Telegram Web Link
Air Conditioner እንዴት ተጀመረ? አሁንስ ምን ጋር ነው?

AC ቅርብ ጊዜ የተጀመረ ለሚመስላችሁ በጣም የቆየ ነው :: ማለትም ከ 2ኛው የአለም ጦርነት በፊት ነገር ግን እየተሻሻለ አሁን ያለበት ቦታ ደርሷል :: የሚጠቀመውም ጋዝ ከ Rበፊቱ የተለየ ነው :: ግን ለምን አሁን ወዳለው ጋዝ ሊቀይሩ ቻሉ? እንዴት ተጀመረ? አሁን የደረስንበት ቴክኖዎሎጂ ምን ጋ ነው? የሚለውን በዝርዝር በዛሬው ቪዲዮ እናያለን ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/Lwlc1InuWMI

በጣም እናመሰግናለን 50 ሺህ ሰብስክራይበርስ አልፈናል ዩትዩብ ላይ :: በ 2023 አንዳንድ ፕሮጀክቶችንም አስበናል ቀስ በቀስ የምታዩት ይሆናል :: በቃ አናንዛዛባችሁ ዩትዩብ ላይ ቪዲዮውን ተመልከቱት ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#AC
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪኖች በየጥጉ እንደዚህ ቆመው አቧራ እየጠጡ የቆሻሻ ማከማቻ ሆነው እናያለን :: ግን ደግሞ ትንሽ እድሳት ቢደረግላቸው ተመልሰው መነዳት የሚችሉ ብዙ መኪኖች አሉ :: ስለዚህ ይህንን በማሰብ መኪኖችን እያደስን እንደ Series ብዙ ቪዲዮ ለመስራት ስላሰብን እንደዚህ የተቀመጡ መኪኖቻችሁን መሸጥ ከፈለጋችሁ ገዝተን አልያም ደግሞ አብረናችሁ ለማደስ ስለምንፈልግ እንደዚህ አይነት መኪና ያላችሁ ሰዎች @Yonathandesta ላይ የመኪናውን ፎቶ እና የሚሸጥ ከሆነ ደግሞ ዋጋውንም አንድ ላይ ላኩልን ::

መልካም ቀን ተመኘን
#CarsforSale #OldCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከአቫታር ፊልም ላይ ሀሳብ በመውሰድ የተሰራ አስገራሚ የኮንሴፕት መኪና

Mercedes Vision AVTR

በ 2 አመት ውስጥ ዲዛይን የተደረገው ይህ አስደናቂ መኪና እያንዳንዱ የጨመሯቸው ነገሮች ከፊልሙ ሀሳብ ጋር ይሄዳሉ :: ዲዛይኑ ፣የበሩ አከፋፈት ከጀርባ ያሉት ስከሎች ፣የጎማው ዲዛይን ውስጡ ላይ ደግሞ ያለው እስክሪን እና መኪናው የሚነሳበት መንገድ ከፊልሙ ሀሳብ የተወሰዱ ናቸው :: በዛሬው ቪዲዮ ስለሱ የምናይ ይሆናል :: ሙሉ ቪዲዮ ዩትዩብ ላይ ተለቋል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/X32e_YLzziY

ውብ ምሽት ተመኘን
#Mercedes #Avatar
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህ መኪና በአንድ ቻርጅ 700 ኪሎሜትር ይጟዛል
2024 VW ID.7 Review

ይሄ በ ID Family ውስጥ የሚገኝ አዲስ መኪና ነው :: ID.7 ከ ID.6 ተለቅ ያለ SUV ይሆናል ብላችሁ ስትጠብቁ ከነበረ ተሳስታችሗል :: VW ID.7 ከ Hyundai Ioniq 6 ጋር የሚፎካከር ኤሌክትሪክ መኪና ነው :: በአንድ ቻርጅ 700 ኪሎሜትር መጟዝ የሚችል ነው :: ከ ID.6 በጣም የተሻሻለ ቴክኖዎሎጂ እንዲሁም የተሻለ የውስጥ ቦታ አለው :: ግን ሌላስ ምን ፊቸሮች አሉት :: በዛሬው የዩትዩብ ቪዲዮ በጥልቀት እናያለን ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/j8Ke_M6x_cQ

ግሩም ምሽት ተመኘን
#VW #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
@Hulemekina
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ
በዓሉ የሰላም እና የደስታ በዓል ይሁንላችሁ

መልካም በዓል

@OnlyAboutCarsEthiopia
ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም ገባ።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው የዋጋ ክለሳ ዝቅተኛ ገቢ ላለው ሕብረተሰብ የሚሰጠው ድጎማ እንዲጨምር መደረጉንም ገልጿል።

በዚህም በአንድ ሊትር ቤንዚን ሲሰጥ የነበረው ድጎማ ከብር 15 ከ 76 ሳንቲም ወደ ብር 17 ከ 33 ሳንቲም እንዲሁም የአንድ ሊትር ናፍጣ ድጎማ ከብር 19 ከ02 ሳንቲም ወደ ብር 22 ከ 68 ከፍ እንዲል መደረጉ ተገልጿል።

በቀጣይ ፤ ሦስተኛ ዙር እና ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ÷

- ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም፣

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ብር ከ 30 ሳንቲም

- ኬሮሲን በሊትር 67 ብር ከ30 ሳንቲም

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ67 ሳንቲም፣

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 48 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 67 ብር ከ91 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡

ምንጭ - tikvahethiopia

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Fuel #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከ 2023 እስከ 2025 የሚወጡ 11 አዳዲስ አጟጊ መኪኖች

የመኪና አምራቾች ከገበያ እኩል ለመቀጠል እንዲሁም ከሌሎች የመኪና አምራቾች ጋር ለመወዳደር ወይም የተሻሉ ሆነው ለመገኘት በየጊዜው አዳዲስ መኪኖችን ይለቃሉ :: ስለዚህ በዛሬው ቪዲዮ ከ 2023 - 2025 ድረስ ከሚወጡ መኪኖች 11 አጟጊ ያልናቸውን መኪኖች ይዘን ቀርበናል :: ተከታተሉን
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/07fKu9RR8f8

ውብ ምሽት ተመኘን
#NewCars #2023
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም በፍቅር በጤና አደረሳችሁ አደረሰን መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ!

መልካም በዓል ተመኘን 🙏
@OnlyAboutCarsEthiopia
የኤሌክትሪክ መኪኖች ጥገና እና ቻርጀር ገጠማ

የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ሪቪው ለመስራት በሄድንበት ጊዜ ብዙ ሰው የኤሌክትሪክ መኪና የተሻለ ነው ሲባል ገዝቶ ግን የት እንደሚያሰራ ግራ ገብቶታል :: እንዲሁም ደግሞ መኪኖቹ የሚያሷዩትን ችግሮች ባለን የ OBD2 መሳርያ የምናስተካክል ሲሆን አዲስ ኤሌክትሪክ መኪኖች ገዝታችሁ በሚያውቅ ባለሙያ ማስገጠም ከፈለጋችሁ በ 0911663121 ላይ በመደወል የጥገና ኢንስፔክሽን የቻርጀር ገጠማ ከማብራርያ ጋር እና ያገለገለም አዲስም ሆነ ያገለገለ ኤሌክትሪክ መኪና ስትገዙ የፍተሻ አገልግሎት በተለይ ደግሞ የቮልስ መኪኖች ከሆኑ እነዚህን አገልግሎቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እኛ ጋር ታገኛላችሁ ::

ግሩም ቀን ተመኘን
#EV #Hulemekina
@OnlyAboutCarsEthiopia
የቆሙ የቆዩ ያገለገሉ መኪኖችን ያላችሁ እና መሸጥ ለምትፈልጉ

መኪኖች በየጥጉ እንደዚህ ቆመው አቧራ እየጠጡ የቆሻሻ ማከማቻ ሆነው እናያለን :: ስለዚህ እነሱን እያደስን ቪዲዮ በመስራት ማደስ ስለምንፈልግ እንደዚህ የተቀመጡ መኪኖቻችሁን መሸጥ ከፈለጋችሁ ገዝተን ለማደስ ስለምንፈልግ እንደዚህ አይነት መኪና ያላችሁ ሰዎች በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም @Yonathandesta ላይ የመኪናውን ፎቶ እና የሚሸጥ ከሆነ ደግሞ ዋጋውንም አንድ ላይ ላኩልን ::

ልዩ ከሰአት ተመኘን
#CarsforSale #OldCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
በተደጋጋሚ ስትጠይቁን ለነበራችሁ መኪናን በብድር ለመግዛት ለምን ከባድ ሆነ ለሚለው ምላሽ

ባንኮች አዳዲስ የብድር ማመልከቻዎችን ለጊዜው እንዲያቆሙ ያስገድዳቸዋል። ብዙ ቅርንጫፎች ብዙ ቼኮችን በማካሄድ ላይ ችግር እያጋጠማቸው ነው እና ቀደም ሲል ለተፈቀደላቸው የብድር ጥያቄዎች ብድር በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ለዛም ነው በብድር መኪና ለመግዛት አስቸጋሪ የሆነው ::

ምንጭ፡- ሪፖርተር

ግሩም ቀን ተመኘን
#Loan
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከ ID.4 በምን በምን ይሻላል?

የ 2022 Mazda CX-30 ኤሌክትሪክ መኪና

አብዛኛዎቹ እኛ ሀገር የሚመጡት መኪኖች በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ ቻይና ውስጥ ተገጣጥመው ወይም ደግሞ ተስርተው የሚመጡ መኪኖች ናቸው :: ከእነዚህ መኪኖች አንዱ Mazda CX-30 ኤሌክትሪክ መኪና ነው :: ይህ መኪና ለቻይና ገበያ ብቻ ስለሚሰራ እነዚህ መኪኖች ላይ መረጃ እንደመፈለግ ከባድ ነገር የለም መኪናውን በአካል ሄጄ ካስተዋልኩት ነገሮች እንዲሁም ከ ID.4 ጋር እያነፃፀርን በዛሬው ቪዲዮ እናያለን :: የተሻለበትንም ምክንያት አሳያችሗለሁ እንዲሁም ደግሞ የማይሻልበት ነገርም አለ እሱንም አብረን እናያለን ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/VSF7rmKKazQ

ስለቴክ ፊቸሮቹ ደግሞ በቅርብ ቀን በቲክቶክ እንለቃለን ::


ብሩህ ምሽት ተመኘን
#Mazda #Electric
@OnlyAboitCarsEthiopia
Job Title: Content Writer (Social Media Manager)

Job Type: Intern (Unpaid)

Work Location: Anywhere/remote

Vacancies: 1

Description: We are seeking a highly motivated and creative Content Writer Intern to join our team and assist in creating compelling and engaging content for our social media.

Responsibilities:

- Research and write scripts for Youtube, Tiktok and Instagram.
- Collaborate with the creative team to develop and pitch new video ideas
- Assist in the editing and post everyday on Telegram and Facebook
- Utilize SEO best practices to optimize titles, descriptions, and tags for discoverability
- Stay current with industry trends and best practices in digital media
- Attend team meetings and contribute ideas for future video projects
- Any other duties assigned by the Content Manager

Requirements:

- Strong writing skills and the ability to write in different styles and formats
- Knowledge of SEO and digital marketing best practices
- Strong organizational skills and ability to manage multiple tasks simultaneously
- Strong verbal and written communication with entertaining skills
- Strong teamwork skills and ability to work in a fast-paced environment

Education and Experience:

Currently enrolled in a related field of study (e.g. Marketing, Car Stuff, Media Studies)
Experience with digital media
Mostly works with Amharic content and scripts and can handle translation

If you fulfill the requirements
Contact us - @ArielAtom4s

From: @OnlyAboutCarsEthiopia
ከዛሬ 137 አመት በፊት ነበር በትላንትናው እለት 1886 ላይ Carl Benz የመጀመሪያውን የመኪና ንድፍ ያስመዘገበው :: የመኪኖች ውልደትም ያኔ ነው የጀመረው :: አሁን ላይ ምን ጋር እንደደረሰ የምናውቀው ነው :: ወደፊት ደግሞ ምን ጋር እንደሚደርስ ማየት ነው ፈጣሪ እድሜ እና ጤና ይስጠን

መልካም ቀን ተመኘን
#CarFacts #Mercedes
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቶዮታ በ2022 10,610,604 መኪኖች በመሸጥ ቀዳሚ ሆኗል :: ቮልክስዋገን ግሩፕ 8.3 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን በመሸጥ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ።

ግሩም ቀን ተመኘን
#Toyota #VW
@OnlyAboutCarsEthiopia
መንግስት ነዳጅ የሚጠቀሙ መኪኖች ላይ የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ለማፅደቅ እየሰራ ይገኛል

በዚህም መሰረት አዲስ መኪኖች ማለትም እስከ 1 አመት ድረስ ያሉ እና እስከ 4000 ኪሎሜትር የተጟዙ መኪኖችን ስታስገቡ በሚሻሻለው ኤክሳይስ ታክስ መሰረት ከ 1500 cc በታች 10%, ከ 1500cc እስከ 2500cc 20%, ከ 2500cc እስከ 3000cc 30%, ከ 3000cc በላይ ደግሞ 60% እንደሚሆን ገልጸዋል :: በዚህ ሁለት ሳምንት ውስጥ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል :: እሱ ሲወጣ ደግሞ የምንገልጽ ይሆናል ::
ተጨማሪ መረጃዎችን በቲክቶክ እና በዩትዩብ ፔጃችን ላይ የምንለቅ ነው የሚሆነው ::

ፍክት ያለ ቀን ተመኘን
#Ethiopia #Excisetax
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው Toyota BZ4X መኪና ነው ::

Toyota ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም አቀፍ ገበያ ከዲዛይኑ ጀምሮ ለኤሌክትሪክ መኪና ብሎ የሰራው መኪና ነው :: እንደእድል ሆኖ በሌላ ስራ ምክንያት የመኪናውን አስመጪ የማግኘት እድል አግኝቼ መኪናው እንደገባ በደንብ ሳይታወቅ ነው የሰራሁት :: ያመጡትም ትልቁን ትሪም ሌቭል ስለሆነ በጣም ለየት ያሉ ፊቸሮችን አካተውበታል :: ብቻ እዩት እና ያላችሁን ሀሳብ እዛው ላይ አስቀምጡልን ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/qTL80md_qMk

መኪናው ለግል አገልግሎት ሳይሆን ለመሸጥ ስላስመጡት መግዛት የምትፈልጉ ተጨማሪ መረጃ በ 0991157053 ወይም በ 0911663121 ላይ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Toyota #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ፍሬቻችሁ በፍጥነት ብርት ጥፍት ሲል ሊሆኑ የሚችሉት 3 ምክንያቶች አሉ ::

1. ሲገጠም በትክክል ካልተገጠመ
2. ሾርት የሚያደርግ ከሆነ እና
3. ሊቃጠል ሲል ይህንን ምልክት ያሳያል ::

ስለዚህ ከእነዚህ ምክንያቶች አንዱ ሊሆን ስለሚችል በተራ ቼክ አድርጟቸው ::

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Turnsignal #Light
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለብዙዎች የገቢ ምንጭ የነበረው የላዳ ታክሲ ታሪክ | LADA Riva

ይህንን ላዳ ታክሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ደግሞ አዲስ አበባ የማያውቀው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም :: አሁን ላይ ሌሎች የታክሲ ድርጅቶች መተው እያስወጧቸው ቢሆንም በጊዜው ግን የከተማው መለያ ነበሩ :: ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ገቡ? ምን ነበር እንደዚህ እንዲበዙ ያደረጋቸው ምክንያት? እንዴት ተሰሩ የሚለውን የዩትዩብ ቪድዮ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/JyxYlRMIiOI

በዚሁ ደግሞ የቆሙ ክላሲክ እና የቆዩ መኪኖች ያላችሁ ሰዎች የምትሸጡ ከሆነ ገዝተን ቪድዮ ሰርተን ለማሳየት ስለሆነ አናግሩን ::

ገራሚ ከሰአት ተመኘን
#Lada #Taxi
@OnlyAboutCarsEthiopia
Ford Mustang Mach 1

ይህ የ 2021 Ford Mustang Mach 1 ኢትዮጵያ ውስጥ የገባ መኪና ነው ::
Stone gray ቀለም ያለው 5 liter V8 ሞተር ሲኖረው 454 HP ወይም የፈረስ ጉልበት እና 390 Nm of ቶርክ ያለው መኪና ነው ::
Mach 1 ላይ 19 inch ጎማዎችን ስታገኙ Brembo brakeም አንድ ላይ ታገኛላችሁ ::
የጀርባው Axle Cooler አለው :: ይህም ትራክ ላይ ለረጅም ሰአት ሲነዳ እንዳይሞቅ በማሰብ ነው ::
ማሞቅያ እና ማቀዝቀዣ ያላቸው ወንበሮች, የትራክሽን ኮንትሮል ሲስተም, መሪውን ኮንትሮል ለማድረግ የሚመች በተን እና የድራይቪንግ ሞድ በተን ታገኛላችሁ ::
በ 10 ማርሽ Automatic ወይም በ 6 ማርሽ manual transmission ይመጣል ::
ዋጋው ከ 53,400 የአሜሪካን ዶላር ጀምሮ ነው ::
አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMYr6EkCX/

ማንኛውንም መኪኖቻችሁን እየነዳን ሪቪው እንድንሰራ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሰዎች @Yonathandesta ላይ መልእክት ላኩልን ::

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#Ford #Mustang
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/24 12:23:04
Back to Top
HTML Embed Code: