Telegram Web Link
#ዜና

Ranger Rover Sport SV በካምፓኒው ታሪክ ትልቅ የተባለውን ፍሬን ተገጠመለት።


አዲሱ Ranger Rover Sport SV ካምፓኒው ከዚህ በፊት ተጠቅሞት ከሚያውቃቸው በላይ ትልቅ የሆነ ፍሬን ተገጥሞለታል። ግዙፍ ባለ 8 Piston የፊት Caliperዎች እና ከ400mm ወይም 17inch በላይ የሆነ የሴራሚክ ዲስክ አለው።

ይህ ማለትም ከአንዳንድ የመኪኖች ጎማ እራሱ ይሚበልጥ ሲሆን አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ላይ ትልቅ የሚባል ፍሬን ከሆነ ከLamborghini Urus መኪና ፍሬን ጋር ተመሳሳይነት አለው።

ፍሬኑ ከስታንዳርድ በቅይጥ ብረት ከሚዘጋጁት ፍሬኖች በ34 km ያነሰ ክብደት ያለው ሲሆን ቶሎ የሚያልቅ አይነትም አይደለም። Range Rover እንደተናገረው የመኪናው 4 ሞዴሎች 1,600 km ኖርማል መንገድ ላይ፣ 990 km ትራክ ላይ ተነድተው የፍሬን ጫማቸው ከአገልግሎት እድሚያቸው ላይ ገና 30% ያህል ይቀራቸዋል።

የ180,000 ዶላር መነሻ ዋጋ ያለውን መኪና ለሚገዛ ሰው የፍሬን ዋጋ ያን ያህል ቁብ ሚሰጠው ነገር ባይሆን ለመቀየር በሺ የሚቆጠሩ ዶላሮችን ያሶጡታል። ይሄ የፍሬን ሲስተምም የመኪናውን የመሸጫ ዋጋ በ15,000 ዶላር ከፍ እንደሚያረው ተገምቶዋል።

#Ranger_Rover_Sport_SV #ceramic_Breaking
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nissan አዲስ Qashqai SUV መኪና አውሮፓ ላይ ይፋ አረገ።


Nissan የተሻሻለውን የQashqai SUV መኪና ቨርዥኑን አውሮፓ ላይ ይፋ አድርጓል። ተሽከርካሪው  አዲስ የfront-end ዲዛይን ሲኖረው እንዲሁየኋላው ስታይል ላይም  ማሻሻያ ተደርጎበታል። በአውሮፓ ውስጥ የNissan የመጀመሪያው የGoogle ሲስተምን ያካተተ ተሽከርካሪ ነው። ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንደ Around View Monitor፣ ለፓርኪንግ አገልግሎት የሚሆን bird's eye view (የወፍ በረር እይታ) የተደረጉበት ሲሆን ለተሻሻለው የDriving Assistance ፊውቸር ተስማሚ ነው።

Qashqai ሁለት የኃይል አማራጮችን ይዞ ቀርቦዋል። የመጀመሪያው Mild Hybrid ነው ሲሆን Nissan እስካሁን ዝርዝር መረጃዎችን አልሰጥበትም።

E-Power ብሎ የሰየመው ሁለተኛው የኃይል አማራጩ ግን ከሌሎች የE-Power ተሽከርካሪዎች በተለየ መልኩ ይሰራል። ለ140 kilowatt የኤሌክትሪክ ሞተሩ የኤሌክትሪክ ሃይልን ለማመንጨት  ባለ 3 ሲሊንደር ቱርቦ engine ይጠቀማል።
ትራንስሚሽን (gear box) የሌለው ሲሆን ሞተሩ ቀጥታ ከጎማው ጋር ነው የተያያዘው።

አዲሱ Qashqai እንግሊዝ በሚገኘው የNissan ማምረቻ ውስጥ መመረት የጀመረ ሲሆን በተጨማሪም  በካናዳ ገበያ ላይ መሸጥ የሚጀምር ይሆናል።

#Nissan #Qashqai
@OnlyAboutCarsEthiopiw
#ዜና

የTesla መኪኖች ከሁሉም የመኪና አይነቶች ዝቅተኛ የሆነ የጥገና ወጪ ነው ያላቸው።


የቴስላ መኪኖች በአሜሪካ ላይ ከየትኛውም የመኪና ብራንድ ያነሰ የጥገና ወጪ ነው ያላቸው። በቅርቡ Consumer Reports እንዳረገው የዳሰሳ ጥናት የራሱን አባላት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ መኪናቸውን ለማስጠገን ከኪሳቸው ያወጡትን ገንዘብ በመጠየቅ እና የየተለያዩ የመኪና ብራንዶች በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ለጥገና የሚያወጡት ወጪ ምን ያህል ሊሆን እንደሚች ሲያነፃፅር  በ4,000 የአሜሪካ ዶላር የጥገና ወጪ Teslaን ዝቅተኛው ሆኖ አግኝቶታል።
በ4,900 ዶላር የጥገና ወጪ Buick እና Toyotal ዝርዝሩ ላይ ቴስላን ተከትለውም ተቀምጠዋል።

ከዚ በጠቃራኒው ከፍተኛ የጥገና ወጪ የሚያወጡት የRange Rover መኪና ባለቤቶች ሲሆኑ በ10 አመት ጊዜ ውስጥ 19,250 የአሜሪካ ዶላር ይወጣሉ። ይሄም ከPorsche መኪና የጥገና ወጪ በ5,000 ዶላር ብልጫ ያለው ሲሆን Porsche የደረጃ ሰንጠረዡ ላይ 2ኛ ውዱ የጥገና ወጪ የሚጠይቅ የመኪና ብራንድ ሆኖ ተቀምጦዋል።

#Tesla #RangeRover #Repair_Cost
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Smart አስካሁን ካመረተው ትልቅ የሚባለው መኪና ይፋ አረገ።


በፓረንት ካምፓኒው Geely ስር የሚተዳደረው እና ትናንሽ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው Smart ተለቅ ባሉ የመኪና ሞዴሎች ለመምጣት ያሰበ ይመስላል። ያው ከብራንዱ መኪኖች አንፃር ተለቅ ያለ።

smart አዲስ #5 የተባለ የmid-size SUV መኪና  concept ይዞ የቀረበ ሲሆን በፓረት ካምፓኒው Geely SEA በተባለው ፕላትፎርም ነው የተሰራው። ፕላት ፎርሙ Smartን ጨምሮ እንደ Geely ፣ Volvo እና zeekr ባሉ የፓረንት ካምፓኒው የመኪና ብራንዶች በተለያየ ሳይዝ ላሉ መኪኖቻ የሚጠቀሙት ነው።

Smart አንዳለው መኪናው በ800 ቮልት አርክቴክቸር የተሰራ ሲሆን ትልቅ የሆነ ባለ 100 kilowatt hour ባትሪ ፓክ ነው የተገጠመለት። ይሄም በፍጥንት ቻርጅ መደረግን የሚያስችለው ሲሆን በአንድ ቻርጅ ከ550 km በላይ ይጓዛል።

ለገበያ መች እንደሚቀርብ ይፋ የሆነ ባይሆንም የ#5 የምርት ቨርዝኑን በያዝነው አመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ይፋ የሚሆን ይሆናል።

#Smart #Geely
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Kia የመጀመሪያውን ፒክ አፕ መኪና ይፋ አደረገ።


Kia የመጀመሪያውን ፒክ አፕ መኪና ቀጣይ አመት ላይ ለገበያ ሊያቀርብ ሲሆን አዲሱ መኪናው Tasman ብሎ ሰይሞታል። የተለመደው የፒክ አፕ መኪና ገፅታ ሲኖረው እንደ Ford Ranger እና Toyota Tacoma የቻንሲ ፍሬም ላይ የተቀመጠ ቦዲ ይሁን ወይ እንደ Honda Ridgeline እና Hyundai Santa Cruz ወጥ የሆነ አንድ ቦዲ (uni-body) ይሁን ያለው መለየት ቢከብድም ከተለመደው የፒክ አፕ ካቢን እና በእቃ መጫኛው መካከል ካለው መለያ የተለየ መለያ ነው ያለው።

kia እንዳለው መኪናው ለስራ አገልግሎትም ሆነ ለግል መገልገያነት ለመጠቀም የተመቸ ነው። Tasman ቀጣይ አመት ላይ ሙሉ በሙሉ ይፋ የሚሆን ሲሆን በኮሪያ፣ በአውስትራሊያ፣ በአፍሪካ ፣ እና በመካከለኛው ምስራቅ ገበያ ላይ የሚቀርብ ይሆናል።

#Kia #Tasman
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BYD ፒክአፕ መኪናቸውን ነገ ለእይታ ያቀርባሉ


BYD Shark ብሎ የሰየመውን ፒክአፕ ትራክ ለእይታ ከመቅረቡ በፊት ምን ሊመስል እንደሚችል አሳይቷል :: ይህ ብቻ ሳይሆን ያስተዋወቁት በቻይንኛ ሳይሆን በእንግሊዘኛ ቋንቋ በመሆኑ ለቻይና ገበያ ሳይሆን ለሌሎች ገበያ ሊያቀርብ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ::

በግራም በቀኝም የመሪ አማራጭ እንዳለውም የተነሱት ፎቶ ላይ ያሳያል :: ይህም የቀኝ መሪው ለአውስትራሊያ እና ለደቡብ አሜሪካ ያቀርቡታል :: ሞተሩን እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን ነገ ለእይታ ሲቀርብ በዝርዝር የምናቀርብ ይሆናል ::

#BYD
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ Model 3 መኪናውን በፐርፎርማንስ ቨርዥን አቀረበው።


ቴስላ Model 3 መኪናውን በፐርፎርማንስ ቨርዥን ያቀረበው ሲሆን  2 የኤሌክትሪክ ሞተሮች ያሉት All Wheel Drive መኪና ሲሆን የሁለቱ ሞተሮች አንድ ላይ በመሆን 510 የፈረስ ጉልበት ያመነጫሉ። ፍጥነቱን በሰአት ከ0 እስከ 100 km ለመድረስ 2.9 ሰከንድ ብቻ ይወስድበታል።

ከዚህ ሁሉ በላይ የፐርፎርማንስ springዎች, damperዎች, bushingዎች, stabilizer bar, የውድድር መኪና ፍሬኖች እና መቀመጫዎች የተገጠሙለት ሲሆን አሽከርካሪዎች ማእከላዊ እስክሪኑንን በመጠቀም ብቻ የመሪ ባላንሱን ፣stability controlሉን እና regenerative brakingጉን በፈለጉት መንገድ customize ማረግ ይችላሉ።

የመነሻ ዋጋውም ከ53,000 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ ነው።

#Tesla #Model_3_Performance
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Mercedes ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ የሆነ የG- Class ሞዴሉን ይፋ አረገ።


የጀርመኑ የመኪና አምራች ካምፓኒ Mercedes የአዲሱ G-Class ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ የሆነ ቨርዥኑን ይፋ ያረገ ሲሆን መኪናው ለየብቻቸው በሚሰሩ ጎማው አጠገብ በተገጠሙ 4 የኤሌክትሪክ ሞተሮች ይነዳል።

የ4ቱ ሞተሮች ድምር ለመኪናው 432 kilowatt ወይም 580 የፈረስ ጉልበትን ሲያመነጩለት ፍጥነቱ በሰአት ከ0 እስከ 100km ለመድረስ 4.7 ሰከንድ ይወስድበታል። በተጨማሪ Mercedes G- Turn ብሎ የሰየመውን መኪናው ባለበት ቦታ እንደቆመ 360° እንዲሽከረከር ያስችለዋል።

የተገጠመልት ባትሪ ፓክ 116 kilowatt hour ሲሆን መኪናውን በአንድ ቻርጅ እስከ 473 km እንዲጓዝ ያስችለዋል። መኪናው ከሃይል አጠቃቀም አንፃር  በጣም Efficient የሚባል አይደለም 100km ለመጓዝ ከ28-30 kilowatt hour የባትሪውን ሃይል ይወስዳል። አሁን ላይ አሪፍ የሚባሉ የኤሌክትሪክ መኪኖች የዚህን እጥፍ ሃይል ይቆጥባሉ።

ለG-Class መኪኖች ሁሌም Off-Road ( ከአስፋልት መንገድ ውጪ የሆኑ አስቸጋሪ መንገዶች) ላይ የመጓዝ ችሎታቸው የትሬድ ማርካቸው እንደመሆን መጠን አዲሱ G-class የኤሌክትሪክ ቨርዥን ላይ የለየጎማዎቹ በየግል የሰስፔንሽን ሲስተም ከ2 wishboneዎች ጋር እና ከኋላ ላይ በቅርብ የተመረት ጠንካራ Axle ተገጥሞለታል።

አሁን ላይ መች ለገበይ እንደሚቀርቡ ይፋ የሆነ መረጃ የለም።

#Mercedes #GClass #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

LG Chem እና Factorial በSolid State የባትሪክ ምርት ላይ አጋርነትን ፈጠሩ።


Solid State ባትሪዎች አገልግሎች እና ምርት እያደገ ነው። የታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ አምራች ካምፓኒ LG እህት ኩባኒያ የሆነው LG Chemም የረዥም አመት የSolid State ባትሪ የማምረት እውቀቱን በቅርቡ ወደዚህ ስራ ለተቀላቀለው Factorial ለተባለ የባትሪ አምራች እያካፈለው ነው።

ሁለቱ ካምፓኒዎች የ Solid State ባትሪ ምርት ሂደትን ለማፋጠን በጋራ ለመስራት ስምምነት መፍጠራቸውን ይፋ አድርገዋል።

LG Chem ለአብዛኛው የኤሌክትሪክ መኪና አምራቾች ባትሪን ማቅረብ ከጀመረ የቆየ ሲሆን Factorial ደግሞ Mercedes ፣ stellantis እና Hyundaiን በፓርትነርነት ይዞ ባትሪ ያቀርብላቸዋል።

#LG_Chem  #Factorial #Solid_State
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BYD በቤጂንጉ  Auto Show ላይ አዲሱን Hot Hatch መኪናውን ይፋ አረገ።

አንዳንድ አውሮፓዊያን የቻይና መኪኖች የአውሮፓ ገበያን ሊያጥለቀልቁት ነው ብለው ስጋት ገብቶአቸዋል።BYD ደግሞ አውሮፓላይ በጣም ተፈላጊላጊነት ያለው የመኪና ሴግመንት ለመቀጣጠር እየሰራ ነው። ሴግመቱ Hot Hatch ሲሆን BYD Ocean-M ብሎ የሰየመውን አዲሱን Hot Hatch በቤጂንጉ Auto Show ላይ ይፋ አርጎዋል።

Ocean-M ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ የሆነ Rear Wheel Drive መኪና ሲሆን ባለ 4 በር ነው። በዚ አመት ሶስተኛው እሩብ አጋማሽ በቻይና ገበያ ላይ ይቀርባል።

#BYD #OceanM
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቶዮታ የኤሌክትሪ መኪና Concept


ቶዮታ "BZ" የተባለውን የኤሌክትሪክ መኪና የስየማ መንገዱ ሊተወው እያሰበ ይመስላል። ነገር ግን እስካሁን ጨርሶ ተስፋ አልቆረጠበትም።

ባለፈው አመት በቤጂንጉ የAuto Show ላይ Conceptአቸውን ቀርቧቸው የነበረውን የBZ Sport Crossover እና የBZ FlexSpace መኪኖች የproduction(የምርት) ቨርዥናቸውን ይፋ አረገ። ነገር ግን አሁን ላይ ስማቸውን ወደ BZ3c እና BZ3X ወደ ሚል ስም ቀይሮታል።

ቶዮታ እንደተናገረው ሁለቱም በመኪኖች ዘመናዊ የDriving Assistance ፊውቸር ተካቶባቸው ከአመት ቡሃላ ለገበያ ይቀርባሉ።
BZ3C ከቻይና የመኪና አምራች ከሆኑት BYD እና FAW ጋር አጋርነትን በመፍጠር  የተሰራ ሲሆን ወጣት ለተባለው የማህበረሰብ ክፍልን ኢላማ በማረግ የተሰራ ነው።

BZ3X የተባለው መኪናው ደግሞ ከGAC Motors ጋር አጋርነትን በመፍጠር  የተሰራ ሲሆን ቤተሰብን ያማከለ የቤተሰብ መኪና የምንለው የመኪና አይነት ነው።

ለአሁኑ ስለመኪኖቹ ማወቅ የቻልነው መረጃ ይሄንን ነው።

#Toyota #BZ3C #BZ3X
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volkswagen በቤጂንጉ Auto Show የአዲሱን የID Conceptቱን ይፋ አረገ።


አዲሱን የID CODE ኮንሰፕት በመመልከት የVolkswagen የኤሌክትሪክ መኪናዎች አዲስ የቦዲ ስታይልን እየያዙ እንዳለ መናገር እንችላለን።

ከቀድሞዎቹ ሞዴሎች ካለው ልዩነት መካከል አንዱ የመብራቶቹ ናቸው። መብራቶቹ እንደ ቀድሞ ሁሉ ከመኪናው ፊት አና ኋላ ላይ ተለጥጠው ያሉ ሲሆን ነገር ግን ከበፊቶቹ በጣም ወፈር ያሉ ናቸው። ቦዲ panelሉ ወደ ሃላ በደንብ የተሳበ ሲመስል ከFastBack Rooflineኑ ጋር ተደማምሮ ID CODEን በጣም የSporty መኪና ገፅታን አላብሶታል።

Volkswagen እንዳለው መኪናው የወደፊቱ ትልቁ SUV መኪና ሲሆን ዲዛይኑ እስከ level 4 Autonomous Driving ማስጠቀም የሚችል ነው።
በተጨማሪ ካምፓኒው በመጪው 10 አመታት ውስጥ ቻይና ላይ 30 አዲስ የመኪና ሞዴሎችን እንደሚለቅ ተናግሮዋል።

ይህም የነዳጅ ፣ የሃይብሪድ፣ የፕለጊ ሃይብሪድ መኪኖችን እና ከአዲሱ የካምፓኒው ንኡስ ብራንድ ID.UX አምስት የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎችን ሰርቶ ለገበያ ያቀርባል።

የVolkswagen ኑዑስ ብራንድ የሆነ ID.UXም የመጀውመሪያ የመኪና ሞዴሉ የሆነውን ID UNYX ሰርቶዋል። መኪናው All Wheel Drive የሆነ ሲሆን Cupra Tavascan በቮልስ ዋገን ቨርዥን ተሰርቶ ነው ማለት ያስደፍራል።

#Volkswagen #ID
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Honda ሁለት አዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በቻይና ይፋ አረገ።

Honda በ2022 ላይ የጀመረውን "e:N "የተባለው የኤሌክትሪክ መኪና ላይን አፑን እያስፋፋ ነው።  ከGAC ጋር አጋርነትን በመፍጠር e:NP2 ሲል የሰየመውን መኪና የሰራ ሲሆን መኪናው የሚጠቀመው ፕላትፎርም በአንድ ቻርጅ እስከ 545 km እንዲጓዝ ያስችለዋል።

ሁለተኛው ቨርዥን e:NS2 የሚባል ሲሆን ከe:NP2 ጋር ትንሽ የስታይል ልዩነት ይኖረዋል። ሚመረተውም ከሌላኛው የHonda ፓርትነር Dongfeng ጋር በመሆን ሲሆን እነዚህ ሁለት የኤሌክትሪክ መኪናዎችን እና ሌላ ሁለት የe:N ላይን አፕ የሆኑ መኪናዎችን በሽያጭ ላይ ይገኛሉ።

Honda እስከ 2027 ባለው ጊዜ 10 የኤሌክትሪክ መኪኖችን ሰርቶ በቻይና ገበያ ላይ ለማቅረብ አቅዶዋል።

#Honda #eNP2 #eNS2
@OnlyaboutCarsEthiopia
#ዜና

Mazda ሁለት አዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቻይና ላይ ይፋ አረገ።


Mazda በቤጂንጉ የአውቶሞቲቭ ሾው ላይ ሁለት አዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ይፋ ያረገ ሲሆን አንደኛው EZ-6 ይባላል። መኪናውን ከቻይናው የመኪና አምራች Changan ጋር አጋርነትን በመፍጠር የሰራው ሲሆን በኤሌክትሪ እና በፕለጊን-ሃይብሪድ አማራች ቀርቦዋል። የኤሌክትሪኩ በአንድ ቻርጅ እስከ 600 km የሚጓዝ ሲሆን ፕለጊን-ሃይብሪዱ እስከ 1000 km ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለተኛው መኪና Arata Crossover ሲሆን Mazda ስለዚህ መኪና ብዙ መረጃ ይፋ አላረገም። ነገር ግን እንደ EZ-6 ሁሉ በኤሌክትሪክ እና በፕለጊን-ሃይብሪድ አማራጭ ሲኖረው በቀጣይ አመት ማገባደጃው ላይ መመረት ይጀምራል።

#Mazda #EZ-6 #Arata
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

ከ 500 ሺህ ብር ጀምሮ የሚሸጥ መኪና ለመግዛት አስበዋል?

እንግዲያውስ ሁሌመኪና ላይ ከ 500 ሺህ ብር ጀምሮ የሚሸጡ መኪኖችን እንዲሁም የተለያዩ መኪኖቻችሁን በሁሌመኪና በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ
በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ ቴሌብር ላይ ከላይ ባስቀመጥነው ስልክ ላይ በመክፈል መሸጥ እና ማከራየት ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

RAM አዲስ RHO የተባለ የፐርፎርማስ ትራክ/ ፒክ አፕ  መኪና ሰራ።


TRX የተባለው የRam Off-Road ፐርፎርማንስ መኪና ምርት ባለፈው አመት ላይ ያበቃ ሲሆን አሁን ላይ አዲስ RHO የተባለ Off-Road መኪና ይዞ ብቅ ብሎዋል።

Hellcat በቦዲ ተሸፍኖ መሆኑ ቀርቶ አዲሱ RHO የStellantisሱን Hurricane engine ፐርፎርማንስ ቨርዥን ነው ሚጠቀመው። ይህም 540 የፈረስ ጉልበት እንዲያመነጭ ያስችለዋል።
ሴታፑ የTRXን ፍጥነቱ በሰአት ከ0 እስከ 100km  በ4.6 ሰከንድ ውስጥ መግባት እንዲችል ካስቻለው የHellcat ኢንጅን በ68 kg ያንሳል። የRHO Accelerationም ከTRX Acceleration በሰከንድ 1/10 ብቻ ነው የሚያንሰው።


ይሄ ሁሉ ጉልበት በBorgWarner full-time active transfer ስር የሚያልፍ ሲሆን የDana 60 የኋል Axle ከኤሌክትሮኒክ Lock ዲፈረነሻል ጋር ተገጥሞለታል። የፊለፊቱ  ሰስፔንሽን እራሱን የቻለ ሲስተም ሲጠቀም በአልሙኒየም የተሰራ upper እና lower control arm ሲኖረው ከBlistin adaptive ሾክ አብዞርበር ጋር ተገጥሞለታል። ኋላ ላይ ተመሳሳይ ሰስፔንሽን ከ5 link coil ሲስተም ጋር ሆኖ ይገኛል።

ካምፓኒው RHO ላይ ትዛዝ መቀበል የጀመረ ሲሆን የመሸጫ ዋጋው የማድረሻውን ጨምሮ 72,000 የሜሪካን ዶላር ነው።

#Ram #RHO #OFF-ROAD
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota በቻይና የRoboTaxi / የሹፈር አልባ የታክሲ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው።


ከውጪ የመኪና አምራቾች ውስጥ ቴስላ ብቻ አይደለም ቻይና ውስጥ በRoboTaxi/ በሹፌር አልባ የታክሲ አገልግሎት ቢዝነስ ውስጥ በጣም ትልቅ ገቢ አንዳለ የታየው። ያለፈው አመት ላይ Toyota እና የቻይናው አጋሩ AGC የLevel 4 RoboTaxiዎችን ለመስራት በቅርብ አመታት ውስጥ ወደ ስራ ከገባው Autonomus vehicle/ የሹፌር አልባል ተሽከርካሪዎች ላይ ከሚሰራው Pony.ai ከተባለው ካምፓኒ ጋር ጥምረትን የፈጠሩት።

አሁን ላይ ስለ ጥምረቱ ተጨማሪ መረጃዎችን አጋርተዋል። ካምፓኒዎቹ በቤጂንጉ የአውቶ ሾው ላይ ያሳዩትን የPony.ai Self-driving ቴክኖሎጂ የተጫነባቸውን BZ4X መኪኖችን በቻይና ጎዳናዎች ላይ ለማሰማራት ያቀዱ ሲሆን ስራው በተገቢው መንገድ እንዲከናወን የመኪኖቹን ጥገና፣ ቻርጅ ማረግ፣ እና ፅዳት በካምፓኒዎቹ የሚሰራ ይሆናል።

#Toyota #RoboTaxi #AGC #Pony.ai
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Fisker ካምፓኒውን ለማትረፍ ሲል ቅንጡ መኖሪያ ቤቱን ሊሸጠው ነው።


Henrik Fisker ካምፓኒውን ለማትረፍ ተስፋ አስቆራጭ ፍልሚያ ላይ ነው። ኪሳራ ሊወድቅ ጫፍ ላይ የደረሰ ሲሆን ለካምፓኒውን ገንዘብ ለማሰባሰብ ሲል በLos Angeles የሚገኘውን ቅንጡ መኖሪያውን ሊሸጠው ነው።

1,096 m² ላይ ያረፈው መኖሪያ ቤት በ35 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የመሸጫ ዋጋ ለሽያጭ ቀርቦዋል። የቤቱ ዋጋ ከተገዛበት 13.2 ሚሊየን የጨመረ ከመሆኑ በላይ ዋጋው ከመኪና ካምፓኒው Fisker Motor ሙሉ የማርኬት ካፒታል ይበልጣል።

ቤቱን መግዛት ካልፈለጋቹ በወር 125,000 ዶላር ክፍያ መከራየት ትችላላቹ።
የመዋኛ ገንዳ ፣ 6 መኝታ ቤቶች ፣ 8 መፀዳጃ ቤቶች እና አይምሮአቹ ውስጥ ሊመጣ የሚችል ቅንጡ ነገሮች ሁሉ ተካተውበታል።

#Henrik_Fisker #Fisker_Motors
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አውሮፓ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የህዝብ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮች ያስፈልጓታል።


የኤሌክትሪክ መኪኖች በገፍ መመረት ከመጀመራቸው በፊት ብዙ የቻርጅ ስቴሽኖች እንደሚያስፈግ ሁሉም የሚያው ነገር ነው። እናም የአውሮፓው ACEA በትክክል ምንያህል ተጨማሪ ቻርጀሮች እንደሚያስፈልጉ ያውቃል።

European Automobile Manufacturs Association እንደተናገረው በአውሮፓ 2020 ላይ 8.8 ሚሊየን የህዝብ ቻርጀሮች ያስፈልጋሉ። የቻርጀር ገጠማ ሬቱ በአመት 1.2 ሚሊየን መድረስ አለበት። ይህ ማለትም ካሁኑ ሬት በ8እጥፍ የጨመረ መሆን ይኖርበታል።

Associationኑ እንደተናገረው ከ2017 እስከ 2023 ከነበረው የህዝብ የመኪና ቻርጀሮች ገጠማ በ3 እጥፍ የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ አድጎዋል።
ያለፈው አመት 150,000 ቻርጀሮች አውሮፓ ላይ የተገጠሙ ሲሆን እጠቃላይ ድምሩን ድምሩን 630,000 አድርሶታል። ነገር ግን ACEA አውሮፓ የካርበን ልቀት የመቀነስ እቅዷን የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግ ስቴሽኖች እስካልተስፋፉ ድረስ አታሳካም ብሎዋል።

#EV_Chargers #Europe #EACA
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Rvian የቻርጂንግ ስቴሽኖቹን ለሁሉም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ክፍት አረገ።


የኤሌክትሪክ adventure መኪኖችን አምራች የሆነው Rivian የቻርጂን ስቴሽኖቹን ለሁሉም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ክፍት አረገ። በዚ አመት መገባደጃ ላይ ረዣዥም የቻርጅ ገመድ ያላቸው እና በ400 - ወይም በ800 - ቮልት አርክቴክቸር የተሰሩ መኪኖችን ቻርጅ ማረግ የሚችሉ ቻርጀሮችን መግጠም ይጀምራል።

ቻርጀሮቹ መጀመሪያ ላይ CCS የሚባለው connector ሲኖራቸው ነገር ግን ትክክለኛውን Adaptor በመጠቀም ለቴስላ መኪኖች እንዲያገለግሉ ማረግ ይቻላል። 
Rivian እንዳለው ዘግየት ብሎ የሚወጣው አዲሱ ቻርጀር North American Charging Standard ( NACS ) ወይም SAE J3400 በመባል የሚታወቀውን የቴስላ connector ነው የሚኖረው።


Rivian አሁን ላይ በሰሜን አሜሪካ 400 DC ፋስት ቻርጀሮች ያሉት ሲሆን ይሄን ቁጥር ወደ 3,500 DC ፋስት ቻርጀሮች የማሳደግ እና ተጨማሪ 10,000 level 2 ቻርጀሮችን ለመግጠም አቅዶዋል።

#Rivian #EV_Chargers
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/22 16:36:23
Back to Top
HTML Embed Code: