Telegram Web Link
#ዜና

BMW የማምረቻ ሮቦቶቹ በፍጥነት እንዲሰሩ ሲል 3D Printed በሆኑ ክፍሎች እየሰራቸው ነው።


የጀርመኑ የመኪና አምራች BMW የማምረቻ ሮቦቶቹን በክብደታቸው ቀላል የሆኑ በ3D printed በተደረጉ ክፍሎች እየሰራቸው ያለ ሲሆን ይሄም ሮቦቶቹ ስራቸውን በቅልጥፍና እንዲያከናውኑ እና ረዥም የአገልግሎት ዘመን እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል።

መኪና ላይ ክብደቱን መቀነሳችን ብዙ ነገር የሚያቀልልን ሲሆን አነስ ያሉ ሾክ አብሶርበሮችንን እና አነስ ያሉ የፍሬን ዲስክ መጠቀም እንድንችል ያረገናል። ሮቦቶች ላይም እንደ መኪና ሁሉ የሚሰሩበትን ክፍሎች በቀላል ማቴሪያሎች የምንሰራ ከሆነ አነስ ያሉ ሮቦቶችን እንድንጠቀም የሚያስችለን ሲሆን ይህም ምንጠቀመውን ሃይል በመቀነስ የማምረቻችንን የካርበን ልቀት እንድንቀንስ አስተዋፆ ያረጋል።


በቅርቡ ዲዛይን የተደረገው በማምረቻ ውስጥ የሚገጣጠሙ መኪኖችን ሙሉ የላይኛውን ክፍል(ጣሪያ) እና ሙሉ የመኪናውን የታችኛውን ክፍል ለመሸከም የሚጠቀምበት ሮቦት አሁን ላይ ክብደቱ ከ100 kg ያነሰ ሲሆን ከመጀመሪያው ሮቦት ሲነፃፀር  በ45% ያነሰ ክብደት ነው ያለው።

ይህ ማለትም በፊት ሶስት ሮቦቶች ሙሉ የመኪናን የላይኛውን ክልፍ(ጣሪያ) ለመሸከም ያስፈልጉ የነበረውን አሁን ላይ አንድ ሮቦት ብቻውን ይሸከመዋል።

BMW 3D printed የሆኑ ክፍሎን ከተሸካሚው ሮቦት ላይ ከመጠቀሙ ባለፈ መኪኖቹ ላይም ይጠቀማቸዋል። ያለፈው አመት ላይ በመላው ማምረቻዎቹ ወደ 400,000 የሚሆኑ 3D printed የሆኑ ክፍሎችን ተጠቅሞዋል።

#BMW #Manufacture_Robots #3D_Printing
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የአሜሪካ ወጣቶች የቻይና መኪኖችን ለመጠቀም ፍቃደኛ ናቸው።


የባይደን አስተዳደር የአሜሪካን የመኪና ገበያን ከተቀናቃኙ ለመጠበቅ ሲል የቻይና መኪኖች ላይ 100% የቀረጥ ታሪፍ ጥሎዋል። ለዚህም ጥሩ ምክንያት አለው። Autopacific የተባለ ድርጅት ባደረገው የዳሰሳ ጥናት 76% የሚሆኑ እድሜያቸው ከ40 አመት በታች የሆኑ ሰዎች በሃገረ ቻይና የተመረቱ መኪኖችን ለመግዛት ፍቃደኛ የሆኑ እና የቻይና መኪኖች ከምርጫ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዳሉ ተናግረዋል።

Autofasfic ይሄ ሁሉ ወጣት ስለቻይና የመኪና ብራንዶች ማወቃቸውን ማወቁ እንዳስገረመው የተናገረ ሲሆን ለዚህም ማህበራዊ ተስስር ገፆች ከፍተኛ አስተዋኦ እንዳላቸው አክሎ ተናግሮዋል።

በእድሜ ገፋ ያሉ አሜሪካዊያን ማለትም እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑት በተጋነነ ሁኔታ የቻይና መኪኖች ላይ ጥላቻ ያላቸው የሆነ ቢሆንም ከነሱ ውስጥም 25% የሚሆኑት የእድሜ ባለፀጎች የቻይና መኪኖች ሊገዙ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የዳሰሳ ጥናቱ ከተካሄደባቸው 16% የሚሆኑ መላሾች የቻይናዎቹ መኪኖቹ በአሜሪካ በአሜሪካ እና በሃገረ ሜክሲኮ ሚመረቱ ከሆነ ለመግዛይ ያላቸው ፍላጎት ይበልጡን እንደሚጨምር ገልፀዋል።

ከ70% የሚሆኑ በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ መላሾች የመረጃ ደህንነት(privacy) ስጋት እንዳለባቸው የተናገሩ ቢሆንም የቻይና መኪኖች ላይ  ፍላጎት ከማሳደር አልገደባቸውም።

#USA #China_Cars
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volkswagen ID-7 ለገበያ የሚቀርብበትን ቀን አዘገየው።


አንጋፋው የመኪና አምራች Volkswagen ID-7 የተሰኘውን የኤሌክትሪክ ሴዳን መኪናውን በአሜሪካ እና በካናዳ ገበያ ላይ ሊያቀርብበትን የነበረበትን ጊዜ ያራዘመው ሲሆን እንደ እቅዱ ከሆነ በዚ አመት ውስጥ ለገበያ ሊቀርብ ነበር።

የመኪና አምራቹ  መኪናውን በሰሜን አሜሪካ ላይ ለሽያጭ የሚቀርብበትን ቀን ያዘገየበትን ምክንያት ያልተናገረ ሲሆን ብዞዎች ለዚህ ምክንያት የመኪናው ሴዳን መሆኑ እና በሰሜን አሜሪካ ገበያ ላይ እምብዛም ሴዳን መኪኖች ተፈላጊ አለመሆናቸው ነው ይላሉ።

Volkswagen የኤሌክትሪክ መኪና ሽያጩን በሰሜን አሜሪካ ከማዘግየቱ በተጨማሪ አውሮፓ ላይም ተመሳሳይ ነገር እያደረገ ነው።
የመኪና አምራቹ የፋይናንስ ዋና ሃላፊ እንደተናገሩት በአውሮፓ የሚገኘው የባትሪ ማምረቻቸው ሙሉ አቅሙ ላይ ለመድረስ ከታቀደለት ጊዜ በላይ ይወስዳል።

Volkswagen አሁንም ቢሆን የባትሪ ምርቱን በቀጣ አመት ላይ ለመጀመረ ያቀደ ቢሆን የኤሉአክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ፍላጎት መቀዛቀዙ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ መጠን ወደ ማምረት የሚገባ አይሆንም።

#Volkswagen #ID-7
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Porsche ቻይና ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪኖቹን መሸጥ ከብዶታል።


ታዋቂው የቅኑጡ መኪኖች አምራች የሆነው Porsche አዲሱን 911 መኪናን ለመጀመሪያ ጊዜ በሃይብሪድ ቨርዥን ትናንት ይፋ አድርጎታል።

አይኖች ሁሉ ምንም አዲሱ Porsche 911 ላይ ቢሆኑም Porsche ቻይና ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖቹን መሸጥ ከብዶታል። ያለፈው አመት በቻይና ገበያ ላይ ያለው ሽያጩ በ23% የቀነሰ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ ገና በመጀመሪያው የእሩብ አመት አጋማሽ ሽያጩ ተጨማሪ 24% ቀንሶዋል።

ብዙዎች ለዚህ ምክንያት የሆነ በቻይና ከሚገኙት ተቀናቃኞቹ በመጣ ጫና ምክንያት ነው ይላሉ።  በቻይና የሚገኙት የPorsche አከፋዮች አሁን ላይ Taycanን በዝቅተኛ ዋጋ እያሸጡ ያሉ ሲሆን ይሄንን ደግሞ የPorsche መኪኖች የመሸጫ ዋጋን ከፍ በማረግ ማካካስ ይፈልጋሉ።

ቻይና ውስጥ ብዙ የውጪ ሃገር የመኪና ብራንዶች የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመሸጥ ሲታገሉ ማየት የሚያስገርም ባይሆንም እንደ Porsche ያለ Iconic የመኪና ብራንድን በእንደዚ አይነት ነገር ሲቸገር መመልከት አጀብ የሚያሰኝ ነው።

#Porsche #911 #China
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ብራዚል ከቻይና መኪኖችን ኢምፖርት በማረግ የ#1ቱን ደረጃ ያዘች።



እንደ China Passenger Car Association መረጃ መሰረት ብራዚል ቤልጀምን በመብለጥ ትልቋ የቻይና የመኪና የኤክስፖርት ገበያ ሆናለች።
በወርሃ ኤፕሪል ከ40,000 በላይ የሚሆኑ የኤሌክትሪክ እና የፕለጊን ሃይብሪድ መኪኖች ወደ ብራዚል ኤክስፖርት የተደረጉ ሲሆን ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ13 እጥፍ ከፍ ያለ ነው። እናም ለተከታታይ ሁለት ወራት ብራዚል ትልቋ የቻይና መኪና ኤክስፖርት ገበያ ሆናለች።

ይህም የብራዚል መንግስ በወርሃ ጁላይ የሃገር ውስጥ የተሽከርካሪዎችን ምርት ለመደገፍ ሲል ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ የኤሌክትሪክ እና የሃይብሪድ መኪኖች ላይ የቀረጥ ታሪፉን ከፍ እንዲያረግ ካረጉት ምክንያቶች አንዱ ነው።
ይሁን እንጂ ብራዚል ለቻይና የመኪና አምራቾች ትልቋ ገበያ ሆናለች። በአለም አቀፍ ደረጃም ሁሉንም አይነት ተሽከርካሪዎ ኢምፖርት በማረግ ከሩሲያ ቀጥላ ሁለተኛዋ ትልቋ የኤክስፖርት ገበያ መዳረሻ ሆናለች።

#Brazil #China #NEV_Import
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota የካርበን ልቀት የሌላቸውን ሞተሮች እያበለፀገ ነው።


Toyota ፣Mazda፣ እና Subaru በጋራ ሆነው የሚሰሩበት Mulipathway Workshop የፈጠሩ ሲሆን 3ቱም የመኪና ብራንዶች የኤሌክትሪክ የሆኑ እና  የካርበን ልቀት የሌላቸውን ኢንጅኖችን ማበልፀግ ይጠበቅባቸዋል ይሆናል።

ነገር ግን አላማው የተለመዱትን አይነት ኢንጅኖችን መስራት አይደለም። አዲስ የኢንጅን አይነቶችን ሲሆን የመኪና አምራቾቹ የብራንዳቸው መገለጫ ከሆኑትን ነገሮች ውስጥ ጥቂት ነገሮች የሚያበለፅጉት አዲስ ኢንጅን ላይ ይኖራል። 

ለምሳሌ Subaru አግድም ተቃራኒ የሆኑ 'Boxer' ኢንጅኖችን መስራቱ ይቀጥላል ነገር ግን በኢንጅን እና በሃይብሪድ powertrain መካከል  ያለ የኤሌክትሪክ ሞተር በሚመስል መልኩ ወደ ሃይብሪድ እንዴት እንደሚቀይራቸው በተሻሻለው Crosstrek ላይ ፕሮቶታይፕ ሰርቶ አሳይቶዋል።

በሌላ በኩል Mazda በRotary ኢንጅኖች ላይ እንደሚሰራ የተናገረ ሲሆን ባለ 1 ሞተር እና ባለ 2 ሞተር የኤሌክትሪክ መኪና ሲስተምን አሳይቶዋል። የሚጨመርበት ኢንጅንን ደግሞ እንደ የkm ሬንጅ ማራዘሚያ የሚጠቀምበት ይሆናል።

ሌላኛው ካምፓኒዎቹ የነዳጅ መኪኖችን የካርበን ልቀት ለመቀነስ ካቀዱበት መንገድ አንዱ የኢንጅኖቹን ሽፋን መቀነስ ሲሆን Toyota እንደ Subaru ሁሉ ይሄን ለማሳካት ከኤሌክትሪክ ሞተር ጋር ተጣምሮ መስራት የሚችል ኢንጅን ዲዛይን በማረግ እንደሆነ ያምናል።
ዲዛይኑ በኢንጅን እና በሃይብሪድ powertrain መካከል የኤሌክትሪክ ሞተር የተቀመጠ ሲመስል የPowertrainኑን ሳይዝ በመቀነስ አጣቃላይ የመኪናውን ሳይዝ መቀነስ እንደሚችል ያምናል።
....
.
....

እናም ሶስቱ ካምፓኒዎ ኢንጅኖቻቸውን ከካርበን ገለልተኛ ከሆኑ ነዳጆች ጋር ተስማሚ ለማረግ የሚሞክሩም ይሆናል።
Toyota ባለ2L ቱርቦ ቻርጅድ ክፍል ያሳየ ሲሆን ከENEOS፣Mitsubishi Heavy Industries እና Idemitsu Kosan ከተባሉ ድርጅቶች ጋር ለመኪናዎች ከካርበን-ገለልተኛ ነዳጆችን ለማምረት እና ለገበያ ለማቅረብ አጋርነት መፍጠሩን አስታውቋል።

ሆኖም ግን ጊዜ የሚወስድ ይሆናል። አሁን ላይ ገና ነዳጁ ላይ ጥናት ማረግ የመሩ ሲሆን በቅርቡ ለአለም ይፋ ያረጓቸዋል ተብሎ አይጠበቅም። እስከ 2030 ባለው ጊዜ ጃፓን ላይ ነው ይፋ የሚደረጉት።

#Toyota #Subaru #Mazda
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Jeep 25,000 ዶላር የመሸጫ ዋጋ ያለውን አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ሊሰራ ነው።/ የCitroen አዲሱ መኪና አውሮፓ ላይ በ23,000 ዩሮ።


Jeep ለአሜሪካ ገበያ የሚውል አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴል በ25,000 ዶላር የመሸጫ ዋጋ ይዞ ሊቀርብ ነው። የሚመረተውም ከአዲሶቹ Opel ፣ Vauxhall Fontera እና በአውሮፓ ገበያ ላይ በ23,000 ዩሮ ለሽያጭ ከሚቀርቡት  Citroen e-C3 ጋር ተመሳሳይ በሆነ ፕላትፎርም ይሆናል።

Citroen e-C3 በተገጠመለት 44 kilowatt hour LFP ባትሪ በአንድ ቻርጅ እስከ 320km መጓዝ ይችላሉ።
የኤሊክትሪክ ሞተሩ 113 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጭ ሲሆን ፍጥነቱ በሰአት ከዜሮ እስከ 100 km ለመድረስ 11 ሰከንዶች ይወስዱበታል። Top speedዱም በሰአት 135 km ነው።

citron እንዳለው በቀጣይ አመት ላይ ከ20,000 ዩሮ ባነሰ ዋጋ ከዚህኛው የረከሰ ቨርዥን በ200 km የድራይቪንግ ሬንጅ ይዞ እንደሚቀርብ ተናግሮዋል።

የ25,000 ዶላሩ Jeep ብዙ የሚዲያ ሽፋን የሚያገኝ ቢሆንም ከCitroen e-C3 ጋር ተመሳሳይ በሆነው ስፔስፊኬሽኑ አሜሪካ ላይ ያን ያህል አይሸጥም እየተባለ ነው።

#Jeep #Citroen e-C3
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የIONNA የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀሮቹን ኢንስታቴሽን በታቀደበት ጊዜ አይጀመርም።



በቅርቡ የተመሰረተ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጂንግ ካምፓኒ IONNA በዚህ Summer አቅዶት እንደነበረው ቻርጀሮቹን መትከል አይጀምርም።

IONNA በBMW ፣ Hond ፣ Hyundai ፣ Kia ፣ Mercedes እና Stellantis አጋርነት ፈጥረው የመሰረቱት እና በያዝነው አመት መጀመሪያ ላይ ይፋ ያረጉት ካምፓኒ ነው።
አላማው 30,000 የቻርጂን ስቴሽኖችን ሰሜን አሜሪካ ላይ መገንባት ነው። ከቀም ብሎ እንዳሳወቀው የካምፓኒው የመጀመሪያዎቹ ፈጣን ቻርጀሮች በዚህ Summer መገጠም እንደሚጀምሩ ቢሆንም WardsAuto ይዞት የወጣው መረጃ ላይ ህብረቱ ውስጥ ያሉ ሁለት የመኪና አምራቾች በተባለው ጊዜ ቻርቸሮቹ መገጠም እንደማይጀምሩ ገልፀዋል።
በዛ ምትክ በአመቱ ማገባደጃ ላይ የሚጀመር ይመስላል።

IONNA የቻርጀሮቹን ኢንስታሌሽን ለማዘግየቱ ምክንያት ከሆኑት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ቻርጀሮቹን በCCS እና በቴስላው NACS ኮኔክተሮች ማቅረብ ስለፈለገ ነው።

#IONNA #EV_Charging_Station
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Archer የተባለው VTOL(vertical take-off and landing aircraft) ኮሪያ ላይ ትልቅ ሽያጭ አገኘ።


የአሜሪካው የVOTL ካምፓኒ Archer Aviation ደቡብ ኮሪያ ላይ 50 እንደ ሄሊኮፕተር በቆሙበት ወደ መብረር የሚችሉ እና በዛው መልክ ማረፍ የሚችሉ Aircraftቶችን ለመሸጥ ስምምነት ፈረመ።

aircrafቶቹን ለመግዛት ስምምነቱን የፈረመው KakaoMobility የባለ የመጓጓዣ ካምፓኒ ሲሆን በ250 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ነው ስምምነቱን ያደረጉት።

ካምፓኒው ደቡብ ኮሪያ ላይ የeVTOL ትራንፖርት አገልግሎትን መስጠት የሚጀምር ሲሆን ከ2026 ጀምሮ ለ30 ሚሊየን ለሚሆኑ ተጠቃሚዎቹ ይሄን የአየር ጉዞ ማቅረብ የሚጀምር ይሆናል።

የኮሪያ መንግስትም የከተማ ላይ የአየር ጉዞዎችን ወደ ንግድነት ከ2030 በፊት ለመጀምር ያቀደ ሲሆን አገልግሎቱ በዋና ከተማዋ Seoul ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

በነገራችን ላይ Archer በተባለው የVTOL ካምፓኒ ላይ Stellantis ፣ American Airlines እና Boeing ኢንቨስት አድርገውበታል።

#Archer #VTOL-Aircraft
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Jeep የመጀመሪያ ኤሌክትሪክ መኪናውን ለአሜሪካ ገበያ አቀረበ።


የ2024 Jeep Wagoneer S የብራንዱ የመጀመሪያ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን በመጀመሪያም የቀረበው በአሜሪካ እና በካናዳ ገበያ ላይ ነው።

ይህ መኪና Four wheel drive ሲሆን 600 የፈረስ ጉልበት እና 836 Nm torque ይኖረዋል። በዚህም አቅርቦቱ ከ0 ወደ 100 ኪሎሜትር በሰአት በ3.4 ሴኮንድ መድረስ እንደሚችል እና በ አንድ ቻርጅ እስከ 482 ኪሎሜትር እንደሚሄድ ተነግሯል።

Jeep ብራንድ የራሱ የሆነ ያለመንሸራተት ቴክኖሎጂ ያስገባበት ሲሆን በ Auto, sport, Eco, Snow እና sand በማንኛውም አየር ሁኔታ እና መንገድ ላይ መነዳት እንደሚችል አሳውቋል።

በስታንዳርድ ቨርዥኑ ካሉት ፊቸሮች መካከል 20 inch ጎማ 45 inch ስክሪን እና Panoramic sunroof ወጣ ብለው የሚታዩት ገፅታዎቹ ናቸው።

የዚህ መኪና ዋጋ ከ 72,000 የአሜሪካን ዶላር የሚጀምር ሲሆን በ2024 የመጀመሪያ ግማሽ አመት ላይ የJeep መሸጫዎች ውስጥ ይገኛል።

#Jeep #Wagoneer_S
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Ad

Yango pro ላይ በቀን በትንሹ ለ 5 ሰአታት በመስመር ላይ በመሆን እና የሚመጣውን ጥሪዎች ተቀብሎ በማጠናቀቅ በትንሹ በየሳምንቱ የተረጋገጠ 10,000 ብር ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

አሽከርካሪዎች አፑን ለመጫን ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
bit.ly/4bEE8m8

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ገፃቸው
https://www.tg-me.com/YangoETH

እንዲሁም የፌስቡክ ገፃቸው
https://www.facebook.com/groups/1171500204006823

#Yango_pro #Earnings #Driving
ነገ ግንቦት 25, 2016 የ ራሊ የመኪና ውድድር ይካሄዳል

ቦታው - ገላን ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት ነው የሚሆነው ::

መታሰቢያነቱ ከዚህ በፊት ተወዳዳሪ ለነበረው ጆርጅ ፓውሎ ነው ::

ነገ እዛው እንገናኝ

#CarRace #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

DS የሽያጭ ሰልፉ ላይ ጥይት የማይበሳው መኪና አስገባ።


DS በሚባል የሚታወቀው የፈረንሳይ አምራች DS 7 Elysee ያሳየውን ተቀባይነት በመደገፍ እና DS 7 E-Tense 4x4 300ን መሰረት በማድረግ  DS 7 Vauban የተባለ Armored plug-in ሀይብሪድ መኪና ለገበያው አቅርቧል።

ይህ መኪና የሚመረተው ፈረንሳይ ውስጥ ሲሆን ከDS 7 E-Tense 4x4 300 ወደ DS 7 Vauban የሚለወጠው Herimoncourt የምትባል ከማምረቻው 100 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ የምትገኝ ከተማ ውስጥ ነው።

ክብደቱ በጣም እንዳይጨምር በማድረግ እና የተገጠመለት Armor (ጥይት እንዳይበሳው) ለይቶ እንዳይታይ የተደረገ በመሆኑ ከተመሰረተበት DS 7 E-Tense 4x4 300 መኪና ለመለየት ይከብዳል ።

#DS #7_Vauban
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Renault group እና Geely “HORSE powertrain limited” የተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መፍጠራቸውን አሳውቀዋል


July 11, 2023 በተፈረመው ስምምነት መሰረት HORSE powertrain limited May 31, 2024 በRenault group እና Geely ግማሽ ግማሽ ባለቤትነት ተፈጠረ።

አዲሱ ኩባንያ ገበያ ላይ የhybrid እና የነዳጅ መኪና እቃ እና አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግሯል።

Matias Giannini CEO ሲሆኑ የBoard ዳይሬክተር ደግሞ Daniel Li በመሆን ተሹመዋል።

ይህ ኩባንያ 15ቢልዮን ዩሮ ገቢ እንደሚኖረው እና 5ሚልዮን የሀይል አስተላላፊ ክፍል ለገበያ እንደሚያቀርብ ተገምቷል። 

ኩባንያው ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከሚያቀርበው የHybrid system፣ የነዳጅ ሞተር፣ የTransmission system እና የባትሪ መፍትሄዎችን ያጠናቀቀ ፖርትፎሊዮ ይኖረዋል።

#Geely #Renault_group #horsepower_powertrain_limited
#ዜና

የFord ምርት የሆነው የኤሌክትሪኩ F-150 lightning መኪና Demonstrator በPikes peak ላይ እንደሚወዳደር ተገለፀ።


መኪናውን የሚነዳው የPikes peak ሪከርድ የያዘው Romain Dumas ሲሆን ውድድሩ የሚካሄደው June 23, 2024 እንደሚሆን ተነግሯል።

ይህ መኪና በF-150 Lightning ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከSTARD ጋር በመተባበር የተሰራ ሲሆን እስከ 1400 የፈረስጉልበት ይኖረዋል።

በተጨማሪም የመኪናው Aerodynamics 241 ኪሎሜትር በሰአት በሚሄድበት ጊዜ 2721 ኪሎግራም ጭነት በሚያክል ሀይል መኪናውን በመጫን የተሻለ Grip እንዲኖረው ያደርጋል።

ከውድድሩ በተጨማሪ መኪናው በሚያሳየው ጥራት እና ድክመት ላይ ተመስርቶ ለገበያው የሚቀርበው መኪና ላይ ማሻሻያ እደሚደረግ ተነግሯል።

#Ford #F-150_lightning
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Hyundai Ioniq 5 N የተባለው ኤሌክትሪክ መኪናውን ለ Pikes peak ውድድር አቀረበ።


በውድድሩ ላይ ለገበያ የቀረበውን Ionic 5 N እና  በጣም ሞዲፋይ የተደረገውን Time Attack Spec Ionic 5 N ይዛ ቀርቧል።

ይህ መኪና ከተደረገለት Aerodynamic ቦዲ በተጨማሪ ከኖርማሉ Ionic 5 N በ37 የፈረስጉልነት በመብለጥ አጠቃላይ ጉልበቱን ወደ 685 የፈረስጉልበት ሊጨምረው ችሏል።   

በተጨማሪም በዝሁ መኪና ወደ Nurburgring በመመለስ የTCR ክፍል ውድድሩን ለ4ተኛ ጊዜ ለማሸነፍ አቅደዋል።

#Hyundai #Ioniq5
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ford በ2 አመት ውስጥ ሹፌሮች መንገዱን ሳያዩ መንዳት እንደሚችሉ ተናገረ።


የFord CEO Jim Farley ሹፌሮች እጃቸውን ከመሪ ላይ አንስተው አይናቸውንም መንገድ ላይ ሳያደርጉ መንዳት የሚቻል መሆኑን ተናገሩ።

አላማው መኪናን ተንቀሳቃሽ ቢሮ ለማድረግ ሲሆን የዋጋ መቀነስ ጉዳይ ሆኖ እንጂ ይህ ቴክኖሎጂ አሁንም ያለ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መኪኖቹ እንደዚህ ሆነው እስከ 130 ኪሎሜትር በሰአት መነዳት የሚችሉ ቢሆንም በዚህ ፍጥነት ለመንዳት የአየር እና የመንገዱ ሁኔታ በጣም ጥሩ መሆን አለበት።

Ford በአሁኑ ጊዜ የሚጠቀመውን Blue Cruise system በወር 75 የአሜሪካን ዶላር በመክፈል ወይም በ 3 አመት 2100 የአሜሪካን ዶላር በመክፈል መጠቀም ሲቻል ለአዲሱ ሲስተም እንደጨመሩ እና እንዳልጨመሩ አልተናገሩም ።

ይህ ሲስተም ወደ ገበያው እስከ 2026 እንደሚቀርብ ተገምቷል ።

#Ford #Autonomous
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከ TOYOTA BZ4X የተሻለ ኤሌክትሪክ መኪና ነው?

2024 Nissan Ariya

ይሄ የመጀመሪያው የኒሳን ኤሌክትሪክ SUV መኪና ሲሆን በጣም እንዳሻሻሉት የምታውቁት ከውጪ እንዳያችሁት ነው :: ዲዛይኑ ከ Concept ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው :: ለዛም ነው የጃፓን የወደፊት መኪና የሚል ስያሜን የሰጡት :: ታድያ ውስጡ እና ምን የተለየ ፊቸር አለው? ከ Toyota BZ4X ጋር እያወዳደርን እናያለን :: ምን የተሻለ ነገር አለው? የሚሉትን ነገሮች በዛሬው የዩትዩብ ቪድዮ እናያለን :: ተመልሻለሁ ማየት የምትፈልጉትን መኪና በኮሜንት ላይ አሳውቁኝ
የቪድዮውን ሊንክ ከስር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/H60jr1P0pmE

መኪኖቹን ማየት እና መግዛት ከፈለጋችሁ
Afrolink Motors ሾው ሩማቸው ጎራ በማለት መመልከት ትችላላችሁ :: ስለ መኪኖች ማወቅ አለባችሁ የምንላቸውን ቪዲዮዎች እኛው ራሳችን ስለምንለቅ የቴሌግራም ቻናላቸውን ፎሎ ማድረግ እዳትረሱ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

@afrolinkmotors

መኪና መሸጥ እና ማከራየት የምትፈልጉ ሁሌመኪና ላይ 300 ብር ብቻ በመክፈል ማስተዋወቅ እና መሸጥ/ማከራየት ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

@hulemekina

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Nissan #Electric
#Afrolinkmotors #Hulemekina
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota ለሙከራ ካዋላቸው 7 የመንግስት ስታንዳርድ የማያሟሉ ሞዴሎቹን መለሰ።


Toyota ከሚለቃቸው ሞዴሎች ውስጥ ለደህንነት የሚያሰጉ የሆኑትን 3ቱን እንደሚመለስ ገለፀ። 

እነዚህ መኪኖች የደህንነት ፍተሻ የጎደላቸው በመሆኑ ከገበያው ላይ እነዲወጡ መደረጋቸው ተነገረ።

Mazda፣ Honda ፣ Yamaha እና Suzuki እንደዚው አይነት ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር እና የደህንነት ፈተኖቻቸውን አጭበርብረው እነደነበር የጃፓን መንገድ ትራንስፖርት ሚኒስተር አሳውቋል።

#toyota #mazda #Suzuki
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/06/27 09:22:40
Back to Top
HTML Embed Code: