Telegram Web Link
ሰላምታዬ ይድረስ ቤተሰቦች👋

መኪና ላላችሁ እና ባይኖራችሁም ለቤተሰብ ለጟደኛ ለዘመድ ማበርከት የምትችሏቸው መኪናችሁ ላይ ሊያገለግሉ የሚችሉ እቃዎችን በመግዛት ላይ እንገኛለን :: ይህንን እቃዎች ገዝተን ግን መልሰን ለእናንተው ነው የምንሰጠው :: በነፃ አዎ ሰምታችሁናል በነፃ :: ስለዚህ ከእናንተ የምፈልገው ሁለት ቀላል ነገሮችን ነው :: የመጀመሪያው ተጠቅማችሁ የጠቀሟችሁ መኪና ላይ የሚገኙ እቃዎች ካሉ ከነአድራሻቸው ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን :: ሌላው ደግሞ የዩትዩብ ቪድዮዎቹን በምታዩበት ጊዜ በ VPN እንድታዩ ይህንንም ስታደርጉ የተሻለ ገቢ እና ገቢውን ተመልሶ እቃ ገዝተን ለእናንተው ስለምንሰጥ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ :: ይህንን ያደረግንበት ምክንያት ቪድዮዎቻችን ሁሉንም ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ስለምንፈልግ ነው :: ስለዚህ የዩትዩብ ቤተሰብ ይሁኑ
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtube.com/c/yonathandesta?sub_confirmation=1

ፍክት ያለ ከሰአት ተመኘን🙏
#Youtube 
@OnlyAboutCarsEthiopia
የተሽከርካሪ ክፍሎች የጣልያንኛ እና እንግሊዝኛ ስያሜ! ክፍል 6

22. ኢግኒሽን ኮይል (Ignition Coil) - የተሽከርካሪ ኤሌክትሪክ ክፍል ሲሆን ከባትሪ የሚያገኘዉን 12 volt እስከ 30 ሺ volt ድረስ ያሳድጋል። በጣልያንኛ ቦቢና ይባላል።

23. ሾክ አብዞርበር (Shock Absorber) - የሰስፔንሽን ክፍል ሲሆን ተሽከርካሪ ምቹ ባልሆነ መንገድ በሚጓዝበት ጊዜ መርገብገብን የሚቀንስ ሲሆን በጣልያንኛ አሞርዝራተር ይባላል።

24. ሊፍ ስፕሪንግ (Leaf Spring) - ይህም በተመሳሳይ የሰስፔንሽን ክፍል ሲሆን የተሽከርካሪዉን ክብደት ይሸከማል በጣልያንኛ ባሌስትራ በመባል ይታወቃል።

25. ብሬክ (Brake) - ተሽከርካሪ ፍጥነት እንዲቀንስ ወይም ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም የሚያደርግ ሲሆን በጣልያንኛ ፍሬን በመባል ይጠራል።

Credit:- ግዮን አዉቶሞቲቭ!

የሚገርም ከሰአት ተመኘን
#GarageNames
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዬች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችው በአሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የስኬት እና የፍቅር ይሁንላችሁ!

መልካም በዐል ተመኘን 🙏
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ሰው ስሙን ባንጠቅስም አብዛኞቻችን እናውቀዋለን :: ቢልጌትስ የማይክሮሶፍት ባለቤት ነው :: በእኛ እድሜ እያለ ነበር ቢሊየነር የሆነው :: አለማችን ላይ ከሚገኙ ሀብታሞች ሰዎች አንዱ ነው ግን ምን ምን መኪኖችን ይነዳል?

ጋራዥ ውስጥ የሚገኙ 7 አሪፍ መኪኖች
1. 1979 Porsche 911 (140 ሺህ ዶላር)
2. Porsche 959 Sports (2 ሚሊዮን ዶላር)
3. Ferarri 348 (70 ሺህ ዶላር)
4. Porsche Taycan Turbo S (185 ሺህ ዶላር)
5. Chevrolet Suburban (52 ሺህ ዶላር)
6. Ford Focus (25 ሺህ ዶላር)
7. Nissan Figura (18 ሺህ ዶላር)
አሁን ላይ ግን በየቀኑ የሚነዳው መኪና Tesla Model X ነው ::

አለማችን ላይ ያሉ ቢሊየነሮች የሚነዷቸው መኪኖች ለማየት
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/UV1z86a3Tj8

ቪድዮዎቹን በVPN ብታዩ በየጊዜው ብዙ እቃዎችን እየገዛን በነፃ የምንሰጥ ይሆናል :: ስለዚህ በጣም ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ::

ሞቅ ሞቅ የሚል ቀን ተመኘን
#Microsoft #BillGates
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቁልፍ መኪናችሁ ውስጥ ቢቆለፍ እንዴት ይከፈታል?

በአንድም ሆነ በሌላ ሳናውቅ ቁልፋችንን መኪናችን ውስጥ ትተን ወርደን ሊቆለፍብን ይችላል :: በተለይ ደግሞ በተጣደፍንበት ሰአት ወይም የሆነ ሰው ቀጥረን እደዚህ በሚሆንበት ሰአት በጣም ያናድዳል :: እቤታችን ከሆነ እና ሁለተኛ ቁልፍ ካለን ቶሎ ከፍተን ልንቀሳቀስ እንችላለን :: ካልሆነ ግን ራቅ ያለ ቦታ ከሄድን እና ብቻችንን ወይም ከቤተሰብ ጋር ሆናችሁ እንደዛ ከሆነባችሁ ለመክፈት የምትችሉበትን 3 መንገዶች አሳያችሗለሁ :: ሙሉ ቪድዮ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/p9bDVSXmZlo

በጣም እናመሰግናለን VPN አብርታችሁ እያያችሁ ስላላችሁ :: ቪድዮዎቹን በVPN ብታዩ በየጊዜው ብዙ እቃዎችን እየገዛን በነፃ የምንሰጥ ይሆናል :: ስለዚህ በጣም ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ::

ሰላማዊ ምሽት ተመኘን
#carkeys
@OnlyAboutCarsEthiopia
Zayride ከ ኮድ 3 በተጨማሪ ለ ኮድ 2 መኪኖች አዲስ ነገር ይዞ መቷል ::

ከ 2000 አመተምህረት ወዲህ ያሉ መኪኖች ካላችሁ ተመዝግባችሁ የራይድ አገልግሎት መስጠት ትችላላችሁ :: ይህንንም ያደረጉት በሚጨናነቅበት ሰአት ማለትም ስራ መውጫ እና መግቢያ ሰአት ባዶአቸውን ከሚሄዱ ሰውን ጭነው ቢሄዱ የትራንስፖርት እንዲሁም የነዳጅ ፍጆታ ይቀንሳል በሚል ነው :: አሪፍ ሀሳብ ነው :: እኛ በብዛት ፈረስን ነው የምንጠቀመው :: እናንተ የትኛውን የትራንስፖርት አይነት ነው የምትጠቀሙት? የቱ አሪፍ ሆኖ አገኛችሁት?

ግሩም ቀን ተመኘን
#Ride #Transport
@OnlyAboutCarsEthiopia
የኢትዮጵያ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በትላንትናው እለት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቂያ መድረክ እና 60 ተሽከርካሪዎችን በ 40 የቻርጂንግ ማእከላት በመታገዝ ለ 1 ወር ያዘጋጀውን የነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት አስጀምሯል ::

ተቋሙ እያደገ የመጣውን የነዳጅ ተጠቃሚነት አማራጭ የሀይል ምንጭ በሚጠቀሙ እና ለአካባቢ ተስማሚ በሆኑ የኤልክትሪክ መኪኖች ለመተካት እየሰራ ይገኛል ::

ድምቅ ያለ ቀን ተመኘን
#electriccars
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከዚህ በፊት እነዚህን መኪኖች እና ተጨማሪ አንዳንድ መኪኖችን ጠይቀን ነበር :: መኪኖችን እንድንቀርፅ እየፈቀዳችሁልን ስለሆነ እያመሰገንን በቀጣይ ሪቪው ለመስራት ያሰብናቸው መኪኖች ከላይ የምትመለከቷቸው ናቸው :: እናም ከነዚህ ውስጥ አንዱ መኪና ያላችሁ ሰዎች የሚሸጥ ካልሆነ ቪድዮ ለመስራት ስለምንፈልግ ፈቃደኛ ከሆናችሁ በ @yonathandesta ላይ መልእክት በመላክ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን ::
የመኪኖቹ ዝርዝር
- Hyundai Palisade
- Honda CR-V, Ridgeline
- Peugeot 5008
- Nissan Juke
- Mercedes X250D
- Suzuki Vitara
- Toyota Raize
- Toyota Corolla Cross
- Porsche Cayenne
ከዘረዘርኳቸው ውጪ መኪኖችም ካሉሏችሁም በ @yonathandesta አናግሩን :: እናንተ እንዲሰራበት የምትፈልጉትም መኪና ካለ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን :: የግድ የ 2022 ወይም የ 2021 ብቻ መሆን የለባቸውም :: መኪኖቹ ላላቸው ሰዎች ሼር አድርጉላቸው :: እሁድ ማታ በየሳምንቱ የመኪና ሪቪው የምንለቅ ይሆናል ዩትዩብ ላይ እንገናኝ ::
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtube.com/c/yonathandesta?sub_confirmation=1

ልዩ ከሰአት ተመኘን
#CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪናችሁን ቻርጅ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የምትጠቀሙትንም እቃ ቻርጅ ማድረግ እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

ይሄ Hyundai Ioniq 6 ልክ እንደ Hyundai Ioniq 5 እና እንደ KIA EV6 መኪኖች በመኪናችሁ የምትፈልጉትን እቃ ቻርጅ ማድረግ ትችላላችሁ :: እንደምትመለከቱት ላፕቶፕ ቻርጅ ማድረግ እንዲሁም ሌሎችንም ነገሮች ቻርጅ ማድረግ ትችላላችሁ በመኪናችሁ :: ሌሎቹን ተጨማሪ ነገሮች ማለትም ስንት ኪሎሜትር እንደሚሄድ ያሉት ቴክኖሎጂ እና ለየት ብለው ያገኘናቸውን ነገሮች በዩትዩብ ቪድዮ ላይ ታገኛላችሁ ከለቀቅነው ትንሽ ቆይቷል ካላያችሁት ሊንኩን ከስር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/PKm1nyP0ivQ

እኛን መደገፍ ከፈለጋችሁ በ VPN ብታዩት አሪፍ ነው :: ከኢትዮጲያ ውጪ ያላችሁ ማበረታታት የምትፈልጉ ሱፐር ስቲከርም መስጠት ትችላላችሁ ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Hyundai #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪናችሁን ቲንት ማድረግ የምትፈልጉ እነዚህን ነገር ማወቅ አለባችሁ

መስታወታችሁ ላይ ጥቁር ቲንት ማድረግ የምትችሉት እነዚህን 3 ነገሮች ካሟላችሁ ነው ::
1. የመንግስት ባለስልጣን ከሆናችሁ
2. የቆዳ እና የአይን እክል ካጋጠማችሁ እና በህክምና ቦርድ ተፅፎ መንገድ ትራንስፖርት ከፈቀደላችሁ
3. የመኪናው መስታወት ከፋብሪካ እንደዛ ሆኖ ከመጣ መሆን ይችላል :: አሁን ላይ ከዱባይ የሚገቡት መኪኖች በብዛት የሗላ መስታወታቸው ጥቁር ነው ከላይ እንደምትመለከቱት ::
ግን ለጥፋችሁ ከተገኛችሁ 100 ብር እና ትልጣላችሁ :: ስለዚህ ኪሳራ ስለሆነ ባትለጥፉ ብለን እንመክራለን ::

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Tint #Tintwindow
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
አዲስ_መኪኖችን_ከመግዛታችሁ_በፊት_በቀላሉ_ቼክ_ማድረጊያ_ቼክሊስት.pdf
በተደጋጋሚ እየጠየቃችሁን ስላላችሁ አዳዲስ መኪኖች ስትገዙ የሚጠቅማችሁ ቼክ ሊስት ነው :: ከዚህ በፊት የለቀቅነውን ቼክ ሊስት ከስር ታገኛላችሁ :: እንዴት እንደሚደረግ ደግሞ ግራ ከገባችሁ እራሱን የቻለ ቪድዮ ስለቀቅን የቪድዮውን ሊንክም ከስር ታገኛላችሁ :: መኪና ስትገዙ ቼክ እንድናደርግ እንዲሁም የምትፈልጉትን መኪና መምረጥ ከከበዳችሁ @yonathandesta ላይ መልእክት እየላካችሁ በአካል ቢሮ በመምጣት የምናማክር ይሆናል :: ነገ ስለ Hyundai Bayon መኪና ሪቪው የምንለቅ ይሆናል :: ይጠብቁን

የቼክሊስት ሊንክ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://www.tg-me.com/OnlyAboutCarsEthiopia/438

የአዲስ መኪና ቼክሊስት ቪድዮ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/rt63O2HVi-4

ውብ ምሽት ተመኘን
#NewCars #Checklist
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሻሞላ የሚመስል ቅርፅ ያለው የጀርባ መብራት
2021 Hyundai Bayon Hybrid Review

ማርች 2021 ላይ ለእይታ የቀረበው ይሄ መኪና ብዙ ለየት ያሉ ፊቸሮች ያሉት መኪና ነው :: ከውጪ ዲዛይን ጀምሮ ውስጣዊ የተለየ የሞተር አማራጭ እና ቴክኖዎሎጂ ላይ ለየት ያሉ ነገሮችን ያጨቀ መኪና ነው ::ዋጋውም በዚህ ሬንጅ ውስጥ ካሉት ጋር በጣም ተቀራራቢ ነው :: ግን የነዳጅ ፍጆታ ከሌሎቹ የቤንዚን መኪኖች በ 15% የተሻለ ነው :: ለምን እንደሆነ አሳያችሗለሁ :: ቪድዮውን ከስር ሊንኩን ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/wJCVHW55c-Y

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#HyundaiBayon #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
እስከዛሬ ሪቪው ከሰራናቸው SubCompact እና Compact SUV መኪኖች ዋጋቸው ተመሳሳይ ቢሆን የቱን መኪና ትመርጣላችሁ?
Anonymous Poll
9%
Hyundai Bayon
30%
Peugeot 2008
30%
Toyota CHR
5%
Hyundai Kona
3%
Kia Stonic
2%
DS 3 Crossback
8%
Nissan Qashqai
10%
Hyundai Creta
2%
Cherry Tiggo 2 Pro
V6 ወይስ V8?
Ford F-150 Raptor R

Ford F-150 Raptor ወደ V8 ተመልሷል ::
Ford F-150 Raptor በ V6 ብቻ እያመረቱ የቆዮ ሲሆን አሁን ግን ከ RAM TRX ጋር ለመወዳደር ሲሉ V8 አማራጭ ይዘው ቀርበዋል :: በዚህ መሰረት 5.2 ሊትር V8 ሞተር እንደሚሆን የተናገሩ ሲሆን Raptor R የሚልንም ስያሜ ሰተውታል :: 700 hp ሲኖረው TRX 702 hp ቢኖረውም weight to power ratio የተሻለ ስለሆነ Raptor R ፈጣን ነው :: ሌላው ጎማው 37 inch ሲሆን ከ Noramal Raptor ጋር ተመሳሳይ ነው :: ከ TRX ጋር በ 25 mm የመሬት ከፍታው ይበልጣል :: TRX 355 mm ሲሆን Raptor R 380 mm ነው :: የነዳጅ ፍጆታቸው በ V6 Raptor ተሞልቶ ከ 800 ኪሎሜትር በላይ የሚጟዝ ሲሆን TRX ላይ ግን ከ 500-560 ኪሎሜትር ብቻ ነው የምትጟዙት :: የውስጥ ገፅታውም በጣም ተመሳሳይ ነው :: ዋጋው ከ 110 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚጀምር ሲሆን በሚመጡት ወራት ለገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል :: ምን ታስባላችሁ ወደ V8 መመለሳቸው ትክክል ነው ወይስ...? ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZMNHkpqGV/?k=1

የሚገርም ምሽት ተመኘን
#Raptor #TRX #Pickup
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪናችሁ ቱርቦ ቻርጀር ወይስ ሱፐር ቻርጀር ቢኖረው ይሻላል?
Anonymous Poll
59%
ቱርቦ ቻርጀር
41%
ሱፐር ቻርጀር
ይህንን ያውቃሉ?

የመጀመሪያው ቱርቦቻርጀር የተገጠመለት የካምፓኒ መኪና የ 1962 OldsMobile Turbo JetFire መኪና ነው :: አሁን ላይ ብዙ መኪኖች ላይ ቱርቦቻርጀር እናገኛለን :: ምን አልባት የምትነዱት መኪና ቱርቦ ሊኖረው ይችላል :: ግን እንዴት ተጀመረ? ጥቅሙ እና ጉዳቱ ምንድነው? ቱርቦቻርጀር ምን ያህል ሀይል መኪናችሁ ላይ ይጨምራል? የሚለውን በዛሬው የዩትዩብ ቪድዮ ለቀናል :: እንድታዩት ጋበዝናችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/M3q4nRgIF5s

በጣም እናመሰግናለን VPN አብርታችሁ እያያችሁ ስላላችሁ :: ቪድዮዎቹን በVPN እንድታዩ ያልነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁትን ተከታታዮቻችንን ብቻ ነው ::

ልዩ ምሽት ተመኘን
#TurboCharger
@OnlyAboutCarsEthiopia
Mitsubishi Attrage ቱርቦ የለውም!

Mitsubishi Attrage ቱርቦቻርጀር አለው ሲባል ሰምታችሁ ይሆናል :: ግን የሚያሳዩት Air Flow Sensorun ነው :: እሱ ከ Intake manifoldu ጋር የተገናኘ ነው :: Turbo ከ exhaust እና ከ intake ጋር ነው የሚገናኘው :: እንዴት እንደዛ ሊባል ቻለ የሚለውን አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMN9smcVb/?k=1

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Mitsubishi #TurboCharger #Attrage
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/25 00:23:29
Back to Top
HTML Embed Code: