Telegram Web Link
ለምንድነው ፒክአፕ ትራኮች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ እየሆኑ የመጡት?

ከ 100 አመት በላይ ገበያ ላይ የቆዩት እነዚህ መኪኖች በጣም ተመራጭ እየሆኑ ነው :: ምንም እንኳን ዋጋቸው እየጨመረ ቢመጣም :: ግን ለምን?
5 ምክንያቶችን አግኝተናል እሱን እናጋራችሁ

1. ቤት በተወደደበት በዚህ ዘመን መኪናችሁ ውስጥ መኖር ትችላላችሁ
2. Carryboy አድርጋችሁ ከትራክ ወደ SUV መቀየር ትችላላችሁ
3. እንደፈለጋችሁ ማሻሻል ትችላላችሁ ቀላል ስለሆኑ
4. ከተማ ውስጥም ከከተማም ውጪ እንደፈለጋችሁ ይዛችሁ መንቀሳቀስ ትችላላችሁ ::
5. አብዛኛዎቹ ፒክአፕ መኪኖች ወደ ኤሌክትሪክ እየተቀየሩ ነው :: ያ ማለት ብዙውን ነገር ያቃልላል :: ምክንያቱም ብዙ ነዳጅ ስለሚወስዱ ኤሌክትሪክ ሲሆኑ የተሻሉ ወጪ ቆጣቢ ይሆናሉ :: አዲስ የሚወጡ ኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የሰራነው ቪድዮ ነበር :: ትንሽ ቆይቷል ግን ካላያችሁት እንድታዩት ጋበዝናችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

3 አስገራሚ በቅርቡ የሚወጡ የኤሌክትሪክ Pickup መኪኖች
https://youtu.be/QEj7x-WOkIM

ምሽት ላይ በአዲስ ሪቪው YouTube ላይ እንገናኝ

እርፍ የምትሉበት ቀን ተመፕን
#AmazingFacts #PickupTruck #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
Hyundai Tucson DCT ያለውን እንዳትገዙ

እንዳትገዙ በምንልበት ጊዜ ምንድነው ምክንያቱ? ለአዲስ አበባ መንገድ የማይሆንበት ምክንያት ምንድነው? በዛሬው ቪድዮ የትኛውን የቱሰን አይነት ብትገዙ የማይሞቅ ተጨማሪ ብዙ ወጪ እንደማያስወጣችሁ እንመለከታለን :: 2022 Hyundai Tucson N-Line በደንብ አሳያችሗለሁ :: ሙሉውን ቪድዮ YouTube ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MFyK8nVlmIw

ውብ ምሽት ተመኘን
#HyundaiTucson #SUV
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

በአማካይ አዲስ የፒክአፕ መኪና ዋጋ በአለማቀፍ ገበያ 2.1 ሚሊየን ብር ሲሆን ወደእኛ ሀገር ስንመጣ ወደ 4 ሚሊየን ብር ይጠጋል :: እሱም ከታክስ ውጪ 😳 እጥፍ ማለት ነው :: ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ ፒክአፕ መኪና ውድ ቢሆንም ለሚጠቀሙበት ሰዎች ብዙም አያስደንቅም ዋጋው :: ዋናው ነገር መጫን ያለበትን ነገር በደንብ መጫኑ ነው ::

ፍክት ያለ ሰኞ ተመኘን
#Ethiopia #PickupTruck
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

የመጀመርያውን pickup መኪና በ1896 ጎትሊብ ዳይምለር ተሰራ :: ስሙም Horseless Wagon ተባለ :: 4 የፈረስ ጉልበት፣ 2 ሲሊንደር ሞተር እና 1.1 ሊትር Dubbed የሰራውን ተሽከርካሪ ነው :: ስለዚህ አርብ እለት የጠየቅነውን ጥያቄ የመለሰው @Jumpmanz ነው :: የሱዙኪ የቁልፍ መያዣ የሚያገኝ ይሆናል :: የቁልፍ መያዣዎችን የምትፈልጉ @YDLCustoms ላይ ታገኛላችሁ ::

ውብ ምሽት ተመኘን!
#CarFacts #PickupCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

ለተሰሩበት አላማ የሚውሉት 15% ፒክአፕ መኪኖች ብቻ ናቸው ::
ይህ ለአንዳንዶች ሊያስገርም ይችላል። ፒክአፕ መኪና ከገዙት ሕዝብ መካከል ግማሹ የጭነት መኪናውን በግልጽ የሚጠቀም የንግድ ሥራ አላቸው ብሎ ያስባል እና የቀረው ሕዝብ ግማሽ ያህሉ ደግሞ ለመንቀሳቀሻ ብቻ ነው ብሎ ያስባል :: ግን አይደለም :: እንደ እውነቱ ከሆነ ከ15% ያነሱ የፒክ አፕ መኪና ገዢዎች ናቸው የጭነት መኪናቸውን የሚጠቀሙት ከስራ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ነገር ነው። ይህ ማለት በአብዛኛው በመንገድ ላይ የሚታዩት የጭነት መኪኖች እንደሌሎች መኪኖች ለመንቀሳቀሻ ብቻ ነው :: እቃዎች የመሸከም አቅም የሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች በጣም ትንሽ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥስ ስንት የሚሆን ይመስላችሗል? ገምቱ

ሞቅ ሞቅ ያለ ምሽት ተመኘን🙏
#PickupTrucks #CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
አዲስ መኪና ስትገዙ ታርጋ ለማውጣት የሚያስፈልጉ 12 ነገሮች

1. የመኪናው ሰነድ
2. የቴምብር ቀረጥ
3. 500 ብር ለተላላፊ ታርጋ
4. ለቋሚ ታርጋ ከ 2,500-2,710 ብር
5. ለሶስተኛ ወገን መድህን ከ550-1023 ብር
6. 2 ጉርድ ፎቶ
7. ለቴምብር 10 ብር
8. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃፍቃድ
9. የመጀመሪያ እርዳታ ማድረግያ ሳጥን ( First Aid Kit)
10. አንፀባራቂ
11. የእሳት ማጥፊያ
12. ክሪክ ጎማ መፍቻ እና ተቀያሪ ጎማም መኖር አለበት ::
ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ይዞ በመሄድ አዲስ ታርጋ ማውጣት ትችላላችሁ

ምንጭ: ቲክቶክ

ውብ ምሽት ተመኘን
#NewCarPlateProcedure #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
Forwarded from Yonathan Desta
የጉምሩክ_ታሪፍ_ደንብ_ማሻሻያ_ቁጥር_9_.pdf
56.9 MB
የጉምሩክ ታሪፍ ደንብ ማሻሻያ

ይሄ የጉምሩክ ታሪፍ ደንብ ተሻሽሎ የወጣው አጠቃላይ ሁሉንም የያዘ የታሪፍ ደንብ ነው መኪናንም ጨምሮ :: ስለዚህ ከመኪና ጋር ተያይዞ ታክስ እና ቀረጥ ጋር ያላችሁን ጥያቄ ይመልሳል ብለን እናስባለን :: አይታችሁት ደግሞ ያልገባችሁ ነገር ካለ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን :: ለመመለስ እንሞክራለን ::

Source: mekinamarket

ፍክት ያለ ከሰአት ተመኘን
#TaxSystem #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በስራ ላይ ስትሆኑ አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ነገር ያጋጥማል :: ጠንቀቅ ብላችሁ ስሩ ለማለት ነው :: እንደዚህ አይነት ቪድዮዎች ላይ በተለይ በሀገራችን የመኪና ቪድዮዎች ላይ Reaction ቪድዮ YouTube ላይ እንድንሰራ የምትፈልጉ ከሆነ 👍🏽 በማድረግ ፍላጎታችሁን ግለፁ :: 12 ሰአት ላይ በአዲስ ለየት ባለ የመኪና ሪቪው YouTube ላይ እንገናኝ ::

መልካም ቀን ተመኘን
#CarVideos #Mechanic
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰው ማገት የማትችሉበት ብቸኛው ኤሌክትሪክ ፒክአፕ ትራክ
Rivian R1T Truck

Rivian R1T ፒክአፕ ትራክ ከዲዛይኑ ጀምሮ በጣም አሪፍ መኪና ነው :: ውጪውም ውስጡም ላይ ብዙ ፊቸሮች አሉት :: ሌሎች መኪኖች ላይ አይታችሁ የማታውቋቸው :: በጣም ለየት ያለው ግን Gear Tunnel ነው :: እዛ ውስጥ ሰውም መግባት ይችላል :: ከዛ በተጨማሪ የ 5,000 ዶላር ኦፕሽንም አለው :: እሱ ምን እንደሆነ ስንት ኤሌክትሪክ ሞተር እንዳለው ዋጋውን እና በጣም ለየት ያሉትን ነገሮች YouTube ላይ ቪድዮ ሰርተን ለቀናል :: እያያችሁ ፈታ በሉበት ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/SSI5RFKHQKI

4,000 Subscribers 🙏🙏
ሁላችሁንም በጣም እናመሰግናለን

እኛን መደገፍ የምትፈልጉ ቪድዮውን በ VPN ብታዩልን ይመረጣል ::

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Rivian #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?
#ad
ዛሬ ትንሽ ለየት ያለ ነገር ይዘን ብቅ ብለናል :: ከ @YDLCustoms ጋር በመሆን አንድ ቀለል ያለ ሽልማት ያለው ጥያቄ ይዘን መተናል :: 7 ተኛ ሳምንታችን ላይ ነን ::

ጥያቄው

ቮልስ ዋገን ቢትልን ዲዛይን ያደረገው ማነው?

ይህንን መጀመርያ ለመለሰ ሰው የምትመለከቱትን የቁልፍ መያዣ ያገኛል ::
ህጉ አዲስ አበባ ውስጥ መሆን አለባችሁ እና የቁልፍ መያዣውን መታችሁ ነው መውሰድ ያለባችሁ ቦሌ ሚካኤል ድረስ ::
ከዚህ በፊት እንደነበረው መጉላላት እንዳይኖር ::
ይሄ ውድድር በሁለቱም ቻናሎች ማለትም በ @OnlyAboutCarsEthiopia እና @YDLCustoms ላይ ስለሚለቀቅ ከሁለቱ ቻናሎች ቀድሞ የመለሰ አንድ ሰው ነው ሽልማቱ የሚያገኘው

ገራሚ ገራሚ የቁልፍ መያዣዎችን መግዛት የምትፈልጉ @YDLCustoms ላይ ታገኛላችሁ ::
አድራሻችን ቦሌ ሚካኤል ነው ::
በየሳምንቱ እንደዚህ ቀለል ያሉ ሽልማት ያላቸው ጌሞች ስለሚኖሩ Instagram, Tiktok እና telegram ላይ @YDLCustoms ን ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ ::

ገራሚ ምሽት ተመኘን
#CarLogo #ydlcustoms #ad
@OnlyAboutCarsEthiopia @YDLCustoms
ድሮም ዘንድሮም ፌስቲቫል
Derom Zenderom Festival

ግንቦት 6 - May 14

More update soon 👌
Follow 👉🏽 @deromzenderom

ግሩም ምሽት ተመኘን
#deromzenderom #Volkswagen
@OnlyAboutCarsEthiopia
T-GDI የሚል ፅሁፍ ስንቶቻችሁ ከመኪና ጀርባ ወይም ሞተሩ ላይ አይታችሁ ምን እንደሆነ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?

GDI ማለት (Gasoline Direct injection) T ካለው ደግሞ ቱርቦ ያለው የቤንዚን ሞተር የነዳጅ አረጫጭ ስርዓት ነዉ። ይህን የነዳጅ አረጫጭ ሲስተም የሚጠቀሙት ዘመናዊ የቤንዚን መኪኖች ናቸዉ። ለምሳሌ Volkswagen Hyundai እና Kia አምራቾች ስር የሚገኙ መኪናዎች ላይ ይህንን ሲስተም እናገኛለን ፡፡
GDI engine ነዳጅ የሚረጨዉ በከፍተኛ ግፊትና በቀጥታ በእያንዳንዱ ሲሊንደር ውስጥ ነዉ። ይህም ሰአቱን የጠበቀ የነዳጅ አረጫጭ እና የተመጠነ ነዳጅ እንዲረጭ ያመጣጥን እና መኪናውን ነዳጅ ቆጣቢ እንዲሆን ያደርገዋል ።

መልካም ምሽት ተመኘን
#GDI #injectionsystem
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለፋሲካ በአል አደረሳችሁ እያልን በምንሸጣቸው የቁልፍ መያዣዎች ላይ የ 20% ቅናሽ ማድረጋችንን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን ::
#Ad

- የቶዮታ Vitz
- የቶዮታ Yaris
- የሞተር ሳይክል
- የፎርድ, የሱዙኪ, የአውዲ, የላንድ ሮቨር, የሼቭሮሌት, የፔጆት, የሚትሱቢሺ እና የቶዮታ የቁልፍ መያዣዎች ታገኛላችሁ :: ይዘዙን
ለበለጠ መረጃ www.tg-me.com/YDLCustoms Join በማድረግ የምትፈልጉት ታገኛላችሁ ::

አድራሻ ቦሌ ሚካኤል የሱፍ ህንፃ ላይ ታገኙናላችሁ ::

ትእዛዛችሁ ከ 1,000 ብር በላይ ከሆነ ቅዳሜ ቅዳሜ በራሳችን ትራንስፖርት ያላችሁበት ድረስ እናደርሳለን ::

ስልክ 0913611308

⛔️ ማሳሰቢያ : እነዚህ የቁልፍ መያዣዎች ፕላስቲክ ናቸው :: የብረት አይደሉም :: ግን ጠንካራ ናቸው ::

#Keychains
@YDLCustoms @OnlyAboutCarsEthiopia
7 መኪና ላይ የሚገኙ አስገራሚ ፈጠራዎች

መኪና ላይ የሚገኙ ቴክኖዎሎጂዎች በየጊዜው እየተሻሻሉ ይገኛሉ :: የሚሻሻሉትም ያሉትን ነገሮች ቀለል ለማድረግ ታስቦ ነው :: ከዛ በተጨማሪ ደግሞ የመኪና አደጋን ለመቀነስ ብዙ ቴክኖዎሎጂዎች እየተፈጠሩ ይገኛሉ :: ከእነሱም መካከል አየር የሌለው ጎማ, ራሱን በራሱ ፓርክ የሚያደርግ መኪና, የውጪ ኤርባግ እና ሌሎችም በጣም ለየት ያሉ ቴክኖዎሎጂዎች አሉ :: በዛሬው ቪድዮ ለየት ለየት ያሉ ቴክኖዎሎጂዎችን እንመለከታለን :: ሙሉውን ቪድዮ YouTube ላይ ታገኙታላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/EYXqEmUEKpw

እኛን መደገፍ የምትፈልጉ ቪድዮውን በ VPN ብታዩልን ይመረጣል ::

ግሩም ምሽት ተመኘን
#AmazingTechnologies
@OnlyAboutCarsEthiopia
NASA አየር የሌለውን ጎማ እየሰራ እንደሆነ ያውቃሉ?

የ NASA አየር የሌለው ጎማ ለየት የሚያረገው እንደምናውቀው አይነት ጎማ ሳይሆን ሽቦ ነው ::
ምንም እንኳን ሽቦ ቢሆንም ጎማ ታጥፎ የሚቀር ሳይሆን ወደ መጀመርያ ቦታው የሚመለስ ነው ::
ግን ደግሞ አየር ካለው ጎማ ከበድ ይላል :: እና ደግሞ በፍጥነት ለመንዳት አይሆኑም :: ለዛም ነው በሙከራ ላይ ያሉት :: በ 2024 ይወጣሉ ተብሏል መጠበቅ ነው ::

የተለየ ምሽት ተመኘን
#CarFacts #NASA
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት እየተሸጠ ያለው ኤሌክትሪክ VW ID.4 መኪና

ቴስላ በኤሌክትሪክ ገበያው ላይ ቁንጮውን ቢይዝም አንዳንድ ትልልቅ የምንላቸው የመኪና አምራቾች መኪኖቻቸውን ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ገበያ እየገቡ ይገኛሉ :: አንዱ VW ካምፓኒ ነው :: በ Crossover SUV ዘርፉ እና በ Van ወደ ኤሌክትሪክ ገበያው እየተቀላቀሉ ነው :: በዛሬው ቪዲዮ የ tesla Model Y ተቀናቃኝ መኪናቸውን እንመለከታለን :: ይህ የ 2021 VW ID.4 መኪና ነው :: ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን :: በዛሬው ቪድዮ ውስጡን, ውጪውን, እዚህ መኪና ላይ ለየት ብለው ያገኘሗቸውን ፊቸሮች እና በተደጋጋሚ የሚጠየቀውን ጥያቄ ማለትም ቤታችን ውስጥ ቻርጅ ለማድረግ በ single phasem በ 3 phasem የሚፈጀውን ሰአት ስንት እንደሆነ አብረን እንመልከት ::
ሙሉ ቪድዮውን Youtube ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/nI6O9FXwQBI

እኛን መደገፍ የምትፈልጉ ቪድዮውን በ VPN ብታዩልን ይመረጣል ::

ለክርስትና እምነት ተከታዮቹ እንኳን ለፋሲካ በአል በሰላም አደረሳችሁ ::

ግሩም ምሽት ተመኘን
#VW #ID4
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ እያልን
በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና ይሁንልን !

ውብ ዓመት በዓል ተመኘን 🙏
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን በአንድ ቻርጅ እቤታችን ውስጥ ምን ያህል ሰአት እና ወጪ አለው?

ይህንን የማሳያችሁ በ VW ID.4 መኪና ነው :: VW ID.4 82 KWh Battery Pack ሲኖረው መኪናው የሚጠቀመው 77 KWh Battery Packun ነው :: ስለዚህ በአንድ ቻርጅ ወደ 110 ብር ይፈጃል :: በአንድ ቻርጅ ደግሞ 400 ኪሎሜትር ይጟዛል :: በቂ ነው ብዬ አስባለው :: ግን ችግሩ በ 2.3 Kw ቻርጀር ቻርጅ ሲደረግ በየ2 ቀን ነው መጠቀም የምትችሉት :: የተሻለው አማራጭ 7.4 Kw ወይም ደግሞ 3 Phase ካላችሁ 11 kw ቻርጀሩን መጠቀም ነው :: ስትገዙ ይህንን አይታችሁ ግዙ :: የሚጠቀመው Type 2 ቻርጀር ነው ::
VW ID.4 ውስጡ ላይ ለየት ያሉትን ነገሮች ቲክቶክ ላይ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLp5bNGb/

መልካም ምሽት ተመኘን
#VWID4 #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስንቶቻችሁ የድሮ ሞዴሎችን ወደ አዲስ መቀየር እንደሚቻል ታውቃላችሁ?
2024/09/25 14:15:00
Back to Top
HTML Embed Code: