Telegram Web Link
ስንቶቻችሁ ናችሁ መኪና ኢትዮጵያ ውስጥ ስትገዙ ተንከባክበው በስርአት ስለመኪናው ፊቸር አሳይተዋችሁ የገዛችሁት? ይህንን ጥያቄ ያነሳነው በምክንያት ነው
Anonymous Poll
21%
እኔ እንደዛ ነው ያጋጠመኝ በደንብ አሳይተውኛል
51%
ጭራሽ ስለመኪናው ምንም አያውቁም ስጠይቃቸው ይበሳጫሉ
28%
አልገዛሁም ግን ሄጄ ስጠይቅ እንደማያውቁት ይነግሩኛል ወይም መኪናው የእነሱ እንደሆነ ይነግሩኛል
ይህንን Tesla Model Y መኪና 10 ሚሊየን ብር እያሉ ሲቀባበሉት አይታችሁ ይሆናል :: ግን ምን ምን ፊቸሮች አሉት ቴስላ መሆኑ ምን የተለዩ ፊቸሮች አሉት እና ቀረጡ ስንት እንደሚሆን የሰራሁት አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ተለቋል ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMN6TMvE4/?k=1

የተለየ ምሽት ተመኘን
#Tesla #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
4 ሚሊየን የሆነው ምን ቢኖረው ነው? 2021 Peugeot 2008 GT

በዚህ የመኪና ዘርፍ ውስጥ ከሚገኙ መኪኖች የ 1 ሚሊየን ብር ልዩነት አለው እዚህ መኪና ላይ :: ግን ምን ቢኖረው ነው የተወደደው እሱን በዛሬው ቪድዮ የምናይ ይሆናል :: ዩትዩብ ላይ ተለቋል :: ሊንኩን
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/o8_iVnteXOA

እኛን መደገፍ ከፈለጋችሁ በ VPN ብታዩት አሪፍ ነው ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Peugeot #CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
አዲስ መኪና ከገዛችሁ በሗላ ማድረግ የሌለባችሁ 7 ነገሮች

1. መኪናችሁን ረገጥ አድርጋችሁ ባትነዱ ያ ማለት ከ 3,500 RPM በላይ ባትነዱ
2. ክሩዝ ኮንትሮሉን ባትጠቀሙ 1600 ኪሎሜትር እስኪደርስ
3.አጫጭር ጉዞዎችን ባትሄዱ እስከ 5 ኪሎሜትር
4. ከባባድ እቃ ባትጭኑ
5. በሀይል መኪናችሁን ማቆም
6. መኪናችሁን ዛፍ ስር ማቆም
7. የመኪናችሁን ዘይት 1600 ኪሎሜትር ሲደርስ መቀየር

አዲስ መኪና ለገዙ ጟደኞቻችሁ ላኩላቸው ::

የተብራራ ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/QeeUC24sDFE

እኛን መደገፍ ከፈለጋችሁ በ VPN ብታዩት አሪፍ ነው ::

ውብ ምሽት ተመኘን
#NewCar
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስንቶቻችሁ ናችሁ ጋራዥ ስትሄዱ የጣልያን ስም ሲጠሩ ግራ የማይገባችሁ? በ 6 ወይም በ 7 ፓርት ከፋፍለን የምናቀርብ ይሆናል
Anonymous Poll
27%
በጣም ነው ግራ የሚገባኝ
44%
አንዳንዱን እረዳለሁ
29%
አይ እኔ ይገባኛል
የተሽከርካሪ ክፍሎች የጣልያንኛ እና እንግሊዝኛ ስያሜ! ክፍል 1

ብዙ ጊዜ በጋራዥ ባለሙያዎች ዘንድ የጣልያንኛ ስያሜ መጠቀም የተለመደ ሲሆን የትምህርት ተቋማት ደግሞ እንግሊዘኛዉን ስያሜ ይጠቀማሉ። ሁለቱንም መጠቀም እንድንችል ይህን ማብራሪያ ያዘጋጀን ሲሆን መጀመሪያ ላይ የተቀመጠዉ የእንግሊዝኛ ስያሜ ነዉ።

1. ክራንክ ሻፍት(crankshaft).... የሞተር ክፍል ሲሆን በዋናነት የፒስተንን ከፍና ዝቅ እንቅስቃሴ ወደ ክብ ዙር እንቅስቃሴ ወይም እሽክርክሪት የሚቀይር ክፍል ነዉ። በጣልያንኛ ኮሎ በመባል ይታወቃል።

2. ካም ሻፍት(camshaft)... ሲሊንደር ሄድ ላይ የሚገኝ ዘንግ ሲሆን ኢንቴክ እና ኤግዞስት ቫልቮች እንዲከፈቱ እና እንዲዘጉ ያደርጋል። በጣልያንኛ አልብሮ ካም ተብሎ ይጠራል።

3. ኮኔክቲንግ ሮድ(connecting rod)... ፒስተን እና ክራንክ ሻፍትን የሚያገናኝ ሲሆን በጣልያንኛ ቤላ በመባል ይታወቃል።

4. ሲሊንደር ሄድ(cylinder head)... የላይኛ የሞተር ክፍል ሲሆን ካምሻፍት,ቫልቭ,ቫልቭ ስፕሪንግን የመሳሰሉ የሞተር ክፍሎችን አካቶ ይይዛል። በጣልያንኛ ቴስታታ ብለን እንጠራዋለን።

5. ሲሊንደር ብሎክ(cylinder block)... ነዳጅ የሚቀጣጠልበት ዋናዉ የሞተር ክፍል ሲሆን በጣልያንኛ ማኖ ብሎክ ብለን እንጠራዋለን።

Credit:- ግዮን አዉቶሞቲቭ!

ፍክት ያለ ከሰአት ተመኘን
#GarageNames
@OnlyAboutCarsEthiopia
Hyundai Kona ወይስ Peugeot 2008 GT?

ሁለቱን የሚለያቸው 7 ነገሮች
1. ከ 0-100 ፍጥነታቸው - Hyundai Kona ከ 0-100 ኪሎሜትር በሰአት 7.9 ሰከንድ ሲፈጅበት Peugeot 2008 GT 8.2 ሰከንድ ነው የሚፈጅበት
2. ከፍተኛ ፍጥነታቸው - Hyundai Kona 167 ኪሎሜትር በሰአት ሲሆን Peugeot 2008 GT 208 ኪሎሜትር በሰአት ነው ::
3. ውጫዊ ገፅታ Peugeot 2008 GT የተሻለ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ::
4. የውስጥ ገፅታቸው Hyundai Kona ጨርቅ ሲሆን Peugeot 2008 GT አልካንታራ ከቆዳ ጋር ተቀላቅሎ ነው ::
5. የዋጋ ልዩነታቸው ከ 800 እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ ልዩነት አላቸው :: በዋጋ Hyundai Kona ያንሳል ::
6. አስተማማኝነት Hyundai Kona የተሻለ Rating አለው ::
7. ሞተራቸው Hyundai Kona 1 ሊትር ቱርቦ ሲሆን Peugeot 2008 GT 1.2 ሊትር ነው :: ግን ሁለቱም ሶስት ሲሊንደር ነው ያላቸው :: እነዚህን ሁለት መኪኖች ሪቪው ስለሰራን እንጂ ሌላ የሞተር አማራጫቾች አሏቸው ::

የ Peugeot 2008 GT ሪቪው ቪዲዮ ካላያችሁት
ሊንኩ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/o8_iVnteXOA

እኛን መደገፍ ከፈለጋችሁ በ VPN ብታዩት አሪፍ ነው ::

የተለየ ምሽት ተመኘን
#Peugeot2008 #HyundaiKona
@OnlyAboutCarsEthiopia
የተሽከርካሪ ክፍሎች የጣልያንኛ እና እንግሊዝኛ ስያሜ! ክፍል 2

ብዙ ጊዜ በጋራዥ ባለሙያወች ዘንድ የጣልያንኛ ስያሜ መጠቀም የተለመደ ሲሆን የትምህርት ተቋማት ደግሞ እንግሊዝኛዉን ስያሜ ይጠቀማሉ። ሁለቱንም መጠቀም እንድንችል ይህን ማብራሪያ ያዘጋጀን ሲሆን መጀመሪያ ላይ የተቀመጠዉ የእንግሊዝኛ ስያሜ ነዉ።

6. ስፓርክ ፕለግ(Spark Plug) - በቤንዚን ሞተር ብቻ የሚገኘዉ ይህ የኤሌክትሪክ ክፍል ሲሊንደር ዉስጥ የታመቀዉን ነዳጅ እና አየር ብልጭታ በመፍጠር እንዲቀጣጠሉ የሚያደርግ ክፍል ሲሆን የጣልያንኛ ስሙ ካንዴላ ይባላል።

7. ግሎ ፕለግ(Glow Plug) - በናፍጣ ሞተር ላይ የሚገኝ ሲሆን ሞተር በሚነሳበት ጊዜ እንዲሞቅ ለማድረግ ይጠቅማል። በጣልያንኛ ካንዴሊቲ ይባላል።

8. ኢንጀክተር ኖዝል(Injector Nozzle) - ተጣርቶ የመጣዉን ነዳጅ ወደ ሲሊንደር የሚረጭ ክፍል ሲሆን በጣልያንኛ እኛቶሪ ይባላል።

9. ኤር ፊልተር(Air Filter) - ወደ ሞተር የሚገባዉ አየር ንፁህ እንዲሆን የሚያጣራ ሲሆን በጣልያንኛ ደፕራተር በመባል ይጠራል።

Credit:- ግዮን አዉቶሞቲቭ!

ገራሚ ከሰአት ተመኘን
#GarageNames
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቴስላ ሞዴል 3 ወይስ ይሄ Hyundai Ioniq 6?

Hyundai በ Ioniq 5 እንዳስደመመን ሁሉ በዚህ Ioniq 6 ደግሞ ይበልጥ እንድንገረም አድርጟል :: ግን ምን ምን ቢኖረው ነው ከቴስላ ጋር ያወዳደርነው ቴክኖዎሎጂ ዲዛይኑ ወይስ ፍጥነት ? በዛሬው የዩትዩብ ቪድዮ የምንመለከተው ይሆናል :: ቪድዮ ተለቋል ሊንኩን ከስር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/PKm1nyP0ivQ

እኛን መደገፍ ከፈለጋችሁ በ VPN ብታዩት አሪፍ ነው ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Hyundai #HyundaiIoniq
@OnlyAboutCarsEthiopia
የኤልአውቶ ኢንጅነሪንግ (Taxiye) በዛሬው እለት የገጣጠማቸውን 200 መኪኖች ለደንበኞቹ በግዮን ሆቴል አስረክቧል::

ElAuto ኢንጅነሪንግ (Taxiye) የ Chery መኪኖችን በመገጣጠም የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በፊት የ Chery Arizzo እና JAC J4 መኪኖችን ለደንበኞቹ አስረክቦ ነበር :: አሁን ደግሞ 200 መኪኖችን በዛሬው እለት ለደንበኞቹ በግዮን ሆቴል አስረክቧል:: መኪኖቹ የ 2021 ሞዴል ሲሆኑ 1,000 cc ሲሆኑ 3 ሲሊንደር ያላቸው እና ባለ 5 ማርሽ ማንዋል ትራንስሚሽን ያላቸው ናቸው ::

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#Taxiye #ELAuto
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቀደም ሲል ከፍተኛ የትራፊክ ጫና በነበረበት የሳር ቤት - ጎተራ እና የጨርቆስ - ጎፋ ማዞሪያ መስመር ላይ የትራፊክ ፍሰቱን ለማሳለጥ እየተገነባ የሚገኘው የፑሽኪን አደባባይ ጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ግንባታ 98 በመቶ ገደማ ተጠናቋል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት አሁን ላይ ካልተጠናቀቁ የእግረኛ መንገድ እና ከአንዳንድ የእርማት ስራዎች በስተቀር ሌሎች የግንባታ ስራው ዋና ዋና ተግባራት ተጠናቀው በሁሉም አቅጣጫ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡

በአጠቃላይ 3.8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ30 እስከ 45 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጄክት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ እየተገባደደ ይገኛል፡፡

ይህ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት በከተማዋ የመንገድ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነ 320 ሜትር ርዝመት ያለው የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ ዋሻ (Tunnel) እና ከጎፋ ወደ ለገሃር አቅጣጫ የሚያሻግር የማሳለጫ ድልድይን ጨምሮ በቀጣይ ከአካባቢው የመንገድ መረብ ጋር ተሳስሮ ቀልጣፋ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥበት የሚጠበቀውን የፈጣን አውቶቢስ መስመር (Bus Rapid Transit) አካቶ የተገነባ ነው፡፡

Source:AACRA

መልካም እሁድ
#News #addisababa
@OnlyAboutCarsEthiopia
2022 Toyota RAV4 Hybrid

ቶዮታ ሀይብሪድ መኪኖችን በማምረት ቀዳሚ ነው :: በተለይ በ Prius በጣም ይታወቃል :: ግን አሁን ላይ ከነዳጅ ፍጆታ እና አየር ብክለት የተነሳ ብዙውን ሞዴል ወደ ሀይብሪድ እየቀየሩ ይገኛሉ :: አንዱ RAV4 ሞዴላቸው ነው :: በዛሬው ቪድዮ የ 2022 Toyota RAV4 ማይልድ ሀይብሪድ ምን እንደሚለየው ምን አሪፍ ፊቸሮች እንዳሉት የማሳያችሁ ይሆናል :: ቪድዮውን
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/OWrI3HGO4Sw

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Toyota #ToyotaRAV4
@OnlyAboutCarsEthiopia
የተሽከርካሪ ክፍሎች የጣልያንኛ እና እንግሊዝኛ ስያሜ! ክፍል 3

ብዙ ጊዜ በጋራዥ ባለሙያወች ዘንድ የጣልያንኛ ስያሜ መጠቀም የተለመደ ሲሆን የትምህርት ተቋማት ደግሞ እንግሊዝኛዉን ስያሜ ይጠቀማሉ። ሁለቱንም መጠቀም እንድንችል ይህን ማብራሪያ ያዘጋጀን ሲሆን መጀመሪያ ላይ የተቀመጠዉ የእንግሊዝኛ ስያሜ ነዉ።

10. ፊዉል ፊልተር(Fuel Filter) - ለመቀጣጠል ወደ ሞተር የሚገባዉን ነዳጅ የሚያጣራ ሲሆን የጣልያንኛ ስሙ ፊልትሮ ይባላል።

11. ቤሪንግ(Bearing) - የሜካኒካል ክፍሎችን ደግፎ በመያዝ እና ሰበቃን በመቀነስ ዝቅተኛ የሀይል ብክነት እንዲኖር የሚያስችል ሲሆን የጣልያንኛ ስሙ ኩሽኔት ይባላል።

12. ኦይል ፓን(Oil Pan) - የሞተር ዘይትን ለማጠራቀም የሚጠቅም እና ከሞተር የስረኛው ክፍል የሚገኝ ሲሆን በጣልያንኛ ሶቶኮፓ በአማርኛ ደግሞ የዘይት ቋት በመባል ይታወቃል።

13. ፊዉል ታንክ( Fuel tank) - የነዳጅ መያዣ ጋን ሲሆን የጣልያንኛ ስሙ ሳልቫትዮ ይባላል።

Credit:- ግዮን አዉቶሞቲቭ!

ልዩ ከሰአት ተመኘን
#GarageNames
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላምታዬ ይድረስ ቤተሰቦች👋

ከ July 29 ጀምሮ ወይም ከሀምሌ 22 ጀምሮ ዩትዩብ የሁሉንም የሰብስክራይብ ቁጥሩ በግልፅ እንዲታይ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል :: እና እኛም ከ 0 ጀምረን አሁን የደረስንበት ቦታ ደርሰናል :: እናም ይሄ ሁሉ የሆነው በእናንተ ስለሆነ እናመሰግናለን :: ምን አልባት ሲበራ የማትጠብቁት ቁጥር ሊሆን ስለሚችል ከአሁኑ ሰብስክራይብ በማድረግ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛውን የመኪና ሪቪው የሚሰራ ቻናል ቤተሰብ ይሁኑ :: እናም ቪድዮዎቹን በምታዩበት ጊዜ በ VPN እንድታዩ በትህትና እየጠየቅን ይህንንም ስታደርጉ የተሻለ ገቢ ስለሚገኝ እና ገቢውን ለእኛ ሳይሆን የተለያዩ መኪና ውስጥ የሚገጠሙ እቃዎችን እየገዛን Review በማድረግ መልሰን ለእናንተው በነፃ የምንሰጥ ይሆናል :: ስለዚህ ቤተሰብ ይሁኑ
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtube.com/c/yonathandesta?sub_confirmation=1

ምርጥ ቀን ተመኘን🙏
#Youtube 
@OnlyAboutCarsEthiopia
የተሽከርካሪ ክፍሎች የጣልያንኛ እና እንግሊዝኛ ስያሜ! ክፍል 4

14. ዲፕስቲክ(dipstick) - በዘይት ቋት ዉስጥ የሚቀመጥ ቀጭን ዘንግ ሲሆን የዘይት መጠንን ዉፍረትና ቅጥነትን እንዲሁም ንፅህናዉን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነዉ። በጣልያንኛ ሊቤሎ ይባላል።

15. ፍላይ ዊል(flywheel) - ክራንክ ሻፍት ጫፍ ላይ የሚታሰር ሲሆን ቁልፍ በምንከፍትበት ጊዜ ስታርተር ሞተር ጋር በመገናኘትና በመሽከርከር ሞተር እንዲነሳ የሚያደርግ ክፍል ነዉ። የጣልያንኛ ስሙ ቮላኖ ይባላል።

16. ክለች(clutch) - ማርሽ መቀየር ስንፈልግ ሀይል ከሞተር ወደ ጊር ቦክስ እንዳያልፍ የሚያቋርጥ ሲሆን በጣልያንኛ ፍሪሲዮን በመባል ይታወቃል።

17. ሪሊዝ ቢሪንግ( release bearing) - የክለች ወይም ፍሪሲዮን ክፍል ሲሆን ፍሪሲዮን ፔዳል ስንረግጥ ፕሬዠር ፕሌትን በመግፋት ሀይል እንዲቋረጥ የሚያደርግ ክፍል ነዉ። በጣልያንኛ ሪጂስፒንታ ይባላል።

Credit:- ግዮን አዉቶሞቲቭ!

ድንቅ ከሰአት ተመኘን
#GarageNames
@OnlyAboutCarsEthiopia
የተሽከርካሪ ክፍሎች የጣልያንኛ እና እንግሊዝኛ ስያሜ! ክፍል 5

18. ጊር ቦክስ(Gearbox) - ሀይል አስተላላፊ ክፍል ሲሆን የጥርስ ምርጫን በመጠቀም ጉልበት እና ፍጥነትን እንዳስፈላጊነቱ ጨምረን ወይም ቀንሰን እንድንጠቀም የሚያስችል ክፍል ሲሆን በጣልያንኛ ካምቢዮ በመባል ይጠራል።

19. ዩኒቨርሳል ጆይንት (Universal Joint) - ፕሮፔለር ሻፍትን ከጊር ቦክስ አዉትፑት ሻፍት እና ዲፈረንሻል ኢንፑት ሻፍት ጋር የሚያገናኝ ሲሆን በጣልያንኛ ኮሪቸራ በመባል ይጠራል።

20. አክስል (Axle) - ሀይል ከዲፈረንሻል ወደ ጎማ የሚያስተላልፍ ዘንግ ሲሆን በጣልያንኛ ሽሚያስ በመባል ይጠራል።

21. ስታርተር ሞተር (Starter Motor) - ኤሌክትሪካል ሀይልን ወደ መካኒካል ሀይል በመቀየር እና ፍላይዊልን በማሽከርከር ሞተር እንዲነሳ የሚያደርግ ሲሆን በጣልያንኛ ሞተሪኖ በመባል ይታወቃል።

Credit:- ግዮን አዉቶሞቲቭ!

የተለየ ከሰአት ተመኘን
#GarageNames
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/25 02:38:27
Back to Top
HTML Embed Code: