Telegram Web Link
#ክፍል_24
#የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፊያ መንገዶች
www.tg-me.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ሁናችሁ ብቸኝነት ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በዚህ ወረርሽኝ ምክንያትስ እቤት በመክረማችሁ የብቸኝነት ስሜት እያጠቃችሁ ነው? እንግዲያውስ ይሄን ስሜተት የማሸነፊያ የሥነልቦና መፍትሔዎችንና ምክሮችን ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡
__________________________
አዕምሮአችን የተፈጠረው የተለያዩ አይነት ስሜቶችን እንዲረዳና እንዲያስተናግድ ነው ፡፡ እነዚህ ስሜቶች አወንታዊና አሉታዊ ሲሆኑ ለኛ ማንነትና አኗኗር ወሳኝነት አላቸው ፡፡ በውስጣችን የሚፈጠሩት አወንታዊ ስሜቶች የሚገነቡንን ያህል አሉታዊ ስሜቶች ደግሞ ከውስጥ እያፈረሱን ከውጭ ደግሞ በድካም ፣ በድብርት ፣ በጭንቀት ፣ ስለ ነገ ባለ ፍርሀት ያስሩናል ፡፡

በአዕምሮአችን ከሚፈጡሩ አሉታዊ ስሜቶች አንዱ ደግሞ የብቸኝነት ስሜት ነው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት እድሜና ፆታ ፣ ሀብትና ስልጣን ሳይለይ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ፣ ከደሀ እስከ ሀብታም የሚያጠቃ አሉታዊ ስሜት ነው ፡፡

አዕምሮአችን " ማንም አይወደኝም ፣ እኔ ተሸናፊ ነኝ ፣ ሁሉም ሰው ጥሩ አይደለም ፣ ይሄ ወረርሽኝ እኔና ቤተሰቤን እንዳይጎዳ" የሚሉ የተለያዩ ምክንያቶችን ሲያቀርብ በውስጣችን የብቸኝነት ስሜት እንዲያድግ ያሆናል ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የደረሱብንን የስነልቦና ፣ የስሜት ፣ የአካል ... ጥቃቶች ፣ ትችቶች መላልሶ ሲያሰላስል እንዲሁም በሌሎች የመገለል ነገር ሲኖር ወደዚህ ብቸኝነት ስሜት ልንመጣ ይችላል ፡፡

ከዚህ በታች የብቸኝነት ስሜትን ተረድተን እንዴት በጤነኛ መንገድ ማሸነፍ እንደምንችል 3 ሀሳቦችን እናያለን

1.ብቸኝነት ስሜት እንጂ እውነታ እንዳልሆነ መረዳት

ብቸኝነት ስሜት ሲሰማን በሕይወታችን አንድ የተፈጠረ ነገር ይሄን ስሜት እንዳስነሳው መረዳት አለብን ፡፡ የብቸኝነት ስሜት የሚመጣው 'በመገለል ወይም ለብቻ በመሆን ' ብቻ አይደለም ስለዚህ ብቸኝነት ሲሰማን ቁጭ ብለን ጊዜ በመውሰድ ይህን ስሜት ያመጣብንን ምክኒያት ለማወቅ መሞከርና መንስኤውን ለማስወገድ ካልተቻለም ለመቀነስ እቅድ ማውጣት ተገቢ ነው ፡፡


2.በየቀኑ ትርጉም ያለው ስራ በመስራት ማሳለፍ

በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ባለንበት ቦታ ( በቤትም ሆንን በውጭ ) እያንዳንዱን ቀን ትርጉም ያለው ስራ ሰርተንበት እንለፍ ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀኑን ሙሉ ፊልም መመልከት ፣ ማሕበራዊ ሚዲያ ከአንዱ ወደአንዱ እየተሸጋገሩ ማየት ወደባሰ ድብርት ፣ ጭንቀትና ብቸኝነት ስሜት ስለሚመራ በየቀኑ አንድ አዲስ ነገር ለመስራት መሞከር ከብቸኝነት ስሜት ለመውጣት ይረዳል ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ማታ ስንተኛ ዛሬ ከነጋ ምን ሰራሁ ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ነገ ደግሞ ምን መስራት እንዳለብን ማቀድ መልካም ነው ፡፡


3. በጣም የምንወዳቸው ሰዎች ማግኘት ፣ የምንወዳቸውን ነገሮች መስራት

ይሄን ማድረግ በውስጣችን መልካም ሀሳብና ኢነርጂ እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡ ይሄም የተሻለ የስራ ተነሳሽነት ይፈጥርልናል ፡፡ ከሚወዱት ነገር ጋር ጊዜ ማሳለፍ በውስጣችን አወንታዊ ሀሳብ እንዲፈልቅ ፣ አሉታዊዉ ደግሞ እንዲቀንስ ይረዳል ፡፡ በተጨማሪም በዙሪያችን ለብቸኝነት መንስኤ ከሆኑ ሁኔታዎችና ሰዎች መሸሽ ተገቢ ነው፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጥቂጥ መፍትሔዎች ናቸው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት ሲሰማን ሊረዱን የሚችሉ ሌላ ብዙ መንገዶችን ከመጸሐፎች ፣ ከድህረ ገፆች፣ ከሰዎች ልናገኝ እንችላለን ፡፡ከእኔጋር በሌላ ክፍል በደንብ እንመለከተዋለን ፡፡


❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
📖ማስታወቂያ📖
ለፔጁ ቤተሰቦች በሙሉ📌📌📌📌 ላለፉት 9 አመታት ስጽፈው የነበረውን #ታሪካዊ_የሳይኮሎጂ_ልብወለድ መጽሐፍ የዛሬ 2 ሳምንት (ሀምሌ 3) ይመረቃል ፡፡ ከሀምሌ 4 ጀምሮ ደግሞ በገበያ ላይ ታገኙታላችሁ ፡፡ለመጀመሪያ ጥቂት ኮፒዎች ብቻ ስለሚታተሙ ሁላችሁም የፔጃችን ቤተሰቦች ገዝታችሁ እንድታነቡ አበረታታለሁ ፡፡
በውስጡ :- ሥነልቦናዊ ምክሮችን ከታሪካዊ ሁነቶች ጋር አዋዶ ይዟል ፡፡
ርዕሱ "ሜሎሪና" ይሰኛል ፡፡

❖_____________________________❖
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
❖__________________________________❖

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
#ክፍል_24
#የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፊያ መንገዶች
www.tg-me.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ሁናችሁ ብቸኝነት ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በዚህ ወረርሽኝ ምክንያትስ እቤት በመክረማችሁ የብቸኝነት ስሜት እያጠቃችሁ ነው? እንግዲያውስ ይሄን ስሜተት የማሸነፊያ የሥነልቦና መፍትሔዎችንና ምክሮችን ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡
______________________
አዕምሮአችን የተፈጠረው የተለያዩ አይነት ስሜቶችን እንዲረዳና እንዲያስተናግድ ነው ፡፡ እነዚህ ስሜቶች አወንታዊና አሉታዊ ሲሆኑ ለኛ ማንነትና አኗኗር ወሳኝነት አላቸው ፡፡ በውስጣችን የሚፈጠሩት አወንታዊ ስሜቶች የሚገነቡንን ያህል አሉታዊ ስሜቶች ደግሞ ከውስጥ እያፈረሱን ከውጭ ደግሞ በድካም ፣ በድብርት ፣ በጭንቀት ፣ ስለ ነገ ባለ ፍርሀት ያስሩናል ፡፡

በአዕምሮአችን ከሚፈጡሩ አሉታዊ ስሜቶች አንዱ ደግሞ የብቸኝነት ስሜት ነው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት እድሜና ፆታ ፣ ሀብትና ስልጣን ሳይለይ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ፣ ከደሀ እስከ ሀብታም የሚያጠቃ አሉታዊ ስሜት ነው ፡፡

አዕምሮአችን " ማንም አይወደኝም ፣ እኔ ተሸናፊ ነኝ ፣ ሁሉም ሰው ጥሩ አይደለም ፣ ይሄ ወረርሽኝ እኔና ቤተሰቤን እንዳይጎዳ" የሚሉ የተለያዩ ምክንያቶችን ሲያቀርብ በውስጣችን የብቸኝነት ስሜት እንዲያድግ ያሆናል ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የደረሱብንን የስነልቦና ፣ የስሜት ፣ የአካል ... ጥቃቶች ፣ ትችቶች መላልሶ ሲያሰላስል እንዲሁም በሌሎች የመገለል ነገር ሲኖር ወደዚህ ብቸኝነት ስሜት ልንመጣ ይችላል ፡፡

ከዚህ በታች የብቸኝነት ስሜትን ተረድተን እንዴት በጤነኛ መንገድ ማሸነፍ እንደምንችል 3 ሀሳቦችን እናያለን

1.ብቸኝነት ስሜት እንጂ እውነታ እንዳልሆነ መረዳት

ብቸኝነት ስሜት ሲሰማን በሕይወታችን አንድ የተፈጠረ ነገር ይሄን ስሜት እንዳስነሳው መረዳት አለብን ፡፡ የብቸኝነት ስሜት የሚመጣው 'በመገለል ወይም ለብቻ በመሆን ' ብቻ አይደለም ስለዚህ ብቸኝነት ሲሰማን ቁጭ ብለን ጊዜ በመውሰድ ይህን ስሜት ያመጣብንን ምክኒያት ለማወቅ መሞከርና መንስኤውን ለማስወገድ ካልተቻለም ለመቀነስ እቅድ ማውጣት ተገቢ ነው ፡፡


2.በየቀኑ ትርጉም ያለው ስራ በመስራት ማሳለፍ

በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ባለንበት ቦታ ( በቤትም ሆንን በውጭ ) እያንዳንዱን ቀን ትርጉም ያለው ስራ ሰርተንበት እንለፍ ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀኑን ሙሉ ፊልም መመልከት ፣ ማሕበራዊ ሚዲያ ከአንዱ ወደአንዱ እየተሸጋገሩ ማየት ወደባሰ ድብርት ፣ ጭንቀትና ብቸኝነት ስሜት ስለሚመራ በየቀኑ አንድ አዲስ ነገር ለመስራት መሞከር ከብቸኝነት ስሜት ለመውጣት ይረዳል ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ማታ ስንተኛ ዛሬ ከነጋ ምን ሰራሁ ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ነገ ደግሞ ምን መስራት እንዳለብን ማቀድ መልካም ነው ፡፡


3. በጣም የምንወዳቸው ሰዎች ማግኘት ፣ የምንወዳቸውን ነገሮች መስራት

ይሄን ማድረግ በውስጣችን መልካም ሀሳብና ኢነርጂ እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡ ይሄም የተሻለ የስራ ተነሳሽነት ይፈጥርልናል ፡፡ ከሚወዱት ነገር ጋር ጊዜ ማሳለፍ በውስጣችን አወንታዊ ሀሳብ እንዲፈልቅ ፣ አሉታዊዉ ደግሞ እንዲቀንስ ይረዳል ፡፡ በተጨማሪም በዙሪያችን ለብቸኝነት መንስኤ ከሆኑ ሁኔታዎችና ሰዎች መሸሽ ተገቢ ነው፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጥቂጥ መፍትሔዎች ናቸው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት ሲሰማን ሊረዱን የሚችሉ ሌላ ብዙ መንገዶችን ከመጸሐፎች ፣ ከድህረ ገፆች፣ ከሰዎች ልናገኝ እንችላለን ፡፡ከእኔጋር በሌላ ክፍል በደንብ እንመለከተዋለን ፡፡


❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
📖ማስታወቂያ📖
ለፔጁ ቤተሰቦች በሙሉ📌📌📌📌 ላለፉት 9 አመታት ስጽፈው የነበረውን #ታሪካዊ_የሳይኮሎጂ_ልብወለድ መጽሐፍ የዛሬ 2 ሳምንት (ሀምሌ 3) ይመረቃል ፡፡ ከሀምሌ 4 ጀምሮ ደግሞ በገበያ ላይ ታገኙታላችሁ ፡፡ለመጀመሪያ ጥቂት ኮፒዎች ብቻ ስለሚታተሙ ሁላችሁም የፔጃችን ቤተሰቦች ገዝታችሁ እንድታነቡ አበረታታለሁ ፡፡
በውስጡ :- ሥነልቦናዊ ምክሮችን ከታሪካዊ ሁነቶች ጋር አዋዶ ይዟል ፡፡
ርዕሱ "ሜሎሪና" ይሰኛል ፡፡

❖_____________________________❖
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
❖__________________________________❖

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «#ክፍል_24 #የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፊያ መንገዶች www.tg-me.com/psychoet (በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ሁናችሁ ብቸኝነት ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በዚህ ወረርሽኝ ምክንያትስ እቤት በመክረማችሁ የብቸኝነት ስሜት እያጠቃችሁ ነው? እንግዲያውስ ይሄን ስሜተት የማሸነፊያ የሥነልቦና መፍትሔዎችንና ምክሮችን ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡ ______________________ አዕምሮአችን የተፈጠረው…»
የምስራች ለአንባቢያንና ለወዳጆቼ

ሜሎሪና - መጸሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት አንባቢዎች እጅ ይደርሳል ፡፡
መጽሐፉ #ታሪካዊ_የሳይኮሎጂ_ልብወለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበብ ሚና የሚተርክና የአስተሳሰብ ልዕልናን የሚያሳይ የሁላችን ኑሮ ነፀብራቅ የሆነ ልብወለድ መጽሐፍ ነው ፡፡ አቀራረቡም በሀገራችን ያልተለመደና ሰው ከማዝናናት በተጨማሪ #የሥነልቦና_ምክሮችንና ሀሳቦችን #ከታሪካዊ_ክስተቶች ጋር ደምሮ የያዘ መጸሐፍ ነው፡፡

#የገልፅ_ብዛት ፦ 210

#የታሪኩ_መቼት ፦ 1960 - 1994 (ከአፍሪካ አባት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ )

የታሪኩ ቦታዎች በኢትዮጵያ :- መተማ ፣ ላሊበላ ፣ ጎንደር ፣ አዲስ አበባ ፣ ትግራይ (ደብረዳሞ ገዳም ፣ አል ነጃሽ መስጂድ ) ፣ አሜሪካ ( ዋሽንግተን ፣ ኒውዮርክ ፣ ኮሎራዶ) ፣ እንዲሁም እግረመንገድ እስራኤል ።

ምርቃት ሀምሌ 3 : ከምሽቱ 3 ሰዓት በማሕበራዊ ሚዲያ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet
Facebook : በኔ አካውንት እንዲሁም በፔጄ ሥነ ልቡና - Psychology
youtube.com/thenahusenai

ሀምሌ 4 - 5 (ቅዳሜና እሑድ) : በደራሲው በአካል እየተፈረመ የሚሰጥበትና የፎቶ ፕሮግራም ። ለአካላዊ መራራቅ ሲባል በቦታው መገኘት የሚችሉት በአንዴ 4 ሰዎች ናቸው ይህንንም ከግምት በማስገባት ፕሮግራሙ ቅዳሜና እሑድ ሙሉ ቀን ይሆናል (ቦታው በዚህ ሳምንት ይገለፃል ) ፡፡ ያለው ጥቂት ኮፒ ብቻ ስለሆነ አስቀድማችሁ በብዛት መግዛት የምትፈልጉ ተቋማት/ግለሰቦች በFacebook Inbox ልታረጉልኝ ትችላላችሁ፡፡

ሜሎሪና .... የኢትዮጵያ ኩራት ❤️❤️❤️
ከኢትዮጵያ ተነስቶ እስከ አለም ጥግ ይዘልቃል

ይህን መልዕክት #Share በማድረግ ላልሰሙት
ሃዘንን መቋቋም የሚያስችሉ ዘዴዎች

በህወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው እና መልካም አቀጣጫን በመጠቆም ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱልን ሰዎች አሉ ይኖራሉም፡፡ የቤተሰብ አባል ፤ የልብ ጓደኛ ወይም አርአያ የሆኑን በልባችን አግዝፈን የምናያቸው ምግባራቸው ያስከበራቸው ሰዎችን ለምሳሌ ያህል መጥቀስ ይቻላል፡፡ በመወለድ ወደ ህይወት መምጣት እንዳለ ሁሉ የማይቀረው ህልፈተ ህይወት አለና በሞት ሲለዩን የሚሰማንን የቅስም መሰበር፤ የቁጭት፤ የጥፋተኝነት ፤ የጸጸት፤ የንዴት፤ የናፍቆት አልፎ ተርፎም የመንኮታኮትና የውድቀት ስሜት በግርድፉ ለማጠቃለል ያህል የሃዘን ስሜት ብለን እንጠራዋለን፡፡ የሰው ልጅ እንደ ጸባዩ ይህንን የሃዘን ስሜት የሚያመጡበት ገጠመኞችና ሁኔታዎች የተለያዩ ሲሆኑ የስሜቱም ጥልቀት እና ቆይታ ጊዜ የዚያኑ ያህል ይለያያል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሃዘን ስሜትን መቋቋም የምንችልባቸውን ጥቂት ዘዴዎችን እንመለከታለን፡፡

1. የሃዘን ስሜትን አለመካድ

የገባንበትን የሃዘን ስሜት መወጣት እንዳንችል ወደኋላ ወጥረው ከሚያሰቃዩን ስሜቶች ውስጥ አንዱ የሃዘን ስሜትን መካድ ነው፡፡ የገባንበትን መጥፎ ስሜት መካድ ከስሜቶቹ ጋር ያለንን ቆይታ ያረዝመው ይሆናል እንጂ እንድንላቀቃቸው አያግደንም፡፡ ስለዚህም ምንም እንኳን ከማንም እና ከምንም በላይ እናፈቅራቸው ነበረ ቢሆንም ላናገኛቸውና ላይመለሱ እንደተለዩን አምነን ባንወደውም የሚደርስብን ሃዘን መቀበል ከስሜቱ መላቀቅ እንድንችል ይረዳናል፡፡

2. ጠንካራ ነኝ እቋቋመዋለው ብሎ እራስን አለማታለል

አብዛኛውን ጊዜ አሉታዊ የሆኑ ስሜቶችን በመቋቋም ለማለፍ “ዋጥ” አድርገን ለማለፍ ስንጣጣር የባሰ እራሳችን ላይ ከሚደርስብን የመንፈስ ስብራት አልፎ የእንቅልፍ ማጣት፤ የምግብ ፍላጎት መዛባት፤ የድብታ ችግር፤ እንዲሁም ሌሎችንም ሊያመጣብን ይችላል፡፡ ስለዚህም ተመራጭ የሚሆነው የሚሰማንን ስሜት ለመቋቋምና ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ ስሜቱን እንደ አመጣጡ መቀበል ስላጣነው የህይወት አጋር ስንል እራሳችንን ካለንበት የስሜት ዝቅታ ማንሳት እንድንችል ለእራሳችን ዕድል ልንሰጠው ይገባል፡፡

3. የሃዘን ስሜትን ገልጾ ማውጣት ስለስሜቱ ከሌሎች ጋር መነጋገር

ብዙዎች የወዳጃቸውን የማጣት ስሜት አውጥተው ከመናገር ይልቅ በውስጥ አምቆ መብሰልሰልን እንደ አማራጭ አድርገው ይይዛሉ፡፡ ይህ ግን ስሜቱን ያለረዳት ብቻችንን በጫንቃችን ተሸክመን ለመጓዝ እንደ መሞከር ነውና የመድከምና የመሰላቸት ስሜት ይፈጥርብናል፡፡ የሆዴን በሆዴ ለሃዘን ስሜት አይሰራምና ለትዳር አጋራችን፤ ለቤተሰባችን፤ ለልብ ጓደኞቻችን ወይም ደግሞ ለስነ-ልቦና ባለሞያዎች የተሰማንን ስሜት በመናገር፤ በመጻፍ፤ ስዕል በመሳል ወይም በማንኛውም ችሎታችን በሚፈቅደው መንገድ መተንፈስ የሃዘንን ስሜት ይቀንሳልና ስሜታችንን ገልጾ ማጋራት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

4. ታጋሽ መሆን

የሃዘን ስሜቱ ከባድነት የተነሳ ብዙውን ጊዜ በሞት የተለየንን ግለሰብ የሚያስታውሱንን ነገሮች ለማራቅ እንሞክራለን፡፡ ስሜቱን ያራቅነው እየመሰለን ይጠቀሙበት የነበሩ ንብረቶችን ማራቅ፤ መኖርያ ቤታችንን መቀየር፤ የስራ ቦታችንን መቀየር፤ እንደው በአጠቃላይ እንደ ፎቶ ያሉ ትዝታ የሚቀሰቅሱ ንብረቶችን ለማስወገድ አለመቸኮል ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ የሃዘን ስሜቱም ካለፈ በኋላ የእነዚህ ንብረቶች መኖር ያጣናቸውን ግለሰቦች በመልካምነት እንድናስባቸውና እንዳንረሳቸው፤ ለእኛ የነበራቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንድናስታውስ ይረዱናል፡፡

5. የጤናችንን ጉዳይ ቸል አለማለት

ሰዎች በሃዘን ጊዜ እራሳቸውን ይጥላሉ፡፡ ለእራሳቸው ያላቸው ክብር፤ እንክብካቤ ከመቀነስም ባለፈ እራሳቸውን በረሃብ ይቀጣሉ፡፡ የምናደርጋቸው ማናቸውም ድርጊቶች ያጣነውን ግለሰብ አይመልሱምና የጤናችንን ጉዳይ ቸል ልንለው አይገባም፡፡ የምናስበውን ያህል የምግብ ፍላጎት ባይኖረን እንኳን ምግብ መመገብ ይገባናል፡፡ ያጣናቸው ሰዎች በህይወት ቢቆዩ እንዲህ እንድንጎሳቆል እንደማይፈልጉ ለእራሳችን ደጋግመን ልንነግረው ይገባል፡፡

6. የሃዘን ስሜትም ያልፋል

በሃዘን ስሜት ውስጥ ስንሆን አብዛኛዎቻችን ስሜቱ የማይላቀቅና ሽሮ የማያልፍ አድርገን እንስለዋለን፤ ይመስለናልም፡፡ የፈጀውን ያህል ቢፈጅ የሃዘን ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን እየቀነሰ የሚመጣ ነው፡፡ መዘንጋት የሌለብን መኖር ማለት አሉታዊ ስሜቶችን ሳይሰሙን ተንደላቀን የምንፈላሰስበት ሳይሆን ተጋፍጠንና ተቋቁመን የምናልፍበት ነው፡፡ በህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ማናቸውም ነገሮች የሚያልፉ መሆናቸውንና ህይወት የሚቀጥል መሆኑን ልናስተው ይገባል፡፡

በአጠቃላይ ጊዜ የማይሽረው ነገር የለምና ለማንነታችን ሃቀኛ በመሆን ካጋጠመን የተጠበቀ ይሁን ድንገተኛም የሃዘን ስሜት በመቋቋም ማንነታችንን ልንመልስ ይገባል፡፡

©(በዘመነ ቴዎድሮስ zepsychologist)
@Psychoet
ሰኞ ሐምሌ 13 ፥
ከ Fana 98.1 ጋር የነበረኝን ሙሉ ቃለ ምልልስ በቅርቡ እለጥፉለሁ፡፡

@psychoet
የአእምሮ ጤንነትን የሚጠብቁና የሚያሳድጉ 5 ተግባራት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ)

የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡ ሰው እንደ ሰው ፣ ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ባለንበት የኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በዚህ ጊዜም ከወረርሽኙ የተነሳ በአለማችን ሆነ በአገራችን ብዙ ሰዎች ለአዕምሮ (ሥነልቦናዊ) ቀውስ እየተጋለጡ ይገኛሉ በዚህም ብዙዎች ቀናቸውን በድብርት ፣ በፍርሀት ፣ ተስፊ በመቁረጥ ፣ ስለ ነገ አሉታዊ ነገሮችን በማሰብ ያሳልፉሉ ብሎም ብዙ ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል ፣ ከስራተቸው ለቀዋል ፣ ማህበራዊ ህይወታቸውን አቁመዋል ... ብዙ ብዙ ፡፡ ይህ ሁሉ ወረርሽኙ ያስከተለው የሥነልቦና ቀውስ ነው፡፡

ይህ ወረርሽኝ ከሚያመጣው የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

1. አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

አካላዊ ጤንነትና ንቃት ማለት ሁለንተናችን የተመጣጠነ እድገት ሲኖረውና ሰውነታችንን ከተለያዩ በሽታዎች ሲጠበቅ ማለት ነው፡፡ አካላዊ ጤንነት ሁልጊዜ ከአዕምሮ ጤንነት ጋር ይያያዛል ፡፡ በዚህ ንቃት ውስጥ የሚዳብር በራስ መተማመን ፣ ማቀድና መፈፀም እንዲሁም ችግሮችን በስልት መፍታት በሰውነታችን ውስጥ የኬሚካሎች ለውጥ እንዲኖር ያደርጋል ይህም ለኬሚካል ለውጥ በባህሪያችንና በስሜታችን ላይ አወንታዊ ለውጥን ያመጣል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

ባለንበት ቦታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የተለያዩ የሚያስደስቱንን ስራዎች በቤታችን ሁነን መስራት ፣ ጥሩ መጸሐፍትን ማንበብ ፊልሞችን መመልከት ፣በትንሹ እቅድ ማቀድና መተግበርን መለማመድ፡፡

2. አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዳዲስ ክህሎቶችን መማር ለአዕምሮ ጤንነትና እድገት ወሳኝ እንደሆነ ነው ፡፡ አዳዲስ ክህሎቶችን መማር በራስ መተማመናችንን ያሳድጋል ፣ የሕይወትን አላማ የቀለጠ እንድንረዳ ያግዛል በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች ጋር የትውውቅና የስራ እድል ይፈጥራል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች
አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ዩኒቨርስቲ / ኮሌጅ መግባት ፣ ብዙ ገንዘብ ማፍሰስ አይጠይቅም ባሉበት ሆኖ በቅርብ በሚቀኙ ቁሳቁሶች በመጠቀም መማር ይቻላል ፡፡

በዚህ ጊዜ እቤቱ ያለ ሰው የተለያዩ ምግብ አሰራሮችን በየቀኑ መማር ፣ ዩቲዩብ ላይ የተለያዩ ቲቶሪያሎች በማውረድ በነፃ ክህሎቶችን መግኘት ፤ በነፃ ትምህርት የሚሰጡ Online ትምህርቶችን መከታተል በተጨማሪም አዳዲስ ልማዶችን መሞከር ለምሳሌ መጻፍ ፣ መሳል ፣ጥልፍ መስራት አዳዲስ የእስፖርት አይነቶችን መለማመድና እቤት ውስጥ የተበላሸ ነገሮችን መጠገንና ማስተካከል ይቻላል፡፡

በመስሪያ ቤት ያለ ሰው አዳዲስ ሀላፊነቶች
ስራችን ላይ ጨምሮ ቢወጣ ( እዚህ ላይ ግን አብዛኞቻችን ስለምንሰንፍ አሁን ያለኝን ሃላፊነት ራሱ በስነስርአቱ አልተወጣንም ብለን እናስባለን ) ግን አዲስ ሀላፊነት መቀበል የበለጣ የሚከብድ ነገር አይደለም እንዲያውም ቋሚ ሃላፊነቱን የበለጠ እንድንወጣ ይረዳናል፡፡

3. ለሌሎች ማካፈል

ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ደስተኛ ነው ፡፡ ሁሉም ሰው ወይ ለሀይማኖቱ አልያም ለሕሊናው ሲል መለገስ / ማካፈል ይወዳል ፡፡ ይህም የሆነው ሰዎች ከሰጠን / ለሌሎች ካካፈልን በኀላ በውስጣቸን የሚፈጠረው የኬሚካል ለውጥ ምክንያት በጣም ደስተኛ ስለምንሆን ነው ፡፡ መስጠት አወንታዊ አመለካከትን ይፈጥርልናል ፣ ከፈጣሪ ጥሩ መልስ እንድንጠብቅ ያደርጋል ፣ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ያሳድግልናል አላማችንን የበለጠ ለመፈፀም ያተጋናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ሰዎች ላደረጉልን ነገሮች ምስጋናን መለገስ
*በቅርብ ያሉ ሰዎችን ስለውሎአቸው መጠየቅ
*ጊዜያችንን ለሚፈልጉ ሰዎች መገኘት
*ካለን ገንዘብ ፣ ችሎታ ለሌሎች ለተቸገሩ ወገኖች መስጠት
*በመጨረሻም ዋናው መስጠት የምንችለው በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ መሰማራት


4. ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

ጥሩ ወዳጅነት / ዝምድና አይምሮን ከሚያድሱ ነገሮች ቀዳሚው ነው ፡፡ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር ለራሳችን ያለንን አመለካከት ከማሳደጉ በተጨማሪ አስደሳች ጊዜያቶችን እንድናሳልፍ ዕድል ይሰጠናል ፡፡ ከሰዎችም የድጋ ስሜት እንድንቀበልና እንድንሰጥ ይረዳናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ከቤተሰቦቻችን ጋር ጊዜ ሰተን የጫዎታ ፣ የመወያያ የመመገቢያ ጊዜ ማሳለፍ ፡፡
*ድጋፍ የሚፈልጉ ጓረቤት ዘመዶችን ጊዜ ሰተን መጠየቅ ፣ ሰዎችን በሆስፒታልና በእስር ቤት መጎብኘት፡፡
*ካገኘናቸው ጊዜያት ያስቆጠሩ ወዳጆቻችንን ጋር መደወል።
*በዝንባሌያችን መሰረት በአካባቢያችንም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተለያዩ ሕብረቶች ውስጥ መሳተፍ፡፡

5. ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

ከምንም በላይ አሁን ላሉበት ነገር ትኩረት መስጠት የአዕምሮ ጤንነታችን እንዲጠበቅ ያደርጋል ፡፡ ብዙ ሰው አሁን ባገኘው ነገር እንደመደሰትና ፈጣሪን እንደማመስገን ትናንት ስለደረሰበት በደል እያሰበ ያዝናል ፣ ትናንት ስለሰራው ስህተት እየተፀፀተ ይኖራል ። ከዚህም ሲቀጥል ስላልኖረበት ነገ መኖሩን ሳያውቅ ከልክ በላይ "ምን እሆን ?"ብሎ እየተጨነቀ ዛሬውን ያበላሻል ፡፡

ሁልጊዜ አሁን ላይ ትኩረት መስጠት ሕይወትን የበለጠ እንድንረዳና እንድንወድ ያረገናል፡፡

#ማድረግ ያለብን ነገሮች

ትናንት በሕይወታችን የሆኑ መጥፎ ነገሮች መርሳት ባንችልም እነዛ ነገሮች ግን ዛሬ ላይ መተው ሕይወታችንን እንዲረብሹ አለመፍቀድ፡፡

በዚህ ርዕስ (5ኛው ላይ) መጸሐፌ ውስጥ (በሜሎሪና ) ወሳኝ የሆነ ስለጊዜና አስተሳሰብ ያለንን አመለካከት የሚቀይር አጭር ሀሳብ አካትቻለሁና በዛ ላይ ልታገኙት ትችላላችሁ ፡፡

ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ጽሑፉ ለናንተ ከጠቀማችሁ ሎችም እንዲጠቀሙበት #Share በማድረግ አካፍሉ! ማካፈል ከዚህ ይጀምራል፡፡
www.tg-me.com/psychoet
ከመሞታችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 20 ነገሮች
Join Telegram www.tg-me.com/psychoet

1.ትላንትናን እና ነገን እያሰባችሁ አትጨነቁ፡፡ ትናንት አልፏል ነገ አልመጣም ስለዚህ ዛሬን ቀን በሙላት ፣ በደስታ ፣በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፡፡

2.የበደሏችሁን ሰዎች ይቅርታ አድርጉላቸው ፡፡

3.ሁሉንም ሰው በእኩል ዓይን እዩ፡፡

4.ወደዚህ ምድር ያመጧችሁን እናትና አባታችሁን ውደዱ ፣ አክብሩ ፣ ታዘዙ ። *

5.የምትጠሉትን ስራ አትስሩ፡፡

6.የሕይወት ግባችሁን በመለየት በቅጡ ኑሩ፡፡

7.መስታወት ውስጥ ራሳችሁን ተመልክታችሁ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ራሳችሁን ውደዱ፡፡

8.እዚህ ምድር የመጣችሁት በፈጣሪ አላማና እጅግ በጣም ጠቃሚ ሰዎች እንደሆናችሁ አስቡ ፡፡

10.ዘወትር መሄድ እፈልጋለሁ ወደምትሉት ስፍራ ሂዱ፡፡

11.በየቀኑ ለሌሎች ቢያንስ አንድ መልካም ነገር አድርጉ፡፡*

12.ለውጥን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ፡፡

13.ሁሉንም ዓይነት የሕይወት ትምህርት በፀጋ ተቀበሉ፡፡

14.የሕይወት ፈተና ውስጥ ያለውን መልካም አጋጣሚ አስተውሉ እንጂ ተስፋ አትቁረጡ፡፡

15.በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አዎንታዊ እና በጎ አሳቢ ሆናችሁ ዝለቁ፡፡

16.በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ሁሉ ለመውደድ ጣሩ ፡፡*

17.ከቁሳ ቁስ ጋር ያላችሁን ትስስር አላሉ፡፡

18.ልባችሁን ተከተሉ፡፡

19.ሁልጊዜም ትልቅ በመሆን ሌሎችን አነቃቁ፡፡

20.ከሰዎች ሁሉ ጋር ተጫወቱ በሰላም በመግባባት ኑሩ ፤ የተቸገሩትን ደግፉ ፡፡ ደግሞም ይህን ጽሑፍ #Share አርጉ ፡፡*😍😍😍

ዘጠነኛውን አንብባችሁታል ግን? .......
የዘለልኩት እስቲ እኔ ያልጠቀስኩት መደረግ ያለበት ነገር #Comment እንድታረጉልኝ ነው?
#Comment

ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ !
እወዳችኀለሁ 😍
(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ)
አስቸኳይ!!
(ሼር ይደረግ)

~በተለይ ህፃናትና አረጋውያን በአስቸኳይ ይጠብቁናል
~እስከ አሁን ባለው መረጃ 10,415 ዜጎች እርዳታ ይሻሉ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከየቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ባገኘው አሁናዊ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ባደረሰን ሪፖርት መሰረት በተከታዮቹ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖቻችን የሁላችንንም አስቸኳይ እርዳታ ይሻሉ።

ምዕራብ ሐረርጌ 725
ምስራቅ ሐረርጌ 800
ሐረሪ 575
ወሊሶ 1250
ሻሸመኔ 3675
ባሌ /አጋርፋ 2360
ምዕራብ አርሲ 805
ጅማ 225

እስከ አሁን በተገኘው መረጃ መሰረት በድምሩ 10,415 የተፈናቀሉ ዜጎቻችን የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

በዚህም መሰረት

*የማይበልሹ የምግብ ልገሳ አይነቶች
√ ፉርኖ ዱቄት
√ ሩዝ
√ ፓስታ
√ መኮረኒ
√ ዘይት
√ የበቆሎ እህል
√ ምስር
√ የህፃናት የታሸጉ ብትን ወተቶች
√ የሕፃናት አልሚ ምግቦች

*የንጽህና መጠበቂያ አይነቶች
√ ሳሙና ፈሳሽና ደረቅ
√ ኦሞ
√በረኪና
√ ሳኒታይዘር
√ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል
√ የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ (ሞዴስ)
√ የህፃናት ዳይፐር

*አልባሳት
√ ብርድ ልብስ
√ አንሶላ
√ ንጽሕናቸውን የጠበቁ የአዋቂዎችና ህፃናት አልባሳት

ከላይ ከተጠቀሱት መሐል የአቅምዎን ያህል ሐገር ፍቅር ቴአትር ከሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ይዛችሁልን ኑ። በረከቱ በቤታችሁ ሞልቶ ይፍሰስ።

#ቅድሚያ_ለሰብአዊነት
#የሰብአዊ_ድጋፍ_ጥምረት
#CareAndShare
#የኢትዮጵያ_ቀይ_መስቀል_ማህበር
#የሐገር_ፍቅር_ቴአትር

@EliasGebru
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ሜሎሪና
አዲስ #ታሪካዊ #የሳይኮሎጂ ልብወለድ በገበያ ላይ

በሀገራችን ሆነ በዓለማችን በይዘቱ የመጀመሪያ የሆነውን #የታሪክ #የሳይኮሎጂ #የሳይንስ ልብወለድ መጽሐፍ ሐምሌ 25 እና 26 ( ያሁኑ ቅዳሜና እሑድ ) ደራሲው በተገኘበት እየተፈረመ ይሸጣል ፡፡ በመሆኑም በተመቻችሁ ሰዓት እየመጣችሁ ከደራሲው እያስፈረማችሁ እንድትገዙ እንጋብዛለን ፡፡

መጽሐፉ በውስጡ ትላልቅ የስነልቡና ሃሳቦችን የያዘ ሲሆን ፥ ስለ ሕይወት ትርጉምና ዓላማ ፣ስለ አስተሳሰብ አድማስ፣ ስለ ችግር አፈታትና ጊዜ አጠቃቀም ያወራል

በተጨማሪም ቀደምት የዓለማችን ታሪክን ከሀገራችን ጥበባት ጋር አብሮ የሚያስቃኘንና ታሪክን በመልካም አስተሳስሮ የሚያቀርብ ነው፡፡
__________________________________

ያነበቡት ቀጣዩን ክፍል በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ ፡፡ "ሜሎሪና" ልብወለድ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን ራሳችንን የምንፈልግበት የምናይበትና የምናገኝበት ነው ፡፡ በይዘቱም ለጀማሪና ለመደበኛ አንባቢ ምቹ እንዲሆን ተደርጎ ስለተጻፈ ተወዳጅ አድርጎታል ፡፡ ሜሎሪና አለማችን የበፊት መነሻ እንዲሁም የቀጣይ እጣ ፈንታን የሚያስዳስስና የሚተነብይና ብቸኛው ተከታታይ ልብወለድ ሲሆን ለመጻፍ 9 ዓመት ከ 4 ወርና 17 ቀን ወስዷል ፡፡
__________________________________

ቦታ ፦ 5 ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም አጠገብ ሉሲ ሪስቶራንት

ቀን ፦ ሐምሌ 25 እና 26 ከ ጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት (ባመቻችሁ ሰዓት መታችሁ መግዛት ትችላላችሁ)
ዋጋ ፦ 150.00 ብር ብቻ

ደራሲው ወጣት ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ የማኔጅመንት ፣ የሲቪል ምህንድስና ፣ የሊደርሺፕ ባለሙያ ሲሆን የስነልቡና ፣ የስነመለኮትና የፕሮጀክት አስተዳደር ተማሪ ነው ፡፡ በስነልቡና የሕይወት ክህሎት ስልጠና ( የአስተሳሰብ አድማስ ፣ ሕይወት ዓላማ ፣ ስልታዊ ችግር አፈታት ... ) በማሰልጠንና በማማከር እንዲሁም በማሕበራዊ ሚዲያ (በተለይም በሳይኮሎጂ ፔጅ) በሚጽፋቸው የስነልቦና ጽሑፎቹ ይታወቃል ፡፡

የመጽሐፉ ሙሉ ዳሰሳ በቅርቡ በሃገራችን ዋና ዋና የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ሚዲያዎች የሚቀርብ ይሆናል ፡፡ በዚህም ሳምንት በኢቢኤስ ቅዳሜን ከሰዓት ፕሮግራም ላይ ስለ መጽሐፉ ሙሉ ዳሰሳ ይሰጣል ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
youtube.com/thenahusenaipsychology
ከዘጠኝ ዓመታት በላይ የለፋባትን ልጁን "ሜሎሪና" ብሎ ሥም አወጣላት። አባቷ...ደራሲ፣ ማናጀር፣ ሳይኮሎጂስት... ናሁሰናይ ጸዳሉ አበራ፤
እነሆ እናንተም ይህቺን የጥበብ አብራኩን በመሸመት እንኳን ለዚህ አበቃህ በሉት።

የኔ ትውልድ ገና ብዙ አንጸባራቂዎች የሞሉት ነው ስል በምክንያት ነው።

ይዘቷ በብዙ መልኩ ከኔው ኤቶዮጵ ጋር ይመሳሰላል። ጥንታዊነትን ከዘመኑ ጋር ያዋጀች ድርሳን ናት።

መጽሐፏ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ብሔራዊ ሙዚየም ጎን ከሚገኘው ሉሲ ሬስቱራንት በድጋሚ ትመረቃለች። ርቀታችሁን ጠብቃችሁ የደራሲውን ፊርማ ትረከባላችሁ።

መልካም ንባብ፤

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ)

https://www.tg-me.com/EliasGebru/
የስኬታማ ሕይወት ምክሮችና እውነታዎች
www.tg-me.com/psychoet

📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡

📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖
ከሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰዱ ምክሮች
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖

መልዕክቱን ለሌሎችም ወዳጆቻችን #Share እናድርግ

ሜሎሪና መጽሐፍን በመጪው ቅዳሜና እሑድ 5ኪሎ ሉሲ ሬስቶራንት ከደራሲው በቀጥታ ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡

መልካም ቀን
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
@psychoet
2024/09/30 07:27:39
Back to Top
HTML Embed Code: