Telegram Web Link
ከ 1992 ወደ 2015 የተቀየረው Mercedes G-Wagon

አብዛኛው የአለማችን ሀብታም እና ታዋቂ ሰዎች የሚነዱት መኪና ነው :: Mercedes G-Wagon ከ 1979 ጀምሮ መመረት የጀመረ መኪና ቢሆንም እስከአሁን ድረስ ዋና የዲዛይን ለውጥ የለውም :: በዚህም ምክንያት ይመስለኛል ይበልጥ በሰዎች ዘንድ እንዲወደድ ያደረገው :: ታዲያ እንደዚህ የሚወደደው መኪና ምን ምን ቢኖረው ነው? በዛሬው ቪዲዮ ያሉትን ነገሮች አብራርተን ሰርተናል ተከታተሉን ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/FFRXmj6-zBc

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Mercedes #MercedesGwagon
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ እያልን
በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና ይሁንልን !

መልካም ዓመት በዓል ተመኘን 🙏
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከ ቮልስ ID.6 በጣም የተሻለ የ2022 Audi Q5 etron መኪና

Audi Q5 etron ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን ለቻይና ገበያ ብቻ የሚመረት መኪና ነው :: ከ ID.6 ጋር ባትሪው የሚይዘው የሰው መጠን እና ሳይዙ ተመሳሳይ ነው :: ከዛ ውጪ ግን በጣም የተሻለ መኪና ነው :: በምን እንደሆነ ከስር በምታገኙት የዩትዩብ ሊንክ ገብታችሁ ታገኙታላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/ReB4fNQ6Wzw

ውብ ምሽት ተመኘን
#Audi #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህ በ ኤሌክትሪክም በ ፀሀይም የሚሰራ አስገራሚ መኪና

Aptera Solar EV


በአንድ ቻርጅ እስከ 1600 ኪሎሜትር መጟዝ ይችላል :: በፀሀይ ደግሞ በቀን ከ 60 ኪሎሜትር በላይ ይጨምርላችሗል :: ሳይዙ ትንሽ ሊመልስላችሁ ይችላል ግን ወደ ጎን ከ Tesla Model S ጋር ርዝመቱ ደግሞ ከ Toyota Prius ጋር እኩል ነው :: ስለዲዛይኑ ስለቴክፊቸሮቹ እንዴት እንደጀመሩ እና አሁን ምን ላይ እንዳሉ በደንብ የተብራራ ቪዲዮ ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/yaFj28NGzSw

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Aptera #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው ኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ

መልካም በአል ይሁንላችሁ
@OnlyAboutCarsEthiopia
አስገራሚው የLexus RZ ኤሌክትሪክ መኪና መሪ


Lexus RZ ላይ የ Yoke መሪ ሲሆን የምታገኙት ይሄ ቴስላም ሌሎች መኪኖችም ላይ ታገኛላችሁ :: እዚህ መኪና ላይ ለየት የሚለው ነገር መሪውን በአንድ ዙር ሙሉ ጎማውን ማዞር ትችላላችሁ :: ይሄም የሆነው ጎማው እና መሪው ምንም mechanical connection ሳይኖራቸው ወደ ጎማው electronic signal በመላክ ነው የሚሰራው :: በጣም ወድጄዋለሁ እናንተስ?
ስለዚህ መኪና አጭር ቪዲዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMY3RGpvd/

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Lexus #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
mg-comet.pdf
8 MB
ለህንድ ገበያ ላይ በርካሽ የቀረበ የኤሌክትሪክ መኪና

MG Comet EV

በአንድ ቻርጅ 230 ኪሎሜትር መጟዝ የሚችለው ይሄ የኤሌክትሪክ መኪና አራት ሰው የሚይዝ ሲሆን ሳይዙም ከ Kia Ray ጋር ተቀራራቢ ነው በቁመት :: ግን እዚህ ላይ ሁለት በር ነው የምታገኙት :: እንዲሁም ደግሞ ከጀርባም በጣም ጠባብ ቦታ ነው ያለው :: ዋጋውም 14,700 ዶላር ነው :: ተጨማሪ ነገሮችን ብሮሸሩን በማውረድ ሙሉ መረጃ ታገኛላችሁ ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#EV #MG
@OnlyAboutCarsEthiopia
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዋጋ ማስተካከያው ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም  የሚቆይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት፡ -

- ቤንዚን 👉 በሊትር 69 ብር ከ43 ሳንቲም ብር

- ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 71 ብር ከ08 ሳንቲም

- ኬሮሲን 👉 በሊትር 71 ብር ከ08 ሳንቲም

- የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 በሊትር 66 ብር ከ60 ሳንቲም 

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 57 ብር ከ84 ሳንቲም

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 56 ብር ከ50 ሳንቲም ተደርጓል።

መረጃው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍቢሲ ነው።

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Fuel #News
@OnlyAboutCarsEthiopia
2023 Toyota Corolla Cross Hulemekina Brochure.pdf
1.7 MB
Toyota Corolla Cross

ከ2020 ጀምሮ መመረት የጀመረ compact crossover suv ሲሆን በ Toyota CHR እና በ Toyota Rav4 መካከል የሚገኝ መኪና ነው :: በ Toyota TNGA PLATFORM ላይ የተሰራ መኪና ነው :: በነዳጅ እና በ hybrid የሚገኝ ሲሆን በ 1.8 litre ወይም በ 2 litre ባለ 4 cylinder ሞተር ይመጣል:: በሁለቱም በ FWD እንደ እስታንዳርድ እና በ AWD አማራጭ ማግኘት ይቻላል :: 6 trim level ሲኖረው L, LE, XLE ነዳጅ ብቻ ለሚጠቀሙት ለሀይብሪድ ሞዴሎቹ ደግሞ S, SE, XSE ትሪም ሌቭል ሲኖረው በቀላሉ የትኛው ትሪም ሌቭል እንደሆነ በቸርኬያቸው ማወቅ ይቻላል ::
ብሮሸሩ ላይ ሙሉውን መረጃ ታገኛላችሁ :: መኪናውን መግዛት ካሰባችሁ በ 0911663121 ላይ በመደወል ሙሉ መረጃ እንሰጣችሗለን ::

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#Toyota #Corolla
@OnlyAboutCarsEthiopia
ID.4 & ID.6 Simple Guide on OnlyAboutCarsEthiopia.pdf
1.8 MB
VW ID.4 እና ID.6 የገዛችሁ እና ለመግዛት የምታስቡ ሰዎች ይህ ጋይድ መኪናችሁ ላይ ምን ምን ነገሮች እንዳሉ እንዲሁም ደግሞ ምን ምን ምልክቶች እንደሆኑ የሚያብራራ አጠር ያለ PDF ነው :: ይህ መኪና ላላቸው ሰዎችም ሼር አድርጉላቸው :: እንዲሁም ደግሞ VW ID.4 እና ID.6 ከገበያው ባነሰ ዋጋ እኛ ጋር አለ የምትሉ አስመጪዎች መኪኖቹን የሚፈልጉ ደንበኞች ስላሉን በ 0911663121 ላይ ደውሉልን ::

ሞቅ ሞቅ ያለ ምሽት ተመኘን
#VW #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
The New Revised Excise Tax System on OnlyAboutCarsEthiopia.pdf
9.5 MB
አዲሱ ለመኪና የተሻሻለው የኤክሳይስ ታክስ ምን የተለየ ነገር አለው?

አዲሱ የተሻሻለው የመኪና የኤክሳይስ ታክስ ከትንንሽ የነዳጅ መኪኖች ጀምሮ እስከ ትልልቅ ነዳጅ የሚጠቀሙ መኪኖችን የታክስ ሲስተም ላይ ለውጥ አምጥቷል :: እሱ ብቻ ሳይሆን በተሻሻለው ላይ ክፍልፋዩን ያ ማለት በሞተራቸው CC የሚከፋፈሉበትን ከ 3 ወደ 4 አሳድገውታል :: ስለዚህ በአዲሱ ከ 1500 CC በታች, ከ 1500 CC እስከ 2500 CC, ከ 2500 CC እስከ 3000 CC እና ከ 3000 CC በላይ በሚል ተከፍለዋል :: ይህም ለትንንሽ መኪኖች ዋጋቸው እንዲጨምር እና ለትልልቅ መኪኖች ደግሞ የሚከፈለው ቀረጥ እንዲቀንስ ያደርገዋል :: ምንም እንኳን አሁን ላይ የነዳጅ መኪናን በፍራንኮቫሉታ (በተመላሽ) ማስገባት ነው የሚቻለው :: ፀድቆ ተግባር ላይ የዋለው ከባፈው ሳምንት ጀምሮ ሲሆን ሙሉ ዝርዝር መረጃውን ከላይ ባለው PDF ላይ ማግኘት ትችላላችሁ ::
ከበፊቱ የታክስ ሲስተም ጋር ማወዳደር ከፈለጋችሁ ከዚህ በፊት የሰራሁት የዩትዩብ ቪድዮ ከስር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/Ib9S7B59Mhw

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Ethiopia #Tax
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለሞተር ስፖርት ቤተሰቦች በሙሉ

በኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት አሶሴሽን የሚዘጋጀው የራሊ መኪና ውድድር በነገው እለት ግንቦት 13/ 2015 ላይ በገላን ይደረጋል :: ቦታውን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ዛሬ ማታ ወይም ነገ ጠዋት የምናሳውቅ ይሆናል ::

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#Rally #Race
@OnlyAboutCarsEthiopia
የዛሬው በኢዮጵያ ሞተር ስፖርት አሶሴሽን የተዘጋጀው የራሊ ውድድር መነሻ ቦታው ገላን ኮንዶሚኒየም ሲሆን ካርታው ላይ እንደምታዩት እሱን ተከትለው የሚሄዱ ይሆናል :: 2:30 ላይ የሚጀምር ሲሆን እስከ ማታ 11:30 ይቆያል :: ለተወዳዳሪዎች መልካም እድል ተመኘን

#Rally #Race
@OnlyAboutCarsEthiopia
#MarathonTrading

መኪና ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ ማስመጣት ትፈልጋላችሁ?

እንግዲያውስ Marathon Trading ለእናንተ መፍትሄ ይዞ መቷል :: የኤሌክትሪክም የነዳጅም መኪኖችን ቀጥታ ከካምፓኒ እየወሰደ ለእናንተ የሚያቀርብ ድርጅት ነው :: አሁን በብዛት የሚገቡትን የ Toyota VW Audi BMW Honda መኪኖችን በብዛት እየላኩ ይገኛሉ :: ዋጋቸውም በካምፓኒ ዋጋ ነው የሚያቀርቡት :: በብዛትም በፍሬም መግዛት ትችላላችሁ :: ታዲያ እስከ ጅቡቲም እስከ ኢትዮጵያም ያመጣሉ :: ከእናንተ የሚጠበቀው ማዘዝ ብቻ ነው :: ተጨማሪ መረጃ ከስር በምታገኙት አድራሻ ማናገር ትችላላችሁ ::

WhatsApp እና telegram:
+86 185 6539 3229
ከ Tesla Model Y የሚሻል ኤሌክትሪክ መኪና

2023 Cadillac Lyriq

Lyriq የ Cadillac የመጀመሪያው ኤሌክትሪክ መኪና ነው :: በደንብ ከሚታወቀው ከ Cadillac Escalade ረዘም ያለ ነው :: ታዲያ ከ Tesla Model Y በምን ቢሻል ነው? በውጫዊ ዲዛይን ባለው ቴክኖሎጂ በውስጥ ስፋት እና ውስጥ ላይ ከ Google ጋር በመጣመር የሰሩት አስገራሚ ከርቭ እክሪን አለው :: የዛሬው የዩትዩብ ቪዲዮ እዚህ መኪና ላይ ያተኮረ ይሆናል :: ኢትዮጵያ ስለተላከ ሲመጣ ደግሞ ተጨማሪ ነገሮችን አብረን እናያለን :: ዩትዩብ ላይ ከወር በሗላ ስለተመለስን የእናንተ እገዛ እንፈልጋለን :: ስለዚህ እየገባችሁ በማየት እና ላይክ በማድረግ እንድትደግፉን እንጠይቃለን ::
የ Cadillac Lyriq መኪና ሪቪው
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/AP1OQ8WFPrI

መልካም ምሽት ተመኘን
#Lyriq #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024 Toyota Tacoma is the Ultimate Adventure Machine.pdf
1.2 MB
የ 2024 Toyota Tacoma ምን ምን አሻሽለው ነው ያቀረቡት?

የ 2024 Toyota Tacoma መኪና በአዲስ ዲዛይን ያቀረቡት ሲሆን ይሄም 4ኛው ጀነሬሽን ሞዴል ነው :: በ 8 የትሪም አማራጮች ማለትም ከ SR እስከ TRD Pro ያሉትን በአዲሱ ሞዴል ላይ የሀይብሪድ አማራጭም ይዘው ቀርበዋል :: የሞተር አማራጩ በ 2.4 ሊትር ብቻ የሚገኝ ሲሆን ከ 228 እስከ 326 የፈረስ ጉልበት አለው :: ሌላው ደግሞ የባሌስትራ ወይም የሊፍ ስፕሪንግ ወደ ኮይል እስፕሪንግ ቀይረውታል :: ስለዚህ የበለጠ ምቾት እንዲኖረው ያደርጋል :: ግን ከዛ በላይ ደግሞ ውስጡ ያምራል ::
በዛሬው የቲክቶክ ቪዲዮ ስለሱ በጥቂቱ ላስመልክታችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZM2N6SwKU/

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Toyota #Tacoma
@OnlyAboutCarsEthiopia
Volkswagen ID.6 Crozz Pro Review

ይህ የኤሌክትሪክ SUV መኪና በ VW ID ኤሌክትሪክ series ቻይና ውስጥ ብቻ የሚመረት መኪና ነው :: ቮልስዋገን ከ FAW ጋር እና ከ SAIC ጋር አንድ ላይ የሚሰሩት መኪና ሲሆን Pro X በ SAIC ጋር Crozz ደግሞ በ FAW ካምፓኒ ጋር ነው የሚሰሩት :: ስለዚህ ረዘም ያለ አሻም ቲቪ ላይ የተለቀቀ የ Crozz Pro ሞዴል ሪቪው አለ :: ከ Pro X ሞዴሉ ጋር ማወዳደር ከፈለጋችሁ የሁለቱንም ቪዲዮ ሊንካቸውን ከስር አስቀምጫለሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

Crozz Pro
https://youtu.be/TIomyFop47U

Pro X
https://youtu.be/DYacLXpdovs

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#VW #ID6 #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ፍጥነትን ከመቆጣጠር እስከ ራሱን በራሱ የሚነዳ ተሽከርካሪ | ክሩዝ ኮንትሮል ከምን ወደ ምን?

ክሩዝ ኮንትሮል አሁን ላይ አብዛኛዎቹ መክኖች ላይ ተገጥሞ ታገኙታላችሁ ::ግን ክሩዝ ኮንትሮል እንዴት ተፈጠረ? የፈጠረውም ቲቶር በምን አጋጣሚ ሊያስበው ቻለ? እንዴት እያደገ መጣ? አሁን ላይ የሰው አልባ ተሽከርካሪ እየተሰራ ነው? እና ወደፊትስ? በዛሬው ቪዲዮ ስለነዚህ ነገሮች በዝርዝር እንመለከታለን :: ከስር የምታገኙትን የዩትዩብ ሊንክ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/xRycVFv2ykY

ቅልል ያለ ምሽት ተመኘን
#CruiseControl #Selfdrivingcars
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው Porsche Taycan

Porsche Taycan 4S

Porsche Taycan የመጀመርያው የፖርሽ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን ለገበያ የወጣው በ 2019 ላይ ነበር :: ኢትዮጵያ ውስጥ በ 2021 ላይ እንደገባ ሳይ በጣም ነበር የገረመኝ :: በዛሬው ቪዲዮ ስለዚህ ኤሌክትሪክ መኪና በዝርዝር ስላሉት ነገሮች ስለውስጣዊ እና ውጫዊገፅታው ሬንጁ እና በመጨረሻም ስለዋጋው እንመለከታለን :: ከስር የምታገኙትን የዩትዩብ ሊንክ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/8_mZQhwQtvM

ልዩ ያለ ምሽት ተመኘን
#Prosche #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
አንዴ ነው አሉ አፄ ሀይለስላሴ (ጃንሆይ) መኪና እንዲሰራላቸው ለጃፓኑ ቶዮታ መኪና አምራች ካምፓኒ ትእዛዝ ይሰጣሉ ::
የቶዮታ ካምፓኒ ዋና ስራ አስኪያጅ ለክብሮ የሚመጥን ምን አይነት መኪና ይሰራልዎ ብሎ ጥያቄ ያቀርባል :: ጃንሆይም "ለአንድ ኩሩ ዘር" የሚሆን መኪና እንደሚፈልጉ ይነግሯቸዋል :: ከዛም መኪናው ከተሰራ ጀምሮ እስከአሁን "LandCruiser“ ተብሎ ይጠራል ይባላል :: 😁

ምንጭ - በእምነት አውቶሞቲቭ

በዛውም የዩትዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳትረሱ

Https://youtube.com/yonathandesta

ፈታ የምትሉበት ቀን ተመኘን
#LandCruiser
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/25 20:22:17
Back to Top
HTML Embed Code: