Telegram Web Link
4 አሪፍ የምንላቸውን የመኪና መሸጫ APP እና Website እንጠቁማችሁ ::

1. Mekina.Net እዚህ ላይ መኪናችሁ በደንብ ይታያል :: ግን መኪናችሁን ለማስተዋወቅ ከ 400 ብር ጀምሮ ትከፍላላችሁ ::
2. Qefira.com ሲሆን ይህንን አሪፍ የሚያደርገው እዚህ ላይ በነፃ መኪኖችን መልቀቅ ትችላላችሁ :: ፊቸር እንዲደረግ ስትፈልጉ ነው ተጨማሪ የምትከፍሉት :: ብዙ ተመልካችም አላቸው :: ብዙ ነገር ስለምታገኙ ዌብሳይቱ ላይ ::
3. Afrotie ሲሆን እነሱ Android app ብቻ ያላቸው ሲሆን በሱ ምክንያት ሁሉንም ያሳተፈ አይደለም :: ግን አሪፍ እይታ አላቸው :: እና በነፃ መልቀቅ ትችላላችሁ ::
4. Jiji የሚባል App ሲሆን ለ Android እና ለ ios አላቸው :: ከዛ በተጨማሪ ዌብሳይትም አላቸው :: እንደሌሎቹ ብዙ ተመልካች የለውም የመኪናው ላይ ግን በጣም እያደገ ነው :: እናንተ አሪፍ የምትሉትን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

ብሩህ ምሽት ተመኘን
#CarWebsite
@OnlyAboutCarsEthiopia
የመኪና ወንበር ቀበቶ ወይም ሲትቤልት በየ 6 ደቂቃው የአንድ ሰው ያተርፋል :: ስለዚህ ለህጉ ብቻ ብላችሁ ሳይሆን ለደህንነታችሁ ብላችሁ አድርጉ ::

ግሩም ቀን ተመኘን
#SeatBelt #Safety
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?
#ad
ሳምንታዊውን ጥያቄ እና መልስ ይዘን ብቅ ብለናል :: ከ @YDLCustoms ጋር በመሆን አንድ ቀለል ያለ ሽልማት ያለው ጥያቄ ይዘን መተናል :: 12 ኛ ሳምንታችን ላይ ነን ::

ጥያቄው

የዚህ መኪና ስም ምንድነው?

ይህንን መጀመርያ የመለሰ ሰው የቁልፍ መያዣ ያገኛል ::
ህጉ አዲስ አበባ ውስጥ መሆን አለባችሁ እና የቁልፍ መያዣውን መታችሁ ነው መውሰድ ያለባችሁ ቦሌ ሚካኤል ድረስ ::
ከዚህ በፊት እንደነበረው መጉላላት እንዳይኖር ::
ይሄ ውድድር በሁለቱም ቻናሎች ማለትም በ @OnlyAboutCarsEthiopia እና @YDLCustoms ላይ ስለሚለቀቅ ከሁለቱ ቻናሎች ቀድሞ የመለሰ አንድ ሰው ነው ሽልማቱ የሚያገኘው

ገራሚ ገራሚ የቁልፍ መያዣዎችን መግዛት የምትፈልጉ @YDLCustoms ላይ ታገኛላችሁ ::
አድራሻችን ቦሌ ሚካኤል ነው ::
በየሳምንቱ እንደዚህ ቀለል ያሉ ሽልማት ያላቸው ጌሞች ስለሚኖሩ Instagram እና telegram ላይ @YDLCustoms ን ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ ::

ገራሚ ምሽት ተመኘን
#CarLogo #ydlcustoms #ad
@OnlyAboutCarsEthiopia @YDLCustoms
የአለማችን ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የሚነዷቸው ውድ መኪኖች

4 ተጫዋቾችን አካተን የሰራነው ቪድዮ ሲሆን ትልቅ ገንዘብ አውጥቶ የገዛውንም ተጫዋች አካተንበታል :: እንደምትወዱት አንጠራጠርም :: የወደዳችሁትን መኪና ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን :: ሙሉውን ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/YLN6nWgijtc

እርፍ የምትሉበት ምሽት ተመኘን
#Ronaldo #ExpensiveCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
የማንን መኪና ወደዳችሁ? ሙሉውን ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ታገኙታላችሁ
Anonymous Poll
14%
Aubameyang
12%
Neymar
22%
Messi ወይስ
53%
Ronaldo
መኪና ልትሸጡ ስትሉ ስንቶቻችሁ ናችሁ ስለመኪናችሁ ዝርዝር ነገር ለገዢው የምትነግሩት?

ምን ያህል የመኪናውን የእድሳት መረጃ ታስቀምጣላችሁ? ምን ያህሎቻችሁ መኪናችሁ ስላላቸው ፊቸሮች ታነባላችሁ? እነዚህ ነገሮች ገዢው ለመግዛት ወደእናንተ ሲመጣ የሚያያቸው ነገሮች ናቸው :: በደንብ ያሉትን ነገሮች ከነገራችሁት የመግዛት ፍላጎቱ ይጨምራል :: ግን መኪናን እኛ ሀገር በታርጋ ነው የሚገመገመው :: ያ ትክክል ነው ብለን አናስብም :: እናንተስ ምን ታስባላችሁ?

ውብ ሰኞ ተመኘን
#CarSales
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?

የመኪና ዌብሳይት በመስራት ላይ እንገኛለን :: ስሙ ሀገራዊ እና መኪናዊ እንዲሆን አስበናል :: እናም ስም በመስጠት የውዴታ ግዴታዎን እንዲወጡ ነው 😂 :: ማንኛውም አሪፍ ነው የምትሉትን ስሞች ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ::
ከዛ የወደድነውን እንመርጣለን ::

ፍክት ያለ ከሰአት ተመኘን
#Naming #CarWebsite
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ቪድዮ ካያችሁት በሗላ ስለ ሲትቤልት ያላችሁ አስተሳሰብ ይቀየራል

ሲትቤልት እኛ ሀገር በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግዴታ እየሆነ መጣ እንጂ መኪና ውስጥ ጥቅም እንደሌላቸው እቃዎች ነበር የሚቆጠረው :: ነገር ግን ብታምኑም ባታምኑም በየ 6 ደቂቃው የአንድን ሰው ህይወት ያተርፋል :: ግን እንዴት ተጀመረ? እንዴት ነው የሚሰራው? ምን ምን የወንበር ቀበቶ አይነቶች አሉ? ጥቅሙስ ምንድነው? የሚሉትን ጥያቄዎች የምንመልስ ይሆናል :: ሙሉውን ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/kMy-nVja8_g

ግሩም ምሽት ተመኘን
#SeatBelt
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስለ ሲትቤልት ስንቶቻችሁ በደንብ ታውቃላችሁ?
ቪድዮውን ካላያችሁት
👆🏽👆🏽👆🏽ሊንኩን ታገኛላችሁ
Anonymous Poll
48%
በደንብ አውቅ ነበር
35%
ትንሽ ትንሽ አውቅ ነበር
17%
ምንም አላውቅም
ሀገራችን የአዳዲስ መኪኖች ጥርቅም ብቻ ሳትሆን የክላሲክ መኪኖች ስብስብም ያሉባት ሀገር ናት :: ምን አልባት ክላሲክ መኪኖች ላይ ፍላጎት ካላችሁ ከተማው ላይ የሚገኙትን መኪኖች ሰላምታ ሰታችሁ ታልፋላችሁ ፎቶ በማንሳት 😂 እንደነ ኤልያስ ፍቅሩ ከገባባችሁ ደግሞ እየሰበሰባችሁ ታድሳላችሁ :: እናም ይህንን ስናይ ቪድዮ ለመስራት ወስነን ከ 3 ወር በላይ ምን ምን መኪኖች እንዳሉ መኪኖቹን እየፈላለግን ነበር :: በመጨረሻም ወደ 20 የሚጠጉ መኪኖችን አግኝተናል :: ቤተመንግስት ካሉት ውጪ :: እናንተ የምታቋቸው እዚህ ሀገር የሚገኙ መኪኖችን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን :: ፎቶ ቢኖራችሁ ደግሞ ተመራጭ ነው :: ሰብሰብ አርገን ከተቻለ በአንድ ካልሆነ ደግሞ በ 2 ቪድዮ አድርገን የምናቀርብ ይሆናል ::

ድንቅ ከሰአት ተመኘን
#ClassicCars #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
አብዛኛው የመኪና ሽያጭ በከተማችን የሚካሄደው ቅዳሜ ነው :: ከ Research ያገኘነው ውጤት እንደሚያመለክተው አብዛኛው ሰው በዚህ ቀን ነፃ ስለሚሆን ነው :: ብታምኑም ባታምኑም አብዝኛዎቹ መኪና መሸጫዎች ጋር የመኪኖቹ ዋጋ ይጨምራል ቅዳሜ ቅዳሜ :: ያ ማለት እንዲቀንሱላችሁ በደንብ መከራከር አትችሉም ስለማይቀንሱ :: ብዙ ገዢ ስለሚመጣ የዛን ቀን በጣም ይኮራሉ :: ስለዚህ ወደ ማክሰኞ ወይም እሮብ የተሻለ ዋጋ ታገኛላችሁ ::

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Ethiopia #CarSales
@OnlyAboutCarsEthiopia
በቀጣይ ቀድሞ እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉት ቪድዮ ምን ላይ ያተኮረ ቢሆን ጥሩ ነው?
Anonymous Poll
13%
ጎማ ላይ
27%
ሞተር ላይ
16%
ክሩዝ ኮንትሮል ላይ
18%
የመኪና አምራቾች ላይ ወይስ
25%
ቴክኖሎጂ ላይ
5 ስለመኪናችሁ ማወቅ ያለባችሁ ነገሮች

1. የመኪናውን አመተምህረት, ካምፓኒውን እና ሞዴሉን
2. VIN ቁጥር
3. መቼ ሜንቴን እንደሚደረግ
4. የጎማችሁን ፕሬዠር
5. የሞተሩን መብራት ያ ማለት ዳሽቦርዱ ላይ ምን ምልክት እያሳየ እንደሆነ በቀላሉ ትረዳላችሁ ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Cars #CarFact
@OnlyAboutCarsEthiopia
ረከስ ያለ መኪና ሪቪው ስሩ ስትሉ ለነበራችሁ

ይህ የ 2022 Chery Tiggo 2 Pro መኪና ነው :: ዋጋው አሁን ላይ 2.4 ሚሊየን ብር ነው :: ስለዚህ ከተማችን ላይ ከሚገኙ SubCompact Crossover መኪኖች ርካሹ ያደርገዋል :: ዋጋው ብቻ ሳይሆን የፊት ለፊቱ ዲዛይን ያሉት ፊቸሮችም እና በሊትር የሚሄደው ኪሎሜትርም አሪፍ የሚባል ነው :: ከሱ በተጨማሪ ስፔር ፓርቱ ከሌሎቹ ረከስ ይላል :: ግን ደግሞ ስፔር ፓርቱ በቀላሉ አታገኙም :: ከሱ በተጨማሪ Resale Value እየቀነሰ ይሄዳል :: ብቻ መኪናውን አይታችሁ እናንተ ፍረዱ :: ሙሉ ቪድዮውን ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/jjbu0Ks2otI

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Cherry #SUV
@OnlyAboutCarsEthiopia
አብዛኛዎቻችን መኪናችንን ማደያ አቁመን ስንቀዳ ሞተር እናጠፋለን :: ግን ለምን?

ነዳጅ በሚቀዳበት ጊዜ የነዳጅ ትነት ይወጣል :: ይህም ተቀጣጣይ ድብልቅ ይፈጥራል :: በተጨማሪም በአጋጣሚ የመፍሰስ አደጋ ካለ እና የሚሽከረከር ሞተር ካገኘ እዛ አካባቢ የመቀጣጠያ ምንጩን ይጨምራል። ሞተሩን ማጥፋት እሳቱን በጣም ይቀንሳል :: ስለዚህ ስንቀዳ ሞተራችንን እናጥፋ ::

የእረፍት ምሽት ተመኘን
#Fuel #CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቁ ኖሯል?

መኪናችን ከ 40 ኪሎሜትር ወይም ከ 25 ማይልስ በላይ ፍጥነት የማይጟዝ ከሆነ ኤርባጉ አይፈነዳም :: አንዳንድ መኪኖች ላይ ቀበቶ ካላረጋችሁ ኤርባግ አይፈነዳም :: ይህም የሆነው ሰዉ እንዳይጎዳ ነው ::

ውብ ምሽት ተመኘን
#AirBag
@OnlyAboutCarsEthiopia
Airbag ምን ጥቅም አለው?

Airbag መኪናችን ውስጥ ከሚገኙ የሴፍቲ ሲስተም አንዱ ነው :: የመኪናችሁ Airbag የሚፈነዳው ከ 40 ኪሎሜትር በሰአት በላይ ስትነዱ ነው :: እስከ 2020 ድረስ ባለው መረጃ 50,437 ሰው አትርፏል :: ግን ኤርባግ እንዴት ተጀመረ? አሁን ምን ላይ ደርሷል የሚለውን እና ስለ ኤርባግ እንዴት እንደሚሰራ ምን ለየት ያሉ ነገሮች እንዳሉት ዩትዩብ ላይ ቪድዮ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/0XNMLPvnk9U

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Airbag
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ታውቃላችሁ?

አንዳንድ መካኒኮች ብዙ አመት መኪኖችን በመስራት እና በመንዳት ከማሳለፋቸው ብዛት ማንዋል መኪና ላይ ፍሪስዮን ሳይረግጡ ማርሽ ይቀይራሉ :: ይህም የሚሆነው በድምፅ መቼ ጊሩ ሜሽ ማድረግ እንዳለበት ስለሚያውቁ ነው :: ደሞ ሞክሩት አሏችሁ 😂😂

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
#Mechanic #Clutch
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ባስኬት ቦል ተጫዋች ብዙዎቻችሁ ታውቁታላችሁ ብለን እናስባለን :: የጎልደን ስቴት ዋርየርስ ተጫዋች እና የምን ጊዜም የሶስት ነጥብ ሪከርድ ባለቤት ነው :: ስቴፈን ከሪ
እሱ ጋራዥ ውስጥ የሚገኙ 5 አሪፍ መኪኖች
1. Porsche 911 GT3 RS
2. Tesla Model X
3. Infiniti Q50
4. Porsche Panamera Turbo S
5. Mercedes Benz G55


የእረፍት ምሽት ተመኘን
#Basketball #Curry
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስንቶቻችሁ ናችሁ አዲስ የገዛችሁት መኪና ላይ እስከ 1,600 ኪሎሜትር እስኪደርደርስ ድረስ እነዚህን ነገሮች ብታደርጉ እድሜውን ሊያስረዝም እንደሚችል የምታውቁት?

1. መኪናችሁን ረገጥ አድርጋችሁ ባትነዱ
2. ክሩዝ ኮንትሮሉን ባትጠቀሙ
3.አጫጭር ጉዞዎችን ባትሄዱ
4. ከባባድ እቃ ባትጭኑ ከባባድም ሰው ቢሆን 😂😂
ወፍራም ጟድኛ ካላችሁ ላኩለት ወይም ላኩላት
አዲስ መኪና ከገዛችሁ እንዳትጭኗቸው 😂😂
ፈታ እንድትሉ በሚል ነው ደሞ
እነዚህን ባታረጉ መኪናችሁን ለረጅም ጊዜ ትጠቀሙታላችሁ ::
ዩትዩብ ላይ ዛሬ መለቀቅ የነበረበት የ Review ቪድዮ በመጨረሻ ሰአት የ Copyright Claim ስላጋጠመን እሁድ አስተካክለን የምንለቅ ይሆናል :: እስከዛው ግን
የተብራራ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMN6Bp4Dr/?k=1

የሚገርም ምሽት ተመኘን
#NewCar
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/25 08:25:16
Back to Top
HTML Embed Code: