Telegram Web Link
ይህንን ያውቃሉ?

Mazda6 እንደ አውቶማቲክ ባለከፍተኛ ጨረር የፊት መብራቶች፣ የሌይን ጥበቃ እገዛ፣ የእግረኛ መለየት እና የዝናብ ዳሳሽ የንፋስ መከላከያ መጥረጊያ ያሉ ብዙ መደበኛ የደህንነት ባህሪያትን በውስጡ ያካትታል።

የፈካ ቀን ተመኘን!
#CarFacts #SedanCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
በየሳምንቱ በብዛት እያዘዛችሁን ስለምትገኙ በጣም እናመሰግናለን
#Ad

ከላይ የምትመለከቷቸውየዚህ ሳምንት የቁልፍ መያዣ ትእዛዞቻችን ናቸው :: እናንተ ማዘዝ ከፈለጋችሁ በ @Yonathandesta ላይ አናግሩን ::

የዚህ ሳምንት ዲዛይን ውስጥ
- የቶዮታ Vitz የቁልፍ መያዣ
- የቶዮታ Yaris የቁልፍ መያዣ
- የጎማ ቸርኬ የቁልፍ መያዣ
- የሞተር የቁልፍ መያዣ
- የመርሴዲስ SLS AMG የቁልፍ መያዣ
- የፎርድ, የሱዙኪ, የአውዲ, የላንድ ሮቨር, የሼቭሮሌት, የፔጆት, የሚትሱቢሺ እና የቶዮታ የቁልፍ መያዣዎች
- ከዛ በተጨማሪ ፊልም ላይ የምታውቋቸውን ካራክተሮች Minions, Groot, ironMan እና ሌሎችንም @YDLCustoms ላይ እያመረትን ይገኛል :: ይዘዙን

@YDLCustoms ላይ ተጨማሪ ዲዛይኖችን ታገኛላችሁ

አድራሻ ቦሌ ሚካኤል የሱፍ ህንፃ ላይ ታገኙናላችሁ :: ከዛ በተጨማሪ በቅርብ ቀን በ 22 በቆሬ እንዲሁም ዩኒቲ አካባቢዎችም ታገኙናላችሁ ::

መምጣት ካልቻላችሁ ደግሞ ቅዳሜ ቅዳሜ በራሳችን ትራንስፖርት ያላችሁበት ድረስ እናደርሳለን :: ትእዛዛችሁ ከ 1,000 ብር በላይ ከሆነ

ስልክ 0913611308

⛔️ ማሳሰቢያ : እነዚህ የቁልፍ መያዣዎች የፕላስቲክ ናቸው :: የብረት አይደሉም :: ግን ጠንካራ ናቸው ::

#Keychains
@YDLCustoms @OnlyAboutCarsEthiopia
የመኪናችሁ ፍሬቻ ላይ ችግር ካለ እንዴት ያስታውቃል?

የመኪናችሁ የግራ ወይም የቀኝ ፍሬቻ መብራት በፍጥነት ብልጭ ድርግም ካለ ሊሆኑ የሚችሉት 3 ምክንያቶች አሉ ::
1. ሲገጠም በትክክል ካልተገጠመ
2. Short የሚያደርግ ከሆነ እና
3. የምትጠቀሙት መብራት ሊቃጠል ሲል ይህንን ምልክት ታያላችሁ :: ለማወቅ ቀላል ነው :: በጣም ፈጠን ፈጠን እያለ ይበራል :: በብዛት ችግር የሚሆነውም መብራቱ ላይ ነው :: እና እሱን መቀየር ነው ::
ቲክቶክ ቪድዮ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLuNcKsc/

ውብ ምሽት ተመኘን 🙏
#TurnSignallight
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Nissan Altima የቅርብ ቁልፍ-አልባ መግቢያ፣ የርቀት ድምጽ ትዕዛዝ ቁጥጥር ስርዓትን ጨምሮ ከብዙ የቴክኖሎጂ ባህሪያት ጋር አብሮ ይመጣል።

#SedanCars #CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?
#ad
ዛሬ ትንሽ ለየት ያለ ነገር ይዘን ብቅ ብለናል :: ከ @YDLCustoms ጋር በመሆን አንድ ቀለል ያለ ሽልማት ያለው ጥያቄ ይዘን መተናል :: 5 ተኛ ሳምንታችን ላይ ነን :: የባለፈው ሳምንት መላሽ @race_boy1994 ነው ::

ጥያቄው

የመጀመሪያው የመኪና አደጋ መች እና የት ተከሰተ?

ይህንን መጀመርያ ለመለሰ ሰው የምትመለከቱትን የቁልፍ መያዣ ያገኛል ::
ህጉ አዲስ አበባ ውስጥ መሆን አለባችሁ እና የቁልፍ መያዣውን መታችሁ ነው መውሰድ ያለባችሁ ቦሌ ሚካኤል ድረስ ::
ከዚህ በፊት እንደነበረው መጉላላት እንዳይኖር ::
ይሄ ውድድር በሁለቱም ቻናሎች ማለትም በ @OnlyAboutCarsEthiopia እና @YDLCustoms ላይ ስለሚለቀቅ ከሁለቱ ቻናሎች ቀድሞ የመለሰ አንድ ሰው ነው ሽልማቱ የሚያገኘው

ገራሚ ገራሚ የቁልፍ መያዣዎችን መግዛት የምትፈልጉ @YDLCustoms ላይ ታገኛላችሁ ::
አድራሻችን ቦሌ ሚካኤል ነው ::
በየሳምንቱ እንደዚህ ቀለል ያሉ ሽልማት ያላቸው ጌሞች ስለሚኖሩ Instagram, Tiktok እና telegram ላይ @YDLCustoms ን ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ ::

ገራሚ ምሽት ተመኘን
#CarLogo #ydlcustoms #ad
@OnlyAboutCarsEthiopia @YDLCustoms
ይህንን ያውቃሉ?

Hyundai Elentra
የ2021 የሰሜን አሜሪካ ምርጥ መኪና ተብሎ ስለተሰየመ ልዩ እውቅና ያገኘ የsedan መኪና አይነት ነው::
ከመደበኛ የቴክኖሎጂ ባህሪያት ድርድር ጋር ይመጣል እና ለስላሳ እና ምቹ ጉዞ ያቀርባል።

የፈካ ቀን ተመኘን!
#CarFacts #SedanCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
የአለማችን ረጅሙ መኪና

ይሄ 6 Eldrado መኪኖች ተገጣጥመው የተሰሩ ሲሆን ርዝመቱ 30 ሜትር ነው ::
ይሄ መኪና 75 ሰዎች መያዝ የሚችል ሲሆን 26 ጎማዎች አሉት :: ከሳምንታት በፊት ነበር አዲሱ ሪከርድ የተሰበረው :: የድሮውን ሞዴል አሻሽለው ያመጡት ሲሆን ወደ ኤሌክትሪክም የመቀየር ፍላጎት አላቸው ::
ቪድዮውን ስታዩ ይበልጥ ትገረማላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLuq1UqT/

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#CarFacts #Limousine
@OnlyAboutCarsEthiopia
31 መኪና ላይ የሚገኙ አስገራሚ ፊቸሮች

የመኪና አምራቾች ከሚያመርቷቸው መኪኖች በላይ በሚጨምሯቸው Optionoch ብዙ ገንዘብ ያገኛሉ :: የሚያገኙት ገንዘብ ከመኪናው ትርፍ ሁላ ሊበልጥ ይችላል :: ለዛም ነው የመኪና አምራቾች በየጊዜው አዳዲስ ነገሮች ላይ ብዙ ገንዘብ Invest የሚያደርጉት ::
በዛሬው ቪድዮ ለየት ብለው ያገናቸውን 30 አስገራሚ መኪኖች ላይ የሚገኙ Optionoch እንመለከታለን ::
ሙሉውን ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/wV_0c3UsgAE

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#CarOptions #YouTube
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

በዩናይትድ ስቴትስ ከሚሸጡት ሁሉም ተሽከርካሪዎች 18% የሚሆኑት ፒክ አፕ/pickup/መኪናዎች ናቸው።
ልክ ነው፣ በአሜሪካ ውስጥ ካሉት 5 የተሽከርካሪ ግዢዎች 1ዱ PickUp መኪና ነው።

መልካም ውሎ!
#CarFacts #PickupCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
Ford F-150 መኪና ማርሽ ላይ የሚገኙ አስገራሚ ሁለት ፊቸሮች

የመጀመሪያው XL እና STX ትሪም ሌቨል ላይ ማርሹ የጎን ሲሆን አቁማችሁ ምን አልባት ሳታውቁ ማርሹ D ወይም Drive ላይ እያለ በር ስትከፍቱ በራሱ ወደ Park ይቀይረዋል ::
ሌላው ደግሞ ከ XLT ጀምሮ ያሉት ትሪም ሞዴሎች ላይ መሀል ላይ ሲሆን ማርሽ ያለው እሱ በመታጠፍ ወደውስጥ ይገባና ከጀርባ ያለው ይታጠፋል :: ይሄም ለመብላት ወይም PC አስቀምጣችሁ ለመስራት ቀላል ያደርገዋል ::
ቪድዮውን ስታዩት ይበልጥ ትረዱታላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMLHyJHos/

ልዩ ምሽት ተመኘን
#FordF150 #Trimlevels #AmazingFeatures
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Ford F-Series ከ1982 ጀምሮ በአሜሪካ ውስጥ ቁጥር አንድ የተሸጠ መኪና ነው አሁንም በብዛት አየተሸጠ ይገኛል።

በሰላም ዋሉ!
#CarFacts #PickupCars #Ford
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

ፒክአፕ መኪኖችን ለስራ የሚጠቀሙት 15% ባለቤቶች ናቸው :: የተቀሩት ለመዘነጫ ማለትም ልክ እንደ ሌሎች መኪኖች ነው የሚጠቀሙበት :: የእኛ ሀገር መረጃ ቢወሰድ ግን ከዚህ ይለያል :: አሁን አሁን ላይ እንጂ ድሮ ድሮ አብዛኛው ፒክአፕ ለስራ ብቻ ነበር የምንጠቀምበት :: አብዛኛዎቹ የፒክአፕ አምራቾች ዲዛይናቸው በማሻሻል ከስራ መኪናነት ውጪ በየቀኑ መጠቀም እንዲቻል አድርገው እየሰሩ ይገኛል :: ብዙ ቴክኖዎሎጂችን በመጨመር ::

ድንቅ ቀን ተመኘን
#Pickuptruck
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Toyota Tacoma Double Cab ላይ 3 ድብቅ ቦታዎች አሉ ::
ሁለቱ ከጀርባ ያለው ወንበር ላይ ሲሆኑ አንዱ ደግሞ እቃ መጫኛው ላይ ነው ::
የት የቱ ጋር እንደሆነ ቲክቶክ ላይ ቪድዮ ለቀናል ::
እንድትመለከቱ ጋበዝናችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZML9RR7mX/

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Toyotatacoma #Pickuptrucks
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

በ1896 ጎትሊብ ዳይምለር የመጀመርያውን pickup መኪና 4 የፈረስ ጉልበት፣ 2 ሲሊንደር ሞተር እና 1.1 ሊትር Dubbed የሰራውን ተሽከርካሪ ለገበያ አቀረበ ::

ያማረ ቀን ተመኘን!
#CarFacts #PickupCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
2023 Toyota GR Corolla

Toyota እስከዛሬ አይታችሁ ከምታውቁት ገራሚ እና የተሻለውን ኮሮላ ለእይታ አቅርበዋል ::
ይሄ በ Gazoo Racing የተሰራ ሲሆን በጣም ብዙ performance upgrade ተደርጎለታል :: የጎን ስፋቱንም በ 7 centimeter ጨምረውታል :: የራሱ ለየት ያለ ስፖይለር እንዲሁም ጣርያው ሙሉ በሙሉ ካርበን ፋይበር ነው :: ይሄ መኪና በ6 speed manual transmission እና በ AWD ብቻ ነው የሚገኘው :: ወደ ሞተሩ ስንመጣ ደግሞ 1.6 ሊትር 3 ሲሊንደር ያለው ሞተር ሲኖረው 300 hp ያመነጫል :: ዛሬ አርብ ማታ 12:30 ላይ ጥያቄ አዘጋጅተን መጀመሪያ ለመለሱ 2 ሰዎች የእሁዱን የመኪና ውድድር የመግቢያ ትኬት የምንሸልም ይሆናል ::
ሙሉውን ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZML9Qrqrn/

ድንቅ ቀን ተመኘንላችሁ 🙏
#GRCorolla #NewCar #Toyota
@OnlyAboutCarsEthiopia
600 ሺህ ብር የሚያወጣው ቮልስ

በዛሬው ቪድዮ እዚህ መኪና ላይ የወደድኳቸውን ነገሮች አዳዲስ መኪኖች ላይ የምታገኙትን ፊቸሮች እዚህ መኪና ላይ ያሉትን እና አንዳንድ ተጨማሪ ያስገረሙኝን ፊቸሮች አሳያችሗለሁ ::
ሙሉውን ቪድዮ YouTube ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/yYVCyjDXytU

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#CarOptions #YouTube
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም እንዴት ናችሁ?
ዛሬ ትንሽ ለየት ያለ ነገር ይዘን ብቅ ብለናል :: ከሞተር ስፖርት ጋር የተገናኘ ጥያቄ ነው ::

ጥያቄው

የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት በስንት አመተ ምህረት ነው የተጀመረው?

ይህንን መጀመርያ ለመለሱ 2 ሰዎች የምትመለከቱትን የእሁድ የመኪና ውድድር ትኬት ያገኛሉ ::
ህጉ አዲስ አበባ ውስጥ መሆን አለባችሁ እና ውድድሩን መሄድ አለባችሁ :: የማትሄዱ ከሆነ ለሚሄድ ሰው እድሉን ስጡ :: እሁድ እዛው እንገናኝ

ገራሚ ምሽት ተመኘን
#CarLogo #CarRace #Tickets
@OnlyAboutCarsEthiopia
የትላንትናውን ጥያቄ የመለሱት @Tedy1624 እና @E40140 ናቸው መልእክት ልኬላችሗለሁ :: ዛሬ ቦሌ ሚካኤል መጣችሁ መውሰድ አልያም ነገ የውድድሩ ቦታ መውሰድ ትችላላችሁ :: በየሳምንቱ እንደዚህ አይነት ውድድር ስለሚዘጋጅ መወዳደር ትችላላችሁ ::

መልካም ቀን ተመኘን
#Ticket #CarRace
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህንን ያውቃሉ?

Classic VW Beetle ላይ የፊት ቦታው እቃ ማስቀመጫ ሲሆን ከጀርባ ነው ሞተሩ ያለው :: ግን የሚገርመው የዝናብ መጥረጊያ ውሀ መርጫው በፓንፕ ሳይሆን የሚሰራው በስኮርት ጎማው አየር ነው :: ሀሳቡ በጣም ገራሚ ነበር :: ግን አሁን አይጠቀሙበትም :: ለምን?
አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZML9EUB85/

ያበደ ቅዳሜ ተመኘን 🙏
#ClassicCars #VWBeetle
@OnlyAboutCarsEthiopia
ማነው ለነገው የመኪና ውድድር የተዘጋጀው?

ቦታው - Kilinto Industrial Park ውስጥ ነው የሚሆነው :: ትኬት በር ላይ ይሸጣል ለሱ አታስቡ ብቻ ኑ 😁
ሊፍት መስጠት የምትችሉ ሰዎች ኮሜንት ላይ አውርታችሁ አንድ ላይ መምጣት ትችላላችሁ :: ለትውውቅም አሪፍ እድል ነው ::
የመኪናዎቹን ዝርዝር ከደቂቃዎች በሗላ የምንለቅ ይሆናል ::
የነገውን ውድድር አሸናፊ በትክክል ለገመተ የቁልፍ መያዣ የምንሸልም ይሆናል ::

እኛ ተዘጋጅተናል እናንተስ?

ግሩም ምሽት ተመኘን
#CarRace #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/25 18:12:09
Back to Top
HTML Embed Code: