Telegram Web Link
Forwarded from Only About Car Sales
Make:Kia
Model:Stonic
Year:2021
Body Type:Subcompact Crossover SUV
Engine:1.0L Turbo GDI
Drive Type:FWD
Fuel:Benzine
Transmission:Automatic
Color:White & Black
Mileage:0 Km
Fuel Consumption:14-17 KM/L
Plate No.:Never Used in Ethiopia
Condition:Brand New

Features:
Air Conditioner
Auto Air Conditioner
Heated & Ventilated Seat
Leather Seats
Power Steering
Heated Steering Wheel
Cruise Control
USB & Bluetooth
Apple CarPlay & Android Auto
Navigation
Auto Folding Side Mirror
Power Windows
Smart Key
Push Start & Stop
Rear Spoiler
Roof Rack
6 Airbag Driver Airbag
Passenger Airbag
Side Airbag
Curtain Airbag
Park Assist Sensor
Rear View Camera
ABS (Anti-lock Brake System)
ESP (Electronic Stability Program)
Sunroof
Lane keeping assist
Lane departure warning
Traction Control
Decent Boot Space (352 Liters)
17 inch Tires

Price:2.7 Million Birr

ላምጭው እንዲከፈል ሕግ ያስገድዳል።

📱0991157053

@YonathanDesta @OnlyAboutCarSales
ሮልስ ሮይስ HP-15 በፕላኔታችን ላይ ካሉ በጣም ብርቅዬ መኪኖች አንዱ እንደሆነ ያውቃሉ?

ብርቅዬ ለመኪናም አለ እንዴ ትሉ ይሆናል ::
አዎ 😂
ለምን ይሆን ብላችሁ እያሰባችሁ ነው?
አጠቃላይ 6 መኪኖች ናቸው የተሰሩት ። ከእነዚህ መኪኖች ውስጥ አንዱ ብቻ ነው በአለም ላይ የሚገኘው ። እና ዋጋው 35 ሚሊዮን ዶላር ነው ተብሎ ይገመታል :: መኪናው 3 ሲሊንደሮች ሲኖረው ከፍተኛ ፍጥነቱም 63 ኪሎሜትር በሰአት ነው ::

ገራሚ ቅዳሜ ተመኘን
#CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ክሩዝ ኮንትሮልን የፈጠረው ሰው ዓይነ ስውር መሆኑን ያውቁ ኖሯል?

ስሙ ራልፍ ቴተር ይባላል፣ እና በጣም ደካማ ሹፌር በነበረው በጠበቃው ምክንያት ክሩዝ ኮንትሮልን ለመፈልሰፍ ተነሳሳ።
የሚገርም ታሪክ ነው እሱ ላይ የሰራሁትን አጭር ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtube.com/shorts/2R6o7sWfdNs?feature=share

አሪፍ የስራ ቀን ተመኘን
#CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
በአውቶፓይለት እርዳታ ቴስላ መኪና ውስጥ ልጇን ተገላግላለች ::

አሁን ልጇ ቴስላ ይባል ይሆን?🤔😂

ሰዎች በቴስላ አውቶፓይለት የመንዳት ቴክኖሎጂ ላይ በጣም በመተማመን አንዳንድ የተለየ ነገሮችን ሲያደርጉ ሰምተናል። አሁን የተሰማው ግን ትንሽ ለየት ያለ ነገር ነው ::

የፔንስልቬንያ ሴት ይራን ባለቤቷ መኪና እየነዳ እያለ በቤተሰቡ ቴስላ ሞዴል 3 የፊት ለፊት ተሳፋሪ ወንበር ላይ ወንድ ልጅ ተገላግላለች - በመኪናው ላይ ባለው አውቶፓይለት ትልቅ እገዛ።

የይራን ሼሪ ውሃ በሴፕቴምበር 1 ቀን ጠዋት ተሰብሯል፣ ነገር ግን ባለቤቷ ኪቲንግ ሼሪ ወደ ሆስፒታል ከመሄዳቸው በፊት የ3 አመት ወንድ ልጃቸውን ራፋን ወደ ትምህርት ቤት እንዲወስደው ነገረችው። ነገር ግን ምጧ ስለመጣ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል መጟዝ ጀመሩ። የ 11 ኪሎሜትር ጉዞ በዛ ላይ መንገድ በሚዘጋጋበት ሰአት ስለነበር ሆዷ ውስጥ ያለው ልጃቸው መድረሻቸው እስኪደርሱ ድረስ መጠበቅ አልፈለገም።

ይራን መግፋት መጀመር አለባት የሚለውን በማሰላሰል ህመሟን በመቆጣጠር ላይ አተኩሯል። ኪቲንግ አውቶፓይለት ሲስተሙ በማብራት በዚህ ለመረዳት በሚያስቸግር አስጨናቂ የመጓጓዣ ጉዞ ውስጥ በጣም የሚፈለግ እገዛን ሰቷል :: ግራ እጁን በተሽከርካሪው ላይ በማቆየት ይራን እንድትገፋ እያገዛት ነበር ። ሆስፒታል ሲደርሱ የሶስት ቤተሰብ አባላት አራት ሆኑ ።ይራን ልጅቷን በመንገድ ላይ ወልዳለች።

ሜቭ ብለው ነው የሰየሟት ህጻን በቴስላ ውስጥ የተወለደ የመጀመሪያው ሕፃን እንደሆነ ይታመናል።

መኪና ውስጥ ከመውለድ ይጠብቃችሁ ልል ነበር ግን እንደዚህ አይነት ገራሚ መኪና ውስጥ መወለድም እድል ነው 😂😂ምን አልባት እንደኔ ቤት ውስጥ የተወለዳችሁ ስለምትኖሩ 😁

መልካም ቀን ተመኘን
#AmazingCarStory
@OnlyAboutCarsEthiopia
በቡና የሚሰራ መኪና እንዳለ ያውቃሉ?
Car-Puccino

ታዳሽ የኃይል ምንጭ ለመፍጠር በተደረገ ሙከራ በካፑቺኖ የሚነዳ መኪና ተፈጠረ። የመኪናው አሠራር ጥቅም ላይ የሚውለው ቡናን ወደ ተቀጣጣይ ጋዝ በመለወጥ ነው :: በ"Car-Puccino" ውስጥ 1.6 ኪሎሜትር ለመጟዝ 56 ኤስፕሬሶዎች ይፈልጋል።
ቢቀርስ ያስብላል 😂
ዋናው ግን ፈጠራው ነው

ፈታ ብላችሁ የምትሰሩበት ቀን እንዲሆን ተመኘን
#CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሪቪያን የመጀመሪያውን ሁለት SUV መኪናቸው ለተጠቃሚዎች አደረሱ


ሪቪያን ባለፈው ሳምንት ስለተሰጡት የመጀመሪያዎቹ ሁለት R1S ትንሽ ተጨማሪ ዝርዝሮችን አውጥቷል :: ነገር ግን በአብዛኛው በድብቅ ሁኔታ ላይ ነው ያለው ።

የመጀመሪያዎቹ ሁለት መኪኖች ለኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ (RJ Scaringe) እና CFO (ክሌር ማክዶን) ተሰጥተዋል::

እንደምናስታውሰው የመጀመሪያው R1T ለ RJ Scaringe ነበር የተሰጠው :: አብዛኛዎቹ የመጀመሪያ R1Tዎች ለሪቪያን ሰራተኞች ተሰተዋል ።

ሪቪያን የመጀመሪያዎቹን ተሽከርካሪዎች ለሠራተኞች የማድረስ ስልቱን እንደቀጠለ እና ከፍ ባለ ፍጥነት ወደ ደንበኞች እንደሚያሰፋ ግልጽ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ ዓለም ተሽከርካሪውን ከመመልከቱ በፊት እና ገለልተኛ ግምገማዎችን ከመስጠቱ በፊት ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን የመጨረሻ ዝርዝሮችን ለመያዝ እና ጥራቱንም ለማሻሻል ይረዳል ።

ሪቪያን የኢቪ ጅምር ሲሆን ይህ ማለት ኩባንያው የመጀመሪያዎቹን ምርቶች ለመጀመር ቀላል አልነበረም ፣ በተለይም ሶስት ምርቶች በአንድ ጊዜ ስለጀመሩ - R1T ፣ R1S እና EDV van።

እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ ወደ 1,200 R1T/R1S መኪኖችን ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል :: እስኪ የምናየው ይሆናል ::

የሚገርም ምሽት ተመኘን
#CarNews #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለከተማ የሚሆን SUV መኪና | 2021 Kia Stonic Review
ሙሉውን ቪድዮ YouTube ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/8oMtzNLwp1c

መኪናውን ለመግዛት የምታስቡ እዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
@OnlyAboutCarSales

ፈታ የምትሉበት ከሰአት ተመፕሁላችሁ
#yonathandesta #CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
የጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማበረታቻ ተጠቃሚዎች እነማን ናቸዉ?

መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታትና የስራ እድልን ለመፍጠር እንዲሁም ሀገራችን ከወጪ ንግድ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ከፍ ለማድረግ የተለያዩ የታክስ ማበረታቻዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ከሚስጣቸው የታክስ ማበረታዎች ውስጥ አንዱ የጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማበረታቻ ነው፡፡

በሚከተሉት የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማራ ባለሀብት የማበረታቻው ተጠቃሚ ይሆናል
• በማምረቻ ኢንዱስትሪ፤
• በግብርና
• በኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭነት
• የኮከብ ደረጃ ባላቸዉ ሆቴሎች(ሪዞርት) ሞቴሎች ሬስቶራንቶችና ሎጆዎች
• በመገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) ልማት
• በአስጎብኝነት ስራ
• በኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ማስተላለፊያና ማሰራጫ
• የራስን ህንፃ በመገንባት የሚሰጥ ትምህርትና ስልጠና
• የራስን ህንፃ በመገንባት የሚሰጥ የጤና አገልግሎት
• በአርቲቴክቸር እና ኢንጅነሪንግ ስራዎች የቴክኒክ ምርመራና ትንተና፣
• ተሽከርካሪ የማይጨምር የካፒታል እቃዎች ኪራይ ላይ የሚሰማራ ባለሀብት የቀረጥ ነጻ ማበረታቻ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ማበረታቻ ለማግኘት ሊቀርቡ የሚገቡ ሰነዶች
• የኢንቨስትመንት ስርተፊኬት፤
• የንግድ ሥራ ፈቃድ (ሥራ ለጀመረ)፤
• የግብር ከፋይ መለያ/TIN/፤
• ኮሜርሻል ኢንቮይስ( COMMERCIAL INVOICE )፤ማስጫኛ ሰነድ፤
• የባንክ ፈቃድና የግዢ ትእዛዝ LC፤
• በትውልድ ኢትዮጲያዊ የውጭ ዜጋ እና በዜግነት የውጭ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ፤ውጭ አገር ነዋሪ ኢትዮጲያዊ ከኢትዮጲያ ኤምባሲ ተፅፎ በዉጭ ጉዳይ ሚ/ር የተረጋገጠ ደብዳቤ ናቸው፡፡

Source: EthioCarMarket

የምታርፉበት እሁድ ተመኘን
#Cardata
@OnlyAboutCarsEthiopia
2021 Cadillac Escalade

የ 2021 Cadillac Escalade ሙሉ በሙሉ ነው Redesign የተደረገው ::
- አዲሱ ከበፊቱ Escalade ስለረዘመ ለሁለተኛውና ለሶስተኛው መደዳ ወንበሮች እንዲሁም የእቃ መጫኛው ሰፋ ያለ እንዲሆን አድርጎታል ::
- እንዲሁም የሚገርሙ ቴክኖዎሎጂዎች ተካተውበታል ::
- የ Cadillac's Super Cruiseን ጨምሮ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፊቸሮችን እዚህ መኪና ላይ ታገኛላችሁ እና አብዛኛውን ዳሽቦርድ የሚሸፍነው ትልቅ እስክሪን ነው።
- ከስር ደግሞ ጠንካራ አክሰል ዲዛይን የበለጠ የምቾት ጉዞ እንዲሰጥ አስበው የሰሩት ነው።
- የEscalade ስታንዳርድ ሞተር 6.2-ሊትር V8 ሲሆን እንደ አማራጭ በ V6 ሞተርም ይገኛል ::
- የ2021 Escalade ባለ ሶስት ረድፍ ትልቅ የቅንጦት SUV ሲሆን በአምስት የትሪም ደረጃዎች፡ Luxury, Premium Luxury, Sport, Premium Luxury Platinum and Sport Platinum. Escalade እስከ ስምንት ሰዎች ድረስ መያዝ ይችላል ::
- ካስፈለገ ደግሞ እንደ አማራጭ የመሀለኛውን ወንበሮች በማውረድ ለሰባት ሰዎች በቂ ቦታ ይሰጣል ።

ተጨማሪ መረጃ ደግሞ Tiktok ላይ ተለቋል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZM8wShngU/

ገራሚ ምሽት ተመኘን
#CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
Toyota LandCruiser አለማችን ላይ ከሚገኙ መኪኖች በጣም አስተማማኝ እንደሆነ ያውቃሉ?

በ 2020 አሜርካ ውስጥ በተደረ ጥናት ከ ማንኛውም መኪና በላይ LandCruiser አስተማማኝ እንደሆነ አረጋግጠዋል ::
ጥናት ከተደረገባቸው መኪኖች ከ 15% በላይ LandCruiser ከ 320,000 ኪሎሜትር በላይ ያለምንም ዋና የሚባል ችግር እንደሚጟዙ አስመስክረዋል ::
ከሱ ቀጥሎ ያለው መኪና Toyota Highlander Hybrid ሲሆን ከ5% በታች የሆኑት ናቸው 320 ሺህ ኪሎሜትሩን ያለፉት ::
ምን ያህል ትልቅ ልዩነት እዳለው ተመልከቱ ::
ለዛ ነው ብዙ ጊዜ እነዚህን መኪኖች ጋራዥ ቆመው የማናያቸው ::
እስኪ የእናንተን ሀሳብ ኮሜንት ላይ አጋሩን ::

ስለ አዲሱ Toyota LandCruiser 300 Series ቪድዮ ለመመልከት
YouTube
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/nQUCSUL_S80
Tiktok
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZM8w9Xjuw/

ገራሚ ከሰአት ተመኘን
#CarFacts #ToyotaLandCruiser
@OnlyAboutCarsEthiopia
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረግያ ተመረቀ።

በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪካዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን በመገጣጠም ፈር ቀዳጅ በመሆን የሚታወቀውየማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያውን የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማደያ እና ሁለተኛውን ሞዴል ሃዩንዳይ KONA SUV የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት አስመርቋል።

Source: YeneTube

አሪፍ ምሽት ተመኘንላችሁ
#CarNews #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
Lincoln Navigator መኪና ላይ ያሉ 5 ገራሚ ነገሮች


- የመጀመርያው Automatic መርገጫዎች አሏቸው :: ይህ ማለት መኪናው ሲከፈት የሚወርድ ሲዘጋ ደግሞ ከፍ የሚል ነው ::
- ሁለተኛው የጀርባው መስታወት ብቻ ይከፈታል :: ትንንሽ እቃ ከያዙ ሙሉ በሙሉ መክፈት አይጠበቅባችሁም ::
- ሶስተኛው ደግሞ ይህ መኪና የቤተሰብ መኪና ስለሚሆን የ3ተኛ መደዳ ላይ ልጆቻችሁ ካስቸገሯችሁ የጭንቅላት ማስደገፊያውን ወደታች ዝቅ ስለሚል በዛ መቅጣት ትችላላችሁ ::
- አራተኛው ተጨማሪ የፊት መስታወት ስለተገጠመለት ልጆቻችሁን በደንብ መከታተል ትችላላችሁ ::
- የመጨረሻው ደግሞ የ3ተኛው መደዳ ሰፊ ስለሆነ ለልጆች ብቻ ሳይሆን ለትልቅ ሰውም ተመቻችቶ ለመቀመጥ የሚያስችል ነው ::

ተጨማሪ ቪድዮ Tiktok ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZM8wTgeS4/

አሪፍ ምሽት ተመኘን
#CarReview #LincolnNavigator
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ እስከዛሬ በሰራናቸው ቪድዮ የትኛው ለኔ ይሆናል ብላችሁ አሰባችሁ?
Anonymous Poll
16%
Hyundai Kona
24%
Ford F-150 Lightning
3%
Hyundai Ioniq
13%
Tesla Cybertruck
4%
Hyundai Ioniq 5
17%
Tesla Model S
14%
Hummer EV
9%
Tesla Model 3
BMW X7 ላይ የሚገርመው ማርሽ

BMW X7 ላይ የተጠቀሙት ማርሽ የክሪስታል ማርሽ ሲሆን እንደዚህም ያደረጉበት ምክንያት የቅንጦት መኪና መሆኑን ለማሳወቅ ነው :: ይሄ በከተማችን አንድ እንደሚገኝ አረጋግጠናል :: እናንተም ያያችሁት ካለ አሳውቁን :: እዚህ መኪና ላይ ተጨማሪ ፊቸሮችን Tiktok ላይ ለቅቀናል
ተመልከቱ
በርግጠኝነት ትወዱታላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽
https://vm.tiktok.com/ZM8KFHShX/

ውብ ምሽት ተመኘን
#CarReview #SUV
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/27 11:25:05
Back to Top
HTML Embed Code: