Telegram Web Link
#ዜና

8 የመኪና አምራቾች በደንበኞቻቸው የግል መረጃ አያያዝ ላይ የተዛባ መረጃ ለደንበኞቻቸው በመስጠት ተወንጅለዋል።


የመኪና አምራቾች ሲዋሹ ተያዙ። 2014 ላይ 8 የመኪና አምራቾች ከPrivately ጋር ተያይዞ በፈቃደኝነት የደንበኞቻቸውን መረጃዎች ለመንግስት አካላት በፍርድ ቤት ትዛዝ ፍቃድ ተሰቶአቸው ሲመጡ ለማቅረብ ፈርመው ነበር።

መኪኖች ይበልጥ በዘመኑ እና የተለያዩ መረጃዎችን የመኪና አምራቾፅ መሰብሰብ በጀመሩ ቁጥር Privacy ጥያቄ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ሆኖዋል። የዲሞክራቶቹ ሴናተሮች Ed Markey ከMassachusetts ግዛት እና Ron Wyden ከOregon ግዛት 8 የመኪና አምራቾችን የደንበኞቻቸውን መኪኖች የGPS location ለፖሊስ ስለመስጠታቸው የተዛባ መረጃ በመስጠታቸው እና ግልፅ ባለማረጋቸው ከሰዋቸዋል።

የመኪና አምራቾቹ Toyota፣ Nissan፣ Subaru፣ Volkswagen፣ BMW፣ Mazda፣ Mercedes-Benz እና Kia ሲሆኑ ለህግ አውጪዎች ይደንበኞቻቸውን መረጃ ካለፍርድ ቤት ትዛዝ እና ፍቃድ ለፖሊስ ሲሰጡ እንደነበር ተናግረዋል።

ሴናተሮቹም የመኪና አምራቾቹ ይሄን ለደንበኞቻቸው ግልፅ ባለማረጋቸው የከሰሷቸው ሲሆን ለFederal Trade Commission ካምፓኒዎቹ ላይ ምርመራ እንዲያረ ሲሉ ደብዳቤ ፅፈዋል።

#AutoMakers #Privacy
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nio ቴስላን እንዲቀናቀን በማሰብ አዲስ የመኪና ብራንድ ይፋ አረገ።



የቻይናው የመኪና አምራች Nio በዋጋቸው ቀነስ ያሉ መኪኖች የሚያመርት Onvo የተሰኘ አዲስ ብራንድ ይፋ አድርጎዋል።  የብራንዱ የመጀመሪያ መኪና የሆነው L60 ሲሆን የቦዲ ስታይሉ Mid-Size Crossover የምንለው እና በቀጥታጣየቴስላውን ሞዴል Y አንዲቀናቀን ታስቦ የተሰራ ነው።

መኪናው ባለ 900- ቮልት አርክቴክቸር የሚጠቀም ሲሆን የሃይል አጠቃቀሙ በየ100Kmሩ 12.1 kilowatt hour ነው። ይሄም ከቴስላ ሞዴል Y በትንሹ ያነሰ ነው።

ሶስት የባትሪ ፓክ አማራጭ ያለው ሲሆን እነሱም ባለ 60፣ ባለ 90፣ እና ባለ 150 kilowatt hour ነው። እንደ ባትሪ ፓክ ሳይዙ ከ555 km ጀምሮ እስከ 1,000 km የሚደርስ የKm ሬንጅ አለው። 
Nio  እንዳለው እንዴሌሎቹ የNio መኪኖች ሁሉ L60ም የBattery swapping ፊውቸር ተካቶለታል።

አሁን ላይ L60ን ኦርደር ማረግ የተጀመረ ሲሆን የመነሻ ዋጋው ከ30,500 ዶላር ጀምሮ ነው። ይሄም ከቴስላ ሞዴል Y  አንፃር በ12% ቅናሽ አለው። በደንበኞች እጅ ላይም በሶስተኛው የሩብ አመት አጋማሽ ላይ የሚደርስ ይሆናል።

#Nio #Onvo #L60
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አሜሪካ የቻይና የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪዎች እና የባትሪ ክፍሎች ላይ ያለውn የቀረጥ ታሪፍ ከፍ አረገች።



ከትናንትና ወዲያ የወጣ ዘገባ በሃገረ ቻይና ተመርተው በBuick እና በLincoln አሜሪካ ላይ የሚሸጡ መኪኖች ላይ 100% የቀረጥ ታሪፍ ይኖርባቸዋል ይል ነበር። ነገር ግን ቀረጡ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ብቻ የሚመለከት በመሆኑ Buick እና Lincoln የሚጎዳቸው አይሆንም።

አሁን ላይ የቀረጥ ታሪፉ በቻይና የሚመረቱ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪዎች እና የባትሪ ክፍሎች ላይ የተጨመረ ሲሆን በፊት ላይ ከነበረበት 7.5% ወደ 25% ከፍ ብሎዋል። ይሄም ለኤሌክትሪክ መኪኖቻቸው ከቻይና ባትሪን ኢምፖርት የሚያረጉ ካምፓኒዎች ላይ ጫና ይኖረዋል።

ለምሳሌ እንደ አንዳንድ የMustang Mach E እና F-150 Lightning ያሉ የፎርድ መኪናዎች በቻይናው የባትሪ አምራች በሆነው CATL የሚመረቱ LFP ባትሪዎችን ይጠቀማሉ።
አሁን የተጣለው የ25% የቀረጥ( Tax) ክፍያ ለመኪና አምራቾች ከቻይና  LFP ባትሪዎችን በቅናሽ በማስገባት ያገኙት የነበረውም Advantage ሙሉ በሙሉ ያስቀረዋል።

#LFP_Batteries #USA #Tax
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አሜሪካ ላይ አዲስ መኪና ለመግዛት ካሰቡ ሰዎች ውስጥ 80% የሚሆኑት የኤሌክትሪክ መኪኖች የመግዛት ፍላጎት አላቸው።


ስለ ኤሌክትሪክ መኪኖች ሲነሳ ብዙ ጊዜ እንደ መሞገቻ ነጥብ ሰዎች ከሚያነሱት ውስጥ " ማንም አይፈልጋቸውም" የሚለው ሃሳብ ነው ። ነገር ግን እንደ Cox Automotive የዳሰሳ ጥናት መረጃ መሰረት 80% የሚሆኑ አዲስ መኪና ለመግዛት ያሰቡ አሜሪካዊያን የኤሌክትሪክ መኪኖችን ነው የሚፈልጉት። ብቸኛው ነገር መኪኖቹን አሁን ላይ አይደለም የሚፈልጓቸው። እንዳሉት በመጪው ከ3 እስከ 5 አመት ባለው ጊዜ ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለመሸመት እና ለማሽከርከር ዝግጁ ይሆናሉ።


ይሄም ማለትም በ2030 ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ በጣም ይጨምራል። ከCox Automotive የዳሰሳ ጥናት ላይ የተገኙት ሁለት አበይት መረጃዎች
የመጀመሪያው አብዛኞቹ የመኪና ሸማቾች የኤሌክትሪክ መኪና በመጠቀማቸው የሚያገኟቸውን ጥቅማ ጥቅሞች አያውቁም። የመኪና አምራቾች በማስታወቂያዎቻቸው ውስጥ እነዚህን ጥቅማ ጥቅሞች አካተው ማሳየት ይኖርባቸዋል።

ሌላኛው ደግሞ አብዛኛው ሰው በቅርብ የሚያውቁት የኤሌክትሪክ መኪና የሚጠቀም ሰው ካለ አነሱም የመግዛት ፍላጎታቸው ይጨምራል።

#Electric_Cars #USA
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Renault: Rafaleን በፕለጊን ሃይብሪድ ቨርዥን ከፍ ባለጉልበት ሰራው።



Renault አዲስ መኪና ይፋ ያረገ ሲሆን መኪናው Rafale የተባለው ባለፈው አመት ላይ የወጣው የRenault አዲስ የSUV መኪና ስፖርት ቨርዥን በፕለጊን ሃይብሪድ የሃይል አማራጭ ነው።

መኪና Rafale E-Tech 4×4 300hp ሲሆን ከስሙ ተነስታቹ ምን ያህል የፈረስ ጉልበት እንዳለው መገመት አይከብድም።
ሴታፑ ቱርቦ ቻርጅድ የሆነ ባለ1.2 L 3ሲሊንደር ኢንጂን ከኤሌክትሪ ሞተር ጋር አጣምሮ የያዘ ሲሆን አንደኛው የፊተኛው Axle ላይ እና ሌላኛው ደሞ የኋለኛው ላይ የተገጠመ ነው።

200 የፈረስ ጉልበት ካለው ከስታንዳርዱ ፕለጊን ሃይብሪድ Rafale፤ Rafale E-Tech 4×4 300hp ሲነፃፀር ፍጥነቱ ከዜሮ እስከ 100 ለመድረስ ከ2 ሰከንድ የሚፈጥን ሲሆን በ6.4 ሰከንድ ውስጥ ፍጥነቱ 100Km/h ይገባል።የተገጠመለት 22 kilowatt hour ባትሪ ፓክ ተጨማሪ 100km በኤሌክትሪክ ሃይል እንዲጓዝ ያስችለዋል።

ስለ መሸጫ ዋጋው እስካሁም ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም በመኸር ወር ለገበያ ይቀርባል።

#Renault #Rafale E-Tech 4×4 300hp #PHEV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volkswagen የGolfን አዲስ ፕለጊን ሃይብሪድ ቨርዥን በአውሮፓ ይፋ አረገ።


አንጋፋው የመኪና አምራች Volkswagen: Golf የተባለው መኪናውን አዲስ የፕለጊን ሃይብሪድ ቨርዥን የሰራለት ሲሆን በሁለት አማራጭ ማለትም ስታንዳርድ እና የስፖርት ቨርዥን ነው ያቀረበው።

ሁለቱም ቨርዥኖች ቱርቦ ቻርጅድ የሆነ 1.5 L ኢንጂን ከኤሌክትሪክ ሞተር ጋር አጣምረው የያዙ ሲሆኑ  front wheel drive የሆኑ መኪኖች ናቸው። ነገር ግን ስታንዳርዱ eHaybrid 200 የፈረስ ጉልበትን ሲያመነጭ የስፖርት ቨርዥኑ Golf GTE እስከ 270 የፈረስ ጉልበት ያመነጫል።

19.7 kilowatt hour ባትሪ ፓክ የተገጠመለት ሲሆን ከቀደም ብሎ ከወጣው ቨርዥን አንፃር በእጥፍ የጨመረ እና እስከ 143 km በኤሌክትሪክ ሃይል እንዲጓዝ ያስችለዋል።

አሁን በአውሮፓ ሁለቱንም ሞዴሎች Order ማረግ የተጀመረ ሲሆን eHybrid 44,400 ዩሮ የመነሻ ዋጋ ሲኖረው GTE ደግሞ እዚህ ላይ ተጨማሪ 2,500 ዩሮ ያለው የመነሻ ዋጋ ነው ያለው።

#VW #Golf #eHybrid #GTE
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nio የAutonomous ባትሪ swapping ቴክኖሎጂ ይዞ ብቅ አለ።


የቻይናው የመኪና አምራች Nio የመንገድ ጉዞን የሚያዘምን ቴክኖሎጂ ይዞ የመጣ ሲሆን እንደ Gasgoo ዘገባ ከሆነ አዲሱ ቴክኖሎጂ Autonomous የባትሪ swapping ሰርቪስ ነው።

ይህ ማለትም የSelf driving(መኪናው እራሱን በራሱ ማሽከርከር) የሚያስችለው ቴክኖሎጂ የተካተተባቸው መኪኖቹ Highway ላይ እራሳቸውን በራሳቸው ከማሽከርከር አልፈው ከፈጣን መንገዱ ወተው እራሳቸውን ወደ ባትሪ swapping ስቴሽን በማሽከርከር፤ የswapping ስቴሽን ውስጥ ገብተው ቻርጅ ያለቀውን ባትሪያቸው ቻርጅ በተደረገ ባትሪ ቀይረው እራሳቻውን እያሽከረከሩ ወደ ፈጣኑ መንገድ(Highway) መመለስ ያስችላቸዋል።

Nio የቻይና Highwayዎች መስመር ተከትሎ ወደ 243 የሚሆኑ ከዚ ቴክኖሎጂ ጋር ተስማሚ የሆኑ የባትሪ swapping ስቴሽኖች እንዳሉት ተናግሮዋል።

#Nio #Autonomous_Battery_swapping
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Baidu በ28,000 ዶላር የኤሌክትሪክ Robotaxi ሰራ።



ሹፌር አልባ የሆኑ/Robotaxi አገልግሎት መስጠጥ የሚችሉ መኪናዎች ተግባራዊ መሆን ብዙ ጥርጣሬ ያለበት ነገር ቢሆንም ግዙፉ የቻይናው የቴክኖሎጂ ካምፓኒ 6ኛ ትውልድ የRobotaxi መኪናውን ይፋ አርጎዋል።

መኪናው RT6 የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን Level 4 Autonomous ( እራሱን በራሱ ማሽከርከር) የሚያስችለው ሶፍትዌር ያለው ነው። RT6 አምስት የLidar ካሜራዎች እና ወደ 40 የሚሆኑ Sensorዎችም ተገጥመውለታል።
ይሄን ሁሉ ቴክኖሎጂ አቅፎ የያዘ ቢሆንም 28,000 ዶላር ብቻ ነው የፈጀው።ይህም ቀደም ብሎ ከወጣው ከ5ኛው ትውልድ Robotaxi ጋር ሲነፃፀር በ50% ያነሰ ዋጋ ነው።

መኪናው በJiangling Motors የተሰራ የሆነ ሲሆን 110 kilowatt የሆነ የBYDን ኤሌክትሪክ ሞተር እና Swapp መደረግ የሚችል LFP ባትሪ ነው የተገጠመለት።ነገር ግን የባትሪ ፓኩ ሳይዝ ግን አልተገለፀም። ፍጥነቱም በሰአት እስከ 135 km ይርሳል።

RT6 Robotaxiዎች በቻይናዋ Wuhan ከተማ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን በያዝነው አመት መጨረሻ 1,000 Robotaxiዎችን አምርቶ ስራ ላይ ለማዋል አቅዶዋል።

#Baidu #RT6 #Robotaxi
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የDodge ሃላፊ የነበረው Kuniskis ጡረታ ወጣ።


በstellantis ካምፓኒ ውስጥ ያልተጠበቀ የአስተዳደራዊ ለውጥ ተፈጥሮዋል።  በStellantis ስር ያሉትን Dodge እና Ram ብራንዶች የበላይ ሃላፊ የነበው Tim Kuniskis ከ32 አመት የአገልግሎት ዘመን ቡሃላ ጡረታ ወጣ።

የሱንም ቦታ ሁለት ሰዎች የሚሸፍኑት ። 'Christine Feuell ' ከChrysler ብራንድ በተጨማሪ Ramን የምታስተዳድር ሲሆን የDodge የሽይጭ ሃላፊ የነበረው Matt McAlear የብራንዱ CEO ሆኖዋል።


ይሄ የአስተዳደር ለውጥም ከ June 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

#Tim_Kuniskis #Stellantis #Dodge #Ram
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ ሞዴል 2 ከ20 ወራት ቡሃላ ይፋ ይሆናል።


ቴስላ የምር ሞዴል 2 ላይ እየሰራ ነው? አዎን።
በሁለት ቨርዥን እየሰራው ያለ ሲሆን አንደኛው ለአሜሪካ ገበያ የሚውል እና ከሱ ትንሽ ለየት ያለውን ቨርዥን ደሞ ለአውሮፓ ገበያ የሚያውለው ይሆናል።


Autoforcast Solutions እንደዘገበው ቴስላ ሞዴል 2ን Austin እና Berlin በሚገኙ ግዙፍ ማምረቻዎች ውስጥ ማረት የሚጀምር ሲሆን ለአሜሪካ ገበያ የሚውለው 2x ሲል ሰይሞታል። ይህም Autoforcast እንዳብራራው ትሽን ጠንከር ያለ የOff-Road ቨርዥን ነው።

በጀርመን Berlin የሚመረተው የሞዴል 2 ቨርዥን Compact የሆነ ሲሆን በዋጋውም ርካሽ የሚባል ነው።
በJuly 2027 ላይም ወደ ምርት ይገባል።

የአሜሪካው ቨርዥን 2x Austin በሚገኘው ማምረቻ January 2026 ላይ መመረት የሚጀምር ሲሆን በምርት ላይ የሚቆየው ግን እስከ December 2030 ነው። ከዛም በJanuary 2031 ቀጣዩ የ2x ትውልድ ወደ ምርት ይገባል።

#Tesla #Model-2
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota: Tundra እና Sequoia መኪኖቹብ በፕለጊን ሃይብሪድ አማራጭ ለማቅረብ እያቀደ ይሁን?



Toyota በአሜሪካ Texas ግዛት ውስጥ የሚገኘውን ግዙፍ ማምረቻውን ለማሻሻል 530 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ኢንቨስ ለማረግ አቅዶዋል።ማምረቻውም Tundra እና Sequoia መኪኖቹን የሚያመርትበት ነው።

Automotive News እንደዘገበው Toyota ማስፋፊያውን ለማረግ Tax እንዲቀነስለት የጠየቀ ሲሆን ስለማስፋፊያው ግን ምንም የተናገረው ነገር የለም።

በዚህ ጉዳይ ሁለት መላምቶች የተቀመጡ ሲሆን
1ኛ Toyota የምምረቻውን የምርት መጠን ከፍ ለማረግ አቅዶዋል።
ወይ ደግሞ የማምረጫ መሳሪያዎችን ቀያይሮ Tundra እና Sequoia መኪኖቹ በፕለጊን ሃይብሪድ የሃይል አማራጭ ሊያመርታቸው ነው።

General Motors ፒክ አፕ መኪኖቹን በፕለጊን ሃይብሪድ አማራጭ 2027 ላይ እንደሚያቀርባቸው የተናገረ ሲሆን ያጊዜም Toyota ማምረጫው ላይ ማስፋፊያውን አድርጎ የሚጨርስበት ጊዜ ነው።

#Toyota #Factory_Expansion
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አዲሱ የFord Pro የኤሌክትሪክ Van።


በአውሮፓ የሚገኙ በFleets(የተለያዩ እቃ እና አገልግሎቶችን ቤት ለቤት በማድረስ ስራ ላይ ለተሰማሩ ካምፓኒዎች Van መኪኖቻቸውን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ሃይል አማራጭ ወደሚሰሩ መኪኖች የሚለውጡበትን አማራች አገኙ። Ford Pro: summer ላይ E-Transit Coustom ሲል የሰየመውን የንግድ Van ለሽያጭ ያቀርበዋል።

መኪናው ባለው 64 kilowatt hour ባትሪ ፓክ እስከ 337 km የሚደርስ የdriving ሬንጅ ሲኖረው በሁለት የ ሞተር አማራጭ ቀርቦዋል። አንደኛው ባለ 100 Kilowatt ሲሆን 134 የፈረስ ጉልበት ያመነጫል። ሁለተኛው ደግሞ ባለ 160 kilowatt ሲሆን 214 የፈረስ ጉልበት ያመነጫል።

በተጨማር MS-RT የተባለ የስፖርት ቨርዥንም ያለው ሲሆን በ281 የፈረስ ጉልበት ማመንጨት በሚችል በ210 kilowatt የኤሌክትሪክ ሞተር ነው የቀረበው።

Vanኑ በሁለት የቁመት አማራጭ እና በአራት የቦዲ ስታይል የቀረበ ሲሆን ከ1,000 kg በላይ የሚሆን ጭነትን መሸከም እና እስከ 2,300 km የሚሆን ክብደት ያለው ጭነትን መጎተት ይችላል።

E-Transit Custom አሁን ላይ በሃገረ ቱርክ እየተመረተ ያለ ሲሆን በተመረጡ ገበያዎች ላይ ብቻ ነው የሚውለው። ነገር Ford በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እነዛን የተመረጡ ገበያዎች ይፋ ያላረገ ቢሆንም ቀጣይ አመት ላይ በመላው አውሮፓ ላይ ይዳረሳል።

#Ford #E-Transit Custom
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቻይና ወደ ሃገሯ የሚገቡ መኪኖች ላይ ያወጣቸው የቀረጥ ታሪፍ የአውሮፓ የመኪና አምራቾችን ሊጎዳ ይችላል።


የቻይና መንግስት ወደ ሃገሯ ውስጥ የሚገቡ 2.5 L ሲሊደር ኢንጅን እና ከዛ በላይ ያላቸው የቤንዚል መኪኖች ላይ 25% የቀረጥ ታሪፍ ጥላለች። አንዳንድ የዘርፉ ጠበብቶች እንደሚሉት ከሆነ ይሄ የታሪፍ ጭማሪ የቻይና ኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ 100% የቀረጥ ታሪፍ ለጣለው የባይደን አስተዳደር አፀፋዊ ምላሽ ነው።

ነገር ግን ይሄ ውሳኔ የቻይና መኪኖች ላይ የ30% የቀረጥ ታሪፍ ለመጣል እያሰበ ላላው አውሮፓ ህብረት ስጋት ነው። ቻይናም የአውሮፓ ህብረት ሊያፀድቀው ያለውን የቀረጥ ታሪፍ ደግሞ እንዲያስብበት አስባ ያረገችው ይመስላል።

የአውሮፓ የመኪና አምራቾች በተለይ የጀርመን የመኪና አምራቾች በዚ የቀረጥ ታሪፍ ጦርነት መሃል ገብተዋል። ቻይና ትልቋ ገበያቸው ስትሆን በቀጥታ ከጀርመን እና በአሜሪካ ከሚገኙ ማምረቻዊቻቸው ወደ ቻይና ኤክስፖርት ያረጋሉ።

ለምሳሌ Mercedes እና BMW በአሜሪካ Alabama እና በደቡብ Carolina ግዛት ያመረቷቸው SUV መኪኖቻቸውን ወደ ቻይና ይልካሉ።

ቻይና አሁን ላይ የትኛውም በአሜሪካ የተመረተ መኪና ላይ 25% የቀረጥ ታሪፍ ጥላለች። ሌላ 25% የቀረጥ ታሪፍ የአውሮፓ መኪኖች ላይ የምትል ከሆነ ቻይና ላይ ያላቻውን ሽያች በከባዱ ይጎዳባቸዋል።

#Tax #China #USA #EU
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BYD ለንደን ላይ Double-Decker (ተደራራቢ) ባስ ይፋ አረገ።


የለንደን ከተማ ፈርጥ የሆኑትን Black Cabs የተባሉትን ታክሲ የሚያመርተው የለንደኑ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ከ2012 ጀምሮ በቻይናው የመኪና አምራች Geely ባለቤትነት ስር ነው ያለው።
አሁን ላይ ደሞ ሌላኛው የከተማዋ መንገዶች ፈርጥ የሆነው ተሽከርካሪ በቻይና ስር ሊሆን ነው።

BYD በነዳጅ የሚሰሩትን የለንደን ተደራራቢ ባሶች እራሱ በሚያመርታቸው ተደራራቢ የኤሌክትሪክ ባሶች ሊቀይራቸው ሲሆን BD11 የተሰኘውን ተደራራቢ ባሱን በለንደን በሚገኘው የባስ ሙዚየም ላይ ይፋ አርጎታል።
ባሱ ከ532 kilowatt hour ባትሪ ፓኩ ሃይልን የሚያገኝ ሲሆን በአንድ ቻርጅ እስከ 640 km መጓዝ ይችላል።


የለንደንን ተደራራቢ ባሶች የሚያስተዳድረው ካምፓኒ 100 እነዚህን BD11 የተባሉ ባሶች ከBYD አዞዋል። የአንዱ ባስ ዋጋም 400,000  የእንግሊዝ ፖውንድ ሲሆን በሃገረ እንግሊዝ ከሚገኙ ተፎካካሪዎቹ ካቀረቡት ዋጋ በ100,000 ፓውንድ ቅናሽ አለው።

የBYD ባሶች ቻይና ውስጥ የሚመረቱ ቢሆንም BYD አንድ ሶስተኛው የሚሆነው የባሶቹ ክፍሎች ከአውሮፓ እንደሚመጣ ተናግሮዋል።

#BYD #BD11#Double_Decker_Bus
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Ad

ምንም ምቾት ሊሰማኝ አልቻለም

ዘመናዊ መኪና ላይ Yango እስክጀምር ድረስ
እርስዎም የትም ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው ከ 10 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተመዝግበው እንደኔ በመስራት ገቢዎትን በ ጉርሻ ብቻ እስከ 9200 ብር በሳምንት ተጨማሪ ገንዘብ ያግኙ።

አሽከርካሪዎች አፑን ለመጫን ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
bit.ly/4bEE8m8

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ገፃቸው
https://www.tg-me.com/YangoETH

እንዲሁም የፌስቡክ ገፃቸው
https://www.facebook.com/groups/1171500204006823
#Yango_pro #Earnings #Driving
ሼር
አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ!

ለዚህ ቴሌግራም ቻናላችን የአውቶሞቲቭ አማርኛ ዜናዎችን ከተለያዩ የዜና አውታሮች ላይ እየሰበሰበ የሚሰራ አውቶሞቲቭ ላይ እውቀት ያለው ሰው እንፈልጋለን ::

ብዛት 1

የስራ ቦታ ከቤትዎ ኦንላየን የኮንትራት ስራ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እንደሁኔታው በስምምነት ሊቀጥል የሚችል

ክፍያ - በስምምነት

መስራት የምትፈልጉ ስማችሁን አድራሻችሁን ችሎታችሁን እና ሳምፕል ሰጥተናችሁ መስራት የምትችሉትን ማየት እንፈልጋለን :: ፍላጎቱ ያላችሁ በዚህ የቴሌግራም አድራሻ መልእክት ይላኩልን
@yonathandesta

እናመሰግናለን
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Lucid Motors ተጨማሪ 400 ሰራተኞቹን አሰናበተ።


ከሁለት አመታት በፊት እየጎመሩ የነበሩ አዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪና አምራቾች አሁን ላይ ምን እየገጠማቸው እንዳለ እራሱ ማወቅ ተስኗቸዋል።

በቅርብ አመት የተመሰረተው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች Lucid Motors ተጨማሪ 400 ሰራተኞችን ከስራ ሊያሰናብት ሲሆን ይህም ቁጥር 6% የሚሆነው የካምፓኒው የሰራተኛ ሃይል ነው።

ሽያጩ ካምፓኒ ይሆናል ብሎ ከጠበቀው እጅጉን ያነሰ የሆነበት ሲሆን ሬፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በመጀመሪያው የእሩብ አመት አጋማሽ ከተጠበቀው በላይ ትልቅ ኪሳራ ገጥሞታል።

#Lucid #Ev
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volvo Truck የናፍጣ መኪኖችን በሃይድሮጅን እንዲሰሩ ለማድረግ እየሞከረ ነው።


ብዙ የከባድ መኪና አምራቾች የናፍጣ መኪኖቻቸው በሃይድሮጅ እንዲሰሩ ለማረግ እየሞከሩ ነው። ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ የካርበን ልቀቱት ዜሮ ለማስገባት ቀላሉ፣ ፈጣኑ፣ እና ከዋጋ አንፃር እርካሹ መንገድ ነው።

ይሄ ሃሳብ Green Hydrogenን የሚጠቀሙ ከሆነ እውን ሊሆን ይችላል። የፒስተን ኢንጅኖች ከነዳጅ ዘይት በተሻለ በሃይድሮጅ Efficiently የሚሰሩ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ የሃይድሮጅን ሲስተም እንደሚጠቀም ኢንጅን ግን Efficient አይደሉም።

ይሁን እንጂ በእመቃ የሚሰሩ ኢንጅኖችን ወደ ሃይድሮ ወደሚሰሩ መቀየሩ ቀላል ነው ይላሉ። Toyota፣ Bosch እና ሌሎች የመኪና አምራቾች እዚህ ላይ እየሰሩ ያለ ሲሆን አሁን ላይ Volvo Truck ተቀላቅሏቸዋል።

Volvo እንድተናገረው የWestport Fuel Systemን ዳይሬክት ኢንጄክተሮችን የሚጠቀም ሲሆን  ሃይድሮጅን ወደ ሲሊንደሩ ከመለቀቁ በፊት የእመቃ መቀጣጠል እንዲጀመር ትንሽ የማቀጣጠያ ነዳጅ በከፍተኛ Pressure ወደ ሲሊንደሩ ይለቀቃል።

የመኪና አምራቹ ቀጣይ አመት ላይ የከባድ ጭነት መኪኖቹን በመንገድ መሞከር እንደሚጀርም ያሳወቀ ሲሆን በ2030 ላይ ወደ ምርት እንደሚገባ ተስፋ ያረጋል።

#Volvo #Hydrogen
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/06/29 23:14:43
Back to Top
HTML Embed Code: