Telegram Web Link
ወደ ከፍታህ ውጣ!!

🍂 ታላቁን ንሥር አሞራ (Eagle) የሚደፍረው ቁራ ብቻ ነው ። ቁራ በንሥሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥና ማጅራቱን ደጋግሞ በሹል መንቁሮቹ ይነክሰዋል ።

🍂 ንሥሩ ፤ የቁራው ንክሻ ቢያሳምመውም ከቁራው ጋር በመታገል ጊዜውንና ጉልበቱን አያባክንም ። ንሥሩ ክንፎቹን ዘርግቶ ወደ ላይ ከፍ ከፍ ከፍ እያለ ይበራል ። በቃ ከፍታውን እየጨመረ ወደ ሰማይ ያሻቅባል ። ንሥሩ ከፍታውን በጨመረ ቁጥር ቁራው የመተንፈስ ችግር ያጋጥመዋል ። በመጨረሻም ቁራው በሚያጋጥመው የኦክስጅን እጥረት ይሞትና ሬሳ ሆኖ ወደ መሬት ይወድቃል ።

መልእክት

🍂 ዝም ብለህ ወደ ላይ ወደ ከፍታህ ውጣ ፤ ቁራዎቹ ከአቅማቸው በላይ መሄድ ስለማይችሉ ተመልሰው ይወድቃሉ
©Social Media

@Psychoet
ወደ Facebook ፔጃችን እየተቀላቀላችሁ ስላላችሁ እናመሠግናለን፡፡
https://www.facebook.com/psychologyabc/

አዲስ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠና በቅርቡ ስለምንጀምር በስልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ ራሳቻሁን እያዘጋጃችሁ ጠብቁን ፡፡

መልካም ምሽት !
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ወደ Facebook ፔጃችን እየተቀላቀላችሁ ስላላችሁ እናመሠግናለን፡፡ https://www.facebook.com/psychologyabc/ አዲስ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠና በቅርቡ ስለምንጀምር በስልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ ራሳቻሁን እያዘጋጃችሁ ጠብቁን ፡፡ መልካም ምሽት !»
« #ደስታ

🔴የሰው ልጅ በሙሉ በዋናነት ህይወቱን የሚመራው ደስታን #በመፈለግና የበለጠም ለመደሰት ነው፡፡
:
🔴ሁሉም ሰው ደስታን የትና እንዴት ለማግኘት እንደሚቻል ያውቃል ባይባልም በየትኛውም የህይወቱ መስክ ውስጥ ግን ደስተኝነት በእጅጉ
እንደሚያስፈልገው ያውቃል፡፡
:
🔴እንኳን የዛሬውና የወደፊቱ ህይወታችን አይደለም የእኝነታችን ማንነት ሳይቀር የሚገነባው በደስታ ውስጥ ወይም ደስታን በመፈለግ ውስጥ ነው፡፡
:
🔴በእርግጥ ደስተኛ አለመሆን ይቻላል፡፡ ወይም አንዳንዶች እንደሚሉት በህይወቴ የተደሰትኩባቸው ብለው የሚያስታውሷቸው ቀናት ጥቂት ብቻ ይሆናሉ፡፡
:
►ይህም ማለት ብዙ ጊዜያቸው ያልተደሰቱበት እንደሆነም በተዘዋዋሪ መናገራቸው ነው፡፡
:
►መደሰትም ሆነ አለመደሰት ይቻላል፤ ምርጫም ጭምር ነው፡፡
:
☞አምላክ ለዓለም ህዝብ ያስተማረው ትልቁ ሕግ ፍቅርን ቢሆንም ፍቅር ግን ያለገደብ መፍሰስ የሚችለውና የሚጀምረው ደስተኛ በሆኑ ሰዎች ውስጥ ነው፡፡

ፍቅር አንዱ ሌላውን የማስደስትና የማርካት ጥበብ ነው፡፡
:
ደስተኛ የሆነ ቤተሰብ ውስጥ ፍቅር አለ፤ ከትዳር ውስጥ ደስታ ሲደበዝዝ ደግሞ ፍቅርም ይደበዝዛል፡፡
:
እናም ደስታ የፍቅር መሠረትና ማጣፈጫው ስለሆነ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ስነ ፍጥረት ያስፈልጋቸዋል፡፡
:
☞በእርግጥ በሁሉም ሰው ደስታን ይፈልጋል፡፡ ይሁን እንጅ አብዛኛው ሰው በህይወቱ ውስጥ ዘለቄታዊ ደስታ የለውም፡፡
:
እንደውም አንዳንዱ በገነት ካልሆነ በቀር በዚህች ዓለም መደሰት የሚቻል የማይመስለውም አለ፡፡
:
🔴በሌላ በኩልም መደሰት የሚፈራም ሰው አለ፡፡ በአንዳች ነገር መደሰት በቀጣይ መጥፎ ነገር ያመጣብኛል ብሎ በመፍራት ደስታውን እንደልቡ ማጣጣም የሚፈራም አይጠፋም፡፡
:
🔴እርግጥ ነው በማህበረሰቡ ደረጃም አንድ ሰው ሲደስት ካየን “ዛሬ ደግሞ ምን አገኘና ነው?” የምንል ጥቂቶች አይደለንም፡፡
:
ወይም ደግሞ “ምነው እከሌ ሳቅ ሳቅ አለው፤ ጀማመረው እንዴ ?” በማለት ያለምንም ነገር መደሰትን እንደመቀወስ የምንቆጥር ቀውሶች ጥቂት አይደለንም፡፡

#ይኸውልህ_ወዳጄ
:
☞በእርግጥም ደስታ ለጥቂቶች ብቻ የሚገለጥ ሚስጥር አይደለም፡፡
:
√ደስተኛ መሆን እንፈልጋለን ግን አልቻልንም የሚሉ ሰዎች ገጥመውህ ያውቃል?
:
√ነገር ግን ለመደሰት ከየት ልጀምር? የሚለውን ጥያቄ ግን በሚከተለው መልክ በጥቂቱ መቃኘቱ ግድ ይልሃል፡፡

➊.ደስተኛ ለመሆን ቀጠሮ አትያዝ።

ህይወቴ ሲቀየር፣ ስኬታማ ስሆን፣ ያሰብኩትን ሳሰካ እደሰታለው እያልክ የምታስብ ከሆነ፤ ደስታህ መቼ እንደሚመጣ አታውቀውም፤ መቼ እንደምትመጣ የማይታወቅ ወዳጅህን እንደመጠበቅ ሰቀቀን ይሆንብሃል።
:
ብዙዎቻችን ጤናማ፣ ደስተኛ እና ውጤታማ መሆንን እንመኛለን። ለዚህም የተዋበ መልክ እና ቁመና፣ የተትረፈረፈ ገንዘብ፣ ቆንጆ መኪና አልያም ቪላ ቤት እንዲኖረን እንሻለን።

ይሁን እንጂ እነዚህም ሆኑ ሌሎች የተመኘናቸው ነገሮች ሁሉ ቢሟሉም የፈለግነውን ደስታ እና ጤና ላናገኝና ስኬታማ የሆንን መስሎ ላይሰማንም ይችላል።
:
➋.ደስተኛ ሰው ከዛሬ ጋር በቅጡ የተግባባ ሰው ነው።
:
➌.ደስተኛ ለመሆን፤ የግድ ሃብታም፤ ስኬታማ እና ታዋቂ መሆን
አይጠበቅብንም።
:
➍.እውነተኛ ደስተኛ ሰው በሌለው ነገር እየተጨነቀ ዛሬውን የሚያባክን ሳይሆን፤ ባለው ነገር እየተደሰተ የሌለውን በተስፋ የሚጠብቅ እጅግ ብልህ ነው።
:
➎.ለማመን ቢከብደም ሰው በምንም አይነት የኑሮ ሁኔታ ላይ ቢሆንም ደስተኛ መሆንን ምርጫው ካደረገ፤ በእርግጠኝነት ደስተኛ መሆን ይችላል።
:
➏.ኑሮዋችን እንደ እይታችን ይወሰናል፤ የጎደለንን እያየን ማማረር፤ ወይም ያለንን እያየን ማመስገን።
:
►ሁለቱም ምርጫዎች በኑሮ ገበታችን በየቀኑ የሚቀርቡ ናቸው፤ አስተሳሰባችን ምርጫችንን ይወስነዋል።
:
➐.እርግጥ ነው ደስተኛነት፤ በየቀኑ መፍለቅለቅ አይደለም፤ ምክንያቱም ህይወት በውጣ ውረዶች የተሞላች ስለሆነች።
:
➑.ደስተኛ ለመሆን ሁሌም ምርጫችን ከሆነ ግን፦

ቢያንስ ወጣውረዱን ለመጋፋጥ አንሸበርም፣

ቀናችን በሃዘን እና በማማረር አይባክንም፣

ከሌሎችን ሰዎች ጋር ስንሆን ደስ የሚል መንፈስን እናንጸባርቃለን።

➒.ደስታ ተላላፊ ነው፣

ሳቅ ልክ እንደ ሰደድ እሳት ይቀጣጠላል፣

ደስተኛ ስትሆን በመንገድህ የምታገኛቸው ሰዎች ላይ ሁሉ ትልቅ ተጽዕኖ እደምታመጣ እመን።

➓.ደስታ የምኞት ውጤት፣ የማሳደድ ትርፍም አይደለም።
:
►ደስታን ተመኝቶ ያገኘ፣ አሳድዶ የያዘ የለም።
:
➊➊.ደስተኛ ለመሆን አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው።
:
ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም።

በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው።

ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።....አበቃሁአመሰግናለሁ

#ፈጣሪ_ሀዘናችንን_አርቆ_ደስታችንን_እልፍ_ያድርግልን_አሚን!
:
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
:
"በደስታ ያቆየን"

@psychoet
https://www.facebook.com/psychologyabc/
መልካም ምሽት ! #Share

በአንድ አካባቢ የሚኖሩ እጅግ ባለጠጋ ሰው ነበሩ ፡፡ እኚህ ሰውዬ ከሀብታቸው የተነሳ ያላቸውን ንብረት ብዛት እንኳን የማያውቁ ለሰው ሁሉ እረጂ ደግና ቸር የነበሩ ሲሆኑ በሕይወታቸውም በጣም የሚሳሱለትና የሚወዱት አንድ ወንድ ልጅ ብቻ ነበራቸው ፡፡ ልጁም በጣም ቆንጆና በህብረተሰቡ መሀል የሚወደድ ነበር ፡፡

ይሁን እንጂ የዚህ ባለጠጋ ልጅ ከህፃንነቱ ጀምሮ በምሽት ትልቅ ፍርሀት ፣ ጭንቀት ድንጋጤ ነበረበት ፡፡ በተለይም በማታ ጊዜ ከሚተኛበት አልጋ ስር አውሬ ያለ ስለሚመስለው ብዙ ቀን እንቅልፍ ተኝቶ አያውቅም ፡፡ ይሄም ተባብሶ አልጋውን እንዲፈራ ፣ በለሊት እንዲቃዥ ብሎም እንዲጨነቅና ጤናው እንዲታወክ አረገ ፡፡
ባለጠጋ አባቱም ይህ ጭንቀት እንዲለቀው ያላረጉት ጥረት አልነበረም ፡፡ ብዙ ሀኪም ቤት ፣ ብዙ መድሀኒት ፣ ብዙ ባህላዊ አዋቂዎች ጋር ቢወሰዱት ለውጥ ሊመጣ አልቻለም ፡፡ ማታ ማታ አልጋው ላይ ሲተኛ ከአልጋው ስር አውሬ ያለ ስለሚመስለው በፍፁም አይተኛም ፡፡

በመጨረሻ ግን በሰው ሰው አባቱ አንድ ሳይኮሎጂስት እንዳለ ይሰሙና ልጃቸውን ካሻለላቸው ብዙ ብር ሊሰጡት ቃል ይገቡለታል ፡፡ ይህም ሳይኮሎጂስት ደስ ብሎት ልጁ ወዳለበት ክፍል ይገባና መኝታ ቤቱን ከተመለከተ በኀላ ትንሽ አሰብ አርጎ ለአባትየው መጋዝ እንዲሰጡት ይጠይቃል ፡፡ ከዛም መኝታ ቤት ገብቶ የልጁን አልጋ አራት እግር ቆርጦ አልጋውን ከመሬት ጋር አገናኘው ፡፡ ከዛም ለልጁ "እንኳን ደስ አለህ ! እስከዛሬ ለሊት ለሊት አውሬዎቹ እየመጡ አልጋ ስር ይሆኑና ያስፈሩህ ነበር ፤ አሁን ግን መሬት ስለወረደ ከስር መግባት አይችሉም ስለዚህ ከአሁን በኀላ ለሊት ለሊት አይመጡም " አለው ፡፡ ልጁም ከዛን ቀን ጀምሮ በሰላም ሳይፈራ ለሊት ለሊት በደንብ መተኛት ጀመረ ፡፡

ደህና አምሹልኝ !
ለሌሎችም በማጋራት ደስ ብሎን እንተኛ 😂😁
@psychoet
ወድቆ መነሳት
በሕይወት ተስፋ አትቁረጡ ፤ አሁንም ገና አልረፈደም ።
በዚህ የሚስማማ #Share

ህይወት ረዥም መንገድ ናት! ጉዞዋም ቀጥተኛ ፤ ገባ ወጣ ፤ አቀበትና ቁልቁለት የበዛበት መዳረሻዋም እሩቅ ሊሆን ይችላል፡፡ በህይወት መንገድ ላይ ወደ ሚፈልጉበት የስኬት ቦታ ለመድረስ ወድቆ መነሳት ወይም ስህተት መስራት አንድ አጋዥ የህይወት ምርኩዝ ነው፡፡ ነገር ግን ስንቶቻችን ከልጅነታችን አንስቶ ስህተት መስራት ለነገ ስኬትና ጠናካራ ማንነት እንደሚያበቃን እየተነገረን ነው ያደግነው? ከዚያ ይልቅ ስህተት አለመስራትና ፍጹምነት የጠንካራ ስብዕና መገለጫ ተደርጎ አንቱታን እንደሚያጎናጽፍ ነው የምናውቀው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ልጆች በሚሰሩት ስራ ስህተት እንዲሰሩ ማበረታታት በእራስ መተማመናቸውን እንደሚያሳድግ እንመለከታለን፡፡

እንደ ሱዛን ባርተል ልጆች አንድን ነገር ለመተግበር በቀላሉ በዕውቀት ከመካን ይልቅ ስህተት እየሰሩ ደጋግመው በመሞከር የሚሰሩ ከሆነ ትልቅ ሰው በሚሆኑበት ወቅት ተግዳሮትን የመቋቋምና በጫና ውስጥ አልፎ ውጤታማ የመሆን ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ በታች ወላጆች ልጆቻቸው ስህተት በሚሰሩበት ወቅት ከቁጣና ተግሳጽ ይልቅ እንዴት ያበረታቷቸዋል የሚለውን እንመለከታለን፡፡

1. ስህተትን ፈጥኖ አለማረም

ጤናማ ልጆች ለማሳደግ ወላጆች ልጆቻቸው ስህተት በሚሰሩበት ወቅት ስህተታቸውን ፈጥኖ ከማረም መቆጠብ አለባው፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን ስህተት ደጋግመው የሚያርሙ ከሆነ በልጆች ጤና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይፈጥራል፡፡ በዚህም ምክንያት ልጆች ስህተት በሚሰሩበት ወቅት እራሳቸውን መቆጣጠር እስኪሳናቸው ድረስ ውስጣቸው ሊረበሽ ይችላል፡፡ ዶክተር ፍሬድ ዘሊንግር ወላጆች ልጆቻቸው ስህተት ሲሰሩ አስተያየት ከመስጠትና ከተግሳጽ የሚቆጠቡ ከሆነ ልጆቻቸው በእራሳቸው ጥረት ስህተታቸውን እንዲያርሙና ወደ መፍትሄ እንዲመጡ ያስችላል በማለት ስህተትን ፈጥኖ ያለማረምን ጥቅም ያስረዳል፡፡

2. ደጋግሞ እንዲሞክሩ ማበረታታት

ልጆች ስህተት በመስራታቸው ሊጨናነቁ ስለሚችሉ፤ ወላጆች ጤናማ ልጆች ለማሳደግ ይረዳቸው ዘንድ ልጆቻቸው በድርጊታቸው ስህተት በሚሰሩበት ወቅት ተስፋ እንዳይቆርጡና ደጋግመው እንዲሞክሩ የሞራል እገዛ ሊያደርጉላቸው ይገባል፡፡

3. ኃላፊነትን ማስተማር

ወላጆች ልጆቻቸው በትህምርት ቤት ስራና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስህተት ሲሰሩ የልጆቻቸውን ስህተት ለማስተባበል በማለት ጥፋታቸውን በመምህራኖቻቸው ወይም በሌላ ሰው ላይ ከማስታከክ ታቅበው ልጆቻቸው ስለሰሯቸው ስህተቶች ኃላፊነት እንዲወስዱና ስህተቶቻቸውን የሚያርሙበትን ዘዴ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም ልጆች ስለሰሯቸው ስህተቶች ኃላፊነት ስለሚወስዱ በእራስ መተማመናቸውን ያሳድጋል፡፡

4. ትዕግስተኛ መሆን

ልጆች ተደጋጋሚ ስህተት ሲሰሩ የወላጆች ጣልቃ ገብነት እንደ ሁኔታው አስፈላጊ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ወላጆች እስከ መጨረሻው ሙከራ ከግብረ መልስ መታቀባቸው የልጆቻቸውን ተነሳሽነት ስለሚጨምረው ነገሮችን በጥሞና የሚመለከቱበት ትዕግስት ያስፈልጋቸዋል፡፡

5. የማይሳካ ግብ አለማስቀመጥ

ወላጆች ልጆቻቸው በሚሰሩት ስራ ላይ ትልቅ ግምት (expectation) ወይም ሊሳካ የማይችል ግብ የሚያስቀምጡ ከሆነ በልጆቻቸው ላይ ትልቅ ጫና ይፈጥራሉ፡፡ አልፎም ወላጆች ልጆቻቸው ይህንን ካላሳኩላቸው የበታችነት ስሜት ይሰማናል ብለው የሚያስቡ ከሆነ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም ወላጆች እራሳቸው ስላስቀመጡት ሊሳካ ስለማይችል ግብ ሳይሆን ማሰብ ያለባቸው ስለልጆቻቸው ጥረትና መነሳሳት ነው፡፡

6. ውጤትን ሳይሆን ጥረትን ማድነቅ

ልጆች በስራቸው ሂደት እዚህ ግባ የሚባል ውጤት ላያስመዘግቡ ይችሉ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ከአመርቂ ውጤት ይልቅ በስህተት ላይ ስህተት ቢሰሩ እንኳን ወላጆች ዘውትር ትኩረት ሰጥተው መመልከት ያለባቸው የልጆቻቸውን ድርጊት ሳይሆን እዚህ ለመድረስ የሄዱበትን ርቀት በመመልከት ማድነቅ ያስፈልጋል፡፡ ጥረትን ማድነቅ ልጆች በጫናና በማይመች ሁኔታ ውስጥ ስህተት እንሰራለን ብለው እንዳይሰጉና በመውደቅ ውስጥ መነሳት እንዳለ እንዲያስቡ ይረዳቸዋል፡፡

በአጠቃላይ ወላጆች ልጆቻቸው በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ ስህተት እንዲሰሩና እንዲወድቁ ማበረታታት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም በመሆኑ ልጆች በስራቸው ሂደት ውስጥ መሳሳትንና መውደቀን ትልቅ ትምህርት ቤት እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፡፡ በተጓዳኝም አንድ ሰው ሲሳሳት አእምሮው ለፈጠራ ዝግጁ እንደሚሆን ፤ መውደቅና ደጋግሞ መሞከር ስንፍና አለመሆኑን እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል፡፡ አልያ ግን ስህተት አለመስራትና ፍጹም መሆን አንድ የጥሩ ልጅ ማንነት መገለጫ አድርገው እንዲወስዱት ስለሚያስገድዳቸው በኋላ ማንነታቸው ላይ ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ይህ እንዳይሆን ልጆች ስህተት በሚሰሩበት ሰዓት ወላጆች ምንም እንዳልሆነ በማሳወቀና ማንኛውም ሰው ውጤታማ መሆን የሚችለው ተሳስቶና ደጋግሞ በመሞከር መሆኑን ከራስ ልምድ በመነሳት ወይም የታላላቅ ሰዎችን ተሞክሮ እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የልጆች ስህተት መስራት ለቀጣይ ስራ ስንቅ እንጂ የስፍናና የአለማወቅ ምልክት እንዳልሆነ አድርገው ስለሚወስዱት በውስጣቸው የደስተኝነት ስሜት አንዲፈጠር ያግዛቸዋል፡፡ ወድቆ መነሳት የአሸናፊነትንና እችላለሁ የማለትን ስነ-ልቦና ያጎናጽፋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከላይ የተመለከትናቸው ነጥቦች አወንታዊ ለሆኑ ድርጊቶች ብቻ ነው፡፡ መልካም ጊዜ!

©zepsychology
(አንቶኒዮ ሙላቱ)

Join My Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
እንኳን ደስ አለን !
የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን 7ኛ ዙር ስልጠና ሀምሌ 17 እና 18 ይጀመራል

ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ 3-5 | ቅዳሜ 10-12
እሑድ 3-5 | እሑድ 10-12

🔔በአንድ ስልጠና 6 ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው ይመዝገቡ ፡፡

የስልጠና አጠቃላይ ክፍያ መመዝገቢያና ሰርተፊኬት ጨምሮ ለ1 ወር - 500 ብር

ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ

የሚሰጡት ስልጠናዎች
✿የሕይወትን አላማ ማወቅ
✿የሕይወት ግብ አዘገጃጀትና ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
✿የስሜት ብልሀት
✿ፍርሀትን ማሸነፍ
✿ተግባቦት

ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ 219 (Nova Training Center)

@psychoet
#Melooriinaa
KALAQA DHOKATAA

Yeroo dhiyoo keessatti Afaan Oromoontiin ni dhiyaata.

ሜሎሪና መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተተርጉሞ ለገበያ በቅቷል ፡፡ ሜክሲኮ- ጃዕፋር መጽሐፍ መደብር ማግኘት ይቻላል ፡፡ በክልል ከተሞች ከሰኞ ጀምሮ መሠራጨት ይጀምራል፡፡

“Dirreen lolaa inni guddaan sammuu namaati, Injifannoo guddaan of mo’uudha”

‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››

Nahusenai Tsedalu - ሜሎሪና
#ተሰሚነት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ብዙዎቻችን የሚጎለን ክህሎት ስለሆነ ሌሎችም እንዲማሩ አንብበን #Share እናርገው

“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡ ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡

ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡

ቅለት

ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡

ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ

“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡

በራስ መተማመን

አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ ጉልበት አላቸው፡፡

በሌሎች ዓይን ማየት

ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣ ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ መቼም አይጠፋም፡፡

ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡

እጥረትን መፍጠር

ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣ የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣ በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡

ዝግጅት

ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመናችንንም ይገነባል፡፡

ለምሳሌ እነዚህን በሙሉ ክህሎቶች ዶ/ር ምህረት ላይ እናገኛለን ፡፡ የመሰማቱ አንዱ ሚስጢር ይሄ ነዉ ፡፡ ሲያስተምር አይታችሁ ከሆነ የሚያስተምረውን ነገር ቀለል አርጎ ፣ በራስ መተማመን ለአድማጭ በሚስብ መልኩ ያደርጋል ፡፡ ይህ በሁላችን አድማጮቹ ዘንድ ተሰሚነትን ፈጥሮለታል ፡፡ በሌላ በኩል አንድ ሰፈር /ስራ ቦታ የምናውቀውን ሳያቋርጥ የሚያወራ ፣ ንግግር የማያስጨርስ ሰው ስናስብ እንኳን ለመስማት ከሱ ጋር ለማውራት ይቀንቀናል ፡፡ እንግዲህ ሚስጥሩ ይሄው ነው ፡፡

በሰዎች ዘንድ ለመሰማት በዕውቀትና በጥበብ እናውራ !
(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#Share & #Like oue page - fb.com/psychologyabc
_____________________________
#ዛሬ_ቀኑ_ደስ_ይላል
www.tg-me.com/psychoet

አንድ እድሜያቸው የጠና ማየት የማይችሉ ሽማግሌ ሁል ጊዜ መንገድ ዳር ተቀምጠው ይለምኑ ነበር ፡፡ ሁሌም በሚለምኑበት ወቅት አንድ የማይለያቸው ጽሑፍ የያዘ ካርቶን ነበር ፡፡ በካርቶኑ ላይ " ማየት አልችልም እርዱኝ " ይላል ። አላፊው አግዳሚም ሰው ጽሑፉን እያየ በአጠገባቸው ያልፋል ፡፡ አንዳንዱ ያለውን ጣል ጣል ያረጋል የቀረው ደሞ ትቶ ያልፋል ፡፡

ነገር ግን አንድ ቀን በጠዋት ይህ ተከሰተ ፡፡ ከዚህ በፊት የማያውቁት ሰው ወደ እሳቸው ቀረብ ብሎ ጽሑፍ የያዘውን ካርቶን አንስቶ ጫር ጫር አድርጎ መልሶ ካስቀመጠው በኀላ ምንም ሳይሰጣቸው ጥሎ ሄደ ፡፡ ሽማግሌው በሚሰሙት ግራ ተጋቡ ። ሰውየው አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ብዙ ብር ሊሰጣቸው አልያሞ ችግራቸውን ሊጠይቃቸው መስሎቸው ነበር ነገር ግን ምንም ሳይል ነበር ጥሎአቸው የሄደው ፡፡

ትንሽ ቆይቶ ግን የሳቸውን ሁኔታ የሚቀይር ነገር ተፈጠረ ፡፡ አላፊ አግዳሚው ሁሉ ያለውን እያወጣ ይሰጣቸው ጀመረ ፡፡ ከሳንቲም አልፎ ብዙ ሰዎች ብር በእጃቸው ይሰጡአቸው ጀመር ። ሽማግልው ግራ ተጋቡ ቆይ ያ ሰውዬ ምን አርጎ ነው የሄደው ብለው ራሳቸውን ሲጠይቁና ግራ ሲጋቡ ዋሉ ፡፡ በዛች ሰአት ብቻ ሰዎች የረዱአቸው ወር ሙሉ ለምነው ካገኙት ይበልጥ ነበር ፡፡

በዚህ ግርምት ቆይተው ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደሳቸው ቀረበ ፡፡ እሳቸውም በጥርጣሬ "ቅድም አንተ ነህ ጽሑፍ የጻፍከው ? ቆይ ምን ብለህ ነው የጻፍከው? " ልጄ አሉት ። ሰውየውም በደስታ " አባቴ እኔ ሳይኮሎጂስት ነኝ ፡፡ በእርግጥ በገንዘብ አልረዳሆትም ነገር ግን ጽሑፉን እንዳየሁ የተጻፈው ነገር ሰዎች እንዲረዱዎት ብዙ እንደማያስችል ስላወኩ የተጻፈውን ነው የለወጥኩት ፡፡ መጀመሪያ ' #ማየት_አልችልም_እርዱኝ ' ይል ነበር እኔ ደግሞ ከጀርባው ' #ዛሬ_ቀኑ_ደስ_ይላል_ግን_እኔ_አላየውም ' ብዬ አስተካከልኩት ፡፡ አዩ አባቴ ሰው ይህን ሲያነብ የእርሷን አለማየት ሳይሆን የራሱን ማየት ስለሚያስብ በደስታ ለእርሶ ያለውን ይለግሳል ። " አላቸው ፡፡ ሽማግሌው እጁን ከያዙ በኀላ እያመሰገኑት እጁን ይስሙ ጀመር ፡፡

(በናሁሰናይ ፀዳሉ) ተፃፈ

መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ !
እወዳችኀለሁ!
መልዕክቱ መልካም ከሆነ መልካምነትን ለሌሎች አካፍሉ #Share
JOIN ME IN TELEGRAM www.tg-me.com/psychoet
በቴሌግራም ይቀላቀሉ www.tg-me.com/psychoet
የ አንድ ወር የሕይወት ክህሎት ሰልጣኞቻችን (LIT ተመራቂዎች) እንኳን ደስ አላችሁ !
🎊🎉🎉🎉🎊🎉🎉🎉🎊🎊🎉

ቀጣዩን አመት በምኞት ሳይሆን በእቅድና በለውጥ የምትሻገሩበት እንዲሆን እንመኛለን ፡፡ ለውጥ በተግባር ስላሳያችሁን እናመሠግናለን ፡፡

ለአዲስ ሰልጣኞች ልዩ የክረምት ስልጠና አዘጋጅተናል፡፡ @Psychoet
ቀኑ ደረሰ ! አዲሱን አመት በብሩህ ተስፉ ይቀላቀሉ!
7ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን ሀምሌ 17 እና 18 ይጀመራል

ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ 4-6 | ቅዳሜ 10-12
እሑድ 4-6 | እሑድ 10-12

🔔በአንድ ስልጠና 6 ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው ይመዝገቡ ፡፡

የስልጠና አጠቃላይ ክፍያ መመዝገቢያንና ሰርተፊኬትን ጨምሮ - 500 ብር ብቻ

ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ

የሚሰጡት ስልጠናዎች
✿የሕይወትን አላማ ማወቅ
✿የሕይወት ግብ አዘገጃጀትና ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
✿የስሜት ብልሀት
✿ፍርሀትን ማሸነፍና ተግባቦት

ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

በተጨማሪም ቅዳሜና እሑድ ለማይችሉ ከሰኞ - አርብ በስራ ሰዓት ልዩ ስልጠና አዘጋጅተናል ፡፡

0912664084 ይደውሉ ይመዝቡ
የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ 219 (Nova Training Center) @Ethionova

@psychoet
ንዴትን ማብረድ

ለብዙ ሰው መድኃኒት የሆነ ሞክር #Share it

አንዳንድ ሰዎች ምንም የሚያበሳጭና የሚያስቆጣ ነገር ሳይኖር በትንሹ ይናደዳሉ ወይም ይቆጣሉ፡፡ ንዴት በመጠኑ ሲሆን የጤናማ ባህርይ መገለጫ ነው ነገር ግን መጠኑን ሲያልፍ ግንኙነትን ከማበላሸት ባሻገር ጤናንና አእምሮአዊ ሰላምን ይነሳል፡፡ ንዴትን በፍጹም ማስወገድ ባይቻልም ማስታገስና ማብረድ ይቻላል፡፡ ታዲያ ንዴትን እንዴት ማብረድ ይቻላል? እነሆ!

1.ከመናገር በፊት ማሰብ፡-በቶሎ የሚናደዱ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ አንድ ነገር ከመናገራቸው በፊት ጥንቃቄ አያደርጉም፡፡ በሚናገሩት ነገር ሰዎችን ያስቀይሙና “ምነው አፌን በቆረጠው!” ብለው ይጸጸታሉ፡፡

2.ስሜትን አረጋግቶ እራስን መግለጽ፡- ሳያስቡ መናገር ጸጸትን እንደሚያመጣ ሁሉ የተናደዱበትን ምክንያት ስሜትን አብርዶ አለማስረዳትና አለመናገር በእራሱ ሌላ ንዴት ስለሚፈጥር እራስን መግለጽ ያስፈልጋል፡፡

3.መተንፈስ፡- በቀላሉ የሚናደዱ ሰዎች የንዴት ስሜት በሚሰማቸው ሰዓት አንድ እጃቸውን ደረታቸው ላይ አድርገው ቢያንስ ሶስቴ ዓየር በረጅሙ በአፍንጫቸው መሳብና በአፋቸው ማስወጣት ስሜታቸውን ለማረጋጋት ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡

4.ንዴትን ከሚቀሰቅሱ አካባቢዎች መራቅ፡- ንዴትን በቀላሉ መቆጣጠር አስቸጋሪ ከሆነ የንዴት ስሜት በሚፈጠርበት ወቅት አካባቢውን ለቆ መሄድ፡፡ ከቻልክ አካባቢህን ቀይር አካባቢህን መቀየር ካልቻልክ እራስህን ቀይር እንደሚባለው፡፡

5.መፍትሄ መፈለግ፡-የሚያበሳጨኝና የሚያናድደኝ ነገር ምንድን ነው ብሎ ከማሰብ ይልቅ ንዴቴን እንዴት መቆጣጠርና ማብረድ እችላለሁ ብሎ በራስ መፍትሄ ማፈላለግ፡፡

6.ለራስ እውቅና መስጠት፡- ንዴትን በውስጥ አምቆ ያልተናደዱ ከመምሰል ለአእምሮ ሰላምና እርፍት ለመስጠት እንዲያስችል “አዎ እኔ ተናዳጅ ሰው ነኝ ቢሆንም እራሴን መቀየር እችላለሁ“ ብሎ ለራስ ዕውቅና መስጠት፡፡

7.ቂም አለመያዝ፡- ሰዎች የፈለጉትን የሚያናድድ ነገር በእኛ ላይ ቢያደርጉ ይቅር የሚል አእምሮ ካለንና ቂም የማንይዝ ከሆነ ንዴታችን በቀላሉ መቆጣጠር እንችላለን፡፡

8.እውነታውን ለማወቅ መጣር፡- ስሜትን በንዴት ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅረጋ ብሎ ስለሁኔታው ማጤንና የሰከነ ውይይት ለማድረግ መሞከር፡፡

9.ትዕግስትን መለማመድ፡-የመጨረሻዋን የንዴት ጣሪያ ላለመንካት ትዕግስተኛ መሆን፡፡ ይህንን ለማድረግ ዘውትር ትዕግስተኝነትን መለማመድ፡፡

10.የሌሎች ዕርዳታን መሻት፡- አንዳንድ ጊዜ ለዘመናት አብሮ የቆየን ንዴት በእራስ መንገድ ብቻ ለማብረድ መሞከር አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሌሎች ሊያግዙን የሚችሉ ሰዎችን ዕርዳታ መጠየቅ ትልቅ ብልሃት ነው፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©ZePsychology

Join My Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
በአንድ መድረክ ላይ ቻርሊ ቻፕሊን አንድ ቀልድ ቀልዶ ሁሉንም ታዳሚሚዎች በጣም ይስቃቸዋል።ሁለተኛም ያንኑ ቀልድ ደገመዉ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሳቁ።ለሶስተኛ ጊዜ ያንኑ ቀልድ ደገመዉ፤በዚህን ጊዜ ግን ማንም አልሳቀም ነበር።ይህን ያየዉ ቻርሊ ለታዳሚዎቹ እንዲህ አላቸዉ........

"በአንድ ቀልድ ደጋግማችሁ ካልሳቃችሁ ለምን ታዲያ በአንድ ችግር ደጋግማችሁ ትጨነቃላችሁ።" ነበር ያላቸዉ።

በዚህች አለም ላይ ምንም ዘላቂ ነገር የለም ችግራችንም ቢሆን!!!!!!
©ማህበራዊ ሚዲያ
በደስታ ለሌሎች #ሼር ያድርጉት
አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ...እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰው አየ ... እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ እንኳን እንደዚህ ሰዉዬ አልሆንኩ አለ"።
:
ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ከዚያም የታመመው ሰውየ ሆስፒታል ሲደርስ የሞተን ሰው ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና አለ"።
:
ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም? ከሌለን ነገር እኮ ያለን በእጅጉ ይበልጣል ፡፡
:
* # ሕይወት * # ምንድን_ነው ?
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
* 1. መቃበር *
* 2. ሆስፒታል *
* 3. እስር ቤት *
:
በመቃብር ቦታ ሕይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትገነዘባለህ።
:
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ።
:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው።

ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ እንሁን። ስንት ቤተሰቦቻችን ፣ ጓደኞቻችን ዛሬ በሕይወት የሉም እኛ ግን በፈጣሪ ፈቃድ ጊዜያችንን እየጠበቅን በሕይወት መቆየት ችለናል ፡፡ ከሞትን በኀላ ደግሞ በዚህች አለም በሰወች ዘንድ የሚቀርልን ትዉስታ ስራችን ከተጨመረ ደግሞ ፎቶአችን ነዉ ፡፡ ስለዚህ ለሰዋች ደግሞ ሁል ጊዜ መልካም ነገር ሰሪ እንሁን ፡፡ በተጨማሪ ሁሌ አመስጋኝ እንሁን ሌላዉ ቢቀር ይህን ፅሁፍ በማንበባችን አምላክን እናመስግን ምክንያቱም ብዙ ሰዋች 1.ማንበብ ስለማይችሉ አያነቡትም 2.ይህን መልዕክት ስላልጀረሳቸዉ አያነቡትም 3. 4. 5. ...
ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን።
መልካም ሰንበት
Nahu|ናሁ
#Share if you really like it

@psychoet
fb.com/psychologyabc
🐘🐘🐘 እና 🐕🐕🐕
#ከለታት_በአንድ_ቀን_አንድ_ዝሆንና_አንድ_ዉሻ_በተመሳሳይ_ቀን_አረገዙ፡፡
ከሶስት ወር በኀላ ዉሻዋ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኀላም ዉሻዋ በድጋሜ አረገዘች እናም በዘጠነኛዉ ወር ሌሎች ብዙ ቡችሎችን ወለደች ፡፡ ዉሻዋ እንዲህ እያለች ብዙ ቡችሎችን ወለደች፡፡

በ18ኛዉ ወር ግን ግራ የገባት ዉሻ ወደቀድሞ ዝሆን ጓደኛዋ ሂዳ እንዲህ ስትል ጠየቀቻት "እርግጠኛ ነሽ ግን ማርገዝሽን? " ካስታወሽ የ ዛሬ 18 ወር እኩል ነበር ያረገዝነዉ ይሁን እንጂ ባለፋት ወራት እኔ ብዙ ቡችሎችን ወልጄ አሁን ትላልቅ ሁነዋል፡፡ አንቺ ግን እስካሁን የምር እርጉዝ ነሽ? ምን እየሆነ ነዉ ስትል ጠየቀቻት፡፡

ይህን የሰማችዉ ብልህ ዝሆን በእርጋታ እንዲህ ስትል መለሰች ፡፡ ዉድ ጓደኛዬ፥ እንድታዉቂዉ የምፈልገዉ አንድ ነገር አለ፡፡ ያረገዝኩት እኮ ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡ በሁለት አመት አንድ ዝሆን ብቻ ነዉ እኔ ልወልድ የምችለዉ፡፡ ነገር ግን ልጄን በወለድኩ ጊዜና ልጄ መሬት ሲረግጥ መሬት ራሱ ትናወጣለች ፡፡ ልጄ መንገድ ሲያቋርጥ የሰዉ ልጆች ሁሉ ቆመዉ በአድናቆት ይመለከቱታል፡፡ እኔ ያዘልኩት ፅንስ ትኩረትን የሚስብ ነዉ፡፡ የያዝኩት ትንሽ ነገር ሳይሆን ሀያል የሆነ ዝሆን ነዉ ብላ መለሰች፡፡

#ትምህርት / Lesson

💠ሌሎች የራሳቸዉን ግብ በፍጥነት ሲመቱ የኔ አይሳካም ብለን ተስፋ አንቁረጥ በሌሎችም አንቅና ምክንያቱም
፩ . የኛ ስኬት የሚወሰነዉ በራሳችን ትጋት(ፅንስ) እንጂ በሌሎች ላይ ስላልሆነ
፪ . ጥሩ ነገር ሁሌ ግዜ ይወስዳል ( ትልቅ ነገር ለመስራት ብቻ ሳይሆን ለማሰብም ግዜ ይወስዳል ዉጤቱ ግን ታላቅ ነዉ )
፫ . ....
ይህንን ካነቡ አይቀር 👉በዉስጣቸዉ ትልቅ ነገር አለ ለምትሉት ጓደኛ/ዘመድ/ቤተሰብ ይህን #FORWARD #Share ያድርጉ፡፡
🙌🙌🙌
ናሁ|Nahu
@Psychoet
ተስፋ ምኞትና ናፍቆት ብቻ ሳይሆን አለኝታና መተማመን የሚገኝበት ነዉ ፡፡

ተስፋ ከምንኖርበት ቦታ ፣ ካለንበት አካባቢ አልፈንና ተሻግረን አርቀን እንድናስብ የሚረዳን ነዉ፡፡ ተስፋ ሀሳብ ነዉ ፥ ተስፋ ምኞት ነዉ ፡፡ ተስፋ ይሰብራል፥ ተስፋ ያነሳል ፡፡ ይቺ አለም ከሞላ ጎደል ለተስፈኞች ብቻ የሆነች ትመስላለች ምክንያቱም ምንም ነገር ሳይታይ ፣ ሳይሰማ ፣ ሳይዳሰስና ሳይጨበጥ በፊት በሀሳብ ደረጃ እያለ የማይታየዉን ሀሳብ እንዲታይ ፣ ያልተጨበጠዉን እንዲጨበጥ ያረጉት ትላልቅ ተስፈኞች ናቸዉ ፡፡ ስለዚህ ተስፋ እናድርግ ደስ የሚለዉ ለተስፋ ለማድረግ 5 ሳንቲም ወጪ የለውም ... ተስፋ ማረግ መከራ አይሁንብን ፡፡

ስለዚህ ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ እንደምንችል ተስፋ እናድርግ ፡፡ እንደዚህ ጀግና ልጅ በሳር ቤት ብንኖርም ሁኔታዋች ምቹ ባይመስሉም ተስፋችንን ግን አናርቀዉ ከችግራችን ጎን አስቀምጠን ሁሌ ለችግራችንና ለሀዘናችን ያለንን ተስፋ እናሳያቸዉ ፡፡ ምንም እንኳን አሁን መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ዉስጥ ብንሆንም በቅርቡ ወደ በለጠ ደስታ ድል ስኬት እንደምንሸጋገር እንመን ፤ በቅርብ ያስቀመጥነዉንም ተስፋ ሁሌ እንመልከት ፡፡ በዚህ ችግር ዉስጥ የምንኖረዉ ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደሆነ ለችግራችን እንንገረዉ ፡፡ በነገ መልካም ተስፋ ዛሬን በደንብ ጠንክረን እንስራ በደስታም እንኑር ፡፡

የተመቸዉ #Share አይከፈልበትምና !
ናሁ|Nahu @PSYCHOET
7ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠና !

በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ/ ስራ ላይ የምትገኙና የሕይወት ክህሎት ስልጠና መውሰድ የምትፈልጉ ቅዳሜና እሑድ በዚህ ስልጠና ልታገኙኝ ትችላላችሁ ፡፡

ያሉን ፈረቃዎች
🗓እሑድ 4-6 | 🗓እሑድ 10-12
በተጨማሪም ቅዳሜና እሑድ ለማይችሉ
🗓ሰኞ 4-6 | 🗓ረቡዕ 4-6 | 🗓አርብ 4-6 ልዩ ስልጠና አዘጋጅተናል ፡፡

በሳምንት በመረጡት ፈረቃ አንዴ (ለ አንድ ወር የሚቆይ) ስልጠና ከ ሀምሌ 24 ቅዳሜ ጀምሮ ፡፡

🔔በአንድ ስልጠና 6 ሰው ብቻ ስለምናሰለጥን ቀድመው ይመዝገቡ ፡፡

የስልጠና አጠቃላይ ክፍያ መመዝገቢያንና ሰርተፊኬትን ጨምሮ - 500 ብር ብቻ

ይምጡና ለ 2014 ጥሩ የሕይወት ክህሎት ይሰንቁ

የሚሰጡት ስልጠናዎች
✿የሕይወትን አላማ ማወቅ
✿የሕይወት ግብ አዘገጃጀትና ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም
✿የስሜት ብልሀት
✿ፍርሀትን ማሸነፍና ተግባቦትና Public Speech

ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

0912664084 በመደወል/በአካል በመገኘት ይመዝቡ
የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ 4ኪሎ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ 219 (Nova Training Center) @Ethionova

@psychoet
2024/09/28 21:37:09
Back to Top
HTML Embed Code: