Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_2
ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አርጉት !
የፔጃችን ቤተሰብ ያልሆናችሁ ፔጁን Like በማረግ ጥሩ ትምህርት በነፃ ያግኙ ።

የሥነ ልቡና ሳይንስ ትምህርት እንዴትና በማን ተጀመረ ?

ሥነ ልቡና ከሰው ልጅ ፍጥረት ጀምሮ (በ Evolution ለሚያምኑ ደግሞ አሁን ያለው የሰዉ ዘር Evolv ካረገበት ጊዜ ጀምሮ ) በተለያየ የህይወት መስተጋብር ሲጠና ሲገለጥ ሲታወቅ የመጣ ሙያ ነዉ ፡፡ ይሁን እንጂ ሥነልቡና እራሱን እንደቻለ ትምህርት / ሳይንስ መጠናት የጀመረው ከ 19ነኛው ክፍለ ዘመን በኀላ ነው ፡፡
Wilhelm Wundt የሚባል ሰው በጀርመን ሀገር 1879 የመጀመሪያውን የሥነ ልቡና የሙከራ (ምርምር) ተቋም በ Leipzig ዩኒቨርስቲ ከፈተ ፡፡ ይህ በታሪክ የመጀመሪያው የሥነልቡና ምርምር ቤተሙከራ ለመሆን በቅቷል ፡፡ በዚህም ሳቢያ አቶ Wundt አብዛኛውን ጊዜ የሥነልቡና አባት በመባል ሊጠራ ችሏል ለዘመናዊ ሥነልቡና ጥናት መጀመርም መሰረት ሆኗል ፡፡

ከዚህ በፊት የፈረንሳዩ ፈላስፋ ሬኒ ዴካርት (1596 -1650) በስነልቡና ሙያ እድገትና ሙያውን ከፍልስፍና ትምህርት ራሱን ችሎ እንዲወጣ ብዙ ሚና የተጫወተ ነው ፡፡ በ Interactive dualism Theory ( በበይነግንኙነታዊ ሁለትዮሽ ፅንሰ ሀሳቡ ) የሰውን ልጅን አዕምሮ /አስተሳሰብ ከ ስጋው በመነጠል ያላቸውን መስተጋብር ለማጥናት የሞከረ ፈላስፋ ነው ፡፡ በ 17 ክፍለ ዘመንም ጆን ሎክ እና ቶማስ ሆብስ ለዚህ ሙያ እድገት ከፍልስፍናው ጎን ብዙ ሚና ተጫውተዋል ፡፡

#የሥነልቡና_ታሪካዊ_አመጣጥ

ሥነልቡና በታሪክ ዉስጥ በፍልስፍና ስር የሚጠና ሙያ የነበረ ሲሆን ትርጓሜውም ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋና እየተስተካከለ እራሱን ችሎ ወቷል ፡፡ የሥነልቡና ትምህርት እድገት በታሪክ ውስጥ በአራት ተከፍሎ ይታያል ። እነርሱም
1 ፡ Ancient Greekperiod / በጥንታዊ የግሪክ ክፍለጊዜያት
2 ፡ per-modern period / ቅድመ ዘመናዊነት ጊዜ
3 ፡ modern period / በዘመናዊነት ጊዜ
4 ፡ current status / አሁን ያለንበት (ድህረ ስልጣኔ እንዲሁም ተሻጋሪያዊ ስልጣኔ ) ዘመን

1.በጥንታዊ የግሪክ ክፍለጊዜያት የግሪክ ፈላስፎች ለዕድገቱ ብዙ ሚና አበርክተዋል ፡፡ ከነዚህም በጉልህ ተጠቃሾቹ ሶቅራጥስ ፣ ፕሌቶና አርስቶትል ናቸው ፡፡
በዚህ ጊዜ ሥነልቡና የሚጠናው ከነፍስ / አዕምሮ አንፃር ብቻ ነበረ ፡፡ እነዚህ ፈላስፎችም በስራቸው የሚያነሱት ስለ አዕምሮ እንጂ ስለ ባህሪ አልነበረም ፡፡

2.ቅድመ ስልጣኔ ዘመን በፊት ፡ ሥነልቡና ከፍልስፍና ተነጥሎ ለብቻው የወጣው በዚህ 1800ዋቹ ጊዜ ነበር ፡፡ ለዚህ ትልቅ ሚና ያበረከቱት Wilhelm Wundt and William James ናቸው ፡፡

3.በዘመናዊነት ጊዜ : በዚህ ዘመን ብዙ የስነባህሪ ተመራማሪዎች የመጡበት ጊዜ ሲሆን ሥነ ልቡናን ከአዕምሮ /ነፍስ በተለይ #ከባህሪ አንፃር ለማየት የተሞከረበት ጊዜ ነው ፡፡

4.አሁን ያለንበት ጊዜ ፡ ከዚህ በፊት የነበሩት የሥነ ልቡና ትርጓሜዎች ሙሉ ያልነበሩ ሲሆኑ በዚህ ጊዜ ግን ሥነ ልቡና የአዕምሮ አሰራር ሂደትንና ባህሪን አጠቃሎ የሚያጠና ሳይንስ ተብሎ ተተርጉሟል ፡፡

#በሥነልቡና ስር ያሉ ዋና ዋና ሙያዎች (Sub fields )

ዘርፉ እራሱን ችሎ እንደ ሳይንስ ከወጣ ገና 140 አመት በመሆኑና በዚህ ጊዜም በጣም ብዙ በስሩ ያሉ የሙያ አይነቶች እየታወቁና እየተጠኑ በመሆናቸው ትክክለኛ ቁጥሩ አሻሚ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ የሥነ ልቡና ተቋማች ውስጥ ያሉ ሰዎች ያሉት ሙያዎች በዚህ ጊዜ ከ 100 እንደሚያልፉ ይነገራሉ ፡፡
ካሉት ሙያዎች ውስጥ በጣም የሚታወቁትን ጥቂቶች መርጬ እንደሚከተለው አቀርባለሁ

1. Clinical (ክሊኒካል ሳይኮሎጂ ) :- ከቀላል እስከ አስከፊ የአዕምሮ የስሜትና የባህሪይ ህመሞችን (ችግሮችን) የሚያጠናና የሚያክም ነው ፡፡

2.Counseling psychology
የሰው ልጅ የሚገጥሙትን የቀን ተቀን ግላዊ / ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት የሚሞክር ነው ፡፡ሰዎችንም ችግርን ለመቋቋምና ለመፍታት እንዲረዳቸው ያላቸውን ጥንካሬ እንዲያውቁ ይረዳል፡፡

3.Cognitive and Perceptual psychology
የሰዉን የመረዳት ፣ የማሰብ ፣ የመገንዘብና የማስታወስ ሁኔታ የሚያጠና ነው፡፡ በዚሀሸ ስር አዕምሮአችን እንዴት ዕውነታን እንደሚረዳ ? ሰዎች ነገሮችን እንዴት እንደሚማሩ ? ሰዎች ቋንቋን እንዴት እንደሚረዱና እንደሚያወጡ ? ሰዎች እንዴት እንደሚወስኑ ፣ እንደሚፈርዱ እምክንያታዊ ሀሳብ እንደሚያመነጩ ያጠናል ፡፡

4.Neuropsychologists and Behavioral neuropsychologists
በአዕምሮና በባህሪይ መካከል ስላለው ግንኙነትና የአሰራር ዘዴ ያጠናል ፡፡

5.Health psychology
እንዴት ስነህይወት ፣ ሥነልቡናና ማህበራዊ ጉዳዮች የሰው ልጅ ጤናን አፊክት እንዳሚያረጉ ያጠናል ፡፡

6.Developmental psychology
የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ የሚያሳልፋቸውን የተለያዩ የእድገት ደረጃዎች ያጠናል ፡፡

7.Social psychology
የሰው ልጅ እርስ በርሱ በሚያረገው ማህበራዊ ግንኙነትና መስተጋብር ያሚደርስበትን ተፅዕኖዎች ያጠናል ፡፡

8.School & Educational psychology
ከመማር ማስተማር ጋር የተያያዙ እያንዳንዳቸው ጉዳዮች የሚጠኑበት ነው ፡፡

9.Industrial-Organizational Psychology
በአንድ የስራ ቦታ ላይ የሚገኙ የሰዎችን ግንኙነት ፣የሥራ ተዛምዶና ባህሪይ የሚያጠና ነው ፡፡

??????????
#ከዚህ በላይ ከዘረዘርኳቸው ጥቂት የሥነልቡና ሙያዎች ( Sub fields ) የቱን ወደዳችሁት ? ወደፊትስ የቱን አተኩረን እንድንማማር ይፈልጋሉ? #Comment አርጉ
??????????

❖❖______❖______❖❖
Source:- personal knowledge from different text books.
ምንጭ ፦ ካለኝ ዕውቀት ማለትም ከዚህ በፊት ከሰማኀቸው ፣ ከተማርኩት እንዲሁም ካነበብኩት ለአንባቢ እንዲቀር አድርጌ በአማረኛ የፃፍኩት ነው ።

http://psychology-hari.blogspot.com/2012/01/brief-historical-background-of.html?m=1

https://opentextbc.ca/introductiontopsychology/chapter/1-2-the-evolution-of-psychology-history-approaches-and-questions/

http://colfa.utsa.edu/psychology/subfields_of_psychology

በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል፡፡
ማንኛውም ጥያቄ / ተጨማሪ ሀሳብ Comment ማረግ ይቻላል ፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት እንዚህን እናያለን ፦
1.በብዙ ሰው ከተመረጠው ሙያ ውስጥ ፤ በሙያዉ ስር ያሉ መሰረታዊያንን እንመለከታለን
በተጨማሪ የሰው ልጅ እንዴት ነገሮችን እንደሚማርና እንደሚያውቅ በአስደናቂ መንገድ እንማራለን

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!


🎡@🎡መልካም ቀን
#Join #Join #Join
🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
🚗 @Psychoet👍
🚕 @Psychoet👍
ማኅበራዊ ፍርሃት ማስወገድ
Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
ይህን ጠቃሚ ትምህርት #Share እናድርገው

ማኅበራዊ ፍርሃት #ብዙ_ሰው_በተሰበሰበበት ቦታ ለመናገር ወይም አንድን ድርጊት ለመፈጸም በተዳጋጋሚ የሚፈጠር በብዙ ግለሰቦች ላይ የሚስተዋል #ምክኒያታዊ_ያልሆነ_ፍርሃት ነው፡፡ ይህ #የጭንቀት ዓይነት ያለባቸው ግለሰቦች ብዙ ጊዜ ንግግር ያለበት ተግባር አጥብቀው #ይሸሻሉ ምክኒያቱም አይደለም ንግግር አድርገው ገና ለማድረግ ሲያስቡ የሚሰማቸው #የፍርሃት ወይም #የጭንቀት_ስሜት ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ፡፡ ከህጻናት በስተቀር ማኅበራዊ ፍርሃት ያለባቸው ሰዎች ፍርሃታቸው ምክኒያታዊ እንዳልሆነ ይረዳሉ ምንም እንኳን ይህ ከፈርሃታቸው ባይታደጋቸውም፡፡
★እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች ናቸው፡-

1.ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ አጥብቆ መፍራትና በትምህርት ገበታም ሆነ በስራ ቦታ የተዘጋጁትን በአግባቡ ማቅረብ አለመቻል

2.እንደ ካፌ፣ ሬስቶራንት፣ ቤተ-መጻሕፍትና ሌሌች ብዙ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሰዎች እኔን እየተመለከቱኝ ነው ብሎ መሳቀቅ ፣ ከልክ በላይ አንገት አቀርቅሮ መጓዝ

3.ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ በሚያስቡበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ይተቹኛል ብሎ ማሰብ

4.ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ሲያደርጉ በላብ በጠመቅ ወይም ልዋረድ እችላለሁ ብሎ በፍርሃት ማሰብ

5.ብዙ ሰው ባለበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ የሆነ ያልሆነ ምክኒያት በመደርደር እራስን ማቀብ

6.አዲስ ሰው ጋር ለመገናኘት ተደጋጋሞ የሚከሰት ፍርሃት

7.ብዙ ሰው ባለበት ቦታ ምግብ በሚመገቡት ጊዜ ትንታ ወይም መታነቅ እንዲሁም ምግቡ ሊዝረከርክብኝ ይችላል ብሎ መፍራት

8.ከእነዚህ ጋር ተዛምዶ የሚከሰት እንደ የልብ ምት መጨመር፣ ላብ ላብ ማለት፣ የሰውነት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉት ፍርሃት ወለድ አካላዊ ለውጦች ናቸው፡፡

፠፠፠ መፍትሄ ፠፠፠

1.የአስተሳሰብ ለውጥ፡-

ብዙ ጊዜ ማኅበራዊ ፍርሃት እንዲከሰት የሚያደርጉ ከበስተጀርባ ያሉ አሉታዊ አመለካከቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ለራስ የሚሰጥ ዝቅተኛ ግምት አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ለዚህ ፍርሃት መከሰት አስተዋጽኦ የሚያበረከቱ ምክኒያታዊ ያልሆኑ አሉታዊ አስተሳሰቦችን ነቅሶ በመለየትና በአዎንታዊ አመለካከት መተካት፡፡

2.መለማመድ፡-

ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ መናገር ስለሚያስፈራን ንግግር የምንሸሽ ከሆነ የፍርሃቱ መጠን እንዲጨምር መፍቀድ ነው፡፡ ከሸሻችሁት በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው መቼም ቢሆን ከዚህ ችግር እንደማትገላገሉ ነው፡፡ ስለዚህ እራስን ቀስ በቀስ ማለማመድ ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡

3.ስራ ላይ ማተኮር፡-

ብዙ ጊዜ የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ከሚሰሩት ስራ ይልቅ ሌሎች ሰዎች ስለሚሰጧቸው አስተያየትና ምላሽ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ እዚህ ላይ መታሰብ ያለበት ከስራው ይልቅ አድማጭ ተመልካች ላይ የምናተኩር ከሆነ መጀመሪያ በተገቢው ስራን መስራት እንችልም ምክኒያቱም ቀልባችን ሌሌች ሰዎች ላይ ነውና፡፡ ሲቀጥ ልሌሎች ሰዎች ላይ ስናተኩር የበለጠ ስለፍርሃት ስሜታችን ላይ እንድናተኩርና የበለጠ አሉታዊ ሃሳቦች እንዲፈጠሩ ይገፋፋል፡፡

4.ጡንቻን ማዝናናት መለማመድ፡-

ከውስጥ ከሆድ መተንፈስ በመለማመድ ጭንቀቱ የሚፈጥረውን የረብሻ ስሜት መቀነስ፡፡ ይህ በጣም ቀላልና የትም ቦታ ሊለማመዱት የሚችሉት ዘዴ ነው፡፡ ለተወሰነ ደቂቃ (እስከ 10 ሴኮንድ) ወደ ውስጥ በመተንፈስ ትንፋሽህን መያዝ ከዚያም መልቀቅ፡፡ እንደገና ወደ ውስጥ ትንፋሽን በመያዝ አሁንም ወደ ውጪ መተንፈስ፡፡በተደጋጋሚ ይህን በማድረግ የጭንቀት ስሜቱን ማቅለል ይቻላል፡፡ ይህን ዘዴ ጭንቀቱ ቀለል እሰከሚልድረስ መከወን ይቻላል፡፡

5.የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና መውስድ፡-

ዓይንን እየተመለከቱ ማውራት፣ ፈገግታ፣ የንግግር ፍሰትን መጠበቅና የመሰሳሰሉት ልምምዶች በንግግርና በሌሎች ማህበራዊ ተግባቦት ላይ ውጤታማነታችንን ሲለሚጨምሩ ለወደፊት የበለጠ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ መናገርና ሌሌች ተግባሮችን ለመፈጸም አወንታዊ ማበረታቻዎች ናቸው፡፡

6.ሌላው presentation ሲኖርብን ከመስታወት ፊት በመቆም በደንብ መለማመድ ፣ ስናወራ ምን እንደምንመስል ማየትና ራሳችንን እያረምን ደጋግሞ መለማመድ ፡፡ በተጨማሪ ደፋር ሰዎች ራሱ ብንሆን አንዳንድ ያልተዘጋጀናቸውን ነገሮች ስናቀርብ / ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ ስንገኝ ፍርሀት ሊከሰት ስለሚችል ሁልጊዜ ጠንቃቃ መሆን ይጠበቅብናል ደግሞም ከልክ ያለፈ በራስ መተማመንም ማስወገድ መልካም ነው ፡፡

የፍርሃት ስሜት ወይም ጭንቀት የዕለት ተዕለት ህይዎታችን በደስታ እንዳንመራ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማኅበራዊ ፍርሃትም እንደዚሁ በህይወታችን ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽኖ ይኖራል፡፡ ለችግሩ መፍትሄ ማፈላለግ እንጂ ለምን ይህ ተከሰተብኝ ብሎ እራስን መኮነንና ጥፋተኛ ማድረግ አይገባም ምክኒያቱም ምንጩ እኛ ሳንሆን አስተዳደጋችን ፣ አካባቢያችን ፣ አስተማሪዎቻችን ፣ ሊሆኑ ይችላሉና ፡፡ ስለዚህ በዚህ ፍረሀት ያላችሁ ሰዎች የጠቀስኳቸውን ነገሮች በደንብ ተግባራዊ አድርጉ ፡፡ ጥያቄ ካላችሁ ጻፉልኝ፡፡

መልካም ቀን ይሁንላችሁ ።
(በአሸናፊ ካሳሁን እና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist

በቴሌግራም በዚህ አግኙኝ www.tg-me.com/Psychoet
📌🗓📕 የ2013 የመጨረሻ የለውጥ ዕድል
👉ማክሰኞ ይጀምራል
ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ያግኙ።
የ 2013 የመጨረሻ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ጷግሜ 2፣3፣4 ጀምሮ ይሰጣል

የሚሰጡት ስልጠናዎች
📝የሕይወትን አላማ ማወቅ
📝ለ2014 እቅድና ግብ አዘገጃጀት
📝ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
📝የስሜት ብልሀት
📝ተግባቦት፣ በራስ መተማመንና ፍርሀትን ማስወገድ

የስልጠና ቀናት ለተከታታይ 3 ቀናት(ያሉን ፈረቃዎች)

📆📆📆 ጷጉሜ 2፣3፣4
ማክሰኞ፣ ረዕቡ፣ ሀሙስ
4-6 ወይም 8-10

🔔በአንድ ፈረቃ ጥቂት ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው በሚያመችዎት ፈረቃ ይመዝገቡ ፡፡

💸ክፍያ (የመመዝገቢያ ፣ የስልጠና ፣ የሰርተፍኬት ጨምሮ)- 500 ብር ብቻ

ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
በአካል ለመመዝገብ የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 219 (Nova Training Center)

ትርፋችን የሰው ህይወት መለወጥ ነው፡፡ 📖

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «📌🗓📕 የ2013 የመጨረሻ የለውጥ ዕድል 👉ማክሰኞ ይጀምራል ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ያግኙ። የ 2013 የመጨረሻ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ጷግሜ 2፣3፣4 ጀምሮ ይሰጣል የሚሰጡት ስልጠናዎች 📝የሕይወትን አላማ ማወቅ 📝ለ2014 እቅድና ግብ አዘገጃጀት 📝ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም 📝የስሜት ብልሀት 📝ተግባቦት፣ በራስ መተማመንና ፍርሀትን ማስወገድ የስልጠና…»
#ጭንቀትን_መቀነሻ_ቴክኒኮች

ይህም በሥልጠናና በባለሙያ የካውንሰሊንግ አገልግሎት ሊገኝ ይችላል፡፡ ሁለት ቴክኒኮችን ብቻ እንመልከት (በርካታ ቴክኒኮች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል)፡-

1⃣ #ABCDE_ቴክኒክ :

ይህ ቴክኒክ አልበርት ኤሊስ (Albert Ellis) በተባሉ የስነልቦና ባለሙያ የተገኘ ዘዴ ነው፡፡

አልበርት ኤሊስ ሰዎች ወደ ጭንቀት የሚገቡት አግባብ ያልሆነ አስተሳሰቦችና እምነቶች (Irrational beliefs and thoughts) ሲጠናወቷቸው ነው ብለው ያምናል።

ለምሳሌ:-

👉ሰው ሁሉ ይጠላኛል፣
👉ሰው ሁሉ ይወደኛል፣
👉ከሰው ሁሉ ተቀባይነትን ማግኘት አለብኝ፤
👉በምሰራው ስራ ሁሉ መሳሳት የለብኝም...ወዘተ የሚሉ እምነቶችና አስተሳሰቦች ለጭንቀት እንደሚዳርጉ ያሰምሩበታል።

እኚህ ሰው እንደሚሉት፥

✔️አሉታዊ ነገሮችን አጋኖ ማየት (Awfulising)

✔️ጥቁርና ነጭ እሳቤ (Black and White thinking 👉ይህ እንግዲህ አንድን ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ ብሎ መመደብና በውስጡ ሊኖር የሚችለውን የተወሰነውን ጥሩ ነገር አለማየት ነው።

✔️ጠቅላይ እሳቤ(Over generalizing) 👉ሁልጊዜ፣ ሁሉም ሰው፣ በፍፁም.....ወዘተ የሚሉ ቃላትንና ሃሳቦችን መጠቀም፤
(ሁሉም የሚል አባዜ አለባቸው)

✔️Personalizing የማይመለከተንን ነገር ከራሳችን ጋር አቆራኝቶ ማየት፤

✔️Filtering በሁኔታዎች ውስጥ አሉታዊን ነገር ብቻ መርጦ ማየት፤

✔️Mind reading ይህንን አስቦ ነው ብሎ ያለምንም ማስረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ፤

✔️Blaming 👉ሰዎችን መተቸትና መውቀስ

✔️Labeling 👉ለራስ ስያሜ መስጠት

ለምሳሌ: ደካማ ነኝ፤ዋጋ ቢስ ነኝ...ወዘተ ማለት አግባብ ላልሆኑ አስተሳሰቦች ምክኒያት ናቸው ይሉናል፡፡

ቴክኒኩን ተንትነን ለማየት እንሞክር

#Antecedent (Activating event, Stimulus)፡

ይህ ማለት ጭንቀትን የሚቀሰቅሰው ሁኔታ ወይም ነገር ነው (ተንኳሽ እንበለው)፡፡
" ይህ ተንኳሽ የኛን ምላሽ (Response) ይጠይቃል።

ለምሳሌ:- ከስንት አንድ ቀን ቀጠሮ ብናረፍድ ጭንቀት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት ጭንቀትን የሚፈጥርብን ጉዳይ ማርፈዳችን ነው ማለት ነው፡፡

#Belief_our_cognition_about_the_situation ፡-

ይህ እንግዲህ ስለ ተንኳሹ ያለን ሃሳብና እምነት ነው፡፡

ለምሳሌ ማርፈዴ ያለኝን ተቀባይነት ያሳጣዋል፣ በምንም አይነት ምክኒያት ቢሆን ማርፈድ አሳማኝ አይደለም...ወዘተ የሚል እምነት ማለት ነው፡፡

#Consequences- the way that we feel and behave፡

ይህ ውጤት ነው - ጭንቀታችን፡፡ ይህ ምን ባህሪ ይፈጥራል? ቶሎ ለመድረስ አላግባብ ጣልቃ እየገባን መኪናችንን መንዳትን፣ በእጃችንም በአንደበታችንም የተንቀረፈፈ የመሰለንን ሾፌር መስደብ፣ መቆጣት፤ ከአስፋልት ወጥቶ በእግረኛ መንገድ መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ አልበረት ኤሊስ ይሞግታሉ “ያስጨነቀን ማርፈዳችን ነው ወይስ ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው?”

አሳቸው እንደሚሉት፤ ውጤቱን የፈጠረው ማርፈዳችን (stimulus) ሳይሆን ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው ባይ ናቸው፡፡

#Dispute:- is the process of challenging the way we think about situations:

ይኸኛው አስተሳሰባችንን የምንሞግትበት ዘዴ ነው። እሳቸው አግባብነት የሌለውን አስተሳሰብና እምነት መሞገት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

ለምሳሌ ከላይ የጠቀስነውን ማርፈድ ብንወስድ እምነታችንን ስንሞግተው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
“ብዙ ጊዜ በሰዓቱ የምገኝና ቀጠሮ አክባሪ የሆንኩ ሰው ነኝ፡፡ አንድ ዛሬን ባረፍድ ተቀባይነቴን አያሳጣም”፣ “ለማርፈዴ ምክኒያት የሆነኝ የትራፊክ መጨናነቅና ያልጠበቅሁት የመንገዶች መዘጋጋት ነው፡፡ ስለዚህ በቂ ምክኒያት ሊሆን ይችላል፡፡” እነዚህን ምክኒያቶች በማሰብ ነባሩን ሃሳብ መሞገት እንደሚገባ ይጠቁማሉ፤ አልበርት ኤሊስ፡፡

#Effect : ይሄ አዲሱ ውጤት ነው።
አስተሳሰባችንን ከሞገትነውና በአዲስ አስተሳሰብ ከተካነው በኋላ የሚፈጠር ባህሪ ነው፡፡ የላይኛውን ምሳሌ ብንከተል ተረጋግቶ መንዳት፤ ተራ መጠበቅ፤ በተፈቀደው አስፋልት መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

👉ማስተዋል ያለብን ሃሳብ ስሜታችን እና ባህሪያችን ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል፡፡ ማወቅና አስተሳሰብን መለወጥ ደሞ አስፈላጊ ነው፡፡

#share

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet
youtube : youtube.com/thenahusenai
መልካም ቀን!
🌼🌼ለቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ መልካምና ውጤታማ 2014 አመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡ 🙏

2014 በራሱ ይዞ የሚመጣው አንዳች ነገር የለውም ዋና ጉዳይ እኛ ወደ 2014 ምን ይዘን መተናል ነው፡፡ 🌼🌼

መልካም እቅዶችንና ስራዎችን የምንሰራበት ዓመት ይኹን!
መልካም 2014 ❤️

🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼

አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት

አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
አዲስዓመት

ዓመት
አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመት

አዲስአዲስ ዓመት
አዲስ አዲስ ዓመት
አዲስ አዲስ ዓመት
አዲስ አዲስ ዓመት
አመት አዲስ ዓመት
አመት አዲስ ዓመት
አመት አዲስ ዓመት
አዲስ አዲስ ዓመት
አዲስ አዲስ ዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስአመት
መልካም አዲስዓመትአዲስአመት
አዲስ ዓመት
አዲስ ዓመት
አዲስ ዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
🔆🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🔆
🔆🌼🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🌻🌻 መልካም 🌻🌻️🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🌻🌻 አዲስ 🌻🌻🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🌻️🌹🌾🌻💐🌹🌻🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🌼🔆
🔆🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🔆

መልካም አዲስ ዓመት
@psychoet
“አዲስ ዓመት” አዲስ እኔ”ነት ነው!
(New year is the philosophy of self optimism)
(እ.ብ.ይ.)

ሰው ሁልጊዜ አዲስ ይሆን ዘንድ እንዲችል አዲስ ዓመትን ፈጠረ፡፡ ሰው ከራሱ ጋር ይታረቅ ዘንድ፣ እቅዱ ከግቡ እንዲስማማ፤ ውጫዊና ውስጣዊ ሕይወቱ እንዲጣጣም አዲስ ዓመት ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡ የአዲስ ዓመት አፈጣጠሩም ሰው ለራሱ ቀና ለመሆን ከመነጨ ውስጣዊ ጉጉቱ ነው፡፡ የዛሬው ሰውም ለራሱ እንኳ ቀና መሆንን ባልቻለበት የእድሜ ዘመኑ አንዲቷ ቀን አዲስ ዓመት ትሆነው ዘንድና ለራሱና ለወገኑ መልካምና ቅን ያስብባት ዘንድ አባቶቹና ቅድመ አያቶቹ አዲስ አመትን ሰሩለት፡፡

አዲስ ዓመት የሰው ልጅ ራሱን የሚያሻሽልበት፣ ያለፈውን ሕይወቱን ገምግሞ ደካማውን ሽሮ ጠንካራውን ይዞ እንዲቀጥልበት ለራሱ የፈጠረው የቀን ቀጠሮ ነው፡፡ ተፈጥሯዊ ቀኑ ያው ከሌላው ቀን የተለየ አይደለም፡፡ እንደማንኛውም ቀን ይነጋል፤ እንደማናኝውም ምሽት ይመሻል፡፡ ነገር ግን ለቀኑ ስያሜ በመስጠት በቀኑ አማካኝነት ራስን መለወጥ፣ አስተሳሰብን ማደስ፣ አኗኗርን ማስተካከል ማሰብ ማሰላሰል በሚችለው በሰው ልጅ ታሪክ የተለመደ ወግ ነው፡፡ ምክንያት ፈልጎ ወይም ፈጥሮ አንድ ነገር ማድረግ ሰው የሰለጠነበት ልማዱ ነው፡፡ ዛሬም እንደጥንቱ በሰሜናዊው የሃገራችን ክፍል ሰው አይደለም ለደስታው ቀርቶ ለሐዘኑም ጭምር ደረቱን ለመድቃት፣ ፊቱን ለመንጨት እንኳ ቀድሞ የተረዳውን/የሰማውን የወዳጁን ወይም የዘመዱን ሞት እርሙን ለማውጣት ሲል ቀን ቀጥሮ ከዘመድ አዝማዱ ጋር ተሰባስቦ በቀጠሮ ለቅሶ ሐዘን ይቀመጣል፡፡ አዲስ ዓመትም አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ዕቅድ፣ ከበፊቱ የተለየ የሕይወት መንገድ የሚጀመርበት የቀን ቀጠሮ ነው፡፡

አዎ አዲስ አመት ሰው ለራሱ ቀና የሚያስብበት፣ አዲስ ቃል የሚገባት ዕለቱ ነው፡፡ ይሄ ቀን ደግሞ መጪው ጊዜ መልካም እንዲሆን፤ ኑሮው እንዲሳካ፣ ጎጆው እንዲሞላ፣ መንፈሱ እንዲረካ፣ አዕምሮው እንዲሰላ፣ ነፍስያው እንዲጠግብ፣ የውስጡም የውጪውም ሕይወቱ እንዲያምር ሀ ብሎ ስራ የሚጀምርበት ዕለት ነው፡፡ በርግጥ ብዙዎቻችን አዲስ ዓመትን ከአለባበስ፣ ከመብልና ከመጠጥ ጋር ብቻ የምናያይዝ ነን፤ እንዲሁም ከወዳጅ ዘመድ ጋር ተገናኝቶ ለመጫወት ብቻ ቀኑን የምናሳልፍ ጥቂት አይደለንም፡፡ ከቤተሰብ ጋር ሆኖ አምሮና ደምቆ በፍቅርና በደስታ አዲስ ዓመትን ማሳለፍ የሚያስደስት ቢሆንም እውነተኛ የአዲስ ዓመት ትርጉሙ ግን አዲስ ሰውነት፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ለውጥ፣ አዲስ የሕይወት መንገድ የምናበጅበት፣ ለራሳችን ቀና አስተሳሰብ የምንቀይስበት ዕለት ነው፡፡

የስቶይክ ፍልስፍና አራማጆች እንደሚመክሩት የሰው ልጅ ጭንቀቱና ትኩረቱ መሆን ያለበት መቆጣጠር በማይችላቸው በውጫዊ ኩነቶች ሳይሆን በቀላሉ ሊያስተዳድራቸው በሚችላቸው በውስጣዊ ሕይወቱ መሆን አለበት ይላሉ፡፡ የሰውነት ጓዳ ጎድጓዳውን ሳይሞላ ቤቱን በቁስ የሚሞላ ሰው የአዕምሮ ድሃ ነው፡፡ ሕይወቱን ለመብላት ብቻ የሚያኖራት እውነተኛ ደስታ የለውም፡፡ ሆድን ከመሙላት በላይ አዕምሮን በማጥገብ ነው የሕይወት እርካታ የሚገኘው፡፡ የሰው ልጅ በእንጀራ ብቻ አይኖርም እንዲል ቅዱስ ቃሉ፡፡

ሰው ለአዲስ ዓመት አዲስ እቅድ ሲያዘጋጅ ገንዘብ ለማግኘት ብቻ ብሎ ሳይሆን ገንዘብ እንዴት መስራትና በምን አግባብ ሐብት ማከማቸት እንደሚችል የሚያውቅ ጭንቅላት መፍጠር እንዳለበትም ጭምር ካልሆነ እቅዱ ትርጉም አይሰጥም፡፡ ገንዘቡ ግንዛቤ ከሌለው አደጋ ነው፡፡ አዲስ ዓመት በቁስ ሃብታም የመሆን ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ አዲስ ዓመት በአዲስ አስተሳሰብ የመንፈስ ባለፀጋ የዕውቀት ባለሐብት ለመሆን እቅድ ካልተያዘበት ዋጋ የለውም፡፡ ሰውነትን የማያበለጽግ እቅድ ግቡን ቢመታም ህይወትን አስደሳች አያደርግም፡፡

ወዳጄ ሆይ..... የአዲስ ዓመት ፍልስፍናህን ገምግመው፡፡ አንተ ራስህን ለመለወጥ ቆርጠህ ካልተነሳህ አዲስ ዓመት አንተን አይለውጥህም፤ ቀኑ በራሱ ጥንትም ማንንም ለውጦ አያወቅም፤ ወደፊትም አይለውጥም፡፡ አዲስነት በሃሳብ መለየት ብቻ ሳይሆን በግንዛቤ መበልጸግ፣ በጥበብ መጎልመስ፣ ራስን በመቆጣጠር መርቀቅም ጭምር መሆኑን ተረዳ፡፡ አዲስነት የትናንቱን ድካም፤ ያለፈውን አጉል ልማድ መድገም ሳይሆን አዲሱን ኑሮ በአዲስ ሰውነት፣ በሰለጠነ አስተሳሰብና በቀናነት መጀመር ነው፡፡ አዎ! አዲስ ዓመት ከአዙሪት ሕይወትህ ነጻ የምትወጣበት፤ ከአጉል ልማድ እስርህ ሐርነት የምታገኝበት የነፃነት ቀንህ ነው፡፡ አዲስ ዓመት ለራስህ፣ ለወገንህ፣ ለሐገርህ ቅን አስበህ በጎውን የምትከውንበት የስራ ዘመንህም ነው፡፡ አዲሱ ዓመት ሰላም የሞላበት፣ ፍቅር የበዛበት ይሆን ዘንድ ከራስህ ጋር ውል የምትፈፅምበት የቃልኪዳን ዕለትህም ጭምር ነው፡፡ አዲሱን ዓመት በአዲስ ሰውነት ካልተቀበልከው አዲሱ ዓመትህ ያረጃል፣ አንተም በአዲስ ዓመት ከበርቻቻ ትርጉም ታጣለህ፡፡

አዲስ ዓመት የአዲስ ሕይወት ጅማሮ፤ የቀናነት አስተሳሰብ የመጀመሪያው ክፍለጊዜ ነው፡፡

መልካም አዲስ ዓመት!

ቸር ዘመን!

____________
©እሸቱ ብሩ
@Psychoet
ደስተኛ ለመሆን የሚረዱ 10 የሕይወት መርሆዎች!

1."እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር!"

ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ። ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ።

2."አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው!"

የጎደለህ ምንድን ነው?
☞ያለህስ ምንድን ነው?
☞ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3."እራስህን ሁን!"

በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፤

4."ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር!"

አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነትጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5.የውሸት ደስታን አትፈልግ!"

በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤

6."ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅንሁን!"

ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፤

7."መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው!"

ብዙሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ። ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስጠው።

8. "የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን!"

ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?

9."መልካም አስብ መልካም ተናገር!"
<>~ ~<> <>~ <>
በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10."ለምን እንደምትኖር እወቅ!"

ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድንነው? በህይወትህ ማድረግ የምፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱ ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይለወጣል።
(በዚህ ዙሪያ መጽሐፍ ጽፌ የጨረስኩ ሲሆን ጥቅምት አጋማሽ ስለሚወጣ ብታነቡት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ፡፡ )
Source:- Health Insurance Network
@psychoet
የነፍስ ጥሪያችንን መከተላችንን የሚጠቁሙ 10 ምልክቶች
Telegram www.tg-me.com/psychoet

አንዳንዴ በዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ይህ ስራ፣ ይህ ህይወት የምፈልገው ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ አእምሮችንን ሰቅዞ ይይዛል፡፡ በተለይ የምንሰራው ስራ ደስታ አልባ ሲሆን፣ ሁልጊዜ እንደው አንድ ቀን ይህንን አድርጌ ብሞት እንኳ አይቆጨኝም የምንለው ነገር ውስጣችን ሲመላለስ፣ አጋጣሚው ተፈጥሮ ስንሰራውም ሆነ ስንሆነው ትልቅ ደስታ የሚሰጠን ነገር ሲኖር እና አሁን እየሰራን እና እየኖርን ያለነው ህይወት ግን ከዚህ የተለየ ሆኖ ሲገኝ የነፍሳችንን ጥሪ ማግኘት አለማግኘታችን ህይወታችን ውስጥ ትልቅ ጉዳይ ይሆናል፡፡

የነፍስ ጥሪ እያልን ያለነው ማንኛውም መስራት፣ መሆን፣ ማግኘት የምንፈልገውን ነገር ሲሆን ዓላማ፣ ራዕይ፣ የህይወት ግብ የመሳሰሉት ቃላት ሊተኩት ይችላሉም፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ነጥቦች አንድ ሰው የነፍስ ጥሪውን ማግኘቱን የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡

1. ከውልደታችሁ ጊዜ ጀምሮ ለነፍስ ጥሪያችሁ እየተዘጋጃችሁ እንደ ነበር ትረዳላችሁ

ሌላው ቀርቶ ያዘናችሁበት እና የተጎዳችሁበት ነገር እንኳ ለነፍስ ጥሪያችሁ ልምምድ እንደነበር ይሰማችኋል፡፡ የምትወዱት ሰው ሞት፣ ፍቺ፣ ሲያጋጠማችሁ አደጋ ወዘተ ነፍሳችሁ መሆን ለምትሻው ነገር የዝግጅት ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዴ አሳዛኝ ነገሮች ከተፈጠሩ በኋላ ውጤቱ ግን ጥሩ ሲሆን ሰዎች “ለበጎነው” የሚሉት ከዚህ  አኳያ ነው፡፡ ህመም አጋጥሞን የተማርነው ነገር ሊኖር  ይችላል፡፡ ሰዎች ጎድተውን የተማርነው ነገ ርሊኖር ይችላል፡፡ ቅርባችን ያለሰው ህይወት አልፎ የተማርነው እና ህይወታችንን የቀየረ አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ በህይወታችሁ  ከውልደታችሁ ጀምሮ ያጋጠማችሁ ክፉ እና ደግ ነገር ለነፍስ ጥሪያችሁ የዝግጅት ጊዜ እንደነበር ትረዳላችሁ፡፡

2. ምስጥራዊ ነገሮች ይፈጠራሉ

ህይወታችሁ ውስጥ ይሆናል ያላሰባችሁት አስደናቂ ነገሮች ሲፈጠሩ ተአምራዊ አጋጣሚ ብላችሁ ልታስቧቸው ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ ህልማችሁን ለማሳካት የሚያስችሏችሁ አንዳንዴ ለማመን ሁሉ የሚከብዷችሁ ሚስጥራዊ አጋጣሚዎች የነፍስ ጥሪያአችሁን እየተከተላችሁ እንደሆነ ያሳያሉ፡፡

3. ከመንገድ ስትወጡ ወደ መንገዳችሁ ሊመልሷችሁ የሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይፈጠራሉ

የነፍስ ጥሪያችሁ እየተከተላችሁ ካልሆነ አንዳንዴ መንገዱ አልጋ በአልጋ አይሆንላችሁም፡፡ ህይወት አስቸጋሪ ሲሆንባችሁ እያቀናችሁ ያለበት መንገድ የእናንተ መንገድ አለመሆኑን ትገነዘባላችሁ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ስትሆኑ ገንዘብ ሊቸግራችሁ፣ በርትታችሁ እንድትቆሙ ያገዟችሁ ሰዎች ከጎናችሁ ሊሸሹ፣ ደስታ ሊርቃችሁ ወዘተ ይችላል፡፡

4. በችግር እና ፈተና ፊት ተረጋግታችሁ ትቆማላችሁ

መንገዳችሁ ፈተና የበዛበት ሲሆን የትኛው ምክንያት የፈተናው ምንጭ እንደሆነ አንዳንዴ ለመረዳት ሊከብድ ይችላል፡፡ ቁርጠኝነታችሁ እየተፈተነ ነው ወይስ የተሳሳተ መንገድ ውስጥ ገብታችኋል? መሰናክሎች የዕድገታችን አካል፣ እንድንጠነክር የሚያደርጉን ሂደቶች፣ ውስጣችሁ የሚገኘው ጀግና ጉዞ አካል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአንፃሩ የተሳሳተ መንገድ እየተከተላችሁ እንደሆነ የሚጠቁሙ ምልክቶች ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ ልዩነቱን እንዴትነው ማወቅ የምትችሉት? ልዩነቱን የምትረዱት ውስጣችሁ እየተፈጠረ በሚሄደው መረጋጋት እና ሰላም (Ease) ነው፡፡ ሁኔታዎች አስቸጋሪ ሆነው፣ ችግር እና ፈታና ፊታችሁ ተከምሮ እንኳ ውስጣችሁ ሰላም እና መረጋጋት የሚሰፍን ከሆነ የነፍስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ መሆኑን ያሳያል፡፡

5. አስደናቂ አስተማሪዎችን ታገኛላችሁ

የነፍስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ ከሆነ ልምዳቸውን የሚያካፍሏችሁ፣ እገዛ የሚያደርጉላችሁ፣ የሚያበረታቷችሁ ሰዎች በየጊዜው ይፈጠራሉ፡፡

6. ጤናችሁ ሊሻሻል ይችላል

እንግዳ የሚመስል ነገር ነው፡፡ ነገር ግን የነፍስ ጥሪያችሁን እየተከታላችሁ ከሆነ አንዱ የምታገኙት ነገር መልካም ጤንነት ነው፡፡ ለጤናችሁ የማይበጅ ምግብ የመመገብ ፍላጎታችሁ ይቀንሳል፤ ሰውነታችሁን እንደልባችሁ ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ኃይል ታገኛላችሁ፤ እረፍት የሚነሷችሁ ህመሞች፣ መፍለጥ መቁረጦች ሊጠፉ ይችላሉ፤ ድካም አጠገባችሁ ድርሽ ላይል ይችላል፤ ስር የሰደደ ህመም ካለባችሁ እንኳ መሻሻል ልታዩ ትችላላችሁ፡፡

7. ገንዘብ ማግኘት ትጀምራላችሁ

የነፍስ ጥሪያችሁን መከተል ስትጀምሩ ጨርሶ ገንዘብ አትቸገሩም ማለት አይደለም፡፡ የሚላስ የሚቀመስ የምታጡበት ደረጀ ላይ ሁሉ ልትደርሱ ትችላላችሁ፡፡ እዳ ውስጥ ልትነከሩ ትችላላችሁ፡፡ የቤት ኪራይ የምትከፍሉት ገንዘብ እጃችሁ ላይ ላይኖር ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ የነብስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ ከሆነ ገንዘብ እንደ ልብ ታገኛላችሁ፡፡

8. ብዙ ሊያሳስባችሁ የሚችል ነገር እያለ በሚገርም ሁኔታ ሰላም ውስጣችሁ ይሰፍናል

በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች በሙሉ “አብዳችኋል” ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እናንተም በአንድ ጎናችሁ በእነሱ ሃሳብ ልትስ ማሙ ሁሉ ትችላላችሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ውስጣችሁ/ነፍሳችሁ የምትፈልጉትን እንዳገኘ ስለሚያውቅ ሰላም እና መረጋጋት ይበዛላችኋል፡፡ ነብሳችን ኃላፊነታችን ምን እንደሆነ ሁልጊዜም መግለጽ ትፈልጋለች፡፡ ምንም እንኳን በዙሪያችን የሚገኙ ብዙ ነገሮች አስደሳች ባይሆኑም አንድ ጊዜ የነፍስ ጥሪያችንን መከተል ስንጀምር ግን አስደናቂ ሰላም እና መረጋጋት ውስጥ እንገባለን፡፡

9. ዓለም ይተባበራችኋል

አንድ በጣም ትልቅ የህክምና ባለሙያ ሰው እንዲህ ትላለች “ለምን ወረቀት አይሆንም እኔ ከፈለኩት እግር አውጥቶ ይመጣል”፡፡ የነፍስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ ከሆነ የሚተባበራችሁ ሰው በየአቅጣጫው ይገኛል፡፡ የሚጻፍ ነገር ስትፈልጉ ፀሐፊ ደጃችሁ ድረስ ሊመጣ ይችላል፡፡ የሚታተም ነገር ስትፈልጉ ከአታሚዎች ጋር በሆነ አስደናቂ አጋጣሚ ልትገናኙ ትችላላችሁ፡፡ ሰዎች እየደገፏችሁ፣ እያበረታቷችሁ፣ ዕድለኛ እየሆናችሁ እንደሆነ ይሰማችኋል፡፡ እያንዳንዱ ነገር ግልጽ ባይሆን እንኳን በዚህ ድጋፋ እና ማበረታቻ ምክንያት ትክክለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኙ ትረዳላችሁ፡፡

10. አጋሮቻችሁያገኟችኋል

ማንም ሰው ቢሆን ህልሙን ብቻውን ለማሳካት ይቸገራል፡፡ ትልልቅ ለውጦች፣ ትልልቅ ፈጠራዎች፣ ትልልቅ ስራዎች በአጠቃላይ የብዙ ሰው የተባበረ አእምሮ እና ክንድ ውጤት ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ዓለም በፈታና እና በብዙ ውጣውረድ የተሞላች ነች፡፡ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ብቻን ማለፍ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ እናንተ የነብስ ጥሪያችሁን እየተከተላችሁ ከሆነ መንገድ ላይ አብረዋችሁ የሚሰሩ አጋሮችን ታፈራላችሁ፡፡

(በነጋሽ አበበ) ©zpsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#ሰዎች_ሁልጊዜም_የሚሉት_ነገር_አያጡም
Telegram www.tg-me.com/psychoet

አባትና ልጅ ወደ አንድ አካባቢ ረጀም ጉዞ ለማድረግ አህያቸውን ጭነው ከቤታቸው ይወጣሉ፡፡ ጉዞውን እንደጀመሩ ልጅ በአህያው ላይ ቁጭ ብሎ አባት ደግሞ የአህያዋን ልጓም ይዘው በእግራቸው ይጓዙ ጀምር፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ ግን የልጅን በአህያ ላይ መቀመጥ የአባትን በእግር መጓዝ የተመለከቱ ሰዎች “አባቱ በእግሩ እየሄደ እንዴት ልጁ በአህያ ይሄዳል? ምን ዓይነት ስነ ምግባር የጎደለው ልጅ ነው?” በማለት ቅሬታቸውን እና ትችታቸውን ሰነዘሩ፡፡ ይህንን እንደ ሰሙ አባት እውነትም ስህተት የሰሩ መስሏቸው ልጃቸውን በእግሩ የአህያዋን ልጓም ይዞ እንዲሄድ አድርገው እሳቸው ደግሞ በአህያ ላይ ወጥተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አሁን ደግሞ ሰዎች አባት ላይ ትችታቸውን ማዥጎድጎድ ጀመሩ;፡፡ “ምን ዓይነት ጨካኝ አባት ነው? ልጁን በእግሩ እያዳከረ እሱ በአህያ እንዴት ይሄዳል” አሉ፡፡ በዚህም አባት ይደናገጡና ከአህያዋ ላይ በመውረድ እንግዲያውስ ሁለታችንም በእግራችን እንሂድ ተባብለው በእግራቸው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ወደ ሌላ መንደር ሲቃረቡ አሁንም አህያዋን ያለ ምንም ጭነት ተዝናንቶ መሄድ እና የአባትና ልጅን በእግር መጓዝ የተመለከቱ የመንደሩ ሰዎች ሌላ ትችት መሰንዘር ጀምሩ፡፡ “ድሮም ሃብት ያላቸው ሰዎች ችግራቸው ይኼ ነው! እንዴት ያላቸውን ነገር መጠቀም እንዳለባቸው አያውቁም” አሉ፡፡

አሁንም ሰውን ማስደስት እንዳልቻሉ እና ልክ እንዳልሆኑ የተሰማቸው አባት እና ልጅ የሚቀጥለው መንደር ሰው አፍ ላለመግባት ሁለቱም በአህያዋ ላይ ወጥተው መጓዛቸውን ቀጠሉ፡፡ ቀጣዩ መንደር እንደደረሱ ግን አባት እና ልጅ የገጠማቸው አሁንም ሌላ ትችት ነው፡፡ “ምን ዓይነት ጨካኝ ሰዎች ናቸው? አንደበት የላትም ብለው ነው? የእግዜር ፍጥረት ላይ ይታያችሁ እስኪ እንዴት ሁለት ሆነው ጀርባዋ ላይ ተዝናንተው ተቀምጠው ይሄዳሉ አንዳቸውን ከተሸከመች አንሶ ነው” አሉ፡፡ አባት እና ልጅ ተደናግጠው ሁለቱም ከአህያዋ ጀርባ ላይ አፍታ እንኳን ሳይቆዩ ወረዱ፡፡ በየደረሱበት ትችት የገጠማቸው አባት እና ልጅም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ከተመካከሩ በኋላ ቢያንስ ከዚህ በኋላ የምናገኛቸውን ሰዎች ማስደሰት ይኖርብናል ብለው በማሰብ አህያዋን ተጋግዘው ለሁለት ተሸክመው ጉዟቸውን አሁንም ይቀጥላሉ፡፡ አህያዋን በመሸከማቸው ምክንያት እጅግ ተዳክመው ወደ ሚቀጥለው መንድር ይደርሳሉ፡፡ አህያ የተሸከሙትን የከተማዋን ሰዎች የተመለከቱት ሰዎች ወገባቸውን ይዘው መሳቅ ጀመሩ፡፡ ምን ዓይነት ጅል ሰዎች ናቸው አህያዋ ላይ ተቀምጠው እንደመሄድ እንዴት አህያ ተሸክመው ይጓዛሉ በማለት ተሳለቁባቸው፡፡ አባትና ልጅም ምንም ነገር ቢያደርጉ ከሰው ትችት ማምለጥ እንደማይችሉ እና ሁልጊዜም ቢሆን ሰዎች የሚተቹት ነገር ፈልገው እንደማያጡ ተረድተው ጉዟቸውን እነሱ ባሻቸው መንገድ ቀጠሉ፡፡

እውነትም ሰዎች ምንጊዜም ቢሆን የሚሉት አንድ ነገር አያጡም፡፡ የምታደርጉትን ነገር ቢወዱትም ባይወዱትም፤ ልክ ነው ብለው ቢያስቡም ባያስቡም ፤ ቢመለከታቸውም ባይመለከታቸውም አንድ የሚሉት ነገር አያጡም፡፡ መፍትሄው የገዛ ራስን ህይወት በራስ ፍላጎት መምራት ነው፡፡ የአንተ/የአንቺ ህይወት የተባለበትም ምክንያት ይኼ ነው፤ አንተ/አንቺ በአሻችሁ መንገድ ትመሩት ዘንድ ነው፡፡

ስለዚህ የትኛውም ጥሩ ነው፣ ዋጋ አለው፣ ይበጀኛል ወዘተ ብላችሁ ከልባችሁ እስካመናችሁ ድረስ ሰዎች ምንም ይበሉ ምን ከማድረግ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡

(በኤባ ተስፋዬ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ዋጋችሁ ስንት ነው?

የ ሀይላንድ ውሀ የሰፈር ሱቅ ውስጥ 7 ብር ነው እራሱ ውሀ ሬስቶራንቶች ውስጥ ከ 20 እስከ 40 ብር ይሸጣል፤ ትላልቅ ሆቴሎች 60 እስከ 90 ብር ልትገዙት ትችላላችሁ ... የውሀው መጠንና ጥራት እራሱ ምርት ሆኖ ሳለ ለተመሳሳይ እቃ የተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ዋጋ አላቸው ። እንዲህ ያደረገው ግን የቦታዎቹ ጥራት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ዋጋችሁ የረከሰ አይነት እና ሰዎች ሲያራክስዋችሁ አይነት ስሜት ሲሰማችሁ ግድ የላችሁም የናንተ ዋጋ ውድ ወደሆነበት ቦታ ቀይሩ . .እራሳችሁን በሚያበረታቷችሁና ዋጋችሁን በሚያሳድጉ ሰወች መካከል አድርጉ ። ለማይመጥናችሁ ቦታ ጊዜ አትስጡ።
#Share አድርጉት
©Social media
@psychoet
“ሜሎሪና” ታሪካዊ የሥነልቡና ልብወለድ የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበብ ሚና የሚተርክና የአስተሳሰብ ልዕልናን የሚያሳይ ልብወለድ መጽሐፍ ነው ፡፡ በአቀራረቡም #የሥነልቡና_ምክሮችንና ሀሳቦችን #ከታሪካዊ_ክስተቶች ጋር አጣምሮ ይዟል ፡፡

በኹለት ሀገራዊ ቋንቋዎች አማራጭ (በዐማርኛና በአፋን ኦሮሞ) ቀርቧል። በአቀራረቡም የሥነ- ልቡና ምክሮችንና ሀሳቦችን ከታሪካዊ ክስተቶች ጋር አጣምሮ ይዟል ፡፡

በመጽሐፉ የውስጥ ገጽ እንዲሀ ይለናል !!


#ሜሎሪና - ስውር ጥበብ
‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››

‹‹... በምድር ላይ የሚወዱትን ሰው በሞት እንደመቀማትና ተስፋ ያደረጉትን እንደማጣት ትልቅ ህመም የለም፡፡ ሲደጋገም ደግሞ ሐዘን፣ ሥቃይ፣ ችግርና መከራ እንደመጫሚያና ልብስ አጥልቀዋቸው የሚዞሩ ያህል ይሰማል፡፡››

ገጽ 106


#Melooriinaa - KALAQA DHOKATAA

“Dirreen lolaa inni guddaan sammuu namaati, Injifannoo guddaan of mo’uudha”

በኹሉም መጽሐፍ መደብር ያገኙታል የአፋን ኦሮሞ ትርጉም በጃዕፈር መጻሕፍት እየተከፋፈለ ይገኛል።
@psychoet
መልካም ሰንበት!

ቀኑ በራሱ ጥሩም ሆነ መጥፎ ኹኖ አይመጣም እኛ ግን በአስተሳሰባችን፣ በባህሪያችን፣ በአዋዋላችን፣ በስራችን ቀኑን ጥሩም መጥፎም የማድረግ ምርጫ አለን፡፡ ስለዚህ በምርጫችን እንደሰት፡፡ መልካም ሰንበት፡፡

@psychoet
ደስተኛ ሕይወት ለመኖር እነዚህን ተግባሮች ልምዳችን እናድርግ
#መልካም የደስታ ሳምንት

1. ምስጋና ለደስተኛ ሕይወት 😀

🙏 አመስጋኝ የሆኑ ሰዎች ምስጋና ቢስ ከሆኑ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡
እውነት ነው ህይወት በፈተና፣ ችግር እና ውጣ ውረድ የተሞላች ናት፡፡ ይሁን እንጂ ፈተናም ቢሆን ራሱን የቻለ በጎ ጎን ይኖረዋል፡፡ ፈተና ሊያስተምረን፣ ሊያንጸን፣ መልካም አጋጣሚ ሊፈጥርልን ይችላል፡፡ ስለሆነሞ በማንኛውም አጋጣሚ አመስጋኞች መሆን የበለጠ ደስተኛ ያረገናል ፡፡
🙏በቅርባችን የሚገኙ ሰዎች የሚገባ ነገርም አድርገውልን ቢሆን እነሱን ማመስገን ከውስጣችን የሚወጣው አወንታዊ ሀይል (Positive energy ) ስለሆነ ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች መልካም አቅምን እንገነባለን ፡፡


2. ቀና ማሰብ ለደስተኛ ሕይወት 😀

ቀና ማሰብ ብዙ እጅግ በጣም ብዙ ጥቅም አለው፡፡ አንዱ ትርፉ ደስታ ነው፡፡ ቀና አሳባዎች ቀና ከማያስቡ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለግን “ይሆናል፤ ይቻላል፤ ይሳካል፤ ለበጎ ነው ወዘተ” ማለትን እንለማመድ፡፡ ከተራራው ባሻገር ላለለችው ፀሐይ ትኩረታችንን እንሰብስብ፡፡

የዓለምን ችግር ሁሉ ጫንቃቸው ላይ ተሸክመው የሚኖሩ ይመስል ፊታቸው የማይፈታ፤ በጎ ነገር የማይታያቸው፤ ሳቅና ጨዋታ ጠል የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ ኑሯቸው ዳገት በዳገት ብቻ የሆነው አእምሮአቸው በአሉታዊ ሃሳቦች በመሞላቱ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዕድል በራቸውን ሲያንኳኳ ድምጹ ረበሸን፤ እንቅልፍ ነሳን ወዘተ ብለው የሚያማርሩ ዓይነት ናቸው፡፡ ኖርማን ቪንሰንት “The Power Of Positive Thinking” በሚለው መጽሐፉ እንዲህ ይላል፡- “የደስታ ምስጢር ልብን ከጥላቻ ማጽዳት፤ አእምሮን ከጭንቅት ነፃ ማድረግ እና ብዙ መስጠት ነው፡፡ ፀሐይ ስትወጣ እና ስትጠልቅ የምታንጸባርቀውን ውበት እያያችሁ የምትደነቁ ሰዎች ሁኑ፤ ለሌሎችም እንደ ራሳችሁ አስቡ፡፡ ይህንን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት ያህል ሞክሩት፤ በውጤቱም ትደነቃላችሁ”፡፡

መልካም የደስታ ቀን!

ይቀጥላል ...
#Share
👍👍👍 @psychoet
2024/09/28 17:23:09
Back to Top
HTML Embed Code: