Telegram Web Link
#ዜና

Nissan የአሜሪካውን የመኪና አምራች Fisker ከኪሳራ ሊታደገው ነው


ከባንኮች እና ከኢንቨስተሮች ባለበት ከፍተኛ እዳ ምክንያት ካምፓኒው ላይ ኢንቨስት ማድረግ ትልቅ ሪስክ አለው የተባለው የመኪና አምራች ካምፓኒ Fisker በቅርቡ እጄ ላይ ያለውን ገንዘብ ልጨርስ ነው ሰራተኖቼንም መክፈልም ሆነ አዲስ መኪና ማምረት የማልችልበት ሁኔታ ውስጥ ገብቻለው ያለ ሲሆን Nissan ግን ችግር የለውም ከካምፓኒ ድርሻቹህ ላይ ገዝተን በፓርትነርነት አብረን እንሰራለን ብሎዋል።

Fisker አሁን ላይ ወደ 1.17 ቢሊየን ዶላር ያህል ብድር ያለበት ሲሆን Nissan አሁን ላይ ባለበት የገንዘብ አቅም የምር ይታደገዋል? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ቢሆንም ሁለቱ ካምፓኒዎች በዝርዝር ስለ ስምምነታቸው እየተደራደሩ ሲሆን ኒሳንም 400 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ጥያቄ አቅርቧል።

#Nissan #Fisker
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የሃይድሮጅን ነዳጅ ለመሙላት ምን ያህል ገንዘብ ያሶጣል?

እንደ toyota ባሉ የመኪና አምራቾች ወደፊት ገበያውን ይመራሉ ብለው የሚያምኑባቸው የሃይድሮጅን መኪኖችን አሁን ገበያ ላይ ካሉ ሁሉም መኪኖች በላይ ነዳጃቸው ለመሙላት በጣም  ውድ የሚባል ወጪ አላቸው።

እንደምሳሌነት የሀዩንዳዩን ሃይድሮጅን SUV መኪናን ብንወስድ በሙሉ ታንክ 611 ኪሎሜትር ያህል ድራይቪግ ሬንጅ ያለው መኪና ሲሆን 161 የፈረስ ጉልበት አለው። ይህንን መኪና  ሙሉ ታንክ የሃይድሮጅን ነዳጅ ለማስሞላት 227 የአሜሪካ ዶላር ያሶጣናል ።

ከነዳጅ ዋጋቸው ውድነት በተጨማሪ አሜሪካ ውስጥ ራሱ ለሃይድሮጅ መኪኖች የተሟላ መሰረተ ልማት የሌለ ሲሆን በመላው 50 የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ 58 የሃይድሮጅ ማደያዎች ብቻ ሲኖሩ ከዛ ውስጥም 57 በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ የሚገኙ  ሲሆን በ ሃዋይ (Hawaii) ግዛት ላይ ደግሞ አንድ የሃይድሮጅን ነዳጅ ማደያ እናገኛለን።

#HydrogenCell
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Jaguar የነዳጅ መኪኖችን ሙሉ በሙሉ ማምረቱን ሊያቆም ነው


የእንግሊዙ ቅንጡ መኪኖች አምራች የሆነው Jaguar  ምርቱን ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች እየለወጠ ያለ ሲሆን በወርሃ ጁን ላይ  ሙሉ በሙሉ የነዳጅ መኪኖች ማምረቱን ያቆማል።

Jaguar እንዳሳወቀው ከሆነ ሁሉ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎቹን ባለ አራት በር ሴዳን የቦዲ ስታይል የሚኖራቸው ሲሆን እስካሁን ካምፓኒው ካመረታቸው መኪኖች በላይ ጉልበት እንደሚኖራቸው ይፋ አድርጓል።

ከ 2025 በፊት ለገበያ የማይቀርቡት እነዚህ የኤሌክትሪክ መኪኖች በአንድ ቻርጅ 700 ኪሎሜትር የሚጓዙ ሲሆን የመሸጫ ዋጋቸውም 100 ሺህ ፓውንድ እንደሚሆን ተናግረዋል።

#Jaguar
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ጠበቆች ከቴስላ የ6 ቢሊየን ዶላር ክፍያ ይገባናል ብለው ጠየቁ


ቴስላ ከሰራተኞች ጥቅማጥቅም ጋር ተያይዞ በፍርድ ቤት ሊጣልበት የነበረውን የ 56 ቢሊየን ዶላር ክፍያ ተከራክረው እንዲቀር ያረጉለት ጠበቆች ብዙዎች በጣም የተጋነነ ነው ብለው ያሰቡትን የ 6 ቢሊየን ዶላር ክፍያ ይገባናል የሚል ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ካምፓኒውን ከትልቅ ወጪ የታደግነው በመሆኑ እና ባስቀረንለት ወጪ ተጠቃሚ በመሆኑ ይሄ ገንዘብ ይገባናል ብለው ሞግተዋል።

በአንፃሩ የቴስላ መስራች እና CEO የሆነው Elon Musk ይሄ ጥያቄ ወንጀል(ዝርፊያ) ነው ያለ ሲሆን ካምፓኒውን ጎድታቹታል እንጂ ምንም የጠቀማቹት ነገር የለም ብሎ መልስ ሰቷል።

ይሄ ክፍያ ይገባቸዋል ወይ አይገባቸውም የሚለውን ውሳኔም ጉዳዩን የያዙት ዳኛ የሚወስኑት ይሆናል።

በተያያዘ ዜና ቴስላ አሜሪካ ላይ ባለው የ Super Fast ቻርጀር ኔትወርኩ እንዲጠቀሙ ከተፈራረማቸው የመኪና ካምፓኒዎች ትልቅ የሚባል ገቢን እያስገባ ነው

ከነዚህ ካምፓኒዎች ውስጥም የመጀመሪያውን ፈቃድ Ford ባለፈው ሳምንት ላይ ያገኘ ሲሆን የፎርድ መኪና ባለቤቶች እነዚህ ቻርጀሮች ላይ በመጠቀም ከቴስላ መኪና ባለቤቶች አንፃር በ 30% ብልጫ አሳይተዋል

ከቴስላ መኪና ባለቤቶች እኩል ለቻርጅ ማድረጊያ አነስ ያለ ክፍያ ለማግኘትም የአባልነት ክፍያ መክፈል ሲጠበቅባቸው ክፍያውም በወር 13 ዶላር ነው።

#Tesla
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አሜሪካ ላይ በጣም ፈጣን የተባሉ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮች ለህዝብ አገልግሎት ይፋ ሆኑ


በGoogle ካምፓኒ የሚታገዘው Gravity ተብሎ የሚጠራው አዲስ የቻርጅ አምራች ካምፓኒ በጣም ፈጣን የተባሉ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮችን በኒውዮርክ ከተማ ላይ ለህዝብ አገልግሎት ማቅረቡ ተሰማ

በ (manhattan) ከተማ ላይ 24 ባለ 500 Kilowatt ቻርጀሮችን የተከለ ሲሆን ቻርጀሮቹም በ 5 ደቂቃ ውስጥ 320 ኪሎሜትር መጓዝ የሚያስችለንን የኤሌክትሪክ ሃይልን ለመኪኖች  ቻርጅ ማድረግ ይችላሉ።

Gravity በመላው አሜሪካ እነዚህን ቻርጀሮች የማዳረስ እቅድ ያለው ሲሆን በአመት ተመሳሳይ 1000 ቻርጀሮችን የማምረት አቅሙም እንዳለው ተናግሮዋል።

ቻርጀሮቹም አነስ ያለ size ሲኖራቸው ከመለስተኛ የጉዞ ሻንጣ ጋር ተመሳሳይ ትልቀት አላቸው።

#Gravity
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ጠቃሚ_መረጃ

በቀላሉ በጭስ ማውጫው በኩል በሚወጡ ጭሶች በማየት ብቻ መኪናችን ላይ ምን አይነት ችግር እንዳለ ማወቅ እንችላለን

#Fuel #Smoke
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

በየትኛውም የእድሜ ክልል ቢሆኑ መኪናዎትን በቀላሉ ይሽጡ

መኪናዎትን ለመሸጥ እና ለማከራየት በቀላሉ የመኪናዎትን ፎቶ እና ቪዲዮ ወደእኛ በመላክ አስተዋውቀው መሸጥ እንዲሁም ማከራየት ይችላሉ ::

ፎቶ ብቻ - 300 ብር (ኢንስታግራም,ቲክቶክ እና ቴሌግራም ላይ ፎቶዎቹን እንለቃለን)
ፎቶ እና ቪዲዮ - 1000 ብር (ኢንስታግራም,ቲክቶክ እና ቴሌግራም ላይ ፎቶዎቹንም ቪዲዮውንም እንለቃለን የቪዲዮ ድምፅ ግን በዮናታን ደስታ የምንሰራ ይሆናል)

ክፍያውን በቴሌብር ብቻ የምንቀበል ሲሆን የሚከፈለውም በ 0911663121 ስልክ ላይ ነው :: ድርጅቶችም ከእኛ ጋር መስራት ይችላሉ ደረሰኝ ስለሚያገኙ ::

የመኪናዎትን ፎርሙን የሚሞሉበትን ሊስት እንድንልክሎ እና ለተጨማሪ መረጃ በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም በ @hulemekinaadmin መልእክት ይላኩልን ::

@hulemekina
#ዜና

BYD በዋጋ ቀነስ የሚለውን ሞዴላቸው ላይ አሁንም ቅናሽ አደረጉ


አሁን ላይ ወደ 100 የሚጠጉ የኤሌክትሪክ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች ሲገኙ ገበያው ላይ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት በተሻለ ዋጋ የተሻለ መኪና ማቅረብ የግድ ነው :: ቻይና ውስጥ ከሚገኙ በጣም ከሚታወቁት የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ካምፓኒዎች አንዱ BYD ነው ::

BYD መኪኖቹን ብቻ ሳይሆን ባትሪም ስለሚያመርቱ ዋጋ ላይ የተሻለ ቅናሽ ማድረግ ይችላሉ :: በዋጋ ቀነስ ያለው ሞዴላቸው ደግሞ Seagull ሲሆን በፊት ከነበረበት ዋጋ 4,000 ዩአን ቅናሽ በማድረግ አሁን ላይ 69,800 ዩአን ወይም 9,700 የአሜሪካን ዶላር መነሻ ዋጋውን አድርሰውታል :: ከተማችን ላይም እየገቡ ይገኛሉ :: ስለዚህ መኪና ሪቪው እንድንሰራ የምትፈልጉ ኮሜንት ላይ ሀሳባችሁን አጋሩን ::

#BYD #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ከ Tesla Model Y ጋር የሚፎካከረው የ Rivian መኪና ነገ ለእይታ ይቀርባል


ከዚህ በፊት የ Rivian ካምፓኒ Rivian R1T እና R1S ያወጡ ሲሆን አሁን ደግሞ ከ Tesla Model Y ጋር ይፎካከራል ብለው ያሰቡትን መኪና ለገበያ ሊያቀርቡ ነው ::

በዚህም መሰረት Rivian R2 የተሰኘው ኤሌክትሪክ መኪና ለ 5 ሰዎች መቀመጫ ሲኖረው በአንድ ቻርጅ እስከ 531 ኪሎሜትር ድረስ መጟዝ ይችላል :: ከ 0 እስከ 100 ኪሎሜትር በሰአት ለመድረስ 3 ሰከንድ ብቻ ሲፈጅበት ከምንም በላይ ደግሞ የመሬት ከፍታው 248 ሚሊሜትር ሲሆን ይህም ከሱ ጋር ከሚፎካከሩ መኪኖች የተሻለ ያደርገዋል :: መነሻ ዋጋው ደግሞ 47,500 የአሜሪካን ዶላር ነው ተብሏል :: በ 2026 ለገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል ::

ይህንን በሙሉ መረጃ ያወጣው ግለሰብ የ Rivian ዌብሳይት ላይ ኮዱን አይቼ ነው ያገኘሁት ብሎ ነው :: ነገ ለእይታ ሲቀርብ ያለውን ነገር እውነት ይሁን ውሸት የምናይ ይሆናል ::

#Rivian #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ሪቪው

የአለማችን ፈጣኑ MPV
Li Auto Mega


የLi Auto ምርት የሆነው Mega EV የአለማችን ፈጣኑ MPV( Multi Purpose Vehicle) ሚኒባስ ሲሆን በ12 ደቂቃ ውስጥም 500 ኪሎሜትር የሚያስጉዘውን የኤሌክትሪክ ሃይል ቻርጅ ያደርጋል።

በቻይናው የመኪና አምራች Li Auto የሚመረተው እንደ ቤተሰብ መኪናነት ወይም ለተለያዩ አገልግሎቶች ልንጠቀምበት የምንችለው በተለምዶ አጠራር ሚኒባስ ወይም ቫን ብለን ልንሰይመው የምንችለው Li Auto Mega  የአለማችን ፈጣኑ ሚኒባስ ነው ተብሎዋል።

ፍጥነቱ ከዜሮ ተነስቶ 100 ኪሎሜትር በሰአት ለመድረስ 5 ሰከንድ ብቻ ሲፈጅበት በተገጠመለት 102 Kwh ባትሪው በአንድ ቻርጅ ብቻ እስከ 710 ኪሎሜትር የሚደርስ ድራይቪንግ ሬንጅ አለው።

Mega Qilin 5C የሚባለውን ባትሪ የሚጠቀም ሲሆን እነዚህ (highly dense) የሆኑ ባትሪዎችም እስከ 450 ኪሎዋት በሆነ ሃይል ፋስት ቻርጅ መደረግ ይችላሉ።

ውስጡ ላይም በጣም ምቹ የሆኑ 7 መቀመጫዎች ሲኖረው የራሱ ፍሪጅ (ማቀዝቀዣ) ጭምርም አካቶ ይዞዋል።

#LiAuto #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Kia በአዲሱ Ev9 በተባለው የኤሌክትሪክ SUV ላይ ትልቅ ቅናሽ አደረገ


ለመጀመሪይ ጊዜ በወርሃ ሴፕቴምበር 2023 ለገበያ የወጣው የ Kia ኤሌክትሪክ SUV በ2024 ላይ Kia 10% ቅናሽ አድርጎበት ለገበያ ያወጣው ሲሆን ከመሸጫ ዋጋ በተጨማሪ መኪናውን በኪራይ ወስደው ለሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ቆንጆ የሚባል አማራጭም አዘጋጅቶዋል።

AWD(All Wheel Drive) የሆነውን በ282 ኪሎዋት ሞተር 378 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጨውን 99.8 Kwh ባትሪ ፓክ እስከ 495 ኪሎሜትር መጓዝ የሚችለውን የ EV9 ሞዴል መኪናቸው ለ 48 ወራት በ 839 ፓውንድ ከነፃ የመኪና እጥበት እና በ 48ቱ ወራት ውስጥ ከሚደረግ ከ 3 ነፃ የፍሬን ዘይት ቅየራ አገልግሎት ጋር አድርጎ አቅርቦዋል።

#kia #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ኤክስፐርቶች ቶዮታ አውስትራሊያ ላይ በጣም በካይ ነው ከሚባለው የድንጋይ ከሰል ማውጫ በላይ ከባቢ አየርን ይበክላል አሉ።


አስካሁን ምን አይነት የካርበን ልቀት መጠን ገደብ ያልነበራት አውስትራሊያ አሁን ላይ ገደብ አበጅታ ስታንዳርድ የሆነውን መመሪያ ለማርቀቅ በአየር ንብረት ምክር ቤቷ በኩል የዘርፉ ባለሙያዎችን አሰማርታ ጥናት ባደረገችበት ወቅት ሃገሪቷ ላይ ከፍተኛ ብክለት አለው (narrabri underground mine) ከተባለው የድንጋይ ከሰል አውጪ ከሆነው ኩባኒያ በላይ የቶዮታ መኪኖች በላይ ለአየር ንብረቱ ጠንቅ እና በካይ ሆነው አግኝተዋቸዋል።

230,000 የሚሆኑ የቶዮታ ቫኖች፣ፒካፕአፕ ትራክ፣እና የቤት መኪኖች በቶዮታ ካምፓኒ እና በቶዮታ ስር ባለው የቅንጡ መኪና አምራች በሆነ ሌክሰስ ስም ለገበያ ቀርበው ህዝቡ እየተገለገለባቸው ያሉ ተሽከርካሪዎች
በአመት 500,000 ቶን ካርበንዳይ ኦክሳይድ (Co2) ወደ ከባቢ አየር ይለቃሉ።

ስለዚህም ጉዳይ የቶዮታ ካምፓኒ ምን አስተያየት እንዳለው የተጠየቀ ቢሆንም "በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም የምለው ነገር የለም" ሲል መልሷል።

#Toyota
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቻይናው G-Wagon በደቡብ አፍሪካ መሸጥ ጀመረ

ግሬት ዎል የሚያመርተው የቅንጦት መኪኖች አንዱ የሆነው Cybertank 300 መኪና በደቡብ አፍሪካ መሸጥ ጀመረ :: ከ 17 አመታት በላይ ግሬት ዎል መኪኖቹን እየሸጠ ቢቆይም ይህንን የቅንጦት SUV ለመሸጥ ከቻይና ካምፓኒዎች ቀዳሚ ሆኗል ::

ብዙዎቻችን ቻይና ውስጥ ያሉ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች ለየት ያሉ መኪኖችን የሚያመርቱ አይመስለንም :: ግን ይሄ በጣም እየተቀየረ እየመጣ ነው :: በተለይ ከ 2021 ጀምሮ በብዛት ለሀገር ውስጥም ለውጪ ሀገራትም ማለትም ለአውሮፓ እና ለአፍሪካ ይልካሉ :: ስለዚህ እሱን በማሰብ የ G-Wagen ዲዛይን ያለውን መኪና ለገበያ አቅርቧል :: እኛም እዚህ መኪና ላይ ከወራት በፊት ቪዲዮ ሰርተን ለቀናል ::
ሙሉ ቪዲዮውን ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/XgP15d_sGuQ


#Cybertank #GreatWall
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
#ዜና ከ Tesla Model Y ጋር የሚፎካከረው የ Rivian መኪና ነገ ለእይታ ይቀርባል ከዚህ በፊት የ Rivian ካምፓኒ Rivian R1T እና R1S ያወጡ ሲሆን አሁን ደግሞ ከ Tesla Model Y ጋር ይፎካከራል ብለው ያሰቡትን መኪና ለገበያ ሊያቀርቡ ነው :: በዚህም መሰረት Rivian R2 የተሰኘው ኤሌክትሪክ መኪና ለ 5 ሰዎች መቀመጫ ሲኖረው በአንድ ቻርጅ እስከ 531 ኪሎሜትር ድረስ…
#ዜና

ከ Tesla Model Y ጋር የሚፎካከረው የ Rivian R2 መኪና በተሻለ ዋጋ ቀርቧል


በዚህም መሰረት Rivian R2 የተሰኘው ኤሌክትሪክ መኪና ለ 5 ሰዎች መቀመጫ ሲኖረው በአንድ ቻርጅ እስከ 483 ኪሎሜትር ድረስ መጟዝ ይችላል :: ከ 0 እስከ 100 ኪሎሜትር በሰአት ለመድረስ ከ 3 ያነሰ ሰከንድ ሲፈጅበት ከምንም በላይ ደግሞ የመሬት ከፍታው 248 ሚሊሜትር ሲሆን ይህም ከሱ ጋር ከሚፎካከሩ መኪኖች የተሻለ ያደርገዋል :: መነሻ ዋጋው ደግሞ 45,000 የአሜሪካን ዶላር ነው ተብሏል :: ስለዚህ ትላንት ከተባለው ትንሽ ልዩነት አለው :: ከዚህ መኪና በተጨማሪም R3 እና R3X የተባሉ ሞዴሎችንም ለእይታ አቅርበው ነበር :: ግን ስለዚህ ኤሌክትሪክ መኪና ምን ታስባላችሁ?

#Rivian #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW የቴስላ መኪና ባለቤቶችን የሱን ምርት ወደ ሆኑት የኤሌክትሪክ መኪኖች መኪናቸውን ለሚቀይሩ አሽከርካሪዎች 1000 ዶላር እንደሚከፍል ገለፀ


የጀርመኑ የመኪና አምራች ካምፓኒ BMW በአውሮፓ እና በአሜሪካ ላሉ ቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና መኪናቸው ወደእሱ ምርት ወደ ሆኑት የኤለክትሪክ መኪኖች ለሚቀይሩ አሽከርካሪዎች 1000 ዶላር ክፍያ እና እንደ መኪና ሞዴሎቹ የተለያዩ ቅናሾችን አዘጋጅቶ አቀረበ።

(የ2024ቱ bev conquest program) በሚል ስምአዲስ የማርኬቲግ ስትራቴጂ ይዞ የመጣው BMW ኢላማውን አሜሪካ ላይ ከ70% የኤሌክትሪክ መኪኖች ቁጥር የያዘው ቴስላን አድርጎ ቢሆንም ያቀረቡት ለሌላ የኤሌክትሪክ ብራንድ መኪና ተጠቃሚዎችም ተመሳሳይ ፓኬጅ አቅርቦዋል።

እንደ ካምፓኒው ገለፃ ከሆነ ይሄ ቅናሽ ለአንድ ወር  ማለትም አሁን በያዝነው ማርች ወር ማብቂያ ድረስ የሚቆይ ነው የሚሆነው።

#BMW
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

መኪናዎትን በ 300 ብር ብቻ አስተዋውቀው ይሽጡ

የመኪናዎትን ፎቶ ወደእኛ በመላክ አስተዋውቀው መሸጥ ይችላሉ ::

ክፍያውን በቴሌብር ብቻ የምንቀበል ሲሆን የሚከፈለውም በ 0911663121 ስልክ ላይ ነው :: ድርጅቶችም ከእኛ ጋር መስራት ይችላሉ ደረሰኝ ስለሚያገኙ ::

የመኪናዎትን ፎርሙን የሚሞሉበትን ሊስት እንድንልክሎ እና ለተጨማሪ መረጃ በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም በ @hulemekinaadmin መልእክት ይላኩልን ::

@hulemekina
#ዜና

የገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት ተግባራዊ ሊደረግ ነው


አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦቪድ ግሩፕ የትራንስፖርት ችግርን መፍታት የሚያስችል የኬብል ካር (በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት) ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ታደሰ ፥ ኦቪድ ግሩፕ በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ ቤቶችን ከመገንባት ባሻገር የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት በአዲስ አበባ የኬብል ካር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ የፕሮጀክት ጥናት ማጠናቀቁን ይፋ አድርገዋል።

የባቡር እና የመኪና መሰረተ ልማቶችን ማፍረስ ሳያስፈልግ በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት ወይም ኬብል ካር ቴክኖሎጂን በአዲስ አበባ ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት።

መንግስት የአቅመ ደካማና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ኑሮ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው ፥ ለስኬታማነቱ ኦቪድ እገዛና ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በሁሉም የልማት መስኮች የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱንም ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም ኦቪድ ሀገራዊ ልማትን ከማገዝ ባለፈ በግንባታው ዘርፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የመጠቀምና በአጭር ጊዜ የማጠናቀቅ ስራውን ይቀጥላል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

#AddisAbaba #Transportation
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
#ዜና Apple የኤሌክትሪክ መኪኖች ለማምረት የጀመረውን ጉዞ አቋረጠ ከ2014 ጀምሮ ለአስር አመታት self driving የሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች ለማምረት ብዙ ቢሊየን ዶላሮች በጅቶ ጥናት እና ምርምር እያደረገ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ይህን በማቆም ከ2000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖቹን ለማበልፀግ ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞቹን ወደ ካምፓኒው (Generative AI) ፕሮጀክት ስራ ላይ አንዲዘዋወሩ አደረገ።…
#ዜና

Apple የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምረት ጀምሮት በነበረው ፕሮጀክቱ በአመት 1 ቢሊየን ዶላር ወጪ ያደርግ እንደነበር ተናገረ


ባሳለፍነው ሳምንት ታዋቂው የስልክ አምራች apple ከአስር አመት በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምረት ሲሰራበትን የነበረውን ፕሮጀት ማቆሙ ተዘግቦ ነበር።

አሁን ላይ Bloomberg የዜና ጣቢያ ስለ ጉዳዩ አንዳንድ ዝርዝር መረጃዎችን አጋርቷል።

Apple እንደ Mercedes, Ford, BMW, Volkswagen, Tesla, Canoe, Mclaren ያሉ ታዋቂ የመኪና አምራቾችን አብሮ በፓርትነርነት ለመስራት ጥያቄ አቅርቦ የነበር ሲሆን ግን በመጨረሻም የኤሌክትሪክ መኪኖቹን ብቻውን ለማምረት ወስኖ ( Project Titan)  ብሎ ወደሰየመው ጥናት እና ምርምር ገባ።

ለ ፕሮጀክቱ አመታዊ አንድ ቢሊየን ዶላር ወጪ ያደርግ የነበር ሲሆን ፕሮጀክቱን ሀ ብሎ የጀመረው 2014 ላይ ነበር።

Apple የኤሌክትሪክ መኪኖቹን 2020 ላይ ለገበያ ለማቅረብ አቅዶ የነበር ቢሆንም የተባለው ጊዜ 2020 ሲደርስ ፕሮጀክቱ ገና የ5 አመት ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገው ነበር።

ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጋር ባልተያያዘ ዜና General Motors 2008 ላይ ኪሳራ ውስጥ ገብቶ በነበር ሰአት የappleሉ ceo Steve jobs GMን ለመግዛት ጥያቄ አርቦም ነበር።

#Apple
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

የቲንትድ መስታወት ጥቅም ምንድነው?


1. የመጀመሪያው ሴፍቲ ነው ::
መኪናውን ማን እንደሚነዳ ውስጥ ያለውን ሰው ከውጪ ማንም ማየት አይችልም ::
2. ከፀሀይ እና ከሙቀቱ በደንብ ይከላከላል ::
ስለዚህ መኪናችሁን ፀሀይ ላይ አቁማችሁት ስትመለሱ ሙቀቱ አይሰማችሁም ::
3. የመኪኖቻችሁ ወንበሮች ቶሎ ፌድ እንዳያደርግ ይከላከላሉ ::
4. የመጨረሻው እና ዋንኛው መስታወቶቹ የፋብሪካ ከሆኑ እና የማይላጡ ወይም እስቲከር ካልሆኑ በትራፊክም አትቀጡም ::

እነዚህን መስታወቶች የምታገኙት ደግሞ ከ Omega Auto Glass ነው ::
Omega Auto Glass የፋብሪካ ቲንትድ የፕራይቬሲ መስታወቶችን ለአዳዲስ መኪኖችንም ለቆዩትም ታገኛላችሁ ::
አድራሻ ቁጥር 1 ሀብተጊዮርጊስ ድልድል ወደ አሊያንስ በሚወስደው መንገድ ላይ ፓልሪየስ ጎን
ቁጥር 3 ጎፋ መብራት ሀይል ታገኙናላችሁ ::
ስልክ 0911241153 ወይም
0911609080 ወይም
0925494095 ይደውሉ ::

#OmegaAutoGlass
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/23 10:32:58
Back to Top
HTML Embed Code: