Telegram Web Link
አለም ላይ 10 ጥይት የማይበሳቸው ውድ መኪኖች

ጥይት የማይበሳቸው መኪኖች በብዛት አይመረቱም :: የሚመረቱትም ለባለስልጣናት እና ገንዘብ አውጥተው መግዛት ለሚችሉ ሰዎች ነው :: እነዚህ መኪኖች በተለያዩ አማራጮች የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ቪድዮ የተመረጡ 10 ውድ ጥይት የማይበሳቸውን መኪኖች የምንመለከት ይሆናል :: ሙሉውን ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ለቀናል :: እንድትመለከቱ ጋበዝናችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/kb4d9V9tJ_w

ያማረ ምሽት ተመኘን
#ExpensiveCars #NewVideo
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Hyundai Nexo በሃይድሮጂን የሚንቀሳቀስ የነዳጅ ሴል ያለው ብቸኛው compact crossover መኪና ነው::

አሪፍ ሰኞ ይሁንላችሁ!
#CarFacts #CompactCrossover
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?
#ad
በጥያቄዎቻችሁ መሰረት የሚያማምሩ የቁልፍ መያዣዎችን ይዘን መተናል :: እዚህ ውስጥ የሌለ ዲዛይን ካለ ደግሞ Thingverse ዌብሳይት ላይ በመግባት የምትፈልጉትን ዲዛይን በመምረጥ @Yonathandesta ላይ መላክ ትችላላችሁ ::

ቁልፍ መያዣዎቹን መግዛት የምትፈልጉ @YDLCustoms ላይ ከነዋጋቸው ታገኛላችሁ ::
አድራሻችን ቦሌ ሚካኤል ነው

በየሳምንቱ ቀለል ያሉ ሽልማት ያላቸው ጌሞች ስለሚኖሩ Instagram, Tiktok እና telegram ላይ @YDLCustoms ን ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ ::ሁሌ አርብ ምሽት ላይ ነው ጌሞቹ የሚሆኑት :: ስለዚህ በየሳምንቱ ይጠብቁን ::

ገራሚ ከሰአት ተመኘን
#CarLogo #ydlcustoms #ad
@OnlyAboutCarsEthiopia @YDLCustoms
2022 Toyota Raize

ይሄ Subcompact Crossover SUV ሲሆን የሚወዳደረው ከ Kona, Stonic እና Juke ጋር ነው :: ትንሹ RAV4 ብዬዋለሁ :: በጣም ይመሳሰላል በተለይ ከ 5ኛው ጀነሬሽን Toyota RAV4 ጋር Toyota በ hatchback ማለትም ከ Yaris ወይም ከ Agya ወይም Wigo እና በ Chr መሀል ምንም መኪና ስለሌለው ከሌሎቹ የመኪና ካምፓኒዎች ጋር ለመፎካከር የሰራው መኪና ነው :: ወደውስጥ ስንገባ ደግሞ እዚህ መኪና ላይ 8 ወይም 9 inch touchscreen ሲኖረው Apple CarPlay እና Android auto እንደ Standard ይገኛል :: እንደ ውድድር መኪና ነው ይሄንን መኪናዬን መንዳት የምፈልገው ካላችሁም ትችላላችሁ :: ምክንያቱም እዚህ መኪና ላይ Paddle shift አለ :: ግን ከፍ ያሉት ትሪም ሌቨሎች ላይ ነው :: የሞተር አማራጫቹ 1 liter turbo ያለው እና 1.2 ሊትር 3 cylinder ያለው ነው :: እቃ መጫኛውም በቂ ቦታ አለው :: 369 ሊትር መያዝ ይችላል :: ከ Safety አንፃር ደግሞ እንደ Standard ABS Vehicle Stability Control hill start assist, የጀርባ Sensoroch እና ለሹፌሩ እና ከፊት ላለው ተሳፋሪ Airbag አሉት :: ከፍ ያሉት ትሪም ሌቨሎች ላይ ደግሞ የጎን Airbag, የጀርባ ካሜራ, Blind spot monitoring system እና rear cross traffic alert እዚህ መኪና ላይ አለ :: ዋጋው የሚጀምረው ከ 2.5 ሚሊየን ጀምሮ ነው ::

ውብ ምሽት ተመኘን
#ToyotaRaize #CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Compact Crossover SUV ብዙውን ጊዜ ልክ እንደ ሙሉ መጠን SUV እና ማንኛውም መኪና ሊያቀርበው ከሚችለው እጅግ የላቀ ስፋት ያለው የውስጥ interior ያቀርባል። እናም Toyota Rav4 በጣም ጥሩ ምሳሌ ነው።

መልካም ቀን!
#CarFacts #CompactCrossover #Rav4
@OnlyAboutCarsEthiopia
Hyundai Bayon 2021

የ 2021 Hyundai Bayon አዲሱ የHyundai Subcompact Crossover SUV በ 2021 የወጣ መኪና ነው :: ከኮና በታች ያለ አውሮፓ ውስጥ ትንሹ የ Hyundai SUV ነው :: ከፊት ያለው ዲዛይን ከላይ ኮናን ከስር ደግሞ palisade ይመስላል :: ከጀርባ ዲዛይኑ ለየት ይላል :: በተለይ መብራቶቹ ሲበሩ በጣም ያምራል :: ወደውስጥ ስንገባ ደግሞ Digital cluster እንዲሁም 10.25 inch touchscreen አለው :: እዚህ መኪና ላይ የምታገኙት ፊቸሮች wireless apple CarPlay እና Android auto, Bose sound system, ambient lighting, cruise control እና Sunroof ታገኛላችሁ :: ወደ ሞተር አማራጮቹ 1 liter 1.2 liter እና 1.4 liter ናቸው :: እኛ ሀገር ግን በብዛት የሚገባው 1 liter ሆኖ Mild Hybrid መኪና ነው ::
ዋጋው ከ2.6 ሚሊየን ብር ጀምሮ ነው ::
መልካም የሴቶች ቀን ( በተለይ ይህንን ቻናል ቀጥ አርጋ ለያዘችው ለቢታንያ 😊)
የሴቶች ቀንን በማስመልከት የዛሬውን ሪቪው በልዩ መልክ የሰራችው ራስዋ ቢታንያ ነች ::
እንድትመለከቱት ጋበዝናችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLy9jgsB/

ውብ ምሽት ተመኘን
#HyundaiBayon #CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

ከToyota 4Runner ብዙ ጥቅሞች ውስጥ አንዱ በጣም ሰፊ እና ምቹ ናቸው :: ሲቀጥል ደግሞ ወንበሮቹ ከፍተኛ የመቀመጫ ቦታ ስላላቸው ሲነዱ በአካባቢዎ ላይ ጥሩ እይታ ይሰጥዎታል::

አሪፍ ውሎ ተመኘን!
#CarFacts #CompactCrossover #Toyota4Runner
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?

ሰሞኑን በጣም ብዙ ሰው ትእዛዞችን እያዘዘ ይገኛል :: እኛ እቃውን በጊዜ ማቅረብ ብንችልም ግን ሰው ያዘዘውን እቃ በጊዜ ባለመውሰዱ ምክንያት በጣም ብዙ ትእዛዞችን መስራት እየቻልን አይደለም :: ስለዚህ ያገኘነው መፍትሄ ማንኛውንም ከ 200 ብር በላይ እቃ ስታዙ መጀመርያ 50% መክፈል ይኖርባችሗል :: በማንኛውም የባንክ አካውንት መጠቀም ስለምትችሉ @Yonathandesta ወይም 0913611308 ላይ ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ :: የቀረውን 50% ደግሞ ልክ የቁልፍ መያዣው ወይም ማንኛውም ፕሪንት የተደረገው ነገር እጃችሁ ሲገባ የምትከፍሉ ይሆናል :: እና በቅርብ ጊዜ ቦሌ ጫፍ ላይ እና 22 አካባቢ እነዚህን የቁልፍ መያዣዎች የምታገኙ ይሆናል :: ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት @YDLCustoms ን ይቀላቀሉ ::

ውብ ከሰአት ተመኘን
#Announcement #Ad
@YDLCustoms @OnlyAboutCarsEthiopia
Peugeot 2008 2021

የ 2021 Peugeot 2008 ሁለተኛው ጀነሬሽን ሲሆን Active, Allure, GT እና GT Line trim leveloch አሉት :: በ 1.2 ሊትር ቤንዚል ሞተር እና በ 1.5 ሊትር ናፍጣ ሞተር ይገኛል :: እዚህ የሚገባው 1.2 ሊትር 3 cylinder ያለው ሞተሩ ነው :: ከፊትም ከጀርባም ስፖርታዊ ገፅታ አለው :: ያሉትም LED መብራቶች ናቸው :: ወደውስጥ ስንገባ 3D digital cluster ነው እዚህ መኪና ላይ ያለው :: መሀል ላይ 10 inch touchscreen ሲኖረው Wireless apple CarPlay Android Auto እና charging pad አለ :: ከዛ በተጨማሪ Ambient lighting በብዙ የቀለም አማራጮች ታገኛላችሁ :: Lane keeping assist, autonomous emergency braking, blind spot monitoring እና cruise control አለው :: ግን Adaptive cruise control አይደለም :: እቃ መጫኛው 434 ሊትር መጫን ይችላል :: ዋጋው ከ 3.3 ሚሊየን ብር ጀምሮ ነው :: ሙሉውን ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLycDjuM/

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Peugeot2008 #CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Kia Sportage
በዚህ Compact SUV ውስጥ አሪፍ የደህንነት መሳሪያዎችን፣ ጥሩ የውስጥ ክፍል እና ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የመረጃ መስጫ ያቀርባል እናም ስፍቱ በጣም አሪፍ ነው።

ብሩህ ቀን ይሁንላችሁ!
#CarFacts #CompactCrossover #KiaSportage
@OnlyAboutCarsEthiopia
2021 Kia Soul

ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት የማናየው መኪና ነው :: ይሄ መኪና ከ2008 ጀምሮ ለገበያ የቀረበ መኪና ሲሆን የ 2021 ሞዴሉ 3ኛው ጀነሬሽን ነው :: ዲዛይኑን እንደምትመለከቱት Boxy shape ሲኖረው ግን ለየት ያለ መብራት ነው ያለው ዙርያውን :: ለየት ማለቱን ወድጄዋለሁ ::
ውስጡ ላይ ደግሞ ከበሩ ጀምሮ በጣም ይለያል :: በሩ ላይ ለየት ያለ ዲዛይን ያለው Ambient lighting አለው :: ከዛ በተጨማሪ Dual zone climate control, Sunroof, Lane keeping assist, blind spot monitoring, pre collision assist እና Cruise Control እዚህ መኪና ላይ አለ ::ከጀርባ 315 ሊትር መያዝ ይችላል :: እዚህ ዘርፍ ውስጥ ካሉት አነስ ይላል :: በ 1.6 እና በ 2 ሊትር የሞተር አማራጭ የሚገኝ ሲሆን ከዛ በተጨማሪ በኤሌክትሪክም ይመጣል :: ኤሌክትሪክ ሞተር ያለው በአንድ ቻርጅ 415 ኪሎሜትር መጟዝ ይችላል :: ዲዛይኑን ብዙ ሰው ቢጠላውም ያለው አስተማማኝነት እና ዋጋው ተመራጭ ያደርገዋል ::
ስለዚህ መኪና አዲስ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ተለቋል ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLfjUr6U/

ድንቅ ምሽት ተመኘን 🙏
#KiaSoul #CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

2022 Mitsubishi Outlander
እዚህ compact SUV ውስጥ pre collision warning (የፊት ግጭት ማስጠንቀቂያ) Automatic emergency braking (አውቶማቲክ የአደጋ ጊዜ ብሬኪንግ)፣ እና አፕል ካርፕሌይ እና አንድሮይድ አውቶ 8.0 ኢንች ተችስክሪን ያለው እና All-wheel drive አማራጭ ያለው መኪና ነው።

መልካም እርብ!
#CarFacts #CompactCrossover
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?
#ad
ዛሬ ትንሽ ለየት ያለ ነገር ይዘን ብቅ ብለናል :: ከ @YDLCustoms ጋር በመሆን አንድ ቀለል ያለ ሽልማት ያለው ጥያቄ ይዘን መተናል ::

ጥያቄው

አለማችን ላይ በብዛት የተሸጠው የመኪና ሞዴል ምንድነው?

ይህንን መጀመርያ ለመለሰ ሰው የምትመለከቱትን የቁልፍ መያዣ ያገኛል ::
ህጉ አዲስ አበባ ውስጥ መሆን አለባችሁ እና የቁልፍ መያዣውን መታችሁ ነው መውሰድ ያለባችሁ ቦሌ ሚካኤል ድረስ ::
ከዚህ በፊት እንደነበረው መጉላላት እንዳይኖር ::

ገራሚ ገራሚ የቁልፍ መያዣዎችን መግዛት የምትፈልጉ @YDLCustoms ላይ ታገኛላችሁ ::
አድራሻችን ቦሌ ሚካኤል ነው ::
በየሳምንቱ እንደዚህ ቀለል ያሉ ሽልማት ያላቸው ጌሞች ስለሚኖሩ Instagram, Tiktok እና telegram ላይ @YDLCustoms ን ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ ::

ገራሚ ምሽት ተመኘን
#CarLogo #ydlcustoms #ad
@OnlyAboutCarsEthiopia @YDLCustoms
2021 Ford EcoSport

የ 2021 Ford EcoSport ላይ ለየት ብለው የምታገኟቸው 4 ነገሮች
1. የጀርባው እቃ መጫኛ መክፈቻ መብራቱ ላይ ነው ያለው
2. የውስጥ ገፅታው እዚህ ዘርፍ ውስጥ ካሉ መኪኖች ትንሽ ለየት ይላል
3. በተመጣጣኝ ዋጋ ልታገኙ የምትችሉት AWD መኪና ነው ::
4. ለ 4ቱም ጎማዎች የዲስክ ብሬክ ነው ያለው ::
ሙሉውን ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኙታላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLfuUhX1/

ገራሚ ምሽት ተመኘን
#FordEcoSport #Ford
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Nissan Rogue
ሁሉም የ 2021 Nissan Rogue ከኒሳን ሴፍቲ 360 ንቁ የደህንነት ባህሪያት ግጭት ማስጠንቀቂያ፣ Blind spot monitoring ፣ አውቶማቲክ የአደጋ ጊዜ ብሬኪንግ እና አውቶማቲክ ከፍተኛ ጨረሮች ጋር እናም ሰፊ ክፍት የኋላ በሮችን ይይዛል።

ፈታ በሉ!
#CarFacts #CompactCrossover #NissanRogue
@OnlyAboutCarsEthiopia
2021 Kia seltos

የ 2021 Kia Seltos ላይ ለየት ብለው ያገኘሗቸው 4 ጠቃሚ ነገሮች
1. wireless charge ማድረግያው ቦታ ደበቅ ያለ ነው :: ይሄ ከፀሀይም ከሌባም ያድናችሗል ::
2. ለመታጠፍ ምልክት በምታሳዩበት ሰአት ከመሪው ፊትለፊት ባለው ስክሪን በደንብ አጥርታችሁ ለማየት እንዲመቻችሁ cameraውን ያመጣል ::
3. ከጀርባ እቃ መጫኛው እዚህ ዘርፍ ውስጥ ከሚገኙ መኪኖች ተለቅ ያለ ቦታ ነው ያለው :: ዋናው ነጥብ እሱ ሳይሆን እቃ ለመጫን አመቺ እንዲሆን በማሰብ ከፍ በማድረግ ከወንበሮቹ ጋር እኩል ማድረግ ትችላላችሁ ::
4. በቁልፉ ሞተሩን ማስነሳት ትችላላችሁ :: ቁልፉንም በጣም ነው የወደድኩት :: ለየት ያለ ዲዛይን አድርገው ስላመጡት
እዚህ ጋር የጠቀስናቸውን ነገሮች በደንብ ግልፅ እንዲሆን ቲክቶክ ላይ ቪድዮ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLf7FPwW/

ያበደ ምሽት ተመኘን
#KiaSeltos #CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Subaru Forester የተባለው compact crossover SUV በአሜሪካ ውስጥ ብቻ ከ2.2 ሚሊዮን በላይ መኪኖችን ሸጧል። ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ የሽያጭ ቁጥሮች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል እና ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ Subaru በዓመት በአማካይ 177,000 መኪኖችን ሸጧል ::
2019 ከፍተኛው የሽያጭ ዓመቱ ነበር::

መልካም እሁድ!
#CarFacts #CompactCrossover #SubarusForester
@OnlyAboutCarsEthiopia
አዲስ መኪና ስትገዙ ምን ምን ማየት አለባችሁ?

1. የስንት አመተምህረት ሞዴል እንደሆነ ወሩን ማወቅ አለባችሁ
2. Trim levelun check ሳታደርጉ እንዳትገዙ
3. የውጪ ገፅታውን በደንብ መመልከት Scratch ወይም dent ወይም የተፋፋቀ ነገር ካለው እሱን መመልከት ይኖርባችሗል
4. መብራቶች እንደሚሰሩ ቼክ ማድረግ
5. ውስጡ ላይ ሻጩ አሉት ያላቸው ነገሮች በሙሉ ቼክ ማድረግ አለባችሁ
6. VIN ወይም Vehicle Identification Number ወይም ደግሞ እኛ ሀገር የሚታወቀው chassis ቁጥር መኪና ላይ ያለው እና ዶክመንቱ ላይ ያለው ቁጥር ተመሳሳይ መሆኖን ማረጋገጥ
7. የመጨረሻው እና ዋናው ዋጋው ነው ::
እነዚህን ነገሮች ማወቅ ከብዙ ወጪ ይዳርጋችሗል :: እያንዳንዱን አብራርቼ የሰራሁት ቪድዮ ስላለ Youtube ላይ ከስር ታገኙታላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/rt63O2HVi-4

እሁድ እሁድ የሚል እሁድ ተመኘንላችሁ 😁🙏
#NewCar #Yonathandesta
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

የመጀመርያው Sedan የመኪና እይነት የተመረተው በአሜርካ ሲሆን የተመረተውም በ1912 ነበረ::
Studebaker Four እና Six ሞዴሎች ነበሩ::

መልካም ሰኞ!
#CarFacts #SedanCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
አዲስ_መኪኖችን_ከመግዛታችሁ_በፊት_በቀላሉ_ቼክ_ማድረጊያ_ቼክሊስት.pdf
887.2 KB
አዲስ መኪና ስትገዙ በቀላሉ ቼክ ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች የያዘ ቼክሊስት ነው :: Print አድርጋችሁ ለመጠቀም አመቺ አርገን ነው የሰራነው :: ያገለገለ መኪና ስትገዙ ደግሞ ቼክ ማድረግያ ቼክሊስት Pin ስላደረግን እዛ ውስጥ ታገኛላችሁ ::
ሙሉ ቪድዮ YouTube ላይ ተለቋል ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/rt63O2HVi-4

አጭር ቪድዮ ደግሞ Instagram እና Tiktok ላይ ተለቋል ::
Tiktok
👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZMLPDDewV/

Instagram
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
Https://Instagram.com/Yonathan_Desta

Instagram ላይ በብዛት የቀን ውሎአችንን የምንለቅ ስለሆነ Follow ብታረጉ ትጠቀማላችሁ

ውብ ከሰአት ተመኘን
#NewCars #Yonathandesta
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/25 18:21:30
Back to Top
HTML Embed Code: