖

@psychoet
"ብልህ ሰው የትም ቢሆን መፍትሔ አያጣም!"

በአንድ ከተማ የሚኖር አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ነበር፡፡ በጓሮው በሚገኘውን ማሳ ቆፍሮ ድንች መትከል ፈልጎ እርጅና ተጫጭኖታልና አቅሙ አልፈቀደለትም፡፡ ሊረዳው የሚችለው ብቸኛ ልጁ ደሞ እስር ቤት ነው የሚገኘው፡፡ እናም አባት ለልጅ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፈ፡፡

"ውዱ ልጄ ምንም ጥሩ ስሜት አየተሰማኝ አይደለም፤ ምክንያቱም የድንቹን ማሳ መቆፈር አልቻልኩም፡፡ አለመቆፈሬን አልወደድኩትም፤ ምክንያቱም እናተህ አትክልት በጣም ነበር የምትወደው፡፡ አንተ እስር ቤት ባትሆን አውቃለሁ ትቆፍርልኝ ነበር ፤ አባትህ"

በቀጣዩ ቀን አባት አጠር ያለ ፁሁፍ ደረሳቸው፡፡ "በፈጣሪ ስም ይዤካለው አባ ጓሮውን እንዳትቆፍረው፤ ሽጉጡን የቀበርኩት እዚያ ነው"

ከሰዓታት በኀላ በደርዘን የሚቆጠሩ የFBI መርማሪዎችና ፖሊሶች የሽማግሊውን ጓሮ በሙሉ በቁፋሮ ምስቅልቅሉን አወጡት፤ ነገር ግን ምንም ሽጉጥ እዛ አልነበረም፡፡

አባት በጣም ግራ በመጋባት አጠር አድርገው ለልጃቸው ምን እንደተፈጠረ እና ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፃፉለት፡፡

ልጅ "አሁን ድንችህን ትከል አባ፤ ከዚህ ሁኜ ላደርግልህ የምችለው ነገር ቢኖር ይህን ብቻ ነው" ብሎ ፃፈላቸው፡፡

ያለንበት ነባራዊ ሁናቴ እኛን ሊወስነን አይገባም!📡📡 📡 📡 📡
#በጽሑፉ ፈገግ ያለና የተመቸው #Share ያድርግ
©ማኅበራዊ ሚዲያ
@psychoet
ሰው መሆን በቂ ነው!

አንድ ቀን አንድ ሰው በድንገት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀና መውጣትም አልቻለም፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ደክሞት በጉድጓዱ መካከል ቁጭ እንዳለ …

• ከንፈር መጣጭ ሰው አየውና - “ሁኔታህን ሳስበው በጣም በሃዘን እሞላለሁ” ብሎት ሄደ፡፡

• ተመራማሪ ሰው አየውና - “ይህ ጉድጓድ ከተማ መሃል ሆኖ ሰው መውደቁ አያስደንቅም” ብሎት ሄደ፡፡

• ፈራጅ ሰው አየውና- “ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው እንደዚህ ሊወድቁ የሚችሉት” ብሎት ሄደ፡፡

• ነጭናጫና አጉረምራሚ ሰው አየውና- “እኔ ወድቄ የነበረበትን ጉድጓድ አላየህ” ብሎት ሄደ፡፡

• አነቃቂ ንግግር አስተማሪው አየውና- “በራስህ ብታምን ከዚህ ትወጣለህ” ብሎት ሄደ፡፡

• ዘረኛ ሰው አየውና - “የምን ሃገር ሰው ነህ?” በማለት ከጠየቀው በኋላ የእርሱን ቋንቋ ስላልተናገረ ጥሎት ሄደ፡፡

•ውሸተኛ የሀይማኖት ሰው አየውና - " የኔ እምነት ተከታይ ብትሆን አወጣህ ነበር " ብሎት ሂደ፡፡

• በመጨረሻ ይህንን ሁሉ ድራማ ሲመለከት የነበረ አንድ ጨዋ ጎልማሳ ሰው ከብዙ ጥረት በኋላ እየሳበ አወጣው ፡፡


ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? በእርግጥ ሰውነት ከሁሉ ይበልጣል ፡፡

ምንጭ :- ከዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

በቅንነት ሼር ያድርጉ👇
http://www.tg-me.com/psychoet
ነፃ የስልጠና እድል ለኮምፒዩተር እና አይቲ ተማሪዎችና ባለሙያዎች!

የግማሽ ቀን #የነፃ ሳይበር ሴኩሪቲ ስልጠና ከእንግሊዝ አገር በመጡ ባለሙያ ተዘጋጅቶላችኀል፡፡
#Free Cyber Security Awareness Training

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ለስልጠናው ቦታ ለማሲያዝ ቀድመው ይደውሉና ይመዝገቡ
+251912383480

🗓Date : Sunday September 5,
2:00-5:00 Pm afternoon
የስልጠና ቀን : እሑድ ነሀሴ 30- ከሰዓት (8-11)

🏠Venue - Sheger college infront of alemayhu building . (Jacros adebabay to yerer )

አድራሻ : ሸገር ኮሌጅ ከአለማየሁ ህንጻ ፊት ለፊት (ከጃክሮስ አደባባይ ወደ የረር በሚወስደው መንገድ ላይ )

#ለሰልጣኞች በሙሉ የእውቅና ሰርተፊኬት እንሰጣለን

®Zcybersecurity in collaboration with Nova Training Center

በጣም ጠቃሚ ስለጠና ስለሆነኮምፒዩተር ላይ ለሚሰሩ ወዳጆቻችሁ መልዕክቱን በመላክ ይጥቀሟቸው፡፡
@Psychoet
2024/09/28 15:32:58
Back to Top
HTML Embed Code: