Telegram Web Link
#ዜና

የቻይናው የመኪና አምራች MG የአውሮፓ መኪና ገበያ ላይ ቶዮታን እና ሬኖልትን ሊቀናቀን ነው።


የአውሮፓ የመኪና ገበያ በቻይና የኤሌክትሪክ መኪኖች መጥለቅለቁ እየተወራ ሲሆን በቻይናው SAIC ባለቤትነት ስር ያለው  MG ሞተርስ በአውሮፓ ላይ ያለውን የትናንሽ ሃይብሪድ መኪኖች ገበያ ለመቆጣጠር ማቀዱን ገለፀ።

በአውሮፓ የሚገኘው የ MG የሽያጭ ሃላፊ ለአውቶሞቲቪ ዜናዎች እንደተናገሩት " እቅዳችን በአውሮፓ የሚገኘውን የሀይበርዳይዜሽን ሞኖፓሊ ለመሰባበር ነው" ያሉ ሲሆን ይህ ማለትም የMG  እቅድ ቶዮታን እና ሬኖልትን መቀናቀን ነው።

ከ 86 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው የአውሮፓ የትናንሽ ሃይብሪድ መኪኖች ሽያጭን የተቆጣጠሩት ሁለቱ ካምፓኒዎች ሲሆኑ
MG በዚህ አመት አጋማሽ ላይ MG 3 የተባለውን ሃይብሪድ መኪና ለገበያ ያቀርባል። ከ Toyota yaris እና ከ Renault Clio ሃይብሪድ መኪና በ 4,000 ዶላር ቅናሽ የሚኖረው ሲሆን MG በዚህ አመት ከ 300,000 በላይ መኪኖችን እሸጣለው ብሎ አቅዶዋል።

#MG
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Rimac የቴስላው Roadster መኪና ከ0 እስከ 100 ኪሎሜትር በሰአት ፍጥነት ለመድረስ 1 ሰከንድ ብቻ ይወስድበታል የተባለውን የምር ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል አለ።


በጣም ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪኖችን አምራች ካምፓኒ የሆነው የRimac መስራች እና CEO የሆነው Mate Rimac እንደተናገረው "Elon Musk ባለፈው ስለ Tesla Roadster ከ 0 እስከ 100 ኪሎሜትር በሰአት ፍጥነት ለመድረስ 1 ሰከንድ ብቻ ይወስድበታል' ብሎ የተናገረውን የምር ተግባራዊ ማረግ ይቻላል" 

Mate ከቡድኑ ጋር በመሆን ሲሙሌሽኑን የሰሩት ሲሆን (Thusters) በመጠቀም የተባለውን ፍጥነት ማሳካት ይቻላል

ነገር ግን ብዙ ደካማ ጎኖችም ይኖሩታል ማለትም የነዳጅ መኪና ከሆነ ተጨማሪ የነዳጅ ታንኮች, ኮምፕረሰሮች, ቫልቮች, ኖዝሎች, ሲያስፈልጉት የኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን ደግሞ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ሞተር፣ ኢንቨርተር፣ ጊርቦክስ እና ድራይቭ ሻፍት ይፈልጋል ::

#Rimac #Tesla
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volkswagen, Honda አና Nissan አዲስ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለገበያ አቀረቡ።

Volkswagen አዲሱን የID 7ን station wagon ቨርዥኑን ID 7 Tourer በጀርመን ሃገር ለገበያ ያቀረበ ሲሆን መነሻ ዋጋውም ከ55,000 ዩሮ ጀምሮ ነው።

Honda እንደተናገረው ሁለቱም prologue እና Acura ZDX የአሜሪካ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የሚጣለውን የሙሉ ታክስ ክፍያ መስፈርት($7,000) የሚያሟሉ ሲሆን ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ዴሊቨር መደረግ ይጀምራሉ ::

Prologue  47,400 ዶላር መነሻ ዋጋ ሲኖረው ZDX ደግሞ የ64,500 ዶላር መነሻ ዋጋ አለው።

430 የፈረስ ጉልበት ያለው የ Nissan Ariya Nismo መኪና ለገበያ ቀረበ። እስካሁን ባለው መረጃ የጃፓን ገበያ ላይ ብቻ የቀረበ ሲሆን መነሻ ዋጋውም 57,000 ዶላር ነው።

#VW #Honda #Nissan
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
#ዜና Jaguar የነዳጅ መኪኖችን ሙሉ በሙሉ ማምረቱን ሊያቆም ነው የእንግሊዙ ቅንጡ መኪኖች አምራች የሆነው Jaguar  ምርቱን ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች እየለወጠ ያለ ሲሆን በወርሃ ጁን ላይ  ሙሉ በሙሉ የነዳጅ መኪኖች ማምረቱን ያቆማል። Jaguar እንዳሳወቀው ከሆነ ሁሉ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎቹን ባለ አራት በር ሴዳን የቦዲ ስታይል የሚኖራቸው ሲሆን እስካሁን ካምፓኒው ካመረታቸው መኪኖች በላይ…
#ዜና

የቀድሞ የአመቱ ምርጥ የኤሌክትሪክ መኪና ተብሎ ተሰይሞ የነበረው መኪና ባጋጠመው የባትሪ ችግር በፖሊሶች ትብብር ሊቆም ተገደደ።


ከ62 በላይ አለም አቀፍ ሽልማቶችን የበላው፣ ከዚህ በፊት የአመቱ ምርጥ የኤሌክትሪክ መኪና ተብሎ የተሸለመው Jaguar i-pace አሁን ላይ ነገሮች ጥሩ የሆኑለት አይመስልም።

እነዚህ ሞዴል መኪኖች ብዙ ጊዜ እያጋጠማቸው ባለው ከባትሪ ጋር ተያይዞ ባለ ችግር ምክንያት በእሳት በመያዛቸው እና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወደ ካምፓኒው ተጠርተው(recall) እየተስተካከሉ የነበረ ሲሆን ከሰሞኑን ደግሞ በእንግሊዝ ሃገር በአንድ አሽከርካሪ ላይ የተፈጠረው ክስተት ደግሞ ብዙዎችን አስደንግጦዋል

አሽከርካሪው እንደተናገርው ከሆነ "እንደወትሮው መኪናዬ እያሽከረከርኩ ዳሽ ቦርድ ላይ ባትሪው ላይ ችግር አለ የሚል መልእክት ሲያሳየኝ የመኪናዬን ፍሬን ይዤ ለመቆም ሞከርኩ ነገር ግን መኪናዬ እንደጠበኩት መቆሙ ቀርቶ ይባሱኑ ፍጥነቱን እየጨመረ ሄዶ በ ሰአት 160 ኪሎሜትር መብረር ጀመረ! ያን ግዜ ነበር ወደ አደጋ ጊዜ ጥሪ መቀበያው SOS የደወልኩት።"
የእንግሊዝ ፖሊሶች ባረጉት ጥረት እና በተጠቀሙት ታክቲካዊ ስልቶች መኪናውን ሹፌሩ ሳይጎዳ ማቆም የቻሉት።

ጃጓር እነዚህ መኪኖች ከባትሪ ችግር ጋር ተያይዞ እራሳቸውን በእሳት እያያዙ በመሆናቸው ሙሉ በሙሉ ወደ ካምፓኒው ተጠርተው ማስተካከያ እስኪደረግባቸው እቤት ውስጥ ወይም ህንፃዎች ስር መኪኖቹ ቻርጅ ማድረግ እንደሌለባቸው ያሳወቀ ሲሆን ማስተካከያ ተደርጎባቸዋል ተብለው ወደ ባለቤቶቻቸው የተመለሱት መኪኖችም ሳይቀር እራሳቸውን በእሳት ማያያዛቸው ተሰምቶዋል።

ይሄን አስመልክቶ ጃጓር በዚሁ ከቀጠለ በመጪው 5 አመታት ውስጥ ከባድ ኪሳራ እንደሚገጥመው ተነግሪዋል።

#Jaguar
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BYD በጃፓን በተደረገው የአመቱ ምርጥ የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማት ላይ የ 1ኛ እና 3ኛ ደረጃን ያዘ።


የቻይናው የመኪና አምራች BYD በ2023ቱ የጃፓን የአመቱ ምርት የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማት ላይ BYD Dolphin የተባለው ሞዴሉ የአንደኝነቱን ደረጃ ይዞ ሲያሸንፍ BYD Atto 3 ደግሞ የሶስተኝነቱን ደረጃ ይዞዋል።

ከአንድ እስከ 3 ባለው ደረጃ ውስጥ የትኛውም የጃፓን ምርት የሆነ መኪና ያልገባ ሲሆን የሁለተኛነቱን ደረጃ እራሱ የያዘው የኮሪያ ምርት የሆነው Hyundai kona ነው።

ገበያ ላይ የጃፓን ምርት የሆኑ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎች እጥረት ያለ ሲሆን ውድድሩ ላይ ከተሳተፉ 18 መኪኖች ውስጥም የጃፓን ምርት የሆኑት አራቱ ብቻ ናቸው።

#Japan #BYD
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ford የኤሌክትሪክ መኪኖቹን በጊዚያዊነት ማምረቱን ገታ ባደረገበት ወቅት የኤሌክትሪክ መኪናዎቹ ሽያጭ ላይ የ 81% እድገት ታየ።


የአሜሪካው የመኪና አምራቹ ford የኤሌክትሪክ መኪኖቼ ያን ያህል እየተሸጡልኝ አይደለም፣የምርት ሂደቱን ትንሽ እገታዋለው፣ አዲስ ማምረቻዎችን መገንባቴን ለትንሽ አመታት አዘገየዋለው ብሎ የነበር ሲሆን ገበያው ላይ ግን ሽያጫቸው በ 81% እድገት አሳየ።

2024 ላይ ባሳለፍነው February ወር ላይ
Ford F-150 lightning በተባለው የኤሌክትሪክ ፒክ አፕ ትራክ ላይ 2,600 መኪኖች
Ford Mustang Mach-E በተባለው የኤሌክትሪክ SUV መኪናው ላይ ወደ 2,930 መኪኖች እና
Ford E-Transit በተባለው የኤሌክትሪክ ቫን ላይ 860 መኪኖች
በድምሩ 6,390 የኤሌክትሪክ መኪኖችን በአንድ ወር ውስጥ ሽጠዋል።

#Ford
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
#ዜና Honda fuel cell (ኬሚካል ኢነርጂን ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል የሚቀይር)  የኤሌክትሪክ CR-V አቸውን አስተዋወቁ። Toyota Mirai የተባለው መኪናው ላይ ወደ 40,000 ዶላር ያህል መነሻ ዋጋ ሲኖረውየነበረውን 60% ቅናሽ በማድረግ 12,000 ዶላር እየሸጡ ሲሆን Honda በfuel cell ተንቀሳቃሽ የሆነውን CR-V ቨርዥናቸውን ለማስተዋወቅ ቆንጆ አጋጣሚ ሆኖላቸዋል ። አሜሪካ…
#ጠቃሚ_መረጃ

የቶዮታ ሃይሮጅን መኪና Toyota Mirai መጠቀም የቴስላ ኤሌክትሪክ መኪኖች ከመጠቀም 14 እጥፍ ውድ ነው ተባለ።


GM እና Honda  በጋራ በመሆን የሃይድሮጅን መኪናዎችን እያበለፀጉ መሆናቸውን ያሳወቁ ሲሆን እንደዚሁ ቶዮታ እና ሆንዳ የራሳቸውን የሃይድሮጅን መኪና ለገበያ አቅርበዋል። Hyundai የሃይድሮጅን መኪኖችን (feature cars ) ብሎ የሰየማቸው ሲሆን BMW ደግሞ 2040 ላይ በአለም ደረጃ ዋና የመጓጓዣ መንገድ የሚሆኑት የሃይድሮጅን ተሽከርካሪዎች ናቸው ሲል ተደምጦዋል።

ነገር ግን አሁን ላይ መኪናውን ስትገዙ ለ 2 አመት ነፃ የሃይድሮጅን ጋዝ የሚያቀርብላቹን Toyota Mirai መጠቀም የቴስላ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ከመጠቀም በ14 እጥፍ ወጪ አለው። አሁን ላይ በአሜሪካ በሚገኙ ሁሉም የሃይድሮጅን ነዳጅ ማደያዎች ውስጥ 1 ኪሎ ሃይድሮጅን ጋዝ ዋጋ 36 ዶላር ሲሆን ከ 2 አመት በፊት 2021 ላይ 13 ዶላር ብቻ ነበር።

እንደምሳሌነት የ Toyota Mirai 6 ኪሎግራም ታንክን ለመሙላት ወደ 216 ዶላር ወጪ ሲኖርብን ይህም ማለት 1 ማይል ወይም 1.6 ኪሎሜትር ጉዞ ለማድረግ 0.5 ዶላር / በየሁለት ማይል(3.2 ኪሎሜትር) ጉዞ 1 የአሜሪካ ዶላር ያሶጣናል።

በአንፃሩ ባለ 60 Kwh ባትሪ Tesla model 3 ቻርጅ ለማድረግ 12 ዶላር ሲያሶጣን ቴስላ ሞዴል 3 በዚህ ባትሪ ፓክ ወደ 333 ኪሎሜትር ጉዞ ማድረግ የሚችል ሲሆን ይህ ማለትም ለአንድ ማይል ወይም ለ 1.6 ኪሎሜትር ጉዞ ለማድረግ 0.036 የአሜሪካን ዶላር ብቻ ያሶጣናል።

#Toyota #Tesla
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ተጠንቀቁ‼️

በመኪና የሚሞተው ሰው ከ 93 ሰው አንድ ሰው ነው

በአውሮፕላን አደጋ የሚሞት ሰው በጣም ጥቂት ነው :: ይህም የሆነው አንድ ሰው በአማካይ አውሮፕላን ውስጥ የሚቆይበት ሰአት ትንሽ ስለሆነ ነው :: ከሱም በተጨማሪ ፕሮፌሽናል የሆኑ ፓይለቶች ስለሚቆጣጠሩት ነው :: ግን ወደ መኪና ስንመጣ አሁን ላይ አብዛኛው ሰው በየእለት ተእለት እንቅስቃሴው መኪና ይጠቀማል :: ይህም በጥንቃቄ ካልተነዳ ለከፋ አደጋ ያደርሰናል :: የሞቱት ቤተሰብ ህይወት ብቻ ሳይሆን የእኛን እና የቤተሰባችንንም ህይወት ይጎዳል :: ዛሬም የተፈጠረው ይህ ነው ::

ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ሰሜን ማዘጋጃ ዝቅ ብሎ /ያዳም ዘውድ ሆቴል ፊትለፊት / የተፈጠረ ግጭት ሲሆን ሁለት እግረኞችም ህይወታቸው አልፏል፡፡ እባክዎ! አሽከርካሪዎች በማስተዋል ያሽከርክሩ ::

በተለይ ደግሞ አዳዲስ እና ኤሌክትሪክ መኪኖች የምትነዱ ሰዎች መኪኖቹ ፈጣን ስለሆኑ ብቻ አትፍጠኑ :: እግረኞችም በግድ የለሽነት ማቋረጥ የለባችሁም ::

#AddisAbaba #Accident
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

መኪናዎትን በ 300 ብር ብቻ አስተዋውቀው ይሽጡ

የመኪናዎትን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶ) ወደእኛ በመላክ በቲክቶክ, በኢንስታግራም እና በቴሌግራም አስተዋውቀው መሸጥ ይችላሉ ::

ክፍያውን በቴሌብር ብቻ የምንቀበል ሲሆን የሚከፈለውም በ 0911663121 ስልክ ላይ ነው :: ድርጅቶችም ከእኛ ጋር መስራት ይችላሉ ደረሰኝ ስለሚያገኙ ::

የመኪናዎትን ፎርሙን የሚሞሉበትን ሊስት እንድንልክሎ እና ለተጨማሪ መረጃ በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም በ @hulemekinaadmin መልእክት ይላኩልን ::

@hulemekina
#ዜና

የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ሽያጭ ቢቀንስም እየተደረገባቸው ያለው ኢንቨስትመት ግን አሁንም ትልቅ የሚባል ነው።


(Environmental defense fund) እንዳጋረው መረጃ ከሆነ ከ2021 ጀምሮ እስካሁን በመላው አለም የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ፈሰስ እየተደረገ ያለው መዋለ-ንዋይ 529 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከ2016 እስከ 2020 ባለው አመት 191 ቢሊየን ዶላር ብቻ ነበር።

ግራፉ ላይ እንደምትመለከቱት ከቻይና ይልቅ ሌሎች ሃገራት በእነዚህ አመታት ከፍተኛ የ EV ኢንቨስትመንት እድገት ያሳዩ ሲሆን አንዳንድ ሃገራት በ90% ያህል መሻሻልን አሳይተዋል።

የመኪና አምራቾች አሁን የኤክትሪክ መኪኖች ላይ ያለውን የሽያጭ መቀነስን አስመልክቶ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የሚያረጉትን ኢንቨስትመት ወቅቱን ባማከለ ሁኔታ ማሻሻያ እንደሚያደርጉበትም አሳውቀዋል።

#electric #investment
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volkswagen ID.3 ኤሌክትሪክ መኪናን በጀርመን ለመስራት ያለውን ሀሳብ ሰርዟል

የ VW ID.3 ኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ሽያጭ እየቀነሰ ስለሆነ ምርቱን ማቋረጡ ተዘግቧል ::

ቀደም ሲል በብዛት በመስራት እና በማስቀመጥ ለመሸጥ አስበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ግን የ 10 ቢሊየን ዩሮ የገንዘብ ቅነሳ ለማድረግ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት እያሰቡ ስለሆነ በጀርመን ዎልፍስበርግ በሚገኘው የመኪና ማምረቻቸው የነዳጅ እና ሀይብሪድ መኪና ምርቶቻቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ::

#Volkswagen #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በጀርመን በርሊን የሚገኘው የቴስላ መኪና ማምረቻ ከተጠበቀው ጊዜ ቀደም ብሎ ወደ ስራ የሚመለስ ይመስላል።


ባለፈው ሳምንት አክራሪ የተፈጥሮ ተሟጋቾች በርሊን የሚገኘው የቴስላ ማምረቻ ፓወር ስቴሽን ላይ እሳት በማስነሳት ጥቃት አድርሰው የነበር ሲሆን ጥቃቱ ሙሉ በሙሉ ማምረቻው ስራ እንዲያቆም አስገድዶት ነበር።

ቴስላ የዛሬ ሳምንት ወደ ስራ እመለሳለው ብሎ የነበረ ሲሆን የፖወር ካምፓኒው የሃይል መቋረጥ ችግሩን በዛሬው እለት የተፈታለት ሲሆን ከጠበቀው ጊዜ ቀደም ብሎ ወደ ስራ ሊመለስ ይችላል።

ማምረቻው ስራ ማቆሙ ቴስላን በቀን 1000 መኪና ምርት ያሳጣው ሲሆን የማምረቻው ሃላፊ እንደተናገሩት "ጥቃቱ ካምፓኒውን የሶስት አሃዝ ሚሊየን ዩሮዎች ኪሳራ አድርሶበታል።"

#Tesla
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በአውስትራሊያ የሚገኙ የመኪና አምራቾች ሃገሪቷ ያወጣችውን የነዳጅ ህግ ተቃወሙ


ባለፈው ወር ላይ የአውስትራሊያ መንግስት የኤሌክትሪክ መኪኖችን በጎዳናዎቿ ለማስፋፋት በማሰብ የካርበን ልቀታቸው ከፍተኛ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገሪቷ የሚያስገቡ ወይም የሚያመርቱ የመኪና አምራቾች ላይ ቅጣትን ለመጣል በምትኩ የካርበን ልቀታቸው አናሳ ወይም የሌላቸው  መኪኖችን የሚያመርቱ ወይም የሚያስገቡ አምራቾችን እንደምትሸልም የገለፀች ሲሆን

(Federal chamber of automotive industries)  የሚባለው የአውስትራሊያ የመኪና አምራቾችን የሚወክለው ቡድን አዲሱን ህግ እና እቅድ "የዋጋ ንረትን ያስከትላል፣ አማራቾችንም ያጠባል ለዚህም መንግስት ይሄን ህግ ማስተካከል አለበት" ሲል ትችቱን ሰንዝሯል።

በሃገሪቷ ብዙ የሚባሉ ፒክ አፕ ትራኮችን እና SUV መኪናዎችን የሚሸጠው ቶዮታ ቡድኑን የደገፈ ሲሆን እንደ tesla, polestar, እና Volkswagen ያሉ የመኪና አምራቾች ቡድኑን ተቃርነው "እንደዚህ አይነት ጠንካራ ህግ መኖር አለበት" ሲሉ መንግስትን ደግፈዋል።

#Australia
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

General Motors የ ኤሌክትሪኩን Chevrolet Blazer መኪና ዳግም ወደ ገበያ አቀረበው


መኪናው በትክክል እንዳይሰራ እያረገው የነበረውን የሶፍትዌር ችግር ለማስተካከል ሲሉ ለወራት ሞዴሉ ላይ የነበረውን ሽያጭ አቁመው ኢንጂነሮቹ ሲሰሩበት ነበር።

የBlazer ሶፍትዌር ተሰርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ መኪናው  ለገበያ ከመቅረቡ በፊት አዲስ የመጣው የ GM High-tech የሶፍትዌር አበልፃጊ ቡድን ማሻሻያ አድርጎበት የነበር ሲሆን

አሁን ላይ ሶፍትዌሩ ከመኪናው ጋር ተስማሚ እንዲሆን እና መኪና ውስጥ ያሉ ፊቸሮችን አሽከርካሪዎች በደንብ እንዲገለገሉበት ሲሉ በአዲስ መልክ አዘጋጅተውታል። ይህን ለማድረግም በቀን 40 Blazer መኪኖች ከ600 km በላይ እንዲጓዙ በማድረግ መረጃዎችን ሰብስበዋል።

ዳግም የገዢዎችን ቀልብ ለመሳብ ሲሉም ሞዴሉ ላይ ወደ 6,500  ዶላር ቅናሽ በማድረግ በ50,000 የአሜሪካን ዶላር ለገበያ አቅርበውታል ።

#GM #Blazer
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Porsche የተሻሻለውን አዲሱ Taycan መኪና ሞዴሉ ይፋ አደረገ።


የቅንጡ መኪኖች አምራቹ porsche የተሻሻለውን የTurbo GT ቨርዥኑን ታይካን ትናንት ያስተዋወቀ ሲሆን weissach ፓኬጅ የሚባል የፐርፎርማንስ ፓኬጅም አብሮ ይፋ አድርጎዋል ።

Taycan ከTurbo GT ጋር የስታይል ልዩነት ባይኖራቸውም እንደ  የጀርባ ሞተር እና  Pulse Inverter ያሉ ፓርቶቹ ጉልበቱን ወደ 580 Kw(Kilowatt) ወይም 777 የፈረስ ጉልበት ሲያሻሽሉት (launch control) ሲጨመርበት ደግሞ ጉልበቱን በ2 ሰከንድ ውስጥ ወደ 760 Kw(kilowatt) ወይም 1019 የፈረስ ጉልበት መድረስ እንዲችል ሲያረገው ይህም በሰአት 100 ኪሎሜትር ፍጥነት ላይ ለመድረስ 2.3 ሰከንድ ከሚወስድበት ከTurbo GT፣ 2.2 ሰከንድ ከሚወስድበት አዲሱ weissach ፓኬጁ አንፃር በሰከንዶች ሽርፍራፊም ቢሆን አነስ ያለ ጊዜ ነው የሚወስድበት።

weissach ፓኬጁ ላይ ይበልጥ ጠርዝ ተቀንሶበት የቀረበ ሲሆን (front diffuser) የፊት አየር መሰንጠቂያው, (side winglets) የጎን ክንፎች እና ተለቅ ያለ (rear wing) የኋላ ክንፍ ሲኖሩት በተጨማሪ ታስቦ ለተሰራበት የውድድር track ላይ አስፈላጊ ያልሆኑ  እንደ ኋላ ወንበር ያሉ ክፍሎችን አሶግደውለታል።

ይህም ከነበረው ክብደት ላይ 75 ኪሎግራም እንዲቀንስ አርጎታል።

#Porsche
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Mack ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ሲስተምን አስተዋወቀ።


የከባድ ጭነት ተሸካሚ ተሽከርካሪዎች አምራች የሆነው Mack የኤሌክትሪክ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ማሽከርከር ምን እንደሚመስል ለአከፋፋዮች እና ለተጠቃሚዎች ለማስሞከር ሲል መሞከሪያ የኤሌክትሪክ ተሳቢን ሰራ።

የፕሮፔን ጀነሬተር እና 140kw ቻርጀርን MD የተሰኘው የelectric ተሳቢው ጀርባ ላይ በመግጠም ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀርን ያዘጋጀ ሲሆን ይሄን የሰራበት ምክንያትም አስፈላጊው መሰረተ ልማት ባልተሟላባቸው ቦታዎች ላይ ሌሎች የሙከራ የኤሌክትሪክ ተሳቢዎችን ቻርጅ ለማድረግ በማሰብ ነው።

በዚህ ዝግጅት ላይም አሽከርካሪዎች MD የኤሌክትሪክ ተሳቢን መንዳት ምን እንደሚመስል እንዲያውቁ የሚያደርጉ ሲሆን የኤሌክትሪኩ MD 240 Kwh ባትሪ ፓክ ሲሆን በዚህ የባትሪ አቅሙም በአንድ ቻርጅ እስከ 370 ኪሎሜትር ይጓዛል።

Mack እንደተናገረው ከሆነም ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀሩን ለተጠቃሚዎች የማቅረብ ምንም እቅድ የለውም።

#Mack #Charger
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

LFP ባትሪ የተገጠመለት፣በ20,000 የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ለገበያ ይቀርባል የተባለው MG2 በመስራት ላይ ነው ያለው።


ዋጋው ለብዙ ሰው ተመጣጣኝ ይሆናል የተባለው የ MG ኤሌክትሪኩ ሃች ባክ MG2 ቀጣይ አመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን በዋጋ አሁን ካለው MG4 እራሱ ያነሰ እንደሚሆን የተናገሩ ሲሆን ይገጠምለታል የተባለው አዲሱ የLFP (Lithium iron phosphate) ባትሪ የ500 Kwh ቻርጂንግ ስፒድ ሲኖረው አስከ -20°c ባለ ቅዝቃዜ ውስጥም ካለምንም እክል መስራት ይችላል።

MG2 ገበያው ላይ ላሉ እንደ የአውሮፓው ቨርዥን BYD dolphin፣ Citroen c3, Peugeot 208, Renault 5 እና ምናልባት የቴስላው ሞዴል 2 ተቀናቃኝ ይሆናል።

#MG #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
BZ3.pdf
504.1 KB
Toyota BZ3 ኤሌክትሪክ መኪና

የመጀመሪያው በሴዳን ቦዲ ስታይል በቶዮታ ብራንድ የቀረበው ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ መኪና BZ3 Toyota ከ BYD እና FAW ጋር በመሆን ነው ያመረተው መኪና ነው። ባትሪ እና ሞተር ከ BYD የተወሰደ 50 ወይም 65kwh ብሌድ ባትሪ ፓክ በአንድ ቻርጅ ከ 517 እስከ 616 ኪሎሜትር መጓዝ የሚችል FWD በሆነው 180 kw ሞተሩ እስከ 245 የፈረስ ጉልበትን ያመነጫል። 3 አይነት Trim Level ሲኖሩት
1. Elite Pro ( 49.92 Kwh, 135 (Kilowatt) ሞተር እና 517 ኪሎሜትር ሬንጅ)
2. Long Battery Life Pro ( 65.28 Kwh, 180 (Kilowatt) ሞተር እና 616 ኪሎሜትር ሬንጅ)
3. Long Battery Life Premium ( 65.28 Kwh, 180 (Kilowatt) ሞተር እና 616 ኪሎሜትር ሬንጅ)

ተጨማሪ ልዩነቱን PDF ላይ በዝርዝር ታገኙታላችሁ ::

#Toyota #BZ3
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ የሞዴል 3 Ludicrous እንደ ኪሎሜትር ሬንጁን እና የፍጥነት መጠኑ ያሉ መረጃዎችን ይፋ አረገ።


Tesla model 3 Ludicrous ሁለት ሞተር ያለው ሲሆን ከፊት ያለው ሞተሩ 212 የፈረስ ጉልበትን ሲያመነጭ ከኋላ ያለው ያለው ሞተሩ ደግሞ 406 የፈረስ ጉልበትን በማመንጨት በድምሩ 618 የፈረስ ጉልበትን ለመኪናው ሲሰጡት በዚህ የሞተር አቅሙ ፍጥነቱ ከ0 - 100 ኪሎሜትር በሰአት ለመድረስ 3.2 ሰከንድ ብቻ ይወስድበታል።

ከፍተኛ ፍጥነቱም በሰአት 261 ኪሎሜትር ሲሆን በአንድ ቻርጅ እስከ 500 ኪሎሜትር የሚደርስ ጉዞን ማከናወን ይችላል።

ሞዴል 3 Ludicrous ከ ቤዝ ወይም ዝቅተኛው ሞዴሉ የ 30% ዋጋ ጭማሪ እንደሚኖረው የተናገሩ ሲሆን የመሸጫ ዋጋውም ከ 55,000 - 60,000 የአሜሪካ ዶላር ባለው ውስጥ ይሆናል ብለዋል።

#Tesla #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/23 12:23:35
Back to Top
HTML Embed Code: