Telegram Web Link
ይህንን ያውቃሉ?

Nissan Leaf በ2010 ነበር መመረት የጀመረው እስከ አሁንም ከ400,000 በላይ መኪናዎችም ተሽጠዋል። ይህም በዓለም ላይ በጣም ተወዳጅ የኤሌክትሪክ መኪና ያደርገዋል::

መልካም ሰኞ!
#CarFacts #ElectricCars #Nissan
@OnlyAboutCarsEthiopia
የኤሌክትሪክ መኪኖች ሳምንት

Nissan Leaf

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ከዚህ በፊት ያልጠቀስኳቸውን ኤሌክትሪክ መኪኖች አንድ በአንድ በዚህ ሳምንት እንመለከታለን ::
ከ Nissan Leaf እንጀምር
Nissan Leaf ከ 2010 ጀምሮ መመረት የጀመረ መኪና ሲሆን የመጀመርያው ጀነሬሽን ከ 2011-2017 የቆየ ሲሆን አዲሱ ደግሞ ከ 2018 ጀምሮ እስከ አሁን ያለው ነው ::
የመጀመሪያው ጀነሬሽን ላይ በ 24 እና በ 30 kWh battery pack የሚገኙ ሲሆን ሬንጁ በጣም ትንሽ ነበር ::
ከ 117 ኪሎ ሜትር ወደ 172 ኪሎሜትር በአንድቻርጅ አድርሰውታል ::
ሁለተኛው ጀነሬሽን ላይ ግን በ 40 እና በ 62 kWh battery pack ስላመጡት
በአንድ ቻርጅ 270 ኪሎሜትር በ 40 kWh battery packu እና በ 62 kWh battery packu ደግሞ 364 ኪሎሜትር መጟዝ ይችላል :: እኛ ሀገር ግን ያየሁት 40 kWh battery packun ነው :: የ 2019 እና የ 2020 ሞዴሎች
ኤሌክትሪክ መኪና ላይ ያላችሁን ጥያቄ ጠይቁን ::
ሰብሰብ አርገን እንመልሳለን ::
ቪድዮውን ቲክቶክ ላይ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZMLSQWuF1/

ያማረ ምሽት ተመኘን
#NissanLeaf #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

ከ May 2019 ጀምሮ፣ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ያሉ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረግያ ጣብያዎች ብዛት ከነዳጅ ማደያዎች በልጧል። ከ Zap-Map የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው አሁን በመላው ዩናይትድ ኪንግደም ከ 8,400 የነዳጅ ማደያዎች በተቃራኒው ደግሞ 8,471 የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረግያ ጣቢያዎች አሉ። በእርግጥ የነዳጅ ማደያዎች ቁጥር እየቀነሰ መቷል::

ምርጥ ማክሰኞ ተመኘን!
#CarFacts #ElectricCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከ Nissan Leaf የወደድኩት 3 ነገር

1. Nissan Leaf ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን በ አንድ ቻርጅ ከ 270-364 ኪሎሜትር መጟዝ ይችላል :: ከተማ ውስጥ ለመንቀሳቀስ በቂ የሚባል Range ነው ::
2. ውስጡ እንደምታስቡት ጠባብ አይደለም :: እንደውም ሰፋ ያለ ነው :: Wheelbaseu ወይም ከጎማ እስከጎማ ያለው ርቀት ረዘም ይላል ::
3. ዲዛይኑን በጣም ወድጄዋለው :: በተለይ በአካል ሳየው በጣም ነው የተመቸኝ ::
አጭር ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLAJskjD/

ውብ ቀን ተመኘሁላችሁ
#NissanLeaf #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ውዱ ፒክአፕ ትራክ ምን ይመስላችሗል? Ford F-150 Limited Version ወይስ Mercedes X Class ወይስ Toyota Hilux InvicibleX 3 ቱም አይደሉም Ford Raptor Baja edition ነው :: ትላንት ጠይቀን Merdokios አግኝቶታል :: የ Jeep ቁልፍ መያዣ ከ @YDLcustoms ያገኛል :: ይሄ መኪና 525 hp ሲኖረው ከ Normal Raptor…
ይሄ መኪና ኢትዮጵያ ውስጥ የለም ስትሉ ለነበራቹ ባለቤቱ ደውሎ መኪናዬን ለምን አሳየህ ብሎ ተቆጣኝ 😂😂 ስቀልድ ነው በቅርቡ ሪቪው እንድሰራ እንደሚያመቻችልኝ እና ይህንንም ፎቶ ልኮልኛል :: ለሱ ብቻ ሳይሆን ለሁላችሁም እጅግ አርጌ አመሰግናለሁ መንገድ ላይ ስታዩኝ ጠርታችሁ ሰላም ለምትሉኝ በጥያቄ ለምታጣድፉኝ እና ለምታፈጡብኝም ጭምር 😂

ድንቅ ከሰአት ተመኘን 😊🙏
#ShelbyBajaRaptor #Yonathandesta
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሲም የሚቀበለው መኪና

Audi Q2L

Audi Q2L ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን አብዛኛውን ነገር የወሰዱት ከ Audi Q2 መኪና ነው :: ይሄ መኪና ሲም የሚቀበለው መኪናችሁ ማንኛውም አይነት እክል ወይም ችግር ካጋጠማችሁ ከዋናው Audi ቴክኒሻን ጋር ለመገናኘት እንዲቻል ታስቦ ነው :: Audi Q2L ለመጀመርያ ጊዜ የነዳሁት ኤሌክትሪክ መኪና ነው :: ስነዳ ባለቤቱን አሳቅቄው ነበር 😂😂 መዝጊያውን ደግሞ ራሴ በሰራሁት መኪና እንደሚሆን አልጠራጠርም ::
አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLAYPhyY/

ያማረ ምሽት ተመኝን
#Audi #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በ 1832 ነበረ የተሰራው :: ሮበርት አንደርሰን ነበረ የመጀመሪያውን ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን የሰራው::

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!
#CarFacts #ElectricCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
Forwarded from Only About Car Sales
የሚፈለጉ መኪኖች

- 2021 Toyota RAV4
0 Mileage
Europe Standard
Color- Avocado or Dark Gray

- New Car
0 Mileage
Duty free upto 1.5 Million

- 2021 Suzuki Alto
New Car
0 Mileage

- 2007 Toyota Corolla
Automatic Transmission
Used

እነዚህ መኪኖች ካላችሁ በ 0913611308 መደወል ትችላላችሁ ::
የሚሸጥም መኪና ያላችሁ @Yonathandesta ላይ ሙሉ መረጃውን ላኩልን ::

እንኳን ለአድዋ በአል በሰላም አደረሳችሁ
#Listings
@OnlyAboutCarSales
ይህንን ያውቃሉ?

ቴስላ ሮድስተር ከአብዛኞቹ የስፖርት መኪኖች የበለጠ ፈጣን ነው፣ ፍጥነቱ ከ0 እስከ 100 ለመግባት 1.9 ሰከንድ ብቻ ይፈጅበታል ተብሏል ። ለማነፃፀር፣ ፌራሪ ወይም ላምቦርጊኒ ከ0 ወደ 100 ለመግባት ከ2.8 እስከ 2.9 ሰከንድ ይወስድባቸዋል።
ይህም ቴስላን ፈጣን በኤሌክትሪክ የሚሰራ መኪና አስብሎታል::

ያማረ ቀን ተመኘን!
#CarFacts #ElectricCars #Tesla
@OnlyAboutCarsEthiopia
Forwarded from Only About Car Sales
Make:Suzuki
Model:Swift
Year:2022
Engine:1.2L
Drive Type:FWD
Fuel:Benzine
Transmission:Automatic
Colors: Dark Gray
Mileage:0 Km
Standard:Dubai
Plate No.:Never Used in Ethiopia
Condition:Brand New

Features:
Folding side mirrors, Power Windows, Power Locks,2 Airbags, Air Conditioning, DVD Player, Aux Audio In, Power Mirrors, Fog Lights, Parking Sensors,ABS/ESB,Alloy wheels,vehicle stability control(VSC),Keyless Entry, 12V socket-Front only,IPod Interface,Start Button,Fabric Leather Seats,Android system DVD,
Reverse Camera, Dual Tone, Cruise Control.

Price :1.4 Million Birr

ላምጭው እንዲከፈል ሕግ ያስገድዳል።

Buy and Sell cars with OnlyAboutCarSales.
@YonathanDesta @OnlyAboutCarSales
Toyota Hiace Granvia ( ዶልፊን ላይ በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ችግሮች)

ይህንን መኪና ከገዛችሁ እነዚህ አምስት ነገሮች ችግሮቹ እንደሆኑ ታስተውላላችሁ ::

1. ወፈር ያለ ነጭ ወይም ግሬይ ጭስ ነው ያለው ::
2. ፍጥነት ሲቀነስ ድምፅ አለው ::
3. ፍሪስዩኑ ይንቀጠቀጣል ::
4. የናፍጣ ሞተሩ በጣም ሞቃታማ አየር ላይ አልነሳ ይላል ::
5. ቀዝቃዛ አየር ከሆነ በተለይ ጠዋት ላይ ለመነሳት ያስቸግራል ::

እኔ የምጠቀመው ዶልፊን ላይ ያስተዋልኩት 3 ችግር
1. የቱርቦ ዘይት ያፈሳል ::
2. የጀርባው አንዱ እግር በየጊዜው እድሳት ይፈልጋል ::
3. መኪናው ነዳጅ ይበላል ::
ከዚህ ውጪ መኪናውን በጣም ነው የወደድኩት ::
እዚህ መኪና ላይ የሰራሁትም ሪቪው አለ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/5xJjI5WwCh0

ይሄ መኪና ላላቸው ሰዎች እና መኪና ለሚወዱ ሰዎች ሼር አድርጉላቸው ::
ያሎት መኪና ላይ ምን ምን በተደጋጋሚ እንደሚበላሽ ማወቅ ከፈለጉ የመኪናዎትን አመተምህረት እና ሞዴል ኮሜንት ላይ ያስቀምጡ ::

ውብ ከሰአት ተመኘን
#ToyotaHiace #Problems
@OnlyAboutCarsEthiopia
Mazda MX-30

ይሄ የመጀመሪያው የ Mazda ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን ቀጥታ ከ CX-30 ነው ዲዛይኑን የወሰዱት :: 35.5 KWh battery pack ሲኖረው በአንድ ቻርጅ 200 km መጟዝ ይችላል ::
ወደ ውስጡ ስንመጣ ደግሞ Recycle ከተደረጉ ማቴርያሎች ነው አብዛኛውን ነገር የሰሩት :: የውስጥ ቦታው ከጀርባ ለሚቀመጡ ሰዎች ትንሽ ጠበብ ይላል ::
ሙሉ ቪድዮውን ቲክቶክ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLDrJXch/

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#MazdaMX30 #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

ቴስላ ከሞዴል S እና X Plaid በፊት በሁሉም መኪኖቻቸው ላይ የመርሴዲስ ቤንዝ ማርሽ ነበር የሚጠቀሙት ::

ድንቅ አርብ ተመኘን!
#CarFacts #Tesla #Mercedes
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?
#ad
ዛሬ ትንሽ ለየት ያለ ነገር ይዘን ብቅ ብለናል :: ከ @YDLCustoms ጋር በመሆን አንድ ቀለል ያለ ሽልማት ያለው ጥያቄ ይዘን መተናል ::

ጥያቄው

የምትመለከቱት ፎቶ የምን መኪና ካምፓኒ ሎጎ ነው?

ይህንን መጀመርያ ለመለሰ ሰው ራሱን የምትመለከቱትን የቁልፍ መያዣ ያገኛል ::
ህጉ አዲስ አበባ ውስጥ መሆን አለባችሁ እና የቁልፍ መያዣውን መታችሁ ነው መውሰድ ያለባችሁ ቦሌ ሚካኤል ድረስ ::
ከዚህ በፊት እንደነበረው መጉላላት እንዳይኖር ::

ገራሚ ገራሚ የቁልፍ መያዣዎችን መግዛት የምትፈልጉ @YDLCustoms ላይ ታገኛላችሁ ::
አድራሻችን ቦሌ ሚካኤል ነው ::
በየሳምንቱ እንደዚህ ቀለል ያሉ ሽልማት ያላቸው ጌሞች ስለሚኖሩ Instagram, Tiktok እና telegram ላይ @YDLCustoms ን ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ ::

ገራሚ ከሰአት ተመኘን
#CarLogo #ydlcustoms #ad
@OnlyAboutCarsEthiopia @YDLCustoms
የባለፈው ሳምንት አሸናፊ Merdokiyos ሽልማቱን ወስዷል ::
@E_l_u_s የዚህ ሳምንት አሸናፊ ሆኗል ::
Skoda የመኪና ቁልፍ መያዣ ያገኛል :: ስለዚህ በማንኛውም ሰአት ስጦታህን መተህ መውሰድ ትችላለህ :: ስለምትሳተፉ በጣም እናመሰግናለን :: በየሳምንቱ እንደዚህ አይነት ቀለል ያሉ ጥያቄዎችን አዘጋጅተን ስለምንሸልም ለጟደኞቻችሁ ሼር አድርጉላቸው ::
የቁልፍ መያዣዎችን መግዛት የምትፈልጉ @YDLCustoms ላይ ታገኛላችሁ ::

#YDLCustoms #QandAGifts
@OnlyAboutCarsEthiopia
Weltmeister EX-5

Weltmeister በደንብ የማይታወቅ የቻይና የመኪና ካምፓኒ ነው ::ይሄ ካምፓኒ የሚሸጠው ኤሌክትሪክ መኪኖችን ብቻ ነው ::ለዛም ነው በደንብ የማይታወቀው ::Ex-5 ሞዴሉ 2 አይነት ሲሆን EX-5 400 እና EX-5 520 የሚባሉ አማራጮች አሉት ::EX-5 400 በአንድ ቻርጅ 400 ኪሎሜትር የሚጟዝ ሲሆን 52.5 KWh battery pack ነው ያለው ::EX-5 520 ደግሞ በአንድ ቻርጅ 520 ኪሎሜትር የሚጟዝ ሲሆን 69 KWh battery pack ነው ያለው :: እዚህ ሀገር ግን ያለው EX-5 400 ሞዴሉ ነው ::
ሙሉውን ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኙታላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLDt9ax4/

ገራሚ ምሽት ተመኘን 🙏
#weltmeister #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

ብዙ ሹፌሮች ብዙውን ጊዜ ይደነግጣሉ :: ለምን መሰላችሁ የኤሌክትሪክ መኪና በሚጟዝበት ሰእት ምንም እይነት ድምፅ አያሰማም እና የመጀመሪያ ጊዜ ባለቤቶቹ መኪናቸው መብራቱን እርግጠኛ እንደማይሆኑ እና የሚሰራ እንደማይመስላቸው ጭምር ይናገራሉ።

መልካም ቀን!
#CarFacts #ElectricCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

የ Tesla መኪኖች አንድ አስደሳች አዲስ feature በቅርቡ አስተዋውቀዋል :: የተዋወቀው 'ውሻ ሞድ' /Dog mode/ነው። በመኪናው ውስጥ የቤት እንስሳት ያሏቸው አሽከርካሪዎች መኪናው ውስጥ ለሚቀሩ የቤት እንስሳት ቀዝቃዛ በሆነ የሙቀት መጠን እንዲቆይ ለማድረግ የOverheat Cabin Protection ተግባርን መጠቀም እንደሚችሉ አስታውቋል ::

አሪፍ እሁድ ተመኘን!
#CarFacts #ElectricCars #Tesla
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/25 20:25:37
Back to Top
HTML Embed Code: