Telegram Web Link
መሸበርና መፍራት የነገን ችግር አያስወግድልንም ይልቁኑስ የዛሬን ደስታ ያሳጣናል

ሕይወት፣ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሠራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች ፡፡ የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የሚኖር፣ ሲያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው፡፡ ሰዉ የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቈየት፣ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር…፡፡


ሜሎሪና ገፅ 9
@Psychoet
ዒድ ሙባረክ!

ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች የፔጄ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለ1441ኛው ለታላቁ የዒድ አል-አድሐ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ ከልብ እመኛለሁ!

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «በ Fana - FM 98.1 በጥበባት ፕሮግራም ላይ "ሜሎሪና" መጽሐፍን በተመለከተ ያደረኩት ውይይት እንድታደምጡት እጋብዛለሁ #ሜሎሪና ምን ማለት ነው? #በውስጡ ምን አይነት ጭብጦችን ይዟል? #ሜሎሪና እንዴት ሊጻፍ ቻለ? # ለመጻፍ ምን ያህል ጊዜ ወሰደ? #ወደፊት ምን እንጠብቅ? ሙሉ ቃለ ምልልሱን ለማድመጥ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ https://youtu.be/I07rjVHMKM0 https://yo…»
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
እንደምን አመሻችሁ!

ቅዳሜና እሑድ በሉሲ ሬስቶራንት(5ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም አጠገብ) ንክኪ ሳይኖር ይህን ግሩም መጽሐፍ ከደራሲው እያስፈረማችሁ የግላችሁ አድርጉ ፡፡ ሁሉ ተዘጋጅቶ የምትጠበቁት እናንተ ናችሁ ፡፡ መጨረሻ ሰዓት ላይ የሚኖርን ጭንቅንቅ ለመቀነስ በጊዜ እንድትመጡ እንጠይቃለን?

ሜሎሪና ፦ ከታሪኩ ውበት በተጨማሪ በውስጡ ባሉ በስነልቦና ምክሮችና ሀሳቦች ራሳችንን እንደመስታወት የሚያሳየን ልብወለድ መጽሐፍ ነው፡፡

@Psychoet
<<ለዘመናት፣ ሕይወት ትርጕም ያገኘው ሞት በመኖሩ ነው ተብሏል፡፡ እኛ ግን ሞትን አጥፍተን ለሕይወት ዐዲስ ትርጕም እንሰጣለን፡፡ ለሥነ-ሕይወት ትልቁ ጠላት የኾነውን ሞትን እናጠፋዋለን!>> አለ፡፡

ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር - ሰው፡፡

ሜሎሪና መጽሐፍን ዛሬና ነገ (ቅዳሜና እሑድ) በሉሲ ሬስቶራንት ከደራሲው ናሁሰናይ ፀዳሉ ያገኙታል ፡፡

የሜሎሪና ልብወለድ መጽሐፍ ታሪካዊ ክፍልና አመራረቅ በዚህች 1 ደቂቃ Video ቀርቧል ፡፡

https://youtu.be/aDoGWd6TEEQ
https://youtu.be/aDoGWd6TEEQ
@psychoet
#ክፍል_25
#ጠቢብ ማን ነው
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ሰላም የሳይኮሎጂ ፔጅ ቤተሰቦች፣
ዛሬ ደግሞ በሳምንቱ ትምህርታችን ጠቢብ ማን ነዉ እንዴትስ ያስባል በሚል ከሜሎሪና መጽሐፍ የወጣ ሀሳብ እንመለከታለን፡፡
……………………………………. አንተ ጠቢብ ሰዉ
ያንተነትህ ውቅር፣ ትዝታና ተስፋ ቢኾኑም፣ ዛሬን ግን እንዴት መኖር እንዳለብህ እወቅ፡፡
ምክንያቱም፡-
፩. ትናንትን የምታርመውም ኾነ የምታድሰው ዛሬ ላይ ኾነህ ነው፡፡
፪. ነገ ውብ የምትኾነው ዛሬን ስትንከባከባት ነው፡፡
፫. ነገ ከተስፋነቷ በስተቀር ያንተ አይደለችም፡፡ ተስፋህ ደግሞ እውን ኾኖ የምታገኛት ግን ዛሬን በተጠቀምክባት ልክ ነው፡፡
ስለዚህ፣ ትዝታህ ላይ ተቀምጠህ በተስፋ ጋሪ ተሳፍረህ ዛሬን በደስታ ኑር።

በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

… የሕይወት ትምህርት የሚጨረስ እንዳልኾነ መገንብ ትልቅ ጥበብ ነው፡፡ ለዚህ ነው በሕይወታችን አንድ ተጨማሪ ቀን ባሳለፍን ቊጥር ትናንት የነበረውን ልጅነታችንን በዛሬ ብስለታችን ስናማርር ስንተች የምንከርመው፡፡ …

❖_____________________________❖

ሜሎሪና መጽሐፍን ነገ እሑድ (ሐምሌ 26) ከደራሲው በቀጥታ ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡ ቦታ 5 ኪሎ ሉሲ ሬስቶራንት ከሙዚየም አጠገብ

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
❖__________________________________❖

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
የሜሎሪና ተከታታይ ልብወለድ መጽሐፍ ዳሰሳ

በኢቢኤስ - ቅዳሜ ከሰዓት ፕሮግራም ። "ሰው እንዳያረጅም እንዳይሞትም ማረግ ይቻላል ወይ? ምድር እስር ቤት ነች ወይ? ትልቁ የጦርነት ስፍራ አእምሮ ነው ወይ? ... " ከተወያየንባቸው ሀሳቦች በጥቂቱ ናቸው ፡፡ በቲቪ ያልተከታተላችሁ በዩቲዩብ ሊንክ ይገኛል፡፡

መጽሐፉን ነገ እሑድ በ5 ኪሎ ሉሲ ሬስቶራንት ውስጥ ከእኔ ማግኘት ትችላላችሁ

https://youtu.be/pCMLIRgFKdM
የዓለም የሳቅ ንጉስ ማስተር በላቸው

ሃገራችንን በሳቅ ስላስጠራህ ፣ ሳቅ እንዲሁም ደስታ በገንዘብ እንደማይገዛ ለዓለም ስላሳየህ እናመሰግናለን ፡፡
__________________________
‹‹ዐይን አላችሁ? ተመልከቱ! ጆሮ አላችሁ? እንግዲያውስ ስሙ! ልብ አላችሁ? አስተወሉ! ገንዘብ ምድራዊ ሕይወት እንጂ ደስታን አይገዛላችሁም፡፡ ደስታን የሚገዛላችሁ እረፍት የሚሰጣችሁ ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ የሌለው ላይመጣ ያለው ላይሄድ ዕድሜያችሁን ሙሉ ከመባዘን ተጠበቁ!›› ይሉ ነበር መነኵሴው፡፡

ሜሎሪና ገፅ175
__________________________
#ሜሎሪና መጽሐፍ ዛሬ እሑድ (ሐምሌ 26) ለመጨረሻ በደሪሲው እየተፈረመ በ5ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም አጠገብ ሉሲ ሬስቶራንት ይሸጣል ፡፡

@psychoet
እቅድ
አይደለም በሀገር ደረጃ
በግለሰብ ደረጃ እንኳን
ተሳክቶ ሲታያ ደስ ያሰኛል ፡፡
ሁላችንም እንኳን ለዚህች ጊዜ አደረሰን ፡፡

@PSYCHOET
👉ጠቃሚ ምክሮች👈

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
@Psychoet
Forwarded from Jafer Books 📚 (Zee - Se)
በናሁሰናይ ፀዳሉ የተደረሰው " ሜሎሪና " መጽሐፍ እየተሸመተ ነው :: መጽሐፉ ስነልቡናዊ ይዘት ያለው የፈጠራ ስራ ነው ::
የሜሎሪና ተከታታይ ልብወለድ መጽሐፍ ዳሰሳ

በኢቢኤስ - ቅዳሜ ከሰዓት ፕሮግራም ። "ሰው እንዳያረጅም እንዳይሞትም ማረግ ይቻላል ወይ? ምድር እስር ቤት ነች ወይ? ትልቁ የጦርነት ስፍራ አእምሮ ነው ወይ? ... " ከተወያየንባቸው ሀሳቦች በጥቂቱ ናቸው ፡፡ ብዙዎች አንብበውት ቀጣዩን በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡

በቲቪ ያልተከታተላችሁ በዩቲዩብ ታገኙታላችሁ

መጽሐፉን በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መደብር እየተሸመተ ይገኛል ፡፡

https://youtu.be/pCMLIRgFKdM
ለለውጥ መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

#Share #Like
www.tg-me.com/psychoet

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©Zepsychology
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

_______ሜሎሪና ገጽ 184 _______

ሜሎሪና ❤️❤️❤️
ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ
ያነበቡት ኹሉ ወደውታል

በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መጽሐፍ መደብሮችና አዟሪዎች እጅ ይገኛል

@Psychoet
2024/09/30 05:18:28
Back to Top
HTML Embed Code: