Telegram Web Link
ይህንን ያውቃሉ?

የሮልስ ሮይስ አውቶሞቢሎች ከ1900 መጀመሪያ ጀምሮ በመንገድ ላይ ነበሩ እና የሰዎቹም ፍላጎቶቻቸው በጊዜ ሂደት አልደበዘዘም። በተጨማሪም ዘላቂ መሆናቸውን አረጋግጠዋል :: 75% የሚሆኑት አሁንም እየሰሩ ነው ። የሚገርም ነው 😃

ፍክት ያለ ሰኞ ተመኘን
#CarFacts #RollsRoyce
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?


ታዋቂው የAudi ቀለበቶች በመኪናው ኢንዱስትሪ ውስጥ ካሉት ልዩ ምልክቶች እና በጣም ዝነኛ ከሆኑት መካከል ናቸው። የAudi አራቱ ተደራራቢ ቀለበቶች አራቱን የአውቶ ዩኒየን አምራቾች ያመለክታሉ::
Audi፣ Horch፣ DKW እና Wanderer።

የሚገርም ቀን ተመኘንላችሁ
#Audi #CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

SSC Tuatara
አሁን ላይ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው በመመረት ላይ ያለ መኪና ነው :: ከፍተኛ ፍጥነቱ 508.7 ኪሎሜትር በሰአት ነው :: 😳😮🙈 አዎ ግን አንዳንድ አጨቃጫቂ ነገሮችም አሉት :: ከሱ በፊት ሪከርድ ይዞ የነበረው መኪና Koenigsegg Agera RS ሲሆን ከፍተኛ ፍጥነቱም 447.2 ኪሎሜትር በሰአት ነው ::

ውብ እሮብ ተመኘን
#CarFacts #SSC
@OnlyAboutCarsEthiopia
Audi Etron Sportback

ይሄ በአካል ሄደን የቀረፅነው ውዱ ኤሌክትሪክ መኪና ነው :: Audi Etron Sportback ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን
እንደምታስቡት ትንሽ መኪና አይደለም :: ግዙፍ ነው ::የመኪናውን ከፍታ መጨመር ከፈለጋችሁ የተለያዩ አማራጮች ስላሉት Electronically ከፍም ዝቅም ማድረግ ትችላላችሁ :: Sportback የ Coupe ቅርፅ ነው ያለው :: 94 kWh Battery pack ሲኖረው በአንድ ቻርጅ 350 ኪሎሜትር መጟዝ ይችላል :: ከሁሉም የገረመኝ ግን Noise Cancellation አለው ::
ልክ እንደ Airpod ከውጪ የሚሰማው ድምፅ በጣም ይቀንሳል :: በጣም ነው የገረመኝ

የሚሸጥ ኤሌክትሪክ መኪና ያላችሁ ኮንታክት አርጉን :: ይህንን መኪና መግዛት ያሰባችሁ የት እንደሚሸጥ ቦታውን እንጠቁማችሗለን :: ነገ እና ከነገ ወዲያ ማንኛውም መኪና ላይ ሪቪው ስለምንሰራ ስለመኪናችሁ እንድናወራ ፈቃደኛ የሆናችሁ በ @Yonathadesta ላይ ኮንታክት አርጉን ::
ስለ ኤሌክትሪክ ያላችሁን ጥያቄዎች እያየን ነበር :: ስለዚህ በተመጣጣኝ ዋጋ ያሉትን መኪኖች በቅርብ ጊዜ የምናቀርብ ይሆናል ::

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#Audi #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
Photo
ሰላም የ OnlyAboutCarsEthiopia ቤተሰቦች
ነገ እና ከነገ ወዲያ ሙሉ ቀን በየቦታው እየዞርን ሪቪው ለመስራት አስበናል :: ስለዚህ ማንኛውም መኪና ያላችሁ ሪቪው እንድሰራ ፈቃደኛ ከሆናችሁ እናንተ በሚመቻችሁ ሰአት ባላችሁበት ቦታ በመገኘት የምንሰራ ይሆናል :: ብዙ ሰው ይጠይቀናል እኛ በነፃ ነው ለሰዉ ስለመኪና ለማሳወቅ እንጂ ከእናንተ የምንቀበለው አንድም ነገር የለም :: ስለዚህ ፈቃደኛ የሆናችሁ በ @Yonathandesta ወይም በ @OnlyCarsBot ያላችሁን መኪና ሞዴል እና አመተምህረት እንዲሁም የምትችሉበትን ሰአት ብታናግሩን ፕሮግራማችንን አስተካክለን እንገኛለን ::

የ Audi Etron Sportback ኤሌክትሪክ መኪና ሙሉውን ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኙታላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZML2hN9uh/

ገራሚ ከሰአት ተመኘን
#CarReview #Yonathandesta
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

በ 1940 የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የመጀመሪያውን ባለ አራት ጎማ መኪና አመረተ። ምናልባት ስለሱ ሰምተው ይሆናል :: Jeep Willy ተብሎ ይጠራል :: ይሄ መኪና ለአሜሪካ ቢጠቅምም አሁን ላሉት Full Size SUV መነሻው እሱ ነው :: ለ Toyota LandCruiser ለ Nissan Patrol እና ሌሎችም...

ድንቅ ቀን ተመኘን
#Jeepwilly #CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም የ OnlyAboutCarsEthiopia ቤተሰቦች
ባለፈው በለቀቅነው የ 3D ቁልፍ መያዣዎች በጣም ብዙ ትእዛዞች መተዋል ::
ግን ማሽኑም በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት መስራት አቁሞ ስለነበር ነው የጠፋነው :: ለሁላችሁም በአንድ ጊዜ ማድረስ ባለመቻላችን ይቅርታ እየጠየቅን ስለዚህ ያለን አማራጭ እራሳችንን ብዙ ሰው ሊወዷቸው የሚችሉት ዲዛይኖች በብዛ እየሰራን እና መሸጥ ነው :: ያዘዛችሁትን ቅልፍ መያዣ ወይም ሌላ በ 3D ፕሪንት እንዲደረግ የፈለጋችሁትን እቃ ሁሌ ቅዳሜ ቅዳሜ ነው የምናደርሰው :: ግን እኔ ማዘዝ ነው የምፈልገው 3D ዲዛይን እራሴ እሰጣችሗለሁ የምትሉ ትእዛዝ እንቀበላለን :: ግን ትእዛዝ ሲሆን እንደ ትእዛዛችሁ ይለያያል :: ከ ሳምንት እስከ 2 ሳምንት ሊወስድ ይችላል ::
ስለዚህ ማዘዝ የምትፈልጉት ቁልፍ መያዣ በመምረጥ @Yonathandesta ብላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ :: የምንሰራቸውን ቁልፍ መያዣዎች በ @YDLCustoms ላይ እንለቃቸዋለን ::
Join አድርገው ይጠብቁን
በቅርብ ቀን ይጠብቁን

ውብ ምሽት ተመኘን
#3DPrinted #KeyChains
@OnlyAboutCarsEthiopia
Audi Etron Sportback ላይ የምታገኟቸው ሌሎች መኪኖች ላይ የሌሉ ነገሮች
1. በማታ የሚገርም መብራት ነው ::
2. Navigation System በምትጠቀሙበት ሰአት የግድ ታይፕ ማድረግ አይጠበቅባችሁም ::
3. ስኮርት ጎማ ወይም ቅያሪ ጎማው ከፋብሪካ ሲመጣ ሳይነፋ ተጣጥፎ ነው ::

ይሄንን እና ተጨማሪ ነገሮችን ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZML2pLtb6/

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Audi #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

በአለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤሌትሪክ ትራፊክ ምልክት በዩክሊድ አቬኑ ኦሃዮ በ 1914 ተቀምጧል ። ከዛ በጣም እየረቀቀ መቶ ስማርት ትራፊክ መብራት ላይ አሁን ደርሷል ::

ብሩህ ቀን ተመኘን
#Trafficlight #CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

በ2010 ከተፈቀደው ፉጥነት በላይ ሁለት እጥፍ በስዊዘርላንድ በሰዓት 299 ኪሎሜትር በሆነ ፍጥነት Mercedes Benz SLS AMG መኪናውን ሲያሽከረክር ትይዞ 1.15 ሚሊየን ዶላር ተቀጥቷል። ይህም ከፍተኛው የቅጣት መጠን እስብሎታል::

ውብ ቅዳሜ ተመኘን
#CarFacts #Speedticket
@OnlyAboutCarsEthiopia
Toyota Corolla 2002-2008

እነዚህ አምስት ነገሮች እዚህ መኪና ላይ በተደጋጋሚ የሚበላሹ ፓርቶች ናቸው ::

1. Master cylinder ያስቸግራል ::
2. Timing chain tensioner ይላላል ::
3. Variable valve timing ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች
4. Starter በተደጋጋሚ ይበላሻል ::
5. EVAP ያፈሳል ::

ይሄ መኪና ላላቸው ሰዎች እና መኪና ለሚወዱ ሰዎች ሼር አድርጉላቸው ::
ያሎት መኪና ላይ ምን ምን በተደጋጋሚ እንደሚበላሽ ማወቅ ከፈለጉ የመኪናዎትን አመተምህረት እና ሞዴል ኮሜንት ላይ ያስቀምጡ ::

የተለየ ከሰአት ተመኘን
#ToyotaCorolla #Problems
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስለአዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንጻ የመኪና ማቆሚያ ትንሽ እንበላችሁ

አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ከምድር በታች 4 ወለል የመኪና ማቆሚያ ሲኖረው እስከ 1500 መኪና ማቆም ይችላል። በሁለተኛው ምድር ቤት የሚገኘው የመኪና ማቆሚያ በዓይነቱ ለየት ያለ እና ዘመናዊ ሜካኒካል መኪና ማቆሚያ ሲሆን በአንድ ጊዜ 541 መካከለኛ መኪኖችን ደራርቦ ማቆም እና በካርድ መኪኖችን መጥራት የሚያስችል መሳሪያ የተገጠመለት ነው። አውቶማቲክ መሳሪያው ብልሽት ሲኖር የሚጠቁም እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጠገን የሚያስችል ሲስተም አለው።

የታዋቂው የቻይናው ‘ዳያንግ ፓርኪንግ’ ስሪት የሆነ መሳሪያ የተገጠመለት ይህ መካኒካል መኪና ማቆሚያ በጥቂት ቦታ ብዙ መኪኖችን ማቆም የሚያስችል የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡

Source:- CBE (Commercial Bank of Ethiopia)

መልካም ሰንበት(እሁድ) ተመኘን
#CBE #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
አስገራሚው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጥበቃ

ፕሬዝዳንቶች በጣም እንደሚጠበቁ እናውቃለን :: ግን ምን ያህል ነው ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያስወጣቸው ::
በዛሬው ቪድዮ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ሲንቀሳቀስ ይዟቸው የሚሄደው ከተማ ነው የማሳያችሁ :: ከተማ ስል የመኪና እንጂ የሀገር አይደለም :: እንደዚህ ያልኩበትን ምክንያቱም እነግራችሗለሁ :: በመጨረሻም እንዴት ፕሬዝዳንቱን ያተረፉበትንም መንገድ አሳያችሗለሁ ::
ሙሉውን ቪድዮ YouTube ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
Https://YouTube.com/YonathanDesta

ገራሚ የእረፍት ቀን ተመኘን
#America #Security
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

የዓለማችን ረጅሙ መኪና ርዕስ በካሊፎርኒያ መኪና ጉሩ ጄይ ኦህበርግ በእጅ የተሰራ/custom made/ ሊሞዚን ነው ። መኪናው 100 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ በዓለም ላይ ከተሰራው ረጅሙ መኪና ተብሎ ተመዝግቧል። የሚገርመው መኪናው የመዋኛ ገንዳ እና የሄሊኮፕተር ፓድም አለው።

የተለየ ሰኞ ተመኘን
#CarFacts #Limousine
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስለ Go kart ምን ማወቅ ትፈልጋላችሁ?

ማወቅ የምፈልጉትን በሙሉ በጥያቄ መልክ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ::
የሰራው ሰው ጋር በመሄድ ቪድዮ የምንሰራ ይሆናል ::
ተጨማሪ መረጃዎችን ደግሞ @GokartsinAddis ላይ ታገኛላችሁ ::

ኢትዮጵያዊው የ Formula 3 ተወዳዳሪ ላይ የሰራነው አጭር ቪድዮ አለ
እንድትመለከቱት ጋበዝናችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZML6YTLGD/

መልካም ምሽት ተመኘንላችሁ
#Gokart #F3
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

በአደጋ ጊዜ ኤርባግ በ30 ሚሊ ሰከንድ ባለ ፍጥነት ውስጥ ስራውን የሚጀምረው ::

ውብ ከሰአት ተመኘን
#CarFacts #Airbag
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለምንድነው የድሮ መኪኖች ላይ የማትሰራው ትሉኛላችሁ

ይኸው
Peugeot 404

የፈረንሳይ መኪና ሲሆን የተሰራው ለአፍሪካ ታስቦ ነው ::
በጣም ነው የወደድኩት ካየሁት በሗላ
የጎን ማርሽ መሆኑ
ክላክሱ
ሰስፔንሽኑ
ብቻ ምን አለፋችሁ ቪድዮውን ካያችሁት በሗላ ትወዱታላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZML6uM329/

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
#Peugeot404 #Classiccar
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

የመርሴዲስ ቤንዝ ታዋቂው ባለ ሶስት ጫፍ ኮከብ የኩባንያውን የበላይነት በሶስት ቦታዎች ማለትም በባህር, በአየር እና በመሬት ላይ የሚያሳይ ነው::

ገራሚ ቀን ተመኘን
#CarFacts #Mercedes
@OnlyAboutCarsEthiopia
Custom car Key Chains (የቁልፍ መያዣዎች)

በተለያዩ ዲዛይኖች የተሰሩ የመኪና ሎጎ ያላቸው ቁልፍ መያዣዎች ናቸው ::
በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀረብናቸው ሲሆን ዋጋቸው ከ 150-350 ብር ነው ::
ማዘዝ የምትፈልጉ በ @yonathandesta ላይ ማዘዝ ትችላላችሁ ::
መኪና ዘርፍ ላይ የተሰማራችሁ የመኪና አስመጪዎች ሻጮች ስፔር ፓርት አከፋፋዮች የመኪና ቁልፍ ላይ የምትሰሩ ሰዎች በብዛት ማዘዝ ትችላላችሁ ::

ተጨማሪ መረጃ @YDLCustoms ላይ ታገኛላችሁ ::

#Keychains
@YDLCustoms
2024/09/26 23:19:21
Back to Top
HTML Embed Code: