Telegram Web Link
#ዜና

በዛሬው እለት በፓራጎን የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም በመንጃ ፈቃድ አሰልጣኞች ማህበር ውስጥ ለሚገኙ አባላት አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር በሚል ርዕስ ስልጠና በመካሄድ ላይ ይገኛል ::


በፓራጎን የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም የተዘጋጀው ለመንጃ ፈቃድ አሰልጣኞች አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር በሚል ርዕስ የሙሉ ቀን ስልጠና እየተካሄደ ሲሆን በዚህም ስልጠና ላይ የመንጃ ፈቃድ አሰልጣኞቹ ያላቸው እውቀት እና ልምድ ላይ እንዴት ተጠንቅቀው ማሰልጠን እንደሚችሉ እንዲሁም ጀማሪ አሽከርካሪዎችም በጥንቃቄ እንዴት ማሽከርከር እንዲችሉ ማድረግን እና የስልጠናውም አላማ የአስተሳሰብ ለውጥን ለማምጣት እንደሆነ አሰልጣኝ አቶ ዘላለም ተናግረዋል :: ይህም ለውጥ በዘላቂነት ለአሽከርካሪዎች መፍትሄ እንዴት ማምጣት እንደሚቻል በስልጠናው ላይ ተነስቷል ::

በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንጃ ፍቃድ አሰልጣኞች ማህበር አባላት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን ማዘጋጀት አደጋ ከመቀነስ እንዲሁም ብቁ እና ጠንቃቃ የሆኑ ሹፌሮችን ለማብቃት እንደሚረዳቸው ገልጸዋል :: መንግስትም ይህንን አደጋን ከመቀነስ ጋር በተገናኘ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ በማሰብ እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን እንዲያደርጉ እንዲያግዝ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ::


@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቻርጅ ማረግ ነዳጅ ለሙላት ከሚወስድብ ጊዜ ጋር ተቀራራቢ እየሆነ ነው።


Polestar እና በቅርብ አመት ውስት ስራ የጀመረው የኤሌክትሪክ ባትሪ አምራቹ StoreDot በጋራ በመሆን ነዳጅ እንደመቅዳት ያህል ፈጣን የሆነ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንግን አሳይተዋል።

77 kilowatt hour ባትሪ ፓክ የተገጠመለት የPolestarሩ ፕሮቶታይፕ Polestar 5  ከ10% እስከ 80% በ10 ደቂቃ ውስጥ ብቻ ቻርጅ ማረግ ችሎዋል።
የመኪናው ቻርጂንግ ሬትም ከ310 kilowatt ተነስቶ እስከ 370 kilowatt ከፍ ማለት ችሎዋል።

የSotreDot ፋስት ቻርጂንግ ቴክኖሎጂ የSilicon-dominant cellዎች ከNMC cellዎች ጋር በጋራ ሲሆኑ የማቀዥቀዣ ሲስተም የማያስፍልገው Energy-density ይፈጥራሉ።

የፈጣን የቻርጅ ማረጊያ ጊዜን ለማስመስገብ የሶፍትዌር እገዛን የተጠቀመ ሲሆን የባትሪ ፓኮቹ size ቢያንስ እስር 100 Kilowatt hour ያድጋል ብሎዋል።

#Polestar #SotreDot #Ev_Charging
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አዲሱ ህግ መኪኖች በራሳቸው ፍሬን መያዝ መቻላቸውን እንደ ስታንዳርድ እንዲሆን አድርጎዋል።


የአሜሪካው National Traffic Safety Administration (NHTSA) በ2029 በአደጋ ጊዜ መኪኖች በራሳቸው አውቶማቲካሊ ፍሬን መይዝ እንዲችሉ የሚያስገድደውን ህግ አርቅቆ ጨርሶዋል።

ሁሉም ቀላል ተሽከርካሪዎች የፊቶ ለፊት የግጭት ማስጠንቀቂያ ( Forward collision warning) ፣ የእግረኛ መንገድን መለያ (pedestrian detection braking)፣ እና በአደጋ ጊዜ መኪናው አራሱ ፍሬን መያዝ ሚያስችለውን ( Emergency braking) እንዲኖራቸው ህጉ ያስገድዳል።

አሁን በአሜሪካ የሚገኙ 90% የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች Emergency braking ያላቸው ሲሆን ይሄም የሆነው ከመኪና አምራቾች ጋር በተደረገው በበጎ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ስምምነት ነው። እናም ምን አይነት ግዴታ እና ቅድመ ሁኔታዎች አልተቀመጡም። አሁን ላይ ህጉ እነዚህን እስታንዳርዶች አስቀምጦዋል።

ሲስተሙ መኪናው በ100 km/h ፍጥነት እየተጓዘ ከፊቱ ሌላ ተሽከርካሪ ቢገባበት መቆም መቻል አለበት ፣ መኪናው በ140km/h ፍጥነት እየተጓዘ ከፊት ካለ ተሽከርካሪ ጋር የመጋጨት እዝማሚያው ከፍ እያለ ሲመጣ ፍሬን በራሱ ይዞ መቆም እና በ70km/h ፍጥነት እየተጓዘ ወደ እግረኛ መንገድ ላይ ጥሶ ሊገባ ሲል እራሱ ፍሬን መያዝ መቻል አለበት የሚል ህግ ሲሆን በተጨማሪ ሲስተሙ በምሽትም ጭምር መስራት መቻል አለበት ይላል።

NHTSA ይሄን ሲስተም ማካተት በየአንዳንዱ የመኪና ዋጋ ላይ የ 82 ዶላር ጭማሪ የሚያስደርግ ሲሆን ከሁሉ በላይ ግን በአመት 24,000 የመኪና አደጋዎችን ከመፈጠር እና 362 የብሶችን ከህልፈት የሚታደግ ይሆናል ብሎዋል።

#NHTSA
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የኤሌክትሪክ መኪኖች በአመት በተጓዙባቸው kmዎች  አንፃር ከነዳጅ መኪኖች ጋር ሲነፃፀሩ በጣም ውድ ናቸው።


የኤሌክትሪክ መኪኖች በነዳጅ ከሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ይልቅ ለመጠቀም ርካሽ ሲሆኑ፣ የISeeCars አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው ግን በkm ሲነፃፀሩ የበለጠ ውድ ናቸው። ይህ የሆነበት ምክንያት የኤሌክትሪክ መኪኖች ከነዳጅ መኪናዎች በጣም ያነሰ ስለሚነዱ እና የመግዣ ዋጋቸው በጣም ውድ ስለሆነ ነው።

ጥናቱ ከ1.3 ሚሊየን በላይ 3 አመት ከሆናቸው መኪናዎችን ላይ የተሰበሰበ መረጃ ሲሆን በአማካይ አንድ የነዳጅ መኪና በአመት 20,600 km ይንቀሳቀሳል። ለኤሌክትሪክ መኪኖች ይሄ ቁጥር 16,500 km ያህል ነው።

እና የአንድ አዲስ የነዳጅ መኪና አማካይ ዋጋ 40,000 ዶላር ሲሆን የኤሌክትሪክ መኪና ደግሞ  ከ 52,000  ዶላር ነው። ይህ ማለት የኤሌክትሪክ መኪኖች በአመት ለሚነዱበት ለእያንዳዱ 1,600 kmዎች በአማካይ 5,100 ዶላር ያስወጣሉ። ይህም ከነዳጅ መኪናዎች በ63% ከፍ ያለ ሲሆን የነዳጅ መኪኖች በአማካይ 3,100 ዶላር ያሶጣሉ።

ፕለጊን ሃይብሪድ መኪኖችም በkm ወጪያቸው ውድ ሲሆን ከነዳጅ መኪናዎች በ39% ከፍ ያለ ነው። ነገር ግን ሃይብሪድ መኪኖች በጣም ወጪ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች ናቸው እና በአመት ለተንደዱት እያንዳንዱ 1,600 km ዋጋቸው በአማካይ ሲታይ ከነዳጅ መኪናዎች 2% የቀነሰ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ሃይብሪድ መኪኖች እንደ ነዳጅ መኪናዎች ብዙ ስለሚነዱ እና የመግዣ ዋጋቸው በትንሹ የቀነሰ ስለሆነ ነው።

#Electric #ICE #PHEV #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

toyota አዲስ የሃይል ማመንጫ ሲስተም ከፈተ።


Toyota ከFuelCell energy ከተባለ ካምፓኒ ጋር በመሆን በCalifornia ግዛት Long Beach ወደብ ላይ የገነባውን የሃይል ማመንጫ እያስመረቀ ነው። የሃይል ማመንጫውን "Tri-gen" ተብሎ የተሰየመ ሲሆን 3 የተለያዩ ምርቶችን ያመርታል።
ታዳሽ የኤሌክትሪክ ሃይል፣ ሃይድሮጅን፣እና የመገልገያ ውሃ።

ሲስተሙ የተገነባው ወደቡ ላይ የToyotaን የሎጂስቲክ ስራዎች እንዲያግዝ ሲሆን ወደቡ በአመት 200,000 Toyota እና Lexus መኪኖችን ያስተናግዳል።
የሃይል ማመንጫው Biogas(ባዮ ጋዝ)ን በመጠቀም በቀን 2.3 megawatts ታዳሽ የኤሌክትሪክ ሃይል፣ እስከ 1,200 kg ሃይድሮጅን፣ እና 5,300 ሊትር የመገልገያ ውሃ ያመርታል።

ሃይድሮጅኑን ወደ ወደቡ የሚመጡ እንደ Toyota Mirai ያሉ የሃይድሮጅን መኪኖችን እና ወደቡ ላይ ለሚሰሩ የToyota class 8 የሃይድሮጅን የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለመሙላት ሲጠቀመው ውሃውን ደግሞ ወደ ወደቡ በመርከብ ተጭነው የመጡት መኪኖች ለሽያጭ ከመቅረባቸው በፊት ይታጠቡበታል።

Toyota እንዳለው አዲሱ Tri-gen ሲስተሙ ወደ ከባቢ አየር ይለቀቅ የነበረውን 9,000 ቶን C02 ያስቀራል።

#Toyota #Tri-gen
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የነዳጅ መኪኖችን Alternator የሚጠቀም የኤሌክትሪክ Scooter።


የBMWዉ CE 02 ላይ ያለው የኤሌክትሪክ ሞተር የScooter(እስኩተር) እና የሞተር ሳይክል ድብልቅ ይመስላል።  በእውነቱ የBMW የነዳጅ መኪኖች ላይ ከሚገኙ Alternatorዎች ትንሽ ሞዲፋይ የተደረገ ነው።
(Alternator የእንቅስቃሴ ሃይልን ወደ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚቀይር መሳሪያ ነው)

Alternatorሩ ካለ 48-ቮልት Mild ሃይብሪድ ከሆኑ እንደ 3-፣5-፣7- series መኪኖች እና X Series SUV መኪኖች የተወሰደ ነው። ነገር ግን Valeo የተባለው አቅራቢው ካምፓኒ ለBMWው CE 02 ለተባለው እስኩተር እንዲሆኑ ሲል ትንሽ ሞደፊኬሽን አርጎባቸዋል።

Scooterሩ 15 የፈረስ ጉልበት ማመንጨት የሚችል ሲሆን በሰአት እስከ 52km ፍጥነት መጓዝ ይችላል።

#BMW #EC-02
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

General Motors እና Volkswagen በቻይና ስኬትን መመልከት ጀመሩ።


ከዚ በፊት GM እና Volkswagen የቻይና ገበያ ላይ መኪኖቻቸውን ለመሸጥ ከብዷቸው እንደነበር ዘግበንላቹ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ በኤሌክትሪክ መኪኖቻቸው ሽያጭ ላይ ስኬትን መመልከት ጀምረዋል።

ባለፈው ወር GM የ Buick፣ Cadillac
እና Chevrolet ብራንዶቹ አንድ ላይ
ተደምረው ወደ 9,000 መኪኖችን የሸጠ ሲሆን ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ93% እድገት አሳይቷል።

Volkswagen ዋገን በአንፃሩ 10,000 ID መኪኖችን የሸጠ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ካለፈው አመት ሽያጩ ጋር ሲነፃፀር በ56% እድገት አሳይቶዋል። ከወርሃ March ላይ ከነበረው የሽያጭ ቁጥሩ ተመሳሳይ ነው።

ሁለቱም ብራንዶች የሽያጭ ቁጥራቸው ከሁል ጊዜ ሽያጫቸው ከፍተኛ ከተባለው በግማሽ የቀነሰባቸው ሲሆን ወደእዛ ደረጃ መቼም ላይመለሱ ይችላሉ። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ቻይና ላይ የውጪ የመኪና አምራቾች በሃገር በቀል የመኪና አምራቾች ይዋጣሉ ብለው የፈሩትን ያህል እንዳልሆነ ይሄ ምልክት ሊሆን ይችላል።

#GM #VW #China
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ፈረንሳይ BYDን በደስታ እቀበለዋለው አለች።


ፈረንሳይ ምንም እንኳን በሃገሪቱ ላይ ያለው የቻይና የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ ላይ ገደብ የጣለች ቢሆንም የፈረንሳይ የፍይናንስ ሚኒስተር የቻይናው የመኪና አምራች ሃገሪቷ ላይ የመኪና ማምረቻውን እንዲከፍት ግብዣቸውን አቅርበዋል። በዚህ ላይም አክለው ለቻይና የመኪና ኢንዱስትሪ በራቸው ክፍት መሆኑንም ገልፀዋል።

ፈረንሳይ በቅርቡ በምርት ወቅት ከፍተኛ የካርበን ልቀት ያላቸው የኤሌክትሪክ መኪኖችን ሃገሪቷ ላይ እንዳይገቡ የሚያግድ ህግ ያወጣች ሲሆን ይህም ህግ ብዙ የቻይና መኪና ሞዴሎችን ያካትታል።

የአውሮፓ ህብረት ምንም እንኳን የቻይና መኪኖች ወደ ሃገራቸው እንዳይገቡ የሚፈልጉ ቢሆንም የቻይና የመኪና አምራቾች አውሮፓ ውስጥ ማምረቻ መክፈታቸው ለዜጎቻቸው ይዞት የሚመጣው የስራ እድል ስላለ ፍቃደኛ ናቸው።

#BYD #France #EU
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Xiaomi የተሻሻለ የGiga-Casting/ በትልቅ መጠን ብረትን አቅልጦ በተፈለገው ቅርፅ ማውጫ ላይ የመጋገሪያ መንገድን ይዞ ብቅ አለ።


ወደ መኪና ምርት የገባው የስልክ አምራቹ Xiaomi የቴስላን ግዙፍ የCasting መንገድ የኮረጀ ሲሆን ነገር ግን ትንሽ ማሻሻያ አድርጎበታል።

SU7 ለተባለው ሴዳን መኪናው ይኋለኛ ክፍል ብረትን አቅልጦ የበተፈለገው ቅርፅ ለመጋገር/Cast ለማረግ) ከ9,000 ቶን በላይ ክብደት ያለውን ማሽን የተጠቀመ ሲሆን ይሄም መንገድ የተለያዩ 72 ፓርቶችን እና የተለያዩ ትናንሽ ፓርቶችን ለየብቻ አምርቶ ከዛም አንድ ላይ የመገጣጠም ሂደትን አስቀርቶዋል።

Xiaomi ለመኪኖቹ ባለሶስት ደረጃ የግጭት መከላከያ ሲስተም ያለው ዲዛይን እየተገበረ ያለ ሲሆን መኪኖቹ በመካከለኛ ፍጥነት ላይ እየተጓዙ ግጭት ቢፈጠር ሙሉ Castingጉን በመቀየር ፋንታ አደጋ የደረሰበትን Beam ብቻ መቀየር ያስችላል።


መኪኖች በCasting ፕሮሰስ ሲሰሩ በአደጋ ጊዜ ሙሉ Castlingጉን መቀየር አለብን ? የሚለው ጉዳይ ብዙሃኑን ግር ያሰኘ ነገር ቢሆንም Castingኑን ማጠፍ ፣ ማቃናት፣ መጠናከሪያ ብረቶችን እላያቸው ላይ ደርቦ መበየድ ይቻላል።

ሌላው የCasting ጥቅም መኪኖች የምርት ሂደትን በጣም እንዲፋጠን ያረጋል። Xiaomi እንዳለው 700 ሮቦቶች ማምረቻ ውስጥ የሚኖሩት ሲሆን ይሄም ሙሉ የምርት ሂደቱን ያፋጥነዋል። የመኪና አምራቹ ሙሉ አቅሙን መጠቀም ሲጀር በየ76 ሰከንዱ 1 መኪና መስራት እንደሚችል ተናግሮዋል።
ይሄ ከቴስላ በእጥፍ የፈጠነ ሲሆን ቀደምት የሚባሉ ትላልቅ የመኪና አምራቾችን ጭምር በ1 ደቂቃ ከXiaomi የምርት ፍጥነት ወደኋላ የዘገዩ ናቸው።

#Xiaomi #Casting
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Mercedes -AMG አዲስ Cabriolet የቦዲ ስታይል ያለውን መኪና አስተዋውቆዋል።


በጣም ፈጣን እና ቅንጡ የሆኑ መኪኖች አምራች የሆነ Mercedes ንኡስ ክፍል Mercedes-AMG ሁለተኛ ጣራው ፍት የሆነ የመኪና ሞዴሉን ይፋ አርጎዋል። ከዚ በፊት AMG SL Roadster ይፋ ያረገ ሲሆን አሁን ላይ AMG CLE Cabriolet መኪና ምርቱን ተቀላቅሎዋል።

ባለ 48- ቮልት Mild ሃይብሪድ ሲስተም ከ6 ባለ 3L ሲሊንደር ሞተር ጋር አጣምሮ የያዘ ሲሆን በዘጠኝ የፍጥነት አምራጭ በአውቶማቲክ የቀረበ መኪና ነው።
4ቱንም ጎማዎች ለመንዳት 443 የፈረስ ጉልበት ሲያመነጭ ውስት ላይ 12.3 -inch የጌጅ እስክሪን እና 11.9 ማእከላዊ የኢንፎቴመን እስክሪን ታገኛላቹ።

AMG CLE 53 በያዝነው አመት ሁለተኛ መንፈቅ ላይ ለአሜሪካ ገበያ የሚቀርብ ይሆናል ነገር ግን እስካሁን የመሸጫ ዋጋ አልተቆረጠለትም።

#Mercedes #AMG
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota ወደ ወደብ በመርከብ ተጭነው የመጡ መኪኖቹን recycle የሆነ ቤንዚል እየሞላባቸው ነው።


Toyota ወደ Portland ወደተባለችዋ ወደብ የሚመጡ አዳዲስ መኪኖቹን ለሻጮጭ ከመከፋፈላቸው በፊት Renewable/ ታዳሽ በሆነ ቤንዚል እየሞላቸው ነው።

ነዳጁ Chevron በተባለ የነዳጅ ካምፓኒ የተሰራ ሲሆን ውስጡ ላይ ከ50% በላይ የሚሆነው Recycle በተደረጉ ግበቶች ነው የተሸፈነው።
የነዳጅ ካምፓኒው እንደተናገረው በታዳሽ ግባቶች የተሰራው ቤንዚል ከተለመደው ገበያ ላይ ካለው ቤንዚል በ40% ያክል የካርበን ልቀቱ የቀነሰ ነው።

ታዳሽ ቤንዚሉን Toyota ከChevron ጋር በመተባበር ያበለፀጉት ሲሆን ያለፈው አመት እንደ Camry ፣ Rava 4 Prime ፣ እና Tundra ያሉ የToyota መኪኖችን ይሄን ታዳሽ ቤንዚል በመሙላት ከMississippi እስከ Texas ያሽከረከሯቸው ሲሆን አሁን ላይ ይሄን የጉዞ ሙከራ እስከ Portland ወደብ ድረስ እንዲሆን አድርገዋል።

#Toyota #Renewable_Gasoline #Chevron
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW እንግሊዝ በሚገኘው የኢንጅን ማምረቻ ውስጥ የሮቦት ውሻን እየተጠቀመ ነው።


BMW በእንግሊዝ በሚገኘው የመኪና የኢንጅን(Engine) ማምረቻ ውስጥ የምርት ሂደቱን እንዲያግዝ ሲል የBoston Dynamics የሮቦት ውሻን እየተጠቀመ ነው።  BMW የሮቦቱን ስም ከ Spot ወደ SpOTTO የቀየረው ሲሆን እራሱን ችሎ በማምረቻ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ ሲባል እንደ visual ፣ acoustic እና፣ Thermal ያሉ ሴንሰሮች ተገጥመውለታል።


SpOTTOን BMW ማምረቻ ውስጥ የተለያዩ ዳታዎችን እንዲሰበስብ ፣ የምርት ጥራት ላይ መጓደል እንዳይኖር እዲከታተል እና በምርት እቅድ ላይ እንገዛ እንዲያረግ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የሮቦት ውሻው በማምረቻ ውስጥ ያሉ መሳሪያዎችን የሙቀት መጠን እንዲከታተል፣ የታመቀ አየር የሚታላለፍባቸው የቱቦ መስመሮች ላይ ክፍተት ሲኖር ክፍተት ያለባቸውን ቦታ እንዲለይ ይጠቀምበታል።

BMW እንዳለው SpOTTO ተጨማሪ አገልግሎት ሊሰጥባቸው የሚችልባቸውን መንገዶች በማምረቻ ውስጥ እየሞከረ ያለ ሲሆን የሮቦት ውሻዎች በሌላ ማምረቻዎች ውስጥም ሊጠቅሙበት የሚችለውን መንገድ ጨምሮ እየሞከረ ነው።

#BMW #SpOTTO #Robotic_Dog
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nio አዲስ በዋጋቸው ቀነስ ያሉ የመኪና ብራንዶች አውሮፓ ላይ ሊያቀብ ነው።



የቻይናው የመኪና አምራች Nio ባለፈው አመት ላይ 160,000 Premium የኤሌክትሪክ መኪኖችን ሸጦዋል። እንደሌሎች የመኪና አምራቾች ሁሉ የተለያዩ ሞዴል መኪኖችን ሰርቶ ለገበያ ያቀረበ ቢሆንም ሽያጩ እንደመቀዛቀዝ ብሎዋል። ለዛም በሱ ስር ያሉ በዋጋቸው ቀነስ ያሉ መክኖችን ሚያመርቱ ብራንዶን አስተዋውቆዋል።

አንደኛውን ብራንድ Onvo ሲል የሰየመው ሲሆን የሽያጭ ቁጥሬን ከፍ ያረግልኛል ብሎ ያምናል።
ዘገባዎች እንደሚሉት ከሆነ አዲሱ የኤሌክትሪክ መኪና ብራንድ የBYD ንኡስ ክፍል ከሆነው FinDreams ባትሪን የሚረከብ ሲሆን ይሄ ለNio የመጀመሪያው ነው። እንደ Car News China ዘገባ ከሆነ ከCATL እና CALB ጭምር ባትሪዎችን የሚረከብ ይሆናል።

Nio በዚህ አመት Onvoን በአውሮፓ ገበይ ላይ የሚያቀርበው ሲሆን እሱን ተከትሎ ሌላኛው Firestar የተባለው አዲስ ብራንድ በ30,000 ዩሮ የመነሻ ዋጋ መኪኖቹን ለገበይ ያቀርባል።

ይሄ እውነት ከሆነ በአመት ከ200,000 መኪኖች በታች ለሚሸጠው Nio ሁለት አዲስ ብራንዶችን በስሩ መጀመሩ እንዳሰበው ቀላል አይሆንለትም።

#Nio #Onvo #Firestar
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Shenzehen ከነዳጅ ማደያዎች በላይ ብዙ የኤሌክትሪክ መኪኖች ፋስት ቻርጂንግ ስቴሽን አላት።


አሁን ላይ በመላው አሜሪካ የነዳጅ ማደያ እና የ ቻርጂግ ስቴሽን ቁጥር ስሌት ለ15 ነዳጅ ማደያ 1 የቻርጂንግ ሲኖር በCalifornia ግዛት ደግሞ ለ5 የነዳጅ ማደያዎች 1የቻርጂንግ ስቴሽን አለ።

ነገር ግን በሃገረ ቻይና የምትገኘው Shenzehen ከተማ ከነዳጅ ማደያዎች በላይ ብዙ የቻርጂግ ስቴሽኖች አሉኝ ያለችው የመጀመሪያዋ ከተማ ናት።
እንደተናገረችው ከሆነ በአጠቃላይ በከተማዋ ውስት 362 የፋስት ቻርጂን ስቴሽኖችን ሲኖሩ በያዝነው አመት በመጀመሪያ እሩብ አመት አጋማሽ ብቻ 670 million kilowatt- hours ሃይል ቻርጅ አርገዋል። ይህም በ 11% ጭማሬን አሳይቶዋል።

ከተማዋ ምን ያህል የነዳጅ ማደያዎች እንዳሏት የጠቀሰች ባይሆንም የታክሲ እና የህዝብ ማመላለሻ ባሶቿን ሲስተም ወደ ኤሌክትሪክ ከቀረች አመታት ተቆጥረዋል።

#Shenzehen #Charging_Station
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በቻይና የተመረቱ የቴስላ መኪኖች ላይ ያለው ሽያጭ ቀነሰ።


በሃገረ ቻይና የተመረቱ የቴስላ መኪኖች ሽያጭ ያሽቆለቆለ ሲሆን እንደ China Passenger Car Association መረጃ መሰረት ባለፈው ወር ላይ ቴስላ 62,000 ቻይና ላይ የተመረቱ መኪኖችን የሸጠ ሲሆን ይሄ ቁጥር ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ18% እሽቆልቁሎዋል።

የቴስላ ሽያጭ እንዲ በተቀዛቀዘበት ወቅት ከዚ በተቃራኒ ቻይና ላይ እንደ የኤሌክትሪክ እና ፕለጊን ሃይብሪድ ያሉ የመኪኖች ሽያች ጨምሮዋል።
በApril ወር ወደ 800,000 መኪኖች የተሸጡ ሲሆን ካለፈው አመት ሲነፃፀር በ33% እድገንት አሳይቶዋል።
የቻይና ትልቁ የመኪና አምራችም 312,000 መኪኖችን በመሸጥ ሽያጩን በ50% አሳድጎዋል።

#Tesla #China
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Daimler Track ደረጃ 4 autonomous የሆነውን የተሳቢ መኪናውን ፕሮቶታይፕ ይፋ አረገ።


የከባድ ተሽከርካሪዎች አምራች የሆነው Daimler Truck የlevel 4 self driving ሲስተም የተጫነበትን የኤሌክትሪኩን eCascadiaን ፕሮቶታይፕ ቨርዥን ይፋ አርጎዋል።
የself driving ሲስተሙ የDaimler ንዑስ ክፍል በሆነው Torc Robotics በተባለ ካምፓኒ የተሰርው ሲሆን አሁን ላይ መኪኖቹን በአሜሪካ አይዌዎች ላይ እየሞከሯቸው ነው።

ካምፓኒዎ እንዳለው ከሆነ ሲስተሙ አሁን ላይ የኤሌክትሪኩ eCascadia ላይ እየተሞከረ ያለ ቢሆንም በደንብ አድጎ እና ተሻሽሎ በማንኛውም የሃይል አማራጭ በሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ተገጥሞ ማገልገል አቅም አለው።

Daimler Truck አንደዚን ደረጃ 4 self driving ሲስተም የተጫነባቸውን ተሳቢ መኪኖች በ2027 የአሜሪካ ገበያ ላይ ለማቅረብ ያቀደ ሲሆን በአስር አመቱ መጨረሻ ላይ ወደ 3.2 ቢሊየን የሚጠጋ ገቢን አስገባለው ብሎ ይተብቃል።

#Daimler-Truck #Level-4_Autonomous
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ram  በሃይድሮጅን የሚሰሩ የከባድ ጭነት ፒክ አፕ መኪኖችን ማቅረብ ሊጀምር ነው።



በstellantis ፓረንት ካምፓኒ ስር የሚገኘው Ram ሙሉ በሙሉ በሃይድሮጅን የሚሰሩ የከባድ ጭነት ፒክ አፕ መኪኖች ለአሜሪካ አና ለአውሮፓ ገበያ ለማቅረብ አቅዶዋል።

የመኪና አምራቹ የሃይድሮጅን ሃይል ክፍል ሃላፊው አንዳለው ለሰሜን አሜሪካ የሚቀርበው በሃይድሮጅን የሚሰራው  Ram 5500 ሜክሲኮ ውስጥ የሚመረት ሲሆን ለአውሮፓ ገበያ የሚቀርበው ደግሞ በአንስተኛ መጠን ፖላንድ ላይ መመረት ጀምሮዋል።

Stellantis በ2030 ላይ በአለም ዙሪያ እነዚህን ሞዴል መኪኖች በአመት እስከ 100,000 ፍሬ ድረስ ለመሸጥ ያለመ ሲሆን ቀስ በቀስ የሃይድሮጅን መኪኖቹ የናፍጣ መኪኖቹን ምርት እንደሚተኩለት ያምናል።

#Ram #Hydrogen #Stellantis
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota ቻይና ላይ የሃይብሪድ ችግር ሳይገጥመው አይቀርም።



የጃፓኑ የመኪና አምራች Toyota ቻይና ላይ ከሃይብሪድ መኪኖቹ ጋር ተያይዞ ችግር ውስጥ የገባ ይመስላል። የመኪና አምራቹ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምረት የተለያዩን መንገዶችን ለመጠቀም ፍቃደኛ የነበር መሆኑ መልሶ የከፈለው ቢሆንም አሁን ላይ ግን የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ፍላጎት ቀንሶ በምትኩ የሃይብሪድ መኪኖች ላይ ያለው ጨምሮዋል።

ነገር ግን የቻይና መንግስት ለሃይብሪድ መኪኖች Green licence ስለማትሰጥ ቻይና ላይ ከኤሌክትሪክ እና ከፕለጊን ሃይብሪድ መኪኖች አንፃር ዝቅተኛ የሚባል ሽያጭ ነው ያላቸው።
አንደ Car News China ዘገባ Toyota ቻይና ገበያ ላይ ያቀረባቸው የፕለጊን ሃይብሪድ መኪኖቹ ያን ያህል ሽያጭ አላገኙም። ለዛም በመጪው ሁለት ሶስት አመት ውስጥ ሁለት ወይ ሶስት አዲስ የBYDን የፕለጊን ሃይብሪድ ፕላትፎርም የሚጠቀሙ መኪኖችን ሰርቶ ለቻይና ገበያ የሚያቀርብ ይሆናል።

ሴታፑ 1.5 L ቱርቦ ቻርጅድ ኢንጅን ከተያየ የባትሪ ሳይዝ ካለቸው እና እስክ 200km ተጨማሪ ሬንጅ ለመኪናው የሚሰጡ የባትሪ ፓኮች አጣምሮ የያዘ ሲሆን የኤሌክትሪኩ ሞተር ከፊትም ከኋላ ያሉትን ጎማዎች የሚነዳ ይሆናል።

Toyota ከBYD ጋር በጋር የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ እየሰራ ያለ ሲሆን አጋርነታቸውን በፕለጊን ሃይብሪድ መኪኖች ላይ የማረግ እድል አላቸው።

#Toyota #Haybrid #plug-in_Haybrid #China
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/22 18:17:29
Back to Top
HTML Embed Code: